የልቤ ትርታ
203 subscribers
473 photos
4 videos
10 files
422 links
Download Telegram
​​ሴና ክፍል አሥራ ዘጠኝ ❤️

. . . ከወንበሬ ተመቻችቼ ከተቀመጥኩ ቡሀላ ግቢ ከገባው ቀን ጀምሮ ያለውን ሁኔታ በሙሉ ሳምንት ያጋጠመኝን ያደረኩዋቸውን ነገሮች ማወቅ ያለባትን ያህል አጫወትኳት፡፡"እኔ በአንድ ሙሉ ሴሚስተር ያላሰለፍኩትን ላይፍ አንቺ በአንድ ሳምንት ኮመኮምሽዋ?" ብላ ሳቀችብኝ፡፡ እኔም አብሬያት ሳኩኝ፡፡"እኔ ምልሽ ግን ለምንድነው ታዲያ እንደዚ ሚሰማኝ? አንድ ሳምንት ማውቀው ልጅ ከይደለም ሚስት ፍቅረኛ ምናምን ቀርቶ ልጅ ቢኖረው ምን አገባኝ? ለምንድነው ውስጤ የሚረበሸው? ለምንድነው ልቤ ሚደነግጠው? በናትሽ ቹቹ ንገሪኝ?" አልኳት ሳቋን እስክትጨርስ እንኳን ሳልጠብቃት አይን አይኗን እያየው፡፡
"የውልሽ ሴና" ሴና አለች በወንበሯ ተመቻችታ እየተቀመጠች "የውልሽ ሴና ምናልባት አንቺ ወንድ እንደዚ ስትቀርቢ ይህ የመጀመሪያሽ ስለሆነም ሊሆን ይችላል እንደዚ የተሰማሽ፡፡ ሳታስቢው ፍቅር እየያዘሽ . . .." "ምን?! ፍቅር?" አቋረጥኳት፡፡ ደነገጥኩ "ምንድነው ምትይው? እንዴት በአንድ ሳምንት ውስጥ. . . ማለቴ . . .ደሞ የፍቅር ፅሁፎች ብዙ አንብቤያለው እነዴት . . . እኔ ምልሽ ቆይ ስታስቢው . . . " ተንተባተብኩ ፊቴን ላብ አሰመጠኝ ፤የምናገረው ግራ ገባኝ 'እንዴት ነው ፍቅር ቆይ እንደዚ ነው እንዴ?' ከራሴጋር መጨቃጨቅ ጀመርኩ፡፡"የውልሽ ሴና አዳምጪኝ" አለች ቹቹ ረጋ ባለ መንፈስ፡፡"እኔም ለመጀመሪያ ግዜ እንዳንቺው ነበር የሆንኩት እመኚኝ በቃ የቡሀላውን ባናውቅም ለግዜው ግን ፍቅር ይዞሻል፡፡" ደገመችልኝ "እንዴት ነው በዚህ ቀን ውስጥ ፍቅር? ፍቅር እንደዚ ነው እንዴ?ምን አይነት ፍቅር ነው ይሄ?" አፈጠጥኩባት ፤ጥያቄ ላይ ጥያቄ አከታተልኩባት፡፡ ቹቹ ዝም ብላ ስትመለከተኝ ከቆየች ብሀላ "ቆይ ለልጁ ምንም ስሜት የለሽም?
"አረ ምንም ስሜት የለኝም በቃ እናወራለን እንጫወታለን አለቀ ከዛ ውጪ ምምም ማስበው ነገር የለም፡፡"እንደመናደድ ብያለው፡፡"እና ብታጪውም ምንም አይመስልሽማ?" አለችኝ ቹቹ አይኔን ትኩር ብላ እየተመለከተች"አዎ እንዴ ምን አይመስለኝም"አልኳት አይኔን እያርገበገብኩ፡፡ "እሺ በአንድ ነገር እንስማማ"አለችኝ፡፡ ምንድነው እንኳን አላልኳትም ወዲያው እሺ አልኩኝ፡፡ "ፍቅር ይዞሻል ብቻ አትበይኝ ሌላ ነገር እስማማለው "አልኳት፡፡ "ለልጁ ምንም ስሜት ከሌለሽ እስከዛሬ ሳምንት በስልክም በአካልም እንዳታገኚው፡፡እውነት ምንም ስሜት ከሌለሽ አይደለም አንድ ሳምንት እስከመጨረሻሽ እንኳን ባትገናኙ ምንም አይመስልሽም ማለት ነው" አለችኝ ፡፡ ደነገጥኩ! ግን ፍቅር እንዳልያዘኝ ለራሴም ለቹቹም ማሳየት ፈልጋለው፡፡ ተስማማው ፤እሺ አልኳት፡፡ "አንድ ሳምንት ፍሬ ሚባል ሰው እንኳን አልገናኝም፡፡" አልኳት፡፡ በውስጤ ግን አንድ ነገር አሰብኩ፡፡ 'እንዴ ከነሚጣ ጋር ከሆንኩ እኮ ፍሬን መገናኘቴ አይቀርም፡፡ ከቹቹ ጋር ደሞ መዋል አልችልም፡፡ እና ብቻዬን ልሆን ነው?' ምን ማድረግ እንዳለብኝ ከራሴ ጋር ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡
እንዴት ነው ይሄንን አንድ ሳምንት ማሳልፈው? አንድ ሀሳብ መጣልኝ ወንድሜ 'አግኚያት የመስራቤታችን ሰውዬ ልጅ ናት ያለኝ ትዝ አለኝ፡፡ አዎ ከሷጋር ሆናለው የዛኔ ማንንም አላገኝም ማለት ነው፡፡'በዚህ ሀሳብ ከራሴ ጋር ተስማማው፡፡'ግን እኮ አላውቃት አታውቀኝ አባቱዋና ወንድሜ አንድ ቦታ ሰሩና እኔና እሱዋ እንግባባለን ማለት ነው?' ስል ደሞ ሌላ ነገር ማሰብም ጀመርኩ፡፡ በቃ ላይብረሪ ውላለው ወይም ዶርም ተኝቼ ውላለው፡፡ ብዙ ብዙ ነገር አሰብኩ፡፡ እንዴት እንደማደርግ ሳወጣ ሳወርድ በሀሳብ ሄድኩ፡፡
"ሴና ! ምን ሆነሻል?" ከወሰደኝ ሀሳብ የቹቹ ጥሪ መለሰኝ፡፡ እንዲሁ ነው ብያት ከቹቹ ጋር ከተስማማን ብሀላ ጨዋታ ቀይረን ስለሌላ ነገር ማውራት ጀመርን፡፡ በዚህ መሀል ስልኬ ጠራ ፡፡ፍሬ ነው . . .

#ክፍል_ሀያን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

@fiker_markiye

https://telegram.me/geyone

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
​​ሴና ክፍል ሀያ ❤️

. . . "ሴና ምን ሆነሻል?" ከወሰደኝ ሀሳብ የቹቹ ጥሪ መለሰኝ፡፡ እንዲሁ ነው ብያት ከቹቹ ጋር ከተስማማን ብሀላ ጨዋታ ቀይረን ስለሌላ ነገር ማውራት ጀመርን፡፡በዚህ መሀል ስልኬ ጠራ ፡፡ፍሬ ነውስልኬን አይቼ ቀና ብዬ ቹቹን እየተመለከትኳት "ፍሬ ደወለ" አልኩ እንደመደንገጥ ብዬ፡፡"እና ይደውላ ምነው ልታነሽው ባልሆነ፡፡"ስትለኝ ምንም መልስ ሳልሰጣት ስልኬን አስቀምጬ ጨዋታችንን ቀጠልን፡፡ ብዙ ከተጨዋወትን ቡሀላ ቹቹ ምትሄድበት እንዳለ ነግራኝ ካፌ ትታኝ ወጣች፡፡
ትንሽ ብቻዬን እንደተቀመጥኩ ለነ ሚጣ ልደውል አስቤ ደግሞ ፍሬ ቢኖርስ ብዬ ተዉኩት፡፡ ወንድሜ አግኛት ላለኝ ልጅ ልደውል አልደውል ስል ብዙ አመነታው፡፡በመጨረሻም ደወልኩላት፡፡ ረጋ ያለች ልጅ ትመስላለች ትንሽ አናግሬያት ከተዋወቅን ብሃላ ከቻለች እንድንገናኝ ስጠይቃት "ዛሬ ክላስ የለኝም ቤት ነኝ ጥዋት ነው ምመጣው"አለችኝ፡፡ 'ጎሽ ከኔም የባሰ አለ ማለት ነው' አልኩ በሆዴ፡፡ነገ ላገኛት ተቀጣጥረን ስልኩን ዘግቼ ቁጭ ብዬ ቲቪ ላይ ማፍጠጥ ጀመርኩ፡፡ ብቻዬን ነው የተቀመጥኩት፡፡ አይኔ ቲቪ ያያል እንጂ ሀሳቤ ሌላ ቦታ ነው፡፡
"አረ ቆንጆ ብቻሽን ምነው? ከገባው ጀምሮ ሳይሽ ብቻሽን ነሽ የማን ፋራ ነው አስደግፎሽ የቀረው?" እያለ ከፊትለፊቴ ያለ ወንበር ስቦ ተቀመጠ አንድ ፀጉረ ጨበሬ ወንድ፡፡ምንም መልስ አልሰጠውትም፡፡ ከተቀመጠ ቡሃላ "ወንበሩ ግን ሰው አለው?" አለኝ መልስ አልሰጠውትም ወደ ወንበሬ መደገፊያ ደገፍ ብዬ እጄን በደረቴ አድርጌ ተቀመጥኩ፡፡ "ፆም ገባ እንዴ?" አለኝ ፡፡ 'የምን ፆም?' ስለው "ተመስገን አልገባም ማለት ነው፡፡ምነው ብቻሽን እዚ ማንን እየጠበቅሽ ነው?" አለ፡፡ከመጣ ሰአት ጀም ሌላም ያላስታወስኮቸው ብዙ ነገሮች አወራ ፣ሊቀልድ ማከረ ፣ሊያስገርመኝ ሞከረ፡፡ እኔ በራሴ ሀሳብ ውስጥ ነኝ፡፡ ወሬው ቢያቅተኝ ለሚጣ ደውዬ ቀጥሮ እንደሚጠብቅ ሰው'የት ናቹ ቆየው እኮ ከመጣው የት ልምጣ' አልኩኝ እንደመቆጣት ብዬ፡፡ሚጣ ያልኳት ግራ ቢገባትም ያሉበትን ነገረችኝ፡፡ እዛው ጠብቁኝ ብዬ ተነሳው፡፡ ልጁ አብሮኝ ተነሳ"እኔም ወደዛው ስለሆንኩ ልሸኝሽ?" አለኝ፡፡ 'ምሄድበትን እንዴት አወክ?' ብዬ ስጠይቀው "እሱን ስትደርሺ ነዋ ማውቀው"አለኝ፡፡ 'ውይ በናትክ ወንድሜ ተወኝ'ብዬ ወደነሚጣ ገሰገስኩ፡፡
ከነሚጣ ጋር ስገናኝ ረጅም ቀን ያጣዋቸው ያህል ነበር የናፈቁኝ፡፡ ሁሉንም ሰላም ብዬ "ምነው ቅድም ፍሬ እየደወለልሽ አታነሺም አብረን ነበርን" አሉኝ፡፡ ከሰው ጋር እንደነበርኩ ነግሬያቸው ካፌ ውስጥ ያጋጠመኝን ልጅ ነግሬያቸው መሳሳቅ ጀመርን፡፡
ማታ ዶርም ገብቼ ልብሴን ከቀያየርኩ ቡሀላ ክፍል ገብተው ከፃፉት ማስታወሻ ላይ መገልበጥ ስጀምር የፍሬ መልእክት በስልኬ ገባ"ምነው ጠፋሽ በሰላም ነው?" ሚል ነበር፡፡ አንበቤ ብቻ ስልኬን መልሼ አስቀምጬ መፃፌን ቀጠልኩ፡፡ ዶርም ውስጥ እያወራን እየተሳሳቅን ስለነበር ለፍሬ መልእክት አለመመለሴ ብዙም ቅር አላለኝም፡፡
ጥዋት ወደ ክፍል ስንሄድ ፍሬን ባላገኘው ብዬ በውስጤ ተመኘው፡፡ ጠልቼው አይደለም ግን ደሞ . . . በቃ ብቻ ላገኘው አልፈለኩም፡፡ ብዙ ቀን ወደክፍል ስንሄድ ፍሬና ዴቭን እናገኛቸዋለን፡፡ ዛሬ አላገኘናቸውም የሆዴን ሰማኝ መሰለኝ፡፡
ቀን ከክፍል ስንወጣ ምሳ ካፌ እንግባ ወይስ ውጪ እንብላ ብዬ ጠየኩዋቸው፡፡ "አረ ዴቭ ዛሬ ምሳ በኔ ነው ብሎአል ልደውልለት እንደውም ብላ ስልኳን መነካካት ጀመረች፡፡ ደነገጥኩ 'ወይኔ ጉዴ ፍሬም ይመጣል ማለት ነው እኮ' አልኩኝ ለራሴ፡፡ በዚህ መሀል የወንድሜ ባልደረባ ልጅ ደወለች፡፡ ከተመቸኝ አሁን እንዳገኛት ጠየቀችኝ፡፡ እንደሚመቸኝ ነግሬያት ለነሚጣ 'በጣም ይቅርታ ረስቼው ነው ወንድሜ እንዳገኛት የነገረኝ ልጅ አለች አሁን ነበር ቀጠሮዋችን፡፡ረስቼው ነው በጣም ይቅርታ ጉዋደኞቼ ቡሀላ አገኛቹሀለው ብዬ ጉንጫቸውን ስሜያቸው ተሰናበትከበቸው፡፡በመሄዴ ደስ ባይላቸውም በእሺታ ራሳቸውን እየነቀነቁ ተቀበሉኝ፡፡ ትቻቸው ሄድኩ፡፡
ግን እስከመቼ? ለአንድ ሳምንት ወይስ እስከመጨረሻው? ቆይ ዛሬን እንዲ አለፍኩ ነገስ? ምን እያደረኩ ነው? ምን እየሆንኩ ነው? ውስጤ ብዙ ጥያቄ ይመላለሳል፡፡ እየተወዛገብኩ እርምጃዬ ወደ ቀጠሮዬ እያመራኝ ነው . . .

#ክፍል_ሀያአንድን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
​​ሴና ክፍል ሀያአንድ

. . . ከቀጠሮዬ ቦታ ደስደርስ ስልክ ደውዬ ተገናኘን፡፡ እንደጠበኳት ግን አይደለችም፡፡ዝንጥ ያለች ቆንጅዬ ልጅ ነች፡፡ ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ተዋውቀን ተቀመጥኩ፡፡ ፌቨን ነው ስሟ፡፡ ትንሽ እንዳወራን ተግባባን ፡፡ ፌቨን ቀለል ያለች ተጫዋች ልጅ ነች፡፡ ቡዙ ተጨዋወትን በዚህ መሀል ስልኬ ሶስት ግዜ ተደውሎአል፡፡ ፍሬ ነው አላነሳውትም፡፡ ቀኔን ከፌቨን ጋር አሳለፍኩ፡፡
ወደ አመሻሽ ላይ እና ሚጣ ደውለው እራት አብሬያቸው እንድበላ ጠየቁኝ፡፡ አብሬያቸው መሆንን ፈልጌያለው፡፡ ግን ፍሬ ሊኖር ይችላል ብዬ ስላሰብኩ ሰበብ ፈጥሬ መቅረትን መረጥኩ፡፡"ትንሽ አመም አድርጎኝ ወደ ዶርም እየሄድኩ ነው፡፡ ባይሆን ስትመጡ እራት ይዛቹልኝ ኑ" ብያቸው ወደ ዶርሜ አቀናው፡፡
ዶርሜ ስገባ ያቺን ባለ መነፅር አልጋዋላይ ተኝታ ኮምፒውተሯን እየጎረጎረች አገኘዋት፡፡ ሰላም ተባብለን ለምን ብቻዬን እንደመጣው ስትጠይቀኝ ትንሽ ራሴን አመም አድርጎኝ እንደሆነ ነግሬያት ልብሴን ቀይሬ ተጣጥቤ አልጋዬላይ ወጥቼ ተኛው፡፡ ከእንቅልፌ የባነንኩት በሚጣ ጥሪ ነው፡፡ "ምን ሆነሽ ነው? በጣም አመመሽ እንዴ?" አለችኝ ግንባሬን በእጇ እየዳበሰች፡፡ "የት ውለሽ ነው? ምን ሆነሽ ነው? የጥያቄ መአት እያከታተሉ ይጠይቁኝ ጀመር፡፡ ብዙም አላወራውም ያመጡልኝን እራት ከበላሁ ቡሀላ ተመልሼ አልጋዬላይ ወጣሁ፡፡ ስለውሎዋቸው ያጫውቱኝ ጀመር፡፡ እያወራን ስልኬ መልእክት ገባ ፡፡ ፍሬ ነው አነብቤው ተውኩት፡፡ ጨዋታችን ቀጠለ፡፡
እንዲ እንዲያ እያልኩ ቀናት ተቆጠሩ ፣ሳምንቱም አለቀ ፣ቤት ደርሼ ተመለስኩ፡፡ ለቹቹ ቃል እንደገባውላት ፍሬን አንድ ሳምንት ሳላገኘው፡፡ በቀጠሮዋችን ቀን ከቹቹ ጋር የተለመደው ቦታ ተቀምጠን ስላለፈው ነገር ማውራት ጀመርን፡፡ "ይኸው ፍቅር እንዳልያዘኝ እወቂ፡፡ አንድ ሳምንት አላገኘውትም ግን ምንም አልተሰማኝም ፣ምንም አልሆንኩም" አልኳት ግዳጁን እንደተወጣ መልእክተኛ ፡፡ "ስለዚህ በዚሁ ትቀጥያለሽ ማለት ነው" አለችኝ ቹቹ፡፡ አልገባኝም ፤ደነገጥኩ "ማለት ከዚህ ቡሀላ ፍሬን ላላገኘው?" አልኳት፡፡ "እንደዛ ማለቴ አይደለም ከዚህ ቡሀላም ስለፍሬ አታስቢም ፣ብዙ ግዜሽን ከፍሬ ጋር አታሳልፊም፡፡ በቃ እንደማንኛውም ተራ ጉዋደኛ ብቻ ይሆናል ምትቀራረቢው" አለችኝ፡፡
" 'ለምንድነው?' ብለሽ እንደምታስቢ አውቃለው፡፡ አንቺ በዚህ ግዜ ስለ ፍቅር ምንም ማሰብም ፣ፍቅረኛ እንዲኖርሽ አትፈልጊም፡፡ ፍሬ ደሞ በአጭር ቀን ውስጥ በጣም የቀረብሽው ወንድ ነው፡፡ በዚህ ከቀጠልሽ ደሞ ወደ ፍቅር ማይቀየርበት ምክንያት አይኖርም፡፡ስለዚህ ግንኙነታቹን ትቀንሻለሽ፡፡ ይሄንን ደሞ ምመክርሽ ላንቺው ብዬ ነው፡፡" አለችኝ ቹቹ፡፡ ዝም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ምንም ሳልናገር ከ አስር ደቂቃ በላይ አሳለፍኩ፡፡ ብዙ አወጣው አወረድኩ፡፡ "እውነቷን ነው? አይ ምንም ችግር የለውም . . . "ቹቹም ዝም ብላ ታየኝ ጀመር፡፡ እንደመጀመሪያው ቀን ዛሬ ወዲያው ልስማማ አልቻልኩም፡፡ "እሺ" የማለት ድፍረት አጣው፡፡ "ይሄንን ግዜ ወስደሽ በደንብ አስቢበት፡፡ የምርጫ ጉዳይ አይደለም፡፡ እሺ ወይ እንቢ እንድትይኝ አይደለም፡፡ ራስሽ እንድታስቢው ፤ራስሽን በራስሽ እንድትመረምሪበት ነው የነገርኩሽ" አለችኝ ቹቹ አይኔን እያየች፡፡ እንማስብበት ነግሬያት በተለመደው ሰአት ተለያየን፡፡
ወደሚጣ ስልክ ስደውል ፍሬ አነሳው፡፡ "ሴና ግን ምን አድርጌሽ ነው? እንደዚ ሚያስከፋ ነገር አደረኩሽ ግን? . . ."ገና እያወራኝ ስልኩን ዘጋውት፡፡ ደነገጥኩኝ፡፡ 'እውነት ምን አድርጎኝ ነው ግን?' ብዬ አሰብኩ፡፡ 'እንዴት ግን የሚጣን ስልክ አነሳው?ምናልባት አብረው ሆነው ይሆናል፡፡' እነሚጣ የት እንዳሉ ለማወቅ ነበር የደወልኩት፡፡
ትንሽ ቆይቶ ፍሬ በራሱ ስልክ መልእክት ላከልኝ፡፡ በቆምኩበት ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ እያነበብኩ ወደመሀል ስደርስ ሳላስበው እንባዬ መጣ፡፡ ማንበቤን ቀጠልኩ፡፡ እንባዬ አይኔን ሸፎኖኝ ስልኬላይ መንጠባጠብ ጀመረ፡፡ የላከልኝ መልእክት እንዲህ የሚል ነው . . .

#ክፍል_ሀያሁለትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️


https://telegram.me/geyone
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
​​ሴና ክፍል ሀያ ሁለት ❤️


. . . የላከልኝ መልእክት እንዲህ የሚል ነው"ሴና ይሄንን መልእክት ማታ ነበር ልልክልሽ የነበረው፡፡ ግን ምናልባት ሳይመቻት ይሆናል ስልም መልሼ አሰብኩ፡፡ አሁን ገን ጥርጣሬዬ እውነት መሆኑን አሳየሽኝ፡፡
ሴና በዚች አንድ ሳምንት ያሳለፍነው ግዜ ለብዙ ግዜያት አብሬያቸው የቆየው ሌሎች ሴቶች ጋር ያሳለፍኩትን ግዜ በእጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡ ምን እንዳስቀየምኩሽ ፣ምን እንዳጠፋው ወይ ያልተመቸሽ ነገር ምን እንደሆነ ራሱ ሳትናገሪ በድንገት ጠፋሽ፡፡ 'አንድ ሳምንት ለምታውቃት ልጅ ምንድነው እንደዚ ሙጭጭ ማለት፡፡' እስኪሉኝ የዶርም ልጆች ስላንቺ ሳስብ ስጨነቅ ነበር፡፡አንቺ ግን ትክክል አልሰራሽም፡፡ በእውነት እልሻለው ትክክል አልሰራሽም፡፡ አንቺ ምክንያት ሊኖርሽ ይችላል፡፡ ግን ምንም ሆነ ምን ከኔጋር ሚገናኝ ምክንያት የሚኖርሽ አይመስለኝም፡፡ መጀመሪያ ያገኘውሽ ቀን የሆነ ነገር ነበር የተሰማኝ፡፡ያለፈውን መጥፎ ግዜ አስታወሽኝ አሁን ፡፡ ምን እንደሆነ ልነግርሽ አልችልም፡፡ እና ሴናዬ በቃ አንቺ ያመንሽበት ነገር ከሆነ ችግር የለውም አልደውልም ፣ መልእክትም አልክም፡፡ እኔ ሴት ምናምን ወዲያ ወዲ ማደርግ መስሎሽም ከሆነ ተሳስተሻል፡፡ እንደዛ ቢሆን አንድ ሳምንት ላወኩሽ ይሄንን ሁሉ ባለፈለፍኩ በሁለተኛው ቀን ነበር ምረሳሽ፡፡ እና በቃ እኔን ሽሽት ከ ጉዋደኞችሽ አትራቂ፡፡ እኔ አልደርስብሽም፡፡ መንገድ ላስ ስንገናኝ 'ሰላም' በይኝ ግን እሺ፡፡ ደና ሁኚ፡፡"
አንብቤው እንደጨረስኩ ባለሁበት አካባቢ መቀመጫ ፈልጌ ቁጭ አልኩ፡፡ ሳላስበው በጉንጬ ላይ የወረደውን እንባዬን አብሼ መልሼ መልእክቱን ማየት ጀመርኩ፡፡ አላውቅም ብቻ የሆነ ነገር ረበሸኝ፡፡ ልቤ ድንግጥ ድንግጥ ይላል፡፡ የማላውቀው የጭንቀት ስሜት ተሰማኝ፡፡ እንደምንም ራሴን አረጋግቼ ወደ ዶርም ሄድኩኝ፡፡
ዶርሜ አልጋዬላይ ጋደም እንዳልኩ ፊቴ ላይ ሚመጣው ፍሬ ነው፡፡ ብገላበጥም ፣ጥቅልል ብዬ ብተኛም ፍሬን ብቻ ማሰብ ሆነ ስራዬ፡፡ ስልኬን አውጥቼ ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ከፍሬ ጋር የተላላክናቸውን መልእክቶች ማንበብ ጀመርኩኝ፡፡ እነዛን ቀናት በውስጤ እያሰብኳቸው ብቻዬን ፈገግ እላለው፡፡ ዛሬ የላከልኝን መልእክት ደግሜ ሳነበው እንባዬ ይመጣል፡፡
እውነቱን ነው እኮ ግን ምን አደረገኝ ቆይ? ከኔጋር ግዜውን ስላጠፋ ነው? አብሮኝ ስለሆነ ነው? ስለቀረበኝ ነው? የራሴን ስሜት ብቻ ለምን ተከተልኩ? ሳላስበው እንባዬ ይፈሳል፡፡ የሆነ ቅር ቅር ሚል ነገር ይሰማኛል፡፡ አልጋዬላይ ጋደም በዬ በትዝታ ከፍሬ ጋር እየተጫወትኩ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡
ከእንቅልፌ ስነሳ እኩለ ለሊት አልፎአል፡፡ ራሴን በጣም አሞኛል፡፡ አልጋዬ ላይ እንዳለው ቀና ብዬ ዶርሙን በአይኔ ቃኘው፡፡ ሁሉም ተኝተዋል፡፡ ጠረቤዛ ላይ የፕላስቲክ ምሪንዳ እና ብስኩት ተቀምጦአል፡፡ ምናልባት ለኔ ይሆናል ብዬ አሰብኩ፡፡ ስልኬን ስመለከት 16 ግዜ ተደውሎአል፡፡ደነገጥኩ ወንድሜ እና አባቴ ናቸው፡፡ አሁን እንዳልደውል ወረበሽ ይሆናል፡፡ የፍሬን መልእክት ስላጣው ቅር አለኝ፡፡ተመልሼ ተኛሁ ግን እንቅልፍ አልወስድ አለኝ፡፡ እንዲሁ ስገላበጥ አነጋው፡፡
ጥዋት የዶርሜ ልጆች ሲነሱ ሁሉም በየተራ "ሴና ማታ ምን ሆነሽ ነው?" ይሉኝ ጀመር፡፡መልሼ ጠየኳቸው"ምን ሆንኩኝ?" ስል፡፡ "እንዴ ማታ ብንጠራሽ አትሰሚ ደሙ አልቅሰሽ ነበር? ስልክሽም ያንን ሁሉ ግዜ እንደዛ እየጠራ መጨረሻ እንዳይጨነቁ ብዬ 'ትንሽ ራሱዋን አመም አድርጎዋት ተኝታ ነው'አልኩልሽ፡፡ ቆይ ግን ምን ሆነሽ ነው?" አለችኝ እኑካ፡፡'አይ ተመስገን ስልኬን ካነሳቹ ሌላው ቀላል ነው' አልኩኝ በሆዴ፡፡
"ሜምናልባት እራት ካልበላሽ ብለን ነው ያመጣንልሽ እኮ ፆምሽን ነዋ ያደርሽው?" አለችኝ ሚጣ እንደመቆጣት ብላ፡፡ "እሺ አሁን ቁርስ በላዋለው "ብያቸው ልተጣጠብ ወጣው፡፡ ተጣጥቤ ስመለስ ራስምታቴ ባሰብኝ፡፡ አልጋዬ ላይ ተመልሼ ተኛው፡፡ ቢጠይቁኝም መልስ የለኝም፡፡ "የክፍል ሰአት እየደረሰ ስለሆነ እናንተ ሂዱ በቃ እኔ እዚ አለው" አለች ቹቹ፡፡ አሁን ድምፁዋን ስሰማ ነው መኖሩዋን ያወኩት፡፡ "አይ እኔ አለው እናንተ ሂዱ" አለች ሚጣ፡፡ ከቹቹ ጋር ተቃራኒ እንደሆኑ አውቃለው፡፡ "ካልሽ እንዳልሽ ይሁን "ስትል ቹቹና ጉዋደኞቹዋ ተያይዘው ወጡ፡፡ እነ እኑካም ተከታትለው ወጡ፡፡ በመጨረሻም ባለ መነፅሯ ወጣች፡፡ እኔና ሚጣ ብቻ ቀረን፡፡ አልጋዬላይ ተጠቅልዬ ጋደም እንዳልኩ ነኝ፡፡
"ምን ሆነሽ ነው ግን? ሰሞኑን እኮ ልክ አይደለሽም" አለችኝ ሚጣ፡፡ "ምንም አልሆንኩም" አልኳት እንባ እየተናነቀኝ፡፡"የሆነ ነገርማ ሆነሻል ፤ግድ የለሽም ንገሪኝ" ስትል በጥያቄ አስጨነቀችኝ፡፡" እኔም ግራ ገብቶኛል ሚጣ ፡፡ እኔ ራሴ አላውቅም! እንዲነው ምልሽ ! ተረድቼ ማስረዳሽ ! የሆንኩትን ማውቀው ነገር የለኝም! እኔም ግራ ገብቶኛል እኮ! ምን ሆንኩ ልበልሽ!? እንዴት ላስረዳሽ!? " እንባዬ እየወረደ ሀይለቃል የተቀላቀለበት መልስ መለስኩላት፡፡ ራስምታቴ ጨመረ . . .

#ክፍል_ሀያሶስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️


https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
​​ሴና ክፍልሀያሶስት ❤️

. . . ራስ ምታቴ ጨመረ በጣም ጭንቅንቅ ሚያደርግ ስሜት ይሰማኛል፡፡እንደምንም ራሴን ለማረጋጋት እየሞከርኩ ነው፡፡ሚጣ በተደጋጋሚ ብትጠይቀኝም ምክንያቴን እኔ ራሱ እንደማላውቀው ነገርኳት፡፡
ቀናት ተቆጠሩ የሆዴን በሆዴ ይዤ ቀጠልኩ፡፡ቅዳሜና እሁድ ቤት ስሄድ ከበፊቱ ይበልጥ ይጨንቀኝ ጀመር፡፡ ትምህርቱም እየቀጠለ ፣እኔም ተማሪዎችን እየተግባባው ግቢውንም በደንብ እየለመድኩት ፣ዶርም ውስጥም ሁላችንም እየተግባባን መጣን፡፡ የኛ ዶርም ውስጥ የተመደብነው 8ብንሆንም አንደኛዋ ግን መጥታም አታውቅም የቀረነው ግን ከቀን ወደቀን የዶርም አንድነታችን እየጠነከረ መጣ፡፡ እነ ቹቹ ሚያመሹ ቀን እንጠብቃቸው ጀመርን፡፡ ዶርማችንን እየወደድኩት መጣው፡፡ወር አለፈ ቀናት ተቆጠሩ፡፡ይሄንን ሁሉ ግዜ ግን በውስጤ ያለውን ነገር ለማንም አልተናገርኩም፡፡ ዛሬም ድረስ ስልኬ ላይ የፍሬን መልእክቶች አነባቸዋለው፡፡ እነዛ ወክ ያደረግንባቸው ምሽቶች የመጀመሪያዎቼም ስለሆኑ መሰለኝ ዛሬም ድረስ ውስጤ አሉ፡፡
በዚህ ሁሉ ግዜ ፍሬን በአካል አግኝቼው አላውቅም፡፡ አንድ ግቢውስጥ ሁነን አለመገናኘታችን አስገርሞኛል፡፡እኔ ከነሚጣጋር ስሆን ፍሬ አይመጣም፤እንዳጋጣሚ እኔ የሌለው ቀን ፍሬ እንደመጣ ይነግሩኛል፡፡አለመገጣጠም ይሁን ፍሬ ከኔ እየራቀ አልገባኝም፡፡ስለሱ ወሬ ሲነሳ ደስ ይለኛል ፣ናፍቀዋለው ለሱ የሆነ ስሜት ይሰማኛል፡፡"ምን እየሆንኩ ነው ግን?"ስል ራሴን ጠይቃለው፡፡ ዴቭን ሳገኘው ስለፍሬ ልጠይቅ እያልኩ ተወዋለው፡፡ ሽንፈት መስሎ ይታየኛል፡፡ "ግን ምኑን ነው ምሸነፈው?" የተደበላለቀ ነገር ውስጥ ነኝ፡፡ አሁንም ድረስ ውስጤ አልተረጋጋም ፣የሆነ ነገር የጎደለ ያህል ቅር ቅር ይለኛል፡፡
ዛሬ የዶርም ልጆች ተሰብስበን እራት አንድ ላይ ልንበላ ተቀጣጥረናል፡፡ ሀሳቡን ያመጣችው ቹቹ ነች፡፡ ሁላችንም ምሽት ላይ ግቢውስጥ በአንዱ ካፌ ተሰብስበን እራት ከበላን ብሀላ ቹቹ አንድ ልታሳየን ምትፈልገው ነገር እንዳለ ነግራን ሁላችንም ተያይዘን ወደ ምትወስደን ቦታ እንከተላት ጀመር፡፡
ከአንድ ተማሪዎች ከማይበዙበት ቦታ እንደደረስን እዚ እንድንቀመጥ ነገረችን፡፡ እኔ ውስጤ ተጨነቀ፡፡ ይሄ ቦታ ከፍሬጋር ማታ መታ እንቀመጥበት ነበር፡፡ ሁላችንም ቦታ ቦታ ይዘን ተቀመጥን፡፡ ቹቹ ከመሀከላችን ቆማ ንግግር ታደርግ ጀመር "እህቶቼ እንደምን አመሻቹ፡፡ ያው እንግዲ ዛሬ እንዲ እንድንሰባሰብ ያደረኩዋቹ እኛ አንድ ክፍል ውስጥ ምንኖር ልጆች ነን፡፡ ያ' ማለት ደሞ ልክ እንደ አንድ ወላጅ ልጆች ነን ማለት ነው፡፡ እዚ ሆነን የሆነ ነገር ቢደርስብን ከወላጆቻችንም ሆነ ከማንም ቀድመን አንዳኝን ነን ለአንዳችን ምንደርሰው፡፡ በዶርም ውስጥ ስንኖኖር አንዳች የሌላውን ደስታም ሆነ ሀዘን እንጋራለን፡፡ አብረን ስንሆን በጋራ ምናሳልፋቸው ነገሮች ደሞ ብዙ ናቸው፡፡ዛሬ እንደመጀመሪያ በዶርማችን የተፈጠረ አንድ ነገር አለ እሱን እናስተካክላለን፡፡እና ብዙ እንዳለፈልፍባቹ ሴና ተነሺ "አለች፡፡
እኔን እንድነሳ ካደረገችን ቡሀላ በአንድ ጨርቅ አይኔን ልታስረኝ እንደሆነ ነገረችኝ፡፡ፈራው ምን ሊፈጠር እንደሚችል ልገምትም አልቻልኩም፡፡"እንግዲ ሴና ዛሬ ላንቺ አንድ ደስ ሚል ነገር አለ" አለች ቹቹ አይኔን አስራ ስታበቃ፡፡'ምን ይሆን?' አልኩኝ ፤አይኔ እስኪፈታ ቸኮልኩ ፤የተዘጋጀልኝ ነገር ምን እንደሆነ ለማየት በጣም ጓጓው . . .

#ክፍል\ሀያአራትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️
@geyone
@geyone
@geyone

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
🎁ኢትዮ-ቴሌኮም ትርፉን በማስመልከት ለህዝቡ ለ3 ቀናት የሚቆይ የ1GB ኢንተርኔት እና የ303 Flexi Unit ነፃ አገልግሎት አቀረበ።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
,,,,አይ እሷ
እንደ እናት አንደ አባት፣
እንደ ባል ሁኘ አገለገልኳት፣
እኔ ለሷ ብየ አንገቴን ብደፋላት፣
እሷ እዳትደክም ብየ እኔ ስሰራላት፣
በለለኝ አንደበት ፍቅሬን በሰጠዋት፣
ወገቤን አጥፌ እሷን ባነገስኳት፣
እዚ እኔን ሚስት አርጋ፣
ለካ እዛ ባል አላት።
$$$$$$$=Job
eyoba
https://telegram.me/geyone
​​ሴና ክፍል ሀያ አራት ❤️

. . . የተዘጋጀልኝ ነገር ምን እንደሆነ ለማየት ጓጓው፡፡ "ይሄንን ያደረኩት በብዙ መልኩ አመዛዝኜ ነው፡፡ በዶርማችን ውስጥ የሴና የሰሞኑ ጭንቀቱዋ ሁላችንንም ያስጨነቀን ነገር ነው፡፡ እናም ዛሬ . . ."
ቹቹ ስትናገር እኔ ይበልጥ ጉጉቴ ጨመረ፡፡ ምንድነው ያዘጋጀችልኝ? ጭንቀቴን ሚቀርፈው ነገር ምንድነው? የተጋረደው አይኔን ለመፍታት ከጫፍ ደረስኩ፡፡ 'አረ ማብራሪያው ቡሀላ ይደርሳል!' ብዬ ልጮህ ምንም አልቀረኝም፡፡ በመሀል ዝምታ ሰፈነ፡፡ ጨነቀኝ እየተጫወቱብኝ መሰለኝ፡፡በመቀጠል ቹቹ ከሁዋላዬ ቆማ ጨርቁን ከአይኔ ላይ ልታነሳልኝ ስትሞክር በጣም በመቸኮሌ እኔም አገዝኳት፡፡ በሁለት እጄ አይኔላይ የተሸፈነውን ጨርቅ ገለጥኩት፡፡ ደነገጥኩ! የሆነ ነገር ሰውነቴን ውርር አደረገኝ!
ፍሬ ነው፡፡ አዎ አጠገቤ የቆመው ፍሬ ነው፡፡' አ . . .እ . . . 'ተንተባተብኩ ፡፡ማውራትም አልቻልኩም፡፡ 'ፍ . . . ፍ . . . ፍሬ . . .አን . . ተ' ተንቀጠቀጥኩ ፡፡ምን እንደተሰማኝ እንኳ በቅጡ አላውቀዉም፡፡ ፍሬ ወደኔ ተጠጋ . . . አይኖቼ እንባ አቀረሩ፡፡ እቅፍ አደረገኝእኔም እቅፍ አደረኩት፡፡ ጭምቅ . . .አድርጌ አቀፎኩት፡፡ እንባዬ መውረድ ጀመረ፡፡ አላመንኩም ፍሬን ነው ያቀፍኩት? ቀና ብዬ አይኑን አየውት መልሼ አቀፍኩት፡፡ "እንዴት ግን ይሄንን ሁሉ ቀን ?" አላስጨረሰኝም አንድ ጣቱን ከንፈሬ ላይ አድርጎ "ሁሉንም እርሺው በቃ"አለኝ፡፡ 'እሺ 'አልኩት መልሼ እያቀፍኩት አንገቱ ስር ሽጉጥ ብዬ፡፡ እንባዬ በጉንጬ ላይ ይወርዳል፡፡ "አታልቅሺያ አሁን እኮ አለሁ" አለኝ ፍሬ ጉንጬን በሁለት እጆቹ እየጠረገ፡፡
እኔ የተሰማኝን ደስታ መግለፅ እንኳ አልቻልኩም፡፡ ውስጤ ሰላም አገኘ ፡፡ትልቅ መረጋጋት ነው የተሰማኝ፡፡ ሁሉም ቆመው በደስታ እየተመለከቱን ነበር፡፡ ፍሬ ጉንጬን ከጠረገ ቡሀላ እጄን ይዞኝ ከአንደኛው መቀመጫላይ አብረን ቁጭ አልን፡፡ ሁሉም ተቀመጡ፡፡ የሁሉም ፊት ላይ ደስታ ይነበባል፡፡ እኔም በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ ያ' ሁሉ ጭንቀቴ ወዴት እንደገባ፡፡ ቅልል ነው ያለኝ፡፡ በተቀመጥንበት መቀመጫ ላይ የፍሬን ትከሻ ድግፍ ብዬ በእጆቼ ወገቡን እና ሆዱን እቅፍ እንዳደረኩ እሱም አንገቴን አቅፎኝ እስሩ ሹግጥ ብዬ ሁሉንም ተራ በተራ እመለከታቸው ጀመር፡፡ የሁሉም ፊት ላይ ደስታ ይነበባል፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን ቆማ ትመለከት የነበረችው ቹቹ አሁንም እንደቆመች ናት፡፡ ሁላችንም ቦታ ቦታ ይዘን ክብ ሰርተን ከተቀመጥን ቡሀላ ንግግሩዋን ቀጠለች፡፡"ያው እንግዲ እህታችን ሴና ሰሞኑን ይረብሻት እና ሰላም ይነሳት የነበረው ነገር አሁን ላይ የተፈታ ይመስለኛል፡፡ ይሄንን ደሞ እንድናደርግ ሀሳብ ያመጣችው ሚጣ ስትሆን ሁላችንም በመተባበር አንድ ነገር እናድርግ ባልነው መሰረት ይኸው እንዲህ ሆነ፡፡ ሁላቹም ፈጣሪ ያክብራቹ፡፡ በጣም ደስ ሚል ምሽት ነበር፡፡ እና በቃ አሁን መሽቶአል ወደ ዶርም" አለች ፡፡ በንግግሩዋ መጨረሻ ላይ ሁሉም አጨበጨቡ፡፡ እየተሳሳቅን እና እየተጨዋወትን ትንሽ ከቆየን ቡሀላ ወደ ዶርም መሄድ ጀመርን፡፡
ወደ ዶርም መግቢያ ስንደርስ ፍሬ ሁሉንም ከተሰናበተ ቡሀላ በመጨረሻ ሁለታችን ቀረን፡፡ እንደከዚ ቀደሙ 'ደና ደር ፣ደና ደሪ' ብቻ ተባብለን መለያየት አልቻልንም፡፡ ሊሄድ ሲል ጠራዋለው ፣ልሄድ ስል ይጠራኛል፡፡ በመጨረሻም "በቃ ግቢ በስልክ እናወራለን ብዙ ካመሸው ዶርም ይቅጡኛል" ካለኝ ቡሀላ አቅፎኝ ተሰናብቶኝ ሄደ፡፡ መንገድ እንደሚሄድ ሰው ትንሽ ቆሜ አየሁት፡፡
ዶርም ስገባ በ ላፕቶፕ ዘፈን ከፍተው እየጨፈሩ ዶርሙን አድምቀውታል፡፡ እንኳን ደስ አለሽ እያሉ ሁሉም በተራ አቀፉኝ፡፡ የዶርማችን ፍቅር እውነት ደስ አለኝ፡፡ "ግን እንዴት እንደዚ ልታደርጉ ቻላቹ?"አልኩኝ ከወደበሩ ከሚገኘው አልጋ ላይ እየተቀመጥኩ፡፡ ጭፈራቸውን አቁመው ዘፈኑን ከዘጉ ቡሀላ ሁሉም ቦታ ቦታ ይዘው መቀመጥ ጀመሩ፡፡ ጥያቄዬን ደገምኩት "ግን እንዴት መጣላቹ ይሄ ሀሳብ?" አልኩኝ በፈገግታ የተሞላ ፊታቸውን መልሼ በፈገግታ እየተመለከትኩ፡፡ "የውልሽ ሴና" አለች ሚጣ ተመቻችታ እየተቀመጠች፡፡ "የውልሽ ሴና . . . ."

#ክፍል_ሀያአምስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
Audio
ማሚቴና ከበደ 😂❤️

@geyone
@geyone
​​ሴና ክፍል ሀያ አምስት ❤️

. . . "የውልሽ ሴና እኛ አንድ ዶርም ምንኖር ልጆች እንደ አንድ ቤተሰብ ነን፡፡ አብረን እንማራለን ፣አብረን እንበላለን እንጠጣለን ፣ውሎዋችን አንድ ላይ ነው ፣አዳራችንም አንድ ላይ ነው፡፡ ይሄ አንድ ቤት ውስጥ ማኖሩ እህታማቾች እንኳን ብዙ ግዜያቸውን እንደኛ አያሳልፉም፡፡ እኛ በዚህ ሁሉ ቀናት አብረን እንደ አንድ እናት ልጆች ነበር ስንውል ስናድር የነበረው፡፡ በነዚህ ቀናቶች ደግሞ አንዳችን የሌኛችንን ሁኔታ ለመረዳት ብዙም አይከብደንም፡፡
ሴና ያንቺም ነገር አሁን እንዳልኩሽ ነው፡፡ ተጫዋች ፣ሳቂታ ፣ደስተኛ ፣ንቁ የነበርሽ ልጅ በአንድ ግዜ ያ' ሳቅሽ ሲጠፋ ፣ጭንቅንቅ ስትይ ስታዝኚ ስናይ 'ምን ሆና ነው?' የሚል ጥያቄ ውስጣችን ይፈጠራል፡፡ አብረን እስከኖርን ድረስ ደሞ ያንቺን ደስታና ሀዘን መጋራት ግድ ይለናል፡፡ እናም በቹቹ አነሳሽነት በሁላችንም ተሳታፊነት ችግርሽ ምን እንደሆነ አጣርተን ከደረስንበት ቡሃላ መፍትሄ አግኝተን ይኸው ለዚ ደረስን እልሻለው፡፡" አለች የደስ ደስ ያለው ሳቋን እየሳቀች፡፡
ሚጣ ስታወራ ሁሉም በተመስጦ አተኩሮ ያዳምጡዋት ነበር፡፡ ተናግራ ስትጨርስ ሳናስበው ሁላችንም አጨበጨብን፡፡ ሁሉንም ተራ በተራ ተነስቼ አቀፍኳቸው፡፡ አብሮ መኖር ይኼው ነው፡፡ አንዱ ሌላውን መረዳት ፣አንዱ ስለሌላው ማሰብ፡፡ እውነት ያደረጉት ነገር በጣም ውስጤን ነካው፡፡ሳላስበው የደስታ እንባ አነባው፡፡የዛን ምሽት እየተጫወትን እየተሳሳቅን በእህታማችነት መንፈስ አደርን፡፡
ጥዋት ስነሳ ደስተኛዋ ሴና ሆኛለው፡፡ ነቃ ያልኩ ፣ቀኔን በፈገግታ ምጀምር ፡፡ተጣጥበን ቀርሳችንን በልተን ክፍል ስንገባ ሙሉ ትኩረቴን ትምህርቴ ላይ አድርጌ እከታተል ጀመርኩ፡፡ ወደቀድሞዋ ሴና ተመለስኩ፡፡ ከክፍል ስወጣ ፍሬን አገኘዋለው፡፡ አብረን ምሳ እንበላለን፡፡ ግቢውስጥ ያለኝ ነገር በሙሉ የሚያስደስት ሆነ፡፡
እንዲ እንዲያ እያልን ቀናት ተቆጠሩ ፣ሳምንታትም አለፉ፡፡ የዶርማችን ፍቅር ፣አንድነት ፣ህብር ቀን ከ ቀን እየጨመረ መጣ፡፡ እነ ቹቹ ማምሸታቸውን ሆነ መስከራቸውን አላቆሙም ነገር ግን መጠናቸውን በጣም ቀንሰዋል፡፡ ከበዛ በሳምንት ሶስት ቀን ብቻ ቢያመሹ ነው፡፡ ብዙውን ግዜ የዶርም ልጆች አብረን ማሳለፍ ጀመርን፡፡
ከፍሬ ጋር ያለኝ ቅርርብ በጣም ጥልቅ እየሆነ መጣ፡፡ ቀን በቀን እንገናኛለን ፣ምሽት በስልክ መልእክት እናወራለን ይባስ ብሎ ቫይበር ፣ፌስቡክ እንድጠቀም አድርጎኝ ቅዳሜና እሁድ ቤት ሆኜም እንኳን አብሮኝ ያለ ያህል እንዲሰማኝ ያደርግ ጀመር፡፡ በግቢ ውስጥ ሆነ በውጪ ብዙ ወንዶች ያወሩኛል፡፡ እኔ ለአንዳቸውም ቦታ አልሰጥም፡፡ግቢ ውስጥ ከፍሬ ውጪ ምቀርበው ወንድ ዴቭ ብቻ ነው፡፡ የክፍሌን ወንዶች ክንኳን ከሰላምታ በዘለለ አልፎ አልፎ ለትምህርት ነክ ጉዳዮች ካልሆነ ስለሌላ ነገር አላወራቸውም፡፡ ፍሬ ብዙ ነገሬ እየሆነ መጣ፡፡
ከወራት ቡሀላ የመጀመሪያ መንፈቅ ትምህርት ማለቂያ ፈተና ተፈትነን ከጨረስን ቡሀላ በመሀል ባለን እረፍት ሁላችንም ወደየቤታችን ስለምንሄድ ፈተና ከጨረስን በነጋታው ያለውን ሙሉ ቀን አብረን እንድናሳልፍ ተስማምተን ቀኑን አብረን አሳለፍን፡፡ ምሽት ላይ እኔና ፍሬ ብቻችንን ሆነን ወደ አንድ ተማሪ ወደማይበዛበት ቦታ ሄድን፡፡ ቅዳሜና እሁድ ለሁለት ቀን ቤት ስሄድ ሚናፍቀኝ ልጅ አሁን ደሞ ከሁለት ሳምንት በላይ እንደማላገኘው ሳውቅ ልቤ ይረበሽ ጀመር፡፡
ከቦታው ስንደርስ ከዛፍ ስር የሚገኝ አንድ መቀመጫ ላይ ጎን ለ ጎን ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን፡፡"ሆዴ ለሁለት ሳምንት ልትናፍቂኝ ነው እኮ. . ." አለኝ አንገቴን አቅፎ ወደ ራሱ እያስጠጋኝ፡፡ "እኔም እኮ ትናፍቀኛለክ . . ." አልኩት አንገቱ ስር ሽጉጥ እያልኩኝ፡፡ትንሽ ካወራን ቡሃላ እንዴት እንደሆነ ባላውቅም አንድ ያልጠበኩት ነገር ተፈጠረ፡፡ በመጀመሪያ ደነገጥኩ ሰውነቴ በሙሉ ነዘረኝ፡፡ ከዛ ግን . . .


#ክፍል_ሀያስድስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️
👇👇👇👇
@geyone
@geyone
@geyone
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
​​ሴና ክፍል ሀያ ስድስት ❤️

. . . ከዛ ግን ደስ ሚል ነገር እየተሰማኝ መጣ፡፡ ፍሬ አንገቴ ስር ሲስመኝ ሰውነቴ ይነዝአኝ ጀመር፡፡ ሳላስበው ከንፈሬን ሳመኝ፡፡ መጀመሪያ ደነገጥኩ ግን ማንገራገር አልቻልኩም፡፡ ደስ የሚል ነገር አለው፡፡ ስሜቱ አዲስ ሆነብኝ ግራ ሚያጋባ፡፡ ደስ ሚል እእእእእ...... እኔንጃ ብቻ ወስብስብ ፤ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ተሰማኝ፡፡የመጀመሪያዬ ስለሆነም መሰለኝ እኔንጃ ማልገልፀው አይነት ስሜት ተሰማኝ፡፡ ፍሬ ከሳመኝ ቡሀላ ወደ ጆሮዬ "አፈቅርሻለው!" አለኝ ለሹክሹክታ፡፡ "ሴና አፈቅርሻለው! የኔ ብቻ እንድትሆኚ ፈልጋለው!" አለኝ ጆሮዬን እየሳመኝ፡፡ በጣም ደነገጥኩ ፣ፊቴን ሲያልበኝ ይሰማኛል! የፍሬ ትንፋሽ ሙቀት ጆሮዬን አልፎ ሙሉ ሰውነቴን እያሞቀኝ፡፡ እኔ ለማስቆም ምንም አላደረኩም ፣ሚያደርገውን ከመቀበል ውጪ "ሆዴ በጣም ነው ምወድሽ" አለኝ ፍሬ እቅፍ አድርጎ ደረቱ ላይ ድግፍ እያደረገኝ፡፡
በፍሬ እቅፍ ውስጥ ሆኜ ብዙ ነገር ማሰብ ጀመርኩ፡፡ 'አፈቅርሻለው' ሲለኝ የተሰማኝ ስሜት የደስታ ይሁን የድንጋጤ አላውቅም፡፡ ምንም መልስ አልሰጠውትም፡፡ በፍሬ እቅፍ ውስጥ እንዳለው ስልኬ ጠራ ወንድሜ ነበር፡፡
ከፍሬ ራቅ ብዬ ወንድሜን ካወራውት ቡሀላ ሰአቱም ስለመሸ ከፍሬ ጋር ተያይዘን ወደ ዶርም መሄድ ጀመርን፡፡ ወደ ዶርሜ ስደርስ ፍሬን እቅፍ አድርጌ ጉንጩን ሳምኩት፡፡ እሱ እጁን ኪሱ ከቶ እንደቆመ ነበር፡፡ ፍጥነቴ የገረመው ይመስላል፡፡ ቻው ከተባባልን ቡሀላ ወደ ዶርሜ ሄድኩ፡፡ ዶርሜ እንደገባው ሁሉንም ጉዋደኞቼን ደስታ በተሞላው ሁኔታ ሰላም ካልኳቸው ቡሀላ አልጋዬ ላይ ወጥቼ ጋደም አልኩ፡፡
"አፈቅርሻለው!" የፍሬ ድምፅ በውስጤ እየተመላለሰ ነው፡፡"አፈቅርሻለው!" አልፎ አልፎ የሳመኝ ከንፈሬን አጣቴ እየዳበስኩ ፈገግ እላለው፡፡ ምሽቷን እያሰበኩ በሀሳቡ ወደ ፍሬ ሄጃለው፡፡ ፍሬ በዚ ሰአት ምን እየሰራ ይሆን? እሱስ ምን እያሰበ ይሆን? ሀሳቤ እንዳለ ፍሬ ሆነ፡፡ አልጋዬ ላይ እየተገላበጥኩ ፍሬን ብቻ አስበዋለው፡፡ እነ ሚጣ ዝም ብለው ይታዘቡኛል፡፡ እኔ በሀሳብ ፍሬ ጋር ሄጃለው፡፡
"አንቺ ልጅ አረ ወደራስሽ ተመለሽ ፍንድቅድቅ አልሽ እኮ፡፡" አለችኝ እኑካ ወደ ቤት ምትወስዳቸውን እቃዎች እያስተካከለች፡፡ "አዎ ምን ተገኝቶ ነው እስኪ?" ሁሉም የተለመደ ጥያቄያቸውን አከታተሉብኝ፡፡ "አረ ረፍት ስለደረሰ ነው፡፡ ሌላ ምንም አይደለም"ብዬ ጉዳዩን ካደባበስኩ ቡሀላ ጨዋታ ለማስቀየር ሞከርኩ፡፡ስለ ሌላ ነገሮች ማውራት ስንጀምር ስልኬ መልእክት ገባ፡፡ ፍሬ ነው የላከልኝ መልእክት ግን በፊት ከሚልክልኝ የተለየ ነው፡፡ ጋደም ካልኩበት ቀና ብዬ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ መልእክቱ እንዲህ ይላል"ሴና ገና የመጀመሪያ ቀን ካገኘውሽ ግዜ ጀምሮ ላንቺ ለየት ያለ ነገር ነበረኝ፡፡ በቀረብኩሽ ቁጥር ደግሞ ይበልጥ ነው የወደድኩሽ፡፡ ያኔ ትዝ ይልሻል . . . " ሚጣ ስልኬን ነጠከችኝ፡፡ አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ እያነበብኩት ሲጠሩኝም አልሰማውም ሚጣ መጥታ ስልኬን እስክትቀማኝ ድረስ በ ፍሬ ፅሁፍ ላይ አተኩሬ ሚያደርጉትን አልሰማውም ነበር፡፡
የተነጠኩትን ስልኬን ለመቀበል ብሞክርም ማይቻል ሆነብኝ፡፡ ያለኝ አማራጭ መለመን ብቻ ነው፡፡ "እኛ ሰው አይደለንም? ስልክሽ ላይ ምን ቢኖረው ነው እንደዚ እስክትተሪ የማትሰሚን?" ሚጣ ስልኬን እንደያዘች በንዴት ስሜት ትተይቀኝ ጀመር፡፡ "አረ እኔ እንደዛ አይደለም . . . እኔኮ እ. . ." አላስጨረሰችኝም "ቆይ ምን ተልኮልሽ ነው ? ልየው እስኪ "ብላ ስልኬን መክፈት ጀመረች፡፡ "እንዴ እንደዛማ አይሆንም የውልሽ ሚጣ " መከራከር ጀመርኩ"ይከፈት አይደል?" ሁሉንም በአንድነት ጠየቀቻቸው፡፡" ሁሉም በአንድነት "ይከፈት ! ይከፈት! " በአንድ ድምፅ ዶርሙን ሌላ ድባብ ፈጠሩበት፡፡ ልመናው አልሳካ ቢለኝ ተስፋ ቆርጬ ቁጭ አልኩ፡፡ ሚጣ የተላከችልኝ መልእክት ከፈፈተች "ላንብበው"ላንብበው?" አለች ጮክ ብላ "አዎ ይነበብልን!" ሁሉም ተስማሙ ሚጣ ለማንበብ ጉሮሮዋን ስላ ከተዘጋጀች ቡሀላ . . .

#ክፍል_ሀያሰባትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

https://telegram.me/geyone

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓


🖤 የልቤ ሰራቂ 💔

የውበቷ እንቁ ውቧ ፅጌረዳ
ደምቃ እንደወጣች ገና በማለዳ
አብራት ከወጣችው ከፀሀይዋ ልቃ
ልቤን ወሰደችው ካካሌ ፈልቅቃ
የምን ልቤ ብቻ የምን አካላቴ
በፍቅሯ የነደደው መላ እኔነቴ

የፍቅር ጀግናናት አይደፍሩትን ደፋር
ጥልፉ የጣለችኝ በውበቷ አድባር
ከልቤ ካንጀቴ እኔ እዬወደድኳትሰታ
በፍርሃት ተውጬ ፍቅሬን ስገልፅላት
በፈጣሪ ፀጋ በውበቷ ኮርታ
አሻፈረኝ ብላ ሄደች ጀራባ

የወንድነቴ ጥግ ተሰበረ ወሽመጡ
የማረገው ጠፋኝ አልገባኝም ቅጡ
ኸረ ወቸው ጉዴ አሁን ምን ተሻለኝ?
ከሷ ተነጥዬ መኖር አይቻለኝ
ቀን በቀን ስናፍቅ ልቤ ሲፈልጋት
እንዲው ጥላኝ ስትሄድ ፍቅሬ አልከበዳት
በፍቅሯ ብመንን ካአጀብ ተነጥዬ
መቼም አልጫናት የኔ ሁኚ ብዬ
ውደደኝ ሳትለው ልቤ ከወደዳት
እንዴትስ አድርጌ ሸንጎ ልገትራት
ቀንቶኝም የማያወቀው ደርሶ የኔ ዕጣ
እሷን አገኝ ብዬ እኔው ራሴን ልጣ?

ቶፊቅ መሀመድ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘


➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢
 Rip😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭ያማል
😭😭😭የት ነህ ዶክተር አብይ።።።።።።😭😭

እጨት ቁጭ ብሎ ሰው እየነደደ
ህግ አዋቂው ቆሞ ሌባ እየፈረደ
አሳ መረብ ጥሎ ሰው እያጠመደ
አንበሳ በጅቦች እየተሳደደ
የእርግቦች ማህፀን ጊጥ እየፀነሰ
ሰማይ ጭስ አርግዞ እሳት እያፈሰሰ
ሰው እየተጋዘ አውሬ እየነገሰ
ካህናት ተወግዘው ሌባ እየቀደስ
እምዬ ማቅ ለብሳ ልጅ እየደነስ
ይህ ሁሉ ሲሰራ መላው ጠፍቶን እኛ
ኧረ ወዴት ገባህ የሰማዩ ዳኛ


ፍትህ በግፍ ለተገደሉት ሰወች rip ነፍስ ይማር

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
☞☞ ከደራሲያን አለም
የአለም እውነታዎች!!

❍✰✰✰✰✰◉⚇◉✰✰✰✰✰❍

የያዝከው ነገር በቂ መስሎ ካልታየክ፤ድፍን አለምን ብትጨብጥ እንኳን፤ሀዘንተኛ እንጂ ደስተኛ መሆን አችልም፤እናም ባለህ ነገር ፈጣሪን አመስግነህ ኑር።
የሰው ዋጋው እየቀነሰ የዶሮ እና የእህል ዋጋ እየጨመረ ሲመጣ በርትተህ ፀልይ ፡፡
ሰዎች ስለ አንተ መጥፎነት ቢያወሩ አይድነቅህ ምክንያቱም ውሾች በማያውቁት ሰው ላይ ነው የሚጮሁት::

┈┈┈┈◎◎❍❍┈┈┈┈

✎ ጨውን ሺ ጊዜ ስኳር ብትለው ስሙን እንጂ ጣአሙን መቀየር አችልም።
✎ ከክፋት ስትርቅ ሰላምህን ታበዛለህ፤ቅንና መልካም ስትሆን ደሞ ከጭንቀትና ከጸጸት ትድናለህ።
✎ በሕየውትህ ሰዎችን ለመረዳት እንጂ ለመጉዳት አታስብ።
✎ ፍቅርና መልካምነት ከቃል ይልቅ መተግበርን ይፈልጋል።
✎ የውሸት ጎደኛ እና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ ሁለቱም ፀሐይ እስካሉ ድረስ ነው።

┈┈┈┈◎◎❍❍┈┈┈┈

☛ የፈጣሪ ስዕል እያልክ ስትስም ራሱ ፈጣሪ አክብሮ የፈጠረውን ሰውን ግን ረግጠህ በማለፍህ የወጣልህ አስመሳይ መሆንህን እወቀው፡፡
☛ ውሾች እና ድመቶች አልጋህ ላይ እንዲዘሉ እየፈቀድክ ድሆች ግን የግቢህ ድንጋይ ላይ እንዲቀመጡ ባለመፍቀድህ የፈጣሪህን ምህረት ጠይቅ፡፡
☛ ከዚህ አፍ እና ልብ ከተለያዩበት ቲያትረኛ ማንነትህ ፈጥነህ ውጣ ፡፡
⚠️የሳቀልኝ ሁሉ ስው እየመሰለኝ ጠላቴን ስጠብቅ ወዳጄ ገደለኝ😭
⚠️ ሰዎች ሆይ የሚቀድመውን ብናስቀድም የማይተወን ፈጣሪ ይከተለን ነበር ፡፡
 
📝 ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!!
══════❁✿❁ ═════

https://telegram.me/geyone
•፨•፨•፨•፨•፨• ታስበላብሃለች •፨•፨•፨•፨•፨•

በአንድ ገጠራማ በሆነ ስፍራ የሚኖሩ ቤተቦች ነበሩ ከቤተሰቡም ወንድ ልጁ የቤተሰቡን በጎች ይጠብቅ ነበረ:: ነገርግን ልጁ ሁልጊዜ በጎቹን ወደመስክ አሰማርቶ ትቷቸው ይመጣ ነበረ:: አባቱም በጎቹን ለማን ጥለሀቸው መጣህ ሲለው "ዛሬ ለቅዱስ ሚካኤል ሰጥቼው መጣሁ" ይላል በሌላ ቀንም ሲጠይቀው" ዛሬ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጥቼ መጣሁ" እያለ በልበ ሙሉነት ይናገር ነበረ:: እውነትም እንዳለው ተመልሶ በጎቹን ሲወስድ ከቁጥር ሳይጎድሉ አውሬ ሳይተናኮላቸው ያገኛቸው ነበረ:: አንድ ቀንም እንደለመደው በጎቹን መስክ ላይ ትቶ ይመጣል:: አባቱም "ዛሬስ ደሞ ማንን አስጠብቀህ መጣህ" ብሎ ጠየቀው ልጁም በኩራት" ዛሬ ለድንግል ማርያም ሰጥቻቸዋለሁ::" በማለት ተናገረ አባቱም"እሷስ ታስበላብሃለች" አለው:: ልጁም" እንዴት?" ብሎ ሲጠየቀው "እሷ ርህርህት ስለሆነች የተራበ ጅብ ቢመጣ በጎቹን እንዲበላ ትፈቅደለታለች ስለዚህ ታስበላብሃለች" አለው ይበባላል::


፨•፨ ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰማይን ሰሌዳ አድርገን ብንፅፍ እንኳን ልንጨርሰው አንችልም ይሁንና ውዳሴዋን አናቋርጥ ዘወትር እንትነጋ።
Forwarded from መርጌታ ላቀው የባህል መድሐኒት ቀማሚ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Rahel Getu
እቴሜቴ
Join
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
━━━━━━━━━━━━
══•ೋ•
እንዳሰብነው ባይሆንም እንዳሰበልን አኑሮናል ለፈጠረን አማላክ ለድንግል ማሪያም ልጅ ለአማኑኤል ክብር ምስጋና ይድረስው ...🙏ከዘመን ዘመን አድርሶናል እና ክብር ለፈጣሪ ይሁን ።
አሜን 🙏🙏


ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን: የኛ ማማር በሀገራችን ነውና።አዲሱን አመትም ሰርተን የምንበለፅግበት :ተምረን የምንለወጥበት: አዲስ መንፈሰን ፈጣሪ ይሰጠን ዘንድ እንለምናለን:..💞💞💞

መልካም አዲስ አመት!!!!!


🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻💐💐💐🌻🌻
🌻🌺 እንኳን 🌺🌻
🌻🌹አደረሳችሁ🌹🌻
🌻🌻🌾🌾🌾🌻🌻
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻 አዲስ 🌻🌻 2014 ዓ.ም
🌻🌻 ዓመት 🌻🌻️
🌻️🌹🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊

👇👇👇👇👇👇👇❤️❤️👇👇
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
💚💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️ 🌾🌾💐💐💐🌹🌹🌹🌞🌻🌞🌻