ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ለወራት የሰለጠኑ 4ኛ ዙር የልዩ ኮማንዶ ሰልጣኞች ተመረቁ!
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ስር የሚገኘው 71ኛ ክፍለ ጦር ለወራት ያሰለጠናቸው 4ኛ ዙር ምልምል ልዩ ኮማንዶዎችን ትናንት ሚያዚያ 13/2018 ዓ/ም በታላቅ ድምቀት ማስመረቁን ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አሳውቋል።

በምረቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ የኮርና የክፍለጦር እንዲሁም የሬጅመንት አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች የተገኙ ሲሆን፡ "የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት የሚያስከብር፣ የአማራን ሕልውና የሚታደግ እንዲሁም ፍትሕ ርትዕ የሚያሰፍን ብቁና ንቁ የፋኖ ኃይል መገንባቱን ታዳሚው ተመራቂዎቹ ካሳዩት ትርኢት አረጋግጧል።

ክፍለጦሩ በየቀኑ ከሚያደርገው ውጊያ ጎን ለጎን ያልተቋረጠ የስልጠና መርሃ ግብር በማካሄድ የጠላትን ቅስም የሚሰብር ብቁና እጅግ ጠንካራ ኃይል ማፍራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል
🙏4
​በሸዋ ምድር የታደሰ የለውጥ ቃል-ኪዳን፦ የአፄ ዘረ ያዕቆብ ኮር ናደው ክፍለ ጦር ወታደራዊና ፖለቲካዊ ተሀድሶ

​ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

​ከጊዜ ወደ ጊዜ ራሱን በወታደራዊ ሳይንስና ስልት እያዘመነ የሚገኘው ናደው ክፍለ ጦር፤ የዐለት ያህል የጠነከረ ጽናቱንና ህዝባዊነቱን ዳግም አረጋግጧል።

ክፍለ ጦሩ የአማራን ህዝብ ህልውና ለማስከበርና ብሩህ ተስፋን ሰንቆ የነገውን ድል ለማብሰር የሚያስችለውን ጥልቅ ወታደራዊና ስነ-ልቦናዊ ተሀድሶ አከናውኗል።

​በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ስር የሚገኘው የአፄ ዘረ ያዕቆብ ኮር (ናደው ክፍለ ጦር) ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራዊት ላለፉት ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩትን ስልጠናና ተሀድሶ በአዲስ መንፈስ አጠናቀዋል። በዚህም አመራሩ ለለውጥ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይቷል።

​የአመራሩ ቁርጠኝነትና የውይይቱ ዋና ነጥቦች
​በተሀድሶ መድረኩ ላይ የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፦

​ሻለቃ ሞገስ ለማ
​አርበኛ አንዳርጋቸው አሰፋ
​አርበኛ ትንቢት ኃይለማርያም

​ከእነዚህ የዕዝ አመራሮች ጋር በመሆን የኮሩ ዋና መሪ አርበኛ እዮብ ለማ እና የክፍለ ጦሩ አመራሮች ያለፈውን የትግል ጉዞ በጥልቀት ገምግመዋል። ውይይቱ ድክመቶችን ወደ ጥንካሬ በመለወጥና የነገውን የድል ስልት በመንደፍ ላይ ያተኮረ ነበር።

​አመራሩ ባስተላለፈው መልዕክት፤ ክፍለ ጦሩ በተለያዩ የውጊያ አውደ ግንባሮች ያስመዘገባቸው ድሎች "ከመከላከል ወደ ማጥቃት" ለተደረገው ሽግግር ትልቅ ማሳያ መሆናቸውን ገልጸዋል።
​"ያለፈውን 'ክፉ ጊዜ' እንደ ትልቅ መማሪያ መጠቀም፣ ለወደፊቱ ግልጽ ራዕይና የማይበገር ወታደራዊ ስነ-ምግባር ሰንቀን ተነስተናል። ይህ ተሀድሶ ተራ ስልጠና ሳይሆን የአማራን ህዝብ ክብር ለመመለስ የገባነው ዳግም ቃል-ኪዳን ነው!"

​ሰራዊቱ ካለፈው የውጊያ ተሞክሮ ተምሮ ይበልጥ በታጠቀ ወታደራዊ ሳይንስና በጠነከረ ስነ-ልቦና እንዲገነባ ላደረጉት የዕዙ አመራሮች የክፍለ ጦሩ አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ይህም የሚከተሉትን ዓላማዎች ለማሳካት ጉልበት እንደሚሆን ተገልጿል፦

​በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያና ዘረፋ በአፀፋዊ እርምጃ መመከት።
​የድርጅቱን ግብ ለማሳካት አመራርና ሰራዊቱን በአንድ ልብ ማሰለፍ።
​የጠላትን ምሽግ የሚያናጋ የታሪክ አሻራ ማሳረፍ።

​በመጨረሻም የክፍለ ጦሩ አባላት፦ "እኛ የአፄ ዘረ ያዕቆብ ልጆች፣ ለሸዋና ለአማራ ህዝብ ነጻነትና ክብር እስከ መስዋዕትነት ለመጓዝ ቃላችንን አድሰናል!" በማለት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።

​የመረጃ ምንጭ፦ የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር
​''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
​የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
1🙏1
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር 49ኛ ክፍለ ጦር የሰራዊት ተሃድሶና የአልባሳት መረሀ-ግብር በደማቅ ሁኔታ አካሔደ።

የ102ኛ ኮር አካል የሆነው የ49ኛ ክ/ጦር ከግዳጅ ጎን ለጎን የሰራዊት ተሀድሶና የአልባሳት ፕሮግራም በማድረግ ለወደ ፊት ለሚደረጉ ግዳጆች ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦር አመራሮች ገልፀዋል።

በመርሀ ግብሩ ከተከናውኑት ሁነቶች መካከል በ49ኛ ክ/ጦር የሰልፍ ትሪኢት፣ በግዳጅ የተሻለ አፈፃፀም የነበራቸውን የሻለቃ አመራር፣ የክ/ጦር አመራር፣ የድርጅት አመራርን በመሸለምና ተወዳጅ የሆነውን የአማራ ፋኖ መዝሙር በጣዕመ ዜማ ቀርቧል።

የተሀድሶ ፕሮግራሙን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የ102ኛ ኮር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ቀኝ አዝማች ረዳ ውበቱ ሲሆን ለ49ኛ ክ/ጦር የሰራዊት አባላት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሰብሳቢው አያይዘው እንደገለፁት የአማራን ህዝብ በሀይል ለማንበርከክ የመጣውን ነውረኛ አገዛዝ ለማስወገድ ከመቸውም ጊዜ በላይ ሰራዊቱ ዝግጁ እንድሆን ገለፁ።

በምርጫ ስም በህዝባችን ላይ ህገ-መንግስታዊና መዋቅራዊ በደል ለማስቀጠል እንድሁም የዳር ተመልካች ለማድረግ የመጣውን የብልፅግና አገዛዝ በቀላሉ ለማስወገድ በሰሞኑ በወሰድንበት ጠንካራ ምት የተብረከረከ በመሆኑ በኮራችን ለሚገኙ ክፍለጦሮች ከመቸውም ጊዜ በላይ ዝግጁ እንዲሆኑ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የ102ኛ ኮር ዋና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ጌታቸው መልኩ ለ49ኛ ክፍለ ጦር የሰራዊት አባላት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አሰተላልፈዋል።

ወታደራዊ አዛዡ አያይዘው እንደተናገሩት ከሆነ የአብይ አህመድን ጨፍጫፊ አገዛዝ በአጭር ጊዜ ለማስወገድ ከመቸውም ጊዜ በላይ የሰራዊታቸውን ወትሮ ዝግጁነት እንደሚተማመኑበት ጠንከር ያለ ሀሳብ አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም ንግግር ያደረጉት የአሁኑ 49ኛ ክ/ጦር የቀድሞው የከላኮርማ ክፍለ ጦር መስራችና የ102ኛ ኮር ም/ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ዘውዱ ዳርጌ ለሰራዊት አባሉ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወታደራዊ አዛዡ ለሰራዊቱ ካስተላለፉት መካከል ስለ አላማ ፅናትና የትግል ባህሪያት በመግለፅ ማንም የአማራ ፋኖ ታጋይ የአማራ ብሔርተኝነትን ተላብሶ በህዝባችን ላይ በግደታ የተጫነበትን ቀንበር ከትክሻው ለማስወገድ ዝግጁ እንድሆን መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንድሁም የ102ኛ ኮር የስልጠና መምሪያ ሀላፊ መቶ አለቃ ሲሳይ መንግስቴና የኮሩ የሰው ሀይልና የመስክ ስልጠና መምሪያ ሃላፊ አምሳ አለቃ ያብቃል ቢተው የተሀድሶውን የሰልፍ ትሪኢትና የአልባሳት ፕሮግራም በመምራት ዝግጅቱ እንድያምር የራሳቸውን አሻራ ጥለዋል።

በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ወሎ ቤተ-አማራ ም/የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አርበኛ አሰፋ መሰለ /አሳምነው/ በዝግጅቱ በመገኘት ለ49ኛ ክፍለ ጦር አመራርና የሰራዊት አባላት እንኳን ደስ ያላችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የአረጃጀት ዘርፍ ሀላፊው አያይዘው ለሰራዊቱ ጨፍጫፊውንና አምባገነኑን አገዛዝ ለመፋለምና ህዝባቸውን ከገባበት ቅርቃር ውስጥ ለማውጣት ዝግጁ እንድሆን መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም 102ኛ ኮር ዋና የፖለቲካ መምሪያ ሀላፊ አርበኛ ሻምበል አሌ ለ49ኛ ክፍለ ጦር አመራር የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አያይዘው እንደተናገሩት የአማራ ህዝብ የፍትህ፣ የነፃነትና የህገ-መንግስት ጥያቄ ስላለው በወርድና በቁመቱ ልክ የፖለቲካ ውክልና እስኪኖረው ድረስ ጠንካራ ታጋይ እንድፈጠር ሲሉ አበክረው ገልፀዋል።

እንድሁም የ102ኛ ኮር የፖለቲካ መሪው እንደገለፁት ያለጦርነት መኖር ከማይፈልገው የአብይ አህመድ አገዛዝ የአማራን ህዝብ ነፃ ለማውጣት አመራራችንና የሰራዊት አባላችን በሙሉ በምናስተዳድራቸውና አድስ በተቆጣጠርናቸው አካባቢዎች ለህግና ስርዓት ተገዥ እንድሆን ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ-ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም
🙏2
ሰበር ዜና!!!

አፋብን ወሎ-ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም
🙏2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር 34ኛ ክፍለ ጦር በጋዞ ወረዳ የጥላትን ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ ድል አስመዘገቡ::

ከሚያዚያ 15/2018 ዓ/ም እስከ ሚያዚያ 16/2018 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናቶችን ያስቆጠረው አውደ ውጊያ በ34ኛ ክፍለ ጦር አናብስቶች የአገዛዙ ሰራዊት ከፍተኛ ምት ተፈፅሞበታል። ውጊያው ቀጥሎ ያለ ሲሆን ጥላት እስካሁን ሙትና ቁስለኛውን እያነሳ ላይዋጋበት የቆፈረውን ምሽጉን እየለቀቀ እየፈረጠጠ ይገኛል።

የፋኖዎች የድል ግስጋሴ የጋዞ ወረዳ ዋና ከተማ የእስታይሽ ከተማን ግማሽ አካልና ፖሊስ ጣቢያ በፋኖዎች ቁጥጥር ስር ውሏል። በዚህ የድል ግስጋሴ በብዙ ደርዘን የሁለት ቀን ቁስለኛና ሙቱን አገዛዙ ተሸክሞ ወደ ኋላ እግሬ አውጭኝ እያለ እየፈረጠጠ ይገኛል።

በዚህ ሰዓት የእስታይሽ ሆስፒታል በቁስለኞች የተሞሉ ሲሆን የጤና ጣቢያ እና የጤና ኬላን ባለሞያዎችን አገዛዙ በግድ ካላከማችሁ እየተባሉ በየ ስራ ቦታቸው እየታፈሱ መወሰዳቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም
🙏2