ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በቀን 19/06/2018 ዓ/ም አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ የወጠውን የምረት አዋጅ በመጠቀም ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ ።በሐሙሲት ከተማ የሚገኙት ሻለቃ 11 አባል የሆኑት የአድማ ብተና አባላት የምረት አዋጁን በመጠቀም ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር አሀድ የሆነችውን አንበሶ ብርጌድ ተቀላቀሉ።
1ኛ=ጌታየ ገልጋይ
2ኛ=ታድሎ ሁኔ
3ኛ=ብርሃኑ ተመቸው ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በመምጣት ከፋኖ ጋር አብረው ሁነው ለመታገል ወስነዋል


ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር
ህ/ግ ፍቅሩ ባየ
🙏31👍1😁1
ጉና ክፍለ ጦር ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ የህዝብ ውይይት መድረክ አካሄደ‼️
=============================
ጉና ክፍለ ጦር ከሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች መካከል ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ ከማህበረሰቡ ጋር በዛሬው ዕለት ማለትም በ20/2018 ዓ.ም የአፋብን /ሰ/አ/ቀ/ በላይ ዕዝ ም/ ፖለቲካ መምሪያ ሃላፊ አርበኛ አራገው እንዳለ፣ የአፋብን ሰ/አ/ቀ/ በላይ ዕዝ ጥናትና ስትራቴጅ መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ደራሲ አንተነህ ድረስ፣ የሜ/ጀ/ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ አመኑ አለም አንተ፣ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ኮር ጀኔራል ኃይሌ መለሰ ዘ ውባንተ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አበበ መልኬ፣ የጉና ክፍለ ጦር ስራ አስፈፃሚዎች፣ ስማዳ ሃገረ ቢዘን ብርጌድ ሰራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የወረዳው የፋኖ ጊዜያዊ መንግስት በታደሙበት የህዝብ ውይይት መድረክ ተካሂዶል።

በህዝባዊ ውይይቱም በሚከተሉት ጉዳዮች ሰፊ ውይይቶች ተደርጎባቸዋል።

✔️ የብልፅግናን ስርዓት ማፈረስና የአማራን ህዝብ ህልውና መታደግ፤
✔️ የህዝብ አስተዳደር ፍትህ ማስፈን እና የህዝብ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማስቀጠል፤
✔️ የወረዳው ህዝብ በመደራጀት ከአገዛዙ ወራሪ ሃይል ራሱን እንዲጠብቅ ፤
✔️ የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋም ሰላምና ደህንነት መጠበቅና ማሰጠበቅ፤
✔️ ጠንካራ የህዝብ አደረጃጀት በመፍጠር አካባቢችሁን ከሌባ እና ከዘራፉ ቡድን መጠበቅ ፤
እንዲሁም ሌሎች የፖለቲካ ጉዳዮች በስፋት ውይይት ሲደረግባቸው ውለዋል።

በመጨረሻም የበላይ ዕዝ እና የሜ/ጀ/ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር የፋኖ አመራሮች ከህዝቡ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ እና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ፍፁም ጨዋና ፍቅር በተላበሰ መሌኩ ተጠናቋል።
ህልውናችን በተባባረ ክንዳችን!!
አፋብን በላይ ዕዝ ሜ/ጀ/ ውባንተ አባተ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ፋኖ መምህር ያሬድ ገደፍው
3
ሰሜን ብርቅዬ ክፍለጦር ሪፎርም አድርጓል!!

ይካቲት 20/2018 ዓ.ም

🔸አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ ራስ አሞራው ፫ ኮር የሰሜን በርቅዬ ክ/ጦር ለ4 ቀናት ከራስ አሞራው ሶስተኛ ኮር አስተባባሪ ግብረ-ሀይል ማለትም አርበኛ አስቻለው በለጠ ፣አርበኛ አስምሮ ፍቃዴ ፣ አርበኛ ሸጋ ጌታቸው ፣ አርበኛ አስፋው ሰርፀ ፣አርበኛ እያቸው ብርሃኑ፣ ከኮሩ ከፍተኛ አመራር ጋር በመሆን ጥልቅ ግምገማና ውይይት በማድረግ፣ የስራ ተግዳሮቶችን እና መልካም አጋጣሚዎችን በመለየት ለቀጣይ ክፍለጦሯን በሁሉም ዘርፍ ሁለንተናዊ የድርጅት መርህን በተከተለ መልኩ ስራዎችን እንድትፈፅም ማድረግና ለውጤት መታተር እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል።

በጥልቅ ግምገማ ማጥራትና ማብቃት የሰሜን ብርቅየ ክ/ጦር መልካም ስራዎችንና ተሞክሮዎችን በማድነቅ እንዲሁም እውቅና በመስጠት አድናቆትን ያገኙ ሲሆን በሁለንተናዊው የስራ ዘርፍ ተግዳሮት ሆነው የማያሰሩ እንቅፋቶችን በመለየት የቀጣይ ድርጅታዊ አቅጣጫ በማስቀመጥ ችሎታንና አቅምን ባማከለ እና ለተሻለ ግዳጅ በሚያመች መልኩ መሪዎችን እንደገና ማደራጀት (Reform) በተሳካ ሁኔታ መስራት ተችሏል።

በወቅቱም የአፋብን ምክትል ሊቀመንበር እና ለወታደራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ተገኝተው ለተመረጡ
የክፍለጦርና የብርጌድ አመራሮች መልዕክት አስተላልፏል።
"በአንድ በኩል እያደራጀን እና እያሰለጠን
በሌላ በኩል እየተዋጋን እዚህ ደረጃ ደርሰናል
የያዝነው ዓለማ የተከበረ ነው እንኳን ወገን ጠላት ያከብረዋል "
እናተ የራስ ገብሬ፣ የደጃች ውቤ ልጆች ናቹህ፣ አባቶቻቹህ ሃገር አሰቀጥለዋል የአባቶቻቹህን ታሪክ እንድታስቀጥሉ አደራ ማለት እፈልጋለው ።
አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ከተናገረው የተወሰደ !

ከዚህ በተጨማሪ የሰሜን ብርቅየ ክ/ጦር ሪፎርም በተሳካ ሁኔታ መስራት ተችሏል።
💎የክ/ጦር ሪፎርም
1ኛ አርበኛ አድኖ ዋሴ ዋና አዛዥ
2ኛ አርበኛ ፃዲቅ ምትኬ ም/ል አዛዥ
3ኛ አርበኛ ጌጡ መልካሙ ዘመቻ አዛዥ
4ኛ አርበኛ ታዴ ጥጋቡ ም/ዘመቻ
5ኛ አርበኛ ንጉስ አዲስ ህ/ግንኙነት
6ኛ አርበኛ ደማሙ ነጠረ ፖለቲካ ዘርፍ
7ኛ አርበኛ ደስታው አስማረ ፋይናንስ
8ኛ አርበኛ ኝደጉ እሙሃይ ሎጅስቲክ
9ኛ አርበኛ ወንድሙነይ ፈንቴ ስልጠና
10ኛ አርበኛ በላይ መድፉ ልዩ ኦፕሬሽን
11ኛ አርበኛ ሽቤ ነጋሽ የሰው ሃይል
12ኛ አርበኛ ፍቃድ መሰረት ህግ መምሪያ
13ኛ አርበኛ ሻምበል ይመር ህ/አስተዳደር
14ኛ አርበኛ አዲሱ አወቀ አደረጃጀት
15ኛ አርበኛ ዳኘው በአካል ፅ/ቤት

የተሰራውን የመሪዎች ሪፎርም ሁሉም የሰራዊት አባላት በሙሉ ድምፅ ከማፅደቃቸው በተጨማሪ ሁሉም የክ/ጦር አመራሮች በሰራዊቱ ፊት እንዲሁም ፣ የዕዙና የኮር አመራር ባሉበት በታማኝነት፣ በፍታዊነት፣ በቅንነት፣ እዝ እና ሰንሰለትን በመጠበቅ ከትናንት ተግዳሮቶቻችን ተምረን ጠንካራ ጎኖቻችን የበለጠ አጠንክረን በተሻለ የስራ አፈፃፀም የአማራን የህልውና ትግል አሸናፊ ሆኖ የድል ችቦ ለማብራት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል አማራዊ ግዴታችን እንወጣለን ሲሉ ቃል በመግባት የማጥራትና ማብቃት ሂደቱ በስኬት ተጠናቋል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ
🙏4
የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ስሪንቃ ከተማ ዙሪያ ድል አስመዘገቡ::

ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦርና ምስራቅ አማራ ኮር1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በጋራ በመሆን በሀብሩ ወረዳ በሲሪንቃ ከተማ ከወልደያ ለማጥቃ የተንቀሳቀሰዉን 46ኛ ክፍለ ጦር የጠላት ሃይል ድባቅ በመምታት ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዘገቡ።

አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮርና ምስራቅ አማራ ኮር 1 በለሽርጡ ክፍለ ጦር በጋራ በመናበብ የብልፅግናን ወንበር አስጠባቂ 46ኛ ክ/ጦር የጥላት ሀይል ከወልደያ ከተማ አናብስቶቹ ወደ ሚንቀሳቀሱበት ወደ ሲሪንቃ ከተማ ለማጥቃት እንቅስቃሲ ቢደርግም ከወደ መርጦ ሚካኤል አቅጣጫ በሞላ ጊወርጊስ አቅጣጫ የምስራቆቹ ኮኮብ ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር ማጥቃት ሲገቡ እንደሁም አይበገሪዎቹ 24ኛ ክፍለ ጦር ከወደ ቱላንባ ጥላት ባለበት በስተቀኝ አቅጣጫ አሰላለፋቸዉን በማስተካከል የአብይን ወንበር አስጠባቂ ሀይል አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አሰመዝግበዋል።

ተናበዉ አሰላለፋቸዉን አሳምረዉ የገቡት አናብስቶቹ ለማጥቃት በቅዥት የመጣዉን ሃይል ቅዥት አድርገዉ ሀሳቡን አንኮላሽተዉበት ሙትና ቁስለኛ በማድርግ ቁስለኛዉንና እሬሳዉን ሳያነሳ ወደመጣበት ወደ ወልደያ እግሬ አዉጭኝ ብሎ ፈርጥጧል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 20/2018 ዓ.ም
🙏21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄ ዕልቂት ማቆሚያ አጥቷል። ኢትዮጵያ የግፍ ምድር ሆናለች።
👍2💔1
አሳምነው ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ ጉባላፍቶ ወረዳ ዶሮ ግብር ከተማ በጨለማ ሰርገው በመግባት ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዘገቡ!

አሳምነው ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ የተወሰኑ አባላቶች ጉባላፍቶ ወረዳ ዶሮ ግብር ከተማ የካቲት 20/2018 ዓ.ም ምሽት ሰርገው በመግባት አንድ ጓድ (ቲም) ሙሉ የጠላት መንገድ መሪ ባንዳ ሚሊሻ ላይ እርምጃ በመውሰድ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::

አፋብን ያወጀውን የምህረት አዋጅ መጠቀም ሲገባቸው ሆዳቸውን መርጠው የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለውን የኦሆዴድ ብልፅግና ሰራዊት መንገድ በመምራት ላይ የተሰማሩ እስከ ስምንት የሚደርሱ (አንድ ጓድ) ሚሊሻዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 21/2018 ዓ.ም
1🙏1