ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ሰበር ዜና💪

ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር በላስታ ሰማይ ስር ከጠላት ኃይል ጋር ከባድ ትንቅንቅ በማድረግ አንድ ድሽቃ ሲማርክ ከ65 በላይ የጠላት ኃይልን ደመሰሰ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ፣ተፈራ ማሞ ክፍለጦር፣ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር እና ጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለጦር አንዳንድ ሻለቃዎች የተሳተፉበት 3ኛ ቀኑን የያዘው ከብልባላ ከተማ በባውሽ እስከ ሰኞ ገበያ ባለው ቀጠና ከጠላት ጋር እየተደረገ ባለው ትንቅንቅ ከፍተኛ ድል ተመዘገበ።

ነሐሴ 26/2017ዓ.ም ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ እና ተፈራ ማሞ ክፍለጦር ከገንጅ ዋርካ በጉርዱ በር እስከ መረዝ በር በመዘርጋት የገባውን የጠላት ኃይል ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር የደመሰሱት ሲሆን ማረጉ ተማረ ክፍለጦር ከአርጨቆ በጋሸና እስከ ደረቅማ ድረስ ያለውን ቦታ በመሸፈን በጠላት ላይ ከፍተኛ ተጋድሎ ፈፅመዋል። በተያያዘም ተወርዋሪው ጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለጦር በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በመግባት ጠላት መሽጎበት የነበረውን የወርቃምባና አሞራ ተራራ በሜካናይዝድ በተደገፈ አውደ ውጊያ ጠላት ከምሽጉ ሳይወጣ ለዱር አውሬ ቀለብ እንዲሆን አድርገውታል፤ እሸት ክፍለጦር አንዷ ሻለቃም ከላሊበላ የሚመጣውን ኃይል ሰኞገበያ ላይ በመዝጋት ወገን በጠላት ላይ የበላይነትን እንዲቀዳጅ ሰርግና ምላሽ አድርጋለታለች።

በዚህ አውደ ውጊያም በጠላት ኃይል ላይ የደረሰ ጉዳት ከ65 በላይ ሙት፣ 42 ቁስለኛና 5 ምርኮኛ ሲሆን እንዲሁም አንድ ዲሽቃ፣10 ጥቁር ክላሽ፣ 850 የክላሽ ተተኳሽ፣ 25 የደረት ትጥቅ፣ 16 የወገብ ትጥቅ፣42 የእጅ ቦምብ፣25 የክላሽ ካዝናና 20 የዝናብ ልብስ ሊማርክ ችሏል።

በመጨረሻም አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ስር የሚገኘው ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር በየትኛውም ሁኔታና በማንኛውም ጊዜ በጠላት ላይ የመደበኛና የሽምቅ ውጊያ በማድረግ በጠላት ሀይል ላይ የበላይነትን እንደሚቀዳጅና በሙሉ ዝግጁነትና ቁመና ላይ እንደሚገኝ የኮሩ ዋና አዛዥ አርበኛ 50አለቃ ኮማንዶ ወንድሙ ማሩ አሳስቧል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ነሐሴ 26/ 2017 ዓ.ም
KKidst Zewdu
👍2
Update

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ደጃዝማች ፬ኛ ኮር በቅርቡ ከጠላት ነፃ ባወጣው መተማ ወረዳ  የሽመለጋራ ቀበሌ ሰርገው በመግባት በአገዛዙ ስምሪት ሰጭነት አራት  ንፁሃንን ያገቱ ወንበዴዎች ኮሩ በሰራው ልዩ ኦፕሬሽን አስገድደው ካገቷቸው ንፁሃን የቅማንት ተወላጅ ታጋቾች ጋር እጅ ከፈንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በጥብቅ የመረጃ ክትትል በተሰራው በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን በእርሻ ስራ ልማት የተሰማሩ ንፁሃን የቅማንት ተወላጆችን
1ኛ) ብርሃን ነጋ ጭልጋ ወረዳ አዲዘመን ቀበሌ ነዋሪ፣
2ኛ) መንግስቴ አስማረ ጭልጋ ወረዳ አዲዘመን ቀበሌ ነዋሪ፣
3ኛ) አማረ ስመኘው ጭልጋ ወረዳ አዲዘመን ቀበሌ ነዋሪ እና
4ኛ) አደራጀው ሲሳይ ላይ አርማጭሆ ወረዳ ትክልዲንጋይ ቀበሌ ነዋሪ (350) ሽህ ብር የከፈለ) የተዘረዘሩ ንፁሃንን በቅርቡ ነፃ በወጣው መተማ ወረዳ ሽመለ ጋራ ቀበሌ አስገድደው በማገት ከእያንዳንዳቸው 800 ሽህ ብር የጠየቁ አጋች ወንበዴዎችን በቁጥጥር ስር ማድረግ ተችሏል።

የእገታ ወንጀል ፈፅመው  እጅ ከፈንጅ የተያዙት
1ኛ) ስማቸው ሞላ
2ኛ) ባሻ ገደቡ
3ኛ) ጋሻው ገብሬ የተባሉ ወንበዴዎች ሲሆኑ በቁጥጥር ስር ሲውሉ 150 ሽህ ብርና 3 የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ፣ 3 የወገብ ትጥቅ፣ የክላሽ ተተኳሾችና ቦምቦች ጋር በልዩ ኦፕሬሽን ክፍላችን በቁጥጥር ስር ገብተዋል።

ድርጊቱን ከሌሎች ግብራባሮቻቸው ጋር የፈፀሙት መሆኑን ያመኑት ዕኩይ ዓላማ ያነገቡ ወንበዴዎች በተደጋጋሚ በአማራና ቅማንት ህዝብ መካከል ግጭት ቀሽቃሽ ተግበባራትን እየፈፀሙ በሰላማዊ ወገኖቻችን መካከል በመግባት ያልተፈለገ ግጭት ለማስነሳት እንደሚታትሩ የተደረሰበት ሲሆን ከወር በፊት በመሰል ወንጀል የተጠረጠሩ 50 ወሮበሎች ላይ ደጃዝማች 4ኛ ኮር ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ ከ35 በላይ የቅማንት ተወላጆች ንብረት የሆኑ የቁም እንሰሳትን አስመልሷል።
አጥፊዎች ላይም የማያዳግም መራር ቅጣት ማሳረፉ እንዲሁም ንብረቶች ለባለቤቶች መመለሳቸው ይታወቃል።

ከየትኛውም አካባቢ እና ከየትኛውም ወገን የሚፈፀሙ መሰል ዕኩይ ተግበራትን የማይታገስ መሆኑን በመግለፅ የህዝባችን አብሮነትና መፃኢ ህልው ዕጣ ፈንታ ለማስከበር በጀግንነት መስዕዋትነት እየከፈለ የሚቀጥል መሆኑን ያረጋገጠው ደግሞ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ነው።

      ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

                 አፋብኃ /AFNF
                በላይ ዘለቀ ዕዝ
               ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም
                ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
3
የድል ዜና ‼️

የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር በስቦ መምታት ወታደራዊ ጥበብ በ102 ኛ ክፍለጦር ላይ የፈንጅ ጥቃት ፈፀመ !!

በተቆጣጠሩበት ቀጠና ጠላትን ረፍት  የነሱት የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር በትላንትናው ዕለት መኮይ ከተማ ቃኝዎች በማስገባት
በአገዛዙ ዘራፊ ቡድን ላይ ትንኮሳ በፈፀም ጠላትን ወደፈለጉት ወጥመድ እንዲገባ በማድረግ የስቦ መምታት ወታደራዊ ጥበባቸውን ተጠቅመው በብልፅግና ጦር ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰውበታል።

አገዛዙም ከተማ ላይ በተፈፀመበት ትንኮሳ  ክፍለጦሮን ለመክበብ በአምስት አቅጣጫ በአፍሶ፣ጓርጓዴ፣በባቡር መስመር በችግኝ ጣቢያ እንዲሁም በአጋምሳ አምባ በተባሉ ቦታዎች እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን የመጀመሪያውን ደፈጣ መጎራ ወንዝ የተባለ ቦታ ላይ የመጣውን ጠላት በደፈጣ ኦፕሬሽን ጀግኖቹ በአፈሙዛቸው አቀባበል አደረገውለታል።

በቀጣይም ጠላት ከዚህ ቀደም ችግኝ ጣቢያ መገንጠያ የተባለ ቦታ ለ ዙ 23 እና ለሞርተር ምሽግ ሲጠቀምበት የነበረ ቦታ ላይ የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር የፈንጅ መሀንዲሶች ተቀጣጣይ ፈንጅ አጠመዱ ጠላትም  ወደተዘጋጀለት ወጥመድ የወገንን ጦር ለማጥቃት በከባድ መሳሪያ ለመደብደብ ቦታውን በእግረኛ ጦር አስያዘው በመቀጠልም ጠበብቶቹ በመሬት የቀበሩት ፈንጅ የአገዛዙ ሰራዊት በታቀደለት ወጥመድ ውስጥ መግባቱን ሲያረጋግጡ የብልፅግናን ጦር ወደአመድነት ቀይረውታል ።

በዚህ የተበሳጨው የአብይ አራዊት ሰራዊት በከፍተኛ ፍርሃት እና በመደናገጥ በንፁሃን ቤቶች ላይ ኢላማ ያደረገ ከባድ መሳሪያ ሞርተር በመተኮስ  የሁለት ንፁሃን ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሶ ንፁሃኖቹም ወደከፍተኛ ህክምና ሪፈር የተባሉ ሲሆን በተጨማሪም አገዛዙ በንፁሃን መኖሪያ ቤቶች ላይ በወረወረው ከባድ መሳሪያ የቀንድ ከብቶች እና የጋማ ከብቶች ላይ ጉዳት አድርሷል ።

በመሀመድ ቢሆነኝ ኮር ስር ያሉ ክፍለጦሮች በሁሉም ሸዋ ግንባር ተጋድሎችን እያደረጉ የአገዛዙን ጦር ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ በመጣል የውጊያ የበላይነት እየወሰዱበት ይገኛል ።

ድል ለአማራ ፋኖ
ድል ለህዝባችን
@ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ !!
1🙏1
የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር በስቦ መምታት ወታደራዊ ጥበብ በ102 ኛ ክፍለጦር ላይ የፈንጅ ጥቃት ፈፀመ !!

በተቆጣጠሩበት ቀጠና ጠላትን ረፍት  የነሱት የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር በትላንትናው ዕለት መኮይ ከተማ ቃኝዎች በማስገባት
በአገዛዙ ዘራፊ ቡድን ላይ ትንኮሳ በፈፀም ጠላትን ወደፈለጉት ወጥመድ እንዲገባ በማድረግ የስቦ መምታት ወታደራዊ ጥበባቸውን ተጠቅመው በብልፅግና ጦር ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰውበታል።

አገዛዙም ከተማ ላይ በተፈፀመበት ትንኮሳ  ክፍለጦሮን ለመክበብ በአምስት አቅጣጫ በአፍሶ፣ጓርጓዴ፣በባቡር መስመር በችግኝ ጣቢያ እንዲሁም በአጋምሳ አምባ በተባሉ ቦታዎች እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን የመጀመሪያውን ደፈጣ መጎራ ወንዝ የተባለ ቦታ ላይ የመጣውን ጠላት በደፈጣ ኦፕሬሽን ጀግኖቹ በአፈሙዛቸው አቀባበል አደረገውለታል።

በቀጣይም ጠላት ከዚህ ቀደም ችግኝ ጣቢያ መገንጠያ የተባለ ቦታ ለ ዙ 23 እና ለሞርተር ምሽግ ሲጠቀምበት የነበረ ቦታ ላይ የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር የፈንጅ መሀንዲሶች ተቀጣጣይ ፈንጅ አጠመዱ ጠላትም  ወደተዘጋጀለት ወጥመድ የወገንን ጦር ለማጥቃት በከባድ መሳሪያ ለመደብደብ ቦታውን በእግረኛ ጦር አስያዘው በመቀጠልም ጠበብቶቹ በመሬት የቀበሩት ፈንጅ የአገዛዙ ሰራዊት በታቀደለት ወጥመድ ውስጥ መግባቱን ሲያረጋግጡ የብልፅግናን ጦር ወደአመድነት ቀይረውታል ።

በዚህ የተበሳጨው የአብይ አራዊት ሰራዊት በከፍተኛ ፍርሃት እና በመደናገጥ በንፁሃን ቤቶች ላይ ኢላማ ያደረገ ከባድ መሳሪያ ሞርተር በመተኮስ  የሁለት ንፁሃን ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሶ ንፁሃኖቹም ወደከፍተኛ ህክምና ሪፈር የተባሉ ሲሆን በተጨማሪም አገዛዙ በንፁሃን መኖሪያ ቤቶች ላይ በወረወረው ከባድ መሳሪያ የቀንድ ከብቶች እና የጋማ ከብቶች ላይ ጉዳት አድርሷል ።

በመሀመድ ቢሆነኝ ኮር ስር ያሉ ክፍለጦሮች በሁሉም ሸዋ ግንባር ተጋድሎችን እያደረጉ የአገዛዙን ጦር ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ በመጣል የውጊያ የበላይነት እየወሰዱበት ይገኛል።

ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሚዲያ ክፍል
🙏1
"ከወንዶች ጋር እኩል ነን ለማለት ወንዶች ከዋሉበት መዋል ያስፈልጋል" ሴት ኮማንዶ ተመራቂዎች!

አፋጎ 5ኛ ክ/ጦር የወምበርማ ብርጌድ ያስመረቃቸው ሴት ኮማንዶዎች "ከወንዶች ጋር እኩል ነን ለማለት ወንዶች ከዋሉበት መዋል ያስፈልጋል" ሲሉ ሴቶች ትግሉን እንዲቀላቀሉ አሳሰቡ።

ያነጋገርናቸው  መሠረታዊ ኮማንዶ ቤዛዊት አየነው እና መሠረታዊ ኮማንዶ ሔዋን መንግሥቱ እንደተናገሩት ሴትነታቸው ከወንዶች የተለየ ጫና ሳይፈጥርባቸው ሥልጠናውን በብቃት አጠናቅቀው ተመርቀዋል።

ሴት ተመራቂዎች አክለውም በሀገር እኩል ተጠቃሚነት ብቻ ሳይሆን እኩል መስዋዕትነት ያስፈልጋል" ብለዋል።

ስለዚህ በየቤታችሁ ያላችሁ ወጣት ሴቶች ሀገራችን ለሚያስፈልጋት ሁሉ ከወንዶች ጋር እንድትሰለፉ ሲሉ አሳስበዋል።

ከተመራቂዎች መካከል ያነጋገርናቸው ወንድ ተመራቂዎች መሠረታዊ ኮማንዶ ብርሃኑ ታመነ እና መሠረታዊ ኮማንዶ ታደለ ዓለሙ በበኩላቸው ጠቃሚ የአካል ብቃትና የሥነ-ምግባር ሥልጠና መውሰዳቸውን ገልጸው ለትግሉ ዝግጁ መኾናቸውን አሳውቀዋል።

የወምበርማ ሕዝብ በማያቋርጥ የሬሽን ድጋፉ አሠልጥኖ በምረቃችን ዕለት ደግሞ ትጥቁን ሸልሞ አስደንቆናል ያሉት ተመራቂዎቹ፤ እየመገበ እና ከጠላት እየጠበቀ ለፍፃሜ ያበቃቸውን ሕዝብና የፋኖ አመራር ከልብ አመስግነዋል።

ሥልጠናው አድካሚና ረዥም ጊዜ የወሰደ ቢኾንም በደጋፊዎቻችን ትጋትና በሠልጣኞች ብቃት ለዚህ በቅተናል ያሉት ደግሞ የወምበርማ ብርጌድ ሥልጠና መምሪያ ሓላፊ ም/፲ አለቃ ኮማንዶ ላይችሉህ አሸናፊ ናቸው።
ተመራቂዎቹ ብርጌዱ የሚያደርገውን ትግልም በእጅጉ እንደሚያቃልሉ ሓላፊው አስረድተዋል።

ሥልጠና መምሪያ ሓላፊው አክለውም በአንድነት ጠንክረን በመታገል ያጋጠመንን ፈተና አልፈን ለሁላችንም የምትበጅ አገር መፍጠር አለብን ብለዋል።

©በአፋጎ 5ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!
🙏2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የትግሉን አጠቃላይ ገጽታ የተመለከተ ሲምፖዚየም አዘጋጅቷል።

በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልወና አደጋ ለመመከት ላለፉት ሁለት ዓመታት ታላቅ ተጋድሎ እየተደረገ መሆኑ የሚታወቅ ነው። በተበታተነ ሁኔታ የሚደረገውን ተጋድሎ ወጥ በሆነ ድርጅታዊ መዋቅር ስር ለማድረግ በተጀመረው ጥረት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል የተወለደና ትግሉን በተሻለ ቁመና እየመራ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል። በጥቂት ታጋዮች ከኋላ ቀር መሳሪያ የተነሳው የአማራ ፋኖ ትግል በሁለት ዓመት ውስጥ ያስመዘገበው ድልና የገነባው ግዙፍ ወታደራዊ ሃይል የተጀመረውን የህልውና አደጋ ለመመከት በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲገኝ አድርጎታል። ምንም እንኳን ትግሉ ከሚፈልገው አቅምና ብቃት እንዲሁም የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ካለው መከራና ስቃይ አንጻር የምንገኝበት ምዕራፍ ገና ብዙ እንደሚቀረን የሚያሳይ ቢሆንም በቁርጥኝነትና በተባበረ ሃይል ከቀጠልን በቅርብ ጊዜ የአገዛዙን የጭቆና ቀንበር በጣጥሰን እንደምንጥል ጥርጣሬ የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም።

ለዚህም የተጀመረውን የአንድነት ጉዞ ማፋጠንና ወደኋላ የማንመለስበት የፋኖ ወጥ መዋቅር ለመገንባት ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረግን እንገኛለን። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ለዚህ የአንድነት ጉዞ የሚረዳና የተጋረጡብንን ችግሮች በውይይት ለመፍታት የሚያስችል ታላቅ ሲምፖዚየም ማዘጋጀቱን ሲገልጽ በደስታ ነው።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ) ከዚህ አቅሙ የበለጠ ጠንካራ እንዲሆንና የትግሉ ጊዜ ባጠረ መልኩ ለመቋጨት ያስችል ዘንድ እና ለአለማቀፉ ማህበረሰብ የትግሉን ሂደትና ዓላማ ግልፅ ለማድረግ፣ ለማስተዋወቅ እና በጎ ፈቃደኛ ደጋፊዎችን ለመጨመር ያለመውን ይህን ሲምፖዚየም ጷጉሜ 01 እና 02 ቀን 2017 ዓ.ም ወይም በፈረንጆቹ አቆጣጠር September 06,2025 Saturday Starting 12 Noon and September 07,2025 Sunday Starting 12 Noon በቀጥታ ስርጭት የሚያካሂድ መሆኑን ያስታውቃል።

በሲምፖዚየሙ ላይ የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አመራሮች በጋዜጠኞች ቃለመጠይቅ ይደረግላቸዋል፣ ዝግጅቱም በቴሌቪዥንና በዩቲዩብ፣ ቲክቶክ እና የX (Twitter ) ማህበራዊ ሚዲያዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።

በዚህ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ) ሲምፖዚየም ተሳታፊ በመሆን የአማራ ህዝብ የታወጀበትን እልቂት ለመመከት እየታገለ ያለውን የአማራ ፋኖ በመደገፍ፣ ከአማራም አልፎ በየተራ ሁሉንም ብሄሮች በማጥቃት የጭቆናና የባርነት ስርዓቱን ለማስቀጠል እየሰራ ያለውን "ብልፅግና" የተሰኘውን ጸረ ሕዝብ አገዛዝ እንድንታገልና ሀገርን ከመፍረስ እንድንታደግ ጥሪ እናቀርባለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል - አፋብኃ
🙏21

‎አስደንጋጭ ዜና
‎የብልጽግና የጥፋት ቡድን የአንድ ቀን አራስ ከአምቡላስ በማስወረድ አንቡላንሷንን አቃጠለ
‎=============
‎ወንበደው እና በአማራ ጥላቻ የታወረው የብልጽግና ስርዓት የአንድ ቀን ህጻን ይዛ ከወረኢሉ ተነስታ ወደ ግሸራቤ የምትጓዝ አምቡላስ አቃጥሏል ።

‎ንብረትነቷ የግሸራቤ ወረዳ የራቤል ጤና ጣቢያ የሆነች አምቡላስ ከወረኢሉ ተነስታ የአንድ ቀን ህጻን ይዛ ወደ ራቤል ከተማ እየተጓዘች እያለ ብልጽግና መልምሎ ባሰማራቸው የጥፋት ቡድን በወረኢሉና ግሸራቤ ወረዳ አዋሳኝ ቦታ ላይ ተቃጥላለች።

‎የአምቡላንስ ቃጠሎው የተፈጸመው የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን ፋኖን ከአማራ ህዝብ ለመነጠል በፋኖ ስም አደራጅቶ ባሰማራቸው የሚኒሻ አባላት ነው።

‎የስርዓቱ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት በግሸ ራቤ እና ወረኢሉ አካባቢ ያለውን ጠንካራ የፋኖ ይዞታ በሀይል ለማስለቀቅ አቅም ሲያጥረው የአንድ ቀን ህጻን ከአምቡላስ አውርዶ አምቡላንስ በማቃጠል ፋኖን ከህዝብ ለመለየት የሄደበት ሴራ የራሱን የመንግስት እኩይ ተግባር በአደባባይ አስጥቶለታል።

‎ይሕንን እኩይ ሴራ ለመፈጸም የተገደደው የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን ፋኖ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለው ተቀባይነት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ከርችሞት ሲሆን ስርዓቱ ከገባበት የፍረሃት አሮንቃ ውስጥ ለመውጣት ሲል ለወራት በጀት በጂቶ ስልጠና ሰጥቶ በፋኖ ስም ባሰማራቸው የሚኒሻ አባላት ይህን በአለም አቀፍ ህግ የተከለከለ ፅዩፍ ድርጊት ፈጽሞታል።

‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አጼ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር የብሩኬ ደምሴ ብርጌድ ቃጠሎው በተፈጸመበት ቦታ በመንቀሳቀስ ባደረጉት ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ካዋሏቸው ተላላኪ የብልጽግና የጥፋት ቡድን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አገዛዙ በጀት መድቦ ስልጠና ሰጥቶ ያደራጃቸው መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

‎ይህንን እኩይ ተግባር የአፋብኅ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ አጼ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር የብሩኬ ደምሴ ብርጌድ ቃጠሎውን የፈጸሙትን አካላት ይዞ እያካሄደ ያለውን ዝርዝር ምርመራ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ መሆኑን ከወድሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም
3👍1
ሰበር ዜና !!!
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

“..... አንድ ሁኑ!" ብ/ጀኔራል አሳምነው ፅጌ

ትግላችንን አንድ ቅርጽ' አንድ መዋቅር፤ አንድ ደርጅት፤ አንድ መርኅና የአሠራር መልክ ማስያዝ የኅልውና ትግላችን የማሸነፊያ ቁልፍን እንደመጨበጥ መሆኑን ሕዝባችን፤ ስራዊታችን እንዲሁም ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በጽኑ የሚያምንበት ጉዳይ ነው፡፡

አማራነትን የሚጸየፍ ኢትዮጵያዊነትንና አማራነት የጎደለውን አውራጃዊነትን እንደምንጸየፈው ሁሉ ልዩነትን የማይታገስ አንድነትን እንዲሁም አንድነትን የማይቀበል ልዩነትንም እናወግዛለን: የአማራን ሕዝብ ትግል በአንድ ድርጅት ጥላ ሥርየማንበር፤ በእንድ መዋቅር የመሰብሰብ እንዲሁም በተመሳሳይ መርሀና አስራር እንዲመራ ማድረግ በብዝኃ ሀሳብ የሚሰራውን ያክል በብዝኃ ሀሳቦች መካከልም ልዩነት እና ልዩነትን መቻቻል የሚጠበቁ ጉዳዮች ናቸው:: ልዩነት ተፈጥሯዊ ነው፡ ልዩነትን መግራት ደግሞ ብስለት ነው፡፡

በመሆኑም በቋራ ቃል ኪዳን ድርጅታችንን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልን ከመሰረትን በኋላ በአማራ ፋኖ በጎጃም በኩል የተነሱ የልዩነት ሀሳቦች ነበሩ፣ እነዚህ የልዩነት ሀሳቦች በውስጥና በውጭ ገፊ ምክንያቶች መልካቸውንና ዓይነታቸውን እየቀያየሩ ቢቆይም በተደረጉ ተደጋጋሚ ውይይቶች በዛሬው ዕለት ማለትም ነሃሴ 27/2017 ዓ.ም መቋጫ አግኝቷል፤ በመካከላችን የተፈጠሩ ልዩነቶችን ፈትተን አንድ ሆነናል፣ በውይይታችንም የቋራ ቃል ኪዳንን አድሰናል፡፡ በዛሬው ዕለትም ሙሉ የአፋብኃ የኮማንድ አባላት በተገኘንበት የድርጅታችንን ጉዞ ገምግመን ቀጣይ አቅጣጫዎችንም አስቀምጠናል፡፡ ስለሆነም የአማራ ፋኖ በጎጃምም እንደሌሎቹ ቀጠናዎች ሁሉ ከዚህ ቀደም በቀን 18/10/2017 ዓ.ም በድርጅታችን በተገለጸው መግለጫ መሰረት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና - ቴዎድሮስ ዕዝ ተበሎ የሚጠራ ይሆናል፡፡

በመጨረሻም መላው የአማራ ሕዝብ፣ ደጋፊዎቻችን፤ የሚዲያ አካላት እንዲሁም ሰራዊታችን በስትራቴጅ፣ በእውቀት፣ በእውነት፣ በወንድማዊና ጓዳዊ መስተጋብር የድርጅታችንን አንድነት ጠብቀን እንድንጓዝ እያሳሰብን በመካከላችን በነበሩ ልዩነቶች ምክንያት ለተፈጠሩ ችግሮች በሙሉ የድርጅታችን ማዕከላዊ ኮማንድ ሕዝባችንንና ስራዊታችንን ከልባችን ይቅርታ እንጠይቃለን!! ትግላችንን በውስጣዊ ዴሞክራሲ፤ በመርህና በድርጅታዊ አሰራሮች ለመምራት እና የውስጥ ጉዳዮቻችንን በውስጥ ለመፍታትም ቃል እንገባለን!!!

ጎልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል
7🙏2