ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዳሞት ያስተፋል ሀሞት የተባለለት በምክንያት ነው💪
ትገባለህ ግን አትወጣም ብለናል። ከወንዶች ምድር ደጋ ዳሞት ገብቶ መውጣት የለም።
1👎1
በሮቤ ወረዳ የገደብሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ካህን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ፡፡

በምሥራቅ አርሲ ሮቤ ወረዳ ቤተ ክህነት የገደብሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ካህን ቀሲስ ተስፋዬ ረታ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡30 አካባቢ በታጣቂ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገልጿል።

ማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ደረሰኝ ባለው መረጃ ባለቤታቸው በተመሳሳይ ሁኔታ መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን አካባቢው ካህኑ የተወለዱበት እና ከዲቁና ጀምሮ በአሁኑ ወቅትም በቤተ ክርስቲያኑ በቅስና ማእረግ እያገለገሉ ነበር ተብሏል፡፡

የካህኑ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በሮቤ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙን የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በወረዳው እየተባባሰ የሚገኘውን አፈና እና ግድያን በመፍራት እና በመስጋት በአካባቢው የሚኖሩ ምእመናን ከተማውን ለቀው እየተሰደዱ መሆኑ ታውቋል፡፡
 
ቀሲስ ተስፋዬ ረታ የሰባት ልጆች አባት ሲሆኑ ልጆቻቸውም ምንም አይነት ሥራ መሥራት የማይችሉ እና ሕጻናት በመሆናቸው ለመጠለያ ይሆናቸው ዘንድ የወረዳው አስተዳደር 200 ካሬ ሜትር መስጠቱን የተናገሩት መረጃ ሰጪያችን የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ በጋራ ሆነው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ጣቢያችን ጉዳዩ ከተከሰተበት ሰዓት አንስቶ ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የወረዳው የፀጥታ ኃይል ኀላፊን ለማግኘት በተደጋጋሚ በእጅ ስልካቸው ላይ ብንደውልም መልስ ማግኘት ሳንችል ቀርተናል ሲል የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል።
💔1
የአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በጌምድር ክፍለጦር በአለፋ ጣቁሳ ወረዳ በሶስት ግንባር ማለትም ደልጊ፣አይብጋና አሲን የሚባሉ ቦታዎች ላይ ከአገዛዙ ጥምር አራ*ዊት ሰራዊት ጋር ውጊያ እያደረገ ይገኛል‼️
ድል ለአማራ ፋኖ
ሰኔ 24/2017 ዓ/ም
ጎንደሬ በሻው ክፍለ ጦር ገደብየ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የአገዛዙ ሀይል ላይ ጥቃት አደረሰ

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጠላትን እየደመሰሰ የበላይነቱን እያገኘ ጉዞውን ወደ ፊት ቀጥሏል ።
የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አካል የሆኑት ይታየው እና አጥናፋ ብርጌድ ትናንት ሰኔ 23 /2017 ዓ/ም ከቀኑ አስር ሰዓት የተጀመረው አውደ ውጊያ እስከ ሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲቀጥል ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ገደብየ ከተማን ለቆ አመድየ ተራራ ላይ ተሰቅሎ እንዲያድር ተደርጓል ።
በውጊያው ከ8 በላይ ጠላት ሲደመሰስ ከ13 በላይ የሚሆን የቆሰለ ሲሆን አብዛኛው የአገዛዙ ሀይልም ጨለማውን በመጠቀም የያዘውን ይዞ ከገደብየ ከተማ እንደጠፋ የመረጃ ምንጮቻችን ጠቁመዋል ።

የአገዛዙ ቅልብ እና ሆድ አደር ሰራዊት ቀቢሰ ተስፋ ይዞ ዘመቻ ማዕበል በሚል ድስኩር ፋኖን ለማጥፋት ወደ ተለያዩ የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቀጠና የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ሙትና ቁስለኛ ከመሆን፣ የያዘውን ከማስረከብ ፣ ከመፈርጠጥ ሳይድን እንዲሁም አውራ እንደሌለው የንብ መንጋ በቡድን እና በተናጠል እየተበተነ እየጠፋ ይገኛል። አሁን ላይ አፅጅውና ፀጅው ምድር ላይ እየለየ ብልፅግና ምላሱ ብቻ እንደቀረ የአደባባይ ሀቅ ሁኗል ።


የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር
የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ )
👍41
ገራገሩ ምሬ የአማራዉ አስትንፋስ!!!
ወንዱ የወንዶች ቁና ፈጣሪ ይጠብቅህ!!!!
🙏42🏆1
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል {አፋብኃ} ሰሜን ቀጠና በላይ ዕዝ መይሳው ካሰ 2ኛ ኮር ቋራ ኦሜድላ ክፍለ ጦር ለበርካታ ወራት ያሰለጠናቸውን የፋኖ አባላት አሰመርቋል::

ጠረፍ ጠበቂዎቹ የካሳ ልጁች ዛሬም እንደ ትናት 6ኛ ዙር ሰልጣኞችን አሰመቀረዋል የአፄ ቴዎድሮስ የመንፈስ ልጆች ወደ ፊት!!!!
👍21
የአፋጎ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ 3ኛ ዙር የፋኖ አባላት አስመርቋል!!

እንደራጃለን፣እንሰለጥናለን፣ከጠላቶቻችን እየማረክን እንታጠቃለን የአማራን ህዝብ ከአገዛዙን ስርዓት ነፃ እናወጣዋለን!!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ በሸበል በረንታ ወረዳ ለተከታታይ 5 (አምስት) ወራት ሲያሰለጠናቸው የነበሩ የ3ኛ ዙር ሰልጣኝ የፋኖ አባላትን ሰኔ 24/2017 ዓ.ም በድምቀት አስመርቋል።

በተመራቂ ፋኖዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አመራሮች የሽፈራው ገርባው ብረጌድ አመራሮች እና አባላት እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ማህበርሰብ በተገኙበት የምረቃ ፕሮግራሙ በደማቅ ሁኔታ ተከናዉኗል።

በሰልጣኝ የፋኖ አባላት ተመራቂዎች የምርቃ ስነ-ስርዓት መድርክ የከፈቱት የአፋጎ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ ሰብሳቢ ፋኖ ውዱ ሀይማኖት እንደተናገሩት ይህንን ወታደራዊ ስልጠና እንድንሰለጥን ያሰገደዱን ዘርፈ ብዙ የሆኑ እጅግ በጣም ለመስማት የሚከብዱ አሰቃቂ ጭፍጨፋ እና የዘር ፍጂት በአማራ ህዝብ ላይ ስለደርሰብን አማራ ከሁሉም የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደባይተዋር ተቆጥሮ መጤ እየተባለ ሲፈናቀል ኖሯል። ከዚህም አልፎ አገዛዙ የጥፋት አዋጂ በማወጂ አማራን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በህዝባችን ላይ ቅጥረኛ ወታደሮችን በመላክ ከቤታችን ድረስ መጥቶ ዝርፊያና ንፁሀንን ከመካናይዝድ እስከ አየር ሀይል በመጠቀም እየጨፈጨፈ ይገኛል በማለት መልዕክት አስተላልፎል።


በመቀጠልም የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ባስተላለፈው መልዕክት የተከበራቹህ የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አመራርሮች የተከበራቹህ የሽፈራው ገርባው የብርጌድ አመራሮች እና የሻለቃ አመራሮች እንዲሁም የፋኖ አባላት የተከበራቹህ የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በሸበል በርንታ ወረዳ የሚገኜው ሽፈራው ገርባው ብርጌድ በተከታታይ 5 (አምስት) ወራቶች ወታደራዊ ስልጠና ስትወስዱ የነበራቹህ የ3ኛ ዙር ተመራቂ ፋኖዎችን ለማስመርቅ ጥሪውን አክብራቹህ የተገኛቹህ የክብር እንግዶች የአካባቢው ማህበርሰብ ክፍል በእግዚአብሔር ስም እንኳን በሰላም መጣቹህ እያልኩ በዛሬው እለት ሰኔ 24/2017 ዓ.ም ለመሰባሰባችን ምክንያት የሆናቹህ የሽፈራው ገርባው ብርጌድ 3ኛ ዙር ተመራቂ ፋኖ ወንድሞቻችን እራቡን፣ጥሙን፣ብርዱን፣ሙቀቱን ተቆቁማቹህ በክብር በተጠሩ የክብር እንግዶች ፊት ለመመርቅ በሰላም በመገኜታቹህ እንኳን አደረሳቹህ አደርሰን።

እናተ የዛሬ ተመራቂዎች የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ወደ ፌት ለማራመድ እና የአሸናፌነትን ድል ለማምጣጥ በዛሬው እለት በተከታታይ 5(አምስት) ወራት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ በአካል ብቃት እና በስነልቦና እየተገነባቹህ ይህን ውጣ ውርድ ታግሳቹህ ከእዚህ የምረቃ ስነ-ስርዓት ደረሳቹሀል። እኛ ለእናተ የምንሰጣቹህ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል አደራ ሲሆን እናተ ደግሞ ጀግኖች የወደቁበት ትግል የድል ባለቤት ታደርጉን ዘንድ ሁላችንም ተስፋ አለኝ።

በእንደዚህ አይነት የህልውና/የነፃነት ትግል በዚህ ቦታ የአርበኞች መናህሪያ በሆነው ሸበል በርንታ ቀደም ሲል ጀግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ሀገራችንን ከቀኝ ግዛትና ከባርነት ነፃ አድረገው አስርክበውናል።እንደ ምሳሌ ብንጠቅስ ዛሬ ያለንበት ቦታ ሸበል በረንታ ወረዳ አንዱ ነው።አርበኝነትን ስናነሳ ሸበል በረንታን መረሳት በፍፁም አይቻልም። የአርበኞች መነሀሪያ የአርበኞች መፍለቂያ የጀግኖች መሰባሰቢያ ሸበል በርንታ አንዱ ነው።

በዛሬው እለት በሸበል በረንታ ወረዳ የሚገኜው ሽፈራው ገርበው ብርጌድ ልጆች የምትመረቁት ተመራቂዎች እናተ የጀግኖች የአባት አርበኞች ልጆች ናቹህና በወረዳቹህም ይሁን በመላው አማራ የአማራን ህዝብ ትጥቅ አስፈታለው ብሎ ፌሽካ በመንፋት ባንኩን፣ በምድር ታንኩን፣በሰማይ ድሮን እና መካናይዝድ ጦር በመያዝ በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀውን ዛራፊው ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ አገዛዙ ሀይል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ሥለሚጠበቅብን ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ ራሳችሁን ዝግጁ እንድታደርጉ እያልኩ መልካም የምረቃ ጊዜ እመኝላችኋለሁ ።

በመቀጠልም የክ/ጦር የፍትህ አካል ዋና ሳጅን ፋኖ ካሳሁን መኩሪው ውድ ተመራቂዎች የአማራን ህዝብ ከደርሰበት ግፍና ሰቆቃ ለመታደግ ሲባል የአብይ አህመድ ሰራዊት በአፈሙዝ መመከት እና ከአማራ ምድር ማስወጣት ይጠበቅባቹሀል ሲል ገልፆል። እናተም በስነ- ምግባር ታንፃቹህ ህግን አክብራቹህ መብት እና ግዴታቹህን አውቃቹህ የአማራን ህዝብ ሰላሙን እንድታስከብሩለት ሲል መልዕክቱን አስተላልፎል።

የክ/ጦሩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ፶ አለቃ ኮማንዶ መንበር አደመ የ3ኛ ዙር ልዮ ተመራቂዎችን የቃለ መሀላ ስነ-ስርዓት በማካሄድ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የምርቃ ስነ-ስርዓ ደስ በሚልና በአማር መልኩ በመካሄድ በሰላም ተጠናቋል።

ሰኔ 24/2017 ዓ.ም

ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3👎1🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

የዋግሹም አድማሱ ብርጌድ ባደረሰው ጥቃት የአርቢትን ምሽግ በመስበር በጠላት ኃይል ላይ ድል ተቀዳጀ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
በላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር የሚገኘው ዋግሹም አድማሱ ብርጌድ የአርቢትን ምሽግ በመስበር ጠላትን ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።

በዋግኸምራ ዞን ድሃና ወረዳ አምደወርቅ ከተማ አቶ ያለው ወዳጄ፣የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር አበጄ አሰፋና የሚሊሻ ፅ/ቤት ኃላፊው ሳጅን አማረ ደሳለኝ ያስተባበሩት የድሃና ወረዳና አገው ሸንጎ ሚሊሻዎች የተሳተፉበት አውደ ውጊያ ላይ ተወርዋሪዎቹ ዋግሹም አድማሱ ብርጌድ ሻለቃ አንድ (አስፋው ሻለቃ) አርቢት ከምትባል ቦታ ሰኔ 23 / 2017 ዓ.ም ከንጋቱ 11:30 ሰዓት እስከ ቀኑ 8:15 ሰዓት በወሰደ አውደ ውጊያ አርቢት የሚገኘውን ምሽግ በመስበር በጠላት በኩል አራት የተሰዋ፣ሦስት ቁስለኛ፣አራት ክላሽ፣208 ተተኳሽ በመማረክ ወረዳው ከሚያስተዳድራቸው 33 ቀበሌዎች 13ቱን ቀበሌዎች ነፃ ቀጠና በማድረግና በመቆጣጠር ታላቅ ጀብዱ አስመዝግበዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን አሳውቋል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ሰኔ 24 / 2017 ዓ.ም
3🙏1