ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ስሪንቃ ከተማ ዙሪያ ድል አስመዘገቡ::

ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦርና ምስራቅ አማራ ኮር1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በጋራ በመሆን በሀብሩ ወረዳ በሲሪንቃ ከተማ ከወልደያ ለማጥቃ የተንቀሳቀሰዉን 46ኛ ክፍለ ጦር የጠላት ሃይል ድባቅ በመምታት ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዘገቡ።

አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮርና ምስራቅ አማራ ኮር 1 በለሽርጡ ክፍለ ጦር በጋራ በመናበብ የብልፅግናን ወንበር አስጠባቂ 46ኛ ክ/ጦር የጥላት ሀይል ከወልደያ ከተማ አናብስቶቹ ወደ ሚንቀሳቀሱበት ወደ ሲሪንቃ ከተማ ለማጥቃት እንቅስቃሲ ቢደርግም ከወደ መርጦ ሚካኤል አቅጣጫ በሞላ ጊወርጊስ አቅጣጫ የምስራቆቹ ኮኮብ ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር ማጥቃት ሲገቡ እንደሁም አይበገሪዎቹ 24ኛ ክፍለ ጦር ከወደ ቱላንባ ጥላት ባለበት በስተቀኝ አቅጣጫ አሰላለፋቸዉን በማስተካከል የአብይን ወንበር አስጠባቂ ሀይል አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አሰመዝግበዋል።

ተናበዉ አሰላለፋቸዉን አሳምረዉ የገቡት አናብስቶቹ ለማጥቃት በቅዥት የመጣዉን ሃይል ቅዥት አድርገዉ ሀሳቡን አንኮላሽተዉበት ሙትና ቁስለኛ በማድርግ ቁስለኛዉንና እሬሳዉን ሳያነሳ ወደመጣበት ወደ ወልደያ እግሬ አዉጭኝ ብሎ ፈርጥጧል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 20/2018 ዓ.ም
🙏21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄ ዕልቂት ማቆሚያ አጥቷል። ኢትዮጵያ የግፍ ምድር ሆናለች።
👍2💔1
አሳምነው ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ ጉባላፍቶ ወረዳ ዶሮ ግብር ከተማ በጨለማ ሰርገው በመግባት ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዘገቡ!

አሳምነው ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ የተወሰኑ አባላቶች ጉባላፍቶ ወረዳ ዶሮ ግብር ከተማ የካቲት 20/2018 ዓ.ም ምሽት ሰርገው በመግባት አንድ ጓድ (ቲም) ሙሉ የጠላት መንገድ መሪ ባንዳ ሚሊሻ ላይ እርምጃ በመውሰድ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::

አፋብን ያወጀውን የምህረት አዋጅ መጠቀም ሲገባቸው ሆዳቸውን መርጠው የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለውን የኦሆዴድ ብልፅግና ሰራዊት መንገድ በመምራት ላይ የተሰማሩ እስከ ስምንት የሚደርሱ (አንድ ጓድ) ሚሊሻዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 21/2018 ዓ.ም
1🙏1
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና በደቡብ ወሎ ዞን በተንታ አጅባርና ማሻ የህዝብ ሃብት የሆነን መሬት እየዘረፈ ለታጠቁ ሃይሎች እያደለ ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛል::

ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ የመሬት ወረራና ዘረፋ ጋር ተያይዞ የምኒልክ ዕዝን መመሪያ ተላልፋችሁ ከአገዛዙ ካድሬዎችና ታጣቂዎች መሬት የምትገዙ የአካባቢው ማህበረሰብ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን!

ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና የትጥቅ ትግሉን መቋቋም እንደማይችል ሲያረጋግጥ ለሚሊሻ መሬት እሰጣለሁ በማለትና የተሰጣቸውን መሬት ለማህበረሰቡ እንዲሸጡ በማድረግ ፋኖ ከማህበረሰቡ ጋር ግጭት እንዲፈጥር የማድረግ ሴራ እየሰራ መሆኑን እና ወጣቱም በዚህ ተማሎ እንድገባ በማድረግ እርስ በርስ ግጭትንም ለማፋፋም እየሰራ እንደሆነ ደርሰንበታል!

ስለሆነም በአማራ ህዝብ ሃብት ጦር መሳሪያ እየሸመተና ጦር እያዘመተ የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና የዘረፈውን መሬት የምትገዙ ባለሃብቶችና መሃል ላይ ሆናችሁ ሁኔታዎችን የምታመቻቹ ህገወጥ ደላላዎች ከአገዛዙ ካድሬዎች ለይተን አናያችሁምና ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን ይህንን መመሪያችንን ተላልፎ የተገኘ አካል ላይ ግን የማያዳግም እርምጃ እንደምንወስድ እናሳስባለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 21/2018 ዓ.ም
💔1
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት በአውደ ውጊያ የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው የህዝብን ሃብት እያወደመ ቀጥሏል!

አማራ ሳይንት ወደ ጓ ሜዳ ማጥቃት አድርጎ የፋኖን ቀጠና ለማስለቀቅ ሞክሮ ከንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ጠንካራ መከላከልና መልሶ ማጥቃት ገጥሞት ሽንፈት ተከናንቦ ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ወደ መጣበት የተመለሰው ጠላት በከባድ መሳሪያ ከተሞችን በመደብደብ በሰው ህይወት በንብረትና በእንስሳቶች ላይ ሳይቀር ከባድ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል::

በዚህም የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት መከላከያ በሚል ሽፋን የደንብ ልብስ አልብሶ ያመጣው የኦሮሚያ ብልፅግና ልዩ ሃይል እንደሆነ ተደጋጋሚ በፈፀማቸው ግፎች የታየ ሲሆን ይህንን ተግባሩን አማራ ሳይንት ላይ የማህበረሰቡን ቤትና ንብረት እንዲሁም በጎተራ የተቀመጠ እህል ቤንዚን አርከፍክፎ በእሳት ሙሉ ለሙሉ አውድሞ በመሄድ አሳይቷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 21/2018 ዓ.ም
💔1
የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ. ም

አፋብን ቴወድሮስ እዝ 90 ክላሽ እና 3 ብሬን የማረከበት ውጊያ ተደረገ።

ከዳንግላ እስከ አባድራ፣ ወርቅ ሜዳ እንዲሁም ከዳንግላ እስከ ጭሮ ቢኮሎ የተዘረጋውን የጠላት ኃይል ብትንትኑ ወጧል።

የወገን ኃይል ከምስራቁ ወደ ምዕራቡ የጎጃም ክፍል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል በሚል እቅድ ከዳንግላ ባህርዳር ዋናዉን አስፋልት ለወራት ይዞ የነበረውን የጠላት ጥምር ኃይል (መከላከያ፣ አድማ ብተና እና ፖሊስ) በተቀናጀ መንገድ ለመምታት በወጣው ወታደራዊ እቅድ መሰረት ታላቅ ጀብዱ ተፈፅሟል።

ከጃዊ ወደ ዳንግላ መውጫ ያሉትን ገዥ ቦታወች ካሳች፣ አፄ ዮሃንስ እና ወለቴ ላይ የሰፈረውን ጠላት ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በጠዋቱ ማጥቃት በተጀመረ በደቂቃወች ውስጥ ብሬን የተማረከበትን ውጊያ በድል ቀጥሏል።

የአፋብን ቴወድሮስ እዝ 105ኛ እና 109ኛ ኮሮች በጋራ ያደረጉት ማጥቃት አድማሱን በማስፋት ከዳንግላ እና መርዓዊ መካከል ጭሮ የተባለ ቦታ ላይ የሰፈረውን አረመኔ ሰራዊት መደምሰስ ችሏል።

የወገን ኃይል ላይ ከፍተኛ መነቃቃት እና ወኔን በፈጠረው በዛሬው የውጊያ ውሎ:-
1) 90 (ዘጠና) የነፍስ ወከፍ መሳሪያወች
2) 3 (ሶስት) ብሬን መትረዬስ
3) 1(አንድ) የዲሽቃ አፈሙዝ ከነ ተተኳሹ
4) 10,000 (አስር ሺ) በላይ የክላሽ እና የብሬን ጥይት
5) በርካታ የእጅ ቦንቦች
6/ 20( ሃያ) ምርኮኛ ሰራዊት እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶችን የወገን ኃይል ማርኮ መታጠቅ ችሏል።

እንዲሁም 20(ሃያ) የመከላከያ አባላት ሲማረኩ ከ100 በላይ የጠላት ሰራዊት ተገድሏል።

ይቀጥላል...
3🙏2