ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.32K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.23K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ምስራቅ ጎጃም ናብራ ከተማ
ቀን: መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም

የአንድነት እና አመራር ምደባን አስመልክቶ ከአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ህዝብ የህልወና አደጋ ተጋርጦበት እንዲቆይ ያደረገው እና የህልውና አደጋው ውስጥ እንዲገባ በር የከፈተው የህዝብን ጥቅም እና የህዝቡን ጥያቄ የሚያስቀድም ድርጅት ባለመኖሩ ነው።

በመሆኑም ለግማሽ ምእተ አመት በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ቀድመው በመረዳት አማራው መደራጀት አለበት በሚል ፅኑ እምነት ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እና የትግል አጋሮቻቸው የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት መአህድን ቢመሰረቱም በወቅቱ በነበረው ስርዓት እና ትግል ጠላፊዎች እረጅም ርቀት ሳይጓዝ ቀርቷል።

ዛሬ ላይ ግን ከአማራ ማህፀን የወጣው የአማራ ፋኖ ታላቁን የአማራ ህዝብ የሚመጥን መሰባሰቢያ ድርጅት ለመስራት ብዙ ውጣ ውረዶችን በማለፍ እና ጠንካራ ውይይቶች በማድረግ በቋሚነት የአማራን ጥያቄ ሊፈታ በሚችል አካሄድ ከስምምነት በመድረስ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን)ን መሥርቷል።

​በተፈጠረው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ውህደት መሠረት እና ድርጅታችን አፋብን ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በሸዋ የሚንቀሳቀሱትን ሁለት ግዙፍ ዕዞች በአንድ ወጥ መዋቅር ስር የማደራጀት ስራ በተለያዩ ምዕራፎች ሲከወን ቆይቷል።

በመሆኑም ድርጅታዊ አቅማችንን በፖለቲካዊ፣ በወታደራዊ እና በአስተዳደራዊ ስራዎች ይበልጥ ለማጎልበት እና መዋቅራዊ አሰራርን በማቀላጠፍ ዕዝና ሰንሰለቱን በጠበቀ መንገድ በጠላታችን ላይ የማያዳግም ድል ለመቀዳጀትና የሕዝባችንን የህልውና ጥያቄ ለዘለቄታው ለመፍታት አፉብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝና ሸዋጠቅላይ ግዛት ዕዝ በአንድ ጠንካራ መዋቅር ስር ተዋህደዋል።

በመሆኑም በአድሱ መዋቅር አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ ስር የማዋሃድ ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ለመላው ህዝባችን በኩራት እናበስራለን።

​ይህ ውህደት የአማራን ህዝብ ህልውና ለማስከበር በምናደርገው ጉዞ አዲስ ምዕራፍ የከፈተና የተበታተነ ጉልበትን ወደ አንድ የሰበስበ ታሪካዊ እርምጃ ነው። ውህደቱን ተከትሎ ስራዎችን በብቃት ለመምራት፣ ተቋማዊ እና ግልጽነት ያለው አሰራር ለመዘርጋት የሚከተሉት የኃላፊነት ድልድሎች መደረጋቸውን አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ እንደሚከተለው ይገልፃል።

በዋና መምሪያነት

1. ዋና መሪ -አርበኛ ኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ
2. ም/ል መሪ -አርበኛ ጠጁ ባበይ
3. ወታደራዊ አዛዥ -አርበኛ አማን እሸቱ
4. ም/ወ አዛዥ -አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ
5. ፖለቲካ መምሪያ -ዶ/ር ታደሰ ተ/ስላሴ
6. ህዝብ ግንኙነት መምሪያ- አርበኛ አከበር ስመኘው
7. አደረጃጀት መምሪያ - አርበኛ ግርማ ጌታቸው
8. ፅ/ቤት ሀላፊ -አርበኛ ዳግማዊ ዓምደ ጽዮን
9.ትም/ት እና ስልጠና መምሪያ-አርበኛ ይብዛወርቅ መስፍን
10.ዘመቻ መምሪያ -አርበኛ አሳልፍ (ቀጭን) ደስታ
11.ጥናትና ስትራቴጅ መምሪያ -አርበኛ አበባዬሁ ኃይለጊዮርጊስ
12.ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ - ​​​፶ አለቃ ይርጋ ወንድአለ
13.ሎጅስቲክ መምሪያ -አርበኛ ዘገዬ ዳኜ
14.ወታደራዊ መረጃ እና መገናኛ መምሪያ-አርበኛ ሞገስ መላኩ
15.ሀብት አሰባሰብ መምሪያ-አርበኛ አበበ ፀጋዬ
16.ፋይናንስና ግዢ መምሪያ-አርበኛ አናኒያ ጥላሁን
17.ህዝብ አስተዳደር መምሪያ -አርበኛ ኤፍሬም ባዩ
18.ማህበራዊ ዘርፍ መምሪያ -አርበኛ አስታወሰኝ ላቀ
19.ሕግ እና ስነ-ምግባር መምሪያ-አርበኛ ሽመልስ ንጉሴ
20.ኢንዶክትርኔሽን መምሪያ -አርበኛ ስንታዬሁ ደመቀ
21.መካናይዝድ መምሪያ - ​​​፶ ​​​አለቃ ካሳ ጌታቸው
22.የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ -አርበኛ ግዛቸው ደረበ
23.ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ -አርበኛ እሸቱ ኃ/ሚካኤል
24.ጤና መምሪያ -አርበኛ አበበ አላዩ
25.ሴቶች ጉዳይ መምሪያ -አርበኛ ትንቢት ኃ/ማሪያም
26.ልዩ ዘመቻ መምሪያ -አርበኛ ለማ አስማማው
27. ወታደራዊ ዕቅድና ስትራቴጂ መምሪያ -፻አለቃ ልመነው ሻውል
28.መረጃና ደህንነት መምሪያ -*

እንዲሁም በምክትል መምሪያ
1.ፖለቲካ መምሪያ -አርበኛ ዶ/ር አብደላ ኢድሪስ
2.ህዝብ ግንኙነት መምሪያ -አርበኛ አዶናይ አበበ
3.አደረጃጀት መምሪያ -አርበኛ ደረሰ ታደሰ
4.ትም/ት እና ስልጠና መምሪያ-አርበኛ እያሱ ሙሉጌታ
5.ዘመቻ መምሪያ- ፻ አለቃ ኤርሚያስ ግጨው
6.ጥናት እና ስትራቴጂ መምሪያ -አርበኛ ተስፋማርያም ታፈሰ
7.ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ-አርበኛ ተሰማ ፀዓዳ
8.ሎጅስቲክ መምሪያ - ፲፻ አለቃ ሞገስ ለማ
9.ወታደራዊ መረጃ እና መገናኛ መምሪያ- አርበኛ ዳመን ወርቄ
10.ሀብት አሰባሰብ መምሪያ-አርበኛ በላይ አስማማው
11.ፋይናንስ እና ግዢ መምረመያ- አርበኛ ታደሰ ዳምጠው
12.ህዝብ አስተዳደር መምሪያ- አርበኛ ወርቁ ማሞ
13.ማህበራዊ ዘርፍ መምሪያ-አርበኛ ገነት ጥበቡ
14.ሕግ እና ስነ -ምግባር መምሪያ-አርበኛ ኑሩ ሁሴን
15. ኢንዶክትርኔሽን መምሪያ-አርበኛ አበራ ማንጉዴ
16.መካናይዝድ መምረመያ -- ፲፻ አለቃ አከበረኝ ታለማ
17.የሰው ሀብት አስተዳደር መምረመያ-አርበኛ ይታገስ ተሾመ
18.ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ - ፲፻ አለቃ አቡሽ እንግዳ
19.ጤና መምሪያ- አርበኛ ዳዊት አንተነህ
20.ሴቶች ጉዳይ መምሪያ- አርበኛ አመለወርቅ አበበ
21.ልዩ ዘመቻ መምሪያ- አርበኛ ታድሎ ንጉሴ
22. ወታደራዊ ዕቅድና ስትራቴጅ መምሪያ- አርበኛ አጥላባቸው ተስፋዬ
23.መረጃና ደህንነት መምሪያ- ****
በማድረግ መድቧል።

አዲሱ መዋቅር ማለትም አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ ይህን መግለጫ ከወጣበት ዕለት ከመጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ስራውን በይፋ የጀመረ ሲሆን፣ ​በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች እና ሰራዊታችን፦ ማንኛውም ትዕዛዝ የሚሰጠውና ሪፖርት የሚደረገው በአዲሱ የዕዝ ሰንሰለት መሰረት ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ድርጅታዊ ተልዕኳችሁን በውሳኔው መሰረት ተግባራዊ እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን።

​ለመላው የአማራ ህዝብ እና ደጋፊዎቻችን በሙሉ ፦

ይህ ውህደት የህዝባችንን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሚመልስ የጥንካሬያችን መገለጫ ሲሆን የህዝባችንን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ እና የአማራን ህዝብ ህልውና ለማስከበር አዲስ ምዕራፍ የከፈተ በመሆኑ፣ ከዚህ ቀደም የነበረውን ሁለገብ ድጋፍ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

​ አንገታችን አንድ ፣ዓላማችን አንድ፣ ጠላታችን አንድ፣ መዳረሻችንም አንድ ነው!!
'' ክብር ለተሰውት''
​ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!

​አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
🙏1
መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም

የአመራር ምደባን አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

ከመደበኛው የህልውና ተጋድሎዉ ጎን ለጎን ድርጅታዊ መዋቅሩን በማጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በሚከተሉት የኃላፊነት ቦታወች ላይ አመራሮችን መድቧል። በዚህም መሠረት;-
1ኛ) አርበኛ ማርከው መንግስቴ የአፋብን ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ፤
2ኛ) አርበኛ ፀዳሉ ሙላት የአፋብን ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ፣
3ኛ) አርበኛ ዘበነ በላይነህ የአፋብን ወታደራዊ እቅድ እና ስትራቴጅ መምሪያ ኃላፊ፣
4ኛ) አርበኛ አብርሃም ኩራባቸው የአፋብን መካናይዝድ ጦር መምሪያ ኃላፊ፣
5ኛ) አርበኛ ደሳለኝ ሲያስብሸዋ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሰብሳቢ፣
6ኛ) አርበኛ ዮሀንስ ንጉሱ የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ሰብሳቢ፣
7ኛ) አርበኛ ኤርምያስ ጥጋቤ የአፋብን ሎጅስቲክ መምሪያ ኃላፊ፣
8ኛ) አርበኛ ደሞዝ ግዳፍ የአፋብን ወታደራዊ መረጃና መገናኛ መምሪያ ኃላፊ
9ኛ) አርበኛ አበበ ሙላቱ የአፋብን ወታደራዊ ቃል አቀባይ በማድረግ መድቧል። በቀሪ የኃላፊነት ቦታወች ላይ የሚመደቡ አመራሮችን ወደፊት የምናሳውቅ ይሆናል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ፖሊት ቢሮ
1🙏1
አስደንጋጭ የአሜሪካን ኢንባሲ መግለጫ
1👏1🙏1