ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሰበር የድል ዜና!!

በአለፋ ወረዳ ሻሁራ ከተማ የመሸገው የአገዛዙ ጥምር ሀይል በመደምሰስ የወረዳ ከተማዋን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር በአርበኛ ማንዴላ እያዩ እና ሌሎችም የኮርና የኮር ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ አራቱንም ክ/ጦ በማቀናጀት ካራማራ ክ/ጦ፣ አድዋ ክ/ጦ፣ኦሜድላ ክ/ጦ እና ፊውታራሪ ገበየሁ ክ/ር እንዲሁም አርበኛ ሚኒያስን ጨምሮ የካቲት 15/2018 ከቀኑ 7:00 የጀመረው እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያ 5 ስአት በወሰደ አውደ ውጊያ የአገዛዙን ጥምር ሰራዊት በመደምሰስ ከተማዋን መቆጣጠር ተችሏል። በጀግኖች መስዋትነት ከተማዋን ከመቆጣጠር ባሻገር ዲሽቃዎች፣ ብሬኖችን፣ ስናይፐሮችን፣ በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን፣ በርካታ ተተኳሾችን ፣ ተሽከርካሪዎችን፣ እና አገዛዙ የሚጠቀምባቸውን ቁሳቁሶች በቀላሉ በእጃችን ማስገባት ችለናል።

በዚህ እልህ አስጨራሽ አውደውጊያ ነበልባሎቹ የመይሳው ካሳ(፪ኛ) ከ7 በላይ ትልልቅ የቁም ምሽጎችን በመሰባበር በርካታ ቁጥር ያለው የአገዛዙን ሰራዊት አፈር ከድሜ በልቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አገዛዙ ለግል ጥቅም በግዞት የታሰሩ በርካታ እስረኞችን ማስፈታት ተችሏል። ይህ አውደ ውጊያ የተሳካ እንዲሆን አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት የጣናው ብርጌድ ወደ ቀጠናው ተጨማሪ ሀይል እንዳይኖር ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል።

አውደ ውጊያው ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ስአት ድረስ እንደ ቀጠለ ይገኛል።ከሞትና ከምርኮ የተረፈው የአገዛዙ ጥምር ሀይል ከከተማው በመውጣት ወደ ኋላ እየፈረጠጠ ፋኖ እየተከተለ ፈቃደኛ የሆነውን እየተማረከ ሰባዊ እንክብካቤ እየተደረገለት ከዚህ ውጭ የሆነውን እየተደመሰሰ ይገኛል።

በዚህ አውደ ውጊያ አገዛዙ የሚተማመንበት የድሮን ቅኝት ከምንም ሊያድነው አልቻለም፣ ከ2 ጊዜ በላይ የድሮን ሙከራ ተደርጎ ምንም ሊፈይድ አልቻለም። አሁን ላይ ግዳጃችን ስላልጨረስን የድል ዜናችን በቁጥርና በአይነት በዝርዝር የምናሳውቅ ይሆናል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር የህ/ግ
የካቲት 16/2018 ዓ.ም
2🙏1
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ከፍለ ጦር አስር አለቃ ኤፍሪም አጥናፋ ሻለቃ ልዩ ኮማንዶ ምርቃት ላይ በመገኘት ይህን መልዕክት አስተላልፈናል ።

የተከበራችሁ የአፋብን የቴዎድሮስ ዕዝ አመራሮች፤ የተከበራችሁ የቴዎድሮስ ዕዝ 105 ኮር ከፍተኛ አመራሮች፣የተከበራችሁ የቴዎድሮሰ ዕዝ 105 ኮር የ44 ከፍለ ጦር አመራሮቸ፣የተከበራቸሁ የጊዮን ሻለቃ አመራሮች እና የኤፍሬም አጥናፋ ሻለቃ አመራርና አባላት
የተከበራችሁ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ኮማንድ እጩ የሰራዊት አባላት፣
የተከበራችሁ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ክቡራት እና ክቡራን

በቅድሚያ አድካሚ የሆነውን ወታደራዊ ስልጠና በብቃት በመውሰድ እና የታለፈባቸውን ውጣ ውረዶች በማለፍ ለዚህ የምረቃ እለት የበቃችሁ እጩ የኮማንዶ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

ከሁሉ አስቀድሜ በአጭር ጊዜ ተፀንሶ ፤ ተረግዞና ተወልዶ እንዲሁም ለአቅመ አዳም እድሜ ደርሶ በህዝባችን ላይ የጭቆና ቀንበር ተጭኖ የቆየውን እድሜ ጠገብ እና ጨቋኝ ስርዓት ለመገርሰስና በምትኩ ዘመኑን የዋጀ ትውልዱን የሚመጥን ፤ እኩልነትና ፍትሐዊነትን የዓላማው አልፋና ኦሜጋው አድርጎ ትግል የተነሳው የአማራ ፋኖ ብዙ ውስብውስብ እና ፈተኝ መንገዶችን በከፍተኛ ትግስት፤ እና አርቆ እሳቢነት በመፅናት ወጥ ድርጅት በመሰረትንበት ማግስት እንዲሁም ለአማራ የድል ብርሐን በፈነጠቀበትና በተቃራኒው በጠላቶቻችን ሰፈር የጨለማ ድባብና የሽንፈት መንፈስ በተዘራበት ወቅት ላይ በመመረቃችሁ የዛሬው የእናንተ ምርቃን በአይነቱም ሆነ በይዘቱ ልዩ ስለሆነ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ።

ዛሬ ይህን ታላቅ ቀን ለመድረስ ያደረጋችሁትን ጥረት፣ ያቀረባችሁትን መስዋዕትነት፣ የተጋፈጣችሁትን ከባድ ስልጠናዎችና ውጣ ውረዶች ሁሉ ድርጅታችን በልዩ ክብር እውቅና እንሰጣለን። በሌሊት ተኝታችሁ ተነስታችሁ፣ በዝናብና በፀሐይ፣ በረሃብና በጥማት፣ በአካላዊና በአእምሮአዊ ጫና ሁሉ ተቋቁማችሁ ዛሬ የኮማንዶ ባልደረባ ማዕረግ የተቸራችሁ ሲሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ!

እናንተ ዛሬ የተመረቃችሁት የአማራ ህዝብ የነፃነት በሮች የእናት ኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት ጠባቂዎች ናችሁ።

የህዝባችን ነፃነት፤ ሰላምና ደህንነት በእጃችሁ ነው። የድንበራችን ደህንነት፣ የሀገራችን አንድነት፣ የዜጎቻችን ህይወት በእናንተ ብቃትና ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ ነው።

ዛሬ የእናንተ ቀን ነው። የብዙ ወራት አድካሚ ስልጠና፣ የማይታመን ጽናት፣ ፍርሃት የሌለበት ልብ፤ የማይሸራረፍ ግብረ ገብነት፤ የማይናወጥ ታማኝነት፤ የማያፈገፍግ ቁርጠኝነት፤ የማይታጠፍ ጀግንነት፤ የማይወላውል የዓላማ ወጥነት ፤ የማይዝረከክ ሰራዊትነት፤ በዘረኝነትና በጎጠኝነት የማይርመጠመጥ በሳልነት፤ ወዘተ ሁሉም ዛሬ በዚህ መድረክ ላይ ፍሬያቸውን አፍርተዋል።

ኮማንዶ መሆን ማለት ቀላል አይደለም። በባህሪው እና በተልእኮ ዝግጁነቱ፤ በስምሪት አሰላለፉ፤ በተግባር አፈፃፀሙ ለየት ያለ ቁመና ያለው ወታደራዊ አደረጃጀት ነው።
ኮማንዶ ማለት ለቆመለትና ለተሰለፈለት ዓላማ ውድ እና መተኪያ የሌላትን ህይወቱን ለመስጠት ዝግጁ መሆን ማለት ነው።
ኮማንዶ ማለት በጨለማ ውስጥ ብርሃን መሆን፣ በፍርሃት ውስጥ ደፍረትን መሆን፣ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ተስፋ መሆን ማለት ነው።
እናንተ ዛሬ ያንን ቃል ኪዳን ገብታችኋል። የአማራ ህዝብ ብሎም መላው ኢትዮጵያውያን ነፃነቱ ያለው በእናንተ እጅ ነው። የልጆቻችን የወደፊት ተስፋ በአጠቃላይ የአዲሱ ትውልድ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በእናንተ እጅ ነው።
ህዝባችን በአቅመ ቢሱ እና በልፍስፍሱ ስርዓት ጊዚያዊ የአፈና መዋቅር ውስጥ ሆኖ ዝም ያለ ቢመስልም እየተነፈሰ ያለው በእናንተ ሳንባ ነው። እየራበው ጠግቦ የሚያድረው በየቀኑ በሚመዘገቡ ጀብድና ድሎቻችን ነው፤ እየቆሰለ የሚያገግመው በየሰከንዱ በምናፈሳት ደምና ላባችን ነው።
እየተፅናና ያለው በእኛ ጀግንነት ነው። ተስፋ አድርጎ እና ተማምኖ እየጠበቀ የሚገኘው የእኛ የትግል ግስጋሴ ነው።

ልፍልስፍሱ የብልፅግና ስርዓት የቆመ የሚመስለው የአማራ ፋኖ የውስጥ መከፋፈልን እንደ ዋና እድል አድርጎ በመቁጠር ነበር፤ ጥንካሬውን እና ድክመቱን የሚለካው በእኛ አንድነትና መከፋፈል ነበር፤ ዛሬ የእኛ አንድነት በእሳት ተፈትኖ እንደ ወርቅ ነጥሮ ምርትና ገለባው ተለይቶ ፍንትው ብሎ ሲወጣ ምርቶ በዝቶ ገለባው አንሶ ሲያገኘው ሳይታዩ አብረው በቅለው የነበሩ ኢምንት እንክርዳዶችን ይዞ በድርድር ታርቂያለሁ እያለ ሲጮህ ህዝቡ አፉን በእጁ ይዞ እየተሳለቀባቸው ነው። የሚናገሩትን ፕሮፖጋንዳ እንኳን ለእኛ ለህፃናት የማይመጥን ነው በማለት ህዝቡ ንቀቱን እያሳያቸው ይገኛል። የቀነጨረ እና የጨነገፈ የፖለቲካ ስልትን ተጠቀምኩ እያለ አምስት የማይሞሉ እንክርዳዶች በሰሩት የባንዳነት ስራ አፍረውና ተሸማቀው ሞታችን ዛሬ ይሆን ነገ እያሉ በየጥሻው እንደ ፍልፈል ሲደበቁ ቆይተው ያገኟትን ቀዳዳ ተጠቅመው እጃቸውን ለምርኮ ፈቅደው ሲሰጡ ለብልፅግናም ለእነሱም እኩል የአፍረተቢስ ፕሮፖጋንዳን ለመጠቀም ተፍጨረጨሩ።
የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ነን ባዮች ነገሩን በውል ሳይረዱ ውሸትን እንደ ፖሊሲ የሚከተለው ብልፅግና አደናግሯቸው ከተሰጣቸው ሃላፊነት ወርደው እንክርዳዶቹ ጋር ቆመው መታየታቸው የህብረቱን ሃላፊነት ጭምር ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል።
እኛም በእዚህ አጋጣሚ ለአፍሪካ ህብረትም ሆነ ለሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የምናስተላልፈው መልእክት ስራችሁን መሬት ላይ ካለው እውነት ጋር በትክክል መስማማቱን አረጋግጡ፤ አይቶ አልቃሽ አትሁኑ ፤ የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያን እንደ ሐገር ያቆመ እና እስከ አሁን ያቆየ፤ ለመላው አፍሪካ እና የዓለም ጥቁር ህዝቦች ኩራትና የሞራል ከፍታን ያረጋገጠ ፤ የቅኝ ገዥዎች የአለም መጨረሻ እቅዳቸውን በየዘመኑ እያሳፈረ ከዚህ የደረሰ እንደ ሚስማር ሲመቱት እየጠበቀ የሚቀጥል የአድዋ ድል ባለቤት ህዝብ ነው።
ነገ የድል ጮራ ሲፈነጥቅ የአህጉሩን ጥቅሞችና መብቶችን በተመለከተ አብሮ ቆሞ የሚሟገተው የአማራ ፋኖ እንጅ አስመሳዩ ብስልፅግና ስርዓት አለመሆኑን ተረድታችሁ እውነት ላይ እንዲትቆሙ ጥሪ እናስተላልፍለን።

ስለዚህ በአራቱም የአማራ ንፍቀ ክበብ ማለትም ጎንደር፤ጎጃም ወሎና ሸዋ መላው የህዝባችንን ነፃነት ለማረጋገጥ እየተዋደቀ ከሚገኘው ታሪካዊ ሰራዊታችን ጋር ስትቀላቀሉ የእናንተን የጋለ ስሜት ለወንድሞቻችሁና ለእህቶቻችሁ ተጨማሪ ሞራል እንዲሆን አስችሉ!!!
ሁልጊዜ ብቃታችሁን አሳድጉ!!!
ሁልጊዜም ዲሲፕሊናችሁን አትተዉ!!!
ሁልጊዜም የቡድን መንፈስን ጠብቁ!!!
ሁልጊዜም ለሀገርና ለህዝብ ብቻ ታማኝ ሁኑ!!!
ሁልጊዜም በሁሉም ሁኔታ ክብርን ተጎናፀፉ!!

የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ የህዝባችን የብረት አጥሮች፣ የማትበገሩ ጀግኖች! የዛሬ ተመራቂ ልዩ ኮማንዶ አባላት በሙሉ እንኳን ለዚህ ታሪካዊ የምረቃ ቀን አደረሳችሁ።
በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ።
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!!

የካቲት 14/06/2018ዓ/ም
4
የሜጀር ጄኔራል ውባንተ 1ኛ ኮር ጣና ገላዲዎስ ክፍለ ጦር የማረካቸው አድማ በታኞች ናቸው።
👍3🙏2
የአቢይ አሕመድ አገዛዝ ከኤርትራ ጋር ለማደርገው ጦርነት የዓማራ ክልል በሎጀስቲክ ከጎኑ እንዲሰለፍ ያወጣው ዕቅድ ከዓምሐራ ፋኖ እጅ ገብቷል።


የአቢይ አሕመድ አገዛዝ በነአረጋ ከበደ(ቀንድ አውጣ) በኩል ከአምሐራ ሕዝብ ጥሬ ገንዘብ እና የእህል ዓይነቶች ተሰብስበው ወደ ኦሕዴድ ብልጽግና ገቢ ይደረግልኝ ሲል ጠይቋል

የዓምሐራን ሕዝብ ከመጋቢት 24/2018ዓ.ም ጀምሮ የጥፋት አዋጅ አውጆ በጅምላ እየገደለህ፣ በጅምላ እያፈናቀለህ፣ በጅምላ እየዘረፈህ ከተሞችህን ፣ በጅምላ እያወደመ፣ የአሣምነው ፅጌ ተቋም የሆነው ዓምሐራ ልዩ ኃይልን በብጣሽ ወረቀት አፍርሶብህ፣ ትናንት በጁንታው ጦርነት በሽህ የሚቆጠሩ ልጆችህን ካሥጨረሰ በኋላ መጠቀሚያ አድርጎ ጥሎህ፣ የአምሐራ ሕዝብ የትግል ጽንሥ የሆኑ የአምሐራ ርሥቶችን እንደ ድሬዳዋና አዲሥ አበባ ቀምቶህ፣ ቤተ ዕምነቶችህን አውድሞብህ፣ መዋቅራዊ ጥቃት እየፈጸመብህ፣ በዓለም ሕዝብ የተጠላህ እንድትሆን እየሰራብህ፣ አለ የተባለውን የአየር ጥቃት በንጹሐን ነዋሪዎች ላይ የድሮን ቦምብ እንደዝናብ እያወረደብህ፣ አርሶ አደርህ ማዳበሪያ ተከልክሎ እንዲደኸይ እየተሰራብህ እና በጥቅሉ ጅምላ ዘር ማጥፋት በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ የሚገኘው አውሬው የኦሕዴድ ብልጽግና ዛሬም ዓይናችኹን ጨፍኑና ላሞኛችኹ ሢል በአማራ ብልጽግና በአረጋ ከበደ በኩል ተከሥቷል።

ትንንት ነገደልኳችኹ ሥላልበቃኝና ከኤርትራ ጋር ለማደርገው ጦርነት ገንዘብም እሕል በዓይነትም አውጡልኝ ብሏል በአማራ ብልጽግና በኩል። መሞቻችሁን ተተኳሽም ሆነ ሎጀሥቲክ የምታቀርቡት እናንተ ናችኹ ሲል የከተማና የገጠር ነዋሪዎች የተጠየቁትን እንዲያወጡ አዝዟል።

አውሬው የኦሕዴድ አገዛዝ የአማራ ክልልን ህዝብ የሚያደቅቅበት አዲስ ዕቅድ ተፈጻሚነቱ በአማራ ብልጽግና እንደሆነ አዝዟል። ይኸም ከኤርትራ ጋር ጦርነት ልገጥም ስለሆን ለጦርነቱ ተተኳሽ መግዥያ የሚሆን እና ለወታደሩ ቀለብ መሰብሰብ ያለበት ከህዝቡ ነው በማለት በብርና በአይነት አቅዶ አውርዷል። እነ አረጋ ከበደ ዕቅዱ በዝቷል የሚል ጥያቄ አቅርበው የነበር ቢሆንም ሰሚ ባያገኙም በቀምጫያቸው አቢይ ሸኔ በቀጥታ ወደስራ እንዲገቡ ብቻ ነው የታዘዙት።

ኦሕዴድ ብልጽግና ከዓማራ ክልል በነአረጋ ከበደ በኩል እንዲሰበሰብ ያዘዘው፦
በብር ቢያንስ ሶስት ቢሌን ስምንት መቶ ሀያ አምስት ሚሌን(3,825,000,000) ብር እንዲሰበስቡ ይህን ብር ለመሙላት፦
👉ከሁሉም መንግስት ሰራተኛ=2000ብር
👉ከከተማ ኗሪ ከእያንዳንዱ=400ብር
👉ከአርሶ አደር ከእያንዳንዱ=300ብር
👉ከዝቅተኛ ነጋዴ=1000ብር
👉ከተሻለ ነጋዴ ዝቅተኛ=10000ብር
እንዲሰበሰብ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በዓይነት ሁለት መቶ ዘጠና ስድስት ሽ ሶስት መቶ ሀያ (296,320)ኩንታል በዝርዝር ተቀምጧል።
ቦለቄ፣ሩዝ፣በቆሎ፣ገብስ፣ስንዴ፣ሽንብራ፣ባቄላ፣አተር፣ምስር፣በሶ፣የደረቀ እንጀራ፣ቆሎ፣ዳቦ ቆሎ፣መኮረኒ እና ሌሎች የፋብሪካ ውጤቶች የኤርትራ ጦርነት ተጀመረም አልተጀመረም ሰብስቦ ያስረክባል።የአማራ ክልል አመራር የቀጣይ ስራው የድሀ ቤት እየቆፈቆፈ ብር አምጡ፣ ዱቄት አምጡ ምስርም ይቻላል እያለ የኔ ቢጣ ሁኖ የመሪነት ክብር እንዳይኖረው ያደርገዋል።


ለመላው የዓምሐራ ሕዝብና ለአቢይ ሸኔ አማሮች የሚተላለፍ መልዕክት፦
ለአምሐራ ሕዝብ ገዳይ አገዛዝ ተላላኪ የሆንክ የሥርዓቱ አገልጋይ በየትኛውም መንገድ ተባባሪና አሥፈጻሚ ሆነህ ብትገኝ ለሚደርሥብህ ጉዳት ዓምሐራ ፋኖ ኃላፊነት አይወሥድም። በምድር ላይ እንዳትኖር የተፈረደብህ የዓምሐራ ሕዝብ ደግሞ አገዛዙ የሚላችሁን ሳይሆን መሬት ላይ ያለውን ዕውነታ ተረድታችሁ፣ በቅርቡ ዋጋ የከፈላችኹበትን የወልቃይትና የራያ ርሥትህን እንዴት ኦሕዴድ ብልጽግና እንደቀማችኹ ተረድታችኹ፣ አሁናዊ የዓምሐራ ሕዝብን የባርነት ሕይወት ተመልክታችኹ አገዛዙ ለሚያቀርብላችኹ ተጠየቅ ምላሻችኹ ሕዝባዊ አቢዮት እንደሆነ ማሣየት አለባችሁ። ዓምሐራው ባርነትን በቃኝ ሲል ትግሉን ሕዝባዊ በማድረግና በአንድ ዓምሐራነት በመቆም ፋሽሥቱን የኦሕዴድ ብልጽግና አገዛዝ ከነግሳንግሱ ወደ ኤርታ-ኣሌ እሣተ ገሞራ መወርወር አለበት።


ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔐👊
፩.ዓምሐራ🔐

አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
🔥51💔1
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
[ የካቲት 17/2018ዓ.ም]

የአቢይ አሕመድ ጥምር አራዊት ሰራዊትን ከደብረ ታቦር ከተማ በቅርብ ርቀት ከፀጉር ኪዳነ ምሕረት እሥከ ኮካ፣ ከቆለይ እሥከ ዓለም ሳጋ፣ ከእንቁርቁባ እሥከ ተንሸራታች ድረሥ በደምብ ገርፈውታል።

ውጊያው ከመጀመሩ ጠላት የዓምሐራ ፋኖን ክንድ መቋቋም ተሥኖት አድማ ብተናዎች ተደምሥሠዋል፣ ተማርከዋል፣ ትራፊክ ፖሊሥ እሥከ ወድያኛው ተሸኝቷል፣ ሚሊሺያ ተሸኝቷል፣ የአቢይ መከላከያ ተማርኳል ተደምስሷል።


ጠላት የመዋጋት ሞራሉ ደቅቆ እየተንጠባጠበ ወደ ደብረ ታቦር ከተማ እየፈረጠጠ ይገኛል።


ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን🔑
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑
፩ ዓምሐራ🔑

አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል

ፋኖ ኃቅ-ዓለው ፀጋ አለባቸው
🙏2
ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር እና ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር በጥምረት ጠላት ላይ ድል ተቀዳጁ::

ዛሬ የካቲት 16/2018 ዓ/ም በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ስሪንቃ ቀበሌ መነሻውን ወልድያ ከተማ ያደረገ ጠላት ከሌሊቱ 8:00 ጀምሮ ፋኖ ወዳለበት ቀጠና ማጥቃት ሞክሮ ከፍተኛ ካሳራ ደርሶበት ተመልሷል።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር እንዲሁም ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በተጠቀሰው ቀን ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው ወደመጣበት ወልድያ ከተማ መልሰውታል።

በተጋድሎው ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ እየተደረገ እስከ ማታ 11:00 የዋለ ሲሆን በውጊያው ከባድ ኪሳራ ያስተናገደው ጠላት ከባድ መሳሪያ በመወርወር በንብረትና በሰው ሂወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ሞርተር በማስወንጨፍ የማህበረሰቡን ደን ከማቃጠሉም በተጨማሪ ከግለሰብ ቤት ላይ በመወርወር አንድ የቤተሰብ አባል ሙሉ ከባድ ቁስለኛ አድርጎ የተለመደውን ህዝብ የመጨፍጨፍ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 16/2018 ዓ.ም
2🙏1
የራያ ቆቦ ወርቄ የብልፅግና ታጣቂዎች ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ሁለት ንፁሃኖችን ጎብየ ከተማ ላይ በግፍ ረሸኑ::

የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው የኦሮሞ ብልፅግና ጋር አብረውና ወግነው የተሰለፉት የአድማ ብተና ሚሊሻና ፖሊስ ታጣቂዎች ፋኖን መዋጋት ስለማይችሉ በዋናነት ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎችን ባደባባይ እየረሸኑ ይገኛሉ:: ባለፉት ጊዜያትም በርካታ ንፁሃኖች ላይ ግፍ እንደተፈፀመ ይታወቃል::

ባለፉት ሶስት አመታቶች አማራን ህዝብ ህልውና ለማስከበር ከብልፅግናው አገዛዝ ጋር ብርቱ ተጋድሎ እያደረገ ካለው ፋኖ በተቃራኒ ተሰልፈው ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ በርካታ ንፁሃን አማራዎችን በግፍ እየረሸኑ በቀድሞው ምስራቅ አማራ ፋኖ በአሁኑ ምኒልክ ዕዝ ለህዝብ ሲባል በፍፁም ትግስት በዝምታ እየታለፉ ያሉ ሲሆን ዛሬም ለዋናው አላማ ሲባል ፋኖ ጉዳዩን ለጊዜ ቢታገሳቸውም ይሄንን ወደ ጎን በማለት የተለመደ ድርጊታቸውን በማስቀጠል ራያ ቆቦ ወረዳ ጎብየ ከተማ በመግባት ነጋ ሰለሞን የተባለ የ18 አመት ታዳጊ እና ሃይለማርያም ሞላ የተባለ የ20 አመት ወጣት የካቲት 15/2018 ዓ.ም ምሽት 1:30 ላይ በግፍ ረሽነዋል::

እነዚህ ለሃገርና ለህዝብ የማይበጅ አላማ ያነገቡ የአካባቢውን ማህበረሰብም የማይወክሉ የራያ ወርቄ የብልፅግና ሚሊሻዎች አገዛዙ የሰጣቸውን ድርብርብ አላማ ያለው ተልዕኮ አንግበው ወደ ጎብየ ከተማ በመግባት ሁለቱን ወጣቶች በግፍ ረሽነው ወጥተዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
3
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
[ የካቲት 17/2018ዓ.ም]

የአቢይ አሕመድ ጥምር አራዊት ሰራዊትን ከደብረ ታቦር ከተማ በቅርብ ርቀት ከፀጉር ኪዳነ ምሕረት እሥከ ኮካ፣ ከቆለይ እሥከ ዓለም ሳጋ፣ ከእንቁርቁባ እሥከ ተንሸራታች ድረሥ በደምብ ገርፈውታል።

ውጊያው ከመጀመሩ ጠላት የዓምሐራ ፋኖን ክንድ መቋቋም ተሥኖት አድማ ብተናዎች ተደምሥሠዋል፣ ተማርከዋል፣ ትራፊክ ፖሊሥ እሥከ ወድያኛው ተሸኝቷል፣ ሚሊሺያ ተሸኝቷል፣ የአቢይ መከላከያ ተማርኳል ተደምስሷል።

ጠላት የመዋጋት ሞራሉ ደቅቆ እየተንጠባጠበ ወደ ደብረ ታቦር ከተማ እየፈረጠጠ ይገኛል። ብርቱ ምት ከዓምሐራ ፋኖ የገጠመው አራዊት ሰራዊትም በበቀልና በአጥፊነት ግብሩ 03 ንጹሐን የከተማው ነዋሪዎችን በጭካኔ በጥይት መትቷቸዋል። የተመቱት ንጹሐን 02ቱ ሴቶች ሲሆኑ 01ዱ ደግሞ ወንድ ነው።

ተሥፋ የቆረጠ አገዛዝ ከዚህ የበለጠ ጭካኔውን በንጹሐን ላይ እንደሚያሳርፍ ሕዝቡ አውቆ አውሬውን አገዛዝ ወግድ ማለት ምርጫው ሳይሆን ግዴታው ነው።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን🔑
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑
፩ ዓምሐራ🔑

አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅ-ዓለው ፀጋ አለባቸው

ቋሚ ምሥል፦ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር ሥራ አሥፈጻሚ በከፊል
👍41🙏1
ከአቢይ አሕመድ መከላከያ ላይ በዓለም ሳጋ ምድር በውባንተ አባተ ልጆች ከተራራ የገዘፈ ደማቅ ድል ተመዝግቧል።

ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር
የክፍለጦሩ ቃኝና መሐንዲሥ
አሣምነው ብርጌድ

ጉና ክፍለ ጦር
ገብረ መሥቀል ብርጌድ/ታቦር ሻለቃ
የክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚ

የካቲት 18/2018ዓ.ም

እጅግ አሥደማሚ ድል በውቤ ልጆች ተገኝቷል። ከባሕር ዳርና ከደብረ ታቦር የመጣው መከላከያ ድቅቅ ብሎ ተመትቷል። ከ20+ የመከላከያ ተሽከርካሪ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በ03 ዓመታት ትግላችን የዛሬውን ጣፋጭ ድል የሚተካከል የለም።

ከትናንቱ ምት የተረፈው አዳሩን ሙሉ አማራ በታኙ ፈርሶ እንዳደረ ልብ ይሏል። 31 አማራ በታኞች አዳራቸውን ወደው ሳይሆን ተገድደው ዓምሐራ ፋኖን ተቀላቅለዋል።

ክብርና ምሥጋና ለሜጀር ጀነራል ውብ-አንተ አባተ አብራኮች

ዝርዝሩን እናደርሳለን።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑

አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው።
🙏6