ሴና ክፍል አሥራ አምስት
. . . .ሁለት አለም ቤት እና ትምህርትቤት ፤ ቤት ውስጥ ያሁሉ ቁጥጥር ሰው ሁሉ ሚስጥር ሆኖ በወስጤ የተሳለበት ውጪ ነፃ አለም ከየት ወዴት ጥያቄ የሌለበት . . .
እቤት ስደርስ እናቴ እና አባቴ ቁጭ ብለው እየጠበቁኝ ነበር፡፡ ሰራተኛችን ብና እያፈላች፡፡ ከሩቅ እንደመጣ እንግዳ ሻንጣዬን ተቀብለውኝ አቅፈው ስመው ካስቀመጡኝ ብሀላ ሻማ በርቶ አባቴ በስሜ ዳቦ ቆረሰ፡፡ "ተመስገን ፈጣሪ ልጄ ለዚህ ስላበቃህልኝ፡፡" ሲል ፀሎቱን አደረሰ፡፡ አባቴ እኔን ለማግኘት ብሎ አለወትሮ ከስራ እንደቀረ ገብቶኛል፡፡ እናቴም መርቃ ምግብ በልተን ቡና ጠጥተን ስለ ግቢው እና ስላጋጠሙኝ ነገሮች ማውራት ጀመርኩ፡፡ እነርሱ ማውቅ ያለባቸውን ማወቅ በሚገባቸው አማርኛ፡፡
ከእናት እና ከአባቴ ጋር ካወራሁኝ ቡሀላ ክፍሌ ገብቼ ተኛው፡፡ ካሁኑ ግቢ ናፈቀኝ፡፡ ስልኬን አስሬ እያወጣው አያለው፡፡ቀኑ ረዘመብኝ ክፍሌ ውስጥ አንዴ መፅሀፍ ሳገላብጥ አንዴ ጋደም ስል ቀኑ አላልቅ አለኝ፡፡ ልዪነቱ አሁን ይበልጥ ታየኝ፡፡ በፊት ለመሄድ ምጓጓለት ስላልነበረኝ ቤት ስውል ምንም የተለየ ስሜት የለኝም፡፡ አሁን ግን እስርቤት ያለው ያህል ነፃነቴን የተገፈፍኩ ያህል ጨነቀኝ፡፡ ተንቆራጠጥኩ፣ ሰኞ ናፈቀኝ፡፡
አመሻሽ ላይ ወንድሞቼ መጡ፡፡ ገና ሰላምታ ከመለዋወጣችን የጥያቄ መአት ወረደብኝ፡፡ "ዶርም ያሉ ልጆች እንዴት ናቸው? ምንድናቸው? ሀይማኖታቸው? ከየት ነው የመጡት? ፀባያቸው እንዴት ነው? ክፍል ውስጥ ምን አይነት ልጆች ናቸው ያሉት? ምንምን ተማርሽ? ረፍት ግዜሽን ከማን ጋር ነው ምታሳልፊው? የት ነው ምትመገቢው? ምንድነው ምትመገቢው? . . ." አረ ለማስታወስ የሚያዳግቱ የጥያቄ እሩምታ ወረደብኝ፡፡
ለሁሉም ጥያቄ ምላሽ መስጠት ጀመርኩኝ፡፡ ማወራው አብዛኛው ውሸት እና እነሱ መስማት ሚፈልጉትን ነው፡፡ መቼስ ስሐማሳለፈው ውሉ ብነግራቸው . . .ሆሆሆ ብቻ ወንድሞቼ ተምረዋል ግን ለምን አስተሳሰባቸው እንደዚ እድደሆነ አልገባኝም፡፡ ነገሮችኝ ከአሉታዊ ጎን ነው ሚረዱት፡፡ ዛሬ አንድ ነገር ገባኝ ለካስ እማዬ እና አባዬ በወንድሞቼ አስተሳሰብ ውሰጥ ሆነው፡፡ ቅድም ሁለቱ ብቻ የነበሩ ሰአት ሁሉንም ነገር በቀላሉ ነው የጨረስነው፡፡
"አንድ እኛ መስራቤት ሚሰራ ሰው የሱ ልጅ እናንተጋ ነች፡፡ ስልኳን ሰጥሻለው ሰኞ ተገናኙ አብራቹ ሁኑ፡፡" አለኝ ወንድሜ በአውንታ ምላሽ ጭንቅላቴን ነቀነኩኝ፡፡ 'ምን ማለቱ ነው ግን እኔ ህፃን አይደለሁም ከምፈልገው ሰው ጋር ነው በምፈልገው ግዜ ምሆነው፡፡ ምናልባት የመስራቤታቸውም ሰው የወንድሜ ብጤ ይሆናል፡፡' ብዬ አሰብኩ፡፡ አመሻሽ የተጀመረ አሰልቺ ውይይት እስከ ምሽት ሁለት ሰአት ነበር የቀጠለው፡፡ "አረ ይበቃቹሀል እራት ብሉ ተነሱና፡፡"አለች እናቴ ትልቅ የነፃነት ድምፅ የሰማው ያህል ነው የተደሰትኩት፡፡ እናቴ መጥታ ባትገላግለኝ ኖሮ ጭቅጭቅ የሞላበት ነዝናዛ ውይይት ሚያልቅ አይመስለኝም፡፡
በጠረቤዛ ዙሪያ ቀርበን እራት መመብ ስንጀምር ስልኬ ጠራ አይቼ ዘጋውት፡፡ፍሬ ነበር የደወለው "ማነው እሱ!? ማነው በዚህ ሰአት!?" ወንድሜ ተቆጣ፡፡ "አይ ከዶርም ነው የተደወለው ጉዋደኛዬ ነች፡፡"አልኩት ረጋ ባለ ድምፅ፡፡ "አምጪው እስኪ ስልኩን ስነስርአት የላተም በዚህ ሰአት ምን አስደወላት?" ስልኩ ጠረቤዠ ዛው ላይ እንዳለ ወደወንድሜ አስጠጋውት፡፡ መልሶ ጠራ ወንድሜ አይቶት ዘጋው፡፡ ምንም አልተናገረም፡፡ መጀመሪያም ለምን እንደተቆጣ ታውቆኛል፡፡ ወንድ ነው የደወለው ብሎ ነው፡፡ እኔ የቤተሰቦቼን ፀባይ መች አጣሁት የሁሉንም ስልክ በሴት ስም ነው የመዘገብኩት፡፡ ስልኬ ሲጠራ ስሙ 'ሴና 3' ነው ሚለው ሴና ስለሚል የዶርም ልጅ ናት ብሎ ነው ወንድሜ ዝም ያለው እኔ ግን ፍሬን ነው ሴና 3 ብዬ የመዘገብኩት፡፡
ባለፉት ቀናት የነበረው እራት እና የዛሬው ተለየብኝ፡፡ ለካ ሁሉም ነገር በፍቅር ሲሆን ይጣፍጣል፡፡ ቤት ውስጥ ብዙ አይነት ምግብ ቀርቦ እየተመገብን ምንም ጣእም አልሰጥሽ አለኝ፡፡ አነ ፍሬ ጋር ተሻምቼ ምበላው ነው የጣፈጠኝ፡፡እራቴን ጨርሼ ክፍሌ እስክገባ ቸኩያለው . . .
#ክፍል_አስራስድስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️
https://telegram.me/geyone
,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••

ሴና ክፍል አሥራ ስድስት ❤️
. . . እራት ከተነሳ ቡሀላ ወደ ክፍሌ ገባው፡፡ የክፍሌን በር ከውስጥ ዘግቼ አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ ለፍሬ መልእክት ላኩለት፡፡እስኪመልስልኝ ድረስ ስልኬ ላይ እንዳፈጠጥኩ በጭንቅላቴ ብዙ ጥያቄዎች ይመላለሳሉ፡፡ ለምንድነው ወንድሞቼ ግን እንደዚ ሚያስቡት ግን፡፡ ምንድነው እንደዚ ተጠራጣሪ ያደረጋቸው? ምነናልባት እነርሱ ሚያደርጉት ነገር ይሆን? የፍሬ መልእክት ገባልኝ፡፡ ከሀሳብ መንፈስ ወጣሁ ገና መልእክቱ ሲገባ ደስ የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡
አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ ከፍሬ ጋር ማውራቴን ተያያዝኩት፡፡ አሰልቺ ቀን ነበር ያሳለፍኩት፡፡ በፊት ምንም የማይመስለኝ የወንድሞቼ ጭቅጭቅ ዛሬ በጣም መረረኝ፡፡ ብቻ ፍሬን ሳወራው ማምሻዬን የካሰኝ መሰለኝ፡፡
ጥዋት ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ የወንድሜ ጥሪ ነበር፡፡ በሩን እየደበደበ ሲጠራኝ ውጪ አደጋ የተፈጠረ ነው ሚመስለው፡፡ በሩን ስከፍትለት "ምን መሆንሽ ነው ሰአትሽን አይተሻል? ቆይ ምን ስትሰሪ አምሽተሽ ነው ይህን ያህል?" ወንድሜ አምባረቀብኝ፡፡ ስልኬን አንስቼ ሰአቴን አየሁ 2:30 አካባቢ ነው፡፡ ቢሆንም ግን እንደዚ ሚያስጮህ ነገር የለውም፡፡ምንም አላልኩም ተጣጥቤ ቁርሴን ከበላሁ ቡሀላ ክፍሌን ማስተካከል ጀመርኩ፡፡
ነገ ደርሶ ወደግቢ እስክመለስ ቸኩያለው፡፡ በፊት ምንም የማይመስለኝ ቤት አሁን ግን ነፃነቴን በእጅጉ እንደነፈገኝ ነው የተሰማኝ፡፡ ይዤ የምሄደውን ልብስ እና አንዳንድ መፅሀፍትን በሻንጣዬ ማስተካከል ጀመርኩ፡፡ እንደው ዛሬ ሂጂ ቢሉኝ ትልቅ ደስታ ነው ሚሰማኝ፡፡ ሻንጣዬን አስተካክዬ እንደጨረስኩ ተጣጥቤ ሳሎን ቁጭ ብዬ ቲቪ ማየት ጀመርኩ፡፡ አስር ግዜ ቀና እያልኩ የግድግዳ ሰአት እመለከታለው ሰአቱ አልሄድ አለኝ፡፡ መቼ ነግቶ ከዚህ ቤት እንደምወጣ እያሰላሰልኩ ስልኬ ጠራ፡፡ ከዶርም ነው አንስቼ ሶስቱንም የዶርም ጉዋደኞቼን ተራ በተራ አናገርኳቸው፡፡ ትንሽ ዘና አደረጉኝ ስልኩን ስዘጋው ግን ያ' ድብርት መልሶ ወረረኝ፡፡
እንደለመድኩት ከቤት ሳልወጣ መሸ፤ የተለመደው ምሽት ፣የተለመደው ወሬ ፣የተለመደው እራት ከእራት ብሀላ ክፍሌ ልገባ ስል ትልቁ ወንድሜ ወዴት ነው ምትሮጪው ነይ ቁጭ በይ እናውራ እንጂ አለ፡፡ አልተቃወምኩም ቁጭ ብዬ ሚሉትን መስማት ጀመርኩ ብዙም ሳይቆይ ስልኬ መልእክት ገባ፡፡ መክፈት ግን አልቻልኩም፡፡ ከዚህ ብሀላ ሀሳቤ ወደ ስልኬ ነው፡፡ ቤተሰቦቼ ያወራሉ ይስቃሉ አልፎ አልፎ ለሚጠይቁኝ ጥያቄ መልስ ከመስጠት ውጪ ሀሳቤ ስልኬ ላይ ነው፡፡ ምንም እየተከታተልኳቸው አይደለም፡፡ ወሬያቸው ሚያልቅበት ሰአት ናፈቀኝ፡፡ እንቅልፉ እንደመጣ ሰው መንጠራራት እና አይኔን ማሸት ስጀምር እናቴ "እንቅልፍሽ መጣ መሰለኝ በቃ ግቢና ተኚ፡፡" አለችኝ 'እናቴ ስወድሽ እኮ ነፃነቴን ሰጠሽኝ' እያልኩ በሆዴ ሀሳባቸው ሳይቀየር ፈንጠር ብዬ በመነሳት ስልኬን ይዤ ፈጥኜ ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡
የፍሬን መልእክት መለስኩለት ነገር ግን ሰአቱን ሳየው በጣም መሽቶአል እኩለ ለሊት ሊሆን ምንም አልቀረውም፡፡ 'እነዚ ሰዎች ዝም ብል ኖሮ አስቀምጠው ሊያሳድሩኝ ነበር ማለት ነው?' አልኩኝ በሆዴ፡፡ ፍሬን ትንሽ ጠብቄው እንቅልፌን መቋቋም ስላልቻልኩ ተኛሁኝ፡፡
ዛሬ ሰኞ ነው በጣም ደስብሎኛል፡፡ ወደ ግቢ ልሄድ ነው፡፡ በለሊት ነው የተነሳሁት ደሞ፡፡ ቁርስ እንድበላ ባያስገድዱኝ ኖሮ እንደተነሳው ተጣጥቤ ለባብሼ ያዘጋጀውትን ሻንጣ ሸክፌ ከዚ ቤት ሹልክ ማለት ነበር የፈለኩት፡፡ የኛ ቤት ቁርስ ጣጣው ብዙ ነው ፡፡ ይረፍድብኛል ብልም ወንድሜ ግቢ በር ድረስ አደርስሻለው ስላለ ምንም ማድረግ አልቻልኩም፡፡
ቁርስ እንዳለቀ ከወንድሜ ጋር ወጣን የተለመደውን ጭቅጭቅ እና ንዝንዝ የቀላቀለ ምክሩን እየመከረኝ ነው፡፡ አትኩሬ ባላዳምጠውም አልፎ አልፎ ሰማዋለው፡፡ ወደ ግቢ በቀረብኩ ቁጥር የነፃነት ስሜት ይበልጥ እየተሰማኝ ነው . . .
#ክፍል_አስራሰባትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

ሴና ክፍል አሥራ ሰባት ❤️
. . . ወደ ግቢ በቀረብኩ ቁጥር የነፃነት ስሜት እየተሰማኝ ነው፡፡ እውነት ይሄንን ሁሉ ግዜ ቤት ውስጥ ታስሬ መቆየቴ አሁን ይቅጨኝ ጀምሮአል 'በጣም ተበድያለው ማለት ነው' አልኩኝ፡፡
ግቢ በር ስደርስ ወንድሜ "የመስራቤት ባልደረባዬ ነች አግኛት" ያለኝን ልጅ ሳላገኛት እንዳልውል አስጠንቅቆ ስልኳን ሰቶኝ ተሰነባብተን እኔ ወደ ግቢ እሱ ወደ ሚሄድበት ፡፡ ኡፍፍፍ ተመስገን ተገላገልኩ፡፡ እስከ ቅዳሜ ድረስ ነፃ ሆናለው ማለት ነው በቃ፡፡ የደስ ደስ እየተሰማኝ ወደ ዶርሜ መሄድ ጀመርኩ፡፡
ዶርም ስገባ ሶስቱ ሰካራም ልጆች በየአልጋቸው ላይ ተኝተዋል፡፡ 'እነዚህ ልጆች ግን አይማሩም? ቆይ ከየት ነው የመጡት? ምንድነው ስራቸው? ከማን ጋር እየዋሉ ነው እንደዚ ገና ትምህርት ተጀምሮ ወር እንኳን ሳይሞላው እንደዚ የሆኑት? ከዚ በፊት ይተዋወቃሉ ወይስ እዚ ከገቡ ነው የተዋወቁት?' ዶርም ውስጥ ቆሜ በትዝብት እየተመለከትኳቸው ራሴን ብዙ ነገር መጠየቅ ጀመርኩ፡፡ ባዋራቸው እና ብጠይቃቸው ደስ ይለኛል፡፡ ብቻ እስኪ ቆይ ሻንጣዬን እንዳስቀመጥኩ ለሚጣ ደወልኩ አታነሳም፡፡ ሰአት ስመለከት ሶስት ሠዓት አልፎአል፡፡ ክፍል ገብተዋል ማለት ነው ብዬ አሰብኩ፡፡ ወደ ክፍል ልሄድ አስቤ ከዶርም እስከ ክፍል ያለውን መንገድ አስቤ ተውኩት፡፡
ዶርም ውስጥ ቁጭ ብዬ ምሰራው ሲጠፋኝ ካመጣዋቸው መፅሀፍት ውስጥ አንዱን አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ወዲያው ግን ማንበቤን አቆምኩ ፡፡ለምን እንደሆን እንጃ ማንበብ መፃፍ ሚባሉ ነገሮች ሰሞኑን እያስጠሉኝ ነው፡፡ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ስልኬን መነካካት ጀመርኩ፡፡
ስልኬን እየነካካው ከሶስቱ ልጆች መሀል አንደኛዋ ተነሳች፡፡ ከአልጋዋ ወርዳ እየተንጠራራች "አንቺ አለሽ እንዴ? የት ጠፍተሽ ነው?" አለችኝ ገና ከእንቅልፍ ባልተላቀቀ ድምፅ፡፡ 'አረ አልጠፋሁም አለሁ'አልኳት ደንገጥ እንደማለት ብዬ፡፡ መኖር አለመኖሬን ታውቃለች ማለት ነው? ምንተዋወቅ ምንነጋገር ነው ሚመስለው ሰላምታ አጠያየቁዋ፡፡ "ምነው ክላስ አልሄድሽም?ረፍዶብሽ ነው?" አለችኝ፡፡ "አዎ ከቤት ስመጣ አርፍጄ ነው የደረስኩት" አልኳት፡፡ "እናንተ ለምንድነው ያልገባችሁት?" እኔም መልሼ ጠየኳት፡፡ "ስራ አድረን ነው ውዴ ጥዋት እኮ ነው የመጣነው እኔ ስለራበኝ ነው የተነሳሁት፡፡" አለችኝ ሳጥኗን ከፍታ ልብስ እያወጣች፡፡ ' የምን ስራ?' ብዬ ለመጠየቅ አልፈለኩም፡፡ "ቁርስ በልተሻል? " አለችኝ፡፡ ከቤት ስወጣ እንደበላው ነገርኳት፡፡ ተጣጥባ ልብሷን ቀይራ ልትወጣ ስትል ዶርም ከምቀመጥ አብሬያት እንድሄ ጠየቀችኝ፡፡ መጀመሪያም መሄጃ ስላልነበረኝ እንጂ ዶርም መቀመጥ አልፈለኩም ነበር፡፡ ሳላቅማማ ተከትያት ወጣሁ፡፡
" የሀዋሳ ልጅ ነሽ ማለት ነው?" አለችኝ፡፡ እኔም መለሰኩላት፡፡ ስለቤተሰቦቼ አንዳንድ ነገሮችን እየጠየቀችኝ እኔም ማወቅ ባለባት መንገድ እየነገርኳት ካፌ ደረስን፡፡ እኔን ስጥጠይቀኝ አልበላም ብላትም "ምሳ ሰአት እየደረሰ በመሆነ ምሳ ይሆንሻል አትግደርደሪ ምን ትበያለሽ?" አለችኝ፡፡ ምፈልገውን አዝዤ አብረን መመገብ ጀመርን፡፡ በዚህ መሀል ጨዋታ ጀመርን፡፡እነ ሚጣ ሲደውሉልኝ ምሳ ጋባዥ እንዳገኘው ነግሬያቸው ቡሀላ ለመገናኘት ተስማምተን ወደ ጨዋታዬ ተመለስኩ፡፡ "ግን ምንድነው ምትሰሪው?" አልኩዋት መቀራረባችን ድፍረት ስለሰጠኝ፡፡ "ቡዙ ነገር ነው ምሰራው፡፡ አንቺ ስራ ትሰሪያለሽ ወይስ ትምህርት ብቻ?" "አይ እኔ መማር ብቻ ነው ስራዬ" አልኳት፡፡ ብዙ ነገሮችን አወራን፡፡ ደስ ትላለች ቀለል ያለች ተጫዋች ልጅ፡፡ ሰክረው ሲሳሳቁ ሳይ የሆኑ መጥፎ ልጆች ነበር የመሰሉኝ አሁን ግን ቀርቤ ሳያት ከገመትኳት ተለየችብኝ፡፡ ምናልባት የቀሩት ሁለቱም እንደገመትኳቸው ሳይሆን እንደሷ ጥሩዎች ይሆናሉ ብዬ አሰብኩ፡፡ በጨዋታችን መል 'እኛ አራታችን የዶርም ስም አለን እናንተን ግን ማን ብለን እንደምንጠራ ማለቴ የቤት ስም ወይም ቅጽል ስም . . . ' "ቹቹ ፤ቹቹ ነው የቤት ስሜ" አለችኝ ወሬዬን ሳታስጨርሰኝ፡፡ የጉዋደኞቹዋን ስጠይቃት እነሱ ራሳቸው ቢነግሩኝ እንደሚሻል ነግራኝ "ከኔጋ እንደነበርሽ ግን ለጉዋደኞችሽ አትንገሪያቸው፡፡" አለችኝ ለምን ብዬም አልጠየኳትም ምናልባት ዶርም ውስጥ ፀበኞች ስለሆኑ ይሆናል ብዬ ነው ያሰብኩት፡፡ እንደማልነግራቸው ቃልገብቼላት እኔ ወደጉዋደኞቼ እሷም ወደ ዶርም ተለያየን፡፡
ዛሬ በደንብ ተምረዋል ስለ መምህሩ እና ስለ ተማሪዎቹ እየተጨቃጨቁ ደረስኩባቸው፡፡ ብዙ ቀን ተለያይቶ እንደተነፋፈቀ ሰው ሰላምታ ተለዋውጠን ተበላቀልኳቸው፡፡ እኔ ከመምጣቴ ብዙም ሳይቅይ ዴቭ መጣ፡፡ሰላምታ ከተለዋወጥን ብሀላ 'ፍሬስ?' ብዬ ጠየኩት፡፡ "ባክሽ ከሚስቱ ጋር ነው አናዳዋለች ደሞ" አለኝ፡፡ ደነገጥኩ ለምን እንደሆነ አላውቅም ግን ውስጤ በጣም ጭንቅንቅ ሲል ታወቀኝ፡፡ "እሷ ደሞ አበዛችው እዚም መጥቶ አትፋታውም ቆይ ለምን አዲሷን አይዛትም ሁለት ምን ያደርግለታል? አለች ሚጢጢ ወደ ዴቭ እያየች፡፡ ጭራሽ 'ሁለት ሚስት?' አልኩ በሆዴ፡፡ "አረ ከ አሮጊቷ ጋርማ በጣም የቆየ ታሪክ ነው ያለው በቀላሉ ሚፈታት አይመስለኝም፡፡ይልቅ አዲሷን ቢተው ይመርጣል፡፡"አለ ዴቭ፡፡
ቅናት ይሁን ንዴት ብቻ አላውቅም ውስጤ በጣም ተረበሸ እንዴ ግን ምንድነው እንደዚ ሚያደርገኝ ሳምንት ላወኩት ልጅ? አላውቅም የተወሳሰበ ስሜት ነው ሚሰማኝ የተደላለቀ . . .
#ክፍል_አስራስምንትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👍😍👍
@geyone

"ትዝታ ፣ ናፍቆት ፣ ህመም"
ያምናው በሽታዬን
ያምናው ትዝታዬን ማነው የቀሰቀሰው
ትናፍቀኝ ጀመር የማልናፍቃት ሰው።
ክራሬን አነሳሁ ደሞ ጀማመረኝ
በትዝታ ቅኝት ለናፈቀኝ ልቀኝ ፤
ነካካሁት ክሩን
ገረፍኩት ክራሩን
ያቃስት ጀመረ እንደታመመ ሰው
ነፍሴን አሳቀቃት ልቤን አላወሰው
እህ ብቻ ሆነ የናፍቆት ህመሙ
ሲቃ ብቻ ሆነ ዜማዉና ግጥሙ ፤
ህመም ተለወጠ ነገር ተቀየረ
ከታች አምናው ባሰ መልኩን ቀያየረ
እህ ብቻ ሆኖ ነፍስ ማድማት ጀመረ ፤
እህ ትዝታዬ
እህ በሽታዬ እህ የኔ ህመም
አንችን እያሰቡ
መሞትም ውበት ነው እንኳንስ መታመም።
abu
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@geyone
@geyone
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
❥❥________⚘_______❥❥
ያምናው በሽታዬን
ያምናው ትዝታዬን ማነው የቀሰቀሰው
ትናፍቀኝ ጀመር የማልናፍቃት ሰው።
ክራሬን አነሳሁ ደሞ ጀማመረኝ
በትዝታ ቅኝት ለናፈቀኝ ልቀኝ ፤
ነካካሁት ክሩን
ገረፍኩት ክራሩን
ያቃስት ጀመረ እንደታመመ ሰው
ነፍሴን አሳቀቃት ልቤን አላወሰው
እህ ብቻ ሆነ የናፍቆት ህመሙ
ሲቃ ብቻ ሆነ ዜማዉና ግጥሙ ፤
ህመም ተለወጠ ነገር ተቀየረ
ከታች አምናው ባሰ መልኩን ቀያየረ
እህ ብቻ ሆኖ ነፍስ ማድማት ጀመረ ፤
እህ ትዝታዬ
እህ በሽታዬ እህ የኔ ህመም
አንችን እያሰቡ
መሞትም ውበት ነው እንኳንስ መታመም።
abu
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@geyone
@geyone
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
❥❥________⚘_______❥❥
_
Vergine Tube ድንግል ቱዩብ
ሴና ክፍል አሥራ ስምንት ❤️
. . . ቅናት ይሁን ንዴት ብቻ አላውቅም ውስጤ በጣም ተረበሸ እንዴ ግን ምንድነው እንደዚ ሚያደርገኝ ሳምንት ላወኩት ልጅ? አላውቅም የተወሳሰበ ስሜት ነው ሚሰማኝ እንዲህ ነው ብዬ ማልናገረው፡፡
ዴቭ አዲሷ አሮጌዋ አሮጊቷ እያለ ለፍሬ ሚስት መረጣ ጀመረ፡፡ "እውነት አግብቷል?" አልኩት ዴቭን አይን አይኑን እየተመለከትኩ፡፡ "ያው ቀለበት አላሰረላትም እንጂ ሚስቱ በያት፡፡ደሞ ላልተዋት ቃል ገብቻለው ምናምን ሲል ነበር" አለኝ ወደኔ እየተመለከተ፡፡ ደግሜ አልጠየኩትም፡፡ ቀኑን በጣም ከብዶኝ ዋልኩ፡፡ ዶርም እንደገባው ልብሴን እንኳን ሳልቀይር ነው አልጋዬላይ ወጥቼ ጋደም አልኩ፡፡ ማንንም አላናገርኩም፡፡ ልቤ ድንግጥ ድንግጥ ይላል፡፡ አልጋዬላይ ጋደም እንዳልኩ ስልኬን አስር ግዜ አየዋለው ፍሬ ከደወለ ወይም መልእክት ከላከ ብዬ፡፡ ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ ፍሬን ሳላገኝ ዋልኩ አደርኩ፡፡
ጥዋት እንደተነሳው ልደውልለት አስቤ ነገር ግን ለምን እሱ አይደውልም ስል መልሼ ተውኩት፡፡ ክፍል ገብቼም ቡዙም ደስተኛ አልነበርኩም፡፡ ቆይ ምን ነካኝ እንዴ ፍሬ አይደለም ፍቅረኛ ልጅ ቢኖረው እኔ ምን ቸገረኝ ስል ከራሴ ጋር መሟገት ጀመርኩ፡፡ አስተማሪው ምን እንዳለ በቅጡ ሳልሰማ ከክፍል ወጣን፡፡ ድብርብር ነው ያለኝ፡፡
ምሳ ሰአት ላይ ፍሬን አገኘውት፡፡ ተጠምጥሜበት ነው ሰላም ያልኩት፡፡ ሌላ ግን ምንም ያወራሁለት ነገር የለም፡፡ አብረን ምሳ በልተን የለመድንበት ቦታ ቁጭ ብለን ስንጨዋወት ዋልን፡፡ ፍሬን ስለፍቅረኛው ልጠይቀው እያልኩ ፈራና ተወዋለው፡፡ እነሚጣንም ካወራዋቸው ሌላ ነገር ይመስላል በዬ በማሰብ ተውኩኝ፡፡ ታዲያ ማንን ላውራ? ትንሽ ካሰቡኩ ቡሀላ ለምን ለቹቹ አልነግራትም ስል አሰብኩ፡፡ ምናልባት እሷ ከነ ሚጣ ጋር ስለማትገናኝ ሚስጥሬ የተጠበቀ ይሆናል ብዬ አሰብኩ፡፡ ሳልውል ሳላድር ላነጋግራት ፈለኩ፡፡
ማታ ዶርም ስገባ እሷም ጉዋደኞቿም የሉም፡፡ ጥዋት ወደ ክፍል ሲሄዱ ግን ያየዋቸው መሰለኝ፡፡ ለማንኛውም አምሽተውም ቢሆን መምጣታቸው አይቀርም ብቻ ውጪ እንዳያድሩ እንጂ እያልኩ በሆዴ አወራ ጀመር፡
ማታ ከፍሬ ጋር ፅሁፍ እያወራው አልጋላይ ቁጭ ብዬ የነቹቹን መምጣት እጠባበቅ ጀመር፡፡ 'ወይ ታሪክ ዛሬ ደሞ ቹቹ ናፈቀችኝ' አልኩ በሆዴ ፡፡ ነገሮችን አስቤያቸው ሳቄን ለከኩት፡፡ ብቻዬን ስስቅ እነሚጣ በየ አልጋቸው ላይ እንደሆኑ የየራሳቸውን ስራ እየሰሩ"ሆሆሆ የዛሬው ደሞ ጫን ያለው ነው፡፡" ሲሉ ሰማለው፡፡ አልታወቀኝም እንጂ ብዙ ግዜ ነው ለካ የሳኩት፡፡
ቁጭ እንዳልኩ ትንሽ ቆይተው እነ ቹቹ በር ማንኳኳት ጀመሩ፡፡ ከአልጋዬ ላይ እንዴት ወርጄ በሩን እንደከፈትኩላቸው፡፡ እነ ሚጣ ገርሞአቸው ያዩኛል፡፡ እነ ቹቹን ሰላም ብዬ ወደ አልጋዬ ተመለስኩ፡፡ እንደለመዱት ሰክረዋል፡፡ አሁን ልታናግረኝ ስማትችል ያለኝ አማራጭ ነገ ነው፡፡ ከፍሬ ጋር ተሰነባብቼ ተኛው፡፡ ጥዋት ክፍል እንድሄድ ሲቀሰቅሱኝ ትንሽ ራሴን አመም አድርጎኛል አልሄድም ብያቸው ቀረው፡፡ እነሱ ከወጡ ቡሀላ ቹቹ ከእንቅልፏ እስክትነቃ ቁጭ ብዬ መጠበቅ ጀመርኩ፡፡
ብዙ ከጠበኳት ብሀላ አልነሳ ብትለኝ ትእግስት ስላጣው ቀሰቀስኳት፡፡ ቹቹ የግዷን ተነሳች፡፡ ላናግራት እንደምፈልግ ነግሬያት በዛውም ቁርስ ልጋብዛት ይዥት ወጣው፡፡
ካፌ እንደደረስን ምግብ አዘን እየተመገብን ከምን እንደምጀምርላት ግራ ገባኝ፡፡ "እኔ ምልሽ እእእእ . . . . " እያልኩኝ ስንተባተብ "አቦ ንገሪኛ ልቤን ሰቀልሽው እኮ" አለችኝ ጮክ ብላ፡፡" አረ ድምፅሽን ዝቅ አድርጊ እሺ ነግርሻለው "አልኳት፡፡ ከወንበሬ ተመቻችቼ ከተቀመጥኩ ቡሀላ . . .
#ክፍል_አስራዘጠኝን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

❤️የፍቅር ሚዛን
💛የፍቅርን እውነተኛ ጣዕም ለማወቅ ሁለት ሰዎች እኩል መንገድ መምጣት መቻል አለባቸው። እኩል መምጣት ቢያቅታቸው እንኳን ተቀራራቢ መንገድ መጓዝ ግድ ይላቸዋል። አንዱ ብቻ መንገዱን ገስግሶ ቢመጣና ሌላው ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ ቢጠብቅ የፍቅር ሚዛን ይዳፋል።
❤️ፍቅር ጤናማ የምትሆነው ሚዛናዊ ስትሆን ብቻ ነው። ፍቅር በየጊዜው ዘንበል ቀና ብትልም ፈጽሞ ወደ አንዱ ብቻ መውደቅ የለባትም። ወደ አንዱ ከወደቀች፤ አንዱ ተሸካሚ ሌላው ተጫዋች ይሆናል። ተሸካሚው የፍቅርን አበሳ፤ ተጫዋቹ የፍቅርን ጨዋታ ብቻ ይመለከታሉ። እይታቸው የተለያየ ስለሚሆን፤ ፍቅርን በአንድ አቅጣጫ አይመለከቷትም። ታዲያ እንዴት ሊግባቡ ይቻላል? በፍጹም አይግባቡም።
💜በሰው ስሜት እንዳንጫወት፤ የፍቅርን መንገድ ከመጀመራችን በፊት፤ ምን ያህል እርቀት መጓዝ እንደምንችል እናስብ። ከሚወደን ሰው ጋር መኖር በተጫዋቹ ቦታ መቀመጥ ፤ ከምንወደው ሰው ጋር መሆን በተሸካሚው ቦታ መሆን እንዳይሆንብን።
💛 የፍቅርን ሚዛናዊነት አይቶ ጨዋታውን ለማጣጣም አፍቃሪ እና ተፈቃሪ ሆነን ሳይሆን፤ ሁለት አፍቃሪዎች ሆነን መቅረብ አለብን። እንደ ሚዛን ጨዋታ፤ ጨዋታውን ለማጣጣም አንዴ እላይ አንዴ እታች ቦታ እየተለዋወጥን የፍቅርን ሚዛን መጠበቅ ግድ ይለናል።ፍቅር የባላይ ልሁን ለሚል ሰው አትሆንም፤ ከላይ ብቻ ተሰቅሎ ሚዛኑን ሌላው ላይ ማዳፋት ከፍቅር ጨዋታ የራቀ ነው።
💜ፍቅር እኔ ብቻ ልሸከማት ለሚልም አትሆነም፤ ምክንያቱም ጣዕሟን ለማጣጣም ስለሚከብደው። ምናልባት በፍቅር ሚዛን ላይ ከሆንን ፤ ግንኙነታችን እንቃኘው፤ ማነው ሸክሙን የተሸከመው፤ ማነው ጨዋታውን እያጣጠመ ያለው? በሰው ስሜት እንዳንቀልድ ለፍቅር ሚዛናዊ ለመሆን እንሞክር። የሚወዱን ሰዎች ሊወደዱ ይገባቸዋል፤ እኛ ሚዛኑን መጠብቅ ካልቻልን ከፍ ሊያደርጋቸው ለሚችል ለሌላ ሰው ቦታውን እንልቀቅላቸው። የምንወዳቸው ሰዎችም ሚዛኑን መጠበቅ ካቃታቸው፤ ፍቅር ለሚገባው፤ ዝቅ ካልንበት ከፍ ለሚያደርገን ሰው ቦታውን ቢለቁልን መልካም ነው።
ውብ ምሽት❤️
✍ሚስጥረ አደራው

እንደገና
Mohammud ahmud
Title ➲ እንደገና
Song ➲ Mehammud Ahmed
Size ➲ 1.1 mb
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
ሼር 🙏🙏
Song ➲ Mehammud Ahmed
Size ➲ 1.1 mb
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
ሼር 🙏🙏
💕ሰኞን እንዲህ ብንጀምርስ?💕
🇪🇹በመጀመሪያ ለዛሬዋ እለት ላደረሰን ለቸሩ ፈጣሪያችን 👏ክብር ምስጋና ይገባዋል 🙇♀
እለታትን እያፈራረቀ በእድሜያችን ላይ እድሜ እየጨመረ ዛሬ ላይ አድርሶናል ነገንም በሱ ቸርነት እናያለን
ሁሉም እንደአቅሙ ለሰው ልጅ የሚበጅ መልካም ስራ ሰርቶ መዋል በቅን ልቦና በመነሳሳት እራስና ወገንን በመርዳት እየሰራን ብናልፍ ለራሳችን ክብር ለሀገር ኩራት በሆንን ነበር ነገር ግን ግዜው አልፈቀደም የፊጢኝ ወደሗላ አስሮ እየጎተተን ነው
በፈጣሪ ያችን ቸርነት ሁሉም በግዜው ያልፋልና በግዜያችንም በተሰጠን እለት ያቅማችንን መልካም አድርገን እንለፍ ።
እንኳን ለዛሬዋ እልት በሰላም በጤና አደረሰን እያልኩ ሳምንቱ የታመመ የሚድንበት ያጣ የሚያገኝበት ያዘነ የሚፅናነበት የተራበ የሚጠግብበት የተጠማ ጠጥቶ የሚረካበት ፍቅር ያጣ ፍቅር የሚያገኝበት የታሰረ የሚፈታበት ፍትህ ያጣ ትክክለኛ ፍርድ የሚያገኝበት መልካም የስራ ሳምንት እንዲሆንልን እመኛለሁ እግዚአብሔር ይጠብቀን
ፈጣሪ ሀገራችንን ይባርክ መልካም ቀን

ሴና ክፍል አሥራ ዘጠኝ ❤️
. . . ከወንበሬ ተመቻችቼ ከተቀመጥኩ ቡሀላ ግቢ ከገባው ቀን ጀምሮ ያለውን ሁኔታ በሙሉ ሳምንት ያጋጠመኝን ያደረኩዋቸውን ነገሮች ማወቅ ያለባትን ያህል አጫወትኳት፡፡"እኔ በአንድ ሙሉ ሴሚስተር ያላሰለፍኩትን ላይፍ አንቺ በአንድ ሳምንት ኮመኮምሽዋ?" ብላ ሳቀችብኝ፡፡ እኔም አብሬያት ሳኩኝ፡፡"እኔ ምልሽ ግን ለምንድነው ታዲያ እንደዚ ሚሰማኝ? አንድ ሳምንት ማውቀው ልጅ ከይደለም ሚስት ፍቅረኛ ምናምን ቀርቶ ልጅ ቢኖረው ምን አገባኝ? ለምንድነው ውስጤ የሚረበሸው? ለምንድነው ልቤ ሚደነግጠው? በናትሽ ቹቹ ንገሪኝ?" አልኳት ሳቋን እስክትጨርስ እንኳን ሳልጠብቃት አይን አይኗን እያየው፡፡
"የውልሽ ሴና" ሴና አለች በወንበሯ ተመቻችታ እየተቀመጠች "የውልሽ ሴና ምናልባት አንቺ ወንድ እንደዚ ስትቀርቢ ይህ የመጀመሪያሽ ስለሆነም ሊሆን ይችላል እንደዚ የተሰማሽ፡፡ ሳታስቢው ፍቅር እየያዘሽ . . .." "ምን?! ፍቅር?" አቋረጥኳት፡፡ ደነገጥኩ "ምንድነው ምትይው? እንዴት በአንድ ሳምንት ውስጥ. . . ማለቴ . . .ደሞ የፍቅር ፅሁፎች ብዙ አንብቤያለው እነዴት . . . እኔ ምልሽ ቆይ ስታስቢው . . . " ተንተባተብኩ ፊቴን ላብ አሰመጠኝ ፤የምናገረው ግራ ገባኝ 'እንዴት ነው ፍቅር ቆይ እንደዚ ነው እንዴ?' ከራሴጋር መጨቃጨቅ ጀመርኩ፡፡"የውልሽ ሴና አዳምጪኝ" አለች ቹቹ ረጋ ባለ መንፈስ፡፡"እኔም ለመጀመሪያ ግዜ እንዳንቺው ነበር የሆንኩት እመኚኝ በቃ የቡሀላውን ባናውቅም ለግዜው ግን ፍቅር ይዞሻል፡፡" ደገመችልኝ "እንዴት ነው በዚህ ቀን ውስጥ ፍቅር? ፍቅር እንደዚ ነው እንዴ?ምን አይነት ፍቅር ነው ይሄ?" አፈጠጥኩባት ፤ጥያቄ ላይ ጥያቄ አከታተልኩባት፡፡ ቹቹ ዝም ብላ ስትመለከተኝ ከቆየች ብሀላ "ቆይ ለልጁ ምንም ስሜት የለሽም?
"አረ ምንም ስሜት የለኝም በቃ እናወራለን እንጫወታለን አለቀ ከዛ ውጪ ምምም ማስበው ነገር የለም፡፡"እንደመናደድ ብያለው፡፡"እና ብታጪውም ምንም አይመስልሽማ?" አለችኝ ቹቹ አይኔን ትኩር ብላ እየተመለከተች"አዎ እንዴ ምን አይመስለኝም"አልኳት አይኔን እያርገበገብኩ፡፡ "እሺ በአንድ ነገር እንስማማ"አለችኝ፡፡ ምንድነው እንኳን አላልኳትም ወዲያው እሺ አልኩኝ፡፡ "ፍቅር ይዞሻል ብቻ አትበይኝ ሌላ ነገር እስማማለው "አልኳት፡፡ "ለልጁ ምንም ስሜት ከሌለሽ እስከዛሬ ሳምንት በስልክም በአካልም እንዳታገኚው፡፡እውነት ምንም ስሜት ከሌለሽ አይደለም አንድ ሳምንት እስከመጨረሻሽ እንኳን ባትገናኙ ምንም አይመስልሽም ማለት ነው" አለችኝ ፡፡ ደነገጥኩ! ግን ፍቅር እንዳልያዘኝ ለራሴም ለቹቹም ማሳየት ፈልጋለው፡፡ ተስማማው ፤እሺ አልኳት፡፡ "አንድ ሳምንት ፍሬ ሚባል ሰው እንኳን አልገናኝም፡፡" አልኳት፡፡ በውስጤ ግን አንድ ነገር አሰብኩ፡፡ 'እንዴ ከነሚጣ ጋር ከሆንኩ እኮ ፍሬን መገናኘቴ አይቀርም፡፡ ከቹቹ ጋር ደሞ መዋል አልችልም፡፡ እና ብቻዬን ልሆን ነው?' ምን ማድረግ እንዳለብኝ ከራሴ ጋር ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡
እንዴት ነው ይሄንን አንድ ሳምንት ማሳልፈው? አንድ ሀሳብ መጣልኝ ወንድሜ 'አግኚያት የመስራቤታችን ሰውዬ ልጅ ናት ያለኝ ትዝ አለኝ፡፡ አዎ ከሷጋር ሆናለው የዛኔ ማንንም አላገኝም ማለት ነው፡፡'በዚህ ሀሳብ ከራሴ ጋር ተስማማው፡፡'ግን እኮ አላውቃት አታውቀኝ አባቱዋና ወንድሜ አንድ ቦታ ሰሩና እኔና እሱዋ እንግባባለን ማለት ነው?' ስል ደሞ ሌላ ነገር ማሰብም ጀመርኩ፡፡ በቃ ላይብረሪ ውላለው ወይም ዶርም ተኝቼ ውላለው፡፡ ብዙ ብዙ ነገር አሰብኩ፡፡ እንዴት እንደማደርግ ሳወጣ ሳወርድ በሀሳብ ሄድኩ፡፡
"ሴና ! ምን ሆነሻል?" ከወሰደኝ ሀሳብ የቹቹ ጥሪ መለሰኝ፡፡ እንዲሁ ነው ብያት ከቹቹ ጋር ከተስማማን ብሀላ ጨዋታ ቀይረን ስለሌላ ነገር ማውራት ጀመርን፡፡ በዚህ መሀል ስልኬ ጠራ ፡፡ፍሬ ነው . . .
#ክፍል_ሀያን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️
@fiker_markiye

ሴና ክፍል ሀያ ❤️
. . . "ሴና ምን ሆነሻል?" ከወሰደኝ ሀሳብ የቹቹ ጥሪ መለሰኝ፡፡ እንዲሁ ነው ብያት ከቹቹ ጋር ከተስማማን ብሀላ ጨዋታ ቀይረን ስለሌላ ነገር ማውራት ጀመርን፡፡በዚህ መሀል ስልኬ ጠራ ፡፡ፍሬ ነውስልኬን አይቼ ቀና ብዬ ቹቹን እየተመለከትኳት "ፍሬ ደወለ" አልኩ እንደመደንገጥ ብዬ፡፡"እና ይደውላ ምነው ልታነሽው ባልሆነ፡፡"ስትለኝ ምንም መልስ ሳልሰጣት ስልኬን አስቀምጬ ጨዋታችንን ቀጠልን፡፡ ብዙ ከተጨዋወትን ቡሀላ ቹቹ ምትሄድበት እንዳለ ነግራኝ ካፌ ትታኝ ወጣች፡፡
ትንሽ ብቻዬን እንደተቀመጥኩ ለነ ሚጣ ልደውል አስቤ ደግሞ ፍሬ ቢኖርስ ብዬ ተዉኩት፡፡ ወንድሜ አግኛት ላለኝ ልጅ ልደውል አልደውል ስል ብዙ አመነታው፡፡በመጨረሻም ደወልኩላት፡፡ ረጋ ያለች ልጅ ትመስላለች ትንሽ አናግሬያት ከተዋወቅን ብሃላ ከቻለች እንድንገናኝ ስጠይቃት "ዛሬ ክላስ የለኝም ቤት ነኝ ጥዋት ነው ምመጣው"አለችኝ፡፡ 'ጎሽ ከኔም የባሰ አለ ማለት ነው' አልኩ በሆዴ፡፡ነገ ላገኛት ተቀጣጥረን ስልኩን ዘግቼ ቁጭ ብዬ ቲቪ ላይ ማፍጠጥ ጀመርኩ፡፡ ብቻዬን ነው የተቀመጥኩት፡፡ አይኔ ቲቪ ያያል እንጂ ሀሳቤ ሌላ ቦታ ነው፡፡
"አረ ቆንጆ ብቻሽን ምነው? ከገባው ጀምሮ ሳይሽ ብቻሽን ነሽ የማን ፋራ ነው አስደግፎሽ የቀረው?" እያለ ከፊትለፊቴ ያለ ወንበር ስቦ ተቀመጠ አንድ ፀጉረ ጨበሬ ወንድ፡፡ምንም መልስ አልሰጠውትም፡፡ ከተቀመጠ ቡሃላ "ወንበሩ ግን ሰው አለው?" አለኝ መልስ አልሰጠውትም ወደ ወንበሬ መደገፊያ ደገፍ ብዬ እጄን በደረቴ አድርጌ ተቀመጥኩ፡፡ "ፆም ገባ እንዴ?" አለኝ ፡፡ 'የምን ፆም?' ስለው "ተመስገን አልገባም ማለት ነው፡፡ምነው ብቻሽን እዚ ማንን እየጠበቅሽ ነው?" አለ፡፡ከመጣ ሰአት ጀም ሌላም ያላስታወስኮቸው ብዙ ነገሮች አወራ ፣ሊቀልድ ማከረ ፣ሊያስገርመኝ ሞከረ፡፡ እኔ በራሴ ሀሳብ ውስጥ ነኝ፡፡ ወሬው ቢያቅተኝ ለሚጣ ደውዬ ቀጥሮ እንደሚጠብቅ ሰው'የት ናቹ ቆየው እኮ ከመጣው የት ልምጣ' አልኩኝ እንደመቆጣት ብዬ፡፡ሚጣ ያልኳት ግራ ቢገባትም ያሉበትን ነገረችኝ፡፡ እዛው ጠብቁኝ ብዬ ተነሳው፡፡ ልጁ አብሮኝ ተነሳ"እኔም ወደዛው ስለሆንኩ ልሸኝሽ?" አለኝ፡፡ 'ምሄድበትን እንዴት አወክ?' ብዬ ስጠይቀው "እሱን ስትደርሺ ነዋ ማውቀው"አለኝ፡፡ 'ውይ በናትክ ወንድሜ ተወኝ'ብዬ ወደነሚጣ ገሰገስኩ፡፡
ከነሚጣ ጋር ስገናኝ ረጅም ቀን ያጣዋቸው ያህል ነበር የናፈቁኝ፡፡ ሁሉንም ሰላም ብዬ "ምነው ቅድም ፍሬ እየደወለልሽ አታነሺም አብረን ነበርን" አሉኝ፡፡ ከሰው ጋር እንደነበርኩ ነግሬያቸው ካፌ ውስጥ ያጋጠመኝን ልጅ ነግሬያቸው መሳሳቅ ጀመርን፡፡
ማታ ዶርም ገብቼ ልብሴን ከቀያየርኩ ቡሀላ ክፍል ገብተው ከፃፉት ማስታወሻ ላይ መገልበጥ ስጀምር የፍሬ መልእክት በስልኬ ገባ"ምነው ጠፋሽ በሰላም ነው?" ሚል ነበር፡፡ አንበቤ ብቻ ስልኬን መልሼ አስቀምጬ መፃፌን ቀጠልኩ፡፡ ዶርም ውስጥ እያወራን እየተሳሳቅን ስለነበር ለፍሬ መልእክት አለመመለሴ ብዙም ቅር አላለኝም፡፡
ጥዋት ወደ ክፍል ስንሄድ ፍሬን ባላገኘው ብዬ በውስጤ ተመኘው፡፡ ጠልቼው አይደለም ግን ደሞ . . . በቃ ብቻ ላገኘው አልፈለኩም፡፡ ብዙ ቀን ወደክፍል ስንሄድ ፍሬና ዴቭን እናገኛቸዋለን፡፡ ዛሬ አላገኘናቸውም የሆዴን ሰማኝ መሰለኝ፡፡
ቀን ከክፍል ስንወጣ ምሳ ካፌ እንግባ ወይስ ውጪ እንብላ ብዬ ጠየኩዋቸው፡፡ "አረ ዴቭ ዛሬ ምሳ በኔ ነው ብሎአል ልደውልለት እንደውም ብላ ስልኳን መነካካት ጀመረች፡፡ ደነገጥኩ 'ወይኔ ጉዴ ፍሬም ይመጣል ማለት ነው እኮ' አልኩኝ ለራሴ፡፡ በዚህ መሀል የወንድሜ ባልደረባ ልጅ ደወለች፡፡ ከተመቸኝ አሁን እንዳገኛት ጠየቀችኝ፡፡ እንደሚመቸኝ ነግሬያት ለነሚጣ 'በጣም ይቅርታ ረስቼው ነው ወንድሜ እንዳገኛት የነገረኝ ልጅ አለች አሁን ነበር ቀጠሮዋችን፡፡ረስቼው ነው በጣም ይቅርታ ጉዋደኞቼ ቡሀላ አገኛቹሀለው ብዬ ጉንጫቸውን ስሜያቸው ተሰናበትከበቸው፡፡በመሄዴ ደስ ባይላቸውም በእሺታ ራሳቸውን እየነቀነቁ ተቀበሉኝ፡፡ ትቻቸው ሄድኩ፡፡
ግን እስከመቼ? ለአንድ ሳምንት ወይስ እስከመጨረሻው? ቆይ ዛሬን እንዲ አለፍኩ ነገስ? ምን እያደረኩ ነው? ምን እየሆንኩ ነው? ውስጤ ብዙ ጥያቄ ይመላለሳል፡፡ እየተወዛገብኩ እርምጃዬ ወደ ቀጠሮዬ እያመራኝ ነው . . .
#ክፍል_ሀያአንድን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

ሴና ክፍል ሀያአንድ
. . . ከቀጠሮዬ ቦታ ደስደርስ ስልክ ደውዬ ተገናኘን፡፡ እንደጠበኳት ግን አይደለችም፡፡ዝንጥ ያለች ቆንጅዬ ልጅ ነች፡፡ ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ተዋውቀን ተቀመጥኩ፡፡ ፌቨን ነው ስሟ፡፡ ትንሽ እንዳወራን ተግባባን ፡፡ ፌቨን ቀለል ያለች ተጫዋች ልጅ ነች፡፡ ቡዙ ተጨዋወትን በዚህ መሀል ስልኬ ሶስት ግዜ ተደውሎአል፡፡ ፍሬ ነው አላነሳውትም፡፡ ቀኔን ከፌቨን ጋር አሳለፍኩ፡፡
ወደ አመሻሽ ላይ እና ሚጣ ደውለው እራት አብሬያቸው እንድበላ ጠየቁኝ፡፡ አብሬያቸው መሆንን ፈልጌያለው፡፡ ግን ፍሬ ሊኖር ይችላል ብዬ ስላሰብኩ ሰበብ ፈጥሬ መቅረትን መረጥኩ፡፡"ትንሽ አመም አድርጎኝ ወደ ዶርም እየሄድኩ ነው፡፡ ባይሆን ስትመጡ እራት ይዛቹልኝ ኑ" ብያቸው ወደ ዶርሜ አቀናው፡፡
ዶርሜ ስገባ ያቺን ባለ መነፅር አልጋዋላይ ተኝታ ኮምፒውተሯን እየጎረጎረች አገኘዋት፡፡ ሰላም ተባብለን ለምን ብቻዬን እንደመጣው ስትጠይቀኝ ትንሽ ራሴን አመም አድርጎኝ እንደሆነ ነግሬያት ልብሴን ቀይሬ ተጣጥቤ አልጋዬላይ ወጥቼ ተኛው፡፡ ከእንቅልፌ የባነንኩት በሚጣ ጥሪ ነው፡፡ "ምን ሆነሽ ነው? በጣም አመመሽ እንዴ?" አለችኝ ግንባሬን በእጇ እየዳበሰች፡፡ "የት ውለሽ ነው? ምን ሆነሽ ነው? የጥያቄ መአት እያከታተሉ ይጠይቁኝ ጀመር፡፡ ብዙም አላወራውም ያመጡልኝን እራት ከበላሁ ቡሀላ ተመልሼ አልጋዬላይ ወጣሁ፡፡ ስለውሎዋቸው ያጫውቱኝ ጀመር፡፡ እያወራን ስልኬ መልእክት ገባ ፡፡ ፍሬ ነው አነብቤው ተውኩት፡፡ ጨዋታችን ቀጠለ፡፡
እንዲ እንዲያ እያልኩ ቀናት ተቆጠሩ ፣ሳምንቱም አለቀ ፣ቤት ደርሼ ተመለስኩ፡፡ ለቹቹ ቃል እንደገባውላት ፍሬን አንድ ሳምንት ሳላገኘው፡፡ በቀጠሮዋችን ቀን ከቹቹ ጋር የተለመደው ቦታ ተቀምጠን ስላለፈው ነገር ማውራት ጀመርን፡፡ "ይኸው ፍቅር እንዳልያዘኝ እወቂ፡፡ አንድ ሳምንት አላገኘውትም ግን ምንም አልተሰማኝም ፣ምንም አልሆንኩም" አልኳት ግዳጁን እንደተወጣ መልእክተኛ ፡፡ "ስለዚህ በዚሁ ትቀጥያለሽ ማለት ነው" አለችኝ ቹቹ፡፡ አልገባኝም ፤ደነገጥኩ "ማለት ከዚህ ቡሀላ ፍሬን ላላገኘው?" አልኳት፡፡ "እንደዛ ማለቴ አይደለም ከዚህ ቡሀላም ስለፍሬ አታስቢም ፣ብዙ ግዜሽን ከፍሬ ጋር አታሳልፊም፡፡ በቃ እንደማንኛውም ተራ ጉዋደኛ ብቻ ይሆናል ምትቀራረቢው" አለችኝ፡፡
" 'ለምንድነው?' ብለሽ እንደምታስቢ አውቃለው፡፡ አንቺ በዚህ ግዜ ስለ ፍቅር ምንም ማሰብም ፣ፍቅረኛ እንዲኖርሽ አትፈልጊም፡፡ ፍሬ ደሞ በአጭር ቀን ውስጥ በጣም የቀረብሽው ወንድ ነው፡፡ በዚህ ከቀጠልሽ ደሞ ወደ ፍቅር ማይቀየርበት ምክንያት አይኖርም፡፡ስለዚህ ግንኙነታቹን ትቀንሻለሽ፡፡ ይሄንን ደሞ ምመክርሽ ላንቺው ብዬ ነው፡፡" አለችኝ ቹቹ፡፡ ዝም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ምንም ሳልናገር ከ አስር ደቂቃ በላይ አሳለፍኩ፡፡ ብዙ አወጣው አወረድኩ፡፡ "እውነቷን ነው? አይ ምንም ችግር የለውም . . . "ቹቹም ዝም ብላ ታየኝ ጀመር፡፡ እንደመጀመሪያው ቀን ዛሬ ወዲያው ልስማማ አልቻልኩም፡፡ "እሺ" የማለት ድፍረት አጣው፡፡ "ይሄንን ግዜ ወስደሽ በደንብ አስቢበት፡፡ የምርጫ ጉዳይ አይደለም፡፡ እሺ ወይ እንቢ እንድትይኝ አይደለም፡፡ ራስሽ እንድታስቢው ፤ራስሽን በራስሽ እንድትመረምሪበት ነው የነገርኩሽ" አለችኝ ቹቹ አይኔን እያየች፡፡ እንማስብበት ነግሬያት በተለመደው ሰአት ተለያየን፡፡
ወደሚጣ ስልክ ስደውል ፍሬ አነሳው፡፡ "ሴና ግን ምን አድርጌሽ ነው? እንደዚ ሚያስከፋ ነገር አደረኩሽ ግን? . . ."ገና እያወራኝ ስልኩን ዘጋውት፡፡ ደነገጥኩኝ፡፡ 'እውነት ምን አድርጎኝ ነው ግን?' ብዬ አሰብኩ፡፡ 'እንዴት ግን የሚጣን ስልክ አነሳው?ምናልባት አብረው ሆነው ይሆናል፡፡' እነሚጣ የት እንዳሉ ለማወቅ ነበር የደወልኩት፡፡
ትንሽ ቆይቶ ፍሬ በራሱ ስልክ መልእክት ላከልኝ፡፡ በቆምኩበት ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ እያነበብኩ ወደመሀል ስደርስ ሳላስበው እንባዬ መጣ፡፡ ማንበቤን ቀጠልኩ፡፡ እንባዬ አይኔን ሸፎኖኝ ስልኬላይ መንጠባጠብ ጀመረ፡፡ የላከልኝ መልእክት እንዲህ የሚል ነው . . .
#ክፍል_ሀያሁለትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

ሴና ክፍል ሀያ ሁለት ❤️
. . . የላከልኝ መልእክት እንዲህ የሚል ነው"ሴና ይሄንን መልእክት ማታ ነበር ልልክልሽ የነበረው፡፡ ግን ምናልባት ሳይመቻት ይሆናል ስልም መልሼ አሰብኩ፡፡ አሁን ገን ጥርጣሬዬ እውነት መሆኑን አሳየሽኝ፡፡
ሴና በዚች አንድ ሳምንት ያሳለፍነው ግዜ ለብዙ ግዜያት አብሬያቸው የቆየው ሌሎች ሴቶች ጋር ያሳለፍኩትን ግዜ በእጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡ ምን እንዳስቀየምኩሽ ፣ምን እንዳጠፋው ወይ ያልተመቸሽ ነገር ምን እንደሆነ ራሱ ሳትናገሪ በድንገት ጠፋሽ፡፡ 'አንድ ሳምንት ለምታውቃት ልጅ ምንድነው እንደዚ ሙጭጭ ማለት፡፡' እስኪሉኝ የዶርም ልጆች ስላንቺ ሳስብ ስጨነቅ ነበር፡፡አንቺ ግን ትክክል አልሰራሽም፡፡ በእውነት እልሻለው ትክክል አልሰራሽም፡፡ አንቺ ምክንያት ሊኖርሽ ይችላል፡፡ ግን ምንም ሆነ ምን ከኔጋር ሚገናኝ ምክንያት የሚኖርሽ አይመስለኝም፡፡ መጀመሪያ ያገኘውሽ ቀን የሆነ ነገር ነበር የተሰማኝ፡፡ያለፈውን መጥፎ ግዜ አስታወሽኝ አሁን ፡፡ ምን እንደሆነ ልነግርሽ አልችልም፡፡ እና ሴናዬ በቃ አንቺ ያመንሽበት ነገር ከሆነ ችግር የለውም አልደውልም ፣ መልእክትም አልክም፡፡ እኔ ሴት ምናምን ወዲያ ወዲ ማደርግ መስሎሽም ከሆነ ተሳስተሻል፡፡ እንደዛ ቢሆን አንድ ሳምንት ላወኩሽ ይሄንን ሁሉ ባለፈለፍኩ በሁለተኛው ቀን ነበር ምረሳሽ፡፡ እና በቃ እኔን ሽሽት ከ ጉዋደኞችሽ አትራቂ፡፡ እኔ አልደርስብሽም፡፡ መንገድ ላስ ስንገናኝ 'ሰላም' በይኝ ግን እሺ፡፡ ደና ሁኚ፡፡"
አንብቤው እንደጨረስኩ ባለሁበት አካባቢ መቀመጫ ፈልጌ ቁጭ አልኩ፡፡ ሳላስበው በጉንጬ ላይ የወረደውን እንባዬን አብሼ መልሼ መልእክቱን ማየት ጀመርኩ፡፡ አላውቅም ብቻ የሆነ ነገር ረበሸኝ፡፡ ልቤ ድንግጥ ድንግጥ ይላል፡፡ የማላውቀው የጭንቀት ስሜት ተሰማኝ፡፡ እንደምንም ራሴን አረጋግቼ ወደ ዶርም ሄድኩኝ፡፡
ዶርሜ አልጋዬላይ ጋደም እንዳልኩ ፊቴ ላይ ሚመጣው ፍሬ ነው፡፡ ብገላበጥም ፣ጥቅልል ብዬ ብተኛም ፍሬን ብቻ ማሰብ ሆነ ስራዬ፡፡ ስልኬን አውጥቼ ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ከፍሬ ጋር የተላላክናቸውን መልእክቶች ማንበብ ጀመርኩኝ፡፡ እነዛን ቀናት በውስጤ እያሰብኳቸው ብቻዬን ፈገግ እላለው፡፡ ዛሬ የላከልኝን መልእክት ደግሜ ሳነበው እንባዬ ይመጣል፡፡
እውነቱን ነው እኮ ግን ምን አደረገኝ ቆይ? ከኔጋር ግዜውን ስላጠፋ ነው? አብሮኝ ስለሆነ ነው? ስለቀረበኝ ነው? የራሴን ስሜት ብቻ ለምን ተከተልኩ? ሳላስበው እንባዬ ይፈሳል፡፡ የሆነ ቅር ቅር ሚል ነገር ይሰማኛል፡፡ አልጋዬላይ ጋደም በዬ በትዝታ ከፍሬ ጋር እየተጫወትኩ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡
ከእንቅልፌ ስነሳ እኩለ ለሊት አልፎአል፡፡ ራሴን በጣም አሞኛል፡፡ አልጋዬ ላይ እንዳለው ቀና ብዬ ዶርሙን በአይኔ ቃኘው፡፡ ሁሉም ተኝተዋል፡፡ ጠረቤዛ ላይ የፕላስቲክ ምሪንዳ እና ብስኩት ተቀምጦአል፡፡ ምናልባት ለኔ ይሆናል ብዬ አሰብኩ፡፡ ስልኬን ስመለከት 16 ግዜ ተደውሎአል፡፡ደነገጥኩ ወንድሜ እና አባቴ ናቸው፡፡ አሁን እንዳልደውል ወረበሽ ይሆናል፡፡ የፍሬን መልእክት ስላጣው ቅር አለኝ፡፡ተመልሼ ተኛሁ ግን እንቅልፍ አልወስድ አለኝ፡፡ እንዲሁ ስገላበጥ አነጋው፡፡
ጥዋት የዶርሜ ልጆች ሲነሱ ሁሉም በየተራ "ሴና ማታ ምን ሆነሽ ነው?" ይሉኝ ጀመር፡፡መልሼ ጠየኳቸው"ምን ሆንኩኝ?" ስል፡፡ "እንዴ ማታ ብንጠራሽ አትሰሚ ደሙ አልቅሰሽ ነበር? ስልክሽም ያንን ሁሉ ግዜ እንደዛ እየጠራ መጨረሻ እንዳይጨነቁ ብዬ 'ትንሽ ራሱዋን አመም አድርጎዋት ተኝታ ነው'አልኩልሽ፡፡ ቆይ ግን ምን ሆነሽ ነው?" አለችኝ እኑካ፡፡'አይ ተመስገን ስልኬን ካነሳቹ ሌላው ቀላል ነው' አልኩኝ በሆዴ፡፡
"ሜምናልባት እራት ካልበላሽ ብለን ነው ያመጣንልሽ እኮ ፆምሽን ነዋ ያደርሽው?" አለችኝ ሚጣ እንደመቆጣት ብላ፡፡ "እሺ አሁን ቁርስ በላዋለው "ብያቸው ልተጣጠብ ወጣው፡፡ ተጣጥቤ ስመለስ ራስምታቴ ባሰብኝ፡፡ አልጋዬ ላይ ተመልሼ ተኛው፡፡ ቢጠይቁኝም መልስ የለኝም፡፡ "የክፍል ሰአት እየደረሰ ስለሆነ እናንተ ሂዱ በቃ እኔ እዚ አለው" አለች ቹቹ፡፡ አሁን ድምፁዋን ስሰማ ነው መኖሩዋን ያወኩት፡፡ "አይ እኔ አለው እናንተ ሂዱ" አለች ሚጣ፡፡ ከቹቹ ጋር ተቃራኒ እንደሆኑ አውቃለው፡፡ "ካልሽ እንዳልሽ ይሁን "ስትል ቹቹና ጉዋደኞቹዋ ተያይዘው ወጡ፡፡ እነ እኑካም ተከታትለው ወጡ፡፡ በመጨረሻም ባለ መነፅሯ ወጣች፡፡ እኔና ሚጣ ብቻ ቀረን፡፡ አልጋዬላይ ተጠቅልዬ ጋደም እንዳልኩ ነኝ፡፡
"ምን ሆነሽ ነው ግን? ሰሞኑን እኮ ልክ አይደለሽም" አለችኝ ሚጣ፡፡ "ምንም አልሆንኩም" አልኳት እንባ እየተናነቀኝ፡፡"የሆነ ነገርማ ሆነሻል ፤ግድ የለሽም ንገሪኝ" ስትል በጥያቄ አስጨነቀችኝ፡፡" እኔም ግራ ገብቶኛል ሚጣ ፡፡ እኔ ራሴ አላውቅም! እንዲነው ምልሽ ! ተረድቼ ማስረዳሽ ! የሆንኩትን ማውቀው ነገር የለኝም! እኔም ግራ ገብቶኛል እኮ! ምን ሆንኩ ልበልሽ!? እንዴት ላስረዳሽ!? " እንባዬ እየወረደ ሀይለቃል የተቀላቀለበት መልስ መለስኩላት፡፡ ራስምታቴ ጨመረ . . .
#ክፍል_ሀያሶስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️