ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ከአቢይ አሕመድ መከላከያ ላይ በዓለም ሳጋ ምድር በውባንተ አባተ ልጆች ከተራራ የገዘፈ ደማቅ ድል ተመዝግቧል።

ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር
የክፍለጦሩ ቃኝና መሐንዲሥ
አሣምነው ብርጌድ

ጉና ክፍለ ጦር
ገብረ መሥቀል ብርጌድ/ታቦር ሻለቃ
የክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚ

የካቲት 18/2018ዓ.ም

እጅግ አሥደማሚ ድል በውቤ ልጆች ተገኝቷል። ከባሕር ዳርና ከደብረ ታቦር የመጣው መከላከያ ድቅቅ ብሎ ተመትቷል። ከ20+ የመከላከያ ተሽከርካሪ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በ03 ዓመታት ትግላችን የዛሬውን ጣፋጭ ድል የሚተካከል የለም።

ከትናንቱ ምት የተረፈው አዳሩን ሙሉ አማራ በታኙ ፈርሶ እንዳደረ ልብ ይሏል። 31 አማራ በታኞች አዳራቸውን ወደው ሳይሆን ተገድደው ዓምሐራ ፋኖን ተቀላቅለዋል።

ክብርና ምሥጋና ለሜጀር ጀነራል ውብ-አንተ አባተ አብራኮች

ዝርዝሩን እናደርሳለን።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑

አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው።
🙏6
ሰበር የድል ዜና

የመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር አለፋ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ከጠላት ነፃ በማድረግ የወረዳዋን መቀመጫ ሻሁራ ከተማን መቆጣጠር ተቻለ።

በአርበኛ ማንዴላ እያዩ የተመራው አውደ ውጊያ ሙሉ በሙሉ ማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳን ከአገዛዙ አረመኔ ሰራዊት ነፃ ለማድረግ በታቀደው ልክ ከፍተኛ ታሪካዊ ድል ማስመዝገብ የተቻለበት መንገድ ህዝባችንና ታጋያችን ያስደሰተ ሲሆን ጠላትን ክፉኛ ያሽመደመደ ሆኗል።

ይህ አውደ ውጊያ የኮርና የክ/ር አመራሮች ከብርጌድና የሻለቃ መሪዎች ጋር በመተሳሰር፤ ቋራ ኦሜድላ ክ/ር፣ ካራማራ ክ/ር፣ አድዋ ክ/ር፣ ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ር ካላቸው ሀይል በማውጣጣት የካቲት 15/2018 7:30 የጀመረው አውደ ውጊያ የአገዛዙን አሸርጋጅ አድማ በታኝ፣ ሚሊሻ፣ ፖሊስና የስርአቱ አሸርጋጅ ባንዳዎችን በመደምሰስ እና በመማረክ ከ7 በላይ ከተማ ውስጥ የተሰሩ የቁም ምሽጎችን በመሰባበር ሻሁራ ከተማን በቀላሉ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። ይህ በእንዲህ አንዳለ የአብይ አህመድ የሚተማመንበት እና በየሚድያው እንደ ማስፈራሪያ የሚጠቀምበት የድሮን ጥቃት ለማድረስ የሚችለውን ያህል ሙከራ ቢያደርግም ክንደ ነበልባሎችን የመይሳው ካሳ ልጆችን የሚያቆማቸው ግን አልነበረም፤ እንዲሁም ይህ አውደ ውጊያ የተሳካ እንዲሆን አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጌምድር ክ/ር ጣና ብርጌድ ወደ ቀጠናው ተጨማሪ የጠላት ሀይል እንዳይጨመር ያላሰለሰ እጥረት በማድረግ የተሳካ ስራ ተሰርቷል።

ክንደ ነበልባሎቹ ጠላትን ከሻሁራ ከተማ ጠራርጎ በማስወጣት የካቲት 16/2018 በየስርቻው የተደበቀውን እና ለማምለጥ የሞከረውን የአገዛዙ አሸርጋጅ ቡድን በየገባበት እየተፈለገ እጅ ያልሰጠውን እርምጃ በመውሰድ፣ ከሞት ያመለጠው የብልፅግናው ካቢኔ እና ባንዳ ሰራዊቱ በእግሩ እየማቀቀ ወደ ባ/ዳር ፈርጥጦ ሲያመልጥ በየቦታው በእጁ የያዘውን ትጥቅና ስንቅ እያዝረከረከ፤ እንዲሁም ሙትና ቁስለኛ መሸከፍ ባለመቻሉ የአካባቢው ማህበረሰብ ሁለቱንም ቀን በየቦታውና በየምሽጉ የወደቀውን አስክሬን ሊቀብር ችሏል።

የአገዛዙ ሰራዊት ከሁለት አመት ተኩል በላይ መሽጎበት የነበረው የቁም ምሽጎችን ከመሰባበር ባሻገር ስቶሮችን በፍጥነት በመቆጣጠር ተተኳሾችን፣ መሳሪያዎችን እና መሰል ትጥቆችን በእጃችን ማስገባት ችለናል። ከዚህ በተጨማሪ የአገዛዙ ስርአት የፋኖ ቤተሰብ በማለት እና በውሀ ቀጠነ ለስርአቱ አልተመቸንም የሚሉትን ንፁሀንን ከ45 በላይ እስረኞችን ማስፈታት ተችሏል።

👉በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል
የተደመሰሰ= 231በላይ/ አድማ በታኝ፣ሚኒሻ፣ ፖሊስ፣ አብረው ሲዋጉ የተገኙ የቀጠናው ባንዳዎች እና የፖሊስ አዛዡ ዋና ኢንስፔክተር ውባንተ ይረሳው እና ወንጀል መከላከል ኮማንደር ገብሬ እና በጊዜው አብረው የነበሩ የፖሊስ አባላት አና የሚኒሻ ፅ/ቤት ኃላፊ ጌታነህን ጨምሮ እስከወዲያኛው ተሰናብተዋል።
የተማረከ እጅ የሰጠ= 53
ቁስለኛ ከ67በለይ
👉 በአውደ ውጊያው የተማረከ(የተገኘ) ንብረት
ዲሽቃ= 2
ብሬን= 2
ክላሽንኮቭ= 259
አብራራው= 22
አስር ጎራሽ= 28
1 ስታር ሽጉጥ
የክላሽ ተተኳሽ= 31,000
የብሬን ተተኳሽ= 9000
የዲሽቃ ተተኳሽ= 21,000
የክላሽ ካዝና= ከ700
ወታደራዊ ኮዳ= 50
ወታደራዊ ሻንጣ= 100
ረጅም እርቀት መገናኛ ሬድዮ= 2
የአገዛዙ ሰራዊት የሚጠቀምባቸውን ሙሉ ቁሳቁስ እና 2ተሳቢ ጭነት የሚሆን ሬሽን

👉ሌላው የመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ር በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ነጋዴ ባህር ሌላ ተጨማሪ ድል አስመዝግበዋል።

የካቲት 16/2018 ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ር ከታጠቅ ብርጌድ እና ባይተኩስ ብርጌድ የተውጣጡ የፋኖ ሀይሎች በዚሁ ቀን ተጠግቶ በማደር የአገዛዙን የሚኒሻ አባላትና አድማ በታኝ በመሸገበት ሰርጎ በመግባት አዳኝ አገር ጫቆ ነጋዴ ባህር ልዩ ቦታው አቸራ በር ላይ ሲረፈርፉት አርፍደዋል።

በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል:
የተደመሰሰ= 23
የቆሰለ= 12
የተማረከ እጅ የሰጠ= 5
የተገኘ ንብረት:
ክላሽንኮቭ= 17
ብሬን= 1
የክላሽ ተተኳሽ= 1000
የብሬን ተተኳሽ= 1200

በዚህ ስአት በመየሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ስር የምትገኘው ሻሁራ ከተማ ሁሉም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ባንኮችን ጨምሮ መደበኛ ስራቸውን ፍፁም ሰላም በተሞላበት መንገድ እየሰሩ ይገኛሉ።

ሌላው ጉዳይ ከአሁን በፊት በሚድያ እንዳሳዎቅነው ለአገዛዙ ስርአት እድሜ ማራዘሚያ ሆናችሁ የምታገለግሉ የሚኒሻ አባላት፣ ፖሊስና አድማ ብተና ቀሪ ቀጠናዎችን ነፃ ለማድረግ የሚያግደን ስለሌለ አሁን ባለው የፖለቲካ አሻጥር መጠቀሚያ እንዳትሆኑና ውድ ህይወታችሁን እንዳታባክኑ አሁንም በዚሁ አጋጣሚ ወገናዊ ጥሪያችን ማስተላለፍ እንወዳለን።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ
የካቲት 18/2018
8🙏1
በቀን 19/06/2018 ዓ/ም አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ የወጠውን የምረት አዋጅ በመጠቀም ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ ።በሐሙሲት ከተማ የሚገኙት ሻለቃ 11 አባል የሆኑት የአድማ ብተና አባላት የምረት አዋጁን በመጠቀም ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር አሀድ የሆነችውን አንበሶ ብርጌድ ተቀላቀሉ።
1ኛ=ጌታየ ገልጋይ
2ኛ=ታድሎ ሁኔ
3ኛ=ብርሃኑ ተመቸው ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በመምጣት ከፋኖ ጋር አብረው ሁነው ለመታገል ወስነዋል


ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር
ህ/ግ ፍቅሩ ባየ
🙏31👍1😁1
ጉና ክፍለ ጦር ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ የህዝብ ውይይት መድረክ አካሄደ‼️
=============================
ጉና ክፍለ ጦር ከሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች መካከል ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ ከማህበረሰቡ ጋር በዛሬው ዕለት ማለትም በ20/2018 ዓ.ም የአፋብን /ሰ/አ/ቀ/ በላይ ዕዝ ም/ ፖለቲካ መምሪያ ሃላፊ አርበኛ አራገው እንዳለ፣ የአፋብን ሰ/አ/ቀ/ በላይ ዕዝ ጥናትና ስትራቴጅ መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ደራሲ አንተነህ ድረስ፣ የሜ/ጀ/ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ አመኑ አለም አንተ፣ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ኮር ጀኔራል ኃይሌ መለሰ ዘ ውባንተ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አበበ መልኬ፣ የጉና ክፍለ ጦር ስራ አስፈፃሚዎች፣ ስማዳ ሃገረ ቢዘን ብርጌድ ሰራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የወረዳው የፋኖ ጊዜያዊ መንግስት በታደሙበት የህዝብ ውይይት መድረክ ተካሂዶል።

በህዝባዊ ውይይቱም በሚከተሉት ጉዳዮች ሰፊ ውይይቶች ተደርጎባቸዋል።

✔️ የብልፅግናን ስርዓት ማፈረስና የአማራን ህዝብ ህልውና መታደግ፤
✔️ የህዝብ አስተዳደር ፍትህ ማስፈን እና የህዝብ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማስቀጠል፤
✔️ የወረዳው ህዝብ በመደራጀት ከአገዛዙ ወራሪ ሃይል ራሱን እንዲጠብቅ ፤
✔️ የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋም ሰላምና ደህንነት መጠበቅና ማሰጠበቅ፤
✔️ ጠንካራ የህዝብ አደረጃጀት በመፍጠር አካባቢችሁን ከሌባ እና ከዘራፉ ቡድን መጠበቅ ፤
እንዲሁም ሌሎች የፖለቲካ ጉዳዮች በስፋት ውይይት ሲደረግባቸው ውለዋል።

በመጨረሻም የበላይ ዕዝ እና የሜ/ጀ/ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር የፋኖ አመራሮች ከህዝቡ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ እና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ፍፁም ጨዋና ፍቅር በተላበሰ መሌኩ ተጠናቋል።
ህልውናችን በተባባረ ክንዳችን!!
አፋብን በላይ ዕዝ ሜ/ጀ/ ውባንተ አባተ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ፋኖ መምህር ያሬድ ገደፍው
3
ሰሜን ብርቅዬ ክፍለጦር ሪፎርም አድርጓል!!

ይካቲት 20/2018 ዓ.ም

🔸አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ ራስ አሞራው ፫ ኮር የሰሜን በርቅዬ ክ/ጦር ለ4 ቀናት ከራስ አሞራው ሶስተኛ ኮር አስተባባሪ ግብረ-ሀይል ማለትም አርበኛ አስቻለው በለጠ ፣አርበኛ አስምሮ ፍቃዴ ፣ አርበኛ ሸጋ ጌታቸው ፣ አርበኛ አስፋው ሰርፀ ፣አርበኛ እያቸው ብርሃኑ፣ ከኮሩ ከፍተኛ አመራር ጋር በመሆን ጥልቅ ግምገማና ውይይት በማድረግ፣ የስራ ተግዳሮቶችን እና መልካም አጋጣሚዎችን በመለየት ለቀጣይ ክፍለጦሯን በሁሉም ዘርፍ ሁለንተናዊ የድርጅት መርህን በተከተለ መልኩ ስራዎችን እንድትፈፅም ማድረግና ለውጤት መታተር እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል።

በጥልቅ ግምገማ ማጥራትና ማብቃት የሰሜን ብርቅየ ክ/ጦር መልካም ስራዎችንና ተሞክሮዎችን በማድነቅ እንዲሁም እውቅና በመስጠት አድናቆትን ያገኙ ሲሆን በሁለንተናዊው የስራ ዘርፍ ተግዳሮት ሆነው የማያሰሩ እንቅፋቶችን በመለየት የቀጣይ ድርጅታዊ አቅጣጫ በማስቀመጥ ችሎታንና አቅምን ባማከለ እና ለተሻለ ግዳጅ በሚያመች መልኩ መሪዎችን እንደገና ማደራጀት (Reform) በተሳካ ሁኔታ መስራት ተችሏል።

በወቅቱም የአፋብን ምክትል ሊቀመንበር እና ለወታደራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ተገኝተው ለተመረጡ
የክፍለጦርና የብርጌድ አመራሮች መልዕክት አስተላልፏል።
"በአንድ በኩል እያደራጀን እና እያሰለጠን
በሌላ በኩል እየተዋጋን እዚህ ደረጃ ደርሰናል
የያዝነው ዓለማ የተከበረ ነው እንኳን ወገን ጠላት ያከብረዋል "
እናተ የራስ ገብሬ፣ የደጃች ውቤ ልጆች ናቹህ፣ አባቶቻቹህ ሃገር አሰቀጥለዋል የአባቶቻቹህን ታሪክ እንድታስቀጥሉ አደራ ማለት እፈልጋለው ።
አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ከተናገረው የተወሰደ !

ከዚህ በተጨማሪ የሰሜን ብርቅየ ክ/ጦር ሪፎርም በተሳካ ሁኔታ መስራት ተችሏል።
💎የክ/ጦር ሪፎርም
1ኛ አርበኛ አድኖ ዋሴ ዋና አዛዥ
2ኛ አርበኛ ፃዲቅ ምትኬ ም/ል አዛዥ
3ኛ አርበኛ ጌጡ መልካሙ ዘመቻ አዛዥ
4ኛ አርበኛ ታዴ ጥጋቡ ም/ዘመቻ
5ኛ አርበኛ ንጉስ አዲስ ህ/ግንኙነት
6ኛ አርበኛ ደማሙ ነጠረ ፖለቲካ ዘርፍ
7ኛ አርበኛ ደስታው አስማረ ፋይናንስ
8ኛ አርበኛ ኝደጉ እሙሃይ ሎጅስቲክ
9ኛ አርበኛ ወንድሙነይ ፈንቴ ስልጠና
10ኛ አርበኛ በላይ መድፉ ልዩ ኦፕሬሽን
11ኛ አርበኛ ሽቤ ነጋሽ የሰው ሃይል
12ኛ አርበኛ ፍቃድ መሰረት ህግ መምሪያ
13ኛ አርበኛ ሻምበል ይመር ህ/አስተዳደር
14ኛ አርበኛ አዲሱ አወቀ አደረጃጀት
15ኛ አርበኛ ዳኘው በአካል ፅ/ቤት

የተሰራውን የመሪዎች ሪፎርም ሁሉም የሰራዊት አባላት በሙሉ ድምፅ ከማፅደቃቸው በተጨማሪ ሁሉም የክ/ጦር አመራሮች በሰራዊቱ ፊት እንዲሁም ፣ የዕዙና የኮር አመራር ባሉበት በታማኝነት፣ በፍታዊነት፣ በቅንነት፣ እዝ እና ሰንሰለትን በመጠበቅ ከትናንት ተግዳሮቶቻችን ተምረን ጠንካራ ጎኖቻችን የበለጠ አጠንክረን በተሻለ የስራ አፈፃፀም የአማራን የህልውና ትግል አሸናፊ ሆኖ የድል ችቦ ለማብራት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል አማራዊ ግዴታችን እንወጣለን ሲሉ ቃል በመግባት የማጥራትና ማብቃት ሂደቱ በስኬት ተጠናቋል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ
🙏4