ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
"ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!"

ሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም የምስራቅ አማራ ፋኖ አብሪ ኮከብ አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ስለ አማራ ህዝብ ህልዉና መስዋዕትነትን የተቀበለበት ዕለት ነው!

አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ የህልዉና አደጋ ለመቀልበስና የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ "ሕልው" ለማድረግ ዉድ ህይወቱን የሰዋበት ይህንን ቅዱስ የህልዉና ትግል "ሀ" ብሎ ያስጀመረበትና ችቦ የለኮሰበት ቀን ነው::

ገና በለጋ እድሜው የቀድሞዉን የሃገር መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀል ትግል የጀመረው አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከእግረኛ እስከ ሻምበልነት ማዕረግ ድረስ እንዲሁም የቀድሞው አግዓዚ ኮማንዶ አባል በመሆን ከሃገር ዉስጥ እስከ ዉጭ አገር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ድረስ ወጣትነቱን ለሃገሩ ገብሯል::

አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ባጋጠመው ከባድ ቁስል ምክንያት በጡረታ ያገለለ ሲሆን ከ 2010 ዓ.ም ህዝባዊ እምቢተኝነት ቡሃላ ወጣቶችን በስፖርት በአካል ብቃትና በስነ ልቦና የማንቃት ስራ እየሰራ በኋላም ከነ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ጋር የራያ ፋኖን በመመስረትና በመቀላቀል ፀረ ወያኔ ትግሉን ተቀላቅሎ ሁሉንም ተጋድሎዎች በመሪነትና በአሰልጣኝነት በድል ተወጥቷል:: የቀድሞው ምስራቅ አማራ ፋኖ ስልጠና መምሪያን እየመራ በመካነሰላም በደሴ በሃይቅ በወልድያ በቆቦና በራያ አላማጣ በርካታ ታጋዮችን ያሰለጠነና ያፈራ ሲሆን የአሁኑን የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል በሰራዊትና በመሪነት ላይ ያሉ በርካታ ጀግኖችን አፍርቷል:: በርካታ ጀግኖችን እያሰለጠነና እያስታጠቀ መሆኑን ያየው አገዛዙም በጥላቻ አይን ያየው ጀመረ::

የሰሜኑን ጦርነት እነ አብይ አህመድና በድኑ ብአዴን በፕሪቶሪያው የድራማ ስምምነት ከቋጩት በኋላ የአማራ ፋኖን ህግ ማስከበር በሚል ሽፋን ትጥቅ ለማስፈታት በፌደራልና በክልል ደረጃ መከላከያ በማዝመት ዘመቻ በጀመሩበት ጊዜ ግጭቶች መጀመራቸው ይታወቃል:: በዚህም በተለያዩ ጊዜያት የምስራቅ አማራ ፋኖ ሰራዊትና አመራሮችን ቀዳሚ ኢላማ ያደረገ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጠለ::

አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከነዚህ የፖለቲካ ጥያቄ ካነገቡ ግጭቶች ጋር ተያይዞ የብርሃኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊት ላይ ይመለከት በነበረው ፀረ-ህዝብ ተግባርና ነዉር እጅግ ይበሳጭና ያዝን ስለነበር በአንድ ከአብይ አህመድ ጀኔራሎች ጋር ቆቦ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ በተደረገ ስብሰባ የህዝብ ናችሁ ወይስ የብልፅግና? በሚል ይጠይቃቸዋል:: ያ ከራሱ ህዝብ አልፎ ሰላም ማስከበር ጎረቤት አገር ሄዶ ረሽኑን ለህዝብ ሰጥቶ ቅጠል በልቶ የሚያድር ሰራዊት የት ገባ? ሲል በመጠየቅ እስከ ሰላም ማስከበር በደረሰ ተልዕኮው የነበረዉን ህዝባዊነት በመጥቀስ የግፈኞች ዙፋን ጠባቂ መሆናቸዉንና ነውራቸዉን ነገራቸው::

አይቀሬዉን ጦርነት የተገነዘቡትና የተረዱት የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ከወሎ ምስራቅ አማራ ፋኖ ከሸዋ ከጎጃምና ከጎንደር ፋኖዎች ጋር በመሆን ጎንደር ሱዳን ጠረፍ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን በመመስረት አርበኛ ሰፈር መለሰን ዋና አዛዥ እና ዋርካው ምሬ ወዳጆን ምክትል አዛዥ አድርጎ በመምረጥ እንቅስቃሴ ጀመረ:: ምስራቅ አማራ ፋኖ አጠቃላይ የትግል ጉዞዉን የሚዘክር ታላቅ የተሃድሶ ዝግጅት የምክር ቤቱ ዋና አዛዥ አርበኛ ሰፈር መለሰ እንዲሁም ከፍተኛ የመከላከያ፣ የልዩ ሃይል፣ የብልፅግና አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እና የሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም መላ ሰራዊቱና ህዝብ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አከበረ::

በዝግጅቱም ምስራቅ አማራ ፋኖ የአማራ ህዝብ በክልሉና በተለይ ከክልሉ ዉጭ እየደረሰበት ያለዉን ግፍና ጭፍጨፋ በማንሳትና በማስታወስ የአማራ ህዝብ የህልዉና አደጋ ተጋርጦበታል "ትግል ይቀጥላል" የሚል መልዕክት ለታዳሚው ለሰራዊቱና በዉስጥም በዉጭም ላለው መላው የአማራ ህዝብ በህዝብ ግንኙነቱ አርበኛ አበበ ፈንታው በኩል መልዕክት አስተላለፈ:: ይህንን ተከትሎም ከተሃድሶ ቡሃላ ትጥቅ ያስረክቡናል ይበተናሉ ስንል እንዴት "ትግል ይቀጥላል" ይላሉ በሚል የአገዛዙ ሹማምንት ከፍተኛ ንዴትና ብስጭት ብሎም ድንጋጤ ዉስጥ ገቡ::

ይህንን ተከትሎም አገዛዙ የምስራቅ አማራ ፋኖ ቁስለኞችን ሳይቀር ሰራዊቱን ባገኘበት ምቹ አጋጣሚ ሁሉ መረሸን ጀመረ:: የለየለት ግጭትም ተጀመረ:: ጥቃት የማይወደው አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙም ሰራዊቱን በተጠንቀቅ እንዲቆምና ለሚመጣው ሁሉ ነገር ተመጣጣኝ አፀፋ እንዲሰጥ ድርጅቱና መሪው ዋርካው ምሬ ወዳጆ ያወረደዉን መመሪያ በመቀበል በአንድ ወቅት ምስራቅ አማራ ፋኖ ካምፕ ድረስ ከነ አጃቢዎቹ በፓትሮል የመጣን ኮሎኔል ከመኪናው ወርዶ እስኪፈረጥጥ ድረስ ቆፍጠን ያለ እርምጃዉን ጀመረ::

ምስራቅ አማራ ፋኖም ሰራዊቱን በምዕራብ በኩል ከራያ ቆቦ ጮቢ በር እስከ በላጎ እንዲሁም ወልድያ ዙሪያ ሳንቃና መቻሬ እንዲሁም ሙጃ ድረስ ገዥ መሬቶች ላይ በማስፈር ለአይቀሬው ፍልሚያ ተዘጋጀ:: በበርካታ አካባቢዎች ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ የነበረዉን ከፍተኛ ዉጥረትና የአማራ ልዩ ሃይል በበድኑ ብአዴን እና በነ አብይ አህመድ ሴራ መፍረሱን ተከትሎ ሚያዚያ 1/2015 አ.ም ረፋድ ላይ ቆቦ ከተማ በተጀመረ ከባድ ዉጊያ የአሁኑን የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ጅማሮ ችቦ ለኩሶ አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ መስዋዕትነት ተቀበለ:: የህልዉና ተጋድሎዉም ሸዋ በነበሩ የምስራቅ አማራ ፋኖ አሃዶችና የሸዋ ፋኖ አናብስቶች ተቀጣጥሎ ዛሬ በመላው አማራ የደረሰበት ደረጃ ደረሰ::

አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ስለ አማራ ህዝብ ህልዉና ቀይ መስመር ያለፈዉን በምድርም ይሁን በሰማይ ዘመኑ ያፈራዉን ጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው የታጠቀዉን ጨፍጫፊና ግፈኛ ፋሽስታዊ ስርዓት እስከ መጨረሻው ህቅታ ተናንቆ በጀግንነት ተሰዉቶ ችቦ ለኩሶና አስጀምሮ ይህንን የአማራ ህዝብ ቅዱስ የህልዉና ትግል ለዛሬ ካበቁ ጀግኖች መካከል ግንባር ቀደም ሆኖ አልፏል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

የተሰዋህለትን አላማ ከግብ እናደርሳለን!
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!
አፋብን በወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 1/2018 ዓ.ም
👍3
በላስታ ግንባር ይባር አከባቢ ፋኖ በወሰደው የስቦ መምታት እርምጃ አንድ አመራርን ጨምሮ ከ30 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ተደመሰሱ!

በምስራቅ አማራ ቀጠና ላስታ ግንባር ይባር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የጥራሪ ክፍለጦር አርበኞች በወሰዱት የተቀናጀ የስቦ መምታት እርምጃ የአገዛዙ 45ኛ ክፍለ ጦርን ክፉኛ በመምታት ድል አስመዝግበዋል።

በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር ስር የሚገኙት የጥራሪ ክፍለ ጦር አርበኞች ትናንት ሚያዚያ 01/2018 ዓ/ም እስከ ምሽት ድረስ በወሰዱት እርምጃ አንፀባራቂ ድል ተቀዳጅተዋል።

ከግዳን ሙጃ ከተማ ተነስቶ ወደ ይባርና አምበሳው ከተሞች በፋኖ በተዘጋጀለት ወጥመድ ሰተት ብሎ የገባው የጠላት ኃይል፡ በ360 ዲግሪ ተከቦ ክፉኛ ተቀጥቅጦ ተሸመድምዶ ተብታትኗል።

በጥራሪ ክፍለ ጦር ስር ከሚገኙት ከተመስገን ሬጅመንት፣ ከአቡነ ዮሴፍ፣ ከኤፍሬም እና ከትዕግስቱ ሬጅመንቶች የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ናቸው የስቦ መምታት እርምጃውን በመውሰድ የጠላት አከርካሪን የሰበሩት።

በዚህ ተጋድሎ ማዕረጉና ስሙ ለጊዜው በውል ያልታወቀ አንድ ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ ከአሥር በላይ ወታደሮች ሲገደሉ፡ የአመራሩ አስከሬን ዛሬ ሚያዚያ 02/2018 ዓ/ም በከፍተኛ ወታደራዊ አጀብ በሙጃ ማርያም ቤተክርስቲያን ተቀብሯል።

በተጨማሪም ከ20 በላይ ወታደሮች ከቀላል እስከ ከባድ የቆሰሉ ሲሆን፡ የጦር መሣሪያዎችና ገዢ ወታደራዊ ስፍራዎች በጥራሪ ጀግኖች ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሽንፈትን የተከናነበው የአገዛዙ ሰራዊት፡ ቂሙን በንፁኋን ላይ ለመወጣት ሞርታር፣ ቢኤም እና ዙ-23 በመጠቀም በእንጃፋትና በመለየ አከባቢ ነዋሪዎች ላይ የሽብር ጥቃት ሲፈፅም ውሏል።

ይኸው የነውረኛው ብልፅግና አገዛዝ ተላላኪ ኃይል፡ በህዝቡ ላይ የኢኮኖሚና የስነልቦና ጫና ለማድረስ ከከተማ ወደ ገጠራማ አከባቢዎች ሸቀጦችና የቅባት እህሎች እንዲሁም የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች እንዳይገቡ መንገዶችን መዝጋቱ ተነግሯል።

የጥራሪ ክፍለ ጦር አርበኞች ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎችን በመቆጣጠር በጠላት ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው ቀጥለዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ሚያዚያ 02/2018 ዓ.ም
ነፃ በወጡ ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይቶች እየተደረጉ ነው።

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ በተከታታይ በርካታ ቦታዎች ላይ ውጊያ በመክፈት ሰዴን ጨምሮ ከተሞችን ነፃ እያደረገ ይገኛል። በዚህም በርካታ ወታድራዊ ድሎችን ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን ወታደራዊ ድሉን ወደ ፖለቲካዊ ድል ለመቀየር የሕዝብ ግንኙነት ስራ አስፈላጊ በመሆኑ ከሰዴ ማህበረሰብ ጋር ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።
የቴዎድሮስ ዕዝ አመራሮች ፣ የ201ኛ ኮር አመራሮች ፣የ54ክፍለጦር አመራሮች እና ጊዜአዊ መንግስት አመራሮች በተገኙበት ሕዝባዊ ውይይቱ ተደርጓል።
በስብሰባውም የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች፣ ፋኖ የደረሰበት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ የእድገት ደረጃ ፣ አገዛዙ እየደረሰበት ያለውን ዲፖሎሲአዊ ውድቀት እና የማህበረሰባችን ሰላምና ደህንነት መጠበቅን በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰጧል።
ማህበረሰቡም አገዛዙ ሲያደርስበት የነበውን ጭቆና በመዘርዘር እንኳን መጣችሁልን የትንሳኤን በዓል በሰላም እንድንውል ልታደርጉን ነው በማለት ለፋኖ ምስጋና አቅርቧል።

ሴት ልጆቻችን በአብይ ሠራዊት ተደፍረውብናል ፣ሀብት ንብረታችን ተዘርፏል ፣ የምርጫ ካርድ ካላወጣችሁ እየተባልን ተደብድበናል፣ በየምክንያቱ የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ እየተባልን ተደብድበናል የተገደለም አለ በማለት አገዛዙ ያደረሰባቸውን በደል ተሰብሳቢዎቹ ገልፀዋል።
ወጣቱም እንሰለጥናለን ቤተሰባችንንና የአማራን ሕዝብ ለመታደግ መክፈል ያለብንን ለመክፈል አብረናችሁ እንቆማለን ሲል ድምፁን አሰምቷል።

የፋኖ ትግል የሕዝብ ትግል መሆኑን በተግባር ያሳየ መድረክ መሆኑን ያሳየ ነበር ሲሉ አስተያይት ሰጪዎች ገልፀዋል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም!
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 02/2018 ዓ.ም
1
ማሳሰቢያ፦ ለመላው ሰራዊታችን!!
ሚያዚያ 03/2018ዓም

በአስደናቂ ተጋድሏችን እየተሰባበረ ያለው የአገዛዙ ሰራዊት የወገን ኃይል ላይ የተደራጀ ማጥቃት እንዲፈፅም ተደጋጋሚ ስምሪት ቢሰጥም እግረኛው ስራዊት የተሰጠውን ስምሪት መፈፀም አልቻለም። አንድም የሚደርስበትን ምት በመፍራት ሁለትም የብልፅግና ጦርነት ዓላማ የሌለው መሆኑን በመረዳት።

በዚህ ምክንያት የወገን ሰራዊት ከበዓል ጋር የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴወች እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አገዛዙ የጅምላ ጥቃት ለመፈፀም በሁሉም አካባቢወች የድሮን ስምሪቶች ሰጥቷል።

የዩናይትድ አረብ ኢምሬት አየር ኃይል አባላት የድሮን እና የጀት ጥቃት ለመፈፀም ከሌላው ጊዜ በተለዬ ሁኔታ የወትሮ ዝግጁነት ላይ ይገኛሉ።

በመሆኑም መላው ሰራዊታችን እና አመራሩ ይህንን የድሮን እና የአየር ኃይል ስምሪት ታሳቢ ያደረጉ እንቅስቃሴወች እንዲያደርጉ እና በተለይም በዓል ለማክበር የሚደረጉ ክንውኖች እጅጉን ጥንቃቄ የተሞላባቸው እንዲሆኑ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በጥብቅ ያሳስባል!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር 21ኛ ክፍለ ጦር የአገዛዙን ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ድል ተጎናፀፈ።

ጠላት 21ኛ ጦርን አጠፋለሁ በሚል አጉል ምኞት በሶስት አቅጣጫ ማለትም አገዉየ ሰቀላ ፣ አጤሁዳድ እና ማዉሬ ኪዳህነ ምህረት በሚባሉ ቦታወች አስፍቶ ቢመጣም ንስሮቹ የዘላለም ሲሳይ ግርፎች እንደ ቃርያ ሲያረግፉት ዉለዋል።

ወጊያዉ ዛሬ ማለትም ሚያዚያ 2/2018 ዓ.ም የተደረገ ሲሆን በዚህም ከ30 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት እስከወዲያኛዉ ሲሸኝ ከ20 ያላነሰዉ ደግሞ ቁስለኛ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ጠላትም አስክሬኑን እስከ ምሽት 3:00 ድረስ በየአቅጣጫዉ እየፈለገ ሲቀብር አምሽቷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ገልጿል::

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 2/2018ዓ.ም
ሚያዝያ 03 /08/2018 ዓ.ም

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ ለኦፕሬሽን የተላለፈ የጥንቃቄ መመሪያ!!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ፣ ለመላው የአማራ ህዝብ እና በዱር በገደሉ የአማራን ህዝብ የህልውና ጥያቄ ለማስመለስ ለመትዋዱቁ የፋኖ ሰራዊት አባላት በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን!!

መራሹ የብልፅግናው አገዛዝ የአማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት የከፈተውን መጠነ-ሰፊ ጥቃት በክንዳችን እየተመከተ ቢሆንም፣ ጠላት በበዓል ሰሞን ያለውን የህዝብ እንቅስቃሴ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የክህደት ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጅት ማድረጉን የውስጥ መረጃዎቻችን አረጋግጠዋል። በመሆኑም በዕዝ በኮር፥ በክፍለ ጦር የሻለቃ አመራሮችንና የሰራዊት አባሎች የሚከተለውን አስቸኳይ ጥንቃቄ እንዲደረግ መልክቴን እንደሚከተለው አስተላልፋለሁ።

1. ማንኛውም የሰራዊት አባልም ሆነ አመራር በበዓሉ ሰሞን የሚሰጥ የፈቃድ ዕረፍት የማይኖር ሲሆን ሰራዊቱ በሙሉ በያለበት ቀጠና በንቃትና በጥርነፋ እንዲቆይ

2. በበዓል ስም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለደፈጣ ጥቃቶችና ለንብረት ዝርፊያ ምቹ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥበቃ ማድርግ

3. የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ሰርጎ ገቦችን በማስገባት እና መረጃ በመሰብሰብ ስራዊታችን እና ህዝባችን ላይ ጥቃት ለማድረስ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የውስጥ መረጃዎች ያመላክታሉ በመሆኑም ህዝባችን እና ሰራዊታችን ይህንን ጉዳይ በጥብቅ እንዲከታተል አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው እክል በአፋጣኝ እንዳታሳውቁ ይሁን

4. ተስፋ የቆረጠው መራሹ የብልግና አገዛዝ የሰራዊቱን ስብስብ በመረጃ አረጋግጦ የድሮን ጥቃት ለመሰንዘር እያደባ ስለሆነ የተለመደውን ጥንቃቄ እንዲደርግ።

5. ሰራዊታችን ​ከሲቪሉ ማህበረሰብ ጋር በሰፊው መቀላቀልና በግልጽ ስፍራዎች መሰባሰብ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

6. ጠላት የሰራዊቱን መዘናጋት ጠብቆ ድንገተኛ ወረራ ለማድረግ ያቀደ ስለሆነ ጥንቃቄ እንዲደረግ።

​7. በሁሉም ቀጠናዎች የቀንና የሌሊት የደፈጣ ጥበቃ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

8. የጥንቃቄ መመሪያው ለመላው ሰራዊታችንን ተግባራዊ እንዲሆን እና አስቸኳይ የጠላትን እቅድ ቀድመን በመረዳት የህዝባችንን በዓልና የሰራዊታችንን ደህንነት እናስጠብቃለን።

"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ

የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ምክትል ወታደራዊ አዛዠ ለኦፕሬሽን !!