ዓለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.38K subscribers
4.12K photos
329 videos
17 files
2.15K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሰበር የድል ዜና!!!

የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት ዙ-23 ተኳሽን ጨምሮ በፋኖ ብርቱ ክንድ እየተረፈረፈ ይገኛል።

የአገዛዙ ግሳንግስ ጥምር ሰራዊት ያለ የሌለ ሰራዊቱን በየአቅጣጫው ሰብስቦ መነሻውን ጎንደር በማድረግ ወደ ደልጊ ከተማ ከገባ በኃላ ትናንት መጋቢት 13/2018 ወደ አለፋ ወረዳ ሻሁራ ከተማ ለመግባት ሙሉ ቀኑን በእግሩ ሲማቅቅ ሲወጣ ሲወርድ የዋለ ሲሆን ተናዳፊዎቹ አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ የመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ቋራ ኦሜድላ ክ/ር፣ ካራማራ ክ/ር እና አድዋ ክ/ር በጦር መሀንዲሶች በኮሩ ም/ሰብሳቢ አርበኛ ባበይ አንባየ፣ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ በሊሁን ጌታቸው ፣ ዘመቻ አርበኛ ጌታቸው አማረና በሁሉም የጦር ጠበብት የክ/ር ወታደራዊ አዛዦችና ዘመቻዎች እየተመራ እንዲሁም አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጌምድር ክ/ር ጣና ብርጌድ በአንድ በመጣመር የጠላትን ሰራዊት ስቦ ወደ ሙት ወረዳ ቀለበት ውስጥ በማስገባት ቀኑን ሙሉ በየሜዳው የከባድ መሳሪያ የጭንቀት ተኩስ ሲያደርግ የዋለ ሲሆን አድፍጦ የተሻለ አሰላለፍ ሲያመቻች የዋለው ነበልባሉ ፋኖ ከቀኑ 9:00 ስአትገደማ ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ስአት አምቹሀ ከምትባል ቀበሌ በሁሉም አቅጣጫ በቀጥታ በተሰነዘረበት የማጥቃት ዘመቻ የአብይ ተስፋ ቆራጭ ሰራዊት ክፋኛ ሲረፈረፍ አምሽቷል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ከመሆኑ ባሻገር ሰፊ ቀጠና ሸፍኖ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ወደ አንድ ተሰብስቦ ተራራ ላይ በመውጣት ከበባ ውስጥ የገባው የጠላት ሀይል ሙሉ ሌሊቱን የጭንቀት ተኩስ ሲተኩስ አድሯል። ስለሆነም በቀጣይ የዜና መሰናዶአችን አህዛዊ የድል ዜናዎችን አጠናክረን የምናቀርብ ይሆናል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ
መጋቢት 14/2018
🙏5
አሳዛኝ ዜና!

የወለጋዋ አይሻ ሰይድ የግፍ ግድያ በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ላይ ተደገመ!

በሰሜን ወሎ ዞን በላስታ ወረዳ ከላሊበላ ኤሪፖርት 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዉ 07 ቀበሌ (እርፋ ቀበሌ) ላይ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ የ65 እና 61ኛ ክፍለ ጦር ተብለዉ በብልፅግናዉ መንግስት የሚጠሩት የሰራዊት አባላት ህፃን ሐብታም እያያዉ የምትባል የሰባት ዓመት ልጅ መጋቢት 4 ቀን አፍኖ በመዉሰድ አድራሻዋን ያጠፋ ሲሆን ቤተሰቦቿም ላሊበላ ከተማ እና ላሊበላ ኤሪፖርት (ሽምሽሃ) በመሄድ ልጃቸዉን እንዲሰጧቸዉ የመከላከያ አባላት ተብየዎች ቢማፀኑም በቂ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አትቅረቡን የሚል ማስፈራሪያና ዛቻ አደረሱባቸው::

ማህበረሰብም ጉዳዩን ለቤተሰቦቿ ሳይተዉ የኛም ጉዳይ ነዉ በማለት ላስታ በሚገኙ ሰንሰለታማ ተራራዎች እና ጫካወች እንደ ህዝብ ፍለጋ በመሰማራት ከ 10 ቀናቶች ፍለጋ በኋላ በዛሬዉ ዕለት ማለትም በቀን 14/2018 ዓ.ም በተለምዶ ጠዳ ተብሎ ከሚጠራዉ ጫካ ላይ በግፍ ተገድላ በመጣሉ ምክንያት በጅብ እና በአሞራ ተበልታ ቁርጥራጭ የሰዉነት ክፍሎቻ ሊገኙ ችለዋል።

መደመር ለአማራ መቀነስ ሲሆን አንድነት ሲባል በተናጥል የመግደያ መንገድ ምርጫ የአማራ የመግደያ ሰርተፍኬት መሆኑን ከተረዳን ዉለን አድረናል።

ይህ የሚያሳየዉ አማራን እንደ ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት በማኒፊስቶዉ አዘጋጅቶ እንደተነሳ እንጅ የታጠቀዉን ሃይል ለመዋጋት አለመሆኑን የ7 አመት ህፃን ልጅን በመግደል አሳይቷል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት14 /2018 ዓ.ም
💔41
አራት የአድማ ብተና አባላቶች አንድ ብሬን እና ሶስት ክላሽ በመያዝ የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ::

ከብልፅግ ና አገዛዝ ጋር በመወገን ህዝባችን ላይ ዘር ማጥፋት አንፈፅምም በቃን ያሉ የ አድማ ብተና አባላቶች አንድ ብሬን እና ሶስት ክላሽ በመያዝ ወደ አፋብን ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ተቀላቀሉ:: የኮሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::

ከዚህ ጋር ተያይዞም የ106ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ሻለቃ ሃብቴ እባቡ በአቀባበል ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የእንኳን ወደ ህዝባችሁና ወንድሞቻችሁ ፋኖዎች ደህና መጣችሁ መልክትን አስተላልፈዋል።

የፋኖን የህልውና ትግል የተቀላቀሉ የ አድማ ብተና አባላቶች አማራን ህዝብ የህልውና አዳጋ ለመቀልበስ መጥተናል ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም በአድማ ብተና ውስጥ ሙሉ ሰራዊቱ ወደ ፋኖ መቀላቀል ይፈልጋል። የአማራ ፋኖ አንድነት (አፋብን) ከተመሰረተ በኋላ ጠቅላላ ሰራዊቱ ወደ ፋኖ መቀላቀል ይፈልጋል ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 14/2018 ዓ.ም
🙏41
በምርጫ ስም ተጨማሪ የአማራ ሕዝብን የመጨፍጨፊያ ጊዜ ለማገኘት የምርጫ ቁሳቁስ ይዘው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአገዛዙ ካድሬዎችና ወታደሮች ላይ በተከፈተ ድንገተኛ ጥቃት ከ14 በላይ የሚሆኑት ሙትና ቁስለኛ ተደረጉ!

በምስራቅ አማራ ቀጠና ምዕራብ ወረዳዎች ቲርቲራና ልጓማ አከባቢዎች ትናንት መጋቢት 13/2018 ዓ/ም አመሻሹን ከፍተኛ ቁጥር ባለው ወታደር ታጅበው የምርጫ ቁሳቁስ ይዘው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ባንዳዎች ላይ ከባድ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አባናደው ክፍለጦር በሁለት ቦታዎች ላይ በወሰደው የደፈጣ ጥቃት በአማራ ሕዝብ ስቃይና ሞት ላይ በምርጫ ስም የሚሳለቁ የአገዛዙ ተዋናዮችን ሙትና ቁስለኛ አድርጓቸዋል።

በቲርቲራ አከባቢ ልዩ ስሙ ባከት ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በክፍለጦሩ ስር የሸዋንግዛው ሬጅመን አባላት በተፈፀሙት የደፈጣ ጥቃት ሁለት ወታደሮች ሲገደሉ፡ አምስት ወታደሮችና ካድሬዎች ደግሞ ቁስለኛ ተደርገዋል።

በተመሣሣይ በመጀመሪያው ዙር ባከት ላይ ጥቃት ለፈፀመባቸው ጓዶቹ እገዛ ለማድረግ የተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል፡ በልጓማ አከባቢ በአባ ናደው ክፍለጦር ስር በመሀመድ ዳውዲ ሬጅመንት አባላት ተቆርጦ የደፈጣ እርምጃ ተወስዶበታል።

በዚህም ሦስት ወታደሮችና ካድሬዎች ሲገደሉ ከአምስት በላይ የሚሆኑት ደግሞ በከባድ ሁኔታ ቆስለዋል።

በድምሩ በሁለቱ በታዎች ላይ 14 ወታደሮችና ካድሬዎች ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ ከክላሽንኮቭ መሣሪያ ጀምሮ ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች በፋኖ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ይሄንን ዘር ጨፍጫፊና ሀገር አውዳሚ የአገዛዝ ስርዓት በምርጫ ስም ሕጋዊ ከለላ ሰጥቶ እድሜው እንዲራዘም ለማድረግ በተዋናይነት ከመሳተፍ ጀምሮ ለምረጡኝ ቅስቀሳ በሚሳተፉ ባንዳዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 14/2018 ዓ.ም
🙏5
በመከላከያ ሰራዊት አባላት ታፍና የነበረችው የ7 ዓመቷ ህፃን አስከሬኗ ተቆራርጦ ተጥሎ ተገኘ!

ህፃኗ በመከላከያ ሰራዊቱ ከታፈነች ከ10 ቀናት በኋላ ነው አስከሬኗ በጫካ ተጥሎ ከዱር አውሬና ከሰማይ አሞራ የተረፈው የሰውነት ክፍሏ ተቆራርጦ ተጥሎ የተገኘው።

በምስራቅ አማራ ቀጠና ላስታ ወረዳ ልዩ ስሙ እርፋ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ሀብታም እያያው የተባለች የ7 ዓመት ህፃን በመከላከያ ሰራዊት ታፍና ነበረ።

ህፃኗ የታፈነችው መጋቢት 04/2018 ዓ/ም ሲሆን፡ "የፅንፈኛ ዘር ነሽ" በሚል ህፃኗን ያገቷት በሌተናል ጄነራል አሰፋ ቸኮል በሚመራው በሰሜን ምስራቅ ዕዝ ውስጥ በ803ኛ ኮር ስር የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሆናቸውን ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

ከሹምሹሃ አየር ማረፊያ በግምት በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው 07 እርፋ ቀበሌ የ7 ዓመቷን ህፃን ያገቱት የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ፡ የህፃኗ ወላጆች ልጃቸውን እንዲሰጧቸው ሲጠይቋቸው "ፋኖ ሲጠፋ እንሰጣችኋለን"  በሚል መሳለቃቸው ተነግሯል።

ይባስ ብሎም የህፃኗ ወላጆችን ድጋሚ ልጃቸውን ብለው ወደ ካምፑ እንዳይመጡ በማስጠንቀቅ ጭምር እንዳባረሯቸው ታውቋል።

ከቀናት በኋላ፡ ህፃኗ ተገድላ መጣሏን የሚጠቁም ጭምጭምታ በመሰማቱ የህፃኗ ወላጆች ከአከባቢው ማሕበረሰብ ጋር በመሆን ፍለጋ ሲያካሂዱ ውለው አድረዋል።

በመጨረሻም ህፃኗ ታግታ ከተወሰደችበት ከመጋቢት 04/2018 ዓ/ም ጀምሮ ከ10 ቀናት በኋላ ዛሬ መጋቢት 14/2018 ዓ/ም በአከባቢው ጠዳ ተብሎ በሚጠራዉ ጫካ ውስጥ አስከሬኗ ተጥሎ ከዱር አውሬና ከሰማይ አሞራ የተረፈው የሰውነት ክፍሏ መገኘቱን መረብ ሚዲያ ከአከባቢው ነዋሪዎች ለማረጋገጥ ችሏል።

አስከሬኑ የህፃኗ መሆኑ የተለየው እገታው ሲፈፀምባት ለብሳው በነበረው ልብስ ነው የሚሉት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ ከፊል አካሏ በጅብ ተበልቷል፡ ከፊሉ ደግሞ በአሞራ እየተበላ እንዳለ ነው የተገኘው ብለዋል።

ህፃኗ ተገድላ ከተጣለች 24 ሰዓታት እንደማያልፋት ከቅሪት የሰውነት ክፍሏ ለማረጋገጥ ተችሏል።

ይህም በአከባቢ ማሕበረሰብ ዘንድ ከባድ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን ይህ ቁጣ ወደ አመፅ እንዳይቀየር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር በአከባቢው መሰማራቱ ታውቋል።

በተጨማሪም የሰራዊቱ አዛዥ ነው የተባለ ብዛት ባላቸው ወታደሮች የታጀበ አንድ የጦር መኮነን ወደ ህፃኗ ቤተሰቦች መልዕክተኛ በመላክ "ስለድርጊቱ ለማንም እንዳይናገሩ፡ በተለይ የሚዲያ አካላት እንዳይሰሙ" በሚል በጥብቅ ማስጠንቀቁ ተሰምቷል።

በተመሣሣይ ከዓመት በፊት በዚኸው በላስታ ወረዳ ሽግላ መንደር ተብሎ በሚመራው አከባቢ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈትና ውጤቷን በመጠባበቅ ላይ የነበረች ጥሩየ አለምነው የተባለች አንዲት ታዳጊ በመከላከያ ሰራዊት ታፍና ከተወሰደች በኋላ ተደፍራና በስለታማ መሣሪያ ተገድላ ተጥላ መገኘቷን በወቅቱ መረብ ሚዲያ የሟች ቤተሰቦችን ዋቢ በማድረግ መዘገቡ አይዘነጋም።

የታዳጊዋ አስከሬን ለምርመራ ወደ ላሊበላ ከተማ ከተወሰደ በኋላ የአስገድዶ መድፈር ድርጊት ተፈፅሞባት እንደነበር በምርመራ ውጤቷ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን፡ የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ ሰባት እና ስምንት ሆነው ታዳጊዋን ሲደፍሩ ሕይወቷ ያለፈባቸው በመሆኑ፡ በዚህም ከሰው ጋር ተጣልታ የተገደለች በማስመሰል አንገቷን በስለታማ መሣሪያ (ካሪያ/ጩቤ) ገዝግዘው በመቁረጥ ከወታደራዊ ካምፑ በቅርብ ርቀት ከነበረ የውሃ ቦይ ውስጥ አስከሬኗን ጥለውት መገኘቱን ነው የሕዝብ ድምፅ የሆነው ጣቢያችን መረብ ሚዲያ በወቅቱ ዘግቦ የነበረው።
4💔3
የአደረጃጀት ዜና!

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር አደረጃጀት በመስራት የኮርና የክፍለ ጦር ስያሜ ሰጠ::

በአፋብን ምኒልክ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለ ጦር መልሶ ማደራጀት ብሎም ስያሜ መስጠት ይገኝበታል።

ስለሆነም ከዚህ በፊት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ይባል የነበረው በአሁኑ አደረጃጀት 105ኛ ኮር በሚል መጠሪያ የተሰየመ ሲሆን በስሩ የሚገኙ ክፍለ ጦሮችንም እንደሚከተለው ሰይሟል::

•45ኛ ክፍለ ጦር (መብረቅ ክፍለ ጦር)

•71ኛ ክፍለ ጦር (አርበኛ አደም አሊ አባ ናደው ክፍለ ጦር)

•47ኛ ክፍለ ጦር (አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር)

•29ኛ ክፍለ ጦር (ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር)

•33ኛ ክፍለ ጦር (ዋሲል ክፍለ ጦር) በሚል ክፍለ ጦሮችን ሰይሞ ለትግል እንዲያመች በማድረግ አደረጃጀቱን አዘምኗል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 15/2018 ዓ.ም
👍2🙏1
ሶስት የፋሽስቱ በልፅግና አገዛዝ ሰራዊት አባላቶች የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ!

የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 83ኛ ክፍለ ጦር ሶስት አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ብልፅግናን በመክዳት የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ!

አላማ ቢስ በሆነ ጦርነት ወገናችንን መውጋታችን ፀፅቶናል ያሉት የሰራዊቱ አባላቶች ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን የተቀላቀሉ ሲሆን አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 15/2018 ዓ.ም
🙏2👍1