ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር የአመራርና የክፍለ ጦር መልሶ ማደራጀት አካሄደ!

የካቲት:-23/2018 ዓ/ም

እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ እያለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ወቅቱን የዋጀ የፋኖ አመራርና የክፍለ ጦሮች አደረጃጀት ለተከታታይ ሦስት ቀናት በተደረገ ብስለት የተሞላበትና በስክነት በመወያየት የክፍለ ጦሮች አደረጃጀትና ስያሜ እንዲሁም የኮሩን ስያሜና አመራር መልሶ ማደራጀት እንደሚከተለው ሰርቷል ፤ በድጋሜ እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ።

1ኛ. የኮሩ ስያሜ:- ቀድሞ ከነበረው ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ወደ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር በሚል ስያሜው ተቀይሯል::

2ኛ. የክፍለ ጦሮች መልሶ ማደራጀትን በተመለከተ ኮሩ ከነበረው ስምንት ክፍለ ጦሮችና ሁለት ብርጌዶች ለአሰራርና ቁጥጥር ያመች ዘንድ ወደ አምስት ክፍለ ጦር የተደራጄ ሲሆን :-
2.1. ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር፣ እሸት ክፍለ ጦርና ዋግሹም ብርጌድ በአንድ በመዋሀድ 19ኛ ክፍለ ጦር ፣
2.2. ተከዜና ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦሮች በመዋሀድ 21ኛ ክፍለ ጦር፣
2.3. ኃይሉ ከበዴና ጥራሪ ክፍለ ጦሮች በመዋሀድ 14 ክፍለ ጦር፣
2.4. ውባንተ አባተና ራስ አንችም ክፍለ ጦሮች በመዋሀድ 81ኛ ክፍለ ጦር እንዲሁም፣
2.5. ከሁሉም ክፍለ ጦሮች በማውጣጣት የተቋቋመው ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ክፍለ ጦር 16ኛ ክፍለ ጦር በሚል የክፍለ ጦሮች መልሶ ማደራጀት ተሰርቷል።

3ኛ. የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር የአመራር መልሶ ማደራጀት የተሰራ ሲሆን:-

1. ኮር ሰብሳቢ:- አርበኛ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙሉዬ
2. ኮር ም/ሰብሳቢ:- አርበኛ ታዘበው ሻምበል
3. ወታደራዊ አዛዥ:- አርበኛ ኮማንዶ ብርሐን አሰፋ
4. ፖለቲካ ዘርፍ መምሪያ:- አርበኛ በሪሁን ደምሌ
5. ኮር አስተዳደር:- አርበኛ ሞላ አዳነ
6. መረጃና ደህንነት:-𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥
7. ምክትል ወታደራዊ አዛዥ:- አርበኛ ጣሰው አለልኝ
8. ዘመቻ መምሪያ:- አርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ
9. ምክትል ዘመቻ (ስምሪት):- አርበኛ አያናው እንየው
10. መገናኛና ኦፕሬተር:- አርበኛ አማሪው አያናው
11. ሎጅስቲክ መምሪያ:- አርበኛ መልኩ አለምዬ
12. ኦርዲናንስ መምሪያ:- አርበኛ ብርቁ አራጋው
13. ጥገና ክፍል:- መቶ አለቃ ተስፋዬ አበበ
14. ስልጠና መምሪያ:- ሃምሳ አለቃ መልካሙ ገበየሁ
15. ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ:- አርበኛ ፀጋዬ አካልነው
16. ህዝብ ግንኙነት መምሪያ:- አርበኛ ቢሆነኝ ቢያበይን
17. ህዝብ አስተዳደር መምሪያ:- ሃምሳ አለቃ መንግስቱ ካሳ
18. አደረጃጀት መምሪያ:- አርበኛ ጋሻው አበበ
19. ህግ ክፍል:- አርበኛ ዋኘው አደራው
20. ምክትል ህግ ክፍል:- ሳጅን አድሱ አራጋው
21. ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ:- አርበኛ ግርማ ቅባቴ
22. ሴቶች ጉዳይ መምሪያ:- አርበኛ አባይ ውበቴ
23. ፋይናንስ መምሪያ:- አርበኛ ሲሳይ ተስፋው
24. የሰው ኃይል መምሪያ:- አርበኛ ጥጋቡ ሲሳይ
25. ሐብት አፈላላጊ:- አርበኛ አለበል ነጋሽ
26. ጤና መምሪያ:- አርበኛ ምስጋናው አዱኛው
27. ኦዲተር:- አርበኛ ባለሟል ሽመልስ
28. ምክትል መረጃና ደህንነት:-𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥
29. ፀረ-መረጃ:- 𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥
30. ወታደራዊ አማካሪ :- አርበኛ ተመቼ ቢራራ
31. ፖለቲካዊ አማካሪ:- አርበኛ ፍቅረማርያም ደሴ ሆነው በመመረጥ ኮሩ የአመራርና የኮር መልሶ ማደራጀትና የስያሜ ለውጥ ከዛሬ የካቲት 23/2018 ዓ/ም ጀምሮ ያደረገ መሆኑን እናሳውቃለን።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
1🙏1
አፋብን |ቴዎድሮስ ዕዝ
ዘመቻ ሽመልስ በአድዋ ድል መታሰቢያ 206ኛ ኮር በአምስት ግምባሮች በከፈተው የተቀናጀ ማጥቃት ደማቅ ድል አስመዝግቧል።
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
=====================================
በወርሀ የካቲት የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምልክት በሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን በልዩ ግዳጅ ታሪክ ሰርቶ በጃዊ በተሰዋው እንቁ ታጋይ በሽመልስ ዘመቻ ያወጀው 206ኛ ኮር፤ በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 10:00 ጀምሮ በከፈተው የተጠናከረ ውጊያ በውሀ ጋኑ የመሸገውን ጠላት 14ኛ ክ/ጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ሻለቃ በሞርተር በመታገዝ ባደረገችው ማጥቃት ጠላትን በምሽጉ አንገቱን ቀልተዋለች።

ባልተጠበቀ ሰዓት የታቀደ ውጊያ የከፈተው 206ኛ ኮር በደብረ ማርቆስ ከተማ እስከ ንጋቱ 1:00 በመፋለም አስደናቂ ጀብድ የፈፀመ ሲሆን ፤በተመሳሳይ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 4:00 ሰዓት በሊባኖስ ከተማ የመሸገውን ጠላት የተናነቀው 14ኛ ክ/ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ በጠላት አስክሬን ላይ እየተረማመደ የማይደፈሩ የሚባሉ የቁም ምሽጎችን ሲንዱ አርፍደዋል ። በዚህ አውደ ውጊያ የጠላት የጦር አመራሮች ጨምሮ ሚኒሻና አድማ ብተናዎች መገደላቸው ተረጋግጧል።

ጠላት እንዳይተሳሰር ከደብረ ማርቆስ ደጀን ቁይ ድረስ መጠነ ሰፊ ጥቃት የከፈተው 206ኛ ኮር የጠላትን ዋና ወታደራዊ ካምፕ አድርጎ የተቀመጠበትን የየትኖራ ወታደራዊ ሰፈር በሞርተር በመደብደብ የኃይል ሚዛኑን ያዛባው 34ኛ ክ/ጦር በደጀን ወረዳ በጉብያ ከተማ በመሸገው ጠላት ላይ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ባደረገው የሙሉ ድምሰሳ ውጊያ ከ60 በላይ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ ጠላት ዙ-23 ሞርተር መድፍና BM ቢጠቀምም የኃይል ብልጫ መውሰድ አልቻለም።

በቅጥል ስሙ "ኮከብ" ተብሎ የሚጠራው የአድማ ብተና ዘመቻ መሪ በተገደለበት የጉብያ ግምባር 34ኛ ክ/ጦር ከጠላት ጋር በመተናነቅ ጠንካራ የሚባሉ ምሽጎችን በቦምብ በማፈራረስ ጠላት የሚመካባቸው የሚኒሻ አመራሮችም ተገድለዋል።

በሌላ ግምባር 24ኛ ክ/ጦር በቁይ ከተማና አቅራቢያ በአደረገችው ማጥቃት የደባይ ጮቄ ሻለቃ የተሰጣትን ግዳጅ በብቃት በመወጣት በርካታ የጠላት ኃይል መደምሰሷም የታወቀ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች እስከ 6:30 በተፈፀመው ማጥቃት ከ125 በላይ የጠላት ኃይል ላይ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል።

በጀግናው ሽመልስ ዘመቻ ሰይሞ የጠላትን ኃይል በማዛነፍና የግንኙነት መስመሩን በመበጣጠስ በጉብያ የመሸገውን ጠላት መሉ ድምሰሳ የፈፀመው 206ኛ ኮር በኮሩ ወታደራዊ አመራሮች እና የክ/ጦር ወታደራዊ አመራሮች ሻለቆችን በማቀናጀት ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ያደረጉት ውጊያ የጠላትን ማዘዣ ጣቢያን ጨምሮ በአምስት ግምባሮች ድል መቀናጀታቸውን የ206ኛ ኮር ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
🙏1
አሳምነው ክፍለ ጦር ወልድያ ሽንቁሩ ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ታላቅ ጀብድ ሰርተው ድል ተጎናፀፉ::

አሳምነው ክፍለ ጦር ከ2ኛ እና 4ኛ ሻለቃ የተውጣጡ አባላቶች ወልድያ ሽንቁሩ ላይ ዛሬ የካቲት 23/2018 ዓ.ም የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ከአንድ ጓድ (ቲም) በላይ የጠላት ሃይል በመደምሰስና ቁጥሩ ያልታወቀ በማቁሰል ታላቅ ጀብድ ሰርተው ድል ተጎናፅፈዋል::

በአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለውን የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ጥምር ሰራዊት በስውር ድርጊያ በደፈጣ እና በመደበኛ ውጊያ እረፍት የመንሳት የማሰላቸት የመደምሰስና የመማረኩ ተጋድሎ እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክፍለ ጦሩ አመራሮች ገልፀዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
2🙏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስበር ዜና
አገዛዙ በአለፋ ከተማ ንፁሃንን በድሮን ጨፈጨፈ
💔1
የትራንስፓርት አገልግሎት በተወሰኑ ቦታዎች ላልተወሰነ ጊዜ መከልከሉን በተመለከተ ከንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የተሰጠ መግለጫ!

የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ከሚንቀሳቀስባቸው ወረዳዎች መካከል በሁለቱ ወረዳዎች ማለትም በመቅደላ እና ተንታ ወረዳዎች ውስጥ ከዛሬ ማለትም የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ የተከለከለ ሲሆን ከዛሬው እለት ጀምሮ ወደ መቅደላ እና ተንታ ወረዳዎች ለመግባት የሚሞክር ወይም ከሁለቱ ወረዳዎች ለመውጣት የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ ላይ እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን እናሳውቃለን::

ማንኛውም የተሽከርካሪ ባለንብረት እና አሽከርካሪ ኮራችን ይፋ ያደረገውን የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ በማክበር ድርጅቱ መልሶ መግለጫ እክካላወጣ ድረስ ራሱን እና ንብረቱን ከጥፋት ይጠብቅ ዘንድ ከወድሁ እንመክራለን ሲል ኮሩ ለሚመለከተው አካል ይድረስልኝ ብሎ በላከው መግለጫ አስታውቋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም
2👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አፋብን በላይ እዝ ሜ/ጄ/ውባንተ 1ኛ ኮር ጉና ክ/ጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ የፋኖ ሰልጣኞች የ130ኛ አድዋን  በአል በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።
ንፁሃን በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተገደሉ!!

የካቲት 24/2018 ዓ.ም

1ኛ. "ወጣት ንጉስ ገዜ" የወይራ ቀበሌ ተወላጅ ባለትዳር እና የአንድ ልጅ አባት የነበር ሲሆን በወይራ ቀበሌ ሞባይል ጥገና የኤሌክትሮኒክስ ሞባይል ጥገና ሰራተኛ የነበር ሲሆን ከቀኑ 9:10 ላይ በወይራ ቀበሌ በግፍ ተገደለ።

2ኛ. "ወጣት ዘላለም አስማማው" የባጃጅ ሹፊር እድሜ 22 ብቸና ደብር ተወላጅ ሲሆን የካቲት 9/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ስዓት በእነማይ ወረዳ የሚገኘው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ ሲገደል አድራሻቸውን ማወቅ ያልቻልናቸው ግለሰቦች መቁሰላቸውን አረጋግጠናል።

በእነማይ ወረዳ እና ሸበል በረንታ የሚገኙ የአገዛዙ ቅጥረኛ የሚኒሻ አባላት የሐይማኖት አባቶች ሳይቀር በማሰርና በማንገላታት በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና መከራ አስመልክቶ ዛሬም ድረስ የንጹሃንን ደም ከማፍሰስ ባሻገር የንጹሃንን ማህበረሰቡ ሃብትና ንብረት እየዘረፉ መሆኑን አረጋግጠናል።

በእነማይ ወረዳ ሆድ አደር ፖሊስ እና አጥቦ አይለብሴ ቅጥርኛ ሚሊሻ የሚመራው የጥፋት ቡድን የካቲት 22/2018 ዓ.ም
1ኛ. ቄስ ታዴ አበባውን
2ኛ. አቶ መኩሪያው ዋለን በማሰር በማንገላታት በእንግርግሮ ሲያዋክቡ ውለዋል።
1ኛ. ከአቶ መኩሪያው ዋለ የኪስ ጥሬ ገንዘብ በመቀበል
2ኛ. ቄስ ታዴ አበባውን በቀጥታ በጥይት እንመትሀለን የፋኖ ተላላኪ ነህ፣ ከፋኖ ጋር በመቀራረብ እርቅ ትፈጽማለህ በሚል አገላለጽ ካሰቃዩትና ካንገላቱት በሆላ ከእስር መልቀቃቸውን ማረጋገጥ ችለናል፡፡ ድርጊቱን ከፈፀሙት አካላት ውስጥ:-
1ኛ. ሚሊሻ ጌታነህ ውበት መሪነት
2ኛ. ሚሊሻ መኳንንት ገናነው
3ኛ. ሚሊሻ ንጉሴ አባቴነህ
4ኛ. ሚሊሻ ተሰው አሰፋ
5ኛ.ሚሊሻ ጌታነህ ውበት የተባሉ የአገዛዙ ቅጥረኛ የሚሊሻ አባላት በወይራ ቀበሌ በተፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት ቸሳትፈዋል።

በሐሰት ፕሮፖጋንዳ ህዝባችንን እያወነባበደ የሚገኘው የአገዛዙ ዘራፊ ሀይል በሸበል በረንታ ወረዳ የዕዱውኃ ከተማ ኖሪ የሆኑ ንፁሀንን ሀብት ንብረት መዝረፉን አረጋግጠናል። ከተዘረፉት ንፁሀን መካከል:-
1ኛ. አብየ እጅጉ የዕዱውኃ ከተማ ኖሪ ሲሆን በመኖሪያ ቤቱ የሚገኝ ሙሉ የቤት እቃ ብፊ፣ ሶፋ፣ 3 አልጋ፣ ሳጥን እና ሙሉ የቤት እቃ በአገዛዙ ተጭኖ መወሰዱን አረጋግጠናል።

በሸበል በረንታ እና እነማይ ወረዳ በአገዛዙ ሀይል በሚፈፀሙ የዝርፊያ እና ውድመት ድርጊቶች ጋር ተያይዞ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ከፋኖ ኃይልች ጋር በትኩረት በመሳጠር ይህንን ድርጊት የሚፈፅሙ ሚሊሻ እና የአገዛዙ ቅጥርኛ ሰራዊትን የመጨረሻ ክንፍ ለመስበር ቆርጦ መነሳት አስፈላጊ መሆኑ እናሳስባለን፡፡

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት

የካቲት 23/2018 ዓ.ም
💔1
ተጠናክሮ በቀጠለው የኮሩ ተጋድሎ ጀግናው ሰራዊታችን በብልፅግናው ቅጥረኛ አየር ወለድ ወራሪ ሃይል ላይ የተቀናጀ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል!!!

    አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
         የካቲት 24 / 2018ዓ.ም

በትላንትናው ዕለት በቀጠናው ከባድ ጉዳት ያስተናገደው የብልፅግናው ዙፋን አስጠባቂ ሌላ ተቀያሪ የጥፋት ሃይል ከመንዝ ማማ ወረዳ ሞላሌ ከተማ እና ከጣርማበር ወረዳ በማስገባት መነሻውን ሰላድንጋይ ከተማ በማድረግ ወደ ጀግኖቹ መንደር ባደረገው እንቅስቃሴ ከአፄ አምደ ፅዮን ኮር ከተወጣጡ የራንቦ እና የምኒሊክ ክፍለጦር ውስን ሻለቆች በቅንጅት እየተገረፈ ይገኛል።

የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር ከአገዛዙ ቅጥረኞች ጋር እያደረገ ባለው ተከታታይ ውጊያ በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ሞጃና ወደራ ወረዳ ሰፊ ቀጠናን የሸፈነ ውጊያ ከጠዋቱ 1:00 ጀምሮ ይሕ ዜና እስከተጠናቀረበት ዕኩለ ቀን ድረስ የኮሩን ሻለቆች ያናበበ የቅንጅት ተጋድሎ እያካሔደ ይገኛል።

የኮሩ ራንቦ ክፍለጦር 2ኛ ነበልባል እና 3ኛ ማንበግር ሻለቆች ብርቃ ሸጋ ገበያ በተባለ ስፍራ የቀይ ቦኔት ለባሹን አየር ወለድ ሰራዊት ሲያራግፉት፣የምኒሊክ ክፍለጦር 1ኛ ሻለቃ እና የራንቦ ክፍለጦር 4ኛ ሻለቆች ባደረጉት ጥምረት ልዩ ቦታው አባ በርሶማ በተባለ አካባቢ በቅንጅት እየተፋለሙ ይገኛሉ።

በተካኼደው የተቀናጀ አውደ ውጊያ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ቃኝ የፋኖ ሰራዊት ከራንቦ ክፍለጦር ቃኝዎች ጋር ባደረጉት የተናበበ ውጊያ የወገን ሃይል የውጊያ የበላይነቱን በያዘበት ጠላት በርካታ የሰራዊቱን አስክሬንና ቁስለኛውን በአምቡላንስ ወደ ሰላድንጋይ ከተማ እያመላለሰ ሲሆን፣ እምቧይ ባድ በተባለ አካባቢ በጀግናው የአማራ ፋኖ  የተቆረጠውን የብልፅግናውን አየር ወለድ ለማስወጣት ተጨማሪ ሃይል ከደብረ ብርሀን ከተማ እያጓጓዘ ይገኛል።

ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በታሪካዊቷ የድላችን ቀን ሙሉ ነፃነታቸውን ያወጁ ሶስት (3) የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፊቼ ከተማ ከሚገኘው የብልፅግናው የመከላከያ መሀንዲስ ክፍለጦር በመክዳት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦርን ከነ መሉ ትጥቃቸው በመቀላቀል የአድዋ የድል በዓልን የአማራ ህዝብ ነፃ አውጭ ከሆነው ከጀግናው የአማራ ፋኖ ጋር በማሳለፋቸው ደስታቸውን እጥፍ ድርብ እንዳረገላቸው ክፍለጦሩ ለኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል በላከው የግንባር መረጃው አስታውቋል !!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ፂዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል!!
የአፋብን ምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራሩ አርበኛ አባተ ካሳነው ባለቤት በፋሽስቱ አገዛዝ ኮምቦልቻ በግፍ ታስራ ትገኛለች:: የአርበኛውን ባለቤት ከህፃናት ልጆቿ ነጥለው ስላሰሯት ልጆች በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛሉ::
🔥1💔1
♦️ጠላት የሚተማመንበት ኮንክሬት ምሽግ በአናቭስት ፋኖዎች ተደረመሰ።
ዛሬ የካቲት 24/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ አፋብን በላይ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ፤ ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ፤ መብረቅ ክ/ጦር እና አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ ኪንፋዝ በለሳ ታዲዎስ ታንቱ ክ/ጦር በጥምረት ጠላት በሚኩራራባት ደጎማ ከተማ ላይ ታሪክ ሰርተዋል።
♦️ የአብይ ወንበር አስጠባቂ ኃይል እስከ መጨረሻው እዋጋበታለው ብሎ የተኩራራበትን የቁርጎ ኮንክሬት ምሽግ በጨበጣና ቦንብ ውርወራ በሰከንዶች ውስጥ ደረማምሶ ለ2 ሰዓታት ያህል በመቆጣጠር ኮንክሬት ምሽጉ ውስጥ ሲርመሰመስ የነበረውን የአብይ ግሬሳ ኃይል ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ወደ ሌሎች ጠላት ሰፍሮ ወደነበረባቸው ሴጋና ጭንጭት ወደተባሉት የጠላት ምሽጎች ማምራት ችለዋል።
ሴጋና ጭንጭት ላይ መሽጎ የነበረው ጠላትም ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።
♦️ከፍተኛ ምትን ያስተናገደው ጠላት የድረሱልኝ ጥሪ ለበላይ አዛዦች ያደረገ ሲሆን ጥሪው የደረሳቸው አለቆችም ማክሰኝት ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን ኃይል ወደ ደጎማ ያንቀሳቀሰ ቢሆንም በጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦርና በጥቁር አንበሳ ክ/ጦር አሃዶች ድንዛዝ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ላይ ክፉኛ ምትን አስተናግዷል።
በዚህም ሰበብ አለቆቹ የሰጡትን ቀጭን ወታደራዊ ትእዛዝ ሳይፈጽም ሙሉ ጊዜውን በመንገድ ላይ እንዲፈጅ ተደርጓል።
** ዙ-23 የተባለውን የቡድን መሳሪያና ድሽቃዎችን ይዞ የተንቀሳቀሰው ጠላት የድንዛዝ ከፍተኛ ቦታዎችን በእሩምታ ተኩስ ሲያርሳቸው አርፍዷል።
** በዙ -23 መሳሪያ የሚድን የመሰለው ጠላት ሙትና ቁስለኛ መሆኑም ታውቋል።
** ማክሰኝት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በቁስለኞች የተጥለቀለቀ ሲሆን ከባድ ቁስለኞች በሪፈር ወደ ጎንደር ሆስፒታል መላካቸውም ታውቋል።
♦️ በአጠቃላይ በዛሬው የደጎማ አውደ ውጊያ የተገኙ ድሎች
✔️ የሞተ ከ70 በላይ / መከላከያና ሚሊሻ /
✔️ 65 ክላሽኮኘና የቃታ ጠመንጃዎች
✔️ 45 የወገብ ትጥቆች
✔️ 95 የእጅ ቦንቦች
✔️ ለጊዜው ቁጥሩ ያልታወቀ የነብስ ወከፍና የቡድን መሳሪያ ተተኳሾች ገቢ ተደርገዋል።
በመጨረሻም ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር በሚያቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች ሁሉ ያልተቆጣጠራቸውን ከተሞች በእጁ አስገብቶ ለማስተዳደር ወታደራዊ ዘመቻዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ወታደራዊ ፍንጮች ያሳያሉ።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
አብነት ሞላ
የካቲት 24/2018 ዓ.ም
🙏42
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር
[የካቲት 24/2018ዓ.ም]

በአቢይ አሕመድ አገዛዝ ሥር የነበሩ ታጣቂዎች የ፩ኛ ኮር የምሕረት አዋጅ ማቅረቡን የተጠቀሙ 09 አድማ ብተናዎችና 01 ኢንሥፔክተር ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦርን በዛሬው ዕለት በየካቲት 24/2018ዓ.ም ተቀላቅለዋል።

የአገዛዙ ታጣቂዎች ይህንንን የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር የምሕረት አዋጅ መጠቀም አለባቸው።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን


አፋብን ሰ//አ/ቀ በላይ ዕዝ
፩ኛ ኮር
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር ሕ/ግ ኃላፊ

ፋኖ አረጋ አንሙት
1👍1🙏1
የአብይ አህመድን ሰራዊት በየ አውደ ግንባሩ እንደ አገዳ እየሰበርነው ነው ።

ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ በሰሜን ጎጃም እና በአዊ ዞኖች ብቻ ባደረግነው የተቀናጀ ማጥቃት :-

1/ በጃዊ እና ዳንግላ ወረዳ

1.1 / 1ዲሽቃ የዲሽቃ አፈሙዝ ከበርካታ ተተኳሽ ጋር
1.2/ 3 ብሬን
1.3/ 2 ሲናይፐር
1.4/ 90 ክላሽ
1.5/ 22 ቦምብ
1.6/ 12 መከላከያ የተማረከ
1.7/ 115የክላሽ ካዝና
1.8/ ወታደራዊ ሻንጣ እና ቁሳቁሶች ተማርከዋል ።

2/ በኩምብር

2.1/ 200 ክላሽ
2.2/ 10 ብሬን
2.3/ 4 ስናይፐር
2.4/ 2 ዱሽቃ
2.5/ 4 መገናኛ ሬዲዮ
2.6/ 50 ሺህ ጥይት
2.7/ 150 የእጅ ቦምብ
2.8/ አዋጊ መኮኖች እና ተዋጊዎች ተማርከዋል ።

3/ በትናንትናው የፋግታ አውደ ግንባር
3.1/ 36 ጥቁር ክላሽ
3.2/ 20 ሺህ ጥይት
3.3/ ብዛት ያለው ቦምብ እና ወታደራዊ ቁሳቁስ ተማርኳል።


በድምሩ

1/ 326 ክላሽንኮቭ
2/ 13 ብሬን
3/ 6 ስናይፐር
4/ 2 ዱሽቃ እና 1 የዱሽቃ አፈሙዝ
5/ ሌሎች በርካታ ቁሳቁሶች ተማርከዋል ።


ድል ለጀግናው አማራ !
ድል ለጀግናው ፋኖ !!
5🙏2