ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሰኔ 24/2017 ዓ/ም
ጎንደሬ በሻው ክፍለ ጦር ገደብየ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የአገዛዙ ሀይል ላይ ጥቃት አደረሰ

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጠላትን እየደመሰሰ የበላይነቱን እያገኘ ጉዞውን ወደ ፊት ቀጥሏል ።
የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አካል የሆኑት ይታየው እና አጥናፋ ብርጌድ ትናንት ሰኔ 23 /2017 ዓ/ም ከቀኑ አስር ሰዓት የተጀመረው አውደ ውጊያ እስከ ሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲቀጥል ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ገደብየ ከተማን ለቆ አመድየ ተራራ ላይ ተሰቅሎ እንዲያድር ተደርጓል ።
በውጊያው ከ8 በላይ ጠላት ሲደመሰስ ከ13 በላይ የሚሆን የቆሰለ ሲሆን አብዛኛው የአገዛዙ ሀይልም ጨለማውን በመጠቀም የያዘውን ይዞ ከገደብየ ከተማ እንደጠፋ የመረጃ ምንጮቻችን ጠቁመዋል ።

የአገዛዙ ቅልብ እና ሆድ አደር ሰራዊት ቀቢሰ ተስፋ ይዞ ዘመቻ ማዕበል በሚል ድስኩር ፋኖን ለማጥፋት ወደ ተለያዩ የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቀጠና የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ሙትና ቁስለኛ ከመሆን፣ የያዘውን ከማስረከብ ፣ ከመፈርጠጥ ሳይድን እንዲሁም አውራ እንደሌለው የንብ መንጋ በቡድን እና በተናጠል እየተበተነ እየጠፋ ይገኛል። አሁን ላይ አፅጅውና ፀጅው ምድር ላይ እየለየ ብልፅግና ምላሱ ብቻ እንደቀረ የአደባባይ ሀቅ ሁኗል ።


የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር
የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ )
👍41
ገራገሩ ምሬ የአማራዉ አስትንፋስ!!!
ወንዱ የወንዶች ቁና ፈጣሪ ይጠብቅህ!!!!
🙏42🏆1
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል {አፋብኃ} ሰሜን ቀጠና በላይ ዕዝ መይሳው ካሰ 2ኛ ኮር ቋራ ኦሜድላ ክፍለ ጦር ለበርካታ ወራት ያሰለጠናቸውን የፋኖ አባላት አሰመርቋል::

ጠረፍ ጠበቂዎቹ የካሳ ልጁች ዛሬም እንደ ትናት 6ኛ ዙር ሰልጣኞችን አሰመቀረዋል የአፄ ቴዎድሮስ የመንፈስ ልጆች ወደ ፊት!!!!
👍21
የአፋጎ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ 3ኛ ዙር የፋኖ አባላት አስመርቋል!!

እንደራጃለን፣እንሰለጥናለን፣ከጠላቶቻችን እየማረክን እንታጠቃለን የአማራን ህዝብ ከአገዛዙን ስርዓት ነፃ እናወጣዋለን!!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ በሸበል በረንታ ወረዳ ለተከታታይ 5 (አምስት) ወራት ሲያሰለጠናቸው የነበሩ የ3ኛ ዙር ሰልጣኝ የፋኖ አባላትን ሰኔ 24/2017 ዓ.ም በድምቀት አስመርቋል።

በተመራቂ ፋኖዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አመራሮች የሽፈራው ገርባው ብረጌድ አመራሮች እና አባላት እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ማህበርሰብ በተገኙበት የምረቃ ፕሮግራሙ በደማቅ ሁኔታ ተከናዉኗል።

በሰልጣኝ የፋኖ አባላት ተመራቂዎች የምርቃ ስነ-ስርዓት መድርክ የከፈቱት የአፋጎ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ ሰብሳቢ ፋኖ ውዱ ሀይማኖት እንደተናገሩት ይህንን ወታደራዊ ስልጠና እንድንሰለጥን ያሰገደዱን ዘርፈ ብዙ የሆኑ እጅግ በጣም ለመስማት የሚከብዱ አሰቃቂ ጭፍጨፋ እና የዘር ፍጂት በአማራ ህዝብ ላይ ስለደርሰብን አማራ ከሁሉም የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደባይተዋር ተቆጥሮ መጤ እየተባለ ሲፈናቀል ኖሯል። ከዚህም አልፎ አገዛዙ የጥፋት አዋጂ በማወጂ አማራን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በህዝባችን ላይ ቅጥረኛ ወታደሮችን በመላክ ከቤታችን ድረስ መጥቶ ዝርፊያና ንፁሀንን ከመካናይዝድ እስከ አየር ሀይል በመጠቀም እየጨፈጨፈ ይገኛል በማለት መልዕክት አስተላልፎል።


በመቀጠልም የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ባስተላለፈው መልዕክት የተከበራቹህ የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አመራርሮች የተከበራቹህ የሽፈራው ገርባው የብርጌድ አመራሮች እና የሻለቃ አመራሮች እንዲሁም የፋኖ አባላት የተከበራቹህ የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በሸበል በርንታ ወረዳ የሚገኜው ሽፈራው ገርባው ብርጌድ በተከታታይ 5 (አምስት) ወራቶች ወታደራዊ ስልጠና ስትወስዱ የነበራቹህ የ3ኛ ዙር ተመራቂ ፋኖዎችን ለማስመርቅ ጥሪውን አክብራቹህ የተገኛቹህ የክብር እንግዶች የአካባቢው ማህበርሰብ ክፍል በእግዚአብሔር ስም እንኳን በሰላም መጣቹህ እያልኩ በዛሬው እለት ሰኔ 24/2017 ዓ.ም ለመሰባሰባችን ምክንያት የሆናቹህ የሽፈራው ገርባው ብርጌድ 3ኛ ዙር ተመራቂ ፋኖ ወንድሞቻችን እራቡን፣ጥሙን፣ብርዱን፣ሙቀቱን ተቆቁማቹህ በክብር በተጠሩ የክብር እንግዶች ፊት ለመመርቅ በሰላም በመገኜታቹህ እንኳን አደረሳቹህ አደርሰን።

እናተ የዛሬ ተመራቂዎች የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ወደ ፌት ለማራመድ እና የአሸናፌነትን ድል ለማምጣጥ በዛሬው እለት በተከታታይ 5(አምስት) ወራት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ በአካል ብቃት እና በስነልቦና እየተገነባቹህ ይህን ውጣ ውርድ ታግሳቹህ ከእዚህ የምረቃ ስነ-ስርዓት ደረሳቹሀል። እኛ ለእናተ የምንሰጣቹህ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል አደራ ሲሆን እናተ ደግሞ ጀግኖች የወደቁበት ትግል የድል ባለቤት ታደርጉን ዘንድ ሁላችንም ተስፋ አለኝ።

በእንደዚህ አይነት የህልውና/የነፃነት ትግል በዚህ ቦታ የአርበኞች መናህሪያ በሆነው ሸበል በርንታ ቀደም ሲል ጀግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ሀገራችንን ከቀኝ ግዛትና ከባርነት ነፃ አድረገው አስርክበውናል።እንደ ምሳሌ ብንጠቅስ ዛሬ ያለንበት ቦታ ሸበል በረንታ ወረዳ አንዱ ነው።አርበኝነትን ስናነሳ ሸበል በረንታን መረሳት በፍፁም አይቻልም። የአርበኞች መነሀሪያ የአርበኞች መፍለቂያ የጀግኖች መሰባሰቢያ ሸበል በርንታ አንዱ ነው።

በዛሬው እለት በሸበል በረንታ ወረዳ የሚገኜው ሽፈራው ገርበው ብርጌድ ልጆች የምትመረቁት ተመራቂዎች እናተ የጀግኖች የአባት አርበኞች ልጆች ናቹህና በወረዳቹህም ይሁን በመላው አማራ የአማራን ህዝብ ትጥቅ አስፈታለው ብሎ ፌሽካ በመንፋት ባንኩን፣ በምድር ታንኩን፣በሰማይ ድሮን እና መካናይዝድ ጦር በመያዝ በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀውን ዛራፊው ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ አገዛዙ ሀይል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ሥለሚጠበቅብን ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ ራሳችሁን ዝግጁ እንድታደርጉ እያልኩ መልካም የምረቃ ጊዜ እመኝላችኋለሁ ።

በመቀጠልም የክ/ጦር የፍትህ አካል ዋና ሳጅን ፋኖ ካሳሁን መኩሪው ውድ ተመራቂዎች የአማራን ህዝብ ከደርሰበት ግፍና ሰቆቃ ለመታደግ ሲባል የአብይ አህመድ ሰራዊት በአፈሙዝ መመከት እና ከአማራ ምድር ማስወጣት ይጠበቅባቹሀል ሲል ገልፆል። እናተም በስነ- ምግባር ታንፃቹህ ህግን አክብራቹህ መብት እና ግዴታቹህን አውቃቹህ የአማራን ህዝብ ሰላሙን እንድታስከብሩለት ሲል መልዕክቱን አስተላልፎል።

የክ/ጦሩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ፶ አለቃ ኮማንዶ መንበር አደመ የ3ኛ ዙር ልዮ ተመራቂዎችን የቃለ መሀላ ስነ-ስርዓት በማካሄድ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የምርቃ ስነ-ስርዓ ደስ በሚልና በአማር መልኩ በመካሄድ በሰላም ተጠናቋል።

ሰኔ 24/2017 ዓ.ም

ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3👎1🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

የዋግሹም አድማሱ ብርጌድ ባደረሰው ጥቃት የአርቢትን ምሽግ በመስበር በጠላት ኃይል ላይ ድል ተቀዳጀ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
በላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር የሚገኘው ዋግሹም አድማሱ ብርጌድ የአርቢትን ምሽግ በመስበር ጠላትን ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።

በዋግኸምራ ዞን ድሃና ወረዳ አምደወርቅ ከተማ አቶ ያለው ወዳጄ፣የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር አበጄ አሰፋና የሚሊሻ ፅ/ቤት ኃላፊው ሳጅን አማረ ደሳለኝ ያስተባበሩት የድሃና ወረዳና አገው ሸንጎ ሚሊሻዎች የተሳተፉበት አውደ ውጊያ ላይ ተወርዋሪዎቹ ዋግሹም አድማሱ ብርጌድ ሻለቃ አንድ (አስፋው ሻለቃ) አርቢት ከምትባል ቦታ ሰኔ 23 / 2017 ዓ.ም ከንጋቱ 11:30 ሰዓት እስከ ቀኑ 8:15 ሰዓት በወሰደ አውደ ውጊያ አርቢት የሚገኘውን ምሽግ በመስበር በጠላት በኩል አራት የተሰዋ፣ሦስት ቁስለኛ፣አራት ክላሽ፣208 ተተኳሽ በመማረክ ወረዳው ከሚያስተዳድራቸው 33 ቀበሌዎች 13ቱን ቀበሌዎች ነፃ ቀጠና በማድረግና በመቆጣጠር ታላቅ ጀብዱ አስመዝግበዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን አሳውቋል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ሰኔ 24 / 2017 ዓ.ም
3🙏1
አማራዊ አንድነታችን ውዴታችን ሳይሆን ግዴታችን ነው

አማራን በጎጥ የሚከፋፍል እንዲሁም ከአማራነት ውጪ ሌላ የትግል ርዕዮት የሚፈበርክ ከፋፋይ ሰርጎገብ ወይም ባንዳ ከዘር አጥፊ ጠላቶቻችን የማይተናነስ ጠላት ነው።

ኩርዲስታን እንዴት ፈረሰች⁉️

በኩርድ ህዝብ ላይ የተፈፀመውና የሆነባቸው ሁሉ በአምሓራ ህዝብ ላይ ሊሆን የከጀለው ግን የማይሳካው የመበታተን አደጋ ፍፁም ተመሳሳይ ነው። ኩርዶች በጊዜው ነቅተው ለመታገል ቢነሱም አንድ ለመሆን ግን ዘግይተው ነበር። መቋጫ ያላበጁለትም ውስብስብ ፍጭትም ነበራባቸው። ይልቁንስ…
በሐይማኖት
በክ/ሀገር
በወንዝ ወዘተ

ተከፋፍለው በመጓተት እና ለአንድነት አላማ ሰልፍ በመያዝ ለህልውናቸው በመፋለም ፋንታ… ከድል መልስ በኋላ በሀገር አድባር፣ በሰላም ምኩራብ ለሚፈቱ አጀንዳዎች ቅድሚያ ሰጥተው ተሟገቱ።
የከበቧቸው ጠላቶች ግን ፈጠኑ።
ኢራን
ኢራቅ
ቱርክ
ሶሪያን
መሳይ ጎረቤት ሀገራት የኩርድ ግዛተ-ምድር ቀምተው በቅርጫ በመካፈል ታሪክ እንደሌለው ህዝብ "ወፍ ዘራሽ ስደተኛ" እየተባሉ እንዲኖሩ አደረጓቸው።

አማራ አንድ የመሆን ውድ እና ወሳኝ የአሸናፊዎች ዕሴትህን ከተውሃት ካላነሳሃት ለሺህ አመታት ከፍለህ የማትጨርሰውን ውድ ዋጋ ትከፍላለህ። ይህቺን ታሪካዊት ቀን ማለትም አማራዊ አንድነትን እና የፋኖን አንድነት ዛሬ ካላወጅህ፤ ጠቅላላው አማራ እንዲሁም መጪው የአማራ ትውልድ መራራ ሞት፣ ስደት፣ውርደት፣ እና ባርነት ዘላለማዊ ፍርዳችን ትሆናለች።አንድነት ግዴታህ እንጂ ውዴታህ አይደለችም......
በጎራ፣ በሐይማኖት እና አውራጃ ተከፋፍለህ ስትቧቀስ… ርስትህን ተቀራምተው ሀገር የመሆን ቅዠታቸውን ለማሳካት ለቋመጡ… ጠላቶችህ እድል እየሰጠህ መሆኑን ልብ በል

የአምሓራዊነት ህብር አንድ ሊያደርግህ ካልቻለ…የወንዜ እና ጅረት መር የጎጥ ድጥ፣ ጎትቶ፣ ጎትቶ በቀበሌህ አጥቢያ ከሚፈጠፍጥህ በቀር፣ በግርማ ቆሞ የሚታይ ኃያል ህዝብ አያደርግህም።

እንደ አምሐራ፣ አንድ አንገት መሆን ያቃተው… በአውራጃ ድሪቶ ትንትን ራዕይ ሊሰባሰብ አይችልም።

ይልቅ…አምሐራዊነት ርዕዮተ ሰልፍ ሆኖን…ከኩርድ ህዝቦች ውድቀት እንዲሁ ከራሳችን የዘመነ መሳፍንት አሳፋሪ ታሪክ ተምረን፣ ለአሸናፊነት ሰልፍ በንቃት እንትመም

አማራ አንገቱ ፩ ነው
፩ አምሐራ
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever Amhara

ድላችን በተባበረ ክንዳችን
ፈለገ አሣምነው ፅጌ ዘ ብሔረ አምሐራ

ቋሚ ምሥል፦ አምሐራነት እሥትንፋሡ፣ ጎጠኝነትን ተፋላሚው፣ የፋሽሥተ ናዚዝሙ አገዛዝን ግብር በውል የተረዳው፣ በተደራጀ ሠራዊት የሚያምነው፣ የልብ ትጥቅን ጥግ ድረሥ የተጎናጸፈው፣ የትግላችንና የተቋማችን ጠባቂው፣ በመርሕና አሠራር ተጓዡ፣ ሠራዊትን ምልዑ አድርጎ የአካልም የአእምሮም ጂምናዚዬም የሚያሠራው፣ ለአምሐራዊ ነጻነት እሥከ ቀራኒዮ አደባባይ ተጓዡ የአፋብኃ ሠሜን አማራ ቀጠና/ በላይ ዘለቀ ዕዝ ወታደራዊ አዛዡ አርበኛ ሣሙኤል ባለ'ድል
8🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ሸህ ሁሴን ጅብሪል ክፍለጦር ገነቴ ከተማ ላይ ድል ተቀዳጁ።

ሸህ ሁሴን ጅብሪል ክፍለጦር ምዕራብ ወሎ ገነቴ ከተማ ህዝብ አስገድዶ ሰልፍ ሊያስወጣ በ24/2017 ዓ.ም ንጋት የመጣውን 12 መኪና የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ከሁለት ዲሽቃ ጋር እንዲሁም ሆድ አደር አድማ ብተና እና ፖሊስ ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት በርካታውን ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል።

የንጉስ ሚካኤል ኮር ወታደራዊ ዋና አዛዥ አርበኛ ከረም መሃመድ እንዲሁም ብርጌድ አመራሮቹ አርበኛ ሙራድ አህመድ እና እንድሪስ አቢ በመሩት ድንቅ የከተማ ተጋድሎ በርካታ ጥምር ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት የተደመሰሰና የቆሰለ ሲሆን ዘጠኛ ተማርኳል።

ንስሮቹ በቀን ገነቴ ከተማ ለመግባትና ጠላታቸው ላይ ከባድ እርምጃ ለመውሰድ ያስገደዳቸው ህዝባቸውን የቀረ 5000 (አምስት ሽ) ብር ይቀጣል በሚል አስገድዶ ሰልፍ ሊያስወጣ እና በአንድ እጁ ድሮን ይዞ በአንድ እጁ ሰላም በሚል ዘር ማጥፋት እየፈፀመበት ያለውን ህዝብ ግፍና ጭፍጨፋው አይበቃው ብሎ በቁስሉ ላይ እንጨት መስደዱ ይበቃል በሚል ነው።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ሰኔ 25/2017 ዓ.ም
2🙏2