ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ)

ዳባት ወረዳ ዳራ ቀበሌ የዓብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊትን መተውታል።

የደጃዝማች 4ኛ ኮር የዘራይ ክፍለ ጦር ሸጋው ብርጌድ
በዳባት ወረዳ ዳራ ቀበሌ ይካቲት 26/2018 ዓ.ም በልዩ ወታደራዊ እቅድ የዓብይ አህመድ እና የብአዴን ታጣቂዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ ወስዷል።

በዚህ ግንባር የተገኘ ድል
🔸21 ጠላት ተደምስሷል።
🔸7 እጅ ሰቶ የተማረከ
🔸 16 የተማረከ ነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ የተማረከ ሲሆን በልውል ያልተቆጠረ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያ ተተኳሽም ተማርኳል።

በቅርቡ በጀግንነት ጀብድ ፈፅመው በተሰው ህያው ጀግኖቻችን አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ) እና አርበኛ ደመላሽ ስመኝ (አዳኙ ነብር) መግነጢሳዊ መንፈስ ተጋግሎ የቀጠለው ወታደራዊ ዘመቻ ጠላትን ድል በመንሳት እየተቋጨ ይገኛል።

ዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ)
ተጠናክሮ ይቀጥላል!!

አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ
ህ/ግንኙነት መምሪያ
🙏4
ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ከህልውና ትግሉ ጎን ለጎን ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚዉል የመንገድ ስራም እየሰራ ይገኛል!

አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር ከህልዉና ትግሉ ጎን ለጎን ለአካባቢዉ ማህበረሰብ የልማት ሰራዎችን እያከነወነ የገኛል።

ህዝቡም ፋኖ እየሰጠዉ ላለዉ አገልግሎትና የልማት የምንገድ ጠረጋ ጎን በጎን አብሮ እያገዘና በልማት ስራዉ እጅግ በጣም ደስተኛ ሁነዉ የበኩላቸዉን አስተዋፆ እያደረጉ ይገኛሉ። የአማራ ህዝብ መሰረተ ልማት እንዳያለማ መንገድ መብራት ዉሃ እና የመሳሰሉት አገልግሎቶች እንዳያገኝ ተደርጓል::

አለፍ ሲል ለአማራ ህዝብ ልማት ሰይሆን መጨፍጨፍያ ድሮን የሩሲያ ይሻላን ወይስ የቱርክ እያለ መገደያችን እየገዛ ባለበት ወቅት በኛዉ ድርጅታች በአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ በልጅ እያሱ ኮር በ24ኛ ክፍለ ጦር እየተሰራልን ያለው ልማት ከልብ እናመሰግናለን ሲሉ ደስታቸዉን ገልፀዋል።

እዉነትም የአማራ ህዝብ ልማት ሳይሆን ከነ ጭራሹም ከገፀ መድር ለማጥፋት የብልፅግናዉ ወንበር አስጠባቂና የስራቱ ተሳታፊ የአብይ ሎሌዎች ካድሪ አማራን ለማጥፍት ከምድር እስከ አየር ሀይል ለማጥፍት ቢያቅድም ቅዥትና ህልም ሁኖ ቀርቶበታል።

ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ አድጎና ተመንድጎ ከህልዉናዉ ትግል ጎን በጎን ለህዝቡ መሰረተ ልማት እያለማ ይገኛል ይህ ትልቅ አቅም እንደደረሰ የሚያሳይ አንዱ የትግሉ ዉጤት ማሳያ ነዉ:: የልማት ስራዉ ቀጣይም በተሻለ ሁኔታ ታቅዶበትና ወደ ፊትም ፋኖ በሚስተዳድራቸዉ ቀበሌና ወረዳዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
🙏2
ሰበር የአደረጃጀት ዜና!

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር የ22ኛ፣ 31ኛ እና 34ኛ ክፍለ ጦር ምስረታ ተጠናቋል።

የጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ አካል የሆነው የደጋው መብረቅ ኮር ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ አስደማሚ ተጋድሎዎችን እየፈፀመ ይገኛል። በስሩ የሚገኙትን አምስት ክፍለጦሮችን በማስተሳሰር እረፍት አልባ አውደ ውጊያወችን በመፈፀም በጠላት ላይ በቀጠናው ፍፁም የበላይነት ወስዷል። ድርጅታችን ባወረደው መምሪያ መሰረት ኮራችንን አሁናዊ የትግላችንን አቋም በሚመጥን መልኩ የኮር አደረጃጀት ማሻሻያ አድርገናል።

በአፋብን ምኒልክ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለ ጦር መልሶ ማደራጀት ለበርካታ ቀናት ውይይት ከተደረገበት በኋላ አደረጃጀቱ ተሰርቷል። ከዚህ በፊት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ም/አ/ቀ ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር በሚል ይጠራ የነበረው፤አሁን 106ኛ ኮር በሚል መጠሪያ ስም ተሰይሟል።

እንዲሁም በደጋው መብረቅ ኮር ስር የነበሩትን ታሪካዊቷ ፅናት ክፍለጦር ፣ ጀብደኛዋ አንሻ ሰይድ ክፍለጦር፣ ምሽግ ሰባሪዋ ደጀን ክፍለጦር፣ ነበልባሏ ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለጦር፣ ተናደረፊዋ ሰንጥቅ ክፍለጦሮች እንዲሁም የወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አሃድ የነበሩትን ክፍለጠሮች ወደ ሶስት በማዋሃድ አዲሱን 106ኛ ኮርን አዋቅረናል።

ስለሆነም የሶስቱ ክፍለ ጦሮች ስያሜ፦
22ኛ
31ኛ እና
34ኛ ክፍለጦር
ተብለው ስያሜው በመስጠት የኮሩን መልሶ ማደራጀት ተግባር ተጠናቋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
👍2🙏1