ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአደረጃጀት ዜና

አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን ) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር የአመራር ሪፎርም ሰራ!!!

የትግልን ሁለተናዊ አንድነት፣ አቅምና ጉልበት እሚሻ መሆኑን የተረዱ ብልሆች ተቋም መሰባሰቢያ መሆኑን አምነው አንድ ቤታቸውን ይቀልሳሉ።  በህግ እሚመራ ተቋም ደግሞ የስራዎቹ ሁሉ ማሰርያ ፣ የግቦች ሁሉ ቁልፍ መሆኑን ተረድቶ የትግል መሰረቱ  አደረጃጀት በመሆኑ እንደ ንስር  ራሱን አድሶ ብቅ ያለው  206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ከትናት በተሻለ የአመራር ሪፎርም  ለጠላት ራስ ምታት ለወገን ደግሞ ኩራት የሆነ ተቋም ገንብቶ ብቅ ብሏል ።

በአባታችን ሜጀር ጀኔራል ከፍያለው ደሴ የተሰየመው ኮራችን ባለፉት አንድ አመት  በርካታ አውደ ውጊያዎችን በማድረግ በጠላት ላይ ከባድ ክንዱን ሲያሳርፍ  ቆይቷል ከትናት  የተሻለም  የአመራርነት አቅሙ ላይ በመገኘት የቀጠናው አኩሪ ኮከብ  ሆኖ ለመውጣት እንደሚከተለው  የአመራር መዋቅሩን ሰርቷል ።

1. ዋና ወታደራዊ አዛዥ------  አርበኛ የቆዬ አበጀ
2.ምክትል ወታደራዊ አዛዥ----አርበኛ ኪሮስ አበባው
3. ዘመቻ ኃላፊ -----------አርበኛ ምህረቱ አንዳርጌ
4. መረጃና ደህንነት ኃላፊ----------#####
5.ወታደራዊ ምልመላና ስልጠና ኃላፊ ------አርበኛ ጌትነት ምስጋናው
6. ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ ኃላፊ-----አርበኛ ሰለሞን አዳሙ
7. ጽ/ቤት ኃላፊ---------------አርበኛ ዶ/ር አድማሱ አለምነው
8. ወታደራዊ አስተዳደር ኃላፊ------አርበኛ አያና ሆነ
9. ሎጅስቲስቲክ ኃላፊ----------አርበኛ አይናለም ጥላሁን
10. ፋይናንስና ንብረት ኃላፊ ----አርበኛ ባንቲደር እውነቱ
11. ቁጥጥርና ኦዲት ኃላፊ-------አርበኛ እያዩ በዜ
12. ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ----አርበኛ ልየው ተካልኝ
13. አደረጃጀት ኃላፊ------አርበኛ ዋለ ፈንታሁን
14. ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ----አርበኛ ጋሻው ግዛት
15. ሕዝብ አስተዳደር ኃላፊ---አርበኛ ገበየሁ አማረ
16. ህግ ጉዳይ   ኃላፊ---አርበኛ ኢ/ር አንዳርጌ እሸቴ
ሆኖ  ተደራጂቷል።

ስለሆነም ኮራችን ይህን ሪፎርም ሲሰራ  ከእንደዚህ ቀደሙ ጠላትን በማንበርከክ የህልውና ስጋት ውስጥ ያለውን ማህበረሰባችንን ነጻ ማውጣትና የቀጠናው አቅም እንዲሆን ጭምር ነው ።

ድል ለአማራ ፋኖ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ!!!
የካቲት 25/ 2018 ዓ.ም
🙏31
የካቲት 25/2018
ደቡብ ጎንደር
አምዳቤት ወረዳ
ጃራ-ገዳ ከተማ
ቀደም ብሎ በአንደኛ ኮር
ተማርከው የነበሩ
አስፈላጊው ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ትግል እንዲገቡ ወይም ሰላማዊ ኑሮ እንዲኖሩ ተደርጓል።
🙏3
የደጋው መብረቅ ኮር በአንሻ ሰይድ ክፍለ ጦር በመቄት ወረዳ በሁለት ግምባር የብልፅግና ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ ድል ተጎናፅፈዋል::

አንሻ ሰይድ ክፍለ ጦር ከሲሲጊ እስከ መቅረጫ የካቲት 25/2018 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 ሰዓት ላይ ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት በዘለቀው አውደ ውጊያ የፋሽስቱን ሰራዊት 360° ከበባ ውስጥ አስገብተው ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ አድርሰውበታል፤ውሀ ውሀ እስኪል ድረስ ሙትና ቁስለኛ አድርገው ድል ተጎናፅፈዋል::

በሁለቱም ግምባር ላይ የክፍለ ጦሩ ግስላ ፋኖዎች ጥላት ከመሸገበት ጉሬ ድረስ ዘልቀው በመግባት የብርሀኑ ጁላን ሰራዊት ከአስራ ሰባት (17) በላይ እስከወዲያኛው የተሸኙ ሲሆኑ፤ በውል ቁጥሩ ያልታወቀ ቁስለኛ በመኪና ጭኖ ወደ ፍላቂት ሆስፒታል ሲያጉዝ አምሽቷል። በተጋድሎው 15 ክላሽ እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርከዋል::

የብርሀኑ ጁላ መልክተኞችም ጨለማን ተገን በማድረግ ሙትና ቁስለኛ ሰራዊታቸውን ወደ ፍላቂት ከተማ ሲያመላልሱ ማምሸታቸውን ከአባባቢው ማህበረሰብ የተገኘ መረጃ ጭምር የታወቀ ሲሆን በሌላ መልኩ ፍላቂት ላይ ተወሽቆ የድሀን ልጅ እየላከ እሳት አረር ላንቃ ላይ የሚወረውረው የጁላው ኮሎኔል ለበላይ ጋግስተር አለቆቹ ደውሎ "ድረሱል አስበላችሁኝ! በፋኖ ተከብቢያለሁ"ቢልም ዙር ግጠም የጥላት በሮች ተከርችመው ተገርፏል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
🙏4
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና የአማራን አርሶ አደር በረሃብና በድህነት የማንበርከክ ሴራ በወግዲ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

​የብልፅግናው ፀረ-አማራ ቡድን የአማራን ሕዝብ ትጥቅ አስፈትቼ አምበረክካለሁ በሚል የጀመረው የሴራ ተስፋ አድማሱን አስፍቶ ወደ ዘር ማጥፋት በተጨማሪም ደግሞ ወደ ንብረት ውድመትና ዘረፋ ተሸጋግሯል። በደቡብ ወሎ ወግዲ 05 ቀበሌ (ጡንጊ) በአርሶ አደሩ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ የቡድኑን ማንነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

​የአቶ ጀማል አህመድ ጥሪት የሆነው ሁለት ወፍጮ ተዘርፎና ወድሟል። የሚገርመው ግፍ ግን እህሉን ከአፈርና ከአሸዋ ጋር መቀላቀላቸው ነው! ይሄ በቀጥታ "ካልራባችሁ አትገዙም" የሚል የአገዛዙ መልዕክት ነው። አንዲት ክበድ ላምና በሬ ሰርቀው መሄዳቸው ሳያንስ፣ ቤታቸውን እንዳልነበረ አድርገውታል!

​በጎረንጅ ቀጠናም ሕዝቡ ራሱን የሚከላከልበትን የግል ንብረቱን 63 መሣሪያዎች ነጥቀዋል። ይህ በግልጽ የታወጀ የዘር ማጥፋት አካል ነው። አርሶ አደሩን ሀብት አልባ በማድረግ የእለት ጉርሱን በማሳጣትና መከላከያ መሣሪያውን በመንጠቅ ለጠላት አሳልፎ ለመስጠት የሚደረግ ስልታዊ ጥቃት ነው።

​ይህ ግፍ በዝምታ ሊታለፍ አይገባም! ዛሬ በጀማል አህመድ ላይ የደረሰው ነገ በሁላችንም ደጅ መድረሱ አይቀርምና ሁሉም አማራ ራሱን ከፈፅሞ ጥፋት ይከላከል ዘንድ ዛሬም ጊዜው አልረፈደምና ከፋኖ ጋር ይሰለፍ የዘወትር መልክታችን ነው!

ሚዲያዎችና ማህበራዊ አንቂዎችም የአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት በተደራጀ መንገድ ህዝባችን ብሎም አለማቀፉ ማህበረሰብ እንዲያውቀው እያደረጋችሁ እንዳላችሁ የሚታወቅ ሲሆን አሁንም የህዝባችን መከራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመምጣቱ እየሰራችሁ ካላችሁት በላቀና በተቀናጀ መንገድ እንድትሰሩ መልክታችንን እናስተላልፋለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
💔3
ዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ)

ዳባት ወረዳ ዳራ ቀበሌ የዓብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊትን መተውታል።

የደጃዝማች 4ኛ ኮር የዘራይ ክፍለ ጦር ሸጋው ብርጌድ
በዳባት ወረዳ ዳራ ቀበሌ ይካቲት 26/2018 ዓ.ም በልዩ ወታደራዊ እቅድ የዓብይ አህመድ እና የብአዴን ታጣቂዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ ወስዷል።

በዚህ ግንባር የተገኘ ድል
🔸21 ጠላት ተደምስሷል።
🔸7 እጅ ሰቶ የተማረከ
🔸 16 የተማረከ ነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ የተማረከ ሲሆን በልውል ያልተቆጠረ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያ ተተኳሽም ተማርኳል።

በቅርቡ በጀግንነት ጀብድ ፈፅመው በተሰው ህያው ጀግኖቻችን አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ) እና አርበኛ ደመላሽ ስመኝ (አዳኙ ነብር) መግነጢሳዊ መንፈስ ተጋግሎ የቀጠለው ወታደራዊ ዘመቻ ጠላትን ድል በመንሳት እየተቋጨ ይገኛል።

ዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ)
ተጠናክሮ ይቀጥላል!!

አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ
ህ/ግንኙነት መምሪያ
🙏4