ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በወግድ ወረዳ የመብረቅ ክፍለ ጦር በአብይ አህመድ ሰራዊት ላይ መጠነ ሰፊ ማጥቃት በመሰንዘር ድል አስመዘገበ::

​በደቡብ ወሎ ዞን ወግድ ወረዳ ውስጥ በሚንቀሳቀሰው የንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ስር የሚገኘው መብረቅ ክፍለ ጦር ከትላንት የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽት 5፡00 ጀምሮ በወረዳው በተለያዩ አካባቢዎች ሰፍሮ በሚገኘው የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ላይ የተቀናጀና ብርቱ ማጥቃት መክፈቱ ተገለጸ።

​ከክፍለ ጦሩ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የፋኖ አባላቱ በታቀደ የቆረጣ ስልት ጠላትን ግራ በማጋባት ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ። በዚሁ ኦፕሬሽን ላይ በርካታ ሻለቃዎች የተሳተፉ ሲሆን
​አደነ ሀብትነው እና ነብሮ ሻለቃ በሸመኔ፣ ያጌ፣ ቦርቦር እና የጉርባ አቅጣጫዎች የጠላትን እንቅስቃሴ በመቁረጥ ድንገተኛ ጥቃት ሰንዝረዋል።

​አሳምነው ሻለቃ ምድር ገበያ በተባለ ስፍራ በወሰደው እርምጃ በርካታ የፀጥታ ኃይሎችን (ሚሊሻዎችን) ደምስሷል።

​የወረዳው ወቅታዊ ሁኔታ
​ውጊያው አሁንም ግለቱን ጠብቆ በቀጠለባቸው አበዬ ጉርባ፣ ያጌ፣ ሸመኔ እና ምድር ገበያ አካባቢዎች የክፍለ ጦሩ አባላት አመቺ ቦታዎችን በመያዝ የጠላትን እንቅስቃሴ መግታት ችለዋል። በአሁኑ ወቅት የወግድ ወረዳ በፋኖ ኃይሎች ተከባ የምትገኝ ሲሆን በአብይ አራዊት ሰራዊት በኩል ከፍተኛ የመንፈስ መላሸቅና የመሸነፍ ስሜት እየታየ ይገኛል።
​"አባይ አስገብቻለሁ እያለ ሲፎክር የነበረው ኃይል፣አሁን በገባበት አጣብቂኝ ምክንያት መውጫ አጥቶ በከፍተኛ ጭንቀት ላይ ይገኛል" ሲል ክፍለ ጦሩ ገልጿል።

​ምንም እንኳን የሟቾችና የቁስለኞች ቁጥር በዝርዝር ባይገለጽም የብርሃኑ ጁላ ጦር ከፍተኛ የሰው ኃይል ማጣቱንና ቀሪው ኃይልም እጅ ለመስጠት የሚገደድበት ሰዓት ቀርቧል።​ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ውጊያው እጅግ ጠንካራና ድምፁም በከባድ እንደሚሰማ ገልጸው የፋኖ ኃይሎች በየአቅጣጫው የበላይነት ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ አረጋግጠዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
3🙏1
አሳዛኝ ዜና!!!

የአብይ አህመድ አገዛዝ ንፁሀንን ያነፃፀረ የድሮን ጥቃት በሻሁራ ከተማ ላይ ፈፀመ!!!

ጨፍጫፊውና አውዳሚው ደም መጣጭ ፀረ አማራ የአገዛዙ ሰርአት በእግረኛ ሜካናይዝድ ጦር የአማራን ህዝብ ለእልቂትና ለስቃይ መዳረጉ አልበቃው ብሎ፤ አሁን ላይ በየ ሀገራቱ ተንከራቶና ለምኖ በሚያስገባቸው ድሮኖች ንፁሀንን ያነፃፀረ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል።

በማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ የድሮን ጥቃትና ቅኝት በተለይ በዚህ አንድ ሳምንት በማያቋርጥ መልኩ በቀንም በማታም የተደጋገመ ሲሆን ህዝባችን ለሽብርና ለሞት እየዳረገ ይገኛል። በዛሬው እለት የካቲት 23/2018 ከጧቱ 1:00 ስአት ገደማ ሻሁራ ከተማ ቀበሌ01 ዉሀ የሚቀዱ ንፁሀን ላይ ያነፃፀረ ጥቃት ተፈፅሟል። በዚህ ጥቃት ወ/ሮ አንጓች የሀለም፣ ወጣት ናንየ ደጉ እና አቶ አለሙ አቢታ ለእልፈተ ሞት ሲዳረጉ ዋወይ የሚባል ንፁሀንም ከባድ ቁስለኛ ሆኗል።እንዲሁም አንድ የንፁሀን ቤት ሊወድም ችሏል።

ተስፋ ቆራጩ የአገዛዙ ስርአት የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፍቶት የጀግኖችን የመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ክንድ መቋቋም ሲያቅተው እና ከወረዳው ሰራዊቱን በመደምሰስና በመማረክ አቅመቢስ የሆነው፤ አሁን ላይ እንደ አማራጭ ንፁሀን ህዝባችን ላይ ሂሳብ ለማወራረድ የሚሄድበትን እርቀት ምን ያህል በወታደራዊም ሆነ በፓለቲካዊ ዘርፍ የወረደና የተቀዣቀዠ መሆኑ የአራት ኪሎ እድሜው ያበቃ እንደሆነ ያሳያል።

ፈጣሪ የተሰው ንፁሀንን ነብስ ይማር!!! ወዳጅ ዘመዶቻቸውን መፅናናት ይስጥልን።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ
የካቲት 23/2018
💔31
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ለተከታታይ ሶስት ወራት ወታደራዊ ፖለቲካዊ ስልጠና ያሰለጠናቸውን ምልምል የፋኖ ወታደሮች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

​የአብይ አህመድ ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመው ያለውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እና የህዝቡን ነፃነት ለማስከበር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር እንደ ንስር ተወርዋሪ የፋኖ አባላትን አስመርቁን ቀጥሏል።

​ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ከአዲስ አበባ አራት ኪሎ ቅርብ ርቀት ላይ የአብይን አየር ወለድ ኮማንድ በገባበት እየገባ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የህዝቡን ሰላም ለማስከበር ከሊቅ እስከ ደቂቅ በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ይገኛል።

ሆኖም በዛሬ ዕለት ​ከ400 በላይ የሚሆኑ የኮሩ ፋኖ አባላት በስነ ልቦናና በአካል ብቃት የበቁ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን እንደ ንስር ተወርዋሪ ተዋጊዎቹ የሕዝባቸውን ደህንነት ለመጠበቅ በብቃት የተዋጣላቸው ሰልጣኞችን አስመርቋል ሆኖም ሰልጣኞች በቀጣይ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ ስልጠና አንድ ይለህልውና አደጋ ላይ ያልን እዝብ ነጻ ለማውጣት ብቻ ነው ። ስርዓቱ የሞት ድግስ ደግሶብን ከምድር ገፅ ለማጥፋት እየሰራ ባለበት ስዓት በዱር በገደሉ የህይወት ድልድይ እየገነባን የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች በመሆን ሰልጣኞቹ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በሚሰጠን ማንኛውንም ግዳጅ ለመቀበልና በድል ለመወጣት የሀገራችንን ሉዓላዊነት እና የህዝባቸውን ነፃነት በአጥንታቸው ለመጠበቅ ቃል ገብተዋል።

በዚህ ቅዱስ በሆነው የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል በስም ዘርዝረን የማንጨረሳቸው ጀግኖች የትግል ጓዶች ከጠላት ጋር ተናንቀው ብዙ ዋጋ የከፈሉበት የህልውና ትግል ነው። በመሆኑም ድርጅታችንን እና መሪዎቻችንን ከትግል ጠላፊዎች እንድትጠብቁ አደራ አለባችሁ ለእናተ አደራ የምንሰጣቹህ መሪዎቻችን በብዙ ስቃይ እና መከራ ውጣ ውረድን በማለፍ ፣ ጀግኖች ውድ ህይወታቸውን የገበሩበት ትግል ተቀብላቹህ የድል ባለቤት እንድታደርጉት አደራ እንላለን ሲል የ አሳምነው ዕዝ ምክትል ድርጅት ጉዳይ አርበኛ እያሱ መልዕክቱን አስተላልፏል።

በመጨረሻም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አመራሮች በተገኙበት በመላው አማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀውን የአብይ አህመድ የአረመኔዊ ድርጊት በረካታ ግፎች እና ወንጀሎችን እየሰራ የሚገኜው የአብይ አህመድ ጡት ቆራጭ አረመኔዊ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ስለሚጠበቅብን ሁላችንም በዚህ የምረቃ ፕሮግሬም የምትገኝ በሙሉ ራሳችሁን ዝግጁ እንድታደርጉ እያልኩ ለተመራቂ ፋኖዎች መልካም የምረቃ ጊዜ እንመኛለሁ።

እንደራጃለን፣ እንሰለጥናለን፣ እንታጠቃለን፣ የአማራን ህዝብ ከአረመኔው ጡት ቆራጭ አራጅ ሰራዊት ነፃ እናወጣዋለን።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !!

የካቲት 22/06/2018 ዓ.ም
🙏4
ሰበር ዜና!

መብረቅ ክፍለ ጦር ስትራቴጂካዊቷ ወግዲ ከተማ ዘልቆ በመግባት የግፍ እስረኞችን በማስፈታት ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

​ወግዲ | የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም

​ዛሬ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ዞን የምትገኘው ስትራቴጂካዊቷ ወግዲ ከተማ በፋኖ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ውላለች። በንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ስር የሚንቀሳቀሰው መብረቅ ክፍለ ጦር በከተማዋ በነበረው የመንግስት የፀጥታ ኃይል ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር ከተማዋን አዳሩን ተቆጣጥሯል።

​እንደ ግንባር ምንጮች መረጃ፣ የፋኖ ኃይሎች ጥቃቱን ያከናወኑት በበርካታ አቅጣጫዎች ከበባ በማድረግ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ 01 ቀበሌ (ከተማ)፣ 02 ሰርቶ ማሳያ ቀበሌ፣ በደርቢቱ እና 05 ቀበሌ እንዲሁም 03 ቀበሌ ዙሪያውን በመክበብ ኦፕሬሽኑ ተከናውኗል::

ከዚህም ተያይዞ የፋኖ ኃይሎች የወግዲ ማረሚያ ቤትን በመስበር በውስጡ የነበሩ እስረኞች በሙሉ እንዲለቀቁ አድርገዋል። በመንግስት ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በርካታ ቁስለኞች በአምቡላንስና በፓትሮል ሲጓጓዙ መታየታቸው ተጠቁሟል።

​ይህ ወታደራዊ እርምጃ የተከናወነው በመላው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ የሚከበረውን የ130ኛውን የአድዋ ድል በዓልን ተገን በማድረግ መሆኑን የክፍለ ጦሩ አባላት ገልጸዋል። "የዛሬው ድል የአድዋ አርበኞችን ታሪክ የደገመ ነው" ሲሉ የጦር ግንባር ምንጮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
​ወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት የወግዲ ከተማ መያዝ በደቡብ ወሎ ያለውን የኃይል ሚዛን በእጅጉ ሊቀይረው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
🙏1
አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ውሥን ቀጠና ላይ የማረካቸውን 300+ ምርኮኞች አሥተምሮ በይቅርታ ለቅቋቸዋል።

ታላቁ የጥቁር ሕዝብ የአሸናፊነትን ቀን የካቲት 23/1888ዓ.ምን የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር የማረካቸውን ከ300+ የሚበልጡ የአገዛዙ ምርኮኛ ጥምር አካላትን የተሐድሶ ትምሕርት ሲሰጥ ከቆዬ በኋላ የአባቱ የምኒልክን የይቅር ባይነት መንፈሥ ተላብሶ ይቅርታቸውን ችሯቸዋል።

ከ04ቱም የ፩ኛ ኮር ክፍለ ጦሮች የተማረኩ የአገዛዙ ታጣቂዎች ተገቢውን ትምሕርት እንዳገኙ ከታራሚዎች አንደበት ማድመጥ ተችሏል። የተደረገላቸው ሰዋዊ አክብሮት አገዛዙ ከነገራቸው በፍጹም የተቃረነ መሆኑንና ያልጠበቁት አቀባበል እንዳገኙ ተናግረዋል።

እንኳን ለአድዋ ድል በዓል አደረሳችኹ

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA👊

አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግንኙነት ዘርፍ
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው

ቋሚ ምሥል፦ በ፩ኛ ኮር ምሕረት የተደረገላቸው ከ300+ በላይ የሆኑ የአገዛዙ ጥምር ታጣቂ የነበሩ፦
የመከላከያ ምርኮዎች
አድማ ብተና ምርኮዎች
ሚሊሺያ ምርኮዎች
መደበኛ ፖሊሥ ምርኮዎች
1🙏1
የአፋብን ምኒልክ ዕዝ የህዝብ አስተዳደር መምሪያ ሃላፊው አርበኛ እስራኤል እሸቴ ባለቤት በፋሽስቱ አገዛዝ ኮምቦልቻ በግፍ ታስራ ትገኛለች:: የአርበኛው ባለቤት የአምስት ወር መንታ ህፃን እመጫት ስትሆን ከልጆቿ ተለይታ ስለታሰረች መንታ ህፃናቶቹ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛሉ::
🔥1💔1
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ የጠላትን 59ኛ ክፍለ ጦር በመደምሰስ 130ኛውን የአድዋ ድል የሚያስታውስ ገድል ፈፅሟል‼️

የካቲት 23/2018 ዓ/ም

በጎጃም ጃዊ ቀጠና ኩንብር ከተማ እና አካባቢው የሰፈሩት የጠላት አሃዶች ላይ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ፣ የ206ኛ እና 201ኛ ኮሮች በጥምረት ባደረጉት መብረቃዊ ጥቃት 2ዲሽቃ፣ 10 ብሬን፣ 4 ስናይፐርን እና የክፍለ ጦር መገናኛ ሬዲዮን ጨምሮ በርካታ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርከዋል።

ዛሬ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም አነጋግ ላይ በተደረገው ዉጊያ የጠላት ወታደራዊ መኮንኖች ከእነ እግረኛ ሰራዊታቸው ተደምስሰዋል።

ከሶስቱ ክንደ ብርቱ ኮሮች የተውጣጣ ኃይል አቅደው በተሳተፉበት ዘመቻ ጠላት የቁም ምሽግ ቆፍሮ ከተቀበረበት ዘልቆ በመግባትና አፈና በመፈጸም የጠላትን ሎጀስቲክስና የሠው ሀይል መማረክና መደምሰስ ተችሏል። የእጅ ቦንቦችን በብዛት በመጠቀም በተፈፀመው በዚህ አስደናቂ ወታደራዊ ጀብዱ ከተማረኩት ቁሳቁሶች መካከል:-

1 ከ200 (ሁለት መቶ) በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያወች፣
2) 10 (አስር ) ብሬን/መትረዬስ፣
3) 4 (አራት) ስናፐር፣
4) 2 (ሁለት) ዲሽቃ እስከሙሉ ክሻፋው፣
5) 50,000 (ሀምሳ ሺህ) በመጋዘን የተቀመጠ የክላሽ እና የብሬን ጥይት፣
6) 4 (አራት) መገናኛ ሪዲዮኖች
7) በርካታ የእጅ ቦንቦች እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ይገኙበታል።

እንዲሁም 32 (ሰላሳ ሁለት ) የመከላከያ አባላት በእጅ ሲማረኩ አንድ ማዕረጉ እና ማንነቱ እየተጣራ ያለ ከፍተኛ አዛዥን ጨምሮ ከ150 በላይ የጠላት ሰራዊት ተደምስሷል።

የፋሺዝም መንፈስ ወራሽ የሆነው የአብይ አህመድ አገዛዝ ከባዕዳን ኃይሎች ጋር በመተባበር በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን የጥፋት ዘመቻ ለማስቆም ቆርጠን መነሳታችንን በእለተ አድዋ ቃላችን በድጋሚ በማደስ እናረጋግጣለን‼️

አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ‼️
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት
🙏1