ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር እና ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር በጥምረት ጠላት ላይ ድል ተቀዳጁ::

ዛሬ የካቲት 16/2018 ዓ/ም በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ስሪንቃ ቀበሌ መነሻውን ወልድያ ከተማ ያደረገ ጠላት ከሌሊቱ 8:00 ጀምሮ ፋኖ ወዳለበት ቀጠና ማጥቃት ሞክሮ ከፍተኛ ካሳራ ደርሶበት ተመልሷል።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር እንዲሁም ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በተጠቀሰው ቀን ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው ወደመጣበት ወልድያ ከተማ መልሰውታል።

በተጋድሎው ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ እየተደረገ እስከ ማታ 11:00 የዋለ ሲሆን በውጊያው ከባድ ኪሳራ ያስተናገደው ጠላት ከባድ መሳሪያ በመወርወር በንብረትና በሰው ሂወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ሞርተር በማስወንጨፍ የማህበረሰቡን ደን ከማቃጠሉም በተጨማሪ ከግለሰብ ቤት ላይ በመወርወር አንድ የቤተሰብ አባል ሙሉ ከባድ ቁስለኛ አድርጎ የተለመደውን ህዝብ የመጨፍጨፍ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 16/2018 ዓ.ም
2🙏1
የራያ ቆቦ ወርቄ የብልፅግና ታጣቂዎች ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ሁለት ንፁሃኖችን ጎብየ ከተማ ላይ በግፍ ረሸኑ::

የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው የኦሮሞ ብልፅግና ጋር አብረውና ወግነው የተሰለፉት የአድማ ብተና ሚሊሻና ፖሊስ ታጣቂዎች ፋኖን መዋጋት ስለማይችሉ በዋናነት ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎችን ባደባባይ እየረሸኑ ይገኛሉ:: ባለፉት ጊዜያትም በርካታ ንፁሃኖች ላይ ግፍ እንደተፈፀመ ይታወቃል::

ባለፉት ሶስት አመታቶች አማራን ህዝብ ህልውና ለማስከበር ከብልፅግናው አገዛዝ ጋር ብርቱ ተጋድሎ እያደረገ ካለው ፋኖ በተቃራኒ ተሰልፈው ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ በርካታ ንፁሃን አማራዎችን በግፍ እየረሸኑ በቀድሞው ምስራቅ አማራ ፋኖ በአሁኑ ምኒልክ ዕዝ ለህዝብ ሲባል በፍፁም ትግስት በዝምታ እየታለፉ ያሉ ሲሆን ዛሬም ለዋናው አላማ ሲባል ፋኖ ጉዳዩን ለጊዜ ቢታገሳቸውም ይሄንን ወደ ጎን በማለት የተለመደ ድርጊታቸውን በማስቀጠል ራያ ቆቦ ወረዳ ጎብየ ከተማ በመግባት ነጋ ሰለሞን የተባለ የ18 አመት ታዳጊ እና ሃይለማርያም ሞላ የተባለ የ20 አመት ወጣት የካቲት 15/2018 ዓ.ም ምሽት 1:30 ላይ በግፍ ረሽነዋል::

እነዚህ ለሃገርና ለህዝብ የማይበጅ አላማ ያነገቡ የአካባቢውን ማህበረሰብም የማይወክሉ የራያ ወርቄ የብልፅግና ሚሊሻዎች አገዛዙ የሰጣቸውን ድርብርብ አላማ ያለው ተልዕኮ አንግበው ወደ ጎብየ ከተማ በመግባት ሁለቱን ወጣቶች በግፍ ረሽነው ወጥተዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
3
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
[ የካቲት 17/2018ዓ.ም]

የአቢይ አሕመድ ጥምር አራዊት ሰራዊትን ከደብረ ታቦር ከተማ በቅርብ ርቀት ከፀጉር ኪዳነ ምሕረት እሥከ ኮካ፣ ከቆለይ እሥከ ዓለም ሳጋ፣ ከእንቁርቁባ እሥከ ተንሸራታች ድረሥ በደምብ ገርፈውታል።

ውጊያው ከመጀመሩ ጠላት የዓምሐራ ፋኖን ክንድ መቋቋም ተሥኖት አድማ ብተናዎች ተደምሥሠዋል፣ ተማርከዋል፣ ትራፊክ ፖሊሥ እሥከ ወድያኛው ተሸኝቷል፣ ሚሊሺያ ተሸኝቷል፣ የአቢይ መከላከያ ተማርኳል ተደምስሷል።

ጠላት የመዋጋት ሞራሉ ደቅቆ እየተንጠባጠበ ወደ ደብረ ታቦር ከተማ እየፈረጠጠ ይገኛል። ብርቱ ምት ከዓምሐራ ፋኖ የገጠመው አራዊት ሰራዊትም በበቀልና በአጥፊነት ግብሩ 03 ንጹሐን የከተማው ነዋሪዎችን በጭካኔ በጥይት መትቷቸዋል። የተመቱት ንጹሐን 02ቱ ሴቶች ሲሆኑ 01ዱ ደግሞ ወንድ ነው።

ተሥፋ የቆረጠ አገዛዝ ከዚህ የበለጠ ጭካኔውን በንጹሐን ላይ እንደሚያሳርፍ ሕዝቡ አውቆ አውሬውን አገዛዝ ወግድ ማለት ምርጫው ሳይሆን ግዴታው ነው።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን🔑
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑
፩ ዓምሐራ🔑

አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅ-ዓለው ፀጋ አለባቸው

ቋሚ ምሥል፦ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር ሥራ አሥፈጻሚ በከፊል
👍41🙏1
ከአቢይ አሕመድ መከላከያ ላይ በዓለም ሳጋ ምድር በውባንተ አባተ ልጆች ከተራራ የገዘፈ ደማቅ ድል ተመዝግቧል።

ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር
የክፍለጦሩ ቃኝና መሐንዲሥ
አሣምነው ብርጌድ

ጉና ክፍለ ጦር
ገብረ መሥቀል ብርጌድ/ታቦር ሻለቃ
የክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚ

የካቲት 18/2018ዓ.ም

እጅግ አሥደማሚ ድል በውቤ ልጆች ተገኝቷል። ከባሕር ዳርና ከደብረ ታቦር የመጣው መከላከያ ድቅቅ ብሎ ተመትቷል። ከ20+ የመከላከያ ተሽከርካሪ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በ03 ዓመታት ትግላችን የዛሬውን ጣፋጭ ድል የሚተካከል የለም።

ከትናንቱ ምት የተረፈው አዳሩን ሙሉ አማራ በታኙ ፈርሶ እንዳደረ ልብ ይሏል። 31 አማራ በታኞች አዳራቸውን ወደው ሳይሆን ተገድደው ዓምሐራ ፋኖን ተቀላቅለዋል።

ክብርና ምሥጋና ለሜጀር ጀነራል ውብ-አንተ አባተ አብራኮች

ዝርዝሩን እናደርሳለን።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑

አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው።
🙏6
ሰበር የድል ዜና

የመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር አለፋ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ከጠላት ነፃ በማድረግ የወረዳዋን መቀመጫ ሻሁራ ከተማን መቆጣጠር ተቻለ።

በአርበኛ ማንዴላ እያዩ የተመራው አውደ ውጊያ ሙሉ በሙሉ ማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳን ከአገዛዙ አረመኔ ሰራዊት ነፃ ለማድረግ በታቀደው ልክ ከፍተኛ ታሪካዊ ድል ማስመዝገብ የተቻለበት መንገድ ህዝባችንና ታጋያችን ያስደሰተ ሲሆን ጠላትን ክፉኛ ያሽመደመደ ሆኗል።

ይህ አውደ ውጊያ የኮርና የክ/ር አመራሮች ከብርጌድና የሻለቃ መሪዎች ጋር በመተሳሰር፤ ቋራ ኦሜድላ ክ/ር፣ ካራማራ ክ/ር፣ አድዋ ክ/ር፣ ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ር ካላቸው ሀይል በማውጣጣት የካቲት 15/2018 7:30 የጀመረው አውደ ውጊያ የአገዛዙን አሸርጋጅ አድማ በታኝ፣ ሚሊሻ፣ ፖሊስና የስርአቱ አሸርጋጅ ባንዳዎችን በመደምሰስ እና በመማረክ ከ7 በላይ ከተማ ውስጥ የተሰሩ የቁም ምሽጎችን በመሰባበር ሻሁራ ከተማን በቀላሉ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። ይህ በእንዲህ አንዳለ የአብይ አህመድ የሚተማመንበት እና በየሚድያው እንደ ማስፈራሪያ የሚጠቀምበት የድሮን ጥቃት ለማድረስ የሚችለውን ያህል ሙከራ ቢያደርግም ክንደ ነበልባሎችን የመይሳው ካሳ ልጆችን የሚያቆማቸው ግን አልነበረም፤ እንዲሁም ይህ አውደ ውጊያ የተሳካ እንዲሆን አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጌምድር ክ/ር ጣና ብርጌድ ወደ ቀጠናው ተጨማሪ የጠላት ሀይል እንዳይጨመር ያላሰለሰ እጥረት በማድረግ የተሳካ ስራ ተሰርቷል።

ክንደ ነበልባሎቹ ጠላትን ከሻሁራ ከተማ ጠራርጎ በማስወጣት የካቲት 16/2018 በየስርቻው የተደበቀውን እና ለማምለጥ የሞከረውን የአገዛዙ አሸርጋጅ ቡድን በየገባበት እየተፈለገ እጅ ያልሰጠውን እርምጃ በመውሰድ፣ ከሞት ያመለጠው የብልፅግናው ካቢኔ እና ባንዳ ሰራዊቱ በእግሩ እየማቀቀ ወደ ባ/ዳር ፈርጥጦ ሲያመልጥ በየቦታው በእጁ የያዘውን ትጥቅና ስንቅ እያዝረከረከ፤ እንዲሁም ሙትና ቁስለኛ መሸከፍ ባለመቻሉ የአካባቢው ማህበረሰብ ሁለቱንም ቀን በየቦታውና በየምሽጉ የወደቀውን አስክሬን ሊቀብር ችሏል።

የአገዛዙ ሰራዊት ከሁለት አመት ተኩል በላይ መሽጎበት የነበረው የቁም ምሽጎችን ከመሰባበር ባሻገር ስቶሮችን በፍጥነት በመቆጣጠር ተተኳሾችን፣ መሳሪያዎችን እና መሰል ትጥቆችን በእጃችን ማስገባት ችለናል። ከዚህ በተጨማሪ የአገዛዙ ስርአት የፋኖ ቤተሰብ በማለት እና በውሀ ቀጠነ ለስርአቱ አልተመቸንም የሚሉትን ንፁሀንን ከ45 በላይ እስረኞችን ማስፈታት ተችሏል።

👉በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል
የተደመሰሰ= 231በላይ/ አድማ በታኝ፣ሚኒሻ፣ ፖሊስ፣ አብረው ሲዋጉ የተገኙ የቀጠናው ባንዳዎች እና የፖሊስ አዛዡ ዋና ኢንስፔክተር ውባንተ ይረሳው እና ወንጀል መከላከል ኮማንደር ገብሬ እና በጊዜው አብረው የነበሩ የፖሊስ አባላት አና የሚኒሻ ፅ/ቤት ኃላፊ ጌታነህን ጨምሮ እስከወዲያኛው ተሰናብተዋል።
የተማረከ እጅ የሰጠ= 53
ቁስለኛ ከ67በለይ
👉 በአውደ ውጊያው የተማረከ(የተገኘ) ንብረት
ዲሽቃ= 2
ብሬን= 2
ክላሽንኮቭ= 259
አብራራው= 22
አስር ጎራሽ= 28
1 ስታር ሽጉጥ
የክላሽ ተተኳሽ= 31,000
የብሬን ተተኳሽ= 9000
የዲሽቃ ተተኳሽ= 21,000
የክላሽ ካዝና= ከ700
ወታደራዊ ኮዳ= 50
ወታደራዊ ሻንጣ= 100
ረጅም እርቀት መገናኛ ሬድዮ= 2
የአገዛዙ ሰራዊት የሚጠቀምባቸውን ሙሉ ቁሳቁስ እና 2ተሳቢ ጭነት የሚሆን ሬሽን

👉ሌላው የመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ር በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ነጋዴ ባህር ሌላ ተጨማሪ ድል አስመዝግበዋል።

የካቲት 16/2018 ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ር ከታጠቅ ብርጌድ እና ባይተኩስ ብርጌድ የተውጣጡ የፋኖ ሀይሎች በዚሁ ቀን ተጠግቶ በማደር የአገዛዙን የሚኒሻ አባላትና አድማ በታኝ በመሸገበት ሰርጎ በመግባት አዳኝ አገር ጫቆ ነጋዴ ባህር ልዩ ቦታው አቸራ በር ላይ ሲረፈርፉት አርፍደዋል።

በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል:
የተደመሰሰ= 23
የቆሰለ= 12
የተማረከ እጅ የሰጠ= 5
የተገኘ ንብረት:
ክላሽንኮቭ= 17
ብሬን= 1
የክላሽ ተተኳሽ= 1000
የብሬን ተተኳሽ= 1200

በዚህ ስአት በመየሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ስር የምትገኘው ሻሁራ ከተማ ሁሉም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ባንኮችን ጨምሮ መደበኛ ስራቸውን ፍፁም ሰላም በተሞላበት መንገድ እየሰሩ ይገኛሉ።

ሌላው ጉዳይ ከአሁን በፊት በሚድያ እንዳሳዎቅነው ለአገዛዙ ስርአት እድሜ ማራዘሚያ ሆናችሁ የምታገለግሉ የሚኒሻ አባላት፣ ፖሊስና አድማ ብተና ቀሪ ቀጠናዎችን ነፃ ለማድረግ የሚያግደን ስለሌለ አሁን ባለው የፖለቲካ አሻጥር መጠቀሚያ እንዳትሆኑና ውድ ህይወታችሁን እንዳታባክኑ አሁንም በዚሁ አጋጣሚ ወገናዊ ጥሪያችን ማስተላለፍ እንወዳለን።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ
የካቲት 18/2018
8🙏1
በቀን 19/06/2018 ዓ/ም አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ የወጠውን የምረት አዋጅ በመጠቀም ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ ።በሐሙሲት ከተማ የሚገኙት ሻለቃ 11 አባል የሆኑት የአድማ ብተና አባላት የምረት አዋጁን በመጠቀም ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር አሀድ የሆነችውን አንበሶ ብርጌድ ተቀላቀሉ።
1ኛ=ጌታየ ገልጋይ
2ኛ=ታድሎ ሁኔ
3ኛ=ብርሃኑ ተመቸው ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በመምጣት ከፋኖ ጋር አብረው ሁነው ለመታገል ወስነዋል


ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር
ህ/ግ ፍቅሩ ባየ
🙏31👍1😁1
ጉና ክፍለ ጦር ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ የህዝብ ውይይት መድረክ አካሄደ‼️
=============================
ጉና ክፍለ ጦር ከሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች መካከል ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ ከማህበረሰቡ ጋር በዛሬው ዕለት ማለትም በ20/2018 ዓ.ም የአፋብን /ሰ/አ/ቀ/ በላይ ዕዝ ም/ ፖለቲካ መምሪያ ሃላፊ አርበኛ አራገው እንዳለ፣ የአፋብን ሰ/አ/ቀ/ በላይ ዕዝ ጥናትና ስትራቴጅ መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ደራሲ አንተነህ ድረስ፣ የሜ/ጀ/ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ አመኑ አለም አንተ፣ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ኮር ጀኔራል ኃይሌ መለሰ ዘ ውባንተ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አበበ መልኬ፣ የጉና ክፍለ ጦር ስራ አስፈፃሚዎች፣ ስማዳ ሃገረ ቢዘን ብርጌድ ሰራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የወረዳው የፋኖ ጊዜያዊ መንግስት በታደሙበት የህዝብ ውይይት መድረክ ተካሂዶል።

በህዝባዊ ውይይቱም በሚከተሉት ጉዳዮች ሰፊ ውይይቶች ተደርጎባቸዋል።

✔️ የብልፅግናን ስርዓት ማፈረስና የአማራን ህዝብ ህልውና መታደግ፤
✔️ የህዝብ አስተዳደር ፍትህ ማስፈን እና የህዝብ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማስቀጠል፤
✔️ የወረዳው ህዝብ በመደራጀት ከአገዛዙ ወራሪ ሃይል ራሱን እንዲጠብቅ ፤
✔️ የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋም ሰላምና ደህንነት መጠበቅና ማሰጠበቅ፤
✔️ ጠንካራ የህዝብ አደረጃጀት በመፍጠር አካባቢችሁን ከሌባ እና ከዘራፉ ቡድን መጠበቅ ፤
እንዲሁም ሌሎች የፖለቲካ ጉዳዮች በስፋት ውይይት ሲደረግባቸው ውለዋል።

በመጨረሻም የበላይ ዕዝ እና የሜ/ጀ/ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር የፋኖ አመራሮች ከህዝቡ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ እና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ፍፁም ጨዋና ፍቅር በተላበሰ መሌኩ ተጠናቋል።
ህልውናችን በተባባረ ክንዳችን!!
አፋብን በላይ ዕዝ ሜ/ጀ/ ውባንተ አባተ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ፋኖ መምህር ያሬድ ገደፍው
3