ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ለተከታታይ ሶስት ወራት ወታደራዊ ፖለቲካዊ ስልጠና ያሰለጠናቸውን ምልምል የፋኖ ወታደሮች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

​የአብይ አህመድ ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመው ያለውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እና የህዝቡን ነፃነት ለማስከበር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር እንደ ንስር ተወርዋሪ የፋኖ አባላትን አስመርቁን ቀጥሏል።

​ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ከአዲስ አበባ አራት ኪሎ ቅርብ ርቀት ላይ የአብይን አየር ወለድ ኮማንድ በገባበት እየገባ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የህዝቡን ሰላም ለማስከበር ከሊቅ እስከ ደቂቅ በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ይገኛል።

ሆኖም በዛሬ ዕለት ​ከ400 በላይ የሚሆኑ የኮሩ ፋኖ አባላት በስነ ልቦናና በአካል ብቃት የበቁ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን እንደ ንስር ተወርዋሪ ተዋጊዎቹ የሕዝባቸውን ደህንነት ለመጠበቅ በብቃት የተዋጣላቸው ሰልጣኞችን አስመርቋል ሆኖም ሰልጣኞች በቀጣይ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ ስልጠና አንድ ይለህልውና አደጋ ላይ ያልን እዝብ ነጻ ለማውጣት ብቻ ነው ። ስርዓቱ የሞት ድግስ ደግሶብን ከምድር ገፅ ለማጥፋት እየሰራ ባለበት ስዓት በዱር በገደሉ የህይወት ድልድይ እየገነባን የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች በመሆን ሰልጣኞቹ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በሚሰጠን ማንኛውንም ግዳጅ ለመቀበልና በድል ለመወጣት የሀገራችንን ሉዓላዊነት እና የህዝባቸውን ነፃነት በአጥንታቸው ለመጠበቅ ቃል ገብተዋል።

በዚህ ቅዱስ በሆነው የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል በስም ዘርዝረን የማንጨረሳቸው ጀግኖች የትግል ጓዶች ከጠላት ጋር ተናንቀው ብዙ ዋጋ የከፈሉበት የህልውና ትግል ነው። በመሆኑም ድርጅታችንን እና መሪዎቻችንን ከትግል ጠላፊዎች እንድትጠብቁ አደራ አለባችሁ ለእናተ አደራ የምንሰጣቹህ መሪዎቻችን በብዙ ስቃይ እና መከራ ውጣ ውረድን በማለፍ ፣ ጀግኖች ውድ ህይወታቸውን የገበሩበት ትግል ተቀብላቹህ የድል ባለቤት እንድታደርጉት አደራ እንላለን ሲል የ አሳምነው ዕዝ ምክትል ድርጅት ጉዳይ አርበኛ እያሱ መልዕክቱን አስተላልፏል።

በመጨረሻም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አመራሮች በተገኙበት በመላው አማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀውን የአብይ አህመድ የአረመኔዊ ድርጊት በረካታ ግፎች እና ወንጀሎችን እየሰራ የሚገኜው የአብይ አህመድ ጡት ቆራጭ አረመኔዊ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ስለሚጠበቅብን ሁላችንም በዚህ የምረቃ ፕሮግሬም የምትገኝ በሙሉ ራሳችሁን ዝግጁ እንድታደርጉ እያልኩ ለተመራቂ ፋኖዎች መልካም የምረቃ ጊዜ እንመኛለሁ።

እንደራጃለን፣ እንሰለጥናለን፣ እንታጠቃለን፣ የአማራን ህዝብ ከአረመኔው ጡት ቆራጭ አራጅ ሰራዊት ነፃ እናወጣዋለን።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !!

የካቲት 22/06/2018 ዓ.ም
🙏4
ሰበር ዜና!

መብረቅ ክፍለ ጦር ስትራቴጂካዊቷ ወግዲ ከተማ ዘልቆ በመግባት የግፍ እስረኞችን በማስፈታት ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

​ወግዲ | የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም

​ዛሬ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ዞን የምትገኘው ስትራቴጂካዊቷ ወግዲ ከተማ በፋኖ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ውላለች። በንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ስር የሚንቀሳቀሰው መብረቅ ክፍለ ጦር በከተማዋ በነበረው የመንግስት የፀጥታ ኃይል ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር ከተማዋን አዳሩን ተቆጣጥሯል።

​እንደ ግንባር ምንጮች መረጃ፣ የፋኖ ኃይሎች ጥቃቱን ያከናወኑት በበርካታ አቅጣጫዎች ከበባ በማድረግ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ 01 ቀበሌ (ከተማ)፣ 02 ሰርቶ ማሳያ ቀበሌ፣ በደርቢቱ እና 05 ቀበሌ እንዲሁም 03 ቀበሌ ዙሪያውን በመክበብ ኦፕሬሽኑ ተከናውኗል::

ከዚህም ተያይዞ የፋኖ ኃይሎች የወግዲ ማረሚያ ቤትን በመስበር በውስጡ የነበሩ እስረኞች በሙሉ እንዲለቀቁ አድርገዋል። በመንግስት ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በርካታ ቁስለኞች በአምቡላንስና በፓትሮል ሲጓጓዙ መታየታቸው ተጠቁሟል።

​ይህ ወታደራዊ እርምጃ የተከናወነው በመላው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ የሚከበረውን የ130ኛውን የአድዋ ድል በዓልን ተገን በማድረግ መሆኑን የክፍለ ጦሩ አባላት ገልጸዋል። "የዛሬው ድል የአድዋ አርበኞችን ታሪክ የደገመ ነው" ሲሉ የጦር ግንባር ምንጮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
​ወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት የወግዲ ከተማ መያዝ በደቡብ ወሎ ያለውን የኃይል ሚዛን በእጅጉ ሊቀይረው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
🙏1
አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ውሥን ቀጠና ላይ የማረካቸውን 300+ ምርኮኞች አሥተምሮ በይቅርታ ለቅቋቸዋል።

ታላቁ የጥቁር ሕዝብ የአሸናፊነትን ቀን የካቲት 23/1888ዓ.ምን የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር የማረካቸውን ከ300+ የሚበልጡ የአገዛዙ ምርኮኛ ጥምር አካላትን የተሐድሶ ትምሕርት ሲሰጥ ከቆዬ በኋላ የአባቱ የምኒልክን የይቅር ባይነት መንፈሥ ተላብሶ ይቅርታቸውን ችሯቸዋል።

ከ04ቱም የ፩ኛ ኮር ክፍለ ጦሮች የተማረኩ የአገዛዙ ታጣቂዎች ተገቢውን ትምሕርት እንዳገኙ ከታራሚዎች አንደበት ማድመጥ ተችሏል። የተደረገላቸው ሰዋዊ አክብሮት አገዛዙ ከነገራቸው በፍጹም የተቃረነ መሆኑንና ያልጠበቁት አቀባበል እንዳገኙ ተናግረዋል።

እንኳን ለአድዋ ድል በዓል አደረሳችኹ

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA👊

አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግንኙነት ዘርፍ
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው

ቋሚ ምሥል፦ በ፩ኛ ኮር ምሕረት የተደረገላቸው ከ300+ በላይ የሆኑ የአገዛዙ ጥምር ታጣቂ የነበሩ፦
የመከላከያ ምርኮዎች
አድማ ብተና ምርኮዎች
ሚሊሺያ ምርኮዎች
መደበኛ ፖሊሥ ምርኮዎች
1🙏1
የአፋብን ምኒልክ ዕዝ የህዝብ አስተዳደር መምሪያ ሃላፊው አርበኛ እስራኤል እሸቴ ባለቤት በፋሽስቱ አገዛዝ ኮምቦልቻ በግፍ ታስራ ትገኛለች:: የአርበኛው ባለቤት የአምስት ወር መንታ ህፃን እመጫት ስትሆን ከልጆቿ ተለይታ ስለታሰረች መንታ ህፃናቶቹ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛሉ::
🔥1💔1
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ የጠላትን 59ኛ ክፍለ ጦር በመደምሰስ 130ኛውን የአድዋ ድል የሚያስታውስ ገድል ፈፅሟል‼️

የካቲት 23/2018 ዓ/ም

በጎጃም ጃዊ ቀጠና ኩንብር ከተማ እና አካባቢው የሰፈሩት የጠላት አሃዶች ላይ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ፣ የ206ኛ እና 201ኛ ኮሮች በጥምረት ባደረጉት መብረቃዊ ጥቃት 2ዲሽቃ፣ 10 ብሬን፣ 4 ስናይፐርን እና የክፍለ ጦር መገናኛ ሬዲዮን ጨምሮ በርካታ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርከዋል።

ዛሬ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም አነጋግ ላይ በተደረገው ዉጊያ የጠላት ወታደራዊ መኮንኖች ከእነ እግረኛ ሰራዊታቸው ተደምስሰዋል።

ከሶስቱ ክንደ ብርቱ ኮሮች የተውጣጣ ኃይል አቅደው በተሳተፉበት ዘመቻ ጠላት የቁም ምሽግ ቆፍሮ ከተቀበረበት ዘልቆ በመግባትና አፈና በመፈጸም የጠላትን ሎጀስቲክስና የሠው ሀይል መማረክና መደምሰስ ተችሏል። የእጅ ቦንቦችን በብዛት በመጠቀም በተፈፀመው በዚህ አስደናቂ ወታደራዊ ጀብዱ ከተማረኩት ቁሳቁሶች መካከል:-

1 ከ200 (ሁለት መቶ) በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያወች፣
2) 10 (አስር ) ብሬን/መትረዬስ፣
3) 4 (አራት) ስናፐር፣
4) 2 (ሁለት) ዲሽቃ እስከሙሉ ክሻፋው፣
5) 50,000 (ሀምሳ ሺህ) በመጋዘን የተቀመጠ የክላሽ እና የብሬን ጥይት፣
6) 4 (አራት) መገናኛ ሪዲዮኖች
7) በርካታ የእጅ ቦንቦች እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ይገኙበታል።

እንዲሁም 32 (ሰላሳ ሁለት ) የመከላከያ አባላት በእጅ ሲማረኩ አንድ ማዕረጉ እና ማንነቱ እየተጣራ ያለ ከፍተኛ አዛዥን ጨምሮ ከ150 በላይ የጠላት ሰራዊት ተደምስሷል።

የፋሺዝም መንፈስ ወራሽ የሆነው የአብይ አህመድ አገዛዝ ከባዕዳን ኃይሎች ጋር በመተባበር በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን የጥፋት ዘመቻ ለማስቆም ቆርጠን መነሳታችንን በእለተ አድዋ ቃላችን በድጋሚ በማደስ እናረጋግጣለን‼️

አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ‼️
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት
🙏1
ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር የአመራርና የክፍለ ጦር መልሶ ማደራጀት አካሄደ!

የካቲት:-23/2018 ዓ/ም

እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ እያለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ወቅቱን የዋጀ የፋኖ አመራርና የክፍለ ጦሮች አደረጃጀት ለተከታታይ ሦስት ቀናት በተደረገ ብስለት የተሞላበትና በስክነት በመወያየት የክፍለ ጦሮች አደረጃጀትና ስያሜ እንዲሁም የኮሩን ስያሜና አመራር መልሶ ማደራጀት እንደሚከተለው ሰርቷል ፤ በድጋሜ እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ።

1ኛ. የኮሩ ስያሜ:- ቀድሞ ከነበረው ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ወደ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር በሚል ስያሜው ተቀይሯል::

2ኛ. የክፍለ ጦሮች መልሶ ማደራጀትን በተመለከተ ኮሩ ከነበረው ስምንት ክፍለ ጦሮችና ሁለት ብርጌዶች ለአሰራርና ቁጥጥር ያመች ዘንድ ወደ አምስት ክፍለ ጦር የተደራጄ ሲሆን :-
2.1. ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር፣ እሸት ክፍለ ጦርና ዋግሹም ብርጌድ በአንድ በመዋሀድ 19ኛ ክፍለ ጦር ፣
2.2. ተከዜና ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦሮች በመዋሀድ 21ኛ ክፍለ ጦር፣
2.3. ኃይሉ ከበዴና ጥራሪ ክፍለ ጦሮች በመዋሀድ 14 ክፍለ ጦር፣
2.4. ውባንተ አባተና ራስ አንችም ክፍለ ጦሮች በመዋሀድ 81ኛ ክፍለ ጦር እንዲሁም፣
2.5. ከሁሉም ክፍለ ጦሮች በማውጣጣት የተቋቋመው ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ክፍለ ጦር 16ኛ ክፍለ ጦር በሚል የክፍለ ጦሮች መልሶ ማደራጀት ተሰርቷል።

3ኛ. የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር የአመራር መልሶ ማደራጀት የተሰራ ሲሆን:-

1. ኮር ሰብሳቢ:- አርበኛ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙሉዬ
2. ኮር ም/ሰብሳቢ:- አርበኛ ታዘበው ሻምበል
3. ወታደራዊ አዛዥ:- አርበኛ ኮማንዶ ብርሐን አሰፋ
4. ፖለቲካ ዘርፍ መምሪያ:- አርበኛ በሪሁን ደምሌ
5. ኮር አስተዳደር:- አርበኛ ሞላ አዳነ
6. መረጃና ደህንነት:-𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥
7. ምክትል ወታደራዊ አዛዥ:- አርበኛ ጣሰው አለልኝ
8. ዘመቻ መምሪያ:- አርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ
9. ምክትል ዘመቻ (ስምሪት):- አርበኛ አያናው እንየው
10. መገናኛና ኦፕሬተር:- አርበኛ አማሪው አያናው
11. ሎጅስቲክ መምሪያ:- አርበኛ መልኩ አለምዬ
12. ኦርዲናንስ መምሪያ:- አርበኛ ብርቁ አራጋው
13. ጥገና ክፍል:- መቶ አለቃ ተስፋዬ አበበ
14. ስልጠና መምሪያ:- ሃምሳ አለቃ መልካሙ ገበየሁ
15. ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ:- አርበኛ ፀጋዬ አካልነው
16. ህዝብ ግንኙነት መምሪያ:- አርበኛ ቢሆነኝ ቢያበይን
17. ህዝብ አስተዳደር መምሪያ:- ሃምሳ አለቃ መንግስቱ ካሳ
18. አደረጃጀት መምሪያ:- አርበኛ ጋሻው አበበ
19. ህግ ክፍል:- አርበኛ ዋኘው አደራው
20. ምክትል ህግ ክፍል:- ሳጅን አድሱ አራጋው
21. ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ:- አርበኛ ግርማ ቅባቴ
22. ሴቶች ጉዳይ መምሪያ:- አርበኛ አባይ ውበቴ
23. ፋይናንስ መምሪያ:- አርበኛ ሲሳይ ተስፋው
24. የሰው ኃይል መምሪያ:- አርበኛ ጥጋቡ ሲሳይ
25. ሐብት አፈላላጊ:- አርበኛ አለበል ነጋሽ
26. ጤና መምሪያ:- አርበኛ ምስጋናው አዱኛው
27. ኦዲተር:- አርበኛ ባለሟል ሽመልስ
28. ምክትል መረጃና ደህንነት:-𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥
29. ፀረ-መረጃ:- 𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥
30. ወታደራዊ አማካሪ :- አርበኛ ተመቼ ቢራራ
31. ፖለቲካዊ አማካሪ:- አርበኛ ፍቅረማርያም ደሴ ሆነው በመመረጥ ኮሩ የአመራርና የኮር መልሶ ማደራጀትና የስያሜ ለውጥ ከዛሬ የካቲት 23/2018 ዓ/ም ጀምሮ ያደረገ መሆኑን እናሳውቃለን።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
1🙏1
አፋብን |ቴዎድሮስ ዕዝ
ዘመቻ ሽመልስ በአድዋ ድል መታሰቢያ 206ኛ ኮር በአምስት ግምባሮች በከፈተው የተቀናጀ ማጥቃት ደማቅ ድል አስመዝግቧል።
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
=====================================
በወርሀ የካቲት የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምልክት በሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን በልዩ ግዳጅ ታሪክ ሰርቶ በጃዊ በተሰዋው እንቁ ታጋይ በሽመልስ ዘመቻ ያወጀው 206ኛ ኮር፤ በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 10:00 ጀምሮ በከፈተው የተጠናከረ ውጊያ በውሀ ጋኑ የመሸገውን ጠላት 14ኛ ክ/ጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ሻለቃ በሞርተር በመታገዝ ባደረገችው ማጥቃት ጠላትን በምሽጉ አንገቱን ቀልተዋለች።

ባልተጠበቀ ሰዓት የታቀደ ውጊያ የከፈተው 206ኛ ኮር በደብረ ማርቆስ ከተማ እስከ ንጋቱ 1:00 በመፋለም አስደናቂ ጀብድ የፈፀመ ሲሆን ፤በተመሳሳይ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 4:00 ሰዓት በሊባኖስ ከተማ የመሸገውን ጠላት የተናነቀው 14ኛ ክ/ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ በጠላት አስክሬን ላይ እየተረማመደ የማይደፈሩ የሚባሉ የቁም ምሽጎችን ሲንዱ አርፍደዋል ። በዚህ አውደ ውጊያ የጠላት የጦር አመራሮች ጨምሮ ሚኒሻና አድማ ብተናዎች መገደላቸው ተረጋግጧል።

ጠላት እንዳይተሳሰር ከደብረ ማርቆስ ደጀን ቁይ ድረስ መጠነ ሰፊ ጥቃት የከፈተው 206ኛ ኮር የጠላትን ዋና ወታደራዊ ካምፕ አድርጎ የተቀመጠበትን የየትኖራ ወታደራዊ ሰፈር በሞርተር በመደብደብ የኃይል ሚዛኑን ያዛባው 34ኛ ክ/ጦር በደጀን ወረዳ በጉብያ ከተማ በመሸገው ጠላት ላይ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ባደረገው የሙሉ ድምሰሳ ውጊያ ከ60 በላይ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ ጠላት ዙ-23 ሞርተር መድፍና BM ቢጠቀምም የኃይል ብልጫ መውሰድ አልቻለም።

በቅጥል ስሙ "ኮከብ" ተብሎ የሚጠራው የአድማ ብተና ዘመቻ መሪ በተገደለበት የጉብያ ግምባር 34ኛ ክ/ጦር ከጠላት ጋር በመተናነቅ ጠንካራ የሚባሉ ምሽጎችን በቦምብ በማፈራረስ ጠላት የሚመካባቸው የሚኒሻ አመራሮችም ተገድለዋል።

በሌላ ግምባር 24ኛ ክ/ጦር በቁይ ከተማና አቅራቢያ በአደረገችው ማጥቃት የደባይ ጮቄ ሻለቃ የተሰጣትን ግዳጅ በብቃት በመወጣት በርካታ የጠላት ኃይል መደምሰሷም የታወቀ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች እስከ 6:30 በተፈፀመው ማጥቃት ከ125 በላይ የጠላት ኃይል ላይ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል።

በጀግናው ሽመልስ ዘመቻ ሰይሞ የጠላትን ኃይል በማዛነፍና የግንኙነት መስመሩን በመበጣጠስ በጉብያ የመሸገውን ጠላት መሉ ድምሰሳ የፈፀመው 206ኛ ኮር በኮሩ ወታደራዊ አመራሮች እና የክ/ጦር ወታደራዊ አመራሮች ሻለቆችን በማቀናጀት ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ያደረጉት ውጊያ የጠላትን ማዘዣ ጣቢያን ጨምሮ በአምስት ግምባሮች ድል መቀናጀታቸውን የ206ኛ ኮር ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
🙏1
አሳምነው ክፍለ ጦር ወልድያ ሽንቁሩ ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ታላቅ ጀብድ ሰርተው ድል ተጎናፀፉ::

አሳምነው ክፍለ ጦር ከ2ኛ እና 4ኛ ሻለቃ የተውጣጡ አባላቶች ወልድያ ሽንቁሩ ላይ ዛሬ የካቲት 23/2018 ዓ.ም የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ከአንድ ጓድ (ቲም) በላይ የጠላት ሃይል በመደምሰስና ቁጥሩ ያልታወቀ በማቁሰል ታላቅ ጀብድ ሰርተው ድል ተጎናፅፈዋል::

በአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለውን የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ጥምር ሰራዊት በስውር ድርጊያ በደፈጣ እና በመደበኛ ውጊያ እረፍት የመንሳት የማሰላቸት የመደምሰስና የመማረኩ ተጋድሎ እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክፍለ ጦሩ አመራሮች ገልፀዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
2🙏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስበር ዜና
አገዛዙ በአለፋ ከተማ ንፁሃንን በድሮን ጨፈጨፈ
💔1