Forwarded from 🌋👍
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፦ በላይ ዘለቀ እዝ፣ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር፣ የጥቁር አንበሳ ክፍለ ጦር የኮማንዶ አባላት ምርቃት
❤1
የድል ዜና!!!
3ኛ ቀኑን ባስቆጠረው እልህ እስጨራሽ አውደ ውጊያ የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት ክፉኛ እየተቀጠቀጠ ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ይገኛል።
የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት መነሻውን ከጎንደርና ከሰሜን አቸፈር ሊበን በማድረግ በሁለት አቅጣጫ ወደ ሻሁራ ለመግባት በተደጋጋሚ ሙከራ ባደረገበት ወቅት በአፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ከፍተኛ ኪሳራን አስተናግዶ ቀጠናውን በለቀቀ ከአንድ ወር በኋላ መጋቢት 15/2018 አለፋ ወረዳ ሻሁራ ከተማ የገባ ቢሆንም የፋኖ ሰራዊት ከከተማው በተወሰነ ኪሎ ሜትር እርቀት ዙሪያውን አጥሮ ስለሚገኝ ማናቸውንም አይነት እንቅስቃሴም ሆነ የሀሰት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አልቻለም።
በከፍተኛ የፍርሀት ቆፈን ውስጥ ያለው የአገዛዙ ተጋላቢ ጥምር ሰራዊትና የኦሮምማው የብልፅግና አሸርጋጅ ካቢኔ በአፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር አድዋ ክ/ር ተደጋጋሚ የሆነ የሽምቅ ውጊያ ሙከራ ሲደረግበት፤ ከመሸገበት ከሻሁራ ከተማ ስቦ በማስወጣት በአድዋ ክ/ር ዘመቻ አርበኛ ጌጤ ደሳለኝ በተሰራው የውጊያ ስምሪት ከመጋቢት 29/2018 ጀምሮ በሁለት አቅጣጫ ማለትም በአፀደማርያም በኩል አብዛኛው የጠላት ሀይል የተንቀሳቀሰ ሲሆን በተለያዩ ገዥ ቦታዎች ነበልባሏ አድዋ ክ/ር ንጋት ጮራ ብርጌድ ቀድማ በመቆጣጠር በዚሁ ቀጠና ከጧት ከ12:00 ስአት ጀምሮ ተገማች ያልሆነ ወታደራዊ አሰላለፍን በመቀያየር ጠላትን በመጠጋት በተለይ ችምዝን ከምትባል ቦታ የጨበጣ ውጊያ በማድረግ ክፉኛ ምት ሲደርስበት ተጨማሪ ሀይል ከሻሁራ በመጨመር ቀጠናው ላይ የተፏፏመ እልህ አስጨራሽ አውደውጊያ እየተደረገ ሁለተኛ ቀኑን በተመሳሳይ ሁኔታ የቀጠለ ሲሆን ዛሬም ሚያዚያ1/2018 ፍጥጫው እንደቀጠለ ይገኛል። ሁለተኛው አሰላለፍ ከሻሁራ ከተማ በምዕራብ በኩል የነብሮ ብርጌድ እና ሌሎች ብርጌዶችን በማጣመር ወደ ከተማው በመጠጋት የጠላት አሰላለፍን በማዛባት ለሌላ የማጥቃት እንቅስቃሴ ዝግጅት ላይ እንዳለ የክ/ሩ የህዝብ ግንኙነት አርበኛ ዳንኤል አቡሀይ አድርሶናል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ግብስብስ ሰራዊት ዙ-23 እና መሰል ከባድ መሳሪያዎችን በየአቅጣጫው በመተኮስ የሽብር ስራውን እየሰራ ንፁሀንን በስጋት ላይ የጣለ ሲሆን ኔት ወርክ በማጥፋት እኩይ ተግባራትን እየፈፀመ ይገኛል።
በዚህ አውደ ውጊያ በደርዘን የሚቆጠር ሙትና ቁስለኛ እየሆነ በየ ቦታው አስከሬኑን እየቀበረ ሽንፈትን እየተከናነበ ይገኛ።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ
ሚያዚያ 1/2018 ዓ.ም

🙏3
ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የዕዙን የሥራ አስፈፃሚ አመራር በማስተዋወቅ ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ያለመ የትውውቅ መርሀግብር አካሂዷል።
በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ የአፋብን ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አርበኛ መከታው ማሞ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ በንግግራቸውም የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል።
➾ይህ የትውውቅ መድረክ የአመራር አባላትን ለማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን፣ በመካከላችን የጠነከረ ወንድማማችነትንና የዓላማ አንድነትን በመፍጠር ትግሉን የሚመጥን ስራ እንድንሰራ ለማሳሰብና አደራ ለመስጠትም የተዘጋጀ በመሆኑ፤ አዲሱ የሥራ አስፈፃሚ አመራር ለተጣለበት ከባድ ኃላፊነት ራሱን በቁርጠኝነት ማዘጋጀት ይኖርበታል ያሉ ሲሆን አያይዘውም፦
➾የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የተመሰረተው የሕዝባችንን ክብርና ደህንነት ለማስጠበቅ ነው።ይህ የዕዝ አመራር በሥነ-ምግባር የታነፀ፣ በዕውቀት የሚመራና ለሕዝብ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ኃይል ሆኖ እንዲቀጥል ተቋማዊ አሰራርን መከተልና ለተቋም የስራ ህግ ተገዢ መሆን ወሳኝ ነው ። አያይዘውም የአባቶቻችን ልጆች ነን ስንል በታሪክ በመንገር ብቻ ሳይሆን ለአሁናዊ የህዝባችን ችግሮች በተግባርም በማሳዬት መሆን አለበት በማለት ሀሳባቸውን በመግለጥ መድረኩ የተከፈቱ ሲሆን :-
ከትውውቅ መርሃ-ግብር ቀጥሎ በአፋብን ም/ፖለቲካ መምሪያ ሀላፊ በአርበኛ አሸናፊ ምንዳ እና በአፋብን ወ/ዕ/ስትራቴጂ መምሪያ ሀላፊ በአርበኛ ኢንጂነር ዘበነ በላይነህ የሥራ አቅጣጫ ሰነድ በማቅረብ ፤ በሰነዱ ላይ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ስራ አስፈፃሚዎች ሰፊ ውይይት በማድረግ እና አመራሮችም በአስተያዬታቸው ከእንግዲህ የምንለካው በንግግራችን ብቻ ሳይሆን በምንሰራው ተግባርና በምናመጣው ውጤት ነው። እያንዳንዱ አመራር በየተሰማራበት መስክ የሕዝብን አደራ ተሸክሞ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ የድርጅታችንን ዓላማ በማንገብ የዕዛችንን ተልዕኮዎች በመደጋገፍ በውጤት ለማረጋገጥ መሥራት ይኖርብናል።ድላችን የሚረጋገጠው ከሕዝባችን ጋር ያለንን ቁርኝት እና ከትግል ጓዶች ጋር ፍፁም ወንድማማችነትን ስናጠናክር ብቻ ነው።
በመሆኑም አመራሩ ከሕዝቡ ጋር ተቀራርቦ በመሥራት፣ የትግሉ ባለቤት ሕዝቡ መሆኑን በተግባር ማሳየት አለበት። ጠላታችን ሰፊ የመነጣጠያ ወጥመድ በማጥመድ እኛን እየነጣጠለ ህዝባችንን የሚያዋርድበት ጊዜ አልፏል። ዛሬ በአንድነት ቆመን ለአንድ ዓላማ በመተሳሰብና በመከባበር ጉዟችንን እናጠናክረን የጠላታችንን ቅስም መስበር አለብን በማለት መድረኩ የዕዙን የወደፊት ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ ትልቅ መነሳሳትን የፈጠረ መሆኑን ገልጸው፤ ሁሉም የሥራ አስፈፃሚ አመራር ለተሰጣቸው ተልዕኮ በታማኝነት እንደሚሰሩ በማረጋገጥ የትውውቁና የስራ ስምሪት መርሃ ግብሩ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
'' ክብር ለተሰውት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ !!

🙏4❤1
"ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!"
ሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም የምስራቅ አማራ ፋኖ አብሪ ኮከብ አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ስለ አማራ ህዝብ ህልዉና መስዋዕትነትን የተቀበለበት ዕለት ነው!
አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ የህልዉና አደጋ ለመቀልበስና የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ "ሕልው" ለማድረግ ዉድ ህይወቱን የሰዋበት ይህንን ቅዱስ የህልዉና ትግል "ሀ" ብሎ ያስጀመረበትና ችቦ የለኮሰበት ቀን ነው::
ገና በለጋ እድሜው የቀድሞዉን የሃገር መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀል ትግል የጀመረው አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከእግረኛ እስከ ሻምበልነት ማዕረግ ድረስ እንዲሁም የቀድሞው አግዓዚ ኮማንዶ አባል በመሆን ከሃገር ዉስጥ እስከ ዉጭ አገር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ድረስ ወጣትነቱን ለሃገሩ ገብሯል::
አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ባጋጠመው ከባድ ቁስል ምክንያት በጡረታ ያገለለ ሲሆን ከ 2010 ዓ.ም ህዝባዊ እምቢተኝነት ቡሃላ ወጣቶችን በስፖርት በአካል ብቃትና በስነ ልቦና የማንቃት ስራ እየሰራ በኋላም ከነ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ጋር የራያ ፋኖን በመመስረትና በመቀላቀል ፀረ ወያኔ ትግሉን ተቀላቅሎ ሁሉንም ተጋድሎዎች በመሪነትና በአሰልጣኝነት በድል ተወጥቷል:: የቀድሞው ምስራቅ አማራ ፋኖ ስልጠና መምሪያን እየመራ በመካነሰላም በደሴ በሃይቅ በወልድያ በቆቦና በራያ አላማጣ በርካታ ታጋዮችን ያሰለጠነና ያፈራ ሲሆን የአሁኑን የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል በሰራዊትና በመሪነት ላይ ያሉ በርካታ ጀግኖችን አፍርቷል:: በርካታ ጀግኖችን እያሰለጠነና እያስታጠቀ መሆኑን ያየው አገዛዙም በጥላቻ አይን ያየው ጀመረ::
የሰሜኑን ጦርነት እነ አብይ አህመድና በድኑ ብአዴን በፕሪቶሪያው የድራማ ስምምነት ከቋጩት በኋላ የአማራ ፋኖን ህግ ማስከበር በሚል ሽፋን ትጥቅ ለማስፈታት በፌደራልና በክልል ደረጃ መከላከያ በማዝመት ዘመቻ በጀመሩበት ጊዜ ግጭቶች መጀመራቸው ይታወቃል:: በዚህም በተለያዩ ጊዜያት የምስራቅ አማራ ፋኖ ሰራዊትና አመራሮችን ቀዳሚ ኢላማ ያደረገ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጠለ::
አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከነዚህ የፖለቲካ ጥያቄ ካነገቡ ግጭቶች ጋር ተያይዞ የብርሃኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊት ላይ ይመለከት በነበረው ፀረ-ህዝብ ተግባርና ነዉር እጅግ ይበሳጭና ያዝን ስለነበር በአንድ ከአብይ አህመድ ጀኔራሎች ጋር ቆቦ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ በተደረገ ስብሰባ የህዝብ ናችሁ ወይስ የብልፅግና? በሚል ይጠይቃቸዋል:: ያ ከራሱ ህዝብ አልፎ ሰላም ማስከበር ጎረቤት አገር ሄዶ ረሽኑን ለህዝብ ሰጥቶ ቅጠል በልቶ የሚያድር ሰራዊት የት ገባ? ሲል በመጠየቅ እስከ ሰላም ማስከበር በደረሰ ተልዕኮው የነበረዉን ህዝባዊነት በመጥቀስ የግፈኞች ዙፋን ጠባቂ መሆናቸዉንና ነውራቸዉን ነገራቸው::
አይቀሬዉን ጦርነት የተገነዘቡትና የተረዱት የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ከወሎ ምስራቅ አማራ ፋኖ ከሸዋ ከጎጃምና ከጎንደር ፋኖዎች ጋር በመሆን ጎንደር ሱዳን ጠረፍ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን በመመስረት አርበኛ ሰፈር መለሰን ዋና አዛዥ እና ዋርካው ምሬ ወዳጆን ምክትል አዛዥ አድርጎ በመምረጥ እንቅስቃሴ ጀመረ:: ምስራቅ አማራ ፋኖ አጠቃላይ የትግል ጉዞዉን የሚዘክር ታላቅ የተሃድሶ ዝግጅት የምክር ቤቱ ዋና አዛዥ አርበኛ ሰፈር መለሰ እንዲሁም ከፍተኛ የመከላከያ፣ የልዩ ሃይል፣ የብልፅግና አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እና የሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም መላ ሰራዊቱና ህዝብ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አከበረ::
በዝግጅቱም ምስራቅ አማራ ፋኖ የአማራ ህዝብ በክልሉና በተለይ ከክልሉ ዉጭ እየደረሰበት ያለዉን ግፍና ጭፍጨፋ በማንሳትና በማስታወስ የአማራ ህዝብ የህልዉና አደጋ ተጋርጦበታል "ትግል ይቀጥላል" የሚል መልዕክት ለታዳሚው ለሰራዊቱና በዉስጥም በዉጭም ላለው መላው የአማራ ህዝብ በህዝብ ግንኙነቱ አርበኛ አበበ ፈንታው በኩል መልዕክት አስተላለፈ:: ይህንን ተከትሎም ከተሃድሶ ቡሃላ ትጥቅ ያስረክቡናል ይበተናሉ ስንል እንዴት "ትግል ይቀጥላል" ይላሉ በሚል የአገዛዙ ሹማምንት ከፍተኛ ንዴትና ብስጭት ብሎም ድንጋጤ ዉስጥ ገቡ::
ይህንን ተከትሎም አገዛዙ የምስራቅ አማራ ፋኖ ቁስለኞችን ሳይቀር ሰራዊቱን ባገኘበት ምቹ አጋጣሚ ሁሉ መረሸን ጀመረ:: የለየለት ግጭትም ተጀመረ:: ጥቃት የማይወደው አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙም ሰራዊቱን በተጠንቀቅ እንዲቆምና ለሚመጣው ሁሉ ነገር ተመጣጣኝ አፀፋ እንዲሰጥ ድርጅቱና መሪው ዋርካው ምሬ ወዳጆ ያወረደዉን መመሪያ በመቀበል በአንድ ወቅት ምስራቅ አማራ ፋኖ ካምፕ ድረስ ከነ አጃቢዎቹ በፓትሮል የመጣን ኮሎኔል ከመኪናው ወርዶ እስኪፈረጥጥ ድረስ ቆፍጠን ያለ እርምጃዉን ጀመረ::
ምስራቅ አማራ ፋኖም ሰራዊቱን በምዕራብ በኩል ከራያ ቆቦ ጮቢ በር እስከ በላጎ እንዲሁም ወልድያ ዙሪያ ሳንቃና መቻሬ እንዲሁም ሙጃ ድረስ ገዥ መሬቶች ላይ በማስፈር ለአይቀሬው ፍልሚያ ተዘጋጀ:: በበርካታ አካባቢዎች ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ የነበረዉን ከፍተኛ ዉጥረትና የአማራ ልዩ ሃይል በበድኑ ብአዴን እና በነ አብይ አህመድ ሴራ መፍረሱን ተከትሎ ሚያዚያ 1/2015 አ.ም ረፋድ ላይ ቆቦ ከተማ በተጀመረ ከባድ ዉጊያ የአሁኑን የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ጅማሮ ችቦ ለኩሶ አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ መስዋዕትነት ተቀበለ:: የህልዉና ተጋድሎዉም ሸዋ በነበሩ የምስራቅ አማራ ፋኖ አሃዶችና የሸዋ ፋኖ አናብስቶች ተቀጣጥሎ ዛሬ በመላው አማራ የደረሰበት ደረጃ ደረሰ::
አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ስለ አማራ ህዝብ ህልዉና ቀይ መስመር ያለፈዉን በምድርም ይሁን በሰማይ ዘመኑ ያፈራዉን ጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው የታጠቀዉን ጨፍጫፊና ግፈኛ ፋሽስታዊ ስርዓት እስከ መጨረሻው ህቅታ ተናንቆ በጀግንነት ተሰዉቶ ችቦ ለኩሶና አስጀምሮ ይህንን የአማራ ህዝብ ቅዱስ የህልዉና ትግል ለዛሬ ካበቁ ጀግኖች መካከል ግንባር ቀደም ሆኖ አልፏል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
የተሰዋህለትን አላማ ከግብ እናደርሳለን!
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!
አፋብን በወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ

👍3
በላስታ ግንባር ይባር አከባቢ ፋኖ በወሰደው የስቦ መምታት እርምጃ አንድ አመራርን ጨምሮ ከ30 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ተደመሰሱ!
በምስራቅ አማራ ቀጠና ላስታ ግንባር ይባር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የጥራሪ ክፍለጦር አርበኞች በወሰዱት የተቀናጀ የስቦ መምታት እርምጃ የአገዛዙ 45ኛ ክፍለ ጦርን ክፉኛ በመምታት ድል አስመዝግበዋል።
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር ስር የሚገኙት የጥራሪ ክፍለ ጦር አርበኞች ትናንት ሚያዚያ 01/2018 ዓ/ም እስከ ምሽት ድረስ በወሰዱት እርምጃ አንፀባራቂ ድል ተቀዳጅተዋል።
ከግዳን ሙጃ ከተማ ተነስቶ ወደ ይባርና አምበሳው ከተሞች በፋኖ በተዘጋጀለት ወጥመድ ሰተት ብሎ የገባው የጠላት ኃይል፡ በ360 ዲግሪ ተከቦ ክፉኛ ተቀጥቅጦ ተሸመድምዶ ተብታትኗል።
በጥራሪ ክፍለ ጦር ስር ከሚገኙት ከተመስገን ሬጅመንት፣ ከአቡነ ዮሴፍ፣ ከኤፍሬም እና ከትዕግስቱ ሬጅመንቶች የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ናቸው የስቦ መምታት እርምጃውን በመውሰድ የጠላት አከርካሪን የሰበሩት።
በዚህ ተጋድሎ ማዕረጉና ስሙ ለጊዜው በውል ያልታወቀ አንድ ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ ከአሥር በላይ ወታደሮች ሲገደሉ፡ የአመራሩ አስከሬን ዛሬ ሚያዚያ 02/2018 ዓ/ም በከፍተኛ ወታደራዊ አጀብ በሙጃ ማርያም ቤተክርስቲያን ተቀብሯል።
በተጨማሪም ከ20 በላይ ወታደሮች ከቀላል እስከ ከባድ የቆሰሉ ሲሆን፡ የጦር መሣሪያዎችና ገዢ ወታደራዊ ስፍራዎች በጥራሪ ጀግኖች ቁጥጥር ስር ውለዋል።
ሽንፈትን የተከናነበው የአገዛዙ ሰራዊት፡ ቂሙን በንፁኋን ላይ ለመወጣት ሞርታር፣ ቢኤም እና ዙ-23 በመጠቀም በእንጃፋትና በመለየ አከባቢ ነዋሪዎች ላይ የሽብር ጥቃት ሲፈፅም ውሏል።
ይኸው የነውረኛው ብልፅግና አገዛዝ ተላላኪ ኃይል፡ በህዝቡ ላይ የኢኮኖሚና የስነልቦና ጫና ለማድረስ ከከተማ ወደ ገጠራማ አከባቢዎች ሸቀጦችና የቅባት እህሎች እንዲሁም የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች እንዳይገቡ መንገዶችን መዝጋቱ ተነግሯል።
የጥራሪ ክፍለ ጦር አርበኞች ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎችን በመቆጣጠር በጠላት ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው ቀጥለዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ሚያዚያ 02/2018 ዓ.ም

ነፃ በወጡ ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይቶች እየተደረጉ ነው።
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ በተከታታይ በርካታ ቦታዎች ላይ ውጊያ በመክፈት ሰዴን ጨምሮ ከተሞችን ነፃ እያደረገ ይገኛል። በዚህም በርካታ ወታድራዊ ድሎችን ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን ወታደራዊ ድሉን ወደ ፖለቲካዊ ድል ለመቀየር የሕዝብ ግንኙነት ስራ አስፈላጊ በመሆኑ ከሰዴ ማህበረሰብ ጋር ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።
የቴዎድሮስ ዕዝ አመራሮች ፣ የ201ኛ ኮር አመራሮች ፣የ54ክፍለጦር አመራሮች እና ጊዜአዊ መንግስት አመራሮች በተገኙበት ሕዝባዊ ውይይቱ ተደርጓል።
በስብሰባውም የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች፣ ፋኖ የደረሰበት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ የእድገት ደረጃ ፣ አገዛዙ እየደረሰበት ያለውን ዲፖሎሲአዊ ውድቀት እና የማህበረሰባችን ሰላምና ደህንነት መጠበቅን በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰጧል።
ማህበረሰቡም አገዛዙ ሲያደርስበት የነበውን ጭቆና በመዘርዘር እንኳን መጣችሁልን የትንሳኤን በዓል በሰላም እንድንውል ልታደርጉን ነው በማለት ለፋኖ ምስጋና አቅርቧል።
ሴት ልጆቻችን በአብይ ሠራዊት ተደፍረውብናል ፣ሀብት ንብረታችን ተዘርፏል ፣ የምርጫ ካርድ ካላወጣችሁ እየተባልን ተደብድበናል፣ በየምክንያቱ የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ እየተባልን ተደብድበናል የተገደለም አለ በማለት አገዛዙ ያደረሰባቸውን በደል ተሰብሳቢዎቹ ገልፀዋል።
ወጣቱም እንሰለጥናለን ቤተሰባችንንና የአማራን ሕዝብ ለመታደግ መክፈል ያለብንን ለመክፈል አብረናችሁ እንቆማለን ሲል ድምፁን አሰምቷል።
የፋኖ ትግል የሕዝብ ትግል መሆኑን በተግባር ያሳየ መድረክ መሆኑን ያሳየ ነበር ሲሉ አስተያይት ሰጪዎች ገልፀዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም!
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ