ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሰበር ዜና
የ4ኛ ደጃዝማች ኮር በተለያዩ ቦታዎች ጠላትን ደመሰሰ

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ 4ኛ ደጃዝማች ኮር በቀን 10/6/2018 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰዓት አካባቢ በጠገዴ ወረዳ ማክሰኝት ቀበሌ ልዪ ቦታዉ ሸንበቆ ጎጥ ከጎንደር ወደ ዳንሻ ሲጓዝ በነበረ ጠላት የተከዜ ክፋለ ጦር ታድሎ ብርጌድና የኮሩ ተወርዋሪ ሃይል ዉስጥ ጥቅምት 30 ማይካድራ ብርጌ በጥምረት በተወሰደ እርምጃ ከ3 በላይ ሲሞት 5 ቆስሏል።

በቀን 11/6/2018 ዓ.ም ጠላት ከሶረቃ ተነስቶ ወደ ጎንደር በተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓዝ በደጸጣ በፋኖ ከፋተኛ እርምጃ ተወስዶበታል።
ታድሎ ብርጌድ እና ጥቅምት 30 ማይካድራ ብርጌድ በዚህ በነበረዉ የደፈጣ ዉጊያ ከ7 በላይ የሞተ ሲሆን 8ቁስለኛ አሸሬ ጤና ጣቢያ የገባ ሲሆን ወራሪዉ ሲጓዝበት የነበረዉ ተሽከርካሪዉ በደረሰበት ከባድ ምት ተገልብጧለ።

በቀን 12/6/2018 ዓ.ም በመተማ ወረዳ ሸመለጋራ ቀበሌ በአዲስ አለምና በቁጥር 1 መካከል ጠላት ከመተማ ወደ ምድረ ገነት ሲጓዝ ከአርበኞች ክፋለ ጦር ከጣናዉ ዋሴ ክፍለ ጦር እና ጎቤ ክፍለ ጦር የተዉጣጣ ሃይል ከጧቱ ሁለት ሰዓት የተጀመረዉ እስከ 9 ሰዓት በቆየዉ ዉጊያ በቅጀታሙ ሰራዊት ላይ ከፋተኛ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል።

በዚህ ግብስብስ ሰራዊት ላይ በፋኖ የደረሰበት ምት መቋቋም ያቃተዉ 2 ዙ23 አምጥቶ በአካባቢዉ ያሉ ተራሮችን ሲያሰቃይና ሲደበድብ ዉሏል በዚህ በነበረዉ ዉጊያ ከ20 በላይ ሙት እና ቁስል ሁኗል ።

## በተባበረ ክንዳችን ነፃነታችን እናረጋግጣለን
# ድል ለአማራ ህዝብ
# ድል ለአማራ ፋኖ

ባንዴራዉ ግርማይ ህዝብ ግንኙነት
1🙏1
ለንደን የሚኖሩ አማራዎች እና የአማራ ትግል ደጋፊዎች ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ለሚጨፈጨፉት የአማራ ወገኖቻችን ድምፅ አሰምተዋል።
👍3
የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አቡልታ ቀበሌ ህዝባዊ ውይይቶችን እያካሄደ ነው።

በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አቡልታ ቀበሌ ህዝባዊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱ ላይ የአማራ ህዝብ ከጉሙዝ ማህበረሰብ ጋር ለዘመናት አብሮ የኖረ ስለመሆኑ በመድረኩ ተነስቷል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፋት ነዋሪወች የብልፅግና አገዛዝ በፈጠረው ሰው ሰራሽ ችግር ምክንያት የመተከል ቀጠና የህዝብ እልቂት መፈልፈያ ሆኖ መቆየቱ እንዲሁም ይህ ጉዳይ በትክክለኛው ግዜ ባለመቋጨቱ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ስንከፍል ቆይተናል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። እንዲሁም ሁለቱም ወገኖች ከሃብት ንብረታቸው ሲፈናቀሉና ውድ የሆነው የሰው ህይወት ሲጠፋ አይተናል፣ ስለሆነም ከዚህ በኃላ የአማራ ህዝብና የጉሙዝ ማህበረሰብን ጨምሮ በአካባቢው የሚኖረው ህዝብ በአብሮነት በጋራ የመኖር እሴቱን ማስቀጠል ይገባል በማለት አንስተዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙ የማህበረሰብ ተወካዮች በአገዛዙ ሴራ ተፈጥሮ የቆየው ግጭት እንዲቆም እና ሠላም እንዲሰፍን የሁሉም ማህበረሰብ ጉዳይ መሆን እንዳለበት በማመን በአካባቢው የሚኖረው ህዝብ በሙሉ የተፈጠረውን የአንድነት መንፈስ ለመጠበቅ በጋራ በንቃት እንሰራለን ብለዋል።

ውይይቱን በጋራ የመሩት የአፋብን ቴወድሮስ እዝ እና ጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አመራሮችም ለህዝቦች አንድነት በጋራ እንደሚሰሩ ጠቅሰው በየትኛውም ቦታ ተዘዋውሮ ስለመስራት፣ አርሶ እና ነግዶ ለመኖር እንዲሁም ማንኛውንም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ አገዛዙን በጋራ ታግሎ ማስወገድ እና በምትኩ ህዝባዊ መንግስት መመስረት እንደሚያስፈልግ በትኩረት አንስተዋል።

በመተከል አካባባቢ ተመሳሳይ ተግባራትን በማከናወን አካባቢውን የሰላም ቀጠና በማድረግ ህዝባችን ማህበረ-ፖለቲካዊ እንቅስቃሴውን በዘላቂነት እንዲከውን ለማድረግ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
🙏31
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና በአውደ ውጊያ አይሳካለት ሲል ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃኖችን ኢላማ ያደረገ የከባድ መሳሪያ ድብደባ እየፈፀመ ቀጥሏል::

የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ 08 ቀበሌ ልዩ ስሙ ጣምሬ የተባለ ቦታ ላይ ተደጋጋሚ የመድፍና የሞርተር 120 mm ድብደባ በመፈፀም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል:: በዚህም በተጠቀሰው የመቅደላ ወረዳ በተንቀሳቃሽ ምስል በሚታየው መልኩ ህዝብ በብዛት ወደሚኖርበት ቀበሌ ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍ ጉዳት አድርሷል::

በዚህም ፋሽስቱ አገዛዝ የአብይ አህመዱ ብልፅግና ሰራዊቱ በአውደ ውጊያ የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው የከባድ መሳሪያ ሽፋንና ድጋፍ በሚያገኝበት ሁኔታ በአስተኳሽቹ በኩል ወደ ገጠር መንደሮችና ታዳጊ የገጠር ከተሞች ጭምር በተደጋጋሚ እንዲወነጨፍ በማድረግ የንፁሃኖችን ህይወት በጅምላ እየቀጠፈና አካል እያጎደለ እንስሳቶችንም እያስጨፈጨፈ ቤትና ንብረትም እያወደመ ይገኛል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 13/2018 ዓ.ም