''ተጨማሪ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል'' ቀብራቸው ዛሬ ተፈጽሟል " የሽርካ ወረዳ ቤተክህነት
" ትክክል ነው። የተገደሉት ሰባት ሰዎች ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ አስከሬናቸው ተገኝቷል። እነዚህ ትናንት ወዲያ ከተገደሉት 21 ምዕመናን ውጭ የተገደሉ ናቸው " - የአርሲ ዞን ሀገረስብከት
ከትናንትና ወዲያ " 21 ምዕመናን ሲገደሉ " ፣ ስምንት የደረሱበት አልታወቀም " ፣ " ስምንት ሆስፒታል ገብተዋል " ፣ " ሁለት ታግተዋል " በተባለበት በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ትናንት ምሽት ተጨማሪ " ምዕመናን " መገደላቸው ታውቋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት፣ እንዲሁም በዞኑ የሽርካ ወረዳ ቤተክህነት፣ ከትናንት ወዲያ ግድያ በተፈጸመበት በሽርካ ወረዳ ጃዌ ዋጩ ቀበሌ፣ ትናንት ምሽትም ሌላ ጥቃት ተፈጽሞ " ሰባት ምዕመናን " በታጣቁት አካላት ተገድለዋል ሲሉ ተናግረዋል።
አንድ የሽርካ ወረዳ ቤተክህነት አካል ዛሬ ከሰዓት በሰጡን ቃል፣ " ትናንት ምሽትም ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። ቀብራቸው ዛሬ ተፈጽሟል " ብለዋል። በዚህም እስካሁን ተረጋገጠው መረጃ ብቻ በሁለት ቀናት በቀበሌው የተገደሉት ምዕመናን ብዛት 28 ደርሷል።
" ትናንት ማታም በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል። ሲቃጠሉም ነው ያደረሩት። አንድ ቤተክርስቲያን ተዘርፏል" ያሉን የቤተክህነቱ አካል፣ "ቤተክርስቲያን ዙሪያ ያለ ደጀሰላም እና አዳራሽ ተቃጥለዋል " ብለዋል።
" ስጋቱ አሁንም እንዳለ ነው " ያሉም ሲሆን፣ ይህ ጥቃት የተሰነዘረበት ቤተክርስቲያን ጃዊ አቦ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እንደሚባል ገልጸው፣ " የተወሰነ ኃይል ብቻ ከዞን መጥቷል። ሟቾቹ እንዲቀበሩ ያደረጉት እነርሱ ናቸው። ግን ይቆዩ፣ ይሄዱ ይሆን አይታወቅም " ነው ያሉት።
የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት በበኩሉ፣ " የሚያገኟትን ነገር እየተጠቀሙ " ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠግተው ሲኖሩ የነበሩ " አቃቢት " እና " ነዳያን " በተጠቀሰው ቦታ ትናንት ምሽት በተሰነዘረ ጥቃት " ተድለዋል " ሲል ገልጿል።
ይህን ያሉት አንድ የሀገረ ስብከቱ አመራር በሰጡን ቃል፣ " ትክክል ነው። የተገደሉት ሰባት ሰዎች ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ አስከሬናቸው ተገኝቷል። እነዚህ ትናንት ወዲያ ከተገደሉት 21 ምዕመናን ውጭ የተገደሉ ናቸው " ብለዋል።
ከሟቾቹ ባሻገር " ጀደሰላሙ ሙሉ ለሙሉ ተቃጥሏል። የሰበካ ጉባዔው ጽሕፈት ቤት የስንዴ እህል ነበረው እሱም ወድሟል። ብዙ ቤቶችም ተቃጥለዋል " ሲሉ አክለዋል።
የአትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ትናንት ወዲያ የተገደሉትን 21 ኦርቶዶክሳውያን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም በሽርካ ወረዳ ጃዊ ቀበሌ በታጣቂዎች ጥቃት የካቲት 19 ለ 20/2018 ዓ/ም 21 ኦርቶዶክሳውያን በግፍ መገደላቸውን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ " ለጽ/ቤታችን ከጻፉት ደብዳቤ ስንመለከት እጅግ በከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶናል " ብለዋል። ትናንት ምሽት ተገደሉ ስለተባሉ ሰባቱ ሰዎች እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

💔1
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የእስራኤል አየር ኃይል ዛሬ በኢራን ላይ እስካሁን ካደረጋቸው ወታደራዊ እርምጃዎች ሁሉ ግዙፍ የተባለውን የአየር ድብደባ ማካሄዱን አስታወቀ። በመከላከያ ኃይሉ መግለጫ መሠረት፣ በጥቃቱ 200 የሚጠጉ ተዋጊ ጄቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ በምዕራብና በመካከለኛው ኢራን የሚገኙ የባሊስቲክ ሚሳይል ማስወንጨፊያዎችንና የአየር መከላከያ ሥርዓቶችን ኢላማ አድርገዋል። በዘመቻው ወቅት በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥይቶችና ቦምቦች በ500 የሚጠጉ የኢራን ወታደራዊ ተቋማት ላይ በተመሳሳይ ሰዓት መጣላቸው ተገልጿል።
ይህ ጥቃት በከፍተኛ የደህንነት መረጃና ጥንቃቄ በተሞላበት ዕቅድ የተመራ መሆኑን የገለጸው የእስራኤል መከላከያ ኃይል፣ በኢራን የአየር መከላከያ ሥርዓቶች ላይ የተሰነዘረው እርምጃ የእስራኤል አየር ኃይል በኢራን ሰማይ ላይ የበላይነት እንዲኖረውና የአገዛዙን የማጥቃት አቅም እንዲዳከም አድርጓል ብሏል። በተለይም በታብሪዝ አካባቢ የሚገኝና ወደ እስራኤል በአስር የሚቆጠሩ ሚሳይሎችን ለመተኮስ ታቅዶበት የነበረ የባሊስቲክ ሚሳይል ጣቢያ መመታቱን ሠራዊቱ በዝርዝር አስታውቋል።

የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ አሃድ ዘመቻ መሪ በነበረው ሰማዕቱ አርበኛ ፍሬው አለና ስም በተሰየመው ዘመቻ ምኒልክ ዕዝ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ!
በምዕራብ ወሎ ግንባር የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር ሰራዊት ድባቅ ተመታ! 2 ሞርተር 82 mm ከበርካታ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ጋር ተማርኳል:: በርካታ ጠላትም ተደምስሷል::
"በዘመቻ አርበኛ ፍሬው አለና" መቅደላ፣ ተንታ፣ አማራ ሳይንት እና ወግድ ወረዳ ውስጥ ታሪክ ተሰርቷል::
መቅደላ ወረዳ ውስጥ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ሰራዊት፣ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ሼህ ሁሴን ጅብሪል ሻለቃ እና የልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር በቅንጅት በሰሩት ኦፕሬሽን የመቅደላ ወረዳ መቀመጫ ማሻ ከተማን ጨምሮ ሌሎች ታዳጊ ከተሞችም በወገን ኃይል ቁጥጥር ስር ውለዋል::
የጠላት ሃይል የካቲት 20/2018 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማና ተንታን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን ኔትወርክ በማጥፋት የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃን ጨምሮ ወዳሉበት ቀጠና 83ኛ ክፍለ ጦርን ጨምሮ በበርካታ እግረኛ ሰራዊትና መካናይዝድ እንዲሁም በሁለት ድሮን ታግዞ ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ንስሮቹ በመከላከልና መልሶ ማጥቃት በማድረግ ይዞታዎቹ የነበሩትን መቅደላ ወረዳ ማሻንና አካባቢውን አስለቅቀው በመቆጣጠር ወደ ጊምባና ደሴ እግሬ አውጭኝ ብሎ እንዲሸሽ በማድረግና ሁለት ሞርተርን ጨምሮ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ብሎም በርካታ ሰራዊት በመማረክ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
በተጋድሎው የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃዋን ጨምሮ 2 ሞርተር 82mm አንድ ብሬን፣ አንድ ስናይፐር፣ ከ40 በላይ ክላሽ፣ ከ3500 በላይ የተለያየ ተተኳሽ፣ 9 የመገናኛ ባትሪ እንዲሁም 30 የጠላት ሰራዊት ማርከዋል::
ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሻለቃ ወደ ተንታ ከተማ ማጥቃት በማድረግ በርካታ የጠላት ሰራዊት በመደምሰስ ተንታ ከተማን በቁጥጥራቸው ስር አስገብተዋል:: በተመሳሳይ 23ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ ከሌሎች የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ አሃዶች ጋር በመጣመር ማሻ ከተማን ተቆጣጥራለች:: ባጠቃላይ ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር በአምባሰል ተንታ ማሻ መቅደላና ደሴ ዙሪያ ቀጠናዎች ላይ እየተዘዋወረች ማርሽ ቀያሪ ድሎችን እያስመዘገበች ትገኛልች::
ባጠቃላይ "በዘመቻ አርበኛ ፍሬው አለና" ጠላት በመቶዎች ሙትና ቁስለኛ የተደረገ ሲሆን በዘመቻው የተሳተፉ ሁሉም የምኒልክ ዕዝ አሃዶች ያስመዘገቡት ድል፦
2 ሞርተር
7 ብሬን
6 ስናይፐር
ከ100 በላይ ክላሽንኮቭ ከበርካታ ተተኳሽ እና ከ30 በላይ የጠላት ሰራዊት ጋር ተማርኳል::
የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሞባይል ኔትወርክ በማስጠፋት የመገናኛ አማራጭን ዘግቶ ኦፕሬሽን ለመስራት በማሰብ ዝግጅቱን አጠናቆ ካበቃ በኃላ በተወሰኑ ወረዳዎች ውስጥ እንቅስቃሴ ጀምሮ ስለነበር እንቅስቃሴውን ለመግታት ወግድ ወረዳ ውስጥ መብረቅ ክፍለ ጦር በትናንትናው እለት በአበዬ ጉርባ ቀጠና ገዛዛ አቦ አቅራቢያ ደፈጣ ጥላ በርካታ ኃይል ሙት እና ቁስለኛ ስታደርግ፣
በአማራ ሳይንት ግንባር ደግሞ የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ታቦር ተራራ ሻለቃ ጀብዱ ፈፅሟል:: ከትናንት ማለዳ ጀምሮ ጓሜዳ አቅራቢያ ከባድ ውጊያ ተካሂዷል:: ከሳይንት አጅባር ከተማ ተነስቶ ወደ ጓሜዳ ቀጠና በመግባት ከአርሶ አደሮች ግብር ለማሰባሰብ አስቦ በርካታ ኃይል ይዞ የመጣውን ጠላት ኃይል በመመከት ኦፕሬሽኑን ማበላሸት የቻለ ሲሆን ጠላት ጓሜዳን ሳይረግጥ ሲቀር በብስጭት የከባድ መሳሪያ ቅንቡላ ሲወረውር ውሎ የገበሬዎችን መኖሪያ ቤት እና ንብረት አቃጥሎ ወደመጣበት ፈርጥጧል::
በተለምዶ መለስሳንቃ በሩ የሚባለው ስፍራ ላይ በተደረገው ውጊያ በርካታ የጠላት ኃይል አባላት ስለተመቱ ቁስለኞች ሳይንት አጅባር ሆስፒታል ገብተዋል:: እዚያው አውደ ውጊያ የተደረገበት ቦታ ላይ የሞቱ እንዳሉም የካቲት 21/2018 ዓ.ም ጧት አስከሬን ሲለቅሙ ያዩዋቸው የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል::
በለጋምቦ እና ከላላ ወረዳዎች በኩል የሚንቀሳቀሰውና የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ክንፍ የሆነው ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደዉ) ክፍለ ጦር 3ኛ አህመድ አቀስታ ሻለቃ ወደ ዋርጃ ቀጠና ለመግባት በ20 መኪኖች ተጭኖ የተጓዘውን ጠላት በደፈጣ ጥቃት ዶግ አመድ በማድረግ 18 የደመሰሰ ሲሆን 23 የሚሆነው ጠላት ደግሞ ቁስለኛ ሆኖ አቀስታ የካቲት 12 ሆስፒታል ገብቶ ህክምና ላይ መሆኑ ታውቋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም

🙏4
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፊያለው ደሴ ኮር የአንበሳው ጋይንት ክ/ጦር አመራሮች ከጎብጎብ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በዚህም በወቅታዊ የአማራ ፋኖ የትግል ጉዳይ እና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን ማህበረሰቡም ትግሉን እያገዘ የቆየ መሆኑን እና በቀጣይም ከትግሉ ጎን ሆኖ የጋራ ትግል እሚያደርግባቸውን ሁለተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጭምር አሳውቋል።
ድል ለአማራ ህዝብ!!
ድል ለአማራ ፋኖ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር አንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል!!!
የካቲት 22/2018 ዓ,ም

👍2🙏1
በወግድ ወረዳ የመብረቅ ክፍለ ጦር በአብይ አህመድ ሰራዊት ላይ መጠነ ሰፊ ማጥቃት በመሰንዘር ድል አስመዘገበ::
በደቡብ ወሎ ዞን ወግድ ወረዳ ውስጥ በሚንቀሳቀሰው የንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ስር የሚገኘው መብረቅ ክፍለ ጦር ከትላንት የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽት 5፡00 ጀምሮ በወረዳው በተለያዩ አካባቢዎች ሰፍሮ በሚገኘው የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ላይ የተቀናጀና ብርቱ ማጥቃት መክፈቱ ተገለጸ።
ከክፍለ ጦሩ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የፋኖ አባላቱ በታቀደ የቆረጣ ስልት ጠላትን ግራ በማጋባት ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ። በዚሁ ኦፕሬሽን ላይ በርካታ ሻለቃዎች የተሳተፉ ሲሆን
አደነ ሀብትነው እና ነብሮ ሻለቃ በሸመኔ፣ ያጌ፣ ቦርቦር እና የጉርባ አቅጣጫዎች የጠላትን እንቅስቃሴ በመቁረጥ ድንገተኛ ጥቃት ሰንዝረዋል።
አሳምነው ሻለቃ ምድር ገበያ በተባለ ስፍራ በወሰደው እርምጃ በርካታ የፀጥታ ኃይሎችን (ሚሊሻዎችን) ደምስሷል።
የወረዳው ወቅታዊ ሁኔታ
ውጊያው አሁንም ግለቱን ጠብቆ በቀጠለባቸው አበዬ ጉርባ፣ ያጌ፣ ሸመኔ እና ምድር ገበያ አካባቢዎች የክፍለ ጦሩ አባላት አመቺ ቦታዎችን በመያዝ የጠላትን እንቅስቃሴ መግታት ችለዋል። በአሁኑ ወቅት የወግድ ወረዳ በፋኖ ኃይሎች ተከባ የምትገኝ ሲሆን በአብይ አራዊት ሰራዊት በኩል ከፍተኛ የመንፈስ መላሸቅና የመሸነፍ ስሜት እየታየ ይገኛል።
"አባይ አስገብቻለሁ እያለ ሲፎክር የነበረው ኃይል፣አሁን በገባበት አጣብቂኝ ምክንያት መውጫ አጥቶ በከፍተኛ ጭንቀት ላይ ይገኛል" ሲል ክፍለ ጦሩ ገልጿል።
ምንም እንኳን የሟቾችና የቁስለኞች ቁጥር በዝርዝር ባይገለጽም የብርሃኑ ጁላ ጦር ከፍተኛ የሰው ኃይል ማጣቱንና ቀሪው ኃይልም እጅ ለመስጠት የሚገደድበት ሰዓት ቀርቧል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ውጊያው እጅግ ጠንካራና ድምፁም በከባድ እንደሚሰማ ገልጸው የፋኖ ኃይሎች በየአቅጣጫው የበላይነት ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ አረጋግጠዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም

❤3🙏1
አሳዛኝ ዜና!!!
የአብይ አህመድ አገዛዝ ንፁሀንን ያነፃፀረ የድሮን ጥቃት በሻሁራ ከተማ ላይ ፈፀመ!!!
ጨፍጫፊውና አውዳሚው ደም መጣጭ ፀረ አማራ የአገዛዙ ሰርአት በእግረኛ ሜካናይዝድ ጦር የአማራን ህዝብ ለእልቂትና ለስቃይ መዳረጉ አልበቃው ብሎ፤ አሁን ላይ በየ ሀገራቱ ተንከራቶና ለምኖ በሚያስገባቸው ድሮኖች ንፁሀንን ያነፃፀረ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል።
በማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ የድሮን ጥቃትና ቅኝት በተለይ በዚህ አንድ ሳምንት በማያቋርጥ መልኩ በቀንም በማታም የተደጋገመ ሲሆን ህዝባችን ለሽብርና ለሞት እየዳረገ ይገኛል። በዛሬው እለት የካቲት 23/2018 ከጧቱ 1:00 ስአት ገደማ ሻሁራ ከተማ ቀበሌ01 ዉሀ የሚቀዱ ንፁሀን ላይ ያነፃፀረ ጥቃት ተፈፅሟል። በዚህ ጥቃት ወ/ሮ አንጓች የሀለም፣ ወጣት ናንየ ደጉ እና አቶ አለሙ አቢታ ለእልፈተ ሞት ሲዳረጉ ዋወይ የሚባል ንፁሀንም ከባድ ቁስለኛ ሆኗል።እንዲሁም አንድ የንፁሀን ቤት ሊወድም ችሏል።
ተስፋ ቆራጩ የአገዛዙ ስርአት የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፍቶት የጀግኖችን የመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ክንድ መቋቋም ሲያቅተው እና ከወረዳው ሰራዊቱን በመደምሰስና በመማረክ አቅመቢስ የሆነው፤ አሁን ላይ እንደ አማራጭ ንፁሀን ህዝባችን ላይ ሂሳብ ለማወራረድ የሚሄድበትን እርቀት ምን ያህል በወታደራዊም ሆነ በፓለቲካዊ ዘርፍ የወረደና የተቀዣቀዠ መሆኑ የአራት ኪሎ እድሜው ያበቃ እንደሆነ ያሳያል።
ፈጣሪ የተሰው ንፁሀንን ነብስ ይማር!!! ወዳጅ ዘመዶቻቸውን መፅናናት ይስጥልን።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ
የካቲት 23/2018

💔3❤1