ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አሳምነው ክፍለ ጦር ቃኝ በበርካታ መኪና በመጓጓዝ የነበረ ጠላት ላይ በፈፀሙት የደፈጣ ጥቃት ሁለት መኪና ሙሉ ለሙሉ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

ከአፋር ክልል ጭፍራ ተነስቶ ወልድያን በማቋረጥ ወደ ላሊበላ መስመር በአራት ዙ23 ታጅቦ በበርካታ መኪኖች ይጓዝ የነበረ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት መካከል ሁለቱ መኪና ላይ የአሳምነው ክፍለ ጦር ቃኝ ሳንቃ ከተማ ዙሪያ ደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ሙሉ ለሙሉ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ጉዞ ላይ ባለበት በደፈጣ የተመታው ጠላት ሙትና ቁስለኛውን ሳያነሳ ጉዞውን የቀጠለ ሲሆን ከወልድያና አካባቢው የመጣ ጠላት አስራ ሶስት ቁስለኛ አንስቶ ተመልሷል:: የአማራ ምድር ሲኦል የሆነበት የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊትም በሁሉም አቅጣጫ እየፈረሰ በስፋት ፋኖን እየተቀላቀለም ይገኛል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 8/2018 ዓ.ም
🙏31
#መረጃ

መንገድ ላይ የነበረ የጠላት ጦር ተደመሠሠ።

ትናት ማለትም በቀን 08//06/2018 መነሻውን ከጭልጋ  ወረዳ ጫንድባ ከተማ አድርጎ ወደ ጣቁሳ ደልጊ አቅጣጫ ጉዞ ያደረገ ሐይል ተደመሰሰ።

በአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት  በጌምድር ክፍለጦር እና ዞብል ጃኖ ክፍለጦር  ጥምር ሀይል  መንገድ ላይ ተቆርጦ የተከበበው የጠላት ሐይል በከፍተኛ ሁኔታ የተደመሰሰ ሲሆን አብዛኛው ሐይል መንገድ ላይ ቀርቷል።

በጭልጋና ጣቁሳ ወረዳ አዋሳኝ የሚገኝ ጨውድባና ወርቅድባ በተባለ ቦታ ላይ ከቀኑ 9:00 ገደማ በተጀመረውና እስከ ምሽቱ 2:00 በዘለቀው እልህ አስጨራሽ ትንቅን  ከፍተኛ ተጋድሎ የተደረገ ሲሆን ጠላት ጭኖት ይንቀሳቀስ የነበረ አብዛኛው ጓዝ ከነ ሰራዊቱ ጭቃ ሆኖል።

የጠላት ሻለቃ አመራርን ጨምሮ መቶ አለቃና ትይዩ ሐላፊነት ያላቸውን አመራሮች እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠር መስመራዊ መኮንኖችና ሌሎች የስርዓቱ የፀጥታ ሐይሎች ተደምስሰዋል።

አብዛኛው የጠላት ቁሳቁስ በነበረው የተኩስ ልውውጥ የጋየ፤ በቁጥር ከ150 በላይ ሙትና ቁስለኛ ያስተናገደ ሲሆን የጓዝ መጫኛ የነበሩ የተሽከርካሪዎች ገልብጠው ሙትና ቁስለኛ ማመላለሻ ሆነው አምሽተዋል። በወገን በኩል ሁለት ጓዶች በክብር  ተሰውተዋል።

ከዚሁ ትናት ውጊ ከተደረገበት ቦታ ላይ በ12 ቀን ልዩነት ውስጥ የትናቱ ውጊያ ለአራኛ ጊዜ ሲሆን የትናቱን ጨምሮ 2 ሻለቃ ፤ 5 መቶ  አለቃና ሁለት ሎጅስቲክ መምሪያዎች፤በድምሩ 9 የጠላት ሐይል አመራሮች ከ250 በላይ ሙትና ቁስለኛ ከ150 በላይ የመሳሪያ ምርኮና ከ25ሽ በላይ ቅይጥ ተተኳሽ ገቢ ሆኗል።

በአሁኑ ሰዓት የጠላት ሐይል ቁሰለኞቹን ከወረዳ ወረዳ አንቀሳቅሶ ማሳከም እንዳይችል መንገዱ ሁሉ በቆረጣ የተዘጋ ሲሆን ሄሊኮፍተርን እንደ መጨረሻ አማራጭ እየተጠቀመ ይገኛል።

ስለ ተሰውት ጓዶች ተጋድሎና ስለሰሩት ጀብድ እንመለሳለን።

ድል ለአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!

አፋብን ጎጠግ ዕዝ ግንኙነት መምሪያ!

የካቲት 9/2018 ዓ/ም
2🙏2
"ዘመቻ አስር አለቃ ሀቢብ የሱፍ(ሀቢቦ)"

ተጠናክሮ በቀጠለው አውደ ውጊያ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር በብልፅግና ሰራዊት ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጀ!

የካቲት:-09/2018 ዓ/ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ አካል የሆነው ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ከሁሉም ክፍለ ጦሮች የተውጣጡ እና የኮሩን ነብሮ ኮማንዶና ዋግሹም ብርጌድን ጨምሮ በተሳተፉበት አውደ ውጊያ በአገዛዙ መከላከያ ሰራዊት ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል።

በአርበኛ አስር አለቃ ሀቢብ የሱፍ(ሀቢቦ) የተሰየመው ዘመቻ የካቲት 09/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በቡግና ወረዳ አይና ከተማ ዙሪያ በተደረገ ከባድ ትንቅንቅ የጠላትን ኃይል አራት ምሽግ በመስበር፣ 82 በመደምሰስ፣25 ክላሽ፣1520 የክላሽ ተተኳሽ፣32 የእጅ ቦምብ ፣26 የወገብና የደረት ትጥቅ በመማረክና አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ጠላት ወደ ነበረበት የቀበሮ ጉድጓድ እንዲመለስ አድርገውታል።

በተያያዘ መረጃ የኃይሉ ከበዴ ክፍለ ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆነው አርበኛ ጌታቸው ወርቁ በድሐና መስመር ከጭላ ወደ አዚላ በአምቡላንስ ተጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረ የብልፅግና ካድሬና ፖሊስ ከጭላ በ17 ኪሎ ሜትር ርቀት ቅናባ ማርያም ላይ ደፈጣ በመያዝ የሰቆጣ ወረዳ 02 ቀበሌ ነዋሪ የሆነውን ኢንስፔክተር ወርቁ ባየንና ምርቱ አለሙ የሚባል የሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ 012 ቀበሌ የሚሰራ ፖሊስን እንዲሁም ሁለት ክላሽንኮፍ በመማረክና ለእኩይ አላማ ሲጠቀሙበት በነበረው ተሽከርካሪ ላይ ጉዳት በማድረስ አርበኛ ጌታቸው ወርቁ ታላቅ ጀብዱ ፈፅሟል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል!

ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 09/2018 ዓ.ም
🙏21
ሁለት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ባለሽረጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ


በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወርዳ በውርጌሳ ገንፎ ጨፌ የሚገኘው የሚዋጋለትን አላማ በቅጡ የማያውቀው የአብይ ዙፍን አስጠባቂ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል ።

የ35ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሽ አለቃ የአማራን ህዝብ አንጨፈጭፍም ብለው ሁለት የሰራዊት አባሎች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ሚሊኒክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽረጡ ክፍለ ጦር ጋር በሰላም ተገናኝተዋል ።

መዳረሻችን ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ ተገድሎ ይቀጥላል ።

ህልውናችን በተባበር ክንዳችን
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሚሊኒክ ዕዝ


የካቲት 9 2018 ዓ ም
3🙏1
የአብይ አህመድ የአገዛዙ ሰራዊት ከባድ ሀዘን ላይ ወደቀ!!!

ፋሽስታዊው የአገዛዙ ሰራዊት መነሻውን ማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ በማድረግ ወደ ጎንደር ከተማ ሲንቀሳቀስ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ግፈኛ ሰራዊቱን ብዛት ባለው ተሽከርካሪ ሹፌሮችን ካለውድ በግድ ድብደባና ዛቻ በተሞላበት መንገድ በማንገላታት እንዲሁም ሻሁራ ከተማ ላይ የሽብር ስራ በከባድ መሳሪያ የተኩስ ናዳ በማድረግ ህዝባችን ክፉኛ የበደለው ይህ በደም እና በግፍ የሰከረው ሰራዊት የተወሰነ ኪ.ሜ እንደተጓዘ የካቲት 08/2018 ዙ-23 ሰራዊት እንደጫነ ጎይ ከምትባል ቦታ ክፉኛ ተገልብጦ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአገዛዙ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ ከመሆኑ ባሻገር ዙ-23ቱም ከጥቅም ውጭ ሆኗል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ
የካቲት 10/2018
2
#በማለዳዋ_ጀንበር_ፋኖን_የተቀላቀሉ_ቲም_መሪዎች❗️

     አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
        የካቲት 10/2018ዓ.ም

በአገዛዙ ወታደራዊ ካምፕ ተቆጥረው ቢያድሩም ሲነጋ በማለዳው ፋኖን ተቀላቅለው የሚገኙት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቁጥራቸው ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ይገኛል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ያወጣውን የምህረት ጥሪ በመቀበል በርካታ የብልፅግናው ወታደሮች በገፍ ፋኖን መቀላቀላቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።

ዛሬም በማለዳው መነሻቸውን ከደራ ጉንዶመስቀል ከተማ ያደረጉት የአገዛዙ 15ኛ ክፍለጦር (ጋሻ ክፍለጦር) 5ኛ ሻለቃ የመከላከያ ሰራዊት ሁለት (2) የቲም መሪ አመራሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፂዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦር 3ኛ ቀስተ ንህብ ሻለቃን መቀላቀላቸውን ክፍለጦሩ በላከው መረጃ ገልጿል።

አፋብን ያወጣው የምህረት አዋጅ በበርካታ የሸዋ ከተሞች ከትሞ በሚገኘው የብልፅግናው አየር ወለድ እና እግረኛ ሰራዊት ተቀባይነት አግኝቶ በርካቶች ዕድሉን እየተጠቀሙበት መሆኑን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በህዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል አስታውቋል።

 ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!
       ድል ለአፋብን!!
       ድል ለአማራ ህዝብ!!
      ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!  
     አንድነታችን አሸናፊነታች!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

የካቲት 10/2018 ዓ/ም
🙏3
ቀን፦ የካቲት 10/2018
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ በላይ ዘለቀ ዕዝ፦ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የተሰጠ መግለጫ///

መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር በሚያስተዳድራቸው ማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ እና ነባሩ ጭልጋ ወረዳ፣በ ምዕራብ ጎንደር አዳኝ አገር ጫቆ፣ቋራ ወረዳና ከፊል መተማ የምትገኙ የፖሊስ አባላት፣ ፀረ-ሽምቅ፣ የአገዛዙ የካቢኔ አባላት፣ ሚኒሻ፣ በአገዛዙ የጥላቻ ስያሜ አድማ ብተና እና ስርአቱ በማያባራ ጦርነት እየተማገደ ላለው የመከላከያ ሰራዊት በሙሉ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ባደረገው ጥሪ መሰረት፣ እንደ ፍላጎታችሁ በሰላማዊ መንገድ ወደ ቤተሰብም ሆነ ወደ ፋኖ ትግል እንድትቀላቀሉ በተሰጣችሁ ነፃ ፍቃድ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እና ከከንቱ የህይወት መስዋትነት እንድትድኑ ወገናዊ ጥሪያችን ማስተላለፍ እንወዳለን።
የአገዛዙ ስርአት የፖለቲካ አሻጥር ለአማራም ሆነ ለሀገሪቱ ምንም አይነት ጥቅም የሌለው፣ ሀገሪቱን በደም እያጨቀየ በስልጣን መቆየት የሚፈልግ ፍፁም ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያዊ የፋሽስት ድቅል፣ ከዚህ በኃላ እድሜ እንዲኖረው መፍቀድ አስፈላጊ እንዳልሆነ በውል በመረዳት፣ የህልውና ትግላችን በህዝባዊ አብዮት ጀምሮ አሁን ላይ በመርህ የሚተዳደር አንድ አሻጋሪ ድርጅት (አፋብን) መመስረቱ መተማመኛ አሻራችን መሆኑን እንድታውቁ ማሳሰብ እንወዳለን።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ ያቀረብነውን ጥሪ ችላ በማለት በሚወሰድባችሁ እርምጃ በባንዳነት ጥቁር የታሪክ ጠባሳ ለትውልድ ጥላችሁ እንዳታልፉና ውድ ህይወታችሁን እንዳታባክኑ ማሳዎቅ እንወዳለን።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር
🙏2
አፋብን ያወጣውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ የስርዓቱ አባሎች ከነሙሉ ትጥቃቸው ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ !!


የካቲት 10/2018 ዓ.ም

ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በሁለቱም ግዙፍ ኮሮች ስር ያሉ ሁሉንም ጠንካራ ክፍለ ጦሮች በየግንባሩ ከአርበኞች ጦር ጋር በማሰማራት ሸዋ ምድር በገባው የጠላት አየር ወለድ ኮማንዶ ላይ ጠንካራ ክንዱን በማሳረፍ ጠላት በየበረሃው እና በየተራራው እየቀረ ሲሆን እድለኛ የሆነውም በድርጅት የወጣውን የምህረት አዋጅ በመጠቀም፣ ህዝባችንን አንወጋም በማለት ከነ ትጥቃቸው ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

በዚህም ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ አልዩ አንባ ላይ መሸጎ ከሚገኘው የጠላት ሀይል የከዳች አንድ የአድማ ብተና አባልና ከይፋት አውራጃ ከሸዋሮቢት የከዳ አንድ የአድማ ብተና አባል እና አንድ የሚኒሻ አባል እንዲሁም ደብረ ሲና ከመሸገው112ኛ አየር ወለድ የከዳ 1 ኮማንዶ በድምሩ 4 የስርዓቱ አባል የነበሩ የምህረት አዋጁን በመጠቀም ከነሙሉ ትጥቃቸው ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝን ተቀላቅለዋል!!

በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ከአንኮበር አካባቢ በግዳጅ አፍሶ ለሚኒሻ ስልጠና ወስዷቸው የነበሩ ገበሬዎችን ቁንዲ አካባቢ ካስቀመጣቸው በኋላ ከተቀመጡበት ካምፕ ከጠላት አምልጠው ወደ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በሰላም የተቀላቀሉ ሲሆን እዙም ጥሩ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

አሁንም ለፀረ-አማራው ስርዓት ወግናችሁ የገዛ ወገናችሁን የምትጨፈጭፉ የስርዓቱ አባሎች ድርጅቱ ያወጣውን የምህረት አዋጅ ተጠቅማችሁ ፈኖን እንድትቀላቀሉ በድጋሚ ጥሪ እናስተላልፋለን።

ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!
ድል ለአፋብን!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
https://t.me/shewafa
🙏41
የ25ኛ ክፍለጦር ዘመቻ መሪ ከብልፅግና ሰራዊት በመክዳት ፋኖን ተቀላቀለ።

የአገዛዙን ስርዓታዊ መዋቅራዊ የሴራ አካሔድ ቀድሞውኑ የተረዱትና ሁኔታዎች ለመውጣት አስቻይ ሳይሆኑ መቆየታቸውንና የአፋብን'ን የምህረት አዋጅ መጠቀም የውሳኔኣቸው የመጨረሻ እንደሆና በተግባር ፋኖን መቀላቀል እንዳስደሰታቸው አስረድተዋል።

1.ሀብታሙ አዲስ ...የመከላከያ 25ኛክ/ጦር ዘመቻ መሪ
2. አማረ ሽታ....አድማ ብተና
3.ማማሩ መለሰ...አድማብተና
4.ገብሬ በሌ.....ሚሊሻዎች ከሞጣ እና መርጦለማሪያም ካምፕ በመውጣት ሁሉም ከእነ ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ 54ኛ ክ/ጦርን የተቀላቀሉ ሲሆንበክፍለጦሩ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋለ።

አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 11/2018ዓ.ም
🙏42
የምህረት አዋጁን የተቀበለው ቲም መሪ የሚመራቸውን ስድስት አባላት ይዞ ፋኖን ተቀላቀለ።

ደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ የሚገኘው የብልፅግና የግለሰብ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አባል የነበሩ 5 አድማ ብተና እና አንድ ልዩ ሀይል ሲበተን ወደ ፖሊስ ገብቶ የነበረ በአጠቃላይ ስድስት በተዛባ መንገድ ከተረኛው ስርዓት ጋር ተሰልፈው የነበሩ ምህረት አዋጁንና ጥሪችንን ተቀብለው የካቲት 11/2018 ዓ.ም አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። የየጎፍ ክ/ጦር አመራሮችም ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የየጎፍ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 11/2018ዓ.ም
🙏41
ቀን 11/06/2018
በደቡብ ጎንደር በሐሙሲት ከተማ የአገዛዙ አሽከር የሆኑት አድማ ብተና እና ሚኒሻ ፖሊስ ከ02/062018እስከ 04/06/2018 ከአንበሳሜ እሰከ ሐሙሲት ከተማ በተደረገ አውደ ውጊያ በደረሰበት መመደምሰስ እና ያየዘውን የቡድን መሳሪያ
02 ድሽቃ
02ብሬን
167ክላሽ
32አብራረው
አንድ አይሱዙ ሙሉ የድሽቃ ተተኳሽ
6 ወታደራዊ ፖትሮል ምሮኮ የሆነበት የአብይ አሽከር ሐሙሲት ላይ ከደባርቅ መጦ የተቀመጠው ሐይል የሐሙሲትን ከተማ ህዝብ የአስኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት
ከቀኑ 10:00 ሰዓት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ በመከልከል
ከቀኑ 11:00 ሰዓት የሰው እንቅስቃሴ በመከልከል የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአብይ አማሮች በሱቪሉ ማህበረሰብ ላይ ቤት ለቤት ፍተሻ በሚል ሰበብ ማህበረሰቡን እየዘረፋ እና እያ ገላቱ ይገኛሉ።አመጣጡ የአማራን ህዝብ መጨፍጨፍ አላመው አድርጎ የተነሰው የአብይ አህመድ ስርዓት ከከተማው ማህበረሰብ በተጨማሪ አረሶ አደሮችንም ወደ ገቢያ ሲሂዱ ፍጣ እንዳይለብሱ እና ብትር እንዳይዙም ከልክላል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን

አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎሰ ክ/ ጦር
ህ/ግ ፋኖ ፍቅሩ ባየ
🔥3🙏1
#ከአፄ_ዳዊት_ክፍለጦር_የተላለፈ_ታሪካዊ_ጥሪ❗️

     አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
         የካቲት 11/2018ዓ.ም

ውድ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች እውነተኛ ፋኖዎች፣ የአፄ ዳዊት ክፍለጦር ነባርና አዳዲስ አባላትና አመራሮች፣ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አባላትና አመራሮች በሙሉ በመጀመሪያ ከፈጣሪ ቀጥሎ የትግላችን አርማ፣ የአንድነታችን ማሰሪያ የሆነው የአማራ ህዝብ ጠበቃና አታጋይ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በመመስረቱ በጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር ስም በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን ማለት እንወዳለን።

እንደሚታወቀው የፋኖ ትግልና አማራዊ ድርጅት ምስረታ በበርካቶች ፀረ አንድነት የውስጥ ሾተላይ ገመድ ጎታቾች ቢዘገይም፤ በጥቂት ቀና መሪዎቻችን ትጋትና ጥረት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ከተመሰረተ አንድ ወር ባልሞላው ጊዜ ወስጥ በርካታ አስደማሚ ሁነቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ፣ መላው የፋኖ ሰራዊታችን በከፍተኛ የሞራል ልዕልና ታላላቅ ድሎችን እያስመዘገበ ይገኛል፣ ህዝባችን በልጆቹ አንድነት በእጅጉ ተደስቷል፣ በአፋብን ምስረታ ጠላት ኔትወርክ እስከ ማቋረጥ የደረሰበት ከፍተኛ ፍርሀት ውስጥ ገብቷል፣ በርካታ የብልፅግናው ዙፋን አስጠባቂዎች ከንቅናቄው ምስረታ ማግስት ጀምሮ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣በወሎ ቤተ አምሓራ፣ በጎጃምና በጎንደር ቀጠናዎች በተደረጉ የተቀናጀ ውጊያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአገዛዙ ወታደሮች ተደምስሰዋል፣ ቁስለኛ ሆነዋል፣እድለኞች ተማርከዋል፣ ድርጅቱ ያወጣውን የምህረት ጥሪ ተቀብለው ወደ ፋኖ እየመጡ ያሉ የስርዓቱ አገልጋዮች ከአባላት እስከ አመራር ያሉት ቁጥራቸው ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ይገኛል።

በመሆኑም አጠቃላይ የትግላችን ድርጅታዊ ቁመና ገና ከውልደቱ እዚሕ ደርሷልና፣ የተከበራችሁ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፂዮን ኮር የአፄ ዳዊት ክፍለጦር ነባር ታጋዮች በሙሉ በተለያየ ምክነያት ከትግሉ ውጭ የሆናችሁ በሙሉ የወገን መመኪያ፣ የጠላት እራስ ምታት የሆነው ትላንት በጥቂት የሰው ሃይል ዋጋ የከፈላችሁበት ስመ ገናናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር በትጥቅም ሆነ በሰው ሃይል ከመቸውም ጊዜ በላይ እራሱን አደረጅቶ በከፍታ ማማ ላይ በመሆኑ "ኑ-የመጨረሻዋን የድላችንን ዋንጫ አብረን ከፍ እናድርግ" በማለት ጓዳዊ ጥሪያችንን እንደሚከተለው እናስተላልፋለን።

1ኛ. የአማራ ፋኖ አንድ ድርጅታዊ መዋቅር ባለመያዙና በእርስ በርስ ግጭት ምክነያት እራሳችሁን ከትግሉ  አግልላችሁ ለቆያችሁ የአፄ ዳዊት ክፍለጦር ነባር ታጋዮቻችን በሙሉ፣የአማራ ህዝብ ብሶት አምጦ የወለደው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ተመስርቷልና "ኑ የተመሰረተውን የጋራ ቤታችንን በፅኑ ዓለት ላይ አብረን እናቁም" ሲል ክፍለጦራችን ወንድማዊ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

2ኛ. የሴረኞች እጅ ረጅም ነውና፣ ትግላችን እየጠራ በመሔዱ ሴራቸው ሲጋለጥ፣ ዛሬ ላይ ስራቸውን አጠናቀው እጅ ሰጠን በሚል የተበላ ማደናገሪያ ቁማር ወደ ነባር ቤታቸው በተመለሱ በአመራር ደረጃ በነበሩ የውስጥ ሰርጎ ገብ ሌቦች ተገፍታችሁ ከምትወዱት አፄ ዳዊት ክፍለጦር በግፍ ለተባረራችሁ በሙሉ እኛ በፅናት የቆየን ወንድሞቻችሁ የመጨረሻዋን ሳቅ አብረን እንስቅ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።

3ኛ. ክፍለጦራችን ከሰፈር ጠባቂነት ወጥቶ ትክክለኛ የፋኖነት ቁመናን በመያዝ በሁሉም የሸዋ ቀጠና የተሰጠውን ግዳጅ ለመወጣት ከመርሀቤቴ አውራጃ ተነስቶ እስከ መንዝ አውራጃ፣ ከተጉለትና ቡልጋ አውራጃ እስከ ይፋትና ጥሙጋ አውራጃ በመንቀሳቀስ በሔደበት አዳዲስ ቀጠናዎች ሁሉ ታላላቅ ድሎችን መጎናፀፉ ይታወቃል። በመሆኑም በወቅቱ በተለያዩ ምክነያቶች በመሰል ግዳጅ ላይ ያልተሳተፋችሁ እና እራሳችሀን ከትግሉ ውጭ አድርጋችሁ ለነበራችሁ ነባር የትግል ጓዶቻችን በጀገኖናው ክፍለጦራችን ስም ወንድማዊ ጥሪያችንን ከትግሉ ሜዳ እናቀርብላችኋለን።

4ኛ. አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፅመውም ግፍ ተቃውማችሁ ለወጣችሁ ምልስ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የጄኔራል አሳምነው ፅጌ የቁርጥ ቀን ልጆች የአማራ ልዩ ሃይል አባላት፣የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ የፖሊስ አባላትና ሌሎችም የፀጥታ ሃይሎች በየቤታችሁ ተቀምጣችሁ ለምትገኙ የነፃነት ፈላጊዎች በሙሉ ክፍለጦራችን እናንተን በክብር ለመቀበል ዝግጁ በመሆኑ "ኑ - ህዛባችንን በጋራ እንታደግ" ስንል የከበረ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ከብልፅግናው የከተማ ውስጥ ወታደራዊ አፈሳም አራሳችሁን በፍጥነት እንድትታደጉም ጭምር አስቸኳይ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

5ኛ. በመጨረሻም ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ያወጣውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ በአገዛዙ ቤት የነበሩ በርካቶች በገፍ ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ፣ አሁንም ቢሆን ከአገዛዙ ጋር የተሰለፈ በሙሉ ወቅታዊ ቀጠናዊ ሁኔታዎችን በሚገባ በመረዳት፣ የብልፅግናው ጀንበር እየጠለቀች መሆኑን በማስተዋል ነገ ጥሎሕ ከሀገር ውጭ ለሚፈረጥጠው ስርዓት ህይዎትን በከንቱ ከማጣት ለቤተሰብሕና ለአማራ ህዝብ ትኖር ዘንድ አዋጁ ከመጠናቀቁ በፊት የዕድሉ ተጠቃሚዎች ትሆኑ ዘንድ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፂዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍጦር ታሪካዊ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!
      ድል ለአፋብን!!
     ድል ለአማራ ህዝብ!!
     ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!  
    አንድነታችን አሸናፊነታች!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ፂዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦር

      የካቲት 11/ 2018 ዓ.ም
       ሸዋ ፣ አማራ ፣ ኢትዮጵያ
4🙏2