ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል 4ኛ ደጃዝማች ኮር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ከፍተኛ ዝርፊያ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሌቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

አማራና ቅማንት በሚል ግጭት ለመቀስቀስ የሚሰሩና ማህበረሰቡን በመዝረፍ እረፍት ሲነሱ የነበሩና ድርጊቱንም ፋኖ የፈፀመው በማስመሰል ስም ሲያጠፉ የነበሩ ናቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት። ከዚህ ቀደምም በርካቶችን በቁጥጥር ስር በማዋልና እርምጃ በመውሰድ ማህበረሰቡ ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ ተችሏል።

አሁንም ቢሆን በዚህ የጥፋት መንገድ ላይ ያሉ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

በሌላ መረጃ ኮሩ በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ዕዙ ያወረደውን መመሪያ ከመተግበር አኳያ የ2018 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ እንዲሆን እየሰሩ መሆኑንም ገልጿል።

በቀጠናው ያለውን ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል 4ኛ ደጃዝማች ኮር የህዝብግንኙነት መመሪያ ሃላፊ አርበኛ ባንድራው ግርማይ አድርሶናል። በምሽት የዜና እወጃችን በመረጃ ቴሌቪዥን ይዘን እንቀርባለን።
🙏3
ዓለማቀፍ የአምሓራ ግብረኃይል ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች ጋር በተያያዘ ያወጣው ወቅታዊ የአቋም መግለጫ

የአማራ ህዝብ በአሁኑ ሰዓት መሪ የለውም መሪው እኛ ነን ባዮች የቀድሞ የብአዴን፣ የአሁኑ የአማራ ብልፅግና አመራሮች ህዝባችንን በግፍ በመግዛት ላለፉት 37 ዓመታት እጅና እግሩን አስረው ጨፍጭፈውታል። በክልሉ ወስጥ ብቻ ሳይሆን ከክልሉ ውጪ ያለውን የአማራ ማኅበረሰብ ለዘር ማጥፋትና ለባርነት እንዲዳረግ አድርገውታል።   

የአማራ ህዝብ የራሱ በተባለለት ክልል ውስጥ እንኳን ተሳዳጅ ሆኗል። በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች ቤቱ ፈርሶ፣ ሀብቱ ተነጥቆ፣ በየመጠለያ ካምፑ ተሰግስጓል፣ መቋቋም አቅቶት በየመንገዱ ወድቋል። የእለት ጉርስ በማጣት በችጋር ተገርፏል። የክልሉ መሪዎች አማራን ለዚሁ ሁሉ ቀውስ መዳረጋቸው አልበቃ ብሎ፣ ለኦሆዴድ ብልፅግናና ለኦነግ ጣምራ ወራሪዎች አሳልፈው ሰጡት።  

የዐማራ ህዝብ የአርበኝነት ትግል ከጫፍ አስከጫፍ ተቀጣጥሏል። እነዚህን አምባገነን የክልል ገዢዎች አስወግዶ ህልውናውን በማስከበር፣ በነፃነት ለመኖርና ከጭቆና የጸዳ አዲስ ሕዝባዊ አስተዳደር ለመፍጠር፣ የአማራ ፋኖ ዱር ቤቴ ብሎ የትጥቅ ትግል ከጀመረ ጥቂት አመታትን አስቆጥሯል። በጨፍጫፊው የኦሮሙማው ብልፅግና የተከፈተበትን ጦርነት ለመመከት በዚህ ሰአት የሞት ሽረት ትግሉን በቆራጥ ልጆቹ እያሳለጠው ይገኛል።

ይህ ጦርነት በአንድ በኩል የዐማራ ሕዝብ በዐማራነቱ ሳይሸማቀቅ በመላው አገሪቱ እንደሰው ተከብሮ እንዲኖር፣ በሌላ በኩል ከሌሎች ብሔሮች ጋር በእኩልነት የአገር ባለቤት እንዲሆን ለማስቻል፣ በአማራ ሕዝብና በአገር ወዳድ የቁርጥ ቀን ልጆች በሚከፈል መስዋዕትነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እስካሁኑ ሰዓት ድረስ በሺህዎች የሚቆጠሩ የዐማራ ፋኖ አርበኞች በጦርነቱ የተሰው ሲሆን ቀሪ ጓዶችም የተሰው ወንድምና እህቶቻቸውን የደም ዋጋ ላለማርከስና የህልውና ትግሉን ከዳር ለማድረስ አደራ እየተቀበሉና እየሰጡ በየቀኑ ለመሰዋትነትና ጠላትን ድል ለማድረግ ይተጋሉ። እስከ አፍንጫው ከታጠቀ ጨፍጫፊ የኦሮሙማው መንግስትና፥ የኦነግ መንጋ ጋር በዱር በገደሉ ጠላትን እየጣሉና እየወደቁ ይገኛሉ፡፡    

የዐማራ ህዝብ ለዚህ ዓላማ በዚህ ደረጃ በዐማራነቱ ሲደራጅ ተገድዶ የገባበትና ብዙም የብሄረተኝነት ፍላጎትና ልምዱ ያልነበረው በመሆኑ ብዙ ተግዳሮቶችን አሳልፏል። በአሁኑ ወቅት የዐማራን ህዝብ ትግል በዋናነት እየተመራ ያለው መሬት ላይ ባለው የትጥቅ ትግል መሆኑ የታወቀ ነው። በተፈጥሮ በቡድን የተሰባሰበው የፋኖ አደረጃጀት የተሳካ እንደነበር ቢታወቅም፣ ቡድኖቹ በሂደት ተስማምተው አንድ ሆነው ባለመስራታቸው፣ ደግሞም ይደጋገፋሉ፣ ቢቻልም ታጋዩን ያስተባብራሉ ተብለው የተቋቋሙ አደረጃጀቶች በታጋዮች አለመግባባትና መሰል ምክንያቶች
በሚጠበቀው ደረጃ ግዴታቸውን አለመወጣታቸው፣ የአንድንት ጉዞውን ሲያንቀረፍፈው ታይቷል፣ የድሉን ጊዜም አርቆታል። በሌላ በኩል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ክፍለ ዓለማት፣ አገራትና ከተሞች የተደራጁ የዐማራ ማህበራትና ድርጅቶች ከመነሻው የሀሳብ፣ የሰብአዊ ድጋፍና የዲፕሎማሲ ጥረቶች አንጻር የማይናቅ አስተዋጽኦ ቢያደርጉም፣ ብዙም ጊዜ ሳይቆይ ግን በመሪዎችና በድርጅቶች የጎንዮሽ
መገፋፋት ምክንያት፣ በመለያየት መሬት ላይ ያለውን እውነታ የዋጀ የትግል ስትራቴጂና እንቅስቃሴ ለማድረግ በመቸገራቸው፣ በተለይም ለሌላ ጊዜ ሊተላለፉ በሚችሉ ጥቃቅን ጉዳዮች የተንዛዙ ንትርኮች በመፍጠራቸው፣ አያሌ የአማራ ልጆችንና የደጋፊዎችን አቅም አዳክሟል። በሚታይ መልኩ የደጋፊውን ቁጥርን ቁልቁል እንዲወርድ አድርጓል።

በዲያስፖራ የተፈጥረው አለመግባባት መሬት ላይ ያለውን እልህ አስጨራሽ ትግል ከመጉዳቱም በላይ ለጠላት በር በመክፈት በታጋዮቻችን ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮአል፡፡ በዚህም ምክንያት በውጭ ያሉ አያሌ የፋኖ ወገኖች፣ ትግሉን ከመደገፍ አብዝተው ርቀዋል፡፡ ይህም ችግር ያልታጠቀውን ህዝባችንን ለተጨማሪ ሞት፣ እንግልት፣ መደፈርና ስደት አጋልጧል። አቅም ያለው፣ በጀግንነቱ የተመሰከረለትንና በተግባር እያሳየ ያለውን ፋኖ ወገናችን፣ ድል ተቀዳጅቶ የማህበረሰባችንን መሠረታዊ ጥያቄ በፍጥነት እልባት ሰጥቶ
እፎይ እንዳይል ከማድረጉም በላይ፣ ጠላት ጊዜ አግኝቶ ከተበተነበት እየተሰባሰበ በመመላለስ ጥቃት እንዲፈጽም ረድቶታል።   
 
ስለዚህ፣ ቀጣይ የእማራ የዘር ማጥፋትን ለማስቆምና የባርነት ቀንበርን ከጫንቃው ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል፣ በተቀናጀና ስርአት በተላበሰ ሕብረት ተደራጅቶ፣ ከፍ ሲልም በወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስ በመተሳሰብ፣ ወደ አንድ እዝ በመጠቃለል ጠላትን ማጥቃት ጊዜ የማይሰጠው ተግባር መሆን ይኖርበታል። ይህንንም በወጉ የተረዳና የተቀናጀ አመራር መኖር አለበት። እስካሁን በአንድ ሆኖ አለመታገሉ በተለይ የዐማራ ህዝብን የህልውና ትግል ውጤት አዘግይቶታል፤ የሚከፈለውንም መስዋእትነት ከመጠን በላይ እንዲጨምር አድርጎብናል። የተቀናጀና የተማከለ አመራር ለመስጠት ይቻል ዘንድ ፣ እና የማህበረሰባችንን የህልውና ማስከበር ትግል በፍጥነት ለመፈጸም፣ ብሎም፣ እንደ ዜጋ በእኩልነት፣ በመተባበርና በመከባበር ከትውልድ ወደ ትውልድ ተሻጋሪ ልእልናውን ለማስጠበቅ ይረዳው ዘንድ፣ የአማራ ፋኖ አንድ መሆን ገንቢና ወቅታዊ ነው ብለን እናምናለን።     

ግቡ ማሸነፍ ብቻ የሆነው የዐማራ ህዝብ የህልውና ትግል ከፍተኛ መስዋዕትነትን እየጠየቀ ያለና ወደፊትም የሚጠይቅ፣ ውስብስብና ረጅም ነው፡፡ አያሌዎች እንደሚያስቡት አሁን ባለንበት የትግል ሁኔታ በፍጥነት አልቆ ሁሉም ያለመውንና ያቀደውን በቀላሉ የሚያገኝበት አይደለም፡፡ ለዚህ ነው የአንድነት ጉዞው ፈታኝ የሆነው። ከዚህ ቀደም በእውቀትም ይሁን ባለማወቅ በአሠራር ጉድለት የተከሰቱ አለመግባባቶችን ወደጎን በመተው፣ ለአንድነት በሙሉ ልብና መንፈስ መንቀሳቀስ መጀመሩ፣ በትግሉ ሂደት ተስፋ ለቆረጠው ወገናችን ትልቅ ተስፋ ሰጥቶታል። በአንድነት በጋራ መታገል አማራጭ የሌለውና ጊዜ
የማይሰጠው ግንባር ቀደም ጉዳይ ነው። ዓላማው የተቀደሰና፣ ግብረ ኃይላችንም ለድጋፍ የሚያበረታታ ሆኖ አግኝቶታል። ለስኬቱ
የሚጠበቅብንንና የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን አስረግጠን ማስገንዘብ እንወዳለን።

በፈቃደኝነትና በቁርጠኝነት እንዲሁም
በጽናት አስተዋጾ ለማበርከት በቁርጠኝነት ተሰባስበናል። የአንድነት ጉዞው እንዲጠናከር የድርሻችንን ኃላፊነት መወጣት አለብን ብሎ
ግብረኃይላችን በፅኑ ያምናል። 
 
ትግሉ መብሰልና አሁን ካለበት በበለጠ ጠንካራ ሆኖ በፈጣን ወደ ድል መድረስ አላማ ተደራጅቶ መታገል ያስፈልገዋል፤ በውጭ ሀገራት ሆኖ ለመደገፍና ለማስተባበር የተደራጁት ማህበራት የትግሉን ውስብስብነት በአግባቡ ያለመረዳት ችግር ስለሚታይ፣ ይህ የአንድነት ጥሪ ከጥሪ አልፎ በተግባር መዋል ሲጀምር እስካሁን ከተፈጠሩት ዕውነታዎች በመማር በትብብር ጠንካራ የዐማራ አመራር በውጭ ሀገራት በመፍጠር ትግሉን ከማደናቀፍ ይልቅ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርስ የማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነት ይኖራቸዋል ብሎ ግብረ ኃይላችን ያምናል። 
 
ህልውናችን በክንዳችን!
ድል ለተገፋው የአማራ ሕዝብ! 
ዓለማቀፍ የአምሐራ ግብረኃይል (ዓ/አ/አ/ግ/ኃ)
2🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ሰበር ዜና💪

ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር በላስታ ሰማይ ስር ከጠላት ኃይል ጋር ከባድ ትንቅንቅ በማድረግ አንድ ድሽቃ ሲማርክ ከ65 በላይ የጠላት ኃይልን ደመሰሰ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ፣ተፈራ ማሞ ክፍለጦር፣ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር እና ጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለጦር አንዳንድ ሻለቃዎች የተሳተፉበት 3ኛ ቀኑን የያዘው ከብልባላ ከተማ በባውሽ እስከ ሰኞ ገበያ ባለው ቀጠና ከጠላት ጋር እየተደረገ ባለው ትንቅንቅ ከፍተኛ ድል ተመዘገበ።

ነሐሴ 26/2017ዓ.ም ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ እና ተፈራ ማሞ ክፍለጦር ከገንጅ ዋርካ በጉርዱ በር እስከ መረዝ በር በመዘርጋት የገባውን የጠላት ኃይል ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር የደመሰሱት ሲሆን ማረጉ ተማረ ክፍለጦር ከአርጨቆ በጋሸና እስከ ደረቅማ ድረስ ያለውን ቦታ በመሸፈን በጠላት ላይ ከፍተኛ ተጋድሎ ፈፅመዋል። በተያያዘም ተወርዋሪው ጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለጦር በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በመግባት ጠላት መሽጎበት የነበረውን የወርቃምባና አሞራ ተራራ በሜካናይዝድ በተደገፈ አውደ ውጊያ ጠላት ከምሽጉ ሳይወጣ ለዱር አውሬ ቀለብ እንዲሆን አድርገውታል፤ እሸት ክፍለጦር አንዷ ሻለቃም ከላሊበላ የሚመጣውን ኃይል ሰኞገበያ ላይ በመዝጋት ወገን በጠላት ላይ የበላይነትን እንዲቀዳጅ ሰርግና ምላሽ አድርጋለታለች።

በዚህ አውደ ውጊያም በጠላት ኃይል ላይ የደረሰ ጉዳት ከ65 በላይ ሙት፣ 42 ቁስለኛና 5 ምርኮኛ ሲሆን እንዲሁም አንድ ዲሽቃ፣10 ጥቁር ክላሽ፣ 850 የክላሽ ተተኳሽ፣ 25 የደረት ትጥቅ፣ 16 የወገብ ትጥቅ፣42 የእጅ ቦምብ፣25 የክላሽ ካዝናና 20 የዝናብ ልብስ ሊማርክ ችሏል።

በመጨረሻም አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ስር የሚገኘው ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር በየትኛውም ሁኔታና በማንኛውም ጊዜ በጠላት ላይ የመደበኛና የሽምቅ ውጊያ በማድረግ በጠላት ሀይል ላይ የበላይነትን እንደሚቀዳጅና በሙሉ ዝግጁነትና ቁመና ላይ እንደሚገኝ የኮሩ ዋና አዛዥ አርበኛ 50አለቃ ኮማንዶ ወንድሙ ማሩ አሳስቧል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ነሐሴ 26/ 2017 ዓ.ም
KKidst Zewdu
👍2
Update

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ደጃዝማች ፬ኛ ኮር በቅርቡ ከጠላት ነፃ ባወጣው መተማ ወረዳ  የሽመለጋራ ቀበሌ ሰርገው በመግባት በአገዛዙ ስምሪት ሰጭነት አራት  ንፁሃንን ያገቱ ወንበዴዎች ኮሩ በሰራው ልዩ ኦፕሬሽን አስገድደው ካገቷቸው ንፁሃን የቅማንት ተወላጅ ታጋቾች ጋር እጅ ከፈንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በጥብቅ የመረጃ ክትትል በተሰራው በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን በእርሻ ስራ ልማት የተሰማሩ ንፁሃን የቅማንት ተወላጆችን
1ኛ) ብርሃን ነጋ ጭልጋ ወረዳ አዲዘመን ቀበሌ ነዋሪ፣
2ኛ) መንግስቴ አስማረ ጭልጋ ወረዳ አዲዘመን ቀበሌ ነዋሪ፣
3ኛ) አማረ ስመኘው ጭልጋ ወረዳ አዲዘመን ቀበሌ ነዋሪ እና
4ኛ) አደራጀው ሲሳይ ላይ አርማጭሆ ወረዳ ትክልዲንጋይ ቀበሌ ነዋሪ (350) ሽህ ብር የከፈለ) የተዘረዘሩ ንፁሃንን በቅርቡ ነፃ በወጣው መተማ ወረዳ ሽመለ ጋራ ቀበሌ አስገድደው በማገት ከእያንዳንዳቸው 800 ሽህ ብር የጠየቁ አጋች ወንበዴዎችን በቁጥጥር ስር ማድረግ ተችሏል።

የእገታ ወንጀል ፈፅመው  እጅ ከፈንጅ የተያዙት
1ኛ) ስማቸው ሞላ
2ኛ) ባሻ ገደቡ
3ኛ) ጋሻው ገብሬ የተባሉ ወንበዴዎች ሲሆኑ በቁጥጥር ስር ሲውሉ 150 ሽህ ብርና 3 የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ፣ 3 የወገብ ትጥቅ፣ የክላሽ ተተኳሾችና ቦምቦች ጋር በልዩ ኦፕሬሽን ክፍላችን በቁጥጥር ስር ገብተዋል።

ድርጊቱን ከሌሎች ግብራባሮቻቸው ጋር የፈፀሙት መሆኑን ያመኑት ዕኩይ ዓላማ ያነገቡ ወንበዴዎች በተደጋጋሚ በአማራና ቅማንት ህዝብ መካከል ግጭት ቀሽቃሽ ተግበባራትን እየፈፀሙ በሰላማዊ ወገኖቻችን መካከል በመግባት ያልተፈለገ ግጭት ለማስነሳት እንደሚታትሩ የተደረሰበት ሲሆን ከወር በፊት በመሰል ወንጀል የተጠረጠሩ 50 ወሮበሎች ላይ ደጃዝማች 4ኛ ኮር ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ ከ35 በላይ የቅማንት ተወላጆች ንብረት የሆኑ የቁም እንሰሳትን አስመልሷል።
አጥፊዎች ላይም የማያዳግም መራር ቅጣት ማሳረፉ እንዲሁም ንብረቶች ለባለቤቶች መመለሳቸው ይታወቃል።

ከየትኛውም አካባቢ እና ከየትኛውም ወገን የሚፈፀሙ መሰል ዕኩይ ተግበራትን የማይታገስ መሆኑን በመግለፅ የህዝባችን አብሮነትና መፃኢ ህልው ዕጣ ፈንታ ለማስከበር በጀግንነት መስዕዋትነት እየከፈለ የሚቀጥል መሆኑን ያረጋገጠው ደግሞ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ነው።

      ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

                 አፋብኃ /AFNF
                በላይ ዘለቀ ዕዝ
               ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም
                ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
3
የድል ዜና ‼️

የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር በስቦ መምታት ወታደራዊ ጥበብ በ102 ኛ ክፍለጦር ላይ የፈንጅ ጥቃት ፈፀመ !!

በተቆጣጠሩበት ቀጠና ጠላትን ረፍት  የነሱት የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር በትላንትናው ዕለት መኮይ ከተማ ቃኝዎች በማስገባት
በአገዛዙ ዘራፊ ቡድን ላይ ትንኮሳ በፈፀም ጠላትን ወደፈለጉት ወጥመድ እንዲገባ በማድረግ የስቦ መምታት ወታደራዊ ጥበባቸውን ተጠቅመው በብልፅግና ጦር ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰውበታል።

አገዛዙም ከተማ ላይ በተፈፀመበት ትንኮሳ  ክፍለጦሮን ለመክበብ በአምስት አቅጣጫ በአፍሶ፣ጓርጓዴ፣በባቡር መስመር በችግኝ ጣቢያ እንዲሁም በአጋምሳ አምባ በተባሉ ቦታዎች እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን የመጀመሪያውን ደፈጣ መጎራ ወንዝ የተባለ ቦታ ላይ የመጣውን ጠላት በደፈጣ ኦፕሬሽን ጀግኖቹ በአፈሙዛቸው አቀባበል አደረገውለታል።

በቀጣይም ጠላት ከዚህ ቀደም ችግኝ ጣቢያ መገንጠያ የተባለ ቦታ ለ ዙ 23 እና ለሞርተር ምሽግ ሲጠቀምበት የነበረ ቦታ ላይ የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር የፈንጅ መሀንዲሶች ተቀጣጣይ ፈንጅ አጠመዱ ጠላትም  ወደተዘጋጀለት ወጥመድ የወገንን ጦር ለማጥቃት በከባድ መሳሪያ ለመደብደብ ቦታውን በእግረኛ ጦር አስያዘው በመቀጠልም ጠበብቶቹ በመሬት የቀበሩት ፈንጅ የአገዛዙ ሰራዊት በታቀደለት ወጥመድ ውስጥ መግባቱን ሲያረጋግጡ የብልፅግናን ጦር ወደአመድነት ቀይረውታል ።

በዚህ የተበሳጨው የአብይ አራዊት ሰራዊት በከፍተኛ ፍርሃት እና በመደናገጥ በንፁሃን ቤቶች ላይ ኢላማ ያደረገ ከባድ መሳሪያ ሞርተር በመተኮስ  የሁለት ንፁሃን ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሶ ንፁሃኖቹም ወደከፍተኛ ህክምና ሪፈር የተባሉ ሲሆን በተጨማሪም አገዛዙ በንፁሃን መኖሪያ ቤቶች ላይ በወረወረው ከባድ መሳሪያ የቀንድ ከብቶች እና የጋማ ከብቶች ላይ ጉዳት አድርሷል ።

በመሀመድ ቢሆነኝ ኮር ስር ያሉ ክፍለጦሮች በሁሉም ሸዋ ግንባር ተጋድሎችን እያደረጉ የአገዛዙን ጦር ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ በመጣል የውጊያ የበላይነት እየወሰዱበት ይገኛል ።

ድል ለአማራ ፋኖ
ድል ለህዝባችን
@ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ !!
1🙏1
የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር በስቦ መምታት ወታደራዊ ጥበብ በ102 ኛ ክፍለጦር ላይ የፈንጅ ጥቃት ፈፀመ !!

በተቆጣጠሩበት ቀጠና ጠላትን ረፍት  የነሱት የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር በትላንትናው ዕለት መኮይ ከተማ ቃኝዎች በማስገባት
በአገዛዙ ዘራፊ ቡድን ላይ ትንኮሳ በፈፀም ጠላትን ወደፈለጉት ወጥመድ እንዲገባ በማድረግ የስቦ መምታት ወታደራዊ ጥበባቸውን ተጠቅመው በብልፅግና ጦር ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰውበታል።

አገዛዙም ከተማ ላይ በተፈፀመበት ትንኮሳ  ክፍለጦሮን ለመክበብ በአምስት አቅጣጫ በአፍሶ፣ጓርጓዴ፣በባቡር መስመር በችግኝ ጣቢያ እንዲሁም በአጋምሳ አምባ በተባሉ ቦታዎች እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን የመጀመሪያውን ደፈጣ መጎራ ወንዝ የተባለ ቦታ ላይ የመጣውን ጠላት በደፈጣ ኦፕሬሽን ጀግኖቹ በአፈሙዛቸው አቀባበል አደረገውለታል።

በቀጣይም ጠላት ከዚህ ቀደም ችግኝ ጣቢያ መገንጠያ የተባለ ቦታ ለ ዙ 23 እና ለሞርተር ምሽግ ሲጠቀምበት የነበረ ቦታ ላይ የአስቴጉማ ተራራ ክፍለጦር የፈንጅ መሀንዲሶች ተቀጣጣይ ፈንጅ አጠመዱ ጠላትም  ወደተዘጋጀለት ወጥመድ የወገንን ጦር ለማጥቃት በከባድ መሳሪያ ለመደብደብ ቦታውን በእግረኛ ጦር አስያዘው በመቀጠልም ጠበብቶቹ በመሬት የቀበሩት ፈንጅ የአገዛዙ ሰራዊት በታቀደለት ወጥመድ ውስጥ መግባቱን ሲያረጋግጡ የብልፅግናን ጦር ወደአመድነት ቀይረውታል ።

በዚህ የተበሳጨው የአብይ አራዊት ሰራዊት በከፍተኛ ፍርሃት እና በመደናገጥ በንፁሃን ቤቶች ላይ ኢላማ ያደረገ ከባድ መሳሪያ ሞርተር በመተኮስ  የሁለት ንፁሃን ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሶ ንፁሃኖቹም ወደከፍተኛ ህክምና ሪፈር የተባሉ ሲሆን በተጨማሪም አገዛዙ በንፁሃን መኖሪያ ቤቶች ላይ በወረወረው ከባድ መሳሪያ የቀንድ ከብቶች እና የጋማ ከብቶች ላይ ጉዳት አድርሷል ።

በመሀመድ ቢሆነኝ ኮር ስር ያሉ ክፍለጦሮች በሁሉም ሸዋ ግንባር ተጋድሎችን እያደረጉ የአገዛዙን ጦር ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ በመጣል የውጊያ የበላይነት እየወሰዱበት ይገኛል።

ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሚዲያ ክፍል
🙏1
"ከወንዶች ጋር እኩል ነን ለማለት ወንዶች ከዋሉበት መዋል ያስፈልጋል" ሴት ኮማንዶ ተመራቂዎች!

አፋጎ 5ኛ ክ/ጦር የወምበርማ ብርጌድ ያስመረቃቸው ሴት ኮማንዶዎች "ከወንዶች ጋር እኩል ነን ለማለት ወንዶች ከዋሉበት መዋል ያስፈልጋል" ሲሉ ሴቶች ትግሉን እንዲቀላቀሉ አሳሰቡ።

ያነጋገርናቸው  መሠረታዊ ኮማንዶ ቤዛዊት አየነው እና መሠረታዊ ኮማንዶ ሔዋን መንግሥቱ እንደተናገሩት ሴትነታቸው ከወንዶች የተለየ ጫና ሳይፈጥርባቸው ሥልጠናውን በብቃት አጠናቅቀው ተመርቀዋል።

ሴት ተመራቂዎች አክለውም በሀገር እኩል ተጠቃሚነት ብቻ ሳይሆን እኩል መስዋዕትነት ያስፈልጋል" ብለዋል።

ስለዚህ በየቤታችሁ ያላችሁ ወጣት ሴቶች ሀገራችን ለሚያስፈልጋት ሁሉ ከወንዶች ጋር እንድትሰለፉ ሲሉ አሳስበዋል።

ከተመራቂዎች መካከል ያነጋገርናቸው ወንድ ተመራቂዎች መሠረታዊ ኮማንዶ ብርሃኑ ታመነ እና መሠረታዊ ኮማንዶ ታደለ ዓለሙ በበኩላቸው ጠቃሚ የአካል ብቃትና የሥነ-ምግባር ሥልጠና መውሰዳቸውን ገልጸው ለትግሉ ዝግጁ መኾናቸውን አሳውቀዋል።

የወምበርማ ሕዝብ በማያቋርጥ የሬሽን ድጋፉ አሠልጥኖ በምረቃችን ዕለት ደግሞ ትጥቁን ሸልሞ አስደንቆናል ያሉት ተመራቂዎቹ፤ እየመገበ እና ከጠላት እየጠበቀ ለፍፃሜ ያበቃቸውን ሕዝብና የፋኖ አመራር ከልብ አመስግነዋል።

ሥልጠናው አድካሚና ረዥም ጊዜ የወሰደ ቢኾንም በደጋፊዎቻችን ትጋትና በሠልጣኞች ብቃት ለዚህ በቅተናል ያሉት ደግሞ የወምበርማ ብርጌድ ሥልጠና መምሪያ ሓላፊ ም/፲ አለቃ ኮማንዶ ላይችሉህ አሸናፊ ናቸው።
ተመራቂዎቹ ብርጌዱ የሚያደርገውን ትግልም በእጅጉ እንደሚያቃልሉ ሓላፊው አስረድተዋል።

ሥልጠና መምሪያ ሓላፊው አክለውም በአንድነት ጠንክረን በመታገል ያጋጠመንን ፈተና አልፈን ለሁላችንም የምትበጅ አገር መፍጠር አለብን ብለዋል።

©በአፋጎ 5ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!
🙏2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የትግሉን አጠቃላይ ገጽታ የተመለከተ ሲምፖዚየም አዘጋጅቷል።

በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልወና አደጋ ለመመከት ላለፉት ሁለት ዓመታት ታላቅ ተጋድሎ እየተደረገ መሆኑ የሚታወቅ ነው። በተበታተነ ሁኔታ የሚደረገውን ተጋድሎ ወጥ በሆነ ድርጅታዊ መዋቅር ስር ለማድረግ በተጀመረው ጥረት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል የተወለደና ትግሉን በተሻለ ቁመና እየመራ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል። በጥቂት ታጋዮች ከኋላ ቀር መሳሪያ የተነሳው የአማራ ፋኖ ትግል በሁለት ዓመት ውስጥ ያስመዘገበው ድልና የገነባው ግዙፍ ወታደራዊ ሃይል የተጀመረውን የህልውና አደጋ ለመመከት በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲገኝ አድርጎታል። ምንም እንኳን ትግሉ ከሚፈልገው አቅምና ብቃት እንዲሁም የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ካለው መከራና ስቃይ አንጻር የምንገኝበት ምዕራፍ ገና ብዙ እንደሚቀረን የሚያሳይ ቢሆንም በቁርጥኝነትና በተባበረ ሃይል ከቀጠልን በቅርብ ጊዜ የአገዛዙን የጭቆና ቀንበር በጣጥሰን እንደምንጥል ጥርጣሬ የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም።

ለዚህም የተጀመረውን የአንድነት ጉዞ ማፋጠንና ወደኋላ የማንመለስበት የፋኖ ወጥ መዋቅር ለመገንባት ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረግን እንገኛለን። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ለዚህ የአንድነት ጉዞ የሚረዳና የተጋረጡብንን ችግሮች በውይይት ለመፍታት የሚያስችል ታላቅ ሲምፖዚየም ማዘጋጀቱን ሲገልጽ በደስታ ነው።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ) ከዚህ አቅሙ የበለጠ ጠንካራ እንዲሆንና የትግሉ ጊዜ ባጠረ መልኩ ለመቋጨት ያስችል ዘንድ እና ለአለማቀፉ ማህበረሰብ የትግሉን ሂደትና ዓላማ ግልፅ ለማድረግ፣ ለማስተዋወቅ እና በጎ ፈቃደኛ ደጋፊዎችን ለመጨመር ያለመውን ይህን ሲምፖዚየም ጷጉሜ 01 እና 02 ቀን 2017 ዓ.ም ወይም በፈረንጆቹ አቆጣጠር September 06,2025 Saturday Starting 12 Noon and September 07,2025 Sunday Starting 12 Noon በቀጥታ ስርጭት የሚያካሂድ መሆኑን ያስታውቃል።

በሲምፖዚየሙ ላይ የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አመራሮች በጋዜጠኞች ቃለመጠይቅ ይደረግላቸዋል፣ ዝግጅቱም በቴሌቪዥንና በዩቲዩብ፣ ቲክቶክ እና የX (Twitter ) ማህበራዊ ሚዲያዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።

በዚህ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ) ሲምፖዚየም ተሳታፊ በመሆን የአማራ ህዝብ የታወጀበትን እልቂት ለመመከት እየታገለ ያለውን የአማራ ፋኖ በመደገፍ፣ ከአማራም አልፎ በየተራ ሁሉንም ብሄሮች በማጥቃት የጭቆናና የባርነት ስርዓቱን ለማስቀጠል እየሰራ ያለውን "ብልፅግና" የተሰኘውን ጸረ ሕዝብ አገዛዝ እንድንታገልና ሀገርን ከመፍረስ እንድንታደግ ጥሪ እናቀርባለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል - አፋብኃ
🙏21