ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሰበር ዜና
የ4ኛ ደጃዝማች ኮር በተለያዩ ቦታዎች ጠላትን ደመሰሰ

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ 4ኛ ደጃዝማች ኮር በቀን 10/6/2018 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰዓት አካባቢ በጠገዴ ወረዳ ማክሰኝት ቀበሌ ልዪ ቦታዉ ሸንበቆ ጎጥ ከጎንደር ወደ ዳንሻ ሲጓዝ በነበረ ጠላት የተከዜ ክፋለ ጦር ታድሎ ብርጌድና የኮሩ ተወርዋሪ ሃይል ዉስጥ ጥቅምት 30 ማይካድራ ብርጌ በጥምረት በተወሰደ እርምጃ ከ3 በላይ ሲሞት 5 ቆስሏል።

በቀን 11/6/2018 ዓ.ም ጠላት ከሶረቃ ተነስቶ ወደ ጎንደር በተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓዝ በደጸጣ በፋኖ ከፋተኛ እርምጃ ተወስዶበታል።
ታድሎ ብርጌድ እና ጥቅምት 30 ማይካድራ ብርጌድ በዚህ በነበረዉ የደፈጣ ዉጊያ ከ7 በላይ የሞተ ሲሆን 8ቁስለኛ አሸሬ ጤና ጣቢያ የገባ ሲሆን ወራሪዉ ሲጓዝበት የነበረዉ ተሽከርካሪዉ በደረሰበት ከባድ ምት ተገልብጧለ።

በቀን 12/6/2018 ዓ.ም በመተማ ወረዳ ሸመለጋራ ቀበሌ በአዲስ አለምና በቁጥር 1 መካከል ጠላት ከመተማ ወደ ምድረ ገነት ሲጓዝ ከአርበኞች ክፋለ ጦር ከጣናዉ ዋሴ ክፍለ ጦር እና ጎቤ ክፍለ ጦር የተዉጣጣ ሃይል ከጧቱ ሁለት ሰዓት የተጀመረዉ እስከ 9 ሰዓት በቆየዉ ዉጊያ በቅጀታሙ ሰራዊት ላይ ከፋተኛ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል።

በዚህ ግብስብስ ሰራዊት ላይ በፋኖ የደረሰበት ምት መቋቋም ያቃተዉ 2 ዙ23 አምጥቶ በአካባቢዉ ያሉ ተራሮችን ሲያሰቃይና ሲደበድብ ዉሏል በዚህ በነበረዉ ዉጊያ ከ20 በላይ ሙት እና ቁስል ሁኗል ።

## በተባበረ ክንዳችን ነፃነታችን እናረጋግጣለን
# ድል ለአማራ ህዝብ
# ድል ለአማራ ፋኖ

ባንዴራዉ ግርማይ ህዝብ ግንኙነት
1🙏1
ለንደን የሚኖሩ አማራዎች እና የአማራ ትግል ደጋፊዎች ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ለሚጨፈጨፉት የአማራ ወገኖቻችን ድምፅ አሰምተዋል።
👍3
የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አቡልታ ቀበሌ ህዝባዊ ውይይቶችን እያካሄደ ነው።

በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አቡልታ ቀበሌ ህዝባዊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱ ላይ የአማራ ህዝብ ከጉሙዝ ማህበረሰብ ጋር ለዘመናት አብሮ የኖረ ስለመሆኑ በመድረኩ ተነስቷል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፋት ነዋሪወች የብልፅግና አገዛዝ በፈጠረው ሰው ሰራሽ ችግር ምክንያት የመተከል ቀጠና የህዝብ እልቂት መፈልፈያ ሆኖ መቆየቱ እንዲሁም ይህ ጉዳይ በትክክለኛው ግዜ ባለመቋጨቱ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ስንከፍል ቆይተናል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። እንዲሁም ሁለቱም ወገኖች ከሃብት ንብረታቸው ሲፈናቀሉና ውድ የሆነው የሰው ህይወት ሲጠፋ አይተናል፣ ስለሆነም ከዚህ በኃላ የአማራ ህዝብና የጉሙዝ ማህበረሰብን ጨምሮ በአካባቢው የሚኖረው ህዝብ በአብሮነት በጋራ የመኖር እሴቱን ማስቀጠል ይገባል በማለት አንስተዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙ የማህበረሰብ ተወካዮች በአገዛዙ ሴራ ተፈጥሮ የቆየው ግጭት እንዲቆም እና ሠላም እንዲሰፍን የሁሉም ማህበረሰብ ጉዳይ መሆን እንዳለበት በማመን በአካባቢው የሚኖረው ህዝብ በሙሉ የተፈጠረውን የአንድነት መንፈስ ለመጠበቅ በጋራ በንቃት እንሰራለን ብለዋል።

ውይይቱን በጋራ የመሩት የአፋብን ቴወድሮስ እዝ እና ጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አመራሮችም ለህዝቦች አንድነት በጋራ እንደሚሰሩ ጠቅሰው በየትኛውም ቦታ ተዘዋውሮ ስለመስራት፣ አርሶ እና ነግዶ ለመኖር እንዲሁም ማንኛውንም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ አገዛዙን በጋራ ታግሎ ማስወገድ እና በምትኩ ህዝባዊ መንግስት መመስረት እንደሚያስፈልግ በትኩረት አንስተዋል።

በመተከል አካባባቢ ተመሳሳይ ተግባራትን በማከናወን አካባቢውን የሰላም ቀጠና በማድረግ ህዝባችን ማህበረ-ፖለቲካዊ እንቅስቃሴውን በዘላቂነት እንዲከውን ለማድረግ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
🙏31
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና በአውደ ውጊያ አይሳካለት ሲል ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃኖችን ኢላማ ያደረገ የከባድ መሳሪያ ድብደባ እየፈፀመ ቀጥሏል::

የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ 08 ቀበሌ ልዩ ስሙ ጣምሬ የተባለ ቦታ ላይ ተደጋጋሚ የመድፍና የሞርተር 120 mm ድብደባ በመፈፀም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል:: በዚህም በተጠቀሰው የመቅደላ ወረዳ በተንቀሳቃሽ ምስል በሚታየው መልኩ ህዝብ በብዛት ወደሚኖርበት ቀበሌ ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍ ጉዳት አድርሷል::

በዚህም ፋሽስቱ አገዛዝ የአብይ አህመዱ ብልፅግና ሰራዊቱ በአውደ ውጊያ የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው የከባድ መሳሪያ ሽፋንና ድጋፍ በሚያገኝበት ሁኔታ በአስተኳሽቹ በኩል ወደ ገጠር መንደሮችና ታዳጊ የገጠር ከተሞች ጭምር በተደጋጋሚ እንዲወነጨፍ በማድረግ የንፁሃኖችን ህይወት በጅምላ እየቀጠፈና አካል እያጎደለ እንስሳቶችንም እያስጨፈጨፈ ቤትና ንብረትም እያወደመ ይገኛል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 13/2018 ዓ.ም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የበላይ ዕዝ አመራሮች አስቸጋሪ መልካምድሮችን ራብና ጥም ብርድና ውችንፍር ተቋቁሞ ጠላትን እየተዋጋና እያዋጋ በትጋት ተልዕኮውን እየተወጣ ይገኛል።

የህዝብ ትግል አደራ በላብና በደም ዋጋ ይጠበቃል!!

ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
🙏9
አፋብን| ቴዎድሮስ ዕዝ
_______፩
የካቲት 14/2018 ዓ/ም የምህርት አዋጁን የተቀበሉ የአገዛዙ የአድማ ብተና አባላት ዛሬም እንደትናንቱ ከጠላት ካፕ በመኮብለል 105ኛ ኮር የ55ኛ ክ/ጦር የፋኖ አባላትን እየተቀላቀሉ ነው።
የምህረት አዋጁን የተቀበሉ አባላት፦

1ኛ ረዳት ሳጅን ሀብቴ ላቀው
2ኛ ኮንስታብል ወርቅየ አበበ
3ኛ ኮንስታብል ሰኢድ ሁሴን የተባሉ የአድማ ብተና አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ሻውራ አካባቢ ከሚንቀሳቀሰው የጠላት ሀይል በመውጣት የ105ኛ ኮር የ55ኛ ክ/ጦር የፋኖ አባላት ተቀላቅለዋል።

_____፪
የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም የቆመውና በቋሪት ወረዳ የመሸገው 76ኛ ክፍለ-ጦር አባላት የነበሩ ሦስት ሚሊሻዎች፣ የአገዛዙን ሰንሰለት በመበጠስ ትጥቃቸውን ሙሉ በሙሉ ይዘው የዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄን (አፋብን) በክብር ተቀላቅለዋል።

1.እንዳላማው ድረስ
2. የቻለ በለጠ እና
3. ስሜነህ ታፈረ የተባሉ የሚሊሻ አባላት 102ኛ ኮር 33ኛ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል።
የምህረት አዋጁ አማራን የሚባል ሕዝብ ለማዳን ነውና ሁሉም ሊጠቀምበት ይገባል። አማራ እርስበርሱ መጋደል የለበትም ሊጠፋ የተፈረደበት ሕዝብ ልጆችነንና ኑ ተቀላቀሉን።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 14/2018 ዓ.ም
👍2
የአደረጃጀት/የሪፎርም ዜና

አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር አድዋ ክ/ጦ ለ7 ቀናት ያክል ከቀጠናው የዕዙ ግብረ-ሀይል ማለትም አርበኛ ዮሀንስ ንጉሱ፣ አርበኛ ስጦታው ዳኛው(ባሻ)፣ አርበኛ ታደሰ ወርቁ ፣አርበኛ መቶ አለቃ ቢራራ፣ አርበኛ ኢንጅነር በየነ አለማው፣ አርበኛ ሚኒያስ አለማየሁ፤ ከኮሩ ከፍተኛ አመራር ጋር በመሆን ጥልቅ ግምገማና ውይይት በማድረግ፣ የስራ ተግዳሮቶችን እና መልካም አጋጣሚዎችን በመለየት ለቀጣይ ክ/ጦሯን በሁሉም ዘርፍ ሁለንተናዊ የድርጅት መርህን በተከተለ መልኩ ስራዎችን ተደራሽ ማድረግና ለውጤት መታተር እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል።ከዚህ በተጨማሪ በማንኛውም አይነት የስራ ዘርፍ መርህን ባማከለ መልኩ በኃላፊነት ተግባራትን ከመከዎን ባሻገር በመርህ እዝ እና ሰንሰለትን ጠብቆ መልካም የስራ ውጤቶችን እውቅና መስጠት እንደሚገባ ሁሉ መጠየቅም እንዳለ በአፅኖት ተገልጿል ተፈፃሚም ሆኗል።

በዚህ ጥልቅ ግምገማ የአድዋ ክ/ጦ መልካም ስራዎችንና ተሞክሮዎችን በማድነቅ እንዲሁም እውቅና በመስጠት አድናቆትን ያገኙ ሲሆን በሁለንተናዊው የስራ ዘርፍ ተግዳሮት ሆነው የማያሰሩ እንቅፋቶችን በመለየት የቀጣይ ድርጅታዊ አቅጣጫ በማስቀመጥ ችሎታንና አቅምን ባማከለ እና ለተሻለ ግዳጅ በሚያመች መልኩ የመሪዎች ሪፎርም ሊሰራ ችሏል። ከዚህ በተጨማሪ የአድዋ ክ/ር ካሉት ብርጌዶች መካከል በሁለቱ ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ የብርጌድ ሪፎርም በተሳካ ሁኔታ መስራት ተችሏል።

👉የክ/ር ሪፎርም:
1. የክ/ር ወታደራዊ ዋና አዛዥ.....................አርበኛ ተመስገን ወለላው
2. ም/ወ/አዛዥ.................................አርበኛ ገብረማርያም በየነ
3. የክ/ር ዘመቻ................................አርበኛ ጌጤ ደሳለኝ
4. የክ/ር ም/ዘመቻ............................አርበኛ ቻሌ መኩ
5. የክ/ሩ ልዩ ኦፕሬሽን ኃላፊ..................አርበኛ ገበያው አቤ
6. የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ......................አርበኛ ተስፋ ጌታሁን
7.የፅ/ቤት ኃላፊ.............................አርበኛ ጌታቸው ማንደፍሮ
8. የህ/ግንኙነት ኃላፊ.....................አርበኛ ዳንኤል አቡሀይ
9.ህዝብ አስተዳደር.........................አርበኛ አዳም ውበት
10.አደረጃጀት...................................አርበኛ ተዋቸው አንመው
11. የሰው ሀይል አስተዳደር................አርበኛ ኤፍሬም መዝገቡ
12. ሎጀስቲክ..................................አርበኛ ሀብታሙ ደምለው
13.ትምህርትና ስልጠና.......................አርበኛ ብርሌው አበባው
14.ፋይናንስ........................................አርበኛ አየሁ አለሙ

👉የብርጌድ ሪፎርም:
1ኛ.የንጋት ጮራ ብርጌድ
አርበኛ መኳንንት አንዳርጌ.........ዋና ብርጌድ መሪ
አርበኛ ምረቴ አወቀ....................ምክትል ብርጌድ መሪ
አርበኛ እሸቴ ይስማው.................የብርጌድ ዘመቻ
👉የነብሮ ብርጌድ ሪፎርም
አርበኛ መኳንንት ተገኘ.................ዋና ብርጌድ መሪ
አርበኛ ፍቅሩ ..................ምክትል ብርጌድ መሪ
አርበኛ ደሴ ባየ............................የብርጌድ ዘመቻ

የተሰራውን የመሪዎች ሪፎርም ሁሉም የሰራዊት አባላት በሙሉ ድምፅ ከማፅደቃቸው በተጨማሪ ሁሉም የክ/ጦ አመራሮች በሰራዊቱ ፊት እንዲሁም የአፋብን ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ሳሙኤል ባለድል፣ የዕዙና የኮር አመራር ባሉበት በታማኝነት፣ በፍታዊነት፣ በቅንነት፣ እዝ እና ሰንሰለትን በመጠበቅ ከትናንት ተግዳሮቶቻችን ተምረን፣ ጠንካራ ጎኖቻችን የበለጠ አጠንክረን በተሻለ የስራ አፈፃፀም የአማራን የህልውና ትግል አሸናፊ ሆኖ የድል ችቦ ለማብራት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል አማራዊ ግዴታችን እንወጣለን ሲሉ ቃል ኪዳን ገብተዋል።

በመጨረሻም የዕዝ ግብረሀይሉና የኮሩ አመራር የአድዋን ክ/ጦ አመራሮች በጋራ በመሆን ድርጅታዊ መርህንና አሰራርን ተከትሎ መስራት፣ በየዘርፉ በተጠያቂነትና በኃላፊነት ስራዎችን መከወን፣ በግምገማ ተግዳሮቶችን መለየትና አቅጣጫ ማስቀመጥ፣ የተሻለ የስራ አፈፃፀምን ማስቀጠልና ለታሪክ መሰነድ እንደሚገባ በጋራ መክረዋል። ለቀጣይ የስራ ጉድለቶችን በስልጠና ማስተካከልና በዕውቀት ማማ ስር ሆኖ ትግሉን በፍጥነት ተሻጋሪ እንዲሆን ከማድረግ አንፃር አፅኖት የተሰጠው ጉዳይ ሆኗል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ
የካቲት 14/2018
👍21🙏1