የልቤ ትርታ
202 subscribers
473 photos
4 videos
10 files
422 links
Download Telegram
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
የነገ ሰው ይበለን
አሜን,.........

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
🌙 እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል
በሰላም አደረሳችሁ። 🌙

https://telegram.me/geyone
ለመላው የእሥልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1ሺ 442ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በሠላም አደረሣችሁ #Eid_Mubarak

JOIN US 4 MORE

https://telegram.me/geyone
ለመላው የእሥልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1ሺ 442ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በሠላም አደረሣችሁ #Eid_Mubarak

JOIN US 4 MORE

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
ጠብቂኝ በህልምሽ

ጠብቂኝ በህልምሽ ፤ እመጣለሁ ማታ
አልቀርም አትስጊ ፤ አለሁ ለሰላምታ
ያን የምሽት ጥቁረት ፤ ያን የሌት ፀጥታ
እንደ መብረቅ ጮኬ ፤ ጨለማን ልረታ
እመጣለሁ ማታ ፤ በህልምሽ አልቀርም
አንቺን እረስቼ ፤ ሌላ ቤት አላድርም
ኧረ አይሆንም!
ቀኑም ሲጨላልም……

አይኖችሽ ተከድነው ፤ በናፍቆት ሊያልሙ
በምኞት ጭንቅ አዝለው ፤ እያግደመደሙ
ከጠበቁኝ እማ ፤ መች እኔ እቀራለሁ
አንድ ነገር ብቻ ፤ በእጅግ እፈራለሁ
የጠበቅሽው ጊዜ ፤ የህልም አለም ወቅትሽ
ከደረሰ ወዲያ ፤ አይኔን እንደናፈቅሽ
ሃሳብና ናፍቆት ፤ እንቅልፍ እንዳይነሱሽ

ብሩክ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
በአንድ ወቅት አንድ ወጣት በጣም ቆንጅዬ ከሆነች ልጅ ፍቅር ይዞት ነበር ፡፡ ልጅቷ በጣም ቆንጆ እና የሚያምር ሰውነት ነበራት ፡፡ ወጣቱ በፍቅሯ ከተሸነፈ ቆይቷል ፡፡ እንድታፈቅረው ለማድረግ በጣም ብዙ ነገር ነበር የሚያደርግላት ፡፡ ቀሪ ሕይወቱን ከእሷ ጋር ስለማሳለፍ ማለም ብቻ ሆነው ስራው ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን አንድም ቀን ለሷ ያለውን ስሜት ገልፆላት አያውቅም ፡፡ ጓደኞቹ እንዲነገራት ብዙ ጊዜ አደፋፍረውታል
“ስሜትህን ካለገለፅክላት እንደምትወድህ ወይም እንደማትወድክ በምን ታውቅና ነው ስለ እሷ ብዙ የምታስበው? ለሷ ይህን ሁሉ የምታደርገው? በመጀመሪያ ምን እንደሚሰማክ ንገራት ከዛ የሚሆነውን እናያለን ”፡፡

ከብዙ ምክርና ጭቅጭቅ በውኃላ ያ ትክክለኛ መንገድ እንደሆነ ተሰማው። ልጅቷ በተቃራኒው ከመጀመሪያው ጀምሮ ልጁ እንደሚወዳት ታውቅ ነበር ፡፡ ምንም ነገር ከሱ ካልመጣ ችግር የለውም ብላ ግንኝነታቸውን በተለመደው በኩል እንዲቀጥል አድረጋው ቆይታለች ፡፡ አንድ ቀን ግን ፈራ ተባ እያለ ስለሷ ምን እንደሚሰማው ነገራት ፡፡ ልጅቷ ግን የፍቅሩን ጥያቄ ውድቅ አደረገችው፡፡

ልጁ ያልጠበቀውና ያልተዘጋጀበት ነገር ስለነበር ከባድ ዱብ ዕዳ ሆነበት ፡፡ ከሱ ይልቅ ደግሞ ዜናውን በጉጉት ሲጠብቁ የነበሩት ጓደኞቹ ይበልጥ ደነገጠ።

በነርሱ ግምት ልጅቷም ፍላጎት ይኖራታል ብለው አስበው ነበር፡፡ ጓደኛቸው ልጅቷን ምን ያህል እንደሚወዳት ስለሚያውቁ ያን አስደንጋጭ የሆነ መልስ ካገኘ በውሃላ ልጁ ሰው አይሆንም ብለው ብለው ገመቱ፡፡ በብስጭት አጉል ሱስ ውስጥ ይገባል ወይም እራሱን ይጎዳል የሚል ስጋት ገባቸው፡፡

ልጁ ምንም እንዳለተፈጠረ የእለት ተለት ስራውን ሲሰራ አገኙት፡፡

እንዴት እንዳላዘነ ሲጠይቁት እሱ መለሰ “ለምን መጥፎ ስሜት ይሰማኛል? እኔ የማይወደኝን ሰው አጣሁ ፤ እሷ ደግሞ በእውነት እሷን የሚወድ እና የሚንከባከባት አጣች ፡፡ ሕይወት ይቀጥላል”
***
ያፈቀርነው ስው ሁሉ የኛ መሆን አለበት ብሎ የሙጢኝ ማለት እራስን ለጉዳት ይዳርጋል፡፡ ሰው ካፈቀረው ጋር የግድ መኖር አለበት? ምን ታስባላችሁ?
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንበብ ለንባብ

https://telegram.me/geyone
​​​​​​​​━━━━━━━━》❈《━━━━━━━

ለእኛ መች ጠቀመን


ለእኛ መች ጠቀመን ዘር ዘር ማለታችን፣
ጥላቻ ፈጥሮብን ፈርሶ አንድነታችን፣
መባሉ ቀረ እና ኢትዮጲያ ሀገሬ፣
ዘር እያስቆጠረን እያል ብሄሬ (ዘሬ)፣
ሰላም እየራቀን ከትላንቱ ዛሬ።
ፈጣሪ ሲፈጥረን አላበላለጠን፣
ሁሉንም ሰው ብሎ መጠሪያ ስም ሰጠን።

ፍፁም ሣያዳለ በእኩል አይን አይቶ፣
የሰውነት አካል ሳይቀንስ አሟልቶ፣
እንድንኖርባት መሬትን ዘርግቶ።

ታድያ ምን ይባላልየእኛ ትዛዝ ማጠፍ?
ለእርስ በእርስ ግጭት ለመሞት መሰለፍ።
ልማትን እረስተን ጦርነት መቀጠር፣
ህይወትን ማጨለም እድሜን ለማሳጠር።

ይሄን ዘረኝነት ምናል ብንረሣው፣
ከአፍ ብናጠፋው ደግመን ባናነሣው፣
ለሞት ለእልቂት ሰጥቶን ሲበዛ ወቀሣው፣

ከአሁኑ ብንተወው እንዳይሆን ልማድ፣
አብሮን እንዳያረጅ ከደም ከስጋችን እንዳይዋሀድ፣
እንዳይተላለፍ ለቀጣይ ትውልድ፣
መናገሪያ እንዳይሆን ለልጆች አፍ መፍቻ፣
ስሙን እንዳይወዱት መስሎ መጫወቻ፣
አብሮቸው ካደገ ለጥውልድ ፀር ነው ይፈጥራል ጥላቻ።


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘


አዘጋጅ፦ ፍቅሬን በግጥM

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

https://telegram.me/geyone
ውድ የልቤ ትርታ ቤተሰቦች ሰላማቹ ይብዛ 🙏
ሴና የተሰኘ አዲስ እውነተኛ የፍቅር ታሪክ ላይ የተመሰረተ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ይዜላቹ ተመልሻለው አስተማሪ ታሪክ ስለሆነ ለምትወዱአቸው ጓደኞቻቹ ሼር ያልጉላቸው እነሱም ቢያነብት ሊማሩበት ይችላሉ

መልካሙን ሁሉ እመኝላቹሀለው
👍 በማድረግ አብሮ
‍ ​​​​ .°• ሴ ና🌺

ክፍል አንድ

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
የባለ ታሪኩዋ ስም ተቀይሮዋል፡፡

"ይህ ታሪክ የኔ ስለሆነ ሴና ብዬ ሰይሜዋለው፡፡"

ሴና እባላለሁ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ 2ኛ ዓመት የህግ ተማሪ ነኝ፡፡ ተወልጄ ያደኩት እዚሁ ሀዋሳ 05 ሚባለው አካባቢ ሲሆን የምኖረው ከቤተሰቦቼ ጋር ነው፡፡ ለቤቱ ብቸኛዋ ሴት ልጅ ስሆን 2ታላላቅ ወንድሞች እና 1ታናሽ ወንድም አሉኝ፡፡ ሴት ልጅ እኔ ብቻ ስለሆንኩ ይሁን በሌላ ምክንያት አላውቅም ግን ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር እና ክትትል ነበር ሚደረግብኝ፡፡
በፍፁም privacy ሚባል ነገር የለኝም፡፡ ከ 1ኛ እስከ 12 የተማርኩት እዛው በቅርባችን የሚገኝ ትምህርት ቤት ሲሆን ከትምህርት ቤት ስወጣ ቀጥታ ወደ ቤት ነው ምመለሰወ፡፡ 12ቱን በሙሉ ጓደኛ ምን ምን ሳልል በቤተሰቦች ከፍተኛ ቁጥጥር ስር ሆኜ ምንም ነገር ሳለይ አና ሳላደርግ የዩኒቨርሰቲ መግቢያ ፈተና ተፈተንኩ፡፡
ውጤት ሲመጣልኝ ከቤተሰብ መራቅ ስለምፈልግ ራቅ ያለ ዩኒቨርስቲ መግባት ፈልግ ነበር፡፡ እንደ ፈለኩትም ሌላ ዮኒቨርስቲ ደረሰኝ፡፡ ነገር ግን አባቴ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ውሰጥ የሚያውቃቸው ሰዎች ስለነበሩ ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ አስቀየረኝ፡፡እንዳሰብኩት ነፃነት ማግኘት አልቻልኩም፡፡ አሁንም የቤተሰቤ ቁጥጥር ስር ወደኩ፡፡የምዝገባ ቀን ከታላቅ ወንድሜ ጋር ሄጄ ተመዝግቤ ግቢውን አስጎብኝቶኝ ዶርሜን አሳይቶኝ ወደቤት ተመለስኩ፡፡ሀዋሳ ዩኒቨርስቲን ከዚህ በፊት በ ቲቪ እንጂ በአካል አይቼው አላውቅም ብል ማን ያምነኛል፡፡
ወንድሜ ትምህርት ሚጀመርበትን ቀን ተከታትሎ እንደሚያሳውቀኝ ነግሮኝ ወደቤት ተመለስኩ፡፡ የዶርሜን ልጆች እንኳን አልተዋወኳቸውም፡፡
ለመጀመሪያ ግዜ ስልክ የያዝኩት የዛን ቀን ነበር፡፡ ግን ከቤተሰቦቼ ውጪ የማንንም ስልክ ስለሌለኝ ለግዜው ሙዚቃ ማዳመጫ ነው ያደረኩት፡፡ ሙዚቆቹንም ግን ወንድሜ አስጭኖ ያመጣቸው ናቸው፡፡
ቀናት ቆጠሩ ትምህርት ተጀመረ በጥዋቱ ወንድሜ የ ዩኒቨርስቲው በር ላይ አድርሶኝ ሄደ፡፡ የዩኒቨርስቲው በር ላይ ቆሜያለሁ . . .

ይ ቀ ጥ ላ ል.......

#ክፍል_ሁለትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️ https://telegram.me/geyone https://telegram.me/geyone
••●◉Join us share◉●••
​​ሴና💔

❤️❤️ ክፍል ሁለት ❤️❤️

ቀናት ተቆጠሩ ትምህርት ተጀመረ በጥዋቱ ወንድሜ የዩኒቨርስቲው በር ላይ አድርሶኝ ሄደ፡፡ የዩኒቨርስቲው በር ላይ ቆሜያለው ፡፡
ግራና ቀኙን መመልከት ጀመርኩኝ ተማሪዎች ፣ መምህራን፣ ተሽከርካሪዎች ይገባሉ ይወጣሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ ሰው መሀል አንድ የማውቀውን ሰው ባገኝ ስል በውስጤ እየተመኘው ወደ ገቢው ገብቼ ወደ ዶርሜ ማቅናት ጀመርኩ፡፡ ወደ ዶርሜ አካባቢ ስደርስ ሴት ተማሪዎች ሁለት ፣ሶስት እየሆኑ እየተሳሳቁና እየተጨዋወቱ በእጃቸው ማስታወሻ ደብተር ይዘው ወዲያ ወዲ ሲተራመሱ አየሁ፡፡ 'መቼ ተዋዉቀው እንደዚ ተግባቡ?' ስል ራሴን እየተየኩ ወደ ዶርሜ ህንፃ ገባሁ፡፡ ዶርሜ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ዶ.ቁ21ነው፡፡ ደረጃውን ወጥቼ ወደ ዶርሜ ስቃረብ እኔ ከተመደብኩበት ዶርም 3ሴቶች እየተሳሳቁ ሲወጡ ተመለከትኩ ቀርቤ ሰላምታ አቅርቤላቸው እዚህ ዶርም እንደሆንኩ ነገርኳቸው፡፡ልጆቹም በቅንነት የያዝኩትን ሻንጣ ተቀብለውኝ ወደ ዶርም አብረውኝ ተመለሱ፡፡
ገና ዶርሙን ከፍተው ስንገባ የተለያየ የቅባት ፣ዶድራንት እና የሽቶ ሽታ በመደባለቅ ለዶርሙ ልዩ ጠረን ሰጥተዉታል፡፡ ዶርሙ ዉስጥ አራት ተደራራቢ አልጋዎች ግራና ቀኝ ተቀምጠው በመሃላቸው አንድ ባለ አራት በር ቁምሳጥን አለ፡፡ በተጨማሪም ከመግቢያ በሩ በስተቀኝ እና በስተግራ ባለ ሁለት በር ቁምሳጥኖች አሉ፡፡የተደራራቢ አልጋዎች የታችኞቹ በሙሉ በጨርቅ ተጋርደዋል፡፡ በዉጭ በኩል ያለው መስኮቱ በመጋረጃ ስለተሸፈነ ክፍሉ ጨለም ብሎአል፡፡ በከልጋዎቹ መሀል መሬት ላይ ሁለት ትንንሽ ጠረቤዛዎች ተቀምጠዋል፡፡ሁሉም አልጋዎች ተነጥፈዋል፡፡ መሬቱም በአግባቡ ስለመፀዳቱ ራሱ ይመሰክራል፡፡ ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ፡፡
ሻንጣዬን የተቀበለችን ልጅ ጥግ ካለው አልጋ ላይ እያስቀመጠች "ሴና አልጋሽ ይሄ ነው፡፡ ያው ባዶ ከሚሆን ብለን ነው ያነጠፍነው፡፡" አለችኝ ፈገግ እያለች፡፡ሁለቱ ሴቶች ከወደበሩ ቆመዋል፡፡ስሜን እንዴት እንዳወቀች ገርሞኛል፡፡ ግን መጠየቅ አልፈለኩም፡፡ ልጅቷ ቀጠለች "ይሄ ደሞ ሎከርሽ ነው፡፡"አለች ከባለ አራት በሩ ቁም ሳጥን የአንዱን በር ከፍታ እያሳየችኝ፡፡አንድ ነገር አወኩ እኔ ቁምሳጥን ብዬ የጠራውት የዶርም ስሙ ሎከር መሆኑን፡፡
"የክላስ ሰአት አልደረሰም?" ስል ጠየኳቸው፡፡ "ባክሽ ዛሬ ዝም ብሎ ነው አይጀመርም ነገ እንገባለን፡፡" አለችኝ ሎከሩን መልሳ እየዘጋች፡፡ከሁዋላዬ የቆሙትም በአውንታ ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡እኔም ባሉት ተስማምቼ ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን፡፡ ለመጀመሪያ ግዜ ከክፍል ቀረው፡፡ ቁጭ ብለን ማውራት ከመጀመራችን ስልኬ ጠራ፡፡ ወንድሜ ነው!

#ክፍል_ሶስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
​​ሴና

ክፍል ሶስት

. . . ቁጭ ብለን ማውራት ከመጀመራችን ስልኬ ጠራ፡፡ ወንድሜ ነው! ደነገጥኩ! ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩ ስልኬን ይዤ፡፡ልጆቹ እንደተቀመጡ እየተመለከቱኝ "ምነው?!" አሉኝ፡፡ ወንድሜ እንደሆነና በጣም እንደሚቆጣኝ ስነግራቸው ስልኩን አታንሺው አሉኝ፡፡ ቡሀላ ደውለሽ "ክፍል ስለነበርኩኝ ነው ትይዋለሽ፡፡" አሉኝ፡፡ እሺ ብዬ ስልኬን አስቀመጥኩ፡፡ ጨዋታቸው ስለጣመኝ ቁጭ ብዬ ወሬያችንን ካቆምንበት መቀጠል ጀመርን፡፡ እንደዛ ቀን ወረኛ ሆኜ አላውቅም፡፡ በየወሬው መሀል እኔም የራሴን ነገር ስናገር ስንጨዋወት ስንስቅ . . .ራሴን እስክታዘበው ድረስ ነበር ምስቀው ማወራው፡፡ ከጠበኩት በላይ ደስ አለኝ፡፡ እያወራን እየተጫወትን ምሳ ሰአት ደረሰ፡፡ ለወንድሜ ደውዬ 'ክፍል ነበርኩኝ ለዛ ነው ያላነሳውት' አልኩት፡፡ ለመጀመሪያ ግዜ ዋሸው፡፡ ድምፄ እየተርገበገበ ፊቴን ላብ እያሰመጠኝ ነበር፡፡ "ዶርም እደሬ ባይሆን ነገ መጥቼ ወስድሻለው ልልሽ ነበር፡፡ በይ በቃ ማታ ደውላለው፡፡" ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡ ተመስገን አልተቆጣም፡፡አናግሬ ስጨርስ ልጆቹ እየተመለከቱኝ "ወንድምሽን ለምን እንደዚ ትፈሪዋለሽ?"ሱሉኝ መልስ አልሰጠዋቸውም፡፡ ምሳ የት እንደሚበላ ጠየኳቸው፡፡ "እኛ ካፌ ነን አንቺ ካፌ ኦር ነን ካፌ ነሽ?" ስትል አንዷ ጠየቀችኝ፡፡ አልገባኝም ግን መጠየቅ አልፈለኩም እነሱ ከሚበሉበት እንድንሄድ ተስማምተን ከ ዶርም ወጣን፡፡ ካፌ ስንደርስ ብዙም ተማሪ የለም፡፡ "አይ ዛሬም የበራበት ላይ ነን !" አለች አንደኛዋ፡፡ አረፈድን ማለቷን ውስጥ ገብተን ያለቀበት ሲደርሰን ገባኝ፡፡
ካፌው በጣም ትልቅ አዳራሽ ሲሆን ውስጡ ግን ቡክትክት ብሎአል፡፡ ምግባችንን እንደያዝን ተማሪ ወዳልበዛበት መቀመጫ ሄደን ተቀመጥን፡፡ ገና ከመቀመጣችን ሁለት ወንድ ልጆች እኛ ወደተቀመጥንበት መጡ፡፡

#ክፍል_አራትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️


,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
​​​​​​​​​​​​​​​​​​━━━━━━━━ ❈ ━━━━━━━━



➲ ​••● ፍቅሬን ተረጂልኝ ●​••


ልቤ ላይ ያሰርኩት የዝምታ ማተብ
በሀቅ የታሰረ የእምነቴ ገደብ
ፈሪ ነህ ተብየ በሀሰት ስሰደብ
በቃላቶች ጅረት እውነቴ ሲታጠብ
:
አደዩ ልብሽን በቃላት ባልቀስመው
ጠላት ምቀኛሽን በነገር ባልነድፈው
ቃሌ ባያረካሽ ውስጥሽን ባይነካው
ዝምታየ ጥልቅ ነው ማንም ያተረዳው
:
የቃላት ጥርቅም የሀገሬ ስብጥር
የዓንቀፅ ጋጋታ የድርሰቶች ክምር
ፍቅርን ላያፀና በቃል ለሚሰበር
ዝምታ ሀቅ ነው ምንም የማይበገር
:
ልብሽን ባገኘው በቃላት ደልየ
የሞተ አስነስቼ ያለውን ገድየ
ልብሽ ላይ ከምሰፍር ውስጤን አታልየ
መኖር ይሻለኛል እራሴን በድየ
:
ግን ልብሽ ጆሮ ሁኖ ውስጤን አድምጠሽው
የዝምታ ገዳሜን ቆርበሽ ጎብኝተሽው
የልቤ ኪዳኑን በልብሽ ከትበሽው
ፍቅሬ ላይ ኮብልይ ሀቄን ተረድተሽው።

@Muba88

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘

አዘጋጅ፦ ፍቅሬን በግጥM

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

@geyone
@geyone
​​❤️ ሴና

ክፍል አራት

ገና ከመቀመጣችን ሁለት ልጆች እኛ ወደተቀመጥንበት መጡ፡፡ አጠገባችን እንደደረሱ አንደኛው "አንቺን የመሰለች ቆንጆ ካፌ?" ሲል እንደተገረመ ሰው አፉን ያዘ፡፡ "ችግር አለው እንዴ?" ስል ድምፄን ዝቅ አድርጌ ጠየኩ፡፡ ሁሉም ሳቃቸውን ለቀቁት፡፡ ደነገጥኩኝ! ያወራውት ያስቃል እንዴ? እኔንጃ ብቻ ወንዶቹም እየሳቁ ወንበር ጠርገው ተቀመጡ፡፡ "ይሄ ዴቭ ይባላል ይሄደሞ ፍሬ ከአንድ አገር ነው የመጣነው ጉዋደኞቼ ናቸው፡፡" ስትል ቀልጠፍ ብላ ታስተዋውቀኝ ጀመር ከጎኔ የተቀመጠችው የዶርም ጉዋደኛዬ፡፡ አሁን ገባኝ ለምን እንደሳቁ እነሱ ለካ ቀድሞውኑኑ ይተዋወቁ ኖረዋል፡፡
"ምንድነው ውጦ ዝም?" አለኝ ዴቭ የተባለው 2ክንዱን ጠረቤዛው ላይ አስደግፎ በእጁ ጉንጩን ደግፎ በትኩረት እየተመለከተኝ፡፡ "እንዴ መች በላው ምንድነው የዋጥኩት?" ስል ጠየኩት፡፡ አሁን ከቅድሙ የበለጠ ሳቁ፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ "የኛን ሰምተሽ ዝም አልሽ አንቺም ራስሽን አስተዋውቂን ለማለት ነው፡፡"ሲል ፍሬ የተባለው ቀስ ብሎ ነገረኝ፡፡ አንተ ምን አገባህ እያሉ ወረዱበት፡፡ስሜን እና የሀዋሳ ልጅ መሆኔን ነገርኳቸው፡፡ "ሙሉ ዶርሙ ሴና ሆነ በቃ" ሲል ዴቭ ሳቀ፡፡ ለካ ዶርም ውስጥ ሁላችንም ሴና ነው ስማችን፡፡ አሁን ነው ያወኩት፡፡ ግን ዝም አልኩ፡፡ ምግብን የሁላችንንም አንድ ትሪ ላይ ገለበጡት፡፡ ዴቭ እና ፍሬ ብሉ ሲባሉ "እኛ ሰቅለን ነው የመጣነው፡፡" አለ ዴቭ፡፡ ሚጠቀመው ቃል ግራ እየገባኝ ነው፡፡ ግራ መጋባቴን አይቶ "በልተን ነው የመጣነው ለማለት ነው፡፡" ሲል ፍሬ በኔ አማርኛ ተረጎመልኝ፡፡ መብላት ጀመርን፡፡ ምግቡ ገና ስቀምሰው ጠአሙ ብዙም አይመችም፡፡ ግን እነሱን ላለማስቀየም ስል ዝም ብዬ መመገብ ጀመርኩ፡፡ እኛ እየበላን ዴቭ ይለፈልፋል፡፡ በመሀል ይስቃሉ፡፡ ፍሬ ምንም አይናገርም፡፡ አልፎ አልፎ ፈገግ ይላል፡፡ አይኔን ቀና ባደረኩ ቁጥር አይን ለ አይን እንጋጫለን ከፍሬ ጋር፡፡ ዴቭ ወሬውን እንደቀጠለበት ነው ፡፡ ምግቡን ወደመጨረስ ስንቃረብ "በቃ ይሄ ተመላሽ ነው በቃቹ!" ሲል ትሪውን አነሳው፡፡ አንተ አረ እንብላበት ቢሉትም አልሰማም አለ ትሪውን ይዞት ሄደ፡፡ እኔ ምንም አላልኩም፡፡ "አይ ሊጋብዘን ነው ማለት ነው" ስትል አንደኛዋ ተናገረች እየተሳሳቅን ከመቀመጫችን ተነስተን ወደ ውጪ ወጣን፡፡ ስንወጣ የካፌው መግቢያ በር ዝግ ነበር፡፡ ከወጣን በሗላ ዴቭ "የወሰድኩትን ምሳቹን ልካሳቹ" ሲል ሁሉም እሺ ብለው ተስማሙ፡፡ አኔን ሲጠይቁኝ ብቻዬንም ብሆን መሄጃ ስለሌለኝ ተስማምቻቸው ግቢ ውስጥ ወደሚገኝ ተከፍሎበት ወደሚመገቡበት ካፌ ሄድን፡፡ እንደደረስን ዴቭ "እነሱን ተያቸው ቢሆንላቸው እኔን ይበላሉ ስለዚ አልጠይቃቸውም አንቺ ምንትበያለሽ?" ሲል ጠየቀኝ፡፡ "አረ ዴቭ ይደብራል..."እያሉ ያጉረመርሙ ጀመር "እኔ ምንም አልፈልግም ጠግቤያለው፡፡" አልኩት ደግሞ ቢጠይቀኝም አለመፈለጌን ገለፅኩለት፡፡ በቃ ግብዣው ለ እራት ይሁን በሚለው ተስማምተን ከመጣን አይቀር ለምን ፑል አንጫወትም አሉ፡፡ ሁሉም ተስማሙ፡፡ እኔ ተጫውቼ እንደማላውቅ ነገርኳቸው፡፡ እንደለመዱት መሳቅ ጀመሩ፡፡ ፍሬ "አሁን ይሄ ምኑ ያስቃል ምድረ ዱርዬ ደና ነገር አውቃቹ ሞታችሗል! ነይ አንቺ እነሱ ይጫወቱ" ተያቸው ብሎ እጄን ይዞኝ ከ ካፌው ወጣ፡፡
ከካፌው እንደወጣን እጄን ለቆኝ ቆመ፡፡ እኔንጃ ከ አባቴ እና ወንድሞቼ ውጪ ወንድ እንደዚ እጄን የያዘበት ቀን ትዝ አይለኝም፡፡ ፍሬ እንደዛ ለምን እንደተናደደባቸው እባይገባኝም በኔ ላይ መሳቃቸው እንዳበሳጨው ያስታውቅበታል፡፡ ካፌው በር ላይ እንደቆምን እነ ዴቭ አጥርቼ ባልሰማቸውም ከውስጥ የሆነ ነገር ብለው ይስቃሉ፡፡
"ቡና ትጠጫለሽ?" አለኝ ትህትና በተሞላበት ድምፅ እኔ ብና እንደማልጠጣ ነግሬው እንግዲያውስ አሪፍ ቦታ ላሳይሽ ብሎ ይዞኝ መሄድ ጀመረ፡፡

ዛሬ ቀኑ ተለወጠብኝ፡፡ እንደዚ አይነት ቀን ገጥሞኝ አያውቅም፡፡ ከጥዋት ግቢ ከገባውበት ሰአት አንስቶ ብዙ አዲስ ነገሮችን አደረኩ፡፡ በአንድ ቀን እንደዚ ሰው መቅረቤን እያሰብኩ ገረመኝ፡፡ በዙ ሀሳብ በውስጤ እየተመላለሰ ከፍሬ ጋር መሄዴን ቀጠልኩ . . .

#ክፍል_አምስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
​​💓ሴና

ክፍል አምስት


. . . ብዙ ሀሳብ ውስጤ እየተመላለሰ ከፍሬ ጋር መሄዴን ቀጠልኩ፡፡ አብረን ስንሄድ አናወራም የተኮራረፍን ነው ምንመስለው፡፡ትንሽ እንደሄድን የሆነ መቀመጫ ያለበት መናፈሻ ነገር ስንደርስ እዚ እንሁን ብሎኝ ተቀመጥን ጎን ለጎን፡፡ መንም አናወራም . . ሄአልፎ አልፎ ሰረቅ እያረገ ያየኛል፡፡ ዝምታው ሲበዛ ጨነቀኝ መጨናነቄን አይቶ መሰለኝ "አገሩን ለመድሽው?" ሲለኝ ሳቄን ለቀኩት "ማለቴ ጊቢውን ለመድሽው?" ሲል እየሳቀ አስተካከለው፡፡ "ብዙም ባይሆን . . ." እያልኩ ጨዋታችንን ጀመርን፡፡በጣም ብዙ ሰአት ተቀመጥን፡፡ መምሸት ሲጀምር ዴቭ ለ ፍሬ ደወለ፡፡ተነስተን ወደነ ዴቭ ሄድን፡፡ እዛው ናቸው፡፡ ሌሎች ልጆችም ተሰብስበው ፑል እየተጫወቱ ነው፡፡ "አይደክማቸውም እንዴ?" አለ ፍሬ በግርምት እየተመለከታቸው፡፡ ዴቭ መቶ እጄን ጎትቶ ከልጆቹ ጋር ያስተዋውቀኝ ጀመር፡፡ልጆቹን በሙሉ ተዋወኳቸው፡፡ ወይ ዛሬ ቀን እስከዛሬ ከማውቃቸው ሰዎች በላይ በአንድ ቀን ይሄንን ሁሉ ሰው ማወቄ እያስገረመኝ ነው፡፡
ምሽት እራት ሰአት ሲደርስ ዴቭ በቃሉ መሰረት እራት ጋበዘን፡፡ እራት እየበላን ወንድሜ ደወለ፡፡ ረጅም ሰአት ስልክ አወራው፡፡ እናቴን አባቴን እና ሁለቱ ወንድሞቼን፡፡ ስልክ አውርቼ ስመለስ እራቱን በልተው ጨርሰዋል፡፡ "ስትቆይ እኮ ጨረስነው፡፡ ላንቺ ይምጣልሽ"አሉኝ፡፡ እንደማግደርደር እያልኩኝ ዴቭ ይዞ መጣ፡፡ እንብላ አልኩኝ ዴቭ እሺ ብሎ እጁን ሰነዘረ፡፡"አን ትብላበት!::"ሲል ፍሬ ተቆጣው፡፡ ምንም አልተናገርኩም፡፡
እኔ እየበላው እነሱ እያወሩ እራቴን ጨርሼ እኔም ወደወሬያቸው ተቀላቀልኩ፡፡ በጣም ብዙ አወራን ተጫወትን፡፡ በጨዋታው መሀል ሰአቱ ሳናስበው ሄደ፡፡ እንቅልፍ ተጫጫነኝ፡፡ "አንገባም?" ስል ከጨዋታ አቋረጥኳቸው፡፡ "እውነትም መሽቷል 4 ሰአት ነው፡፡ ሁላችንም ተነስተን ከካፌው ወተን ወደ ሴቶች ዶርም መሄድ ጀመርን፡፡መንገዱ ላይ ቡዙ ተማሪም የለም፡፡ሶስቱን የዶርሜን ልጆች ዴቭ ከወሀላቸው ሆኖ እያሳቃቸው ከፊት ለፊት እኔና ፍሬ ከሁዋላ ሆነን መሄድ ጀመርን፡፡ ወደሴቶች ዶርም መግቢያ መንገድ ስንደርስ ዴቭ እና ፍሬን ተሰናብተን አራታችን ሆነን ወደ ዶርም ገባን፡፡

ዶርሙ ትተነው እንደወጣነው ነው ያለው፡፡ "ቆይ ሌሎቹስ የት ናቸው?" ብዬ ጠየኩኝ ፡፡ ማንም መልስ አልሰጠንም፡፡ ሻንጣዬን ከፍቼ ልብሴን ቀየርኩኝ ሁላችንም ልብሳችንን ቀይረን እኔ አልጋዬ ላይ ወጥቼ ጋደም ከማለቴ ስልኬ ጠራ፡፡የማላውቀው ቁጥር፡፡ አላነሳውትም ሌሎቹ ደክሞዋቸው ስለነበር ብዙም አላወራንም በየመኝታቸው ወጥተው ተኙ፡፡ እኔም ደክሞኛል እንቅልፌ ግን አልመጣ አለ፡፡ አሁንም ስልኬ ጠራ፡፡ የቅድሙ ቁጥር፡፡ "ማነው በዚ ሰአት" አለች እንቅልፍ በተጫጫነው ድምፅ ከኔ በታች የምትተኛዋ ልጅ፡፡
"አላውቀውም"
"ሰካራም ይሆናል አጥፊውና ተኚ፡፡"
"እሺ" አልኳት ስልኬን ሳይለንት አድርጌው ተኛው፡፡ ከመተኛቴ የዶርሙ በር ተንኳኳ፡፡

#ክፍል_ስድስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️
https://telegram.me/geyone

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
​​ሴና💗

ክፍል ስድስት

ከመተኛቴ የዶርሙ በር ተንኳኳ፡፡
"ኡፍፍፍ ዲጄዎቹ መጡ ደሞ!" እያለች በሩን ለመክፈት ተነሳች ከወደበሩ ባለው የላይኛው አልጋ ላይ ምትተኛው፡፡ ተነስታ በሩን ስትከፍተው ሶስት ሴቶች እየተሳሳቁ ገቡ፡፡
"አቦ ለምንድነው ቁልፍ የማታስቀርፁት?" ስትል ተቆጣች በሩን የከፈተችው፡፡"
ባክሽ በቀን አንድ ግዜ ለምንከፍተው በር ነው ቁልፍ ምናስቀርፀው?" ስትል ከሚሳሳቁት ሴቶች መሀል አንደኛዋ በስካር መንፈስ በተኮለታተፈ ቃል እንደማሾፍ ተናገረች፡፡ በሩን የከፈተችው ምንም አላለችም አልጋዋ ላይ ወጥታ ተኛች፡፡ ሶስቱ ልጆች የጀመሩትን ወሬ ቀጠሉ በመሀል በመሀል እየሳቁ የዶርሙን ፀጥታ ያውኩት ጀመር፡፡
"አቦ እንተኛበታ አትረብሹን!" ስትል ደግማ ተናገረች በሩን የከፈተችላቸው አልጋዋ ላይ ሆና፡፡ "እማሆይ ተቆጡ አሽሽሽሽ" እየተባባሉ ድምፃቸውን ቀንተሰው መንሾካሾክ ጀመሩ፡፡
የመጀመሪያዎቹ ሶስቱ የዶርሜ ልጆችን ባወኩ ሰአት በጣም ደስ ብሎኝ ነበር፡፡ገና በመጀመሪያ ቀን በጣም ተግባብቻቸው ሌሎች ጉዋደኞችም አፍርቼ ነበር፡፡ ግን ደሞ አሁን እነዚህ ሶስቱን እንደዚ ሰክረው በዚህ ሰአት ሲመጡ ሳይ የሆነ የመጨናነቅ እና የመረበሽ ስሜት ፈጠረብኝ፡፡ ገና ሳያቸው ምግባባቸው አልመስልሽ አለኝ፡፡ እኔንጃ ብቻ የሆነ ቅር ሚል ነገር ተሰማኝ፡፡ እነሱ ይንሾካሾካሉ ፣ይተራመሳሉ፡፡ ደሞ የቀሩት ሁለቱ ልጆች ምን አይነት ይሆኑ ፊቴን ወደ ግርግዳ አዙሬ ተኛው፡፡
ጥዋት አንደኛዋ ልጅ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰችኝ፡፡
"ክላስ አትገቢም እንዴ?"
ሞባይሌን ከፍቼ ሰአት አየው ሁለት ሰአት ሊሆን ነው፡፡ ማታ ድካም ነበረብኝ እንቅልፍ ግን መች እንደወሰደኝ እንጃ ግን እንቅልፌን አልጨረስኩም፡፡
የማታዎቹ ሰካራም ልበላቸው ፤ሰካራሞቹ አንድ አልጋ ላይ ለብሰው በነበረው ልብሳቸው ተኝተዋል፡፡ ምንም አልተናገርኩም፡፡ እኛ ተጣጥበን ልብሳችንን ቀያይረን ወጣን፡፡
"ግን ቁልፍ ከሌላቸው በምን ይዘጋሉ በሩን?" ስል ጠየኩ
"እንደዚ ጥንብዝ ብለው ከመጡ እስከ ከሰአት አይነሱም፡፡" ሲሉ መለሱልኝ፡፡
ቁርስ እንኳን ረፍዶብናል ቀጥታ ወደ መማሪያ ክፍል አመራን፡፡ እየሄድን እያለ ዴቭ መንገድ ላይ ተገናኝተን አብረን መሄድ ጀመርን፡፡ ሶስቱ ሴቶች ከፊት እኔና ዴቭ ከሁዋላ ሆነን . . .
ወደ ክፍሎቹ ስንደርስ እሱ ከኛ ተለየ ክፍሎቹ አካባቢ ብዙ ተማሪዎች አሉ፡፡ ግን እኔ ማውቀውን በአይን መፈለግ ጀመርኩ፡፡
የኛ ክፍል ወዳለበት ፎቅ ስንደርስ አንድ የሴት ድምፅ "ሴና ሴና" ሲል ከሁዋላችን ተጣራ፡፡ አራታችንም ዞርን . . .

#ክፍል_ሰባትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

https://telegram.me/geyone

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••