ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ከሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመካነሰላም ግንባር ከምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ጋር በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ የከፈተው የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናገደ!

ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ተጋድሎ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ድል ቀንቶታል:: የጠላት ኃይል ቁስለኛ እና አስከሬን በአምቡላንስ ጭኖ ወደ መካነሰላም አቅንቷል::

11ኛ ዕዝ ከመሐል ሳይንት እና አማራ ሳይንት ወረዳዎች ጭምር ሰራዊቱን ወደ መካነሰላም አጓጉዞ መካነሰላም ለሚገኘው ፀረ ህዝብ ኃይል ድጋፍ ለማድረግ ሙከራ ቢያደርግም ኦፕሬሽኑ በእነ ሞት አይፈሬ ብርታት ከሽፏል:: በዚህም የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት በተለምዶ አደሬ ቆቦ የተባለች ቦታ ላይ በትናንትናው ዕለት ክፉኛ የተመታ ሲሆን ሽንፈቱን ለማካካስ በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ መድፍ እና ሞርተር ወደ ገበሬዎች መንደር በመተኮስ በንፁሀን ላይ ጉዳት አድርሷል:: ትናንት አንድት እናት በሞርተር ተመታ ክፉኛ ቆስላ በህክምና ላይ እንደምትገኝ ተረጋግጧል:: ዛሬ ደግሞ አንድ ንፁህ ገበሬ በመድፍ ተመቷል:: መትረፍ እንደማይችልም ነው የህክምና ውጤቱ የሚያስረዳው::

ጠላት በተደጋጋሚ መድፍ ጭምር የተኮሰ ሲሆን ቢሊ ታዳጊ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የሙጎጉቱ ገብርኤል ገዳምን ህንፃ ቤተክርስቲያን ጣራ አውድሞታል::

የጠላት ኃይል የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር  ሰራዊትን ጥሶ አልፎ ቢሊ ታዳጊ ከተማን የመቆጣጠርና ለቀጣዩ ወር ምርጫ ቅድመ ዝግጅት የማድረግ እቅድ አቅዶ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ታዳጊ ከተማዋ ሳይደርስ በትናምትናው እለት መንገድ ላይ ተቀጥቅጦ የተመለሰ ሲሆን በዛሬው እለት ተመልሶ በመድፍ እና ሞርተር የከተማይቱን ነዋሪዎች ሲደበድብ ውሏል:: 

ጠላት የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ መግባቱን የሚያረጋግጥ ክስተት የተፈጠረ ሲሆን በዚህም የ87ኛ ክፍለ ጦር አመራር የሆነ 10 አለቃ ምስጋን የተባለ ወታደር እና ሌላ ጓዱ በበቃኝ ከጠላት ከድተው የወገን ኃይልን ተቀላቅለዋል:: አንድ 50 አለቃም የጠላት ኃይልን ከድቶ አድራሻውን አጥፍቷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም
👍1
ሰበር ዜና

አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተለያዩ ግንባሮች ድልን ተቀዳጀ።

ሚያዚያ 06/2018 ዓ.ም

የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር የአብይ አህመድ አገዛዝ ጅምላ ተጋላቢ አየር ወለድ ኮማንዶ ሀይሉን ከተለያዩ የቡድን መሳሪያ ጋጋታ ጋር ማለትም ዙ *23 መቶ ሰባት ብዛት ያለው ዲሽቃና ሞርተር ከሁሉም አካባቢ ቀራርሞ በማምጣት በሆድ አደር ሚሊሻ መንገድ መሪነት በሸዋ ክፍለ ሐገር መርሓቤቴ አዉራጃ ታች ቤት ቀበሌ ፋኖ አለበት ወደተባለበት ቀጣና ከለሊቱ 9:30 ከዋና ከተማው መቀመጫ አለም ከተማ እና ፌጥራ ተጠራርቶ ጨለማን ተገን አድርጎ በሶስት አቅጣጫ ማለትም በቡዮላይ ፣በሸፈሬ አንባ እና በጮሬ ቀበሌ" በማድረግ ወደ ጎራንዳ ከበባ ለማድረግና ለማጥቃት አቅዶ የገባው ሀይል የመርሐቤቴን ገደላገደልና አቀበት እንደ ሜዳ እየረገጡ፣ "ከፊታችን ሞት ቢኖርም ከኋላችን ታሪክ አለ" በሚል ወኔ የጠላትን ምሽግ የሚሰባብሩት የናደው ክፍለጦር ተርብ ተዋጊዎች፤ በፍጥነት ከበባውን በመክበብ ዕለታዊ ውሏቸው በባሩድ ጢስ ውስጥ የተጻፈ የጀግንነት ታሪክ አድርገውታል። ናደው ክፍለ ጦርን እደመስሳለሁ ብሎ የመጣው የጠላት ሀይልም በእነ ሞት አይፈሬ ነፃነት ክብራቸው ክፉኛ ያልጠበቀው ጉዳት ደርሶበታል።የናደው ክፍለ ጦር ምክትል ጦር አዛዥ ቀኝ አዝማች አቡ አሳምረው የተመራው የዕለቱ ውጊያም የውጊያ ጥበብ እና ብስለት በተሞላበት አውደ ውጊያ ናደው ክፍለ ጦር ድል ማድረግ ችሏል። ከናደው ክፍለ ጦር ከሁሉም ሻለቆች በተወጣጡ ሰራዊት በሶስት አቅጣጫ የመጣውን የጠላት ሀይል ሁሉንም አይነት አለኝ የሚለውን ስልትና ብቃቱን ለመጠቀም የሞከረ ቢሆንም ፤ ከሌሊቱ 9:30 የተጀመረ ውጊያ እስከ ቀኑ 10:00 ድርስ የነበረ ቢሆንም በወገን የስነ ልቦና እና የውጊያ የበላይነት በጠበቀ መልኩ ሲያጪዱት ውለዋል።

በእዚህ አውደ ውጊያ በጠላት ላይ የደረሰው ጉዳት በዝርዝር እንደሚከተለው እንገልፃለን።

👉1ኛ, አንድ ሲኖ መኪና ሙሉ የጠላት ሀይል ከእነ ተሽከርካሪዉ በልዩ ኦፕሬሽን ልዩ ስሙ ቡዮ የተባለው ቦታ ላይ መደምሰስ ተችሏል።
👉2ኛ. ሻንበል አመራሮችን ጨምሮ የተደመሰሰ የጠላት ሀይል 32
👉3ኛ,ከባድ ቁስለኛ 09
👉4ኛ,ቀላል ቁስለኛ 17
👉5ኛ,ቀንደኛ መንገድ መሪ ሚሊሻ 04 መደምሰስ ተችሏል።

በእዚህ አውደ ወጊያ ከፍተኛ ኪሳራ ያስተናገደው ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ስራዓት ሽንፈቱን ሲከናነብ የተለመደውን ዘግናኝ ድርጊቱን ምንም በማያውቁ ገበሬ እና የፋሲካ በአልን ምክንያት በማድረግ ለማክበር እና ሰርግ ላይ የተሰበሰቡ ንፁሃኖችን የበደል ብትሮችን በማሳረፍ እና ንፁሃን አርሶ አደሮችን እየቀጠቀጠ ለፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያነት ይዞ ሄዷል።

በእዚሁ አውደ ውጊያ የተሸነፈው የአገዛዙ ጅምላ ተጋላቢ ሀይል የፋኖን ምት መቋቋም አቅቶት አስከሬኑን እያዝረከረከ በመፈርጠጥ ወደመጣበት ተመልሷል ።

በሌላ የዕለቱ ዜና

አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር የ7ተኛ ሃገር አቀፍ ምርጫ ካርድ በቁጥጥር ስር አውለውታል!!!!

አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ጀግኖቹ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር 4ተኛ ሻለቃ ቃኘዎች በብልፅግና ጥምር ጦር የሚመራው የማጭበርበሪያ የ7ተኛ ሃገር አቀፍ የውሸት ምርጫ ካርድ በባሶና ወረና ወረዳ በደበሌና እሮብ ገበያ ቀበሌ ህዝብን በግዳጅ የምርጫ ካርድ ለማስወጣት ሲሞክር የፋኖን ብትር መቋቋም ሲያቅተው ይዞት የመጣውን በርካታ የምርጫ ካርድ እያዝረከረከ እና አስማርኮ ወደ መጣበት ደብረ ብርሃን የእፈረጠጠ ተመልሷል።

የመረጃ ምንጭ-አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን

ክብር ለተሰውት
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን

አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
🙏21
የሙጎጉቱ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በመድፍ ተመታ!

ከመካነሰላም ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኘውና በቅርቡ የተመሰረተው የሙጎጉቱ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድ ምድብተኞች መድፍ የተመታ ሲሆን የገዳሙ ህንፃ ቤተክርስቲያን ጣራን የመድፉ ፍንጣሪ በሳስቶታል::

መካነሰላም ከተማ ውስጥ አሜጃ የተባለ ስፍራ ላይ መድፍ በማጥመድ ወደ ሙጎጉቱ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተደጋጋሚ ሲተኩስ ውሎ ያደረው የጠላት ኃይል ከገዳሙ ህንፃ ቤተክርስቲያን በተጨማሪ በንፁሀን ላይ ጭምር ጉዳት አድርሷል:: በተለይ 2 ንፁሀን ክፉኛ የቆሰሉ ሲሆን አንዱ የመትረፍ ዕድል እንደሌለው ነው የህክምና ባለሙያዎች የገለፁት::

የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት የሀይማኖት ተቋምን ሲፈልግ እንደ ምሽግ ይጠቀማል እንዳ ሲለው ደግሞ ታርጌት አድርጎ ተኩሶ ህንፃ ያፈርሳል ያሉት የገዳሙ አካባቢ ነዋሪዎች ድርጊቱን አውግዘዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም
💔1
ከአባ ሳሙኤል ማረሚያ ቤት የተሰማ የፖለቲካ እስረኞች የድረሱልን ጥሪ!

"ምግብና ውሃ ተከልክለናል!"

መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቂሊንጦ ወደ አባ ሳሙኤል ማረሚያ ቤት የተዛወሩ የአማራ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች፣ በማረሚያ ቤቱ እየተፈጸመባቸው ያለውን "ኢ-ሰብአዊ አያያዝ" በመቃወም ዛሬ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ።

እስረኞቹ በችሎት ፊት ባሰሙት አቤቱታ ፣ መሠረታዊ የሆኑት የምግብ፣ የንጹህ ውሃ እና የሕክምና አገልግሎቶች በመከልከላቸው ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸውን ገልጸዋል።

በተለይም ማረሚያ ቤቱ የሚሰጠው ምግብ ለፍርደኞች (ቅጣት ለተወሰነባቸው) ብቻ ተብሎ የተዘጋጀ መሆኑንና እስረኞች በራሳቸው ወጪ እንኳን ምግብ ገዝተው እንዳይመገቡ መታገዳቸውን አስረድተዋል።

ቤተሰብ እንደ በሶ ያሉ ምግቦችንና አልባሳትን እንዳያስገባላቸው መከልከሉ ለከፍተኛ ረሃብና ለጤና መታወክ እንደዳረጋቸው በአጽንኦት ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት የታሰሩበት "ዞን አራት" ቀደም ሲል ለከፍተኛ የዲስፕሊን ቅጣት ተብሎ የተለየ ክፍል መሆኑን የጠቀሱት እስረኞቹ፣ የውሃ አቅርቦት በቀን ለ15 ደቂቃ ብቻ በመገደቡ የግልና የአካባቢ ንጽህናን ለመጠበቅ እንዳልተቻለ ገልጸዋል።

የመጸዳጃ ቤቶች መሙላትና የፍሳሽ ቆሻሻ በየክፍሉ ወለል ላይ መፍሰስ በፈጠረው ጠረን ለተላላፊ በሽታዎች እየተጋለጡ መሆኑንና በማረሚያ ቤቱ ያለው የሕክምና አገልግሎትም እጅግ ደካማ እንደሆነ አመልክተዋል። በተጨማሪም ክፍሉ ምንም ዓይነት የቤተ-መጻሕፍትም ሆነ የቴሌቪዥን አገልግሎት እንደሌለው ተገልጿል።

የሕግ ባለሙያዎች እንደሚገልጹት ፣ ገና ጥፋተኝነታቸው ባልተረጋገጠ "የቀጠሮ እስረኞች" እና ፍርድ ባረፈባቸው "ታራሚዎች" መካከል ግልጽ የሆነ የቦታና የአያያዝ ልዩነት ሊኖር ይገባል።

ሆኖም በአባ ሳሙኤል የሚገኙት እነዚህ የአማራ የሕሊና እስረኞች፣ ከባድ ወንጀል ፈጽመው የረጅም ጊዜ እስራት ከተፈረደባቸው ግለሰቦች ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጋቸው ለደህንነታቸው ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ለችሎቱ አስታውቀዋል።

በአባ ሳሙኤል ወደመቶ የሚጠጉ የአማራ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በአስገዳጅ ሁኔታ ተዛውረው መታሰራቸው የሚታወስ ነው!

(ዘሪሁን ገሠሠ)

(አውሎግሶን አንድነት ፣ ሚያዝያ 6/2018)
🔥2
አማራ በመሆናቸው ያለፍትህ በገፍ እና በግፍ ታስረው ከሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች የቀረበ ጥሪ

እየተፈፀመብን ያለውን የሕግ ጥሰትና አስተዳደራዊ በደል መላው የአማራ ሕዝብ ።፣ ሀገር እና ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊያንና ዓለም ይወቅለልን!

እኛ የአማራ ተወላጅ የሆን በእነ ስንታየሁ ንጋቱ መዝገብ ቁጥር 326559 በሽብር ወንጀል የተከሰሰን ተከሳሾች በዛሬው እለት የመከላከያ ማስረጃ እንድናቀርብ የተያዘ ቀጠሮ ነበር።

በመሆኑም በእኛና በእኛ መሰል የሽብር ወንጀል ተከሳሽ ተብለን በማንነታችን ብቻ ተለይተን ከሁለት ዓመት በላይ ከአዋሽ አርባ እስከ ሰመራ እና በአዲስ አበባ ሜክሲኮ ጨለማ ቤትና ማዕከላዊ እስር ቤት ስንሰቃይ ነበርን።

የሀሰት ክስ ከተከሰስን በኋላ አሁንም በፌደራል ማረሚያ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1174/2012 እና የዚህን አዋጅ ድንጋጌ ለማሰፈፀም በወጣ ደንብ ለጊዜ ቀጠሮ እስረኞች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መብቶች የተሰጡ መሆኑ ህጉ ይደነግጋል።

ይኸውም ፦

1.የጊዜ ቀጠሮ እስረኞች እንደየ ወንጀላቸው አይነት በተለያዩ ግቢዎች ሆነው መጠበቅ እንዳለባቸው ፣

2.በከባድ ወንጀል እና በቀላል ወንጀል የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች በአንድ ግቢ ውሰጥ እንዳይኖሩ፣

3.የተፈረደባቸው እሰረኞች እና በቀጠሮ ላይ የሚገኙ የጊዜ ቀጠሮ እስረኞች በአንድ ግቢ ውስጥ መታሰር እንደሌለባቸው ህጉ ይደነግጋል።

4. በተጨማሪም የተጠረጠሩ ተከሳሾች በመንግሰት ወጭ የተመጣጠነ ምግብ የማግኘት መብት እንዳላቸው ህጉ ይደነግጋል።

5. በተጠረጠሩበት የወንጀል አይነት የተለያዩ የደንብ ልብሶች እንዲኖራቸው ይደነግጋል።

6.የተጠረጠሩ ተከሳሾች መንግስት በሚያዘጋጀው ወይም ራሳቸው በሚያዘጋጁት ማንኛውንም የመገናኛ ዘዴ የውጭና የአለም አሁናዊ ሁኔታ የመከታተል መብት እንዳለባቸው፣

ለተጠርጣሪ እስረኞች የተሰጠ ሌሎችም የመብት ማሰከበሪያ ድንጋጌዎች እንዳሉ ቢታወቅም የፌደራል ማረሚያ ቤቱ የተጠረጠሩ ሰዎች ከፍርድ በፊት ንፁህ ሆኖ የመገመት መብት ያለንን ድንጋጌ በመጣስ እና በመተላለፍ ፦

1.የጥፋተኝነት ውሳኔ እሰካልተሰጠን ድረሰ በነፃነት ከመንቀሳቀስ መብት ወጭ ያለ ማንኛውም ሰብዓዊ እና ድሞክራሲያዊ መብት ተገድበናል።

2.የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽኑ በማረሚያ ቤቱ ማቋቋሚያ አዋጅ እና ድንጋጌ የተሰጡንን ህገ መንግስታዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ በመጣስ በአማራነታችን የታሰርነውን የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን ከቂሊንጦ የቀጠሮ እስረኞች ማቆያ ማዕከል ወደ ኦሮሚያ ክልል ሸገር ሲቲ በሚገኝ ገላን ተብሎ ከሚጠራው አባ ሳሙኤል የሚባል እስር ቤት ወሰደው ለከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተዳርገናል በማለት አቶ አሳምነው ታደሰ የሚከተሉትንም ሀሳቦች ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል።

በተጨማሪም ፦
2.1 የከባድ ፍርደኞች መኖሪያ አካባቢ ተወሰደን ከከባድ ወንጀለኞች ጋር ተቀላቅለን እንድንታሰር ተደርገናል።

2.2 የእኛ የቀጠሮ እስረኞች ሲመጡ መንገዱ ለትራንሰፖረት ምቹ ያልሆነ በመሆኑ የተነሳ ማረሚያ ቤቱ ባዘጋጀው አጋች ቡድን እስከ መስመር ድረስ እንሸኛችሁ በሚል ቤተሰቦቻችን ለዘረፋ ተጋልጠውብናል።

2.3 በዚሁ እስር ቤት የመሰረታዊ ፍላጎት የሚባሉ ነገሮች ቴሌቪዥን፣ ካፌ ፣መፅሀፍ ቤት እና ሌሎች ምንም በሌለበት ተወስደን በህይወት እንዳንኖር እየተደረገ ነው።

መንግስት ምግብ ባለማቅረቡ ለሁለት ቀን ያህል በመራባችን እና ከታሰርንበት ክፍል ሺንት ቤቱ በመሺተቱ የተነሳ አቶ ታደሰ መለሰ እና አቶ ቸርነት እሸቱ ታመው በዛሬው እለት እንኳ በዚህ ፍርድ ቤት ፊት መቅረብ አልቻሉም።

2.4 ቋሚ የሆነ የህክምና አገልግሎት የሚከታተሉ ተጠርጣሪዎች ህክምና ባለመግኘታቸው የከፋ አደጋ ውስጥ ይገኛሉ።

2.5 በቤተሰብ በኩል እንኳ እንዲቀርቡልን የጠየቅናቸው መሰረታዊ ፍላጎቶች እንዳይገቡልን ተከሌክለናል።

2.6 .ለሰው ልጅ የእለት ከእለት ኑሮ ያለ ውሃ ጤነትን መጠበቅ እንደማይቻል እየታወቀ እኛ ከታሰርንበት ጋር በቀን ከአምስት ሰዓት እስከ ሰባት ሰዓት ባለው ጊዜ ውሰጥ ለ15 ደቂቃ ብቻ ውሃ የምትመጣ ቢሆንም በዚች ደቂቃ ውሰጥ ለልብሰ ማጠቢያ ቀርቶ ለመጠጥ እንኳ የማናገኝ ሰለሆነ በህይወት የመኖር እድል የለንም።

5. አቶ ይመር ሙሀመድ ለፍርድ ቤቱ እንዳቀረቡት ፦

እኔ የታሰርኩት በማንነቴ ነው። ወንጀል ሰርቼ አይደለም ።እኔ ለዚች ሀገር በመንግሰት ስራ ረዥም አመት እያገለገልን የተባለው ባለበት ወቅት ከምንሰራበት መሰሪያ ቤት ተወሰደን ከታሰርን በኋላ ሙሉ ቤተሰባችን ተበትኗል ለከፋ ማህበራዊና ቁሳዊ ጉዳት ቤተሰቦቼ ተዳርገዎል ።

ሁለት ልጆቼ ከትምህርት አቋርጠዎል ።ሴቶች ልጆቼ ጎዳና ላይ ወጥተዎል ።ይህ አልበቃ ብሎ እኔ በምርመራ ወቅት በደረሰብኝ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የተነሳ ለደም ግፊት፣ ለስኳር፣ ለኮላሰትሮል፣ እና ለልብ በሽታ፣ ተጋልጨ የቃሊቲ ጠቅላላ ሆሰፒታል ለጳውሎሰ የኢሲጅና የኢኮ ምርመራ እንዳደርግ መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓም ታዞልኝ እስከ አሁን ድረሰ መታከም አልቻልኩም።

ስለዚህ መንግስት የትጥቅ ትግል ላይ የነበሩትን በሰላማዊ መንገድ ተቀብሎ እያሰተናገደ መሆኑን እየገለፀ ባለበት በእኛ ላይ ማንነታችን መሰረት ተደርጎ ለከፋ መከራና ስቃይ እየፈፀመ ነው ።ቤተሰቦቻችንም ለከፋ ችግር እየተዳረጉ ነው።

ህክምና እንኳ እንዳገኝ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥልኝ ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

6. አቶ መኳንንት ተስፋ እንዳቀረቡት ፦

እኛ በማንነታችን ነው ታግተን የተቀመጥነው። የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ተቀብለው አይፈፅሙም ። እኛ በዚሁ ፍርድ ቤት ያስፈቅደነውን እንኳ ጫማ እና የሀይማኖት አልባሳት የእኛን ብቻ በልዩ ሁኔታ ታይተን እንዳይገባ ተከልክለናል።

በማንነታችን ብቻ ከዞን ዞን ያለ ምንም ጥፋት በማዘዎወር ያሰቃዩናል ፤ እኔን ከዞን ከአንድ ወደ ዞን አራት ሲያመጡኝ ምክንያቱን እንኳ አላውቅም።

በእኛ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ያላቸው ኃላፊዎች አሉ።

በአጠቃላይ በእኛ ላይ የሚፈፀም ችግር ሰፊ ሰለሆነ በእናንተ በኩል ተግሳፅ ቢሰጥልን እና በፍርድ ቤት የተፈቀደልን ጫማና አልባሳት እንዲገባልን ትዕዛዝ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን።

7.አቶ ጫኔ ደመቀ ደግሞ እንዳቀረቡት ፦

እኔ በህይወት የመኖርና ያለመኖር ውሰጥ ነኝ። በደረሰብኝ ድብደባ ምክንያት ለከፋ በሽታ ተጋልጫለሁ ።

አልጋ ይዘህ ትታከማለህ ብባልም እንዳልታከም ተደርጌያለሁ።

"እናንተ ዳኞች ለህሊናችሁ ስትሉ ስለ እውነት ስትሉ ፍርድ ስጡ" በማለት ቅሬታቸውን አቅረበዋል።

በአጠቃላይ እኛ የማንነትና የፖለቲካ እስረኞች የሆን ህግ ተጥሶ እየተፈፀሙብን ያለ አስተዳደራዊ በደል እና የመብት ጥሰት እንዲቆምልን የምንጠይቀው ብለው ባቀረቡት መሰረት ፦

1.ከከባድ ወንጀለኞችና ፍርደኞች ጋር ተቀላቅለን እንድንኖር መደረጉ ሆን ተብሎ በማንነት ላይ ተመሰርቶ የተደረገ ጥቃትና በደል ስለሆነ ከፍርደኛ ክልል የተወሰዱ የፖለቲካና የህሌና እስረኞች ህጉ ወደ የሚፈቅደው የጊዜ ቀጠሮ እስረኞች ማቆያ ማዕከል እንዲመለሱን፣
2.በማንነታችን ላይ የተፈፀሙብን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የአለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና የሚመለከታቸው አካላቶች በየ አለንበት መጥተው እንዲያጣሩልንና ምርመራ ተደርጎ የተደረገብን አማራ ተኮር ጥቃት መሆኑ ተረጋግጦ ድርጊቱን እንዲወገዝ ሲሉ ለቀይ መስቀል ፣ ለኢሰመኮ እና ለመሳሰሉት ትዕዛዝ እንድሰጥልን በማለት አቤቱታቸውን አቅርበዋል።

(አውሎግሶን አንድነት ፣ ሚያዝያ 6/2018)
2
ሰበር ዜና!

ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ከተማን በከፊል በቁጥጥር ስር በማዋል ታላቅ ድል አስመዘገበ::

ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር በጥላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በራያ ቆቦ ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎችንና የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና መቀመጫን ቆቦ ከተማን በከፊል ተቆጣጥሮ ውሏል።

በተጨማሪም የ102ኛ ኮር እስከ ቆቦ ከተማ ዘልቆ በመግባት 105 የፌደራል ፖሊስና ከ250 በላይ የመከላከያ ሰራዊት ደምስሷል።

ተወርዋሪዋ ልዩ ዘመቻ በቀይ አፈር በነበረው ተጋድሎ 89 የመከላከያ ሰራዊት ደምስሳለች። ጠላት ከጧት ጀምሮ በድሮን፣ በቢ-ኤም፣በዙ-23፣ በመድፍና በታንክ የተጠናከረ ማጥቃት ቢያደርግም አይበገሬዎቹን ማቆም ተስኖት ውሏል።

የወገን ሀይል የ102ኛ ኮር እንድሁም ተወርዋሪ የሆነችው ልዩ ዘመቻ በጥምረት ባደረጉት ማጥቃት በሰሜን ወሎ ቆቦ ከተማን በከፊል በመቆጣጠር የአብይ አህመድን ስልጣን አስጠባቂ የፌደራል ፖለስና የመከላከያ ሰራዊት በከፍተኛ ደረጃ ተመትቶ ሙትና ቁስለኛውን በአንፑላን ወደ ቆቦ ሆስፒታል ሲያመላልስ ውሏል።

በጧት የጀመረው ተጋድሎ በጥላት ላይ ወታደራዊና ፖለቲካዊ የስበት ማዕከሉን በመለየት የ102ኛ ኮር በጮቢ በር የጥላትን ድሽቃ በወገን ሞርተር ሙሉ በሙሉ በማውደም፣ በካራይላና በጠዘጠዛ ካምፕ በከፍተኛ ደረጃ እርምጃ የተወሰደበት ሲሆን በተወርዋሪዋ ልዩ ዘመቻ በቀይ አፈርና አባሆይ ጋሪያ በተመሳሳይ የወገን ጦር የሀይል የበላይነትን በመውሰድ ከላይ የተጠቀሱትን የገጠር ቀበሌዎችንና ከተሞች በቁጥጥር ስር አውሏል።

በመጨረሻም የወገንን ሀይል መቋቋም ያቃተው የአብይ አህመድ ጨፍጫፊው አገዛዝ 01 ቆቦ ዙሪያ የቀመሌ ተክለሀይማኖት ቤተ-ክርስቲያንን ሆን ብሎ በመድፍ በመምታት እንድሁም የንፁህ አማራዎችን ቤት ታርጌት በማድረግ ፋኖን ለማስለቀቅ በሚል ስሌት የበርካታ ሲቪሊያንን ህይወት በከባድ መሳሪያ ቀጥፏል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 7/2018 ዓ/ም
2🙏2
ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር የትንሳኤ በአልን በማስመልከት ተሃድሶ በማድረግ በትግሉ ሁኔታ ላይ ምክክር አደረገ::

ሚያዚያ 6/2018 የትንሳኤን በአልን በማስመልከት በደማቅ ሁኔታ ተሃድሶዉን ሲያደርግ በጃማ ቀጠና አካባቢ ያሉ የአገር ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶችና የአባት አርበኞችን ጨምሮ ነው።በዚሁ ተሃድሶ ኘሮግራም ላይ ያሉ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ፀረ አማራ አገዛዙ አማራ ህዝብ ላይ እያደረሰዉ ያለዉን የንፁኋን ሞት እና ንብረት ላይ በፁኑ አዉግዘዋል።

የክፍለ ጦሩ አመራሮች በተሃድሶው የአማራን ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ ብርቱ ተጋድሎ ላይና በድል ዋዜማ እንገኛለን በቀጣይም በቁርጠኝነት ታግለን ለድል እንበቃለን በሚል ከህዝባችን ጋር ተግባብተናል ብለዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 07/2018 ዓ.ም
🙏3