ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ነፃ በወጡ ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይቶች እየተደረጉ ነው።

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ በተከታታይ በርካታ ቦታዎች ላይ ውጊያ በመክፈት ሰዴን ጨምሮ ከተሞችን ነፃ እያደረገ ይገኛል። በዚህም በርካታ ወታድራዊ ድሎችን ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን ወታደራዊ ድሉን ወደ ፖለቲካዊ ድል ለመቀየር የሕዝብ ግንኙነት ስራ አስፈላጊ በመሆኑ ከሰዴ ማህበረሰብ ጋር ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።
የቴዎድሮስ ዕዝ አመራሮች ፣ የ201ኛ ኮር አመራሮች ፣የ54ክፍለጦር አመራሮች እና ጊዜአዊ መንግስት አመራሮች በተገኙበት ሕዝባዊ ውይይቱ ተደርጓል።
በስብሰባውም የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች፣ ፋኖ የደረሰበት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ የእድገት ደረጃ ፣ አገዛዙ እየደረሰበት ያለውን ዲፖሎሲአዊ ውድቀት እና የማህበረሰባችን ሰላምና ደህንነት መጠበቅን በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰጧል።
ማህበረሰቡም አገዛዙ ሲያደርስበት የነበውን ጭቆና በመዘርዘር እንኳን መጣችሁልን የትንሳኤን በዓል በሰላም እንድንውል ልታደርጉን ነው በማለት ለፋኖ ምስጋና አቅርቧል።

ሴት ልጆቻችን በአብይ ሠራዊት ተደፍረውብናል ፣ሀብት ንብረታችን ተዘርፏል ፣ የምርጫ ካርድ ካላወጣችሁ እየተባልን ተደብድበናል፣ በየምክንያቱ የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ እየተባልን ተደብድበናል የተገደለም አለ በማለት አገዛዙ ያደረሰባቸውን በደል ተሰብሳቢዎቹ ገልፀዋል።
ወጣቱም እንሰለጥናለን ቤተሰባችንንና የአማራን ሕዝብ ለመታደግ መክፈል ያለብንን ለመክፈል አብረናችሁ እንቆማለን ሲል ድምፁን አሰምቷል።

የፋኖ ትግል የሕዝብ ትግል መሆኑን በተግባር ያሳየ መድረክ መሆኑን ያሳየ ነበር ሲሉ አስተያይት ሰጪዎች ገልፀዋል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም!
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 02/2018 ዓ.ም
1
ማሳሰቢያ፦ ለመላው ሰራዊታችን!!
ሚያዚያ 03/2018ዓም

በአስደናቂ ተጋድሏችን እየተሰባበረ ያለው የአገዛዙ ሰራዊት የወገን ኃይል ላይ የተደራጀ ማጥቃት እንዲፈፅም ተደጋጋሚ ስምሪት ቢሰጥም እግረኛው ስራዊት የተሰጠውን ስምሪት መፈፀም አልቻለም። አንድም የሚደርስበትን ምት በመፍራት ሁለትም የብልፅግና ጦርነት ዓላማ የሌለው መሆኑን በመረዳት።

በዚህ ምክንያት የወገን ሰራዊት ከበዓል ጋር የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴወች እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አገዛዙ የጅምላ ጥቃት ለመፈፀም በሁሉም አካባቢወች የድሮን ስምሪቶች ሰጥቷል።

የዩናይትድ አረብ ኢምሬት አየር ኃይል አባላት የድሮን እና የጀት ጥቃት ለመፈፀም ከሌላው ጊዜ በተለዬ ሁኔታ የወትሮ ዝግጁነት ላይ ይገኛሉ።

በመሆኑም መላው ሰራዊታችን እና አመራሩ ይህንን የድሮን እና የአየር ኃይል ስምሪት ታሳቢ ያደረጉ እንቅስቃሴወች እንዲያደርጉ እና በተለይም በዓል ለማክበር የሚደረጉ ክንውኖች እጅጉን ጥንቃቄ የተሞላባቸው እንዲሆኑ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በጥብቅ ያሳስባል!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር 21ኛ ክፍለ ጦር የአገዛዙን ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ድል ተጎናፀፈ።

ጠላት 21ኛ ጦርን አጠፋለሁ በሚል አጉል ምኞት በሶስት አቅጣጫ ማለትም አገዉየ ሰቀላ ፣ አጤሁዳድ እና ማዉሬ ኪዳህነ ምህረት በሚባሉ ቦታወች አስፍቶ ቢመጣም ንስሮቹ የዘላለም ሲሳይ ግርፎች እንደ ቃርያ ሲያረግፉት ዉለዋል።

ወጊያዉ ዛሬ ማለትም ሚያዚያ 2/2018 ዓ.ም የተደረገ ሲሆን በዚህም ከ30 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት እስከወዲያኛዉ ሲሸኝ ከ20 ያላነሰዉ ደግሞ ቁስለኛ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ጠላትም አስክሬኑን እስከ ምሽት 3:00 ድረስ በየአቅጣጫዉ እየፈለገ ሲቀብር አምሽቷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ገልጿል::

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 2/2018ዓ.ም
ሚያዝያ 03 /08/2018 ዓ.ም

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ ለኦፕሬሽን የተላለፈ የጥንቃቄ መመሪያ!!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ፣ ለመላው የአማራ ህዝብ እና በዱር በገደሉ የአማራን ህዝብ የህልውና ጥያቄ ለማስመለስ ለመትዋዱቁ የፋኖ ሰራዊት አባላት በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን!!

መራሹ የብልፅግናው አገዛዝ የአማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት የከፈተውን መጠነ-ሰፊ ጥቃት በክንዳችን እየተመከተ ቢሆንም፣ ጠላት በበዓል ሰሞን ያለውን የህዝብ እንቅስቃሴ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የክህደት ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጅት ማድረጉን የውስጥ መረጃዎቻችን አረጋግጠዋል። በመሆኑም በዕዝ በኮር፥ በክፍለ ጦር የሻለቃ አመራሮችንና የሰራዊት አባሎች የሚከተለውን አስቸኳይ ጥንቃቄ እንዲደረግ መልክቴን እንደሚከተለው አስተላልፋለሁ።

1. ማንኛውም የሰራዊት አባልም ሆነ አመራር በበዓሉ ሰሞን የሚሰጥ የፈቃድ ዕረፍት የማይኖር ሲሆን ሰራዊቱ በሙሉ በያለበት ቀጠና በንቃትና በጥርነፋ እንዲቆይ

2. በበዓል ስም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለደፈጣ ጥቃቶችና ለንብረት ዝርፊያ ምቹ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥበቃ ማድርግ

3. የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ሰርጎ ገቦችን በማስገባት እና መረጃ በመሰብሰብ ስራዊታችን እና ህዝባችን ላይ ጥቃት ለማድረስ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የውስጥ መረጃዎች ያመላክታሉ በመሆኑም ህዝባችን እና ሰራዊታችን ይህንን ጉዳይ በጥብቅ እንዲከታተል አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው እክል በአፋጣኝ እንዳታሳውቁ ይሁን

4. ተስፋ የቆረጠው መራሹ የብልግና አገዛዝ የሰራዊቱን ስብስብ በመረጃ አረጋግጦ የድሮን ጥቃት ለመሰንዘር እያደባ ስለሆነ የተለመደውን ጥንቃቄ እንዲደርግ።

5. ሰራዊታችን ​ከሲቪሉ ማህበረሰብ ጋር በሰፊው መቀላቀልና በግልጽ ስፍራዎች መሰባሰብ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

6. ጠላት የሰራዊቱን መዘናጋት ጠብቆ ድንገተኛ ወረራ ለማድረግ ያቀደ ስለሆነ ጥንቃቄ እንዲደረግ።

​7. በሁሉም ቀጠናዎች የቀንና የሌሊት የደፈጣ ጥበቃ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

8. የጥንቃቄ መመሪያው ለመላው ሰራዊታችንን ተግባራዊ እንዲሆን እና አስቸኳይ የጠላትን እቅድ ቀድመን በመረዳት የህዝባችንን በዓልና የሰራዊታችንን ደህንነት እናስጠብቃለን።

"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ

የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ምክትል ወታደራዊ አዛዠ ለኦፕሬሽን !!
የትንሳዔ በዓል የገበያ ውሎን ለማስተጓጎል በሁለት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ሰራዊት በፋኖ የተቀናጀ ጥቃት እንደተፈፀመበት ክፍለጦሩ ገለፀ።

ሚያዚያ 03/2018ዓ.ም

ሀይማኖታዊ በዓላትን በማስተጓጎል የሚታወቀው የብልፅግናው አገዛዝ ዛሬም እንደተለመደው በነገው ዕለት በህዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ በድምቀት ለሚከበረው የትንሳዔ በዓል ዋዜማ የህዝባችንን በነፃ ወጥቶ የመሸመት የቅዳሜ የገበያ ውሎ እንቅስቃሴን ለማስተጓጎል የብልፅግናው አገዛዝ በዘራፊ ሰራዊቱ በኩል ሞክሯል።

ህዝባዊ ቅቡልነቱን ያጣው የአገዛዙ ሰራዊት መነሻውን ከመንዝ ማማ ወረዳ ሞላሌ ከተማ እንዲሁም ከመንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ በማድረግ ወደ ሸሾ የገጠር ከተማ ያመራ ሲሆን በቀጠናው በሚገኙ የአርበኞች ጦር ሰራዊት እና በምኒሊክ ክፍለጦር የተቀናጀ ጥቃት መፈፀሙን ክፍለጦሩ አስታውቋል።

ከጠዋቱ 1:00 ጀምሮ እስከ እኩለ ቀን ድረስ በተደረገው አውደ ውጊያ የአገዛዙ 104ኛ ክፍለጦር እና እራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራው ስብስብ የአማራ ህዝብ ነፃ አውጭ በሆነወ በጀግናው የአማራ ፋኖ ሰራዊት የተቀናጀ ውጊያ ጉዳት አስተናግዷል።

እየተካሔደ ባለው የቅንጅት ውጊያ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የአፄ ምኒሊክ ክፍለጦር አሃድ በሆኑት የአባተ 1ኛ ሻለቃ እና የአርበኞች ጦር ሰራዊት የህዛባችን የቁርጥ ቀን ደራሽ መሆናቸውን ያሳዩበት ተጋድሎ እያደረጉ መሆኑን ክፍለጦሩ በላከው የግንባር መረጃው አስታውቋል።

መረጃው👇
የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ነው

''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን

የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
3
"ጽናት ለትንሳኤ፣ መስዋዕትነት ለነፃነት!!"

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ በተለይም የህልውና ተጋድሎ እያደረገ ላለው ህዝባችንና ሰራዊታችን እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ።

~ለጀግናው የፋኖ ሰራዊታችን፦
በየዱር ገደሉና በየውጊያ ግንባሩ የምትገኝ የነፃነት ፋና ወጊው ሰራዊታችን፤ የትንሳኤ በዓል ከጨለማ በኋላ ብርሃን፣ ከመከራ በኋላ ደስታ መኖሩን ማብሰሪያ ነው። አንተ ዛሬ እየከፈልክ ያለኸው መስዋዕትነት የህዝባችንን የነፃነት ትንሳኤ ለማረጋገጥ መሆኑን ድርጅታችን አፋብን በኩራት ይገነዘባል። በጠላት ምሽግ ላይ ሆነህ በዓሉን ለምታከብር ጀግናው ሰራዊታችን፣ ብርታቱና ድሉን እንመኛለን።

~ለተከበረው ህዝባችን፦
በትግሉ ሂደት ውስጥ ለደረሰብህ መከራና ግፍ ትዕግስትህና ጽናትህ የሁልጊዜም መመኪያችን ነው። ትንሳኤው የመከራ ማብቂያና የታሪካዊ ፍትህ መጀመሪያ እንዲሆንልህ እየተጋደልን እየተፋለምን እንገኛለን። ይህ በዓል በእምነትና በአንድነት የምንበረታበት እንዲሆን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

~ለደጋፊዎቻችንና ለበዓሉ ተሳታፊዎች በሙሉ፦
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ሆናችሁ ለትግሉ ድጋፋችሁን የምታበረክቱ ወገኖቻችን፤ የትንሳኤ በዓልን ስናከብር የተሰዉ ጀግኖቻችንን ቤተሰቦች በመጠየቅ፣ የተፈናቀሉትንና የተቸገሩትን በማሰብና በመርዳት እንዲሆን እናሳስባለን። የፋኖ ክንድ የሚበረታው በእናንተ አጋርነት ነውና።

~በመጨረሻም፦
እንደ አማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፤ ህዝባችን የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ቀልብሰን፣ የፍትህና የእኩልነት ትንሳኤ እስኪረጋገጥ ድረስ ትግላችን የማይቆም መሆኑን ዳግም እናረጋግጣለን።

~ድል ለአማራ ህዝብ!!
~ክብር ለተሰዉ ጀግኖቻችን!!
~መልካም በዓል!!
~ሚያዝያ 2018 ዓ.ም!!
~የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወታደራዊ ቃል አቀባይ አርበኛ አበበ ሙላቱ