ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የካቲት 25/2018
ደቡብ ጎንደር
አምዳቤት ወረዳ
ጃራ-ገዳ ከተማ
ቀደም ብሎ በአንደኛ ኮር
ተማርከው የነበሩ
አስፈላጊው ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ትግል እንዲገቡ ወይም ሰላማዊ ኑሮ እንዲኖሩ ተደርጓል።
🙏3
የደጋው መብረቅ ኮር በአንሻ ሰይድ ክፍለ ጦር በመቄት ወረዳ በሁለት ግምባር የብልፅግና ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ ድል ተጎናፅፈዋል::

አንሻ ሰይድ ክፍለ ጦር ከሲሲጊ እስከ መቅረጫ የካቲት 25/2018 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 ሰዓት ላይ ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት በዘለቀው አውደ ውጊያ የፋሽስቱን ሰራዊት 360° ከበባ ውስጥ አስገብተው ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ አድርሰውበታል፤ውሀ ውሀ እስኪል ድረስ ሙትና ቁስለኛ አድርገው ድል ተጎናፅፈዋል::

በሁለቱም ግምባር ላይ የክፍለ ጦሩ ግስላ ፋኖዎች ጥላት ከመሸገበት ጉሬ ድረስ ዘልቀው በመግባት የብርሀኑ ጁላን ሰራዊት ከአስራ ሰባት (17) በላይ እስከወዲያኛው የተሸኙ ሲሆኑ፤ በውል ቁጥሩ ያልታወቀ ቁስለኛ በመኪና ጭኖ ወደ ፍላቂት ሆስፒታል ሲያጉዝ አምሽቷል። በተጋድሎው 15 ክላሽ እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርከዋል::

የብርሀኑ ጁላ መልክተኞችም ጨለማን ተገን በማድረግ ሙትና ቁስለኛ ሰራዊታቸውን ወደ ፍላቂት ከተማ ሲያመላልሱ ማምሸታቸውን ከአባባቢው ማህበረሰብ የተገኘ መረጃ ጭምር የታወቀ ሲሆን በሌላ መልኩ ፍላቂት ላይ ተወሽቆ የድሀን ልጅ እየላከ እሳት አረር ላንቃ ላይ የሚወረውረው የጁላው ኮሎኔል ለበላይ ጋግስተር አለቆቹ ደውሎ "ድረሱል አስበላችሁኝ! በፋኖ ተከብቢያለሁ"ቢልም ዙር ግጠም የጥላት በሮች ተከርችመው ተገርፏል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
🙏4
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና የአማራን አርሶ አደር በረሃብና በድህነት የማንበርከክ ሴራ በወግዲ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

​የብልፅግናው ፀረ-አማራ ቡድን የአማራን ሕዝብ ትጥቅ አስፈትቼ አምበረክካለሁ በሚል የጀመረው የሴራ ተስፋ አድማሱን አስፍቶ ወደ ዘር ማጥፋት በተጨማሪም ደግሞ ወደ ንብረት ውድመትና ዘረፋ ተሸጋግሯል። በደቡብ ወሎ ወግዲ 05 ቀበሌ (ጡንጊ) በአርሶ አደሩ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ የቡድኑን ማንነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

​የአቶ ጀማል አህመድ ጥሪት የሆነው ሁለት ወፍጮ ተዘርፎና ወድሟል። የሚገርመው ግፍ ግን እህሉን ከአፈርና ከአሸዋ ጋር መቀላቀላቸው ነው! ይሄ በቀጥታ "ካልራባችሁ አትገዙም" የሚል የአገዛዙ መልዕክት ነው። አንዲት ክበድ ላምና በሬ ሰርቀው መሄዳቸው ሳያንስ፣ ቤታቸውን እንዳልነበረ አድርገውታል!

​በጎረንጅ ቀጠናም ሕዝቡ ራሱን የሚከላከልበትን የግል ንብረቱን 63 መሣሪያዎች ነጥቀዋል። ይህ በግልጽ የታወጀ የዘር ማጥፋት አካል ነው። አርሶ አደሩን ሀብት አልባ በማድረግ የእለት ጉርሱን በማሳጣትና መከላከያ መሣሪያውን በመንጠቅ ለጠላት አሳልፎ ለመስጠት የሚደረግ ስልታዊ ጥቃት ነው።

​ይህ ግፍ በዝምታ ሊታለፍ አይገባም! ዛሬ በጀማል አህመድ ላይ የደረሰው ነገ በሁላችንም ደጅ መድረሱ አይቀርምና ሁሉም አማራ ራሱን ከፈፅሞ ጥፋት ይከላከል ዘንድ ዛሬም ጊዜው አልረፈደምና ከፋኖ ጋር ይሰለፍ የዘወትር መልክታችን ነው!

ሚዲያዎችና ማህበራዊ አንቂዎችም የአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት በተደራጀ መንገድ ህዝባችን ብሎም አለማቀፉ ማህበረሰብ እንዲያውቀው እያደረጋችሁ እንዳላችሁ የሚታወቅ ሲሆን አሁንም የህዝባችን መከራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመምጣቱ እየሰራችሁ ካላችሁት በላቀና በተቀናጀ መንገድ እንድትሰሩ መልክታችንን እናስተላልፋለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
💔3
ዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ)

ዳባት ወረዳ ዳራ ቀበሌ የዓብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊትን መተውታል።

የደጃዝማች 4ኛ ኮር የዘራይ ክፍለ ጦር ሸጋው ብርጌድ
በዳባት ወረዳ ዳራ ቀበሌ ይካቲት 26/2018 ዓ.ም በልዩ ወታደራዊ እቅድ የዓብይ አህመድ እና የብአዴን ታጣቂዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ ወስዷል።

በዚህ ግንባር የተገኘ ድል
🔸21 ጠላት ተደምስሷል።
🔸7 እጅ ሰቶ የተማረከ
🔸 16 የተማረከ ነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ የተማረከ ሲሆን በልውል ያልተቆጠረ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያ ተተኳሽም ተማርኳል።

በቅርቡ በጀግንነት ጀብድ ፈፅመው በተሰው ህያው ጀግኖቻችን አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ) እና አርበኛ ደመላሽ ስመኝ (አዳኙ ነብር) መግነጢሳዊ መንፈስ ተጋግሎ የቀጠለው ወታደራዊ ዘመቻ ጠላትን ድል በመንሳት እየተቋጨ ይገኛል።

ዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ)
ተጠናክሮ ይቀጥላል!!

አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ
ህ/ግንኙነት መምሪያ
🙏4