ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሠሜን አማራ ቀጠና (በላይ ዕዝ)
፩ኛ ኮር
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር
ሠኔ 18/2017ዓ.ም


ደራ ወረዳ አርብ ገበያ ከተማ፣ ገላውዴዎሥ ከተማ፣ ዙሪያ የገጠር ቀበሌዎች እና ልጫ ከተማ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ከአገዛዙ አራዊት ሠራዊት ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ እያደረገ ይገኛል። ይህ የአማራ ሠራዊት የትኛውንም ጠላት የማምበርከክ አቅማቸው ከአባታቸው ውባንተ አባተ የተወረሰ ነውና ድላቸው ሕብረታዊ ነፍጣቸው እንደሆነ በጽኑ አምነው ጠላትን ያደባያሉ። የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት በዚህ ሠዓት ከደብረ ታቦር፣ ከእሥቴ፣ ከአምበሣሜና ከአንዳ ቤት ተጨማሪ ኃይል እያከለ ነው የሚገኘው። 77ኛ ክፍለ ጦር በማሕደረ ማርያም እና መካነ ኢዬሡሥ በኩል ወደ ግንዳ ጠመም መሥመር ለመክበብ ሢሞክር ሌላኛው 74ኛ፣ 23ኛ፣ የ303ኛ ኮር ልዩ ኮማንዶ እና የኮሩ ቃኝና መሐንዲሥ ኃይል አለኝ ያለውን የቡድን መሣሪያ ከ2 ዙ-23፣ ሞርተርና መሠል መሣሪያዎችን እዬተጠቀመ ነው። ነገር ግን ለየትኛውም ፋሽሥታዊ አገዛዝ የማይመበረከኩት ጥበበኞቹ የጥበብ ልጆች ጠላታቸውን ሁሉ እያሣፈሩ ነው የሚገኘው።
የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር አሁን ላይ በቁጥርም በጥራትም ግዙፍ ተቋም ሆኗል። የውባንተ ጦር ባለበት ግምባር ሁሉ ጠላት እዬጠላቸውም ቢሆን አቅማቸውን አደናንቆ ነው የሚመለሰው የሚመሠክረው። ይህ ክፍለ ጦር ሕዝባዊነትን ተቀዳሚና እሥትንፋሡ ያደረገ ነው። አሥረግጠን መናገር የምንችለው በቀጠናው ላይ የውቤ ጦር ሥነ ልቦና፣ የመዋጋት አቅም እና የቡድን መሣሪያ አራዊት ሠራዊቱ መሥክሮላቸው ብቻ ሣይሆን የውባንተ ጦር ባለበት መሄድ እንደማይፈልጉ ነው የሚመሠክሩት። ዘረ ውባንተዎች መዳኛቸው ክንዳቸው፣ ማሸነፊያቸው አምሐራነታቸው፣ ወንድማማችነታቸው ከጽኑ አለት የበረታ ፍቅራቸውና በጥቅሉ ከአገዛዙ የጸጥታ ተቋም የተሻለ ሥልጡን ሠራዊት መያዛቸውና የልብ ትጥቅ ማሥታጠቃቸው የአሸናፊነታቸው ቁልፍ ምሥጢሮች ናቸው።

ይህ ሠራዊት በሕገ ደምብ የሚመራ፣ አድርግ አታድርግን የሚተገብር፣ በዘመናዊ የውጊያ ሥልት የታነጸ፣ ከሽምቅ ውጊያ ይልቅ መደበኛ ውጊያን የሚተገብር፣ ምሽጎችን የመሠባበር አቅም ያለውና በጥቅሉ የሕልውና ትግሉን በውል የተረዳ የውባንተ አባተ ዕውነተኛ የግብር ልጅ ነው።

ዝንተዓለም አምሐራ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር (፩ኛ ኮር) ሕዝብ ግንኙነት
ኢንጅነር ኃቅአለው ፀጋ

ጎንደር/አምሐራ/ኢትዮጵያ

ውጊያው እሥከ ምሽት 12:45 ቀጥሏል
3👍2🔥1
       
  የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው  የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  አደገኛውን ሰላይ በቁጥጥር ስር አዋለ ።

ከአገዛዙ ብልፅግና አመራሮች የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ አርበኛ ወርቁ ዘገየን ለመግደል ተልዕኮ ተሰጥቶት የነበረው አደገኛው እና ሆድ አዳሩ አድኖ ንጉሴ በሬ የተባለው ግለሰብ በጎንደሬ በጋሻው ንስሮች ታድኖ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ግለሰቡ ከአገዛዙ ብልፅግና  ኮማነድ ፖስት ሀላፊ ሌ/ኮ/ል ይሳቅ ሂሳ እና ከጎንደር ዙሪያ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ሀላፊ ሰለሞን እና ሌሎች አመራሮች በመጀመሪያ ዙር ከ400 ሺ ብር በላይ ክፍያ ተከፍሎት   ተልኮውን  ለመፈፀም ወደ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ታጋይ መስሎ የበግ ለምድ ለብሶ የገባው ገዳይ በቁጥጥር ስር ውላል።

ግለሰቡ  ከመጀመሪያው ዙር ክፍያ በተጨማሪ ግዳጁን ከፈፀመ በኃላ ደግሞ የቦታ ፣የገንዘብ  እንዲሁም ከሀገር እስከማስወጣት   ቃል ተገብቶለት  የነበረ ቢሆንም ጉሮሮውን ታንቆ ሳይበላው  በጎንደሬ በጋሻው  ንስሮች ቁጥጥር ስር ውሏል።

  አርበኛ ወርቁ  ዘገየ ጎንደሬ በጋሻው  ክፍለ ጦር የሚኮራበት ፣ጠላት ስሙን ሲሰማ በቁሙ የሚፍረከረክለት  ፣ የብረት አጥር ፣ የአማራ ኩራት ፣ የአገዛዙን  ባንዳዎችን  ከዳባት እስከ በለሳ ከደንቢያ እስከ አርማጭሆ ምድር ላይ እንደ ቄጤማ የዘረረ የወንዶች ቁና በክፍለ ጦሩ የጀግኖች የውሃ ልክ ስሙ በፋኖ ትግል በወርቅ የተመዘገበ  ነው።

ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦርን ጠላት  በምንም ፣ መቸም ቢሆን  ቀንም ሆነ  ለሊት  አይደለም አመራር እና   አባልን መግደል  ቀርቶ በቀጠናው አያልፍም  ምክንያቱም ንስሮቹ ሁሌም ዝግጁ ናቸው።

ስለዚህ ከአሁን በኃላ የፋኖ አመራሮችን እና ታጋዮችን ለመግደል ተልዕኮ እና ትዛዝ ተቀብለው የሚመጡ ሆድ አደሮች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ  የመጨረሻ ወንድማዊ መልዕክት እናስተላልፋለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ጎንደር ቀጠና ዳግማዊ ቴዎድሮስ (5ኛ) ኮር የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ አርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ )
👍2🔥1
አፋብኃ ሰሜን ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ

ሰኔ 18/2017 ዓ.ም
አገዛዙ በተደጋጋሚ ወደ ፋኖ አፈሙዛቸውን እንዲያዞሩና የርስ በርስ ግጭት እንዲፈጥሩ ግፊት ሲያደርግባቸው የነበሩ የታጠቁ ኃይሎች በምዕ/ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ መቃ የተሰኘ ልዩ ቦታ ላይ የአገዛዙ ሰራዊትን ደምስሰውታል።ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት በአገዛዙ የአድማ ብተና ቡድን ላይ ማድረስ የቻሉት የቅማንት ማህበረሰብ ተወላጆች በአገዛዙ ተወጥኖ የነበረውን የጥፋት ድግስ አምክነውታል።
በቀጠናው የሚገኘው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ሰሜን ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሰራዊት ወንድማዊ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የህዝባችን መጻኢ ዕጣ ፈንታ በምናደርገው የመርሃዊ አንድነት ትግል የሚበየን መሆኑ በመታመኑ አገዛዙ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ክሽፈት እንዲደርስበት ሁኗል።

ለበቀል ወደ ቀጠናው የገባው የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በርካታ ንፁሃን የቅማንት አማራ ነዋሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ረሽኗል።የመኖሪያ ቤትና ንብረትም አውድሟል።

በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ ያነጣጠረ ጭፍጨፋን አፋብኃ ጎንደር ቀጠና እያወገዘ ቀጣይ በአንድነት በኦህዴድ ብልፅግና ሰራዊት ላይ ወታደራዊ የአፀፋ ርምጃ ይወሰዳል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ሰሜን ቀጠና በላይ ዕዝ
👍4🔥1
የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ፍ/ቤት ቀርበዋል።

አውሎግሶን አንድነት-Awulogson Andinet፣
ሰኔ 18/2017 ፣ አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

በተለያዩ መዝገቦች የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ሰኔ 18/2017 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።

በእለቱ ፍ/ቤት ከቀረቡት መካከልም ፦

(1) በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ፣
(2) በእነ ሀብታሙ መሀመድ መዝገብ የተካተቱና
(3) ኃይለ ማርቆስ ኃይልዬ በልሁ የተባሉ ተከሳሾች ይገኙበታል።

(1) በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ፦

ተከሳሾች ከቂሊንጦ ማ/ቤት በችሎት የተገኙ ሲሆን መዝገቡ የተቀጠረው ፦

1. የዐቃቤ ሕግን ቀሪ ምስክሮችን ለመስማትና
2. በወ/መ/ስ/ስ ሕግ ቁጥር 143 (2) መሰረት ከመከላከያ በቦርድ ወጥቷል ከተባለው 20ኛ ቃቤ ሕግ ምስክር ምትክ ሌላ ምስክር እንድናሰማ ይፈቀድልን በሚል ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገውን ክርክር መርምሮ ብይን ለመስጠት በሚል ነበር።

በዚህም መሰረት ምስክሮችን በተመለከተ ዐቃቤ ሕግ ከሰኔ 10/2017 ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት "ይቀርባሉ ፣ መንገድ ላይ ናቸው " ሲል የሰነበተ ቢሆንም ዛሬም ተመሳሳይ ምክንያቱም ያቱም ት በመስጠት ለ6ተኛ ጊዜ እንዲቀጠር አድርጓል።

በተጨማሪም ተጨማሪ ምስክርን በተመለከተም ችሎት ክርክሩን ከመረመረ በኋላ ተጨማሪ የተባለው ምስክር ቀርቦ እንዲመሰክር ሲሉ በሙሉ ድምፅ መወሰናቸውን በመግለጽ ስድስቱም ምስክሮች ቀርበው ይመስክሩ በማለት በይደር ለሰኔ 19/2017 ቀጠሮ ይዟል።

(2) በእነ ሀብታሙ መሀመድ መዝገብ፦

በዚህ የሽብር ክስ መዝገብ የተካተቱ 4 ሰዎች ማለትም ፦

1) ሀብታሙ መሀመድ (ጋዜጠኛ)
2) ማቶሳላ መኮንን፣
3) ዳንኤል ደመቀ እና
4) በፍቃዱ ጅንኑ የተባሉ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች በችሎት ተገኝተዋል።

መዝገቡ የተቀጠረው ጉዳዩን እየተመለከተው የሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ እና በተከሳሾች መካከል የሰነድ ማስረጃን በተመለከተ የተደረገውን ክርክር መርምሮ ብይን ለመስጠት በሚል ነበር።

ይሁን እንጁ ተከሳሾች ጠበቃችን በእለቱ አልተገኘልንም በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ፍ/ቤቱም የሰነድ ማስረጃን በተመለከተ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገውን ክርክር መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 27/2017 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

(3) ኃይለ ማርቆስ ኃይልዬ በልሁ ፦

ተከሳሽ ኃይለ ማርቆስ ለግል ስራ ጉዳይ ከደብረ ብርሃን ወደ አዲስ አበባ በመጣበት ሚያዝያ 20/2017 በጎፋ ማርያም መብራት ኃይል አካባቢ ከዘመድ ቤት በነበረበት ከምሽቱ 1 ሰዓት ተኩል ነበር የተያሊዘው።

ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ አፈና የፈፀሙትም ሶስት የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና አንድ ሲቪል የለበሰ የደህንነት አካላት ናቸው።

ከሰኔ 20/2017 ጀምሮ እስከ ሰኔ 12/2017 ድረስ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሜክሲኮ ከቆዬ በኋላ መደበኛ የሽብር ክስ መመስረቱን ተከትሎ ነው ወደ ቂሊንጦ ማ/ቤት የወረደው።

"ፋኖ ነህ ፣ በፋኖ ደጋፊ ነህ" በሚል ክስ ነተመሰረተበት ኃይለ ማርቆስ ሰኔ 18/2017 ፍ/ቤት የቀረበ ሲሆን ክሱ ሳይሰጠውና ሳይነበብለት ለሰኔ 23/2017 ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዞለታል።

(4) በተመሳሳይ ከሰሜን ሸዋ ዞን ሞረት እና ጅሩ ወረዳ ለገበያ ጉዳይ ብለው ወደ አዲስ አበባ በመጡበት የታፈኑና በመጨረሻም በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ግዛቸው ገ/ማርያም የተባሉ የእድሜ ባለፀጋም ሰኔ 18/2017 በነበረው ችሎት ቀርበው ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጣቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ

አሳዛኝ ዜና!

ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ራያ ቆቦ ኩቢ ቀረንሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን በመድፍ አወደመ::

ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለጦር ቁልፍ ይዞታዎች ናቸው ያላቸውን አካባቢዎች ለማስለቀቅና ለመቆጣጠር ጥረት አድርጎ ያልተሳካለት ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ዛሬ ራያ ቆቦ ጮቢ በር በተጠመደ መድፍ ዛሬ ሰኔ 19/2017 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ የገጠር ታዳጊ ከተሞችን ኢላማ ያደረገ ድብደባ እየፈፀመ ያለ ሲሆን ራያ ቆቦ ኩቢ ቀረንሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ ለሙሉ አውድሟል::

ንፁሃንን ኢላማ ያደረገው የመድፍ ድብደባ ከቤተ ክርስቲያኑ በተጨማሪ ትናትና ሰኔ 18/2017 ዓ.ም አንድ ታዳጊ ህፃን በዲሽቃ በከባድ ሁኔታ አቁስሎ የቤት እንስሳቶችንና ንብረትም አውድሟል:: ንፁሃን ህዝብን ኢላማ ያደረገ የመድፍ ድብደባው አሁንም ቀጥሎ በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እያደረሰ ይገኛል::

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ
ሰኔ 19/2017 ዓ.ም
ሰበር ዜና

" የአፋብኋ"ጎንደር ቀጠና
🎯 የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር:- ሰሜን ብርቅዬ ክፍለጦር

መረባ መሽጎ የነበረውን አድማ ብተና እንዲሁም ሰላም አስከባሪ ብሎ ራሱን የሚጠራው የአብይ ወንበር አስጠባቂ የሚሊሻ ስብስብ ዛሬ ሀሙስ በ19/10/2017 ዓ"ም በጀግናው የሰሜን ብርቅዬ ክፍለጦር አባላት ከበባ በማድረግ እና ከምሽግ በማስወጣት ገርፈውታል።

🥏በቁጥር 10 = የሞተ
8= የቆሰለ
30 =የተማረከ እና ከ50 በላይ የነብስ ወከፍ መሳሪያ ከጠላት በመቀበል አኩሪ ጀብድ ተፈፅሟል ።

በመጨረሻም የአብይ ወንበር አስጠባቂ ከነበረው ምሽግ ተጠራርጎ የሞተውን እና ቁስለኛውን አንጠባጥቦ ወደ ወቅን እንዲገባ ተገዷል!

ድል ለአማራ ፋኖ ሞት ለብልፅግና
አንድነት ሃይል ነው

"አፋብኋ" ጎንደር ቀጠና
🎯ራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር

#follow #like #share
👍5
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሠሜን አማራ ቀጠና(በላይ ዕዝ)
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር
ጣና ገላውዴዎሥ
ሠኔ 18/2017ዓ.ም

ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ከልጫ እሥከ ገላውዴዎሥና አርብ ገበያ ባደረገው ውጊያ ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ተወርዋሪ ክፍለ ጦርን ለማገዝ ከገላውዴዎሥ ቴሌ እሥከ ሽሜ ማርያምና ጎኃ ድረሥ አውደ ውጊያ ፈጽሟል። ሁሉቱ ክፍለ ጦሮችም በቅንጅት መልካም ግዳጅን ፈጽመዋል። የአገዛዙ ዕድሜ አርዛሚ ወታደሮች ኣላማውን ያልጠበቀ ከባድ መሣሪያ ተኩሥን የፈጸሙት ካደረባቸው ፍርሃትና መርበትበት የመነጨ እንደሆነ በሚገባ ዓይተናል።

፩ አምሐራ
ዝንተዓለም አምሐራ Forever Amhara

፩ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
ኃቅ ዘ ዮቶር
1
ሰበር_ዜና_አሁን_ሸዋ_ደራ ‼️

አምስት መኪና የብልጽግና ሰራዊት በሸዋ ደራ ፋኖ በፍቃዱ በላይ ክፍለጦር በተደረገበት ደፈጣ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል። በአሁኑ ሰአት የብልጽግና ሰራዊት ከጀማ በረሀ ወደ ሰለልኩላ እየፈረጠጠ ይገኛል ።
👍42
ከፎገራ እስቴ ሰፊ ቀጠና የሸፈነ ውጊያ እየተደረገ ነው።
አፋብኃ ሰሜን ቀጠና በላይ ዕዝ

ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር

ሰኔ 20/2017ዓ.ም
ከአፄ ፋሲል ቴዎድሮስ ብርጌድ እሥከ ጉናው እስቴ ዴንሳ ብርጌድ
ከፎገራ እስከ እስቴ ከንጋት ጀምሮ ፍተኛ አውደ ውጊያ እየተደረገ ነው።

ጠላት ከአንዱ የአማራ ቀጠና ወደ ሌላው ሀይል አቀናንሶ ለመዋጋት ማቀዱ ስለታወቀ አስፈላጊውን ማጥቃት በየ ቀጠናው ማድረግና አሳስቶ የሚተወውን ኃይል የመደምሰስ ንቅኔቄ በበላይ ዕዝ ተግባራዊ እየቸደረገ ነው።

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጠላት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን የእንቅስቃሴ ገደብ መጣል ወታደራዊ አማራጭ እንዲሰራ በአርበኛ ሀብቴ ወልዴና በአርበኛ ሳሙኤል ባለዕድል ትዕዛዝ ተሰቷል።
በሰፊ የውጊያ መስመሮች ፍልሚያ እየተደረገ ሲሆን የውጊያ ትስስር በማድረግ አድማሱን በማስፋት ውጤታማ ምት ጠላት ላይ ማድረስ እንደሚቻልም ይታመናል።

የደ/ጎንደር ቀጠና ወሳኝ መጋቢ መስመር በመሆኑ ስትራቴጂካዊ ወታደራዊ ጠቀሜታውን በውል የተረዱት የአርበኛ ውባንተ ልጆች ብርቱ ተጋድሎ እያደረጉ ይገኛሉ።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
2🔥1
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት "የጤና ባለሙያዎችን በማዋከብ የአገሪቱን የጤና ችግር መፍታት አይችሉም" ሲል  ሂውማን ራይትስ ዋች ገለፀ።

የጤና ባለሙያዎች የሥራ ማቆም አድማ ከመጥራታቸው በፊት ቅሬታቸውን ሲያሰሙ
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት "የጤና ባለሙያዎች ማኅበርን በማገድ፣ ባለሙያዎችን በማሰር እና በማዋከብ አሳሳቢ የሆነውን የአገሪቱን የጤና ችግር መፍታት እንደማይችሉ" የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪው ሂውማን ራይትስ ዋች ገልጿል።

ሂውማን ራይትስ ዋች የጤና ባለሙያዎቹ ያነሷቸውን "ተገቢ ጥያቄዎች ትርጉም ባለው ውይይት መፈታት አለባቸው" ሲሉ የተቋሙ የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ላቲሺያ ባደርን ዋቢ አድርጎ ረቡዕ፣ ሰኔ 18/2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስፍሯል።

የሕክምና ባለሙያዎቹ ከተመጣጣኝ ደመወዝ፣ ጥቅማጥቅም፣ የሙያ ዕድገት ዕድሎች እንዲሁም ከምቹ የሥራ ቦታ እና የሥራ ቦታ ነጻነት ጋር የተያያዙ ባለ 12 ነጥብ ጥያቄዎችን ለጤና ሚኒስትር ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም. ማቅረባቸው ይታወሳል። ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ ባለመሰጠቱም ከግንቦት 10/2017 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የሥራ ማቆም አድማ አድርገው እንደነበር የሚታወስ ነው።

አድማውን ተከትሎ መንግሥት በጤና ባለሙያዎቹ ላይ እስር፣ ማዋከብ፣ የሥራ የማባረር ዛቻዎች፣ አዲስ የሥራ ቅጥር ማውጣት እና ሌሎች ጫናዎች መድረሱን ተቋሙ በመግለጫው አስፍሯል።

ከሥራ ማቆም አድማ ጋር ተያይዞም አመራሩ ታስረውበት የነበረው የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ሰኔ 5/ 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ታግዷል። የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር እገዳን በአስቸኳይ እንዲያነሱ ሂውማን ራይትስ ዋች በዚህ መግለጫው ባለሥልጣናቱን የጠየቀ ሲሆን፤ አክሎም "የጤና ባለሙያዎች ቅሬታዎችን በአግባቡ ይፍቱ" ብሏል።

በአገሪቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ በመጠየቃቸው ባለሥልጣናቱ ለእስር እንደዳረጓቸውም ጠቅሷል።

የሥራ ማቆም አድማው ከተጀመረበት ከግንቦት 5/2017 ዓ.ም. ጀምሮ 148 የጤና ባለሙያዎች ታስረው እንደነበር በበይነ መረብ ላይ ያለ የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ መረጃ እንደረሰው ሂውማን ራይትስ ዋች ገልጾ ሆኖም አኃዙን አላጣራሁም ብሏል።

ፌደራል ፖሊስ በበኩሉ 47 የጤና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቆ ነበር።
"ከግንቦት ወር ጀምሮ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የጤና ባለሙያዎች ከተመጣጣኝ ደመወዝ፣ ጥቅማ ጥቅም እና ከምቹ የሥራ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ከመመለስ ይልቅ አፋኝ ዘዴዎችን ተጠቅመዋል" ሲሉ ላቲሺያ ወቅሰዋል።

አክለውም "መንግሥት የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ላይ የጣለውን እገዳ በአስቸኳይ እንዲያነሳ እንዲሁም በጤና ባለሙያዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ወከባ ሊያቆም ይገባል" ብለዋል።

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የታገደው "ጠቅላላ ጉባኤ አላካሄዳችሁም" እንዲሁም የፋይናንስ ሪፖርት አላቀረባችሁም በሚል እንደሆነ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ዮናታን ዳኜ ከዚህ ቀደም ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ ማኅበራቸው "የአገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው እና መመሪያዎችን በመከተል" እንደሚንቀሳቀሱ የገለጹ ሲሆን፣ ይህ እግድ ከጤና ባለሙያዎች እንቅስቃሴ ጋር የተገናኘ ነው" ብለው መናገራቸው ተቋሙ ሚዲያዎችን አጣቅሶ በዚህ መግለጫው አካቷል።

የጤና ባለሙያዎቹን ጥያቄዎች ከፊት ሆኖ ሲያንቀሳቅስ የነበረው ማኅበሩ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አዘጋጅነት ከመንግሥት ጋር በተደረገ ውይይት ተሳትፎ የነበረ ቢሆንም ለችግሮቹ እልባት መስጠት እንዳልተቻለም ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ የሕብረሰብ ጤና አጠባባቅ ወጪ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) አንጻር ሲሰላ 0.7 በመቶ ሲሆን፣ ይህም በዓለም አቀፍ መመዘኛ ከተቀመጠው እጅጉን ያነሰ መሆኑን ከሦስት ዓመታት በፊት የወጣውን የዓለም ጤና ድርጅትን መረጃ ዋቢ አድርጎ ተቋሙ በዚህ መግለጫው አስፍሯል። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት የጤና አጠባበቅ ወጪያቸው በአማካይ 1.2 በመቶ መሆኑም በዚሁ መግለጫ ተጠቅሷል።

የጤና መድን ሽፋን አለመዘርጋት፣ ከሥራ ጋር በተያያዙ አደጋዎች በቂ ካሳ አለማግኘት፣ የደመወዝ መዘግየት እና ሌሎች መሠረታዊ ጉዳዮች ሲንከባለሉ የቆዩ ነገሮች መሆናቸውን የጤና ባለሙያዎቹ ይጠቅሳሉ።

የጤና ባለሙያዎቹ የሕብረተሰቡን ጤናን በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና ቢጫወቱም የጤና ባለሙያዎች በአማካይ የሚያገኙት በወር 80 ዶላር ሲሆን ነርሶች፣ የጤና መኮንኖች እና ሌሎች ባለሙያዎች ከዚህ ያነሰ እንደሚከፈላቸው አምነስቲ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል። አምነስቲ የኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ለማጠናከር እና በሰላማዊ ተቃውሞ ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን መብት ለማስጠበቅ የልማት አጋሮች የሁለትዮሽ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አድርጓል።

"ባለሥልጣናት ከዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ግዴታዎቻቸው ጎን ለጎን ከፍተኛውን ሃብት እንደ ጤና ላሉ ወሳኝ የሕዝብ አገልግሎቶች መመደባቸውን ለማረጋገጥ አስቸኳይ እርምጃዎችን መውሰድ አላባቸው" ሲል በወቅቱ ባወጣው መግለጫ አጽንኦት ሰጥቶ ነበር።
ይህንን እልባት ለመስጠት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሳምንት በፊት ከተመረጡ የጤና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጤና ባለሙያዎቹ ያነሷቸው የደመወዝ ጭማሪ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ተገቢነት ቢኖረውም "የፖለቲካ ኪሳራ በገጠማቸው እና ሐኪም መሳይ ጋወን ለባሽ" ባሏቸው ሰዎች ተጠልፏል ብለዋል።


'የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ' በሚል ማዕቀፍ የሚታወቁት ባለሙያዎቹ ሲያደርጉት የነበረው እንቅስቃሴ "የመጀመሪያ ምዕራፍ" እንቅስቃሴያቸው የተሳካ እንደነበር ለቢቢሲ የተናገሩ አንድ የንቅናቄው አስተባባሪ፤ ለጤና ሚኒስቴር ያቀረቧቸው አራት ቅድመ ሁኔታዎች በከፊል በመሟላታቸው እና ለማኅበረሰቡ ሲሉ ወደ ሥራ መመለሳቸውን ገልፀዋል።
አንዳንድ የጤና ተቋማት ግን የጤና ባለሙያዎች ወደ ሥራ "አትመለሱም" በሚል ክልከላ እንደተረገባቸውም አስታውቀዋል።

ዘገባው የቢቢሲ ነው
የእሁድ አስገዳጅ ሰልፍ ውጥን ከባድ ዋጋ ያስከፍላል።

በተደጋጋሚ አስገዳጅ ሰልፍ ሞክሮ ያከሸፍንበት አገዛዙ ለሰኔ 22/2017 ዓ.ም እሁድ ለርካሽ ፖለቲካ ዓላማ ሰልፍ ለማስወጣት በርካታ ከተሞች ላይ ህዝቡን ከወዲሁ እያዋከበ መሆኑ ተደርሶበታል።
ህዝባችንም ድረሱልን ብሏል ።
የእሁዱን ሰልፍ ለማስተባበር ህዝብ እያዋከበ በሚገኝ፣እንዲሁም የፖለቲካ፣የሚዲያ፣የወታደራዊ፣የገንዘብና የመረጃ ትብብር ወዶም ሆነ ተገዶ የምታደግ ሁሉ የጥቃታችን ኢላማ ትሆናለህ።ፈጥነው ከሂደቱ የሚወጡ ብቻ ምህረት የምናደርግ ሲሆን የጠላት ሰልፍ መሳተፍም ሆነ ማስተባበር ከባድ አደጋ በራስ ላይ መጋበዝ መሆኑን እናስጠነቅቃለን።

የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ችላ ብሎ በተላለፈ አካል ላይ በየትኛውም ቦታ በየትኛውም ቀንና ሰዓት ከወትሮው ጠንከር ያለ የማያዳግም ርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን።አፋብኃ ሰሜን ቀጠና በላይ ዕዝ !

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ሰ/ቀጠና በላይ ዕዝ
2👍1