ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.22K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ከአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና-በላይ ዕዝ በመንገድ መዘጋት ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ

እንደሚታወቀዉ ፋሽስቱ እና ናዚዝሙ ስርአት ብልፅግና አማራን ከምድረ ገፅ ጨርሶ ማጥፋት የሚል ዘመቻ ከጀመረ ዘመናት ተቆጥረዋል።

አማራ የሚባል ብሄር ነገድ የለም ብሎ ካወጀና አማራን በማንነቱ እየገደለዉና እያሳደደዉ እንዳለ አደለም ፈጣሪ በአምሳሉ የፈጠረዉ ፍጡር ቀርቶ በመድፍ በዙ በጀት በድሮንና በተለያዩ የዘመኑ ቴክኖሎጅ በፈበረካቸዉ መሣሪያወች የሚደበደቡት የአማራ ጫካና ዱር ገደሉ ምስክር ናቸዉ።

ብሄረ አማራን ለማጥፋት
በኢኮኖሚ ማዳከምን
በጤና ዘርፉ ግብአቶችን ማጥፋት
በትምህርት ደካማና መሠረት የሌለዉ ትዉልድ ማድረግ
በፖለቲካ ሽባና ግራ የተጋባ ዜጋ ማድረግ
ማህበራዊ እና ባህላዊ ትዉፊቱን ማክሰም እና ማጥፋት የሚሉ ገዳይ ሀሳቦችን ማራመድና ማስቀጠል ቋሚ ስራዉ አድርጎት ቆይቷል።

ለምሳሌ በዚህ ወር አንድም ቀን ት/ቤት ሂደዉ የማያዉቁ የድሀ ልጆችን ሰብስቦ የ12ኛ የብሄራዊ መልቀቂያ ፈተናን መዉሰድ አለባችሁ ብሎ በየዞኑ ዉስጥ ወደ ሚገኙ ዩኒቨርስቲወች እያጋዛቸዉ ይገኛል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሀል እንዲሉ ለህዝቡ ፋኖ መንገድ ዘግቷል እያለ ፕሮፖጋንዳ እየነዛ ሣይማሩ የጨለማ ፈተና የሚፈተኑት ተማሪወች በሀሳብ እና በሰቀቀን የሚያዉቁትን እንኳን በሰላም እንዳይፈተኑና በፍርሀት ተስፋ ቆራጭ ትዉልድ እያደረጋቸዉ ይገኛል።

ይህ አለማዉ ገበሬዉ ዘር እየዘራና የማዳበሪያ አቅርቦት ማከማቻ ወር ስለሆነ ገበሬዉ አምርቶ የኢኮኖሚዉ ተሣታፊና ተወዳዳሪ እንዳይሆን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ግልፅ ነዉ።

የአማራ ፋኖ ለህዝቡ የቆመ እና መስዋት እየሆነ ያለ እንጅ ምንም የማያቁ ሳይማሩ ተፈተኑ የተባሉ ተማሪወች እንደወጡ እንዲቀሩና ከስርአቱ በላይ መከራ የሚሆናቸዉ አደለም።ወላዶች በዉሊድ ምክንያት ሂወታቸዉ እንዲያልፍ ለረጅም ወራት ገዳዩ እና ፋሽስቱ ስርአት ብልፅግና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዳይሰጡ ያገዳቸዉ መንገዶች መኖራቸዉ ይታወቃል።ነገር ግን ፋኖ እኒህ መንገዶች ተከፍተዉ ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ ትልቅ ትግል እያደረገ ይገኛል።

ስለዚህ ከዛሬ ሰኔ 23/2017 ዓም ጀምሮ የተጣለዉ የትራንስፖርት እገዳ በአፋብኃ በኩል እንዳልሆነና ተቀባይነት የሌለዉ የብልፅግና ፕሮፖጋንዳ እንደሆነ እንዲታወቅ።

አሽከርካሪ ሹፌሮች በአስቸኳይ ስራችሁን እና የተለመደ የህዝብ አገልግሎታችሁን እንድትሰጡ ሲል የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና-በላይ ዘለቀ ዕዝ ጥሪዉን አስተላልፏል።

ማሳሰቢያ፦ የመንገድ መከፈት ለማህበረሰባችን
ህልውና አደጋ እና ለአማራ ትግል እንቅፋት የሚሆን ሁኖ ከተገኘና የአፋብኃ ትዛዝ ከሆነ ተቋማዊ ትዛዝና መመሪያ የሚከበር መሆኑ እንዲታወቅ!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አርበኛ ድረስ ሞላ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና-በላይ ዘለቀ ዕዝ ም/ህ/ግ/ሀላፊ
9
የጉና ክፍለ ጦሯ እሥቴ ዴንሣ ብርጌድ፣ ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር፣ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር እና የ፩ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲሥ የፋኖ ሠራዊት

በደራ ምድር ተከታታይ ቀናትን በጥምረት የሚያደርጉት ውጊያ እንደቀጠለ ነው።

አፋብኃ ሠሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር
ሠኔ 23/2017ዓ.ም

ኃቅአለው ፀጋ
6
አሳዛኝ ዜና፦በደጎእስቴ ወረዳ የሚገኙ ተስፋ የቆረጡ የብልፅግና ሆዳም አመራሮች ከቆማ መኢየሱስ ከተማ ያለውን ትራንስፖርት መስመር ለ3ወር በመዝጋት ህዝቡ እየተሰቃየ ይገኛል።በዚህ ምክንያት 2እናቶች ወሮ አያል ጥለየ እና የዝቤ ደመቀ የተባሉ ነፍሰጡር እናቶች ትራንስፖርት ባለማግኘታቸው በእግር ጉዞ ላይ እያሉ መንገድ ላይ ህይወታቸውን አተዋል።የህዝብ ስቃይ የሚያስደስተውብልፅግና ህዝባችን ላይ ከፍተኛ በደል እያደረሱ ይገኛል።
4
አፋብኃ ሠሜን አማራ ቀጠና (በላይ ዘለቀ ዕዝ)
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር (፩ኛ ኮር)
ሠኔ 23/2017ዓ.ም

ደራ/ጎንደር/አምሐራ
በትናንትናው ዕለት በደራው አምበሣሜ የጀመረው አውደ ውጊያ አድማሡን አሥፍቶ 2ኛ ቀኑን አሥቆጥሯል። በዚህ ውጊያ ዲሽቃና ብሬን ማራኪዎቹ የጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ሠራዊት፣ ጠላትን በግርማቸው የሚያርዱት ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር፣ የጉናዋ ፈርጥ ጥቁሯ አናብሥት እሥቴ ዴንሣ ብርጌድ አንዲት ሻለቃ እና የ፩ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲሥ አካላት ሠኔ ማርያም ላይ የጀመሩት አውደ ውጊያ አድማሡን አሥፍቶ በአርብ ገበያ ዙሪያ፣ ሥንጋጥ፣ አላታ፣ ሠለል በይ፣ ጎሽትር፣ ጎኃ እና አምበሣሜ ዙሪያ መዳረሻዎች ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ አድርገዋል።

በዚህ እልህ አሥጨራሽ ውጊያ የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት አለኝ ያለውን ከባድ መሣሪያ ተጠቅሟል። በተቃራኒው ፍትሕን በልባቸው ያነገቡት የአማራ ፋኖዎች ከልብ ትጥቅ እሥከ ነፍጥ ትጥቅ ተሟልተውና የውጊያ ቦታዎችን በሚገባ እያነበቡ ሢዋጉ ውለዋል።
በትናንትናው ዕለት ዲሽቃ የተማረከው፣ ብሬን ያሥረከበው፣ በሽህዎች የሚቆጠር የብሬን፥ ክላሽና ዲሽቃ ተተኳሽን እንኳችኹ ያለው፣ ተሽከርካሪዎቹን ትቶ የፈረጠጠው፣ አመራሮቹን ያሥደመሰሰውና በጥቅሉ የሞራል፥የቁሥና የአካል ሥብራትን በግድ እንዲቀበል የተደረገው የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት ትናንት ከተጨመረለት ኃይል ሌላ በዛሬው ዕለት ብዛት ያለው ጦር ከባሕር ዳርና ከወሮታ ተጨምሮለት ለመዋጋት ቢሞክርም ዛሬም ሌላኛውን ዲሽቃ ለማሥረከብ ጫፍ ላይ ደርሶ ነበር።
ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ልጆቹ በቦምብ የጠላትን ምሽግ ሠባብረዋል። ለአምሐራነት የሚሠጠውን ክቡር መሥዋዕትነት ከፍለው አይበገሬው አምሐራነትን ለጠላት አሥመልክተው አልፈዋል። በሥፋት ለማጥቃት ከሁሉም አቅጣጫ የመጣውን የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት በሚገባ መክተውታል፣ ከመጠቃት ወደ ፀረ ማጥቃት ተሸጋግረዋል። መራሮቹ አምሐሮች በደራ ምድር ጠላትን አብረክርከዋል። ብዛት የነበረውን የጠላት ግምባርና አሠላለፍ በመጨረሻው ሠዓት ወደ አንድ ግምባር ብቻ እንዲመጣ አሥገድደውታል። ቆራጦቹ አምሐሮች መምረርን ለወገንም ለጠላትም አሣይተው በክቡር መሥዋዕትነት አልፈዋል።

በዚህ የደራ ውጊያ ጠላት አይቀጡ ቅጣት የተቀጣበት፣ ድል በነጻ እንደማይገኝ የተገለጠበት፣ የጠላት ምሽግ የተሰባበረበት፣ ጠላት ዘርፈ ብዙ ኪሳራን የተጎናጸፈበትና በጥቅሉ የፋኖ ሠራዊት አሣማኝ ድልን በተጨባጭ እዬገለጠና ጠላትን እያምበረከከ ይገኛል። በተረፈ ግዮናዊ እሣተ ገሞራ ትውልዱ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላልነጻነቱን በደሙ ያረጋግጣል። ለትግሉም በንጡህ አምሐራነት እሥከ ቀራኒዮ አደባባይ ይታመናል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንተዓለም አምሐራ Forever Amhara
፩ አምሐራ

አፋብኃ ሠሜን አምሐራ ቀጠና
በላይ ዘለቀ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
ኃቅአለው ፀጋ


ጎንደር/አምሐራ/ኢትዮጵያ
👍32👏1🎉1🤩1
ሰበር ዜና!

ሰሜናዊቷ ወርቀ ደቦ ከተማ በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጥላ ስር ሆነች!
          
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው  የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  ድል ተቀናጀ።

የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አካል የሆኑት ይታየው እና አጥናፋ ብርጌድ ዛሬ ሰኔ 23/2017 ዓ/ም ከቀኑ አስር ሰዓት ጀምሮ እስከ አሁን እየተደረገ ባለው አውደ ውጊያ ከገደብየ እና ዳባት ከተማ መካከል የምትገኘውን ወርቀ ደቦ ከተማን ከአገዛዙ ብልጽግና ወንበር አስጠባቂ ሀይል በማስለቀቅ ችለዋል።

ዘመቻ ማዕበል ብሎ ለማፅዳት የገባው የአገዛዙ ቅልብ ሀይል ለፋኖ ቀለብ ሁኖ እየተፀዳ ሲገኝ በውጊያው ጠላት ከፍተኛ የሆነ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ አስተናግዶ ወርቀ ደቦን ለወርቆች ጎንደሬ በጋሻዎች ሰጥቶ እየፈረጨጠ   ወደ ገደብየ ከተማ  ቢያመራም እንደ አራስ ነብር የተቆጡት ጀግኖቻችን እየደረሱ እራት እያደረጓቸው  ይገኛሉ።  

ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን  በዘመቻ ማዕበል ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በአገዛዙ ሀይል ላይ ከፍተኛ ድልን እየተቀናጀ ወደ ፊት  እየገሰገሰ ይገኛል። 

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና  በላይ ዕዝ  ዳግማዊ ቴውድሮስ /5ኛ/ ኮር የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ አርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ )
1👍1
የአፋጎ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር የህዝባዊ ውይይቶችን እያካሄደ ይገኛል።

ሰኔ 23/2017 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሽፈራው ገርባው ብርጌድ በሚያስተዳራቸው ቀበሌዎች በሸበል በርንታ ወረዳ በህዝባዊ አደረጃጀት፣ህዝባዊ አስተዳደሮችና መሰል ጉዳዮች በአራጤና አካባቢው ቀበሌ ሰፋ ያለ የህዝብ ውይይቶች ተካሂደዋል።በህዝባዊ ውይይቶች የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አመራሮች፣የሽፈራው ገርባው ብርጌድ አመራሮች የአራት ቀበሌ ማህበርሰብ እያስተዳደሩ የሚገኙት የጎበዝ አለቃዎች፣ጊዚአዊ አስተዳደሮች በተገኙበት ህዝባዊ ውይይትች በሰላም ተካሂደዋል

ሰኔ 23/2017 ዓ.ም

ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ
👍1
1ኛ ክፍለ ጦር ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ ድል በድል ሁኗል።የቀደመ ታሪኩንም ደግሟል።

  ገና በትግሉ ጅማሬ ማግስት ስለ አማራ ህዝብ ሲሉ ከጠላት ጋር እየተናነቁ ታሪክም እየፃፍ ባለፍት የይልማና ዴንሳ አዴት ጀግኖች አፅም ላይ እንደ ዓለት በጠንካራ መሰረት ላይ የተመሰረተው የያኔው አሳምነው ፅጌ የዛሬው ሻለቃ እንሙት ያዛቸው ብርጌድ ዛሬም በአስደናቂ የድል ጉዳና ላይ ነው።ሀምሌ 2015 ዓ/ም ሁለተኛ ዓመቱን የሚያስቆጥረው ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ በአማራ ፋኖ ትግል ውስጥ ጉልህ የድል ባለቤት ከሆኑት ብርጌዶች መካከል ግንባር ቀደሙ ብርጌድ ነው።በፍፁም ወታደራዊ ዲስፕሊን የተመሰረተው አይበገሬው ብርጌድ ክንዱ እንደ እሳት በሚፋጀው አልሞ ተኳሹ ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ፣በእነ ሞት አይፈሬው ፂም/ይናገር አየለ  ፣ብርሃን ፀጋ ፣አድምጠው መንሸው፣ጌታሲል ያረጋል ... ክብር መስዋትነት ላይ የፀናው ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ በብዙ እየተፈተነ የገጠሙትን ፈተናዎችም ድል እያደረገ ዛሬ ላይ ደርሷል።

         ነሀሴ 23-24/2015 ፤መስከረም 5 /2016 ፤መስከረም 24/2016፤መስከረም 29 እስከ ጥቅምት 4/2017 ለተከታታይ አምስት ቀን ጥር 07/2017 ፣ሰኔ 5/2017 እና ሰኔ 17/2017 ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ በጠላት ላይ ትልቅ ድልን ካስመዘገበባቸው ቀኖች መካከል ትቂቶች ናቸው።በዛሬው ዕለትም በይዞራ/መስታይት ላይ የፋሽሽቱን አብይ ሰራዊት ከበባ ውስጥ በማስገባት ምርኮ በምርኮ አድርገወታል።ጀብደኞቹ በርካታ ቁጥር ያለው ነፍስ ወከፍ መሳሪያ፣ተተኳሽና ምርከኞ ከጠላቶቹ እጅ ነጥቋል።

     የጀብደኞቹ ጀብድ  ይቀጥላል!

     ሻለቃ አንሙት አንረሳህም!!!

      Marshet T Demissie የአፋጎ ቃል አቀባይ
4👎1🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዳሞት ያስተፋል ሀሞት የተባለለት በምክንያት ነው💪
ትገባለህ ግን አትወጣም ብለናል። ከወንዶች ምድር ደጋ ዳሞት ገብቶ መውጣት የለም።
1👎1
በሮቤ ወረዳ የገደብሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ካህን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ፡፡

በምሥራቅ አርሲ ሮቤ ወረዳ ቤተ ክህነት የገደብሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ካህን ቀሲስ ተስፋዬ ረታ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡30 አካባቢ በታጣቂ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገልጿል።

ማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ደረሰኝ ባለው መረጃ ባለቤታቸው በተመሳሳይ ሁኔታ መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን አካባቢው ካህኑ የተወለዱበት እና ከዲቁና ጀምሮ በአሁኑ ወቅትም በቤተ ክርስቲያኑ በቅስና ማእረግ እያገለገሉ ነበር ተብሏል፡፡

የካህኑ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በሮቤ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙን የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በወረዳው እየተባባሰ የሚገኘውን አፈና እና ግድያን በመፍራት እና በመስጋት በአካባቢው የሚኖሩ ምእመናን ከተማውን ለቀው እየተሰደዱ መሆኑ ታውቋል፡፡
 
ቀሲስ ተስፋዬ ረታ የሰባት ልጆች አባት ሲሆኑ ልጆቻቸውም ምንም አይነት ሥራ መሥራት የማይችሉ እና ሕጻናት በመሆናቸው ለመጠለያ ይሆናቸው ዘንድ የወረዳው አስተዳደር 200 ካሬ ሜትር መስጠቱን የተናገሩት መረጃ ሰጪያችን የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ በጋራ ሆነው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ጣቢያችን ጉዳዩ ከተከሰተበት ሰዓት አንስቶ ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የወረዳው የፀጥታ ኃይል ኀላፊን ለማግኘት በተደጋጋሚ በእጅ ስልካቸው ላይ ብንደውልም መልስ ማግኘት ሳንችል ቀርተናል ሲል የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል።
💔1
የአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በጌምድር ክፍለጦር በአለፋ ጣቁሳ ወረዳ በሶስት ግንባር ማለትም ደልጊ፣አይብጋና አሲን የሚባሉ ቦታዎች ላይ ከአገዛዙ ጥምር አራ*ዊት ሰራዊት ጋር ውጊያ እያደረገ ይገኛል‼️
ድል ለአማራ ፋኖ
ሰኔ 24/2017 ዓ/ም
ጎንደሬ በሻው ክፍለ ጦር ገደብየ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የአገዛዙ ሀይል ላይ ጥቃት አደረሰ

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጠላትን እየደመሰሰ የበላይነቱን እያገኘ ጉዞውን ወደ ፊት ቀጥሏል ።
የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አካል የሆኑት ይታየው እና አጥናፋ ብርጌድ ትናንት ሰኔ 23 /2017 ዓ/ም ከቀኑ አስር ሰዓት የተጀመረው አውደ ውጊያ እስከ ሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲቀጥል ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ገደብየ ከተማን ለቆ አመድየ ተራራ ላይ ተሰቅሎ እንዲያድር ተደርጓል ።
በውጊያው ከ8 በላይ ጠላት ሲደመሰስ ከ13 በላይ የሚሆን የቆሰለ ሲሆን አብዛኛው የአገዛዙ ሀይልም ጨለማውን በመጠቀም የያዘውን ይዞ ከገደብየ ከተማ እንደጠፋ የመረጃ ምንጮቻችን ጠቁመዋል ።

የአገዛዙ ቅልብ እና ሆድ አደር ሰራዊት ቀቢሰ ተስፋ ይዞ ዘመቻ ማዕበል በሚል ድስኩር ፋኖን ለማጥፋት ወደ ተለያዩ የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቀጠና የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ሙትና ቁስለኛ ከመሆን፣ የያዘውን ከማስረከብ ፣ ከመፈርጠጥ ሳይድን እንዲሁም አውራ እንደሌለው የንብ መንጋ በቡድን እና በተናጠል እየተበተነ እየጠፋ ይገኛል። አሁን ላይ አፅጅውና ፀጅው ምድር ላይ እየለየ ብልፅግና ምላሱ ብቻ እንደቀረ የአደባባይ ሀቅ ሁኗል ።


የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር
የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ )
👍41
ገራገሩ ምሬ የአማራዉ አስትንፋስ!!!
ወንዱ የወንዶች ቁና ፈጣሪ ይጠብቅህ!!!!
🙏42🏆1
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል {አፋብኃ} ሰሜን ቀጠና በላይ ዕዝ መይሳው ካሰ 2ኛ ኮር ቋራ ኦሜድላ ክፍለ ጦር ለበርካታ ወራት ያሰለጠናቸውን የፋኖ አባላት አሰመርቋል::

ጠረፍ ጠበቂዎቹ የካሳ ልጁች ዛሬም እንደ ትናት 6ኛ ዙር ሰልጣኞችን አሰመቀረዋል የአፄ ቴዎድሮስ የመንፈስ ልጆች ወደ ፊት!!!!
👍21