ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሩዋንዳ የፈፀመውን ታሪካዊ ስህተት በአማራ ህዝብ ላይ እንዳይደግም ሲል አፋብን አሳሰበ!

ድርጅቱ፡ ዛሬም በኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ጭካኔና የዘር ማጥፋት ጥቃት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ገልጿል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በሩዋንዳ በቱትሲዎች ላይ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል 32ኛ ዓመት መታሰቢያን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት፡ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሩዋንዳ የፈፀመውን ታሪካዊ ስህተት በአማራ ህዝብ ላይ እንዳይደግም አሳስቧል።

የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ መምሪያ ዛሬ መጋቢት 28/2018 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ፡ እ.ኤ.አ በ1994 በሩዋንዳ የተፈፀመውና አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ንፁኃን ያለቁበት ክስተት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ ዘግናኝና ጨለማው ምዕራፍ መሆኑን አስታውሷል።

ይህ ዕለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲታሰብ፡ በወቅቱ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የዘር ማጥፋቱን ለመከላከል ባለመቻሉ የተሰማውን ጥልቅ ፀፀት የሚያንፀባርቅበት መሆኑም ይታወቃል።

ይሁን እንጂ፡ ዛሬም በኢትዮጵያ በአማራ ህዝብ ላይ ተመሳሳይ የሆነ የህልውና ስጋትና ቀጣይነት ያለው የዘር ማጥፋት ጥቃት በብልፅግና አገዛዝ ስር እየተፈፀመ መሆኑን መግለጫው በዝርዝር አስቀምጧል።

ዓለም አቀፍ ተቋማትና መንግስታት የሩዋንዳን ሰማዕታት በሚያስቡበት በዚህ ወቅት፡ በአሁኑ ሰዓት በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ እልቂትና ግፍ አይተው እንዳላዩ እንዳያልፉ አፋብን ጥሪውን አቅርቧል።

በመጨረሻም ድርጅቱ፡ "በጭራሽ አይደገም" (Never Again) የሚለው መሪ ቃል ትርጉም ሊኖረው የሚችለው በአሁኑ ሰዓት በአማራ ህዝብ ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በቆራጥነት ሲቃወምና ትኩረት ሲሰጠው ብቻ መሆኑን በመግለጫው አፅንኦት ሰጥቷል።
🙏2
አዲሱ የአፋብን የህዝብ አስተዳደርና የወታደራዊ አደረጃጀት በ4ኛ ኮር ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ሆነ!!

አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ደጃዝማች ፬ኛ ኮር ከአውደ ውጊያ ጎን ለጎን ለወራት በማጥራትና ማብቃት ግምገማና ስልጠና እንዲሁም አደረጃጀት ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል።በዚህም መሰረት የወታደራዊና የህዝብ አስተዳደርና ፖለቲካ ዘርፉን በአዲሱ መመሪያ በማዋቀር አደረጃጀቱን ይፋ አድርጓል።

🎯የሰሜን ምዕራብ ጎንደር የዞን ክላስተር የህዝብ አስተዳደር መዋቅር ...
1. አንዳርግ ጫቅሉ ....... ዋና አስተዳዳሪ
2. ተመስገን መንግስቱ ......... ም/ አስተዳዳሪ
3. መልካሙ ቸኮል .......... ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ
4. እንግዳው ዋኜው ......... ም/ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ
5. ዮናስ ይርጋ ........ ፅ/ቤት
6. ታደሰ ተረፈ ...... ም/ፅ/ቤት
7. አንዳርግ ማሞ ......... አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ
8. ግርማ ተገኘ ............ ም/አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ
9. የሻነው ውብነህ ........ ሰላምና ደህንነት
10. አስተዳድረው ምህረት ......... ገንዘብ አስተዳደር
11. ጋሻው መሰለ ............ ም/ገንዘብ አስተዳደር
12. አዲሱ ስመኜው ......... ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ሀላፊ
13. መሸሻ አባይ ........ ም/ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ሀላፊ
14. ባንዴራዉ ግርማይ ........ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ
15. አስፋው አደራጀው ........ ም/ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ
16. ያያዉ ገብሬ ....... ሀብቴ አፈላላጊ
17. ተቀባ ጫቅሉ ....... ም/ሀብት አፈላላጊ
18. መኳንንት አላምረው ........ ፕሮጀክት አስተባባሪ
19. አሌክስ ገብሩ ...... ም/ፕሮጀክት አስተባባሪ
20. ናቃቸዉ ጌትነት ........ ፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ
21. ዋና ሳጅን እንየው ሞላ ..... ፍትህ
22. ግለጠው አለባቸው ..... ም/ፍትህ
23. ስማቸው ጥላሁን ..... መረጃ

🎯የኮር ወታደራዊ መዋቅር
1. ኤልያስ ድንቁ ......... ዋና አዛዥ
2. እሸቴ አሸብር .......... ም/አዛዥ
3. ጌታቸዉ የሽወንድም ........... ወታደራዊ አስተዳደር
4. ታደለ አጀበዉ ......... ሎጀስቲክ
5. በለጠ ታደለ .......... ፖለቲካ ስርፀት ኃላፊ
6. ዳኜ ድረስ .......... ዘመቻ
7. አበባው አማረ ........ ም/ዘመቻ
8. ሰፊው በየነ ..........ህግና ስነምግባር
9. ቁምነገር ሽጉጤ ....... መረጃ
10. በራ ደሳለኝ ......... ስልጠና
11. አሰፋ ይላቅ ......ኦርዲናንስ
12. ቻሌ ድግስ ......... መገናኛ
13. ግዛት አለበል .... ኦዲተር
14. አስችል አለምየ ..... ፋይናንስ
15. አለነ ተንሳይ ...... ወታደራዊ ቃል አቀባይ
16. እሱባለው ይርጋ ........ ስንቅ አቅርቦት
17. ሞላ አዲሱ ....... ጤና ሀላፊ
18. ወንዴ ጥላሁን ........ም/ጤና
19. አዳነ ፍሰሀ ........ ግዥ በማድረግ የልማደኞቹ ኮር ጥንቅቅ ቅልብጭ ብሎ ተሰርቷል።ለህዝብ አስተዳደር እና የፖለቲካ ስራዎች ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው ይህ አዲስ ድርጅታዊ አወቃቀር ለወታደራዊ ክፍሉ የተሻለ የስራ ነፃነት የሚሰጥ መሆኑም ታምኖበታል።

ህልውናችን በአርበኝነታችን!!


መጋቢት 28/2018 ዓ.ም

ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
3🙏2🥰1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአርበኛ ሸጋ ጌታቸው ጥብቅ መልዕክት
1🙏1
Genet Asmamaw
Yegna Media | Addis Ababa, Ethiopia | April 6, 2023

Genet Asmamaw was arrested on April 6, 2023, in the Ethiopian capital, Addis Ababa.

She was charged with terrorism in June 2023. All five Ethiopian journalists in CPJ’s 2025 prison census are facing this charge, after reporting on conflict in the Amhara region, for which they could face the death penalty if convicted.

Genet was a reporter with YouTube-based Medlot Media, which covered political issues related to the Amhara people, according to her brother Andualem Demissie.

The channel had over 100,000 subscribers in late 2023, according to CPJ’s review, but was no longer online by late 2025.

The five federal police officers who arrested Genet from her home beat and intimidated her, according to Andualem and her lawyer, Henok Aklilu.

In audio recorded during the arrest, published by several media outlets and authenticated by Henok, an officer said, “Beat her; kick her,” and Genet said, “Do not beat me. Why are you hitting me? Why are you kidnapping me without a court order?”

On April 7, 2023, Genet appeared at the Federal First Instance Court and was accused of inciting violence through social media and other platforms and mobilizing young people to overthrow the government, Henok said. Police were granted time to hold her in custody pending investigations.

Genet told the court that the police had abused her during her arrest, and the court ordered the federal police to investigate, Henok said. CPJ was unable to determine whether the investigation was carried out.

Genet was among at least eight journalists and media workers arrested that month over allegations that included inciting violence. Five were later released.

The arrests followed the government’s April 6 decision to integrate regional militia into the federal army, which triggered protests.

The Amhara Regional Special Forces refused to surrender their weapons and the Fano militia took up arms against federal forces — their former allies in a civil war in northern Ethiopia that ended with a peace deal in 2022. The Amhara conflict was ongoing as of late 2025.

On June 7, 2023, the federal ministry of justice filed charges against Genet and 50 other people, including three other journalists in CPJ’s 2025 prison census — Dawit Begashaw, Meskerem Abera, and Gobeze Sisay — according to a charge sheet reviewed by CPJ.

The charge sheet accused the journalists of violating the Proclamation on Prevention and Suppression of Terrorism, which stipulates that those found guilty of “terrorizing or spreading fear among the public” to advance “political, religious or ideological causes” can be given the death penalty.

Prosecutors said that Genet participated in meetings and discussions and received propaganda training from the Amhara Fano Unity Council, which they described as a “clandestine organization, which the defendants used to do their terrorist activities” by bringing together militant groups, including the Fano militia.

They also said she distributed a letter calling on military officers to defect and edited and distributed propaganda via social media.

On July 19, 2023, Genet and her co-defendants were denied bail, according to Henok, and Genet was transferred to the capital’s Kaliti federal maximum security prison the following day.

In October and November 2023, the defendants’ application for their case to be dismissed as politically motivated was rejected, Henok said.

From December 2023 to March 2024, the proceedings were suspended pending a Supreme Court ruling on whether some defendants could be tried in absentia, Henok said. It ruled in favor.

In May 2024, the proceedings were suspended again pending a Supreme Court ruling on a preliminary objection by the defense, demanding that the charge sheet be amended to include specific facts, including details on the damage and violent incidents that the defendants were alleged to have committed or incited, Henok said.
1
On November 12, 2024, the prosecution filed an amended charge sheet naming the people allegedly affected by the incidents, without detailing those incidents.

On November 14, 2024, Genet appeared before the federal court alongside other co-defendants and pleaded not guilty.

In February 2025, the prosecution began presenting its testimonial and documentary evidence against Genet and her co-defendants, another of her lawyers, Solomon Gezahagn, told CPJ.

She is due to present her defense in May 2026, after a federal court ruled on February 4 that the prosecution had enough evidence to proceed.

Ethiopia government spokesperson Legesse Tulu did not answer CPJ’s calls or text messages in late 2024.

CPJ's early 2026 emails requesting comment from the ministry of justice and federal Government Communication Service were also unanswered.

(CPJ)

(Awulogson Andinet, Megabit 28/2018)
1
ጠላት ከሰባ በላይ አስከሬኑን ጥሎ በሸሸበት ፍልሚያ የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት አምባሰልና ጉባላፍቶ ወረዳ ላይ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር እና 104ኛ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር የ106ኛ ኮር 32ኛ ክፍለ ጦርን ተጠባባቂ በማድረግ መጋቢት 27/2018 ዓ.ም አምባሰል ወረዳ ሚለዋ እና ጉባላፍቶ ወረዳ ደንጎላና ሸዋት የጠላትን ሃይል ስበው በማስገባት በጥምረት ባደረጉት ከባድ ተጋድሎ በርካታ የጠላት ሃይል በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

የምኒልክ ዕዝ አሃዶች ጠላትን ከወልድያ እና መርሳ ወደ አምባሰል ወረዳ ሚለዋ እንዲሁም ከደላንታ አቅጣጫ ወደ ጉባላፍቶ ወረዳ ደንጎላና ሸዋት ያለምንም ትንኮሳ እንዲገባ በማድረግ በከፈቱበት ከባድ ከበባና ማጥቃት በርካታ የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ የተደረገ ሲሆን ከሰባ በላይ አስከሬኑን ጥሎ ለመውጣት ተገዶ ፋኖ የአካባቢው ማህበረሰብ በማስተባበር እንዲቀበር አድርጓል::

በምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር እና በ104ኛ ኮር የክፍለ ጦርና የኮር አመራሮች በጥምረት በተመራው ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ የፋሽስቱ ብልፅግና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ከሰባ በላይ አስከሬኑን በረሃ ላይ ጥሎ ከመሸሽ በተጨማሪ በዞንና በወረዳ ከተሞች ዙሪያ ያሉ ምሽጎችን ለቆ ፋኖን መዋጋት እንደማይቻል በማረጋገጥ በርካታ ቀበሌዎችን ለቆ ወደ ወልድያና መርሳ ከተማ አቅራቢያ ባሉ ቀጠናዎች ለመቀመጥ ተገዷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 29/2018 ዓ.ም
🙏2
#ሰበር_የአውደ_ውጊያ_ዜና‼️
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዘ አፄ አምደ ፅዮን ኮር ጀግናው የአፄ ዳዊት ክፍለጦር አሃዶች ከ25 በላይ የብልፅግናውን 101ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር አባላት በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ።

መጋቢት 29/2018ዓ.ም

ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2018ዓ.ም ከንጋቱ 11:00 ጀምሮ በተካሔደው የተቀናጀ ተጋድሎ ሰራዊታችን ታላቅ ድል እየተጎናፀፈ ይገኛል ሲል የአፄ ዳዊት ክፍለጦር አስታወቀ።

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በሚዳና ሬማ ወረዳ ከአገዛዙ 101ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ጋር እየተደረገ ባለው ውጊያ ጀግናው የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ከአፄ ዳዊት ክፍለጦር ሻለቆች እና በቀጠናው የሚገኙት የአርበኞች ጦር ሰራዊት በተወጣጡ የወገን ሀይል ከአራት አቅጣጫ የመጣውን የስርዓቱ ወንበር አስጠባቂ ወራሪ ሀይል ላይ ከፍተኛ ድል መቀዳጀታቸውን ክፍለጦሩ በግንባር መረጃው አስታወቀ።

በጀግናው ሰራዊታችን ተደጋጋሚ ሽንፈት እያስተናገደ ያለው የብልፅግናው ዘራፊ ሰራዊት የፋኖን ሀይል ለማጥቃት አቅዶ መነሻውን ከሬማ ከተማ፣ በሚዳ መራኛ ከተማ፤ ከወሎ ቤተ አማራ ጃማ ደጎሎ ከተማ እንዲሁም ከአለም ከተማ በማድረግ የተንቀሳቀሰ ሲሆን በይጎቪያ ቀበሌ በተደረገበት የመልሶ ማጥቃት ከ25 በላይ የአየር ወለድ የሰራዊቱ አባላት የተደመሰሱ ሲሆን ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ የጥምር ጦር አባላቱ ሙትና ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ ማስተናገዱን ክፍለጦሩ ገልጿል።

ይሕ ዜና እስከተጠናቀረበት ከቀኑ 9:30 ድረስ በርካታ የጠላት ሀይል በወገን ሀይል ከበባ ውስጥ ገብቶ ከፍተኛ ምት እያስተናገደ ሲሆን ውጊያው ተጠናክሮ መቀጠሉን ክፍለጦሩ በግንባር መረጃው አስታውቋል።

መረጃው የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ነው።

👉በሬማ ከተማና አዋሳኝ ቦታዎች ላይ እየተካሔደ ያለው ውጊያ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በጀግናው ሰራዊታችን በመልሶ ማጥቃት ከበባ ውስጥ የገባውን የአገዛዙ ሰራዊት ለማስወጣት ተጨማሪ የጠላት ሀይል ከአለም ከተማ በማምጣት በከተማዋ ዙሪያ ባሉ በድሬና መጅት ቀበሌዎች አድማሱን ያሰፋው ውጊያ በመቀጠሉ ዝርዝር የአውደ ውጊያ መረጃዎችን በቀጣይ ይዘን የምንመለስ መሆኑን ከወዲሁ መግለፅ እንወዳለን።

''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን

የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ

መጋቢት 29 / 2018ዓ.ም
🙏31