ዓለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.38K subscribers
4.13K photos
329 videos
17 files
2.15K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሰበር ዜና

የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) የምስራቅ አማራ ኮር1 ባለሽርጡ ክፍለጦር እና ኮር2 ታጠቅ ክፍለጦር አሃዶች በጋራ በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ አንጦ ጨፌ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ፡፡

ዛሬ ጥር 27/2017 ዓ.ም በተደረገው ተጋድሎ የባለሽርጡ ክፍለጦር ሜካናይዝድ ክፍል 100% ኢላማዉን የጠበቀ የሞርታር ጥቃት በመፈፀም  የፋሽቱን ስርዓት ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት የብልፅግና ሆድ አደር ካድሬ እንዲሁም ሆድ አደር ሚሊሻ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ሰርቷል::

በዚህም የዙፋን ጠባቂው ሰራዊት መርሳ ከተማ ሆድ አደር አድማ ብተና እና ሚሊሻዎችን ለተሻለ ግዳጅ በሚል ጫካ ላይ ስብሰባ ጠርቶ የተሳሳተ ቅስቀሳ ፅንፈኛው ስለተዳከመ የቀጠናውን ሰላም መመለስና አካባቢውን ተረከቡ በሚል በመድረክ ሲደሰኩር የባለሽርጡ ሜካናይዝ ክፍል ወደ ስብሰባው ባስወነጨፈው የሞርተር ጥቃት የስርዐቱን ወንበር ጠባቂ ሰራዊት ሆድ አደር ሚሊሻዎችና አድማ ብተና ሀይልን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ያሰቡትንም መድረክ ሳያሳኩ ስብሰባውን የበተኑት ሲሆን የሜካናይዝድ አጃቢ ሻለቃ በአንጦ ጨፌ የመጣውን ጨፍጫፊ ሀይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወደ መጣበት እንዲመለስ አድርጎታል::   

የታጠቅ ክፍለጦር አሃዶች ዙፋን አቦ ቀበሌ በመነሳት ከላይ ወደታች አጋምሳ እና ወረላሎን ማለትም ከመርሳ ከተማ ደቡባዊዩን አቅጣጫ አድማ ብተናና ሚሊሻ የሰፈረበትን ምሺግ በመስበር በርካታ ጠላት ሲደመስሱና ሲያቆስሉ ጠላት ነፍስ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል::

የባለሽርጡን እና ታጠቅን በትር መቋቋም ያቃተዉ የባንዳ ጥርቅም የግለሰብን ሀብትና ንብረት እየዘረፈ፣ እያወደመና የዘወትር ልምዱ የሆነዉን ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ ሞርታር ጥቃት በመፈፀም ሶስት ገበሬዎችን ሲገድል በተመሳሳይ ከግለሰብ ቤት ላይ በተወረወረ ሞርተር ሁለት እናቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን እነዚህ እናቶች አሁን በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡

በቀጣይም መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ)
ጥር 27/2017 ዓ.ም
👍3
በእናረጅ እናውጋ ወረዳ ጎልውቅማ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎል የሚባል ቦታ ተወልዶ ያደገው አስራቱ ሙሉጌታ ቢሸው ለአገዛዙ ሀይል ቅጥረኛ አገልጋይ የነበረ ሲሆን በሶማ ብርጌድ ወደማይቀረው ተሸኝቷል ።ባንዳን ምንጠራው ይቀጥላል ።ቢዛሞ
👍1
ሰበር ዜና!

የአገዛዙን ዙፋን ጠባቂ ሚሊሻ የወገኖቹ ግፍ ያንገፈገፈው ሚሊሻ በጥይት ነቅሷቸው ወደ ነበልባል ተቀላቀለ።

በትናትናው በዕለተ መድሓኒያለም በቀን 27/5/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:35 ገደማ አንድ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ አገዛዙ በግዳጅ አፍሶ አሰልጥኖ ያስታጠቀው ሚሊሻ በቆይታው የአገዛዙ አስከፊነት አንገፍግፎት ከአማራ አብራክ የወጡት የሚሊሻዎቹ በገዛ ወገኖቻቸው የሚያደርጉት ዘረፋ ፣ድብደባ፣ሴት ደፈራው አልቋቋም ብሎ አገዛዙን ትቶ ለመውጣት ቀን ሲያመቻች ቆይቶ ትናንት በተጠቀሰው ሰዓትና ቀን በአረርቲ ከተማ አረርቲ መለስተኛ ሆስፒታል ፊት ለፊት ባለ መጠጥ ቤት የአገዛዙ ሚሊሾች በመጠጥ ቤቱ የሚጠቀሙ ግለሰቦችን በግዳጅ ጋብዙን እያሉ ሲጋበዙ ውለው ሂሊናቸውን እስኪስቱ ጠጥተው የጋበዙዋቸውን ግለሰቦች በጋበዙ ሲደበድቡ የተረፋቸውን ገንዘብ በግዳጅ ሲቀበሉ አላስችል ያለው ጀግናው ሚሊሻ እንቢ በወገኔ ግፍ በማለት የያዘውን ክላሽ ከትከሻው አውርዶ መጠበቂያ ፈቶ ካታውን ፈልቆ ጥይቱን አቀባበለ ጀግናው ቆርጧል ዛሬ የወንድሞቼን ደም እበቀላለሁ ከራሱ ሙግት ገጠመ የጫካዎቹ ወንድሞቹ ናፈቁት ሌቦቹን ወሰነባቸው ጣቱን ከምላጭ አገናኘው የመጀመሪያውን ጥይት ከዚህ ቀደም የአርሶ አደር ግመል ፣እህል ከጎተራ በመስረቅ ከተወለደበት አካባቢ በእድር በተባረረው   የ አገዛዙ ሚሊሻ ላይ ሌባው ደረጀ ደስታ እሸቴ ማህል ግንባሩ ላይ አረፈች ። ደረጀ ወዲያው ምድርን ተሠናበት።

ጀግናው ደግሞ የክላሹን ምላጭ አባው ጥላሁን እሸቴ ላይ ነካካው አባው እና ደረጀ የወንድም አማች ልጆች በጀግናው ጥይት በጥቁር አስፓልት በቀይ ጥይት ተነድለው ወደቁ።

ጀግናው አሁንም በሌላኛው ሚሊሻ ላይ ተስፋዬ ሠለሞን ለይ ተኩሶ ከአቆሰለው በኋላ ወደ ወንድሞቹ አቅጣጫውን አዙሮ እዬተመናሸረ ብልፅግናን ትቶ ወደ አማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለ ጦር በቆፍጣናው በወንዶቹ ቁና ሃምሳ አለቃ ፍቃዱ ጥላሁን የሚመራውን ነበልባል ብርጌድን ተቀላቀለ።

ሟች ሚሊሻ ደረጀ ደስታ ከዚህ ቀደም በአረርቲ ማርያም ቤተክርስታያን ግቢ አንድ ዳቆን ዮሐንስ (አጥላው) ተሾመ ተፈራን በግፍ የገደለ ወንጀለኛም ነበር።

በአገዛዙ ወንበር ጠባቂዎች ዛሬ መተማመን ጠፍቶ ትርምስ ነግሷል ሚሊሻው እርስ በርሱ አይጥና ድመት ሆኗል።

የወድም አማቾቹ ልጆች በአንድ ቀን ተቀብረዋል ።ሚሊሻ ተስፋዬ ሰለሞንም በአረርቲ ሆስፒታል በሞት አፋፍ ላይ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል።

ነበልባልም ለሟቾች እንዲይ ሲል በግጥም ከዚህ ምድር እስከወዲያኛው ሸኝቷቸዋል።

=እንግዲህ እንዲህ ነው የባንዳ ውለታ፣
  አይ አባው ጥላሁን ደረጀ ደስታ፤

በጥይት ተቆልተው ሲኦል ስትጠብቅ በሮቿን ከፋፍታ፣
በጥይት ተቆልተው ተከታትለው ሄዱ ከማይቀረው ቦታ፤

እንግዲህ እንዲህ ነው የባንዳ ውለታ፣
አይ አባው ጥላሁን ደረጀ ደስታ፤
ሲኦል ስትጠብቅ በሮቿን ከፋፍታ፣
በጥይት ተቆልተው ተከታትለው ሄዱ ከማይቀረው ቦታ።

እምን ልግባ እያለ በሃሣብ ሲዋትት
አለማየሁ በላው በቀይ እርሳስ ጥይት፣
በጥይት በሳስቶህ ቁስለኛ ከምትሆን
ብትሞት ይሻል ነበር ተስፋዬ ሰለሞን፣

ዱላ ቆርጦ አይቀጣም እግዚኣብሔር ሲጣላ፣
የባንዳ ወላጆች ደስታና ጥላ፣
ጥላሁን ደስታ ወንድም አማቾቹ
አቤት ልጆቻቸው ለጥይት ሲመቹ፣

የአባው የደረጀ ዘመድም ወዳጆች
መልዕክት አስተላልፋ ለቀሩት ባንዳዎች።

ድል ለአማራ ፋኖ!!!
ነፃነታችንን በክንዳችን!!!
አዲስ ትውልድ፣
አዲስ ተስፋ።

መረጃው/ የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክ/ጦር የነበልባል ብርጌድ ፋኖ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ነው።

ፋኖ መ/ር አጥናፋ አባተ የነበልባል ብርጌድ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሃላፊ

   ጥር 28/5/2017ዓ.ም
           ነበልባሎች።
👍3
11(አስራ አንድ) የአገዛዙ ዘራፌ ሀይል ተቀንድሸዋል!!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ከህዝባዊ ውይይት ጎን ለጎን ውጊያዎችን እያደረገ ይገኛል።

በሸበል በረንታ የሚገኜው ሽፈረው ገርበው ብርጌድ ጥር 28/2017ዓም በሸበል በረንታ ወንየ ቀበሌ ዘሳ ጎጥ እንዲሁም የዕዱሀ ከተማ በመግባት ከባድ ውጊያ ሲያካሂድ ውሏል።

በሸበል በረንታ ወይንየ የመጀመረያ ደረጃ ት/ቤት በአካባቢው ማህበረሰብ እየተሰበሰበ የነበረ ጤፍ እህልን ዘርፎ ለመውሰድ በመጣው የብርሀኑ ጁላ ዘራፊ ሀይል ላይ ሽፈረው ገርበው ብርጌድ በሸበል በረንታ ወረዳ ወይንየ ቀበሌ ባካሄደው ከባድ ውጊያ 11 የአገዛዙ ዘራፊ ሀይልን ደምስሷል።

3 የአገዛዙ ዘራፊ ሀይል ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ በማድረግ በሸበል በረንታ የዕዱሀ የመጀመረያ ሆሲፒታል መግባታቸው ተረጋግጦል። ሁለት ኤፍኤሳር እና አንድ ካሶኒ የጫነ የጠላት ሀይል ወይንየ ቀበሌ ላይ በሽፈረው ገርበው ልጆች ከጥቅም ውጭ ተደረጓል።

@ፋኖ ይበልጣል ጌቴ
ከአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት
👍2
ሰበር ዜና | የባህርዳሩ አነጋጋሪ ክስተት | በራሱ አባል ምላጭ የሳበው ሚኒሻ | ወሎ ፍጥጫው አይሏል
👍2
ሰበር ዜና | የባህርዳሩ አነጋጋሪ ክስተት | በራሱ አባል ምላጭ የሳበው ሚኒሻ | ወሎ ፍጥጫው አይሏል
👍2
ሰበር ዜና!

ከ10,000(አስር ሽህ) በላይ አማራ የሆኑ ወታደሮች በአብይ አህመድ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ታስረዋል። በርካቶችም በየቀኑ እየተረሸኑ ነው።

ከ10,000(አስር ሽህ) የሚበልጡ የአማራ ልጅ የሆኑ ወታደሮች በአማራ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ እንዲፈጽሙ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ግዳጅ ቀጠና ላይ የነበሩ እና በሌሎች የሐገሪቱ አካባቢዎች የነበሩ ሲሆኑ ለአማራ ህዝብ እና ለፋኖ ከፍተኛ አቅም መፍጠር ተባባሪ ናችሁ የሚል ምክንያት የተነሳባቸው ሲሆን ከእስረኞቹ መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩት በየ ቀኑ እየተረሸኑ ይገኛል።

የአብይ አህመድ ስርዓት ትክክለኛ አማራን ለማጥፋት የተቋቋመ መሆኑን ባለመገንዘብ ጠመንጃ ተሽከመው የአብይን ስርዓት ሲያስቀጥሉ የነበሩ እና ከእግረኛ እሰከ ከ ብርጌዳል ጀኔራል ድረስ ማዕረግ ያላቸው የአማራ ልጆች የአብይ አህመድ ቀጥተኛ ሰለባ መሆናቸው ሌሎች በመከላከያ ውስጥ ላሉ የአማራ ልጆች ሁነኛ ማስተማሪያ ነው።

በመሆኑም አማራ ሆናችሁ በመናጆ ሳንቲም ተታላችሁ መከላከያ ውስጥ ያላችሁ የአማራ ልጆች በሰዓቱ ፋኖን ከተቀላቀሉ ወንድሞቻችን ተምራችሁ በፍጥነት ፋኖን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን ።

አብይ አህመድ ከህወሓት ጋር ጦርነት በገጠመ ጊዜ በርካታ የትግራይ ተወላጅ ወታደራዊ መኮንኖችን አስሮ ሲያሰቃያቸው እንደነበር ይታወቃል ።
ከዚህ ድርጊት ያልተማሩ የአማራ ልጆች መከላከያ ውስጥ ምን ይሰራሉ !?

በነገራችን ላይ የትግራይ ተወላጅ የሆናችሁ አሁን ክፍለጦር እና ሬጅመንት በመምራት ላይ ያላችሁ የጦር መኮንኖች አብይ አህመድ በፈለገ ጊዜ አስሮ ሲያሰቃያችሁ እንደነበር ዘንግታችሁ እሱ በፈለገ ጊዜ ፈቶ ንፁሐን ትገድሉ ዘንድ ወደ አማራ ክልል መጥታችሁ በማታውቁት እና በማይመለከታችሁ ጦርነት እየተሳተፋችሁ በመሆኑ ከዚህ ጨፍጫፊ ስርዓት ራሳችሁን እንድታገሉ እናሳስባለን ።

ሌሎች በመከላከያ ውስጥ ያላችሁ ደግሞ የአማራ ጥያቄ በሐይል እንደማይቀለበስ ተገንዝባችሁ የፋኖ ወንድማችሁን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናደርጋለን ።

አማራም ሆነ ኢትዮጵያ ነፃ የሚወጡት ህዝባዊ መንግስት ሲመሰረት እንጅ ከእንግዲህ በኋላ በኢትዮጵያ ምድር በታንክ ጋጋታ የሚፀና መንግስት እንደማይኖር ልናስገነዝባችሁ እንወዳለን ።

የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀጣይ የሚያወጣውን የምህረት አዋጅ ተጠቅማችሁ የህልውና ፤ የነፃነት ፤ የእውነት እና የሐገር ክብር እና የሐገር ፍቅር ስሜት የሚያንገበግበውን የአማራ ፋኖን እንድትቀላቀሉ ስንል ከወዲሁ እናሳስባለን።

አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ

[የአማራ ፋኖ በጎጃም]
የአማራ ፋኖ በጎጃም የሀዲስ አለማየሁ 7ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎቹ የአብራጂት ብርጌድ ልጆች ከበባ አድርጎ ለማፈን የመጣውን የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ኮርክ ከተማ ላይ ቁም ስቅሉን ሲያሳዩት ዋሉ።

በዚህ ውጊያ ለማፈን የገባው ወራሪ ሰራዊት ታፍኖ ከጥዋቱ 12:00-ቀኑ 10:00 ሰዓት ሲቀጠቀጥ ውሎ ከ35 በላይ አስከሬን እና ከፍ14በላይ ቁስለኛ ይዞ ወደ መጣበት ፈርጥጧል። ክፉኛ በመመታቱ የተበሳጨው የአቢይ ወታደር የንፁሃንን ቤት :ሞተር:የቤት እቃ:የፋኖስ እና የፋኖስ ቤተሰቦች ንብረት አውድሞ ወጥቷል።በስነ ልቦና የበላይነት የተወሰደበት ብልፅግና መዝረፋን ተያይዞ ቀጥሎበታል።

በሌላ ዜና
ከ10,000(አስር ሽህ) በላይ አማራ የሆኑ ወታደሮች በአብይ አህመድ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ታስረዋል። በርካቶችም በየቀኑ እየተረሸኑ ነው።

ከ10,000(አስር ሽህ) የሚበልጡ የአማራ ልጅ የሆኑ ወታደሮች በአማራ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ እንዲፈጽሙ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ግዳጅ ቀጠና ላይ የነበሩ እና በሌሎች የሐገሪቱ አካባቢዎች የነበሩ ሲሆኑ ለአማራ ህዝብ እና ለፋኖ ከፍተኛ አቅም መፍጠር ተባባሪ ናችሁ የሚል ምክንያት የተነሳባቸው ሲሆን ከእስረኞቹ መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩት በየ ቀኑኘ እየተረሸኑ ይገኛል።

የአብይ አህመድ ስርዓት ትክክለኛ አማራን ለማጥፋት የተቋቋመ መሆኑን ባለመገንዘብ ጠመንጃ ተሽከመው የአብይን ስርዓት ሲያስቀጥሉ የነበሩ እና ከእግረኛ እሰከ ከ ብርጌዳል ጀኔራል ድረስ ማዕረግ ያላቸው የአማራ ልጆች የአብይ አህመድ ቀጥተኛ ሰለባ ተደርገዋል።

በአብይ አህመድ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የታሰሩ የሰራዊት አባላት  ሌሎች በመከላከያ ውስጥ ላሉ የአማራ ልጆች ሁነኛ ማስተማሪያ ሊሆን እንደሚችልም ተጠቁሟል።

ጦርነት ጠማቂ የሆነዉ ብልፅግና በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ከከፈተ ማግስት በርካታ የአማራ ብሄር ተዎላጆች ጦርነቱን በመቃወማቸው ለዕስር የተደረጉ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ አማራ የሆነ የሰራዊት አባላት እየተመረጡ እንዲታሰሩ ተደርገዋል።

አብይ አህመድ ከህወሓት ጋር ጦርነት በገጠመ ጊዜ በርካታ የትግራይ ተወላጅና ወታደራዊ መኮንኖችን አስሮ ሲያሰቃያቸው እንደነበር ይታወቃል ።ይህንን ድርጊት ዛሬም በአማራ ተወላጆች እና ወታደራዊ መኮነኖች ላይ ተግባራዊ እያደረገዉ ይገኛል።

ሌሎች በመከላከያ ውስጥ ያላችሁ የሰራዊት አባላት  የአማራ ህዝብ  ጥያቄ በሐይል እንደማይቀለበስ ተገንዝባችሁ የፋኖ ወንድሞቻችሁን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናደርጋለን ሲል ፋኖ አሳስቧል።

አማራም ሆነ ኢትዮጵያ ነፃ የሚወጡት ህዝባዊ መንግስት ሲመሰረት እንጅ  በኢትዮጵያ ምድር በታንክ ጋጋታ የሚፀና መንግስት እንደማይኖር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያዉቀዉ እንደሚገባ ፋኖ አሳስቧል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀጣይ የሚያወጣውን የምህረት አዋጅ ተጠቅማችሁ የህልውና ፤ የነፃነት ፤ የእውነት እና የሐገር ክብር እና የሐገር ፍቅር ስሜት የሚያንገበግበውን የአማራ ፋኖን እንድትቀላቀሉ በማለት ጥሪዉን አስተላልፏል።

በዛሬ ሌላኛው መረጃ
የአዲስአበባ ማህበራዊ ንቅናቄ(አማን) እና አራዳ  መዋሀዳቸው ተሰምቷል።

ሁለቱ  አዲስአበባ ላይ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት አደረጃጀቶች ተዋህደዋል። ሁለቱ አደረጃጀቶች ለየብቻ እንዲሁም በጥምረት ላለፈዉ አንድ አመት ገደማ በከተማችን በአዲስአበባ ላይ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል። እንደማሳያ በተለያዩ የከተማዋ ጎዳናዎች ላይ የተቃውሞ በራሪ ወረቀቶችን መበተን, ባነሮችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ በመስቀል እንዲሁም፤ የገዥዉ ብልፅግና ቢሮዎች ላይ የማስጠንቀቂያ ፍንዳታዎችን በመፈፀም ያለፈዉን አንድ አመት ገደማ አሳልፈዋል።

ሆኖም ግን የአላማም ሆነ የግብ ልዩነት ባለመኖሩ እንዲሁም አዲስአበባ ላይ ያሉ የተበጣጠሱ ትግሎን ወደ አንድ አምጥቶ ጠንካራ የማህበራዊ ንቅናቄ  ድርጅት መመስረት እንዳለበት በመታመኑ በሁለቱ ንቅናቄዎች በተደረጉ ሰፋ ያሉ ውይይቶች ወደ አንድ "አማንአራዳ" የተባለ የማህበራዊ ንቅናቄ  ድርጅትነት እንዲመጡ ተደርጓል።

ሁለቱ ንቅናቄዎች ከተዋሀዱበት ጊዜ አንስቶ ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅርን ከመመስረት ጀምሮ በተለያዩ የአዲስአበባ ሰፈሮች  መዋቅሮችን በመዘርጋት, ግብ እና አላማችውን በማጥራት የማህበራዊ ንቅናቄ እቅዶችን እንዲሁም የትግል ማንፌስቶን ከማውጣት ጎን ለጎንም የተለያዩ ስልጠናዎችን  በመዉሰድ ድርጅታዊ ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል።

በመሆኑም ለመላዉ የአዲስአበባ ህዝብ እና አገዛዙን መታገል የሚፈልጉ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ከአማንአራዳ ጋር በአጋርነት እንትቆሙ የትግል ጥሪ እናስተላልፍለን ሲሉ በመግለጫቸው አስታዉቀዋል።

ከዉጭ
የአሜሪካ እርዳታ መቋረጥ የወባ ስርጭትን እንዳያስፋፋ ተሰግቷል።

አሜሪካ ለወባ በሽታ መከላከያ ፕሮጀክቶች የምታደርገው ድጋፍ በድንገት መቋረጡ ለገዳዩ በሽታ መስፋፋት አስተዋጽዖ ሊኖረው እንደሚችል ተነገረ።

አንድ ግዙፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እንዳለው የርዳታው መቋረጥ በተለይ በአፍሪቃ ብዙ ሰዎችን የሚገድለዉ የወባ በሽታ አዲስ ዝርያ እንዲፈጠር ብሎም የከፋ የጤና ጥፋት እንዳያስከትል ያሰጋኛል ብሏል።

መቀመጫውን ለንደን ብሪታንያ ያደረገውና በመላው ዓለም የወባ በሽታን ለመከላከል የሚጥረዉ ግብረ ሰናይ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ጀምስ ቲቤንደርና «በሽታው የሚያሳከትለውን ጥፋት አስቀድመን ለመገመት ብንሞክርም ሁኔታው ከተጠበቀው በላይ ማለፉን» ተመልክተናል ብለዋል።

አሜሪካ ለወባ በሽታ መከላከያ ፕሮጀክቶች የምታደርገውን ድጋፍ ማቋረጧን ተከትሎ ሞዛምቢክ ውስጥ በወባ መከላከያ ላይ የሚሰራ አንድ መርኃ ግብር እንዲዘጋ እና ሰራተኞች እንዲባረሩ ማድረጉን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ከኢትዮጵያን፣ ከኤርትራ ፣ ከሱዳን ፣ ከደቡብ ሱዳን እና ከዩጋንዳ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የወባ ህክምና ዋነኛ መሰረት በሆነው በአርቴሚሲን ላይ ተመሰረቶ በተቀናጀ መልኩ የሚሰጥ ህክምና መድሃኒትን የሚቋቋም ተዋሐሲ የመጀመሪያ ምልክቶች እየታዩ መሆናቸውም ተሰምቷል።

የአሜሪካ መንግሥት በአብዛኛው በአፍሪካ በየዓመቱ  ከ250 ሚሊዮን በላይ ከሚሆኑ ሕሙማን መካከል ከ600,000 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነውን በሽታ ለመቆጣጠር እና ለመመርመር 40 በመቶ የሚሆነውን ዓመታዊ የገንዘብ ድጋፍ ያደርግ ነበር።

@አለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ ኔትወርክ
የፋኖ ድምፅ !
👍1
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈትን ተከትሎ አዳዲሲ ውሳኔዎችን አሳለፈ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ከዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አመራር አካላት ጋር የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ውይይት ማካሄዱን ገልጿል።

ውይይቱ በተለይ ቤተሰቦቹ ሊደገፉ በሚችሉባቸውና ሃኪሙ በህይዎት ዘመኑ ያከናወናቸው ልዩ ሙያዊ አስተዋጽኦችን መዘከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

ዶ/ር አንዱአለም ምንም እንኳን የተሰጠውን ጸጋ ሳይሰስት በመጠቀም ለበርካቶች የዘርፉ ባለሙያዎችና በሙያው ላገለገላቸው በርካታ ህሙማን የቅን አገልጋይነት ተምሳሌት የነበረ እንቁ ባለሙያ ቢሆንም ገና በ37 ዓመቱ የተቀጠፈ በመሆኑ ለህጻናት ልጆቹና ቤተሰቡ ትቶ ያለፈው ቤትም ሆነ ሌላ ንብረት የሌለው መሆኑ ተገልጿል።

የቀረቡለትን በርካታ ዓለምአቀፍ የስራ ቅጥር ግብዣዎች ባለመቀበል ወገኑን ለማገልገል ቆርጦ የነበረ ባለሙያ ከመሆኑም በላይ በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ክፍል የነበረውን ልዩ አበርክቶና የቀዶ ጥገና ክፍሉን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሻሻል እየጣረ የነበረ እና እውን ለማድረግ ጫፍ ላይ ደርሶ ያለፈ መሆኑ በውይይቱ ተነስቷል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ የነበረውን ሞያዊ አቅም ተጠቅሞ ራሱን ለተገልጋዮች በቅንነት ሰጥቶ ያለፈ ታላቅ ባለሙያ እንደነበረ የስራ ባልደረቦቹ ፣ተማሪዎቹ እና አገልግሎቱን ያገኙ ደምበኞቹ የሚመሰክሩለት ድንቅ ሃኪም የነበረ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አመልክቷል።

በመሆኑም ፦

➡️ የዶ/ር አንዱአለም ልጆች ለከፍተኛ ትምህርት ሲደርሱ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በነጻ እንዲማሩ፤

➡️ ባለቤቱ ከትምህርት ዝግጅት አንጻር በሲቪል ምህንድስና 2ኛ ዲግሪ ያላት እና ጥሩ አቅም ያላት በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል የምትቀጠርበት ሁኔታ እንዲመቻች፤

➡️ ዶ/ር እንዱአለም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና የሰራው እሱ በመሆኑና ክፍሉን እስከ ህልፈቱ ድረስ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረ በመሆኑ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ዋርድ በስሙ ዶ/ር አንዱአለም ዳኘ ቀዶ ጥገና ዋርድ ተብሎ እንዲሰየም፤

➡️ የዶ/ር አንዱአለምን የአገልጋይነት ጥግ እንዲሁም ለሙያው የተሰጠ ተምሳሌታዊነቱን በቋሚነት ለመዘከርና ማስተማሪያ እንዲሆን በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ሃውልት እንዲቆምለት፤

➡️ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ School of Medicine ውስጥ በስሙ BDU Talent Scholarship እንዲቋቋም፤

➡️ ለ40ኛ ቀኑ መታሰቢያ የሚደርስ ስለ ዶ/ር አንዱአለም የህይዎት ታሪክ የሚዳስስ መጣጥፍ እንዲዘጋጅ ዩኒቨርሲቲው ወስኗል።

ውሳኔው ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡
የታሰርኩት ቂም በቋጠሩብኝ ባለስልጣናት ምክንያት ነው - አቶ ክርስትያን ታደለ

በእስር ላይ የሚገኙት የህዝብ እንደራሴ ክርስትያን ታደለ ዛሬ በነበረ አንድ የችሎት ሂደት ላይ ከመታሰራቸው በፊት ከግራም ከቀኝም ሲደርስባቸው የነበረው ጫና አስረድተዋል፡፡

ያልተገቡ አሰራሮችን ለማጋለጥ ጥረት በማደርግበት ወቅት አንዳንድ ባለስልጣናት በግሌ ያስፈራሩኝ ነበር ያሉት አቶ ክርስትያን አሁን የመታሰራቸው ጉዳይ በወቅቱ ቂም ከያዙባቸው ባለስልጣናት ጋር እንደሚገኛኝ ተናግረዋል፡፡

ከአቶ ክርስትያን ታደለ በተጨማሪ እነ ዮሀንስ ቧያለው በዛሬ ችሎት ላይ የታሰሩበት ምክንያት አግባብ አለመሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዐቃቤ ሕግ የሽብር ወንጀል ክስ የቀረበባቸው አማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለው ክስ የቀረበባቸው "የወከላቸው ሕዝብ ላይ የደረሰውን በደል እና ግፍ" በመቃወማቸው መሆኑን ተናገሩ።

አቶ ዮሐንስ ይህን ያሉት ሐሙስ ጥር 29/2017 ዓ.ም. በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሕገ መንግሥት እና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል ነው።

ከእሳቸው በተጨማሪ ሌሎች 15 ተከሳሾችም በዐቃቤ ሕግ ለተመሠረተባቸው ክስ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

አቶ ዮሐንስን ጨምሮ ችሎት የቀረቡት 16ቱም ተከሳሾች የቀረበባቸውን ወንጀል "አልፈጸምንም" ማለታቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የእምነት ክህደት ቃላቸውን በቅድሚያ የሰጡት አቶ ዮሐንስ "የፍትሕ ሚኒስቴር በእኔ እና በእኔ ስም በሚጠራው መዝገብ ላይ ያቀረበው ክስ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የለውም" ብለዋል፡፡

አቶ ዮሐንስ አክለውም "ሕግን በመተላለፍ እና ወንጀል በመፈጸማቸው ሳይሆን ንቁ አማራዎች፣ ፖለቲከኞች እና ምሁራን" በመሆናቸው ምክንያት እንደተከሰሱ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የቀረበባቸውን "ወንጀል እና አሉባልታ" እንደማይቀበሉ እንዲሁም ወንጀልም እንዳልፈጸሙ የጠቆሙት አቶ ዮሐንስ፤ "ፍትሕ የለም እንጂ እኔ ነጻ ሰው ነኝ። ፍርድ ቤቱ በነጻ ለቆ ለደረሰብኝ በደል ሁሉ ካሳ ሊያሰጠኝ በቻለ ነበር" ብለዋል።

ሁለተኛ ተከሳሽ የሆኑት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ በበኩላቸው "[የተከሰስኩት] የመንግሥትን ብልሹ አሠራር በማጋለጤ ነው" ሲሉ የቀረበባቸውን ክስ ክደዋል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዩ አክለውም በእስር ላይ የሚገኙት "የወንጀል ድርጊትን የሚያቋቁም የሕግ መተላለፍ" ስለፈጸሙ አለመሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ክርስቲያን ለእስር ተዳረጉት "የገዢውን ፓርቲ እና የመንግሥት አሠራሮችን እንዲሁም የአመራሮችን ብልሹነት እና ዘረፋ በመታገላቸው እና በማጋለጣቸው" መሆኑን በእምነት ክህደት ቃላቸው ላይ ጠቁመዋል።

በምክር ቤቱ በመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት በነበራቸው ኃላፊነት የሠሩት ሥራ ለእስር እንዳደረጋቸው አቶ ክርስቲያን ጠቁመዋል።

አቶ ክርስቲያን በዚህ ኃላፊነታቸው "ተደጋጋሚ የአመራር ብልሹነት" ያሳዩ አካላት ላይ "የወንጀል እና የፍትሐ ብሔር ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ" ክስ እንዲመሠረት ፍትሕ ሚኒስቴርን ማዘዛቸውን አስታውሰዋል።

በምክር ቤት አባልነታቸውም የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች "የፋይናንስ ግልጸኝነት እና ሕጋዊነትን እንዲከተሉ እና እንዲያረጋግጡ" መጠየቃቸውን አቶ ክርስቲያን አውስተዋል።

"እነዚህ ጥያቄዎች እንዳልጠይቅ አንዳንድ አመራሮች በግል በኢመደበኛ ሁኔታ ለማግባባት ሞክረዋል" ያሉት አቶ ክርስቲያን በዚህ ሳቢያ ለእስር መዳረጋቸውን ገልጸዋል።

ሦስተኛ ተከሳሹ ሆነው የቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ካሳ ተሻገርም በተመሳሳይ የተከሰሱበትን ወንጀል አለመፈጸማቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።
ዶ/ር ካሳ "እኔ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ነኝ። የወከለኝን ሕዝብ ሰቆቃ እና ስቃይ በምክር ቤት ውስጥ በመናገሬ ነው የተከሰስኩት" ሲሉ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዐቃቤ ሕግ በዶ/ር ካሳ ላይ ካቀረበባቸው ክሶች መካከል "ታጣቂዎች የሚመሩበት ወታደራዊ ሰነድ አዘጋጅተዋል" የሚለው አንደኛው ነው።

ዶ/ር ካሳ ተሻገር "ማኅበራዊ ሳይንስ መምህር ነኝ ይሄ የፈጠራ ክስ ነው። እኔ የወታደራዊ ሳይንስ ትምህርትም ዕውቀትም የለኝም" ሲሉ ማስተባበላቸውን ጠበቃ ሰለሞን ገልጸዋል።

ሌላኛው ዝርዝር የእምነት ክህደት የሰጡት አምስተኛ ተከሳሽ ዶ/ር ጫኔ ከበደ ናቸው።

ዶ/ር ጫኔ "እኔ የኢዜማ ሊቀ መንበር ነኝ። በዚህ ፓርቲ በኩል ሰላምን የምሰብክ ስለሰላም የማወራ እንጂ በሽብር ድርጊት እንዲሳተፉ የፓርቲዬን አባላት የምቀሰቅስ አይደለሁም" ማለታቸውን ጠበቃ ሰለሞን ገልጸዋል።

"ክሱ የቀረበብኝ በኢዜማ ስር ሆኜ በማራምደው ፖለቲካ ሳይሆን በአማራነቴ ምክንያት ነው" ያሉት ዶ/ር ጫኔ፤ "እኔ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት አባል ሆኜ በሰላማዊ መንገድ እየታገልኩ ነው ያለሁት እንጂ የፈጠራ ክሱ ላይ የተገለጸውን የሽብር ድርጊት አልፈጸምኩም" ብለዋል።

ፍርድ ቤቱም በተከሳሾቹ ላይ ቃል የሚሰጡ 21 የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ከመጋቢት 5 አስከ 12/2017 ዓ.ም. ለመስማት ቀጠሮ ይዟል።
1👍1