ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ምስራቅ አማራ ኮር 1 እና ኮር 2 ከቆቦ ወልድያ ፌደራል መንገድ ጥቁር አስፓልቱን በመቆጣጠርና ሶስት የጠላት ወታደራዊ ካምፖችን በማውደም ታላቅ ድል መጎናፀፋቸው ይታወቃል::

ስለሆነም በዚህ ድንቅ የዘመቻ ስምሪትና የተሳካ ግዳጅ አፈፃፀም ከሁለት ሳምንት በፊት ራያ ቆቦ ተኩለሽ ገብቶ መሽጎ የነበረው የጠላት ሰራዊት ያለ ምንም ዉጊያ እና የጥይት ድምፅ ከተማዋን ለንስሮቹ አስረክቦ ፈርጥጧል::

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
ሰኔ 21/2017 ዓ.ም
👍4
#የአፋብኃ ጎንደር ቀጠና ሜ/ጀ/ል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክ/ጦር

        ቀን ሰኔ 21/2017 ዓ.ም

   የአፋብኃ ጎንደር አማራ ቀጠና  ሜጀል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክ/ጦር  የተላለፈ  የማስጠንቀቂያ መልዕክት:-

  የአደባባይ ወንጀለኛው፣ ጨፍጫፊው፣ ገዳዩ፣ በጅምላ ቀባሪው፣ አፈናቃዩ፣ ዘራፊው፣ሀይማኖት የለሹ እና ሀይማኖተኞችን አሳዳጁ የብልፅግና ሥርዓት ሁሉም እንደሚያውቀው ወደ መንበረ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በአማራ ሕዝብእና ሀይማኖት  ላይ ያነጣጠረ ግፍ እና በደል ሲያደርስ ቆይቷል አሁንም ይህ ሥርዓት አማራ እንደ ህዝብ ሳይቆጠር በየሄደበት በማንነቱ እንዲያፍር፣ እንዲሸማቀቅ፣ እንዳይኖር ተደርጓል፣ ተፈናቅሏል፣ ሀብት ንብረቱን ተቀመቷል የሀይማኖት አባቶች ታርደዋል ቤተ እምነታቸው  ተቃጥሏል።
     ይህ በእንዲህ አይቀጥልም በማለት የአማራ  ህዝብ አትግደሉን፣ አታፈናቅሉን፣ ሀይማኖታችን አትንኩ ብሎ ወጥቶ አብይ መራሹ ብልፅግናን በማሽመድመድ ላይ ይገኛል። አለው አልሞትኩም መንበረ ሥልጣኔ አለ ለማለት  ከሰሞኑ የብልፅግና አመራር ስሙን ለማደስና ማህበረሰቡ ከእኔ ጋር ነው ብሎ ለካድራዎቹ ለማሳመኛነት ለመጠቀም ሥኳር፣ ዘይትና ማዳበሪያ ልስጣችሁ በሚል የልጂነት ማታለያ በመጠቀም በርካታ አርሶአደሮችንና የከተሜውን ነዋሪ ደግፉኝ እያለ ሰልፍ መጥራቱን አይናል። ነገር ግን ከአሁን በፊት የጠራቸው የድጋፍ ሰልፎች በሁሉም ቀጠናዎች በአማራ ፋኖ የቁርጥ ቀን ልጆች አፍሮና ተዋርዶ ተመልሷል። ከፍተኛም ኪሳራ ደርሶበታል።ከወደቁ ወዲያ መንፈራገጥ ጀርባ መምለጥ የሆነበት ብልፅግና ዛሬ ደግሞ በዝቋላ ገዳም የሚኖሩ አባቶቻችን ዳዊት እንዳንጠለጠሉ ከባዕታቸው በሰይፍና በጥይት ተረሺነዋል፣ እረሽነዋል፣ ያልታየ የግፍ ጥላቻቸውን ዓለም በቃኝ ብለው ሞትን በናቁ መናንያን ላይ ያደረሰውን መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ ለማስቀየስና አጀንዳ ለማስቀየር ታስቦ  እሑድ ሰኔ 22/2017ዓ.ም በአማራ ምድር በግዳጂ የተጠራ ሰልፍ ሲሆን ለምሳሌ በደብረታቦር፣ መካነኢየሱስ፣ አንዳቤት ፣ ወረታ እና አንበሳሜ የደግፋኝ ሰልፍ እንደሚያደርግ መረጃዎች ደርሰውናል። ሰለሆነም ይህንን የጂልነት ጥሪ ሰምቶ ለድጋፍ የሚወጣና ፋኖን የሚያጥላላ መፎክር ይዞ የሚሰለፍ፣ በተሰውት ሰማዕታት አባቶቻችን ደም መቀለድ እና መሳለቅ ነውና በሰልፋ የምትሰለፋ፣ ሀሳብ የምትሰጡ፣ የምትቀሰቅሱ እና የምታስፈራሩ ግለሰብና ማህበራቶች ካላችሁ በዕለቱ በሚወሰደው ፈጣን ርምጃ ለሚደርስባችሁ ጉዳት የጉና ክ/ጦር ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን እንገልፃለንን።
              አማራነት ሀጢያት አደለም ላናሸንፍአ ልጀመርንም እናሸንፋለን እንነግሳለን ያሸናፊዎቹ የነጋሾቹ የአባቶቻችን ልጆች ነን።
    
#ድል ለአማራው ፋኖ።
© መምህር አሃዱ በየነ
4
ሰበር ዜና:- ከራያ አላማጣ ዋጃ እስከ ራያ ቆቦ ያለው ጥቁር አስፋልት በፋኖ ተቆረጠ:: ማንም ማለፍ አይችልም!!

የጠላይ እንቅስቃሴ ተገድቧል:: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 እና ምስራቅ አማራ ኮር 2 ፋኖዎች ከራያ አላማጣ ዋጃ መግቢያ ዋልካ መንደር እስከ ራያ ቆቦ ጎብየ ፌደራል መንገድ ተቆጣጥረዋል::

ምስራቅ አማራ ኮር 2 አንድ መድፍ አንድ ዙ23 እና አንድ ብረት ለበስ በሞርታር በማውደም ከቆቦ ከተማ ሆርማት ወታደራዊ ካምፕ እስከ ራያ ቆቦ ጎብየ ከተማ መግቢያ ድረስ ተቆጣጠሩ::

የምስራቅ አማራ ኮር 2 ሁሉም አሃዶች ዞብል አምባ: ካላኮርማ: ታጠቅ እና ዲቢና ወርቄ ባለሽርጡ በተሳተፉበት ሰፊ ቀጠና በሸፈነ ተጋድሎ ሶስት ወታደራዊ ካምፖችን እንዲሁም ሶስት መካናይዝድ መሳሪያዎችን በማውደምና ሮቢት ከተማን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

ሰኔ 20ለ 21/2017 ዓ.ም ሌሊት በጀመረ ተጋድሎ በሆርማት እና አራዱም ወታደራዊ ካምፕ እንዲሁም በመንጀሎ በሮቢት ከተማ እና አሚድ ውሃ ባሉ ግንባሮች በርካታ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት የተደመሰሰ ሲሆን ከ120-200 የሚሆን ቁስለኛ ቆቦ ሆስፒታል አምስት ኦራል እና አንድ ፓትሮል ቁስለኛ ወደ ወልድያ ሆስፒታል አስገብቷል:: ፋኖ ሙሉ ለሙሉ በተቆጣጠረው ሮቢት ከተማ በርካታ አስከሬን ጥሎ ወደ ወልድያ አቅጣጫ ፈርጥጧል::

ለሁለት አመት ከፍተኛ ማዘዣ ጣቢያ እና የመካናይዝድ ቤዝ አድርጎት የኖረውን ሆርማት ወታደራዊ ካምፕ በደረሰበት ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ምክንያት ዛሬ ማምሻውን ካምፑን ለቆ ወደ ቆቦ ከተማ ገብቷል:: ለዚህ የዳረገውም ከዞብል አምባ ክፍለጦር መካናይዝድ የተቃጣበት ጥቃትና የደረሰበት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ነው:: በጥቃቱ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የወታደራዊ ካምፑ አባላት ሙትና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል::

ከዞብል አምባ ክፍለጦር መካናይዝድ በተፈፀመባቸው ጥቃት አንድ አንድ ብረት ለበስና አንድ መድፍ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ጥገና ለማድረግ ያደረጉት ጥረት አልተሳካላቸውም:: ከዚህ ጋር ተያይዞ የአሳምነው ክፍለጦር መካናይዝድ ካላኮርማ ክፍለጦር ብርቱ ተጋድሎ ባደረጉበት በሮቢት ከተማ ግንባር አንድ ዙ23 አውድመዋል::

በዚሁ ግንባር ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦር 4ኛ ሻለቃ ራያ ቆቦ ጎብየ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት በመፈፀም ታላቅ ጀብዱ የፈፀመች ሲሆን ቀጠናውንም በመዝጋት ጠላት ከወልድያና ሐራ ተጨማሪ የሰው ሃይል እንዳይጨምር በማድረግ ለተመዘገበው አመርቂ ድል ጉልህ ሚና ተጫውታለች::

ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለጦር "ዘመቻ ሃብታሙ ሞላ" ብለው በሰየሙት የተከታታይ የአምስት ቀን ተጋድሎ ነባር ይዞታዎችን ከማስጠበቅ በተጨማሪ ከራያ አላማጣ ዋጃ ከተማ እስከ ጮቢ በር ተቆጣጥረው ይገኛሉ::

ፋሽስቱ አገዛዝ ዘመቻ ማዕበል ብሎ በሰየመው ማጥቃት የሐውጃኖ ክፍለጦር ጠንካራ ይዞታዎችን ለመቆጣጠር በጮቢ በር አማያ ቢጭሮ እና ኩቢቀረንሳ ባለፉት አምስት ተከታታይ ቀናቶች ማጥቃት ቢያደርግም አይበገሬዎቹ በመከላከል በመጨረሻም ዛሬ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ ቀጠናውን በማስለቀቅ እስከ ጥቁር አስፓልት ተቆጣጥረዋል::

ሐውጃኖ ክፍለጦር "በዘመቻ ሃብታሙ ሞላ" ለተከታታይ አምስት ቀናቶች ባደረጉት ተጋድሎ ድሽቃውንና ድሽቃ ምድብተኞችን ጨምሮ እስከ እግረኛ አመራሮች ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ቀጠናቸውንና ጠንካራ ይዞታቸውም በማስጠበቅና የጠላትን ይዞታ ፌደራል መንገድ ጭምር በመቆጣጠር "ዘመቻ ሃብታሙ ሞላን" በታላቅ ድል ደምድመውታል::
12👍1
አፋብኃ ሰሜን ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
  ሰኔ 22/2017 ዓ.ም

     ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ጎንደር ከተማ ዓፄ ቴዎድሮስ ኤርፖርትን ጨምሮ በ5 ወረዳዎች ብርቱ ውጊያ እያደረገ ይገኛል።

ጠላት ኦህዴድ ብልፅግና   ከትላንት ጀምሮ ከሰማይ በድሮን ቅኝት ከምድር አለኝ የሚለውን ሰራዊትና  በሰፊ ቀጠና በማስፈር የመከላከል አጥር ለመስራት ሞክሮ ነበር።ሆኖም በአስደናቂ ወታደራዊ ጥበብና ጀግንነት ሰራዊታችን የጠላትን የመከላከል አጥር በመስበር ወደ ዋና የተልዕኮ ኢላማ እየተሸጋገረ ነው።

      ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

               ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
👍5🔥4
👉👉አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር በአዲስ ዘመን ፣ በማክሰኝት ፣በደጎማ ፣በአርባ ፣በጓህላ ፣ በጠዳ በመገጭ ግድብ ዙሪያ እንዲሁም በጎንደር ከተማ እልህ አስጨራሽ ውጊያ እያካሄደ ነው። ዝርዝር መረጃውን በሰፊው እንመለስበታለን።
አብነት ሞላ
ዳግ/ቴዎ/5ኛ ኮር
👍7🔥3
በአዘዞ ኤርፓርት ከባድ ውጊያ በመኖሩ ከአዲስ አበባ ወደ አዘዞ አየር ማረፊያ ደርሶ የነበረ የአገዛዙ ሁለት አውሮፕላኖች ሳያርፍ ተገዶ ተመልሶ ሂዷል።
ድል ለመይሳው ልጆች💪
👍10
የአፋብኃ
ሰሜን አማራ ቀጠና
ሰኔ 22/2017ዓ.ም

ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር ፩ኛ ኮር ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ አራዊት ሠራዊቱ ጋር እልህ አስጨራሽ ውጊያን እያደረገ ይገኛል። የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ጥምር ጦር በከባድ መሣሪያ እየታገዘ ውጊያን ለማድረግ እዬሞከረ ነው። ነገር ግን ለእውነት የቆመው የፋኖ ሰራዊት ከይስሙላው የመንግስት ተብየው ሀይል ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ ጠላትን እያሺመደመደ ይገኛል።

ድል ለአማራው ፋኖ
👍3
የጎንደር የፋኖ ጦር ከጎንደር እስከ አለፋ ቀጠና የሸፈነ ውጊያ እያደረገ ሲሆን የአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጌምድር ክፍለጦር ጯሒት ቆላድባ ደልጊ ሰልፍ ሳይሆን ሰይፍ ነው ብሎ እየወቃው ይገኛል።
ድል ለጎንደሬው ፋኖ💪
🔥4
በማለዳ ቤተክርስቲያን ማገልገል የነበረባቸው አባቶች : በአደባባይ የብልፅግናን ፀረ እምነት ስርአት እያወደሰ ማየት በእጅጉ ያሳፍራል።

በምዕመን ከአባቶች ምን ይማሩ : ለዕምነት መሞትን ወይስ ለምድራዊ ፍላጎት(ለዚያውም ህሊናን ለሚያደማ : ርካሽ የፖለቲካ ጉዳይ) መሞት!?
👍7
ሰበር ዜና የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክፍለጦር 6ተሽከርካሪ፤1ድሽቃ በርካታ የቡድን መሳሪያ በመማረክ አምበሳሜ ከተማን ተቆጣጥሯል💪
👍4🔥1
በጎንደር በሁሉም አካባቢዎች ትንቅንቁ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በጎንደር ከተማ እና ዙሪያ እንዲሁም አምስት ወረዳዋችን ያካለለ አዉደዉጊያ እየተደረገ ሲሆን የጠላት ኃይል ከባድ ጉዳት አስተናግዷል።

በጧቱ ወደ ማክሰኝት ከተማ የገሰገሱት የቲዎድሮስ አናብስቶች በሰሩት አስደማሚ የከተማ ኦፕሬሽን ከ24 በላይ የሚሊሻ ሀይል ተደምስሶ ቀሪዉ ደግሞ አካላዊ ጉዳት አስተናግዷል።

በደቡባዊ ጎንደር ቀጠና አንበሳሜ በጀጌኖቹ እጅ ገብታለች።ጠላት መዉጫና መግቢያ በማጣቱ ከእነትጥቁ እስከወዲያኛው ተሸኝቷል።

አገዛዙ እና ጦሩ የሚይዘዉ የሚጨቤጠዉ ጠፍቷታል።

ዝርዝር መረጃዉን እናደርሳለን!!!
@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!!
👍8
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቲወድሮስ አምስተኛ ኮር እና ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አኔደኛ ኮር አስደማሚ ኦፕሬሽን በመስራት ድል ተጎናፅፈዋል።

ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር ዲሽቃን ጨምሮ ሌሎች የቡድን መሳሪያዎች መማረክ ችሏል።

ድሉ ቀጥሏል።

ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
መረጃዉን ከስር ከመሰረቱ ወደ እናንተ!!!!
👍1
➧➬ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ድል መቀዳጀቱ ታወቀ !!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ የዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር አብራኮች በጎንደር በተለያዩ ከተሞች በብልጽግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃዎችን ወስደዋል።


ክ/ጦሮች በተሰጣቸው የውጊያ ቀጠናም የጠላትን ሃይል አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል።

ጥቁር አንበሳ ክ/ጦርና የጎንደሬ በጋሻው አካል የሆነችው ነብዩ አሳምነው ብርጌድ በጋራ በመሆን በማክሰኝት ከተማ በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደከተማዋ በመግባት ድልን ደርበው አርፍደዋል።

የጎንደር ዙሪያ ወረዳ የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ የነሆነውን አበበ አስረስን ጨምሮ በርካታ የብልጽግና አገልጋዮች እስከ ወዲያኛው ተሸኝተዋል። የጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ደቦል ሻለቃ በጎንደር ከተማ በ4 ቦታዎች ላይ የቦንብ ፍንዳታዎችን አካሂደዋል።

አራዳ ሁለገብ አካባቢ፣ ጃንተከል ላይ ፣ ቀበሌ 16 በተለምዶ ስሙ ጋዜቦ በተባለው ቦታ ፣ ቀበሌ 18 ማራኪ ክፍለ ከተማ ላይ አመርቂ ስራዎች የተከወኑባቸው ናቸው።

4 የአድማ ብተና አባላት በጋዜቦው የቦንብ ፍንዳታ ሲገደሉ 4ቶች ደግሞ በጃንተከሉ የቦንብ ፍንዳታ ክፋኛ ቆስለዋል።

ማክሰኝት ላይ ከተገኙ ድሎች መካከል:-

የተማረኩ የጠላት ኃይል ብዛት 3 መከላከያ

የተማረከ ብሬን 2 እስከ ጥይቱ 30 ነብስ ወከፍ መሳሪያዎች ከነ ጥይቶቻቸው

የሞቱ የጠላት ኃይል መከላከያ፣ አድማ ብተናና ሚሊሻ ብዛት ከ50 በላይ እንደሆነ መረጃዎች ያስረዳሉ።

መብረቅ ክ/ጦር በደጎማ ከጠላት ፊት ለፊት የተፋለመች ሲሆን በቁርርጎና በታንከሩ ሰፍሮ ነበረውን የጠላት ኃይል ምሽጉ ድረስ በመግባት መሽጉን ጥሎ እንዲፈረጥጥ አድርገውታል።

በውጊያው ላይም የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል። ከዚህ በተጨማሪም ማክሰኝት ፣ ወራህላ፣ አርባያ ለሚገኘው የጠላት ኃይልም ድጋፍ እንዳይሰጥ ተደርጓል። በውጊያው ላይ ገብርየ አሰቻው በለሳ ብርጌድ ፤ ማዕበል በለሳ ብርጌድ ፤ አድዋ ጋሻው ብርጌድ፤ ሳይንቲስት ዶ/ር ኢ/ር ቅ/እጅጉ ቋላ ብርጌድ በውጊያው ላይ ተሳትፈዋል።

የመብረቅ ክ/ጦር አካል የሆነው የህቡዕ አደረጃጀት M-12 የተሰኘውን የቴክኖሎጅ ውጤት በመጠቀም በጎንደር ከተማ በተለያዩ ቦታዎች በፔኘሲ ፣ ቀበሌ18 ኮሌጅ ፣ ፣ በአዘዞ አየር ማረፊያ አካባቢ የቦንብ ፍንዳታዎችን ያካሄዱ ሲሆን በጠላት ላይም ጉዳት አድርሰዋል።

በኮማንዶ ሙላት የምትመራው ማዕበል በለሳ ብርጌድ ና የጎንደሬ በጋሻው አንድ አካል የሆነችው ዳግማዊ ቴዎድሮስ ብርጌድ በጥምረት በወረሃላ ከተማ በመግባት በጠላት ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

ፋናየ ውቤ ክ/ጦርና የዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ተዋርዋሪ ኃይል አዲስ ዘመን ላይ ሰፍሮ በሚገኘው ኃይል ላይ ጥቃት ከፍቷል።

ውጊያው በአዲስ ዘመን ሰንሰለታማ ተራሮች ላይ የተካሄደ ሲሆን የወገን ሃይል ዉጊያውን በበላይነት በመቆጣጠር የአዲስ ዘመን ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ከፍተኛ ቦታዎችን በፍጥነት በእጁ በማስገባት የጠላትን ኃይል አንገት ማስደፋት ተችሏል።

** የሞተ የጠላት ኃይል 2
** የቆሰለ 1
በአሁኑ ሰዓትም አስከሬን ለማንሳት አካባቢውን በድሽቃ እየደበደበም ይገኛል።
በአዲስ ዘመንና በይፋግ በአገዛዙ በሃይል ሊደረግ የነበረው ሰልፍ ሳይካሄድ ተበትኗል።

ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር በተሰጣት ቀጠና ውጊያዎችን ያካሄዱ ሲሆን በውጊያው ላይም የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ከመሆኑም በላይ ተማርኳል።

ፍልሚያዎች ከተካሄዱባቸው የውጊያ ቀጠናዎች መካከል ገደብየ ፣ አምባ ጊዮርጊስ ፤ ጠዳ ፣ ጎንደርና ወራህላ ከተሞች የሚጠቀሱ ናቸው።
በተለይ ጎንደር ከተማ ላይ በተደረገው መጠነ ሰፊ አውደ ውጊያ የጠላት 2 አውሮኘላኖች ከአዲስ አበባ አዘዞ አየር መረፊያ ሳያርፋ ተመለስው ወደመጡበት እንደሄዱ ለማወቅ ችለናል።

እስከ አሁኑ ደቂቃ ድረስ በረራ እንደቆመ ነው መረጃዎች የሚያስረዱን።

የዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር አብራክ የሆነው ታድሎ ብርሃን ክፍለ ጦር በጠዳ ብራህላ በመገጭ ግድብ ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን የአድማ ብተና አባል ላይ ተኩስ ከፍተውበት አርፍደዋል።

በተኩሱም ከ16 በላይ የአድማ ብተና አባላት ሲገደሉ 8 የሚሆኑት ደግሞ ቁስለኛ ሆነዋል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
ፋኖ መ/ር አብነት ሞላ➬ የዳግ/ቴዎ/5ኛ ኮር ህ/ግን/ኃላፊ
5👍1
ሰበር መረጃ
በደ/ጎንደር ደራ ወረዳ (01) አንድ ዲሽቃ (ሞተራይዝድ) የጦር መሳሪያን ጨምሮ ስድስት (06) መኪና እስከ ጭነቱ ከጠላት እቅፍ በክንዳችን መማረክ ችለናል።
አፋብኃ ሰሜን ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜ/ጀ/ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር የድሉ ባለቤት ነው።

የሁሉንም ግንባር ዝርዝር መረጃዎች ከ9:00 ሰዓት በኃላ እናደርሳለን።እጅግ ውጤታማ ኦፕሬሽን በሁለቱ ኮሮች እየተሰራም ይገኛል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
👍6
ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር ተጨማሪ ሁለት የቡድን መሳሪያ ገቢ አድርጓል።

ድሉ ይቀጥላል!!!!
🔥81
"በሰልፍ ለውጥ የሚመጣ ቢሆን ኖሮ የክልሉ መንግስት ከፊት ሁኖ ይመራው ነበር" ድሮ የብአዴን መፈክር

ዛሬ ግን ሰልፍ ለውጥ ያመጣል ብለው ከፊት ተሰላፊ ሆነዋል😂

እኛም እንላለን ሰልፍ ለውጥ አያመጣም፣ በሰይፍ አነጋግሩን ብላችሁ ሰይፍ እንድንጨብጥ ተገደናል። የምንነጋገረው በሰይፍ እንጂ በሰልፍ አይደለም።

አሁንም ለውጥ ያለው ሰይፍ ጋር እንጂ የሰልፍ መዝገብ ተዘግቷል።
6
የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ በፋኖ እጅ መግባቱ እየተገለፀ ነዉ።

ከፍተኛ ትንቅንቅ ከፍተኛ ድል
3🔥1