የልቤ ትርታ
202 subscribers
473 photos
4 videos
10 files
422 links
Download Telegram
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_5

...🖊ቃልዬ በጣም ነው ማፈቅርሽ አንደበቴ ቁልፍልፍ አለ መናገር አቃተኝ በወቅቱ ምን እንደሚሰማኝ አላውቅም በጣም ደስ እንዳለኝ አቃለው ግን ቅር ቅር የሚለኝ ነገር አለ ምንድን ነው እንዴ እረስቼው ሜሮን አ.... ስትል ነበር ስልኬ ጮሆ ማንን እንደነበር ሳልጠይቃት ነበር የመጣውት አሁን ለአቤል እንደምወደው ከነገርኩት እርሷም እርሱን ከወደደችው ትጎዳለች ታዳ ምን ልበለው በጣም ጨነቀኝ ዝምታዬ ያስጨነቀው አቤል ቃልዬ ምነው ዝም አልሽ አንድ ነገር በይ ማፍቀሬ ስህተት ሆኖ ከታየሽ ስደቢኝ ምችኝ ብቻ አላውቅም ቅጪኝ ግን እባክሽ ዝም አትበይኝ ዝምታሽ ያስፈራል አለኝ እኔም እንደማንገራገር አልኩና ትንሽ ጊዜ ስጠኝ ማሰብ እፈልጋለው አልኩት እርሱም ችግር የለውም የፈለግሽውን ያክል ጊዜ ወስደሽ አስቢበት አለኝ እሺ ብዬው ቻው ተባብለን ተለያየን ከአቤል አፍ ይሄ ይወጣል ብዬአንድም ቀን አስቤው አላውቅም ግን በጣም ደስ ብሎኛል አሁን ችግሩ ሜሪ ማንን ነው ምትወደው ነው ከራሴ ጋር እንዲህ እየታገልኩ ዶርም ደረስኩ ስደርስ ግን ሜሪ ብዙ ከማልቀስዋ የተነሳ እራስዋን አሟት ተኝታለች አስተኛኘቷ ልክ እንደህፃን ነው ታሳሳለች በቃ ነገ አወራታለው ብዬ ወደ መኝታዬ ሄድኩ ለመተኛት ብሞክርም ምንም እንቅልፍ አልመጣም አለኝ ላነብ ብልም እንኳ በቃ ቅዥብ ብያለው አይነጋ ነገር ለሊቱ አመታት ሆኖብኝ ነጋ ጠዋት ገና እንደተነሳን በደንብ እንኳን ሳትነቃ ከማን ፍቅር እንደያዛት ጠየኳት ትንሽ እንደመሽኮርመም ብላ አ አ አ ስትል ኧረ በፈጣሪ ይሁንብሽ ንገሪኝ ስላት በቃ እሺ አማንን ነው የወደድኩት አለችኝ ምን አማን አልኳት አዎ አማን አለችኝ እርግጥኛ ነሽ አልኳት ያምሻል ምን ማለት ነው ስትለኝ እውንትም ያመኛል ምን አይነት ጥያቄ ነው የጠየኳት

ግን አቤል ትላንት እንደሚያፈቅረኝ ከነገረኝ በላይ ዛሬ ደስተኛ ሆንኩ ከዛ የስ ምናምን እያልኩ ሳብድ ምን ሆነሽእንዴት ነው ዛሬ ግን በሰላም ነው አለችኝ በጣም ደነገጥኩ የማደርገው ነገር ለራሴም ገርሞኛል ወደ ማታ አካባቢ እኔና ሜሪ ቁጭ ብለን እያወራን እንደወደደችው እና ብዙ ነገር ነገረችኝ ከዛም ቃል ግን እስኳሁን በፍቅር ያሰብሽው ሰው የለም ስትለኝ አሁን አልነግርሽም ሰርፕራይዝ ነው አልኳት እንድነግራት ብዙ ብትለምነኝም አልነገርኳትም የምንመረቅበት ጊዜ ደርስዋል ለፈተና በጣም እየተዘጋጀን ነው በብዛት ላይብረሪ ነው ምናሳልፈው ለአቤልም ልክ ፈተና እንደጨረስን ሁሉንም ነገር ልነግረው አስቤያለው ይህንኑ ሀሳቤን ስለነገርኩት እርሱም እየተጫነኝ አይደለም ዛሬ ግን በጣም የሚያስጠላ የሚያናድድ ነገር ተፈጠረ አማን ደውሎ ሊያገኘኝ እንደሚፈልግና በጣም አስቸኳይ እንደሆነ ነገረኝ ከዛም እኔ ጋር እንደምትመጪ ለማንም እንዳትናገሪ ብሎኛል ከዛም አስቸኳይ ነው ስላለኝ ፍንጥር ብዬ ስወጣ ሜሪ ወዴት ነው ስትለኝ ማሚ ጋር ልደውል ነው እዚህ ኔቶርክ የለም አልኳት ያልኳት ነገር ባይዋጥላትም እሺ አለችኝ ከዛም አማን ከርቁ ሆኖ እየተንጎራደደ አየውት በቻልኩት ፍጥነት ደርሼ ምን ተፈጠረ ችግር አለ አቤል ምን ሆነ አልኩት አይ ማንም ምንም አልሆነም እኔ ለራሴ ጉዳይ ፈልጌሽ ነው አለኝ ምነው ምን ሆንክ አልኩት ይኸውልሽ ቃል ችግር ውስጥ ነኝ አለኝ የምን ችግር አልኩት ፍቅር ያዘኝ አለኝ እኔም ሜሪን ወደዳት ማለት ነው በቃ ጎደኝነታችን ወደ ፍቅር ሊለውጥ ነው ደስ ይላል እያልኩ እና ጥሩ እኮ ነው ግን ከማን እልኩት አማን ዛሬ አስተያየቱ ተቀይሮብኛል ወደ እኔ ቀስ እያለ መጠጋት ጀመረ ቀስ እያለ በጣም ተጠጋኝ ከዛም ካንቺ ሲለኝ ልቤ ቀጥ አለ መናገር አቃተኝ ደርቄ ቀረው አማን ግን ቀስ ብሎ ልክ ሊስመኝ ሲል ዋው ዋው ስታምሩ የሚል ከጭብጨባ ጋር...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 6 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
መልካም ንባብ
@geyone
@geyone
@geyone
@geyone
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_6
...🖊በጣም ተጠጋኝ ከዛም ካንቺ ሲለኝ ልቤ ቀጥ አለ መናገር አቃተኝ ደርቄ ቀረው አማን ግን ቀስ ብሎ ልክ ሊስመኝ ሲል ዋው ዋው ስታምሩ የሚል ከጭብጨባ ጋር ድምፅ ሰማው ስዞር ሜሪ እና አቤል ናቸው በጣም ደነገጥኩ ግን ስረዳ አቤል እኔ ጋር ሲደውል ሜሪ አንስታ እየተጣደፍኩ እንደወጣው እና የሆነ ነገር እንዳለ ስትነግረው ነው ተከታትለው የመጡት ግን አቤል በጣም እንደተናደደ ያስታውቃል በቃ ለዚህ ነበር ምላሽ መስጠት ያቃተሽ ብትነግሪኝ እኮ ችግር አልነበረውም ለምን ለምን ታሰቃይኛለሽ ቆይ ምን ጋር ጥፍቴ አንቺን ማፍቀሬ ግን እንደዚህ አይነት ሴት አልመሰልሽኝም ነበር ብሎኝ ምላሼን ሳይጠብቅ ሄደ ላስቆመው ሞክሬ ነበር ግን አልቻልኩም ይሄ ሁሉ ሲፈጠር ሜሪ ከማልቀስ ውጪ ያወራችው ነገር አልነበረም አሁን ግን ተራዋ የደረሰ ይመስል ቃል አንቺ እኔን እንዲህ ታረጊኛለሽ የውስጤን ስለነገርኩሽ ትረጂኛለሽ ብዬ አንቺ እኮ ጓደኛዬ ሳትሆኚ ልክ እንደህቴ ነበር ማይሽ አሁን ግን እምነቴን ሙሉ በሙሉ አጥፍተሽዋል ክፉ ክፉ ነሽ እያለች እያለቀሰች ወደ ዶርም ሄደች የሚሆነው ሁሉ በህልም ነበር የመሰለኝ ደርቄ ቀረው የቆምኩበት መሬት ላይ ወደኩ ልክ እኔ ስወድቅ አማን ተንበረከከ ምን ሆንሽ ምንድን ነው የተፈጠረው እነ ሜሪ ምን ሆነው ነው እለኝ ምንም ማለት አልቻልኩም አሁን ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ ነገ ስረጋጋ ሁሉንም እነግርሀለሁ አልኩት ሊያስጨንቀኝ ስላልፈለገ እሺ ወደ ዶርም ልሸኝሽ አለኝ አይ እራሴ እሄዳለው ደና ነኝ እልኩት እባክሽ እንዲ ሆነሽ ብቻሽን ትቼሽ መሄድ አልችልም ሲለኝ እባክህ እማን ተወኝ እራሴ መሄድ እችላለሁ ብዬ ጮኩበት እስከዛሬ ስስቅ እንጂ እንዲህ ስሆን አይቶኝ ስለማያቅ በጣም ደነገጠ እሺ በቃ እሺ ተረጋጊ እሄዳለው ብሎኝ ቀስ እያለ መሄድ ጀመረ የሜሪን አይን እንዴት እንደማየው ምን ብዬ እንደማስረዳት ግራ ገብቶኛል ግን ዶርም ስገባ ጥቅልል ብላ ታለቅሳለች ላናግራት አልቻልኩም በቃ ስትረጋጋ አናግራታለው ብዬ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩ በቃ ከአቤል ጋር እስከመጨረሻው ተጣላን ብዬ አለቀስኩ በጣም በሸኩ ከሁሉም በላይ ከአቤል በፊት የማቃትን ጓደኛዬን ጎዳዋት በእርሷ ዘንድ ታማኝነቴን አጣው ሁሉም ቀርቶብኝ ብያንስ ባናግራት ደስ ይለኛል ግን እርሷ አይኔን ማየት አትፈልግም እንደምንም እየተሟዘዘ ነጋ ገና ሲነጋ አማ ደውሎ ላግኝሽ አለኝ እኔም ትላንት ስላስከፍውት በዛው ይቅርታ እለዋለው ብዬ እሺ አልኩት ከአማን ጋር ተገናኝተን ስለተፈጠረው ነገር በሙሉ ነገርኩት አቤል እንደማፈቅረው ሜሪ ደግሞ እርሱን እንደምትወደድ ብቻ ሁሉንም ነገርኩት ሆድ ብሶኝ ስለነበር ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ከዛም እንድረጋጋ ብሎ አማን እቅፍ ውስጥ አስገባኝ ክፍቶኝ ስለነበር ምንም አላልኩም ማታ አቤል እንደዛ ስለተናገረኝ ይቅርታ ሊጠይቀኝ እና ምን እንደተፈጠረ ላስረዳው ፈልጎ ሲመጣ እኔን እና አማንን ተቃቅፈን አየን ከዛ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 7 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

━━━━━━━✦🌹
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
🌹✦━━━━━━━
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_7

...🖊ማታ አቤል እንደዛ ስለተናገረኝ ይቅርታ ሊጠይቀኝ እና ምን እንደተፈጠረ ላስረዳው ፈልጎ ሲመጣ እኔን እና አማንን ተቃቅፈን አየን ከዛ ቃል አለኝ እያለቀስኩ እንደነበር አይቷል እና አማንን ጥሎን ሄደ አቤል አማን የተቀመጠበት ቦታ ላይ ቁጭ አለና ልትነግሪኝ ምትፈልጊው ነገር አለ ብሎ ጠየቀኝ እኔም ከምላሼ ይልቅ እንባዬ ነበር የቀደመኝ ከዛም ሊያረጋጋኝ ሞከረ ግን ባሰብኝ እኔ አልጠቅምም እያልኩ ማልቀስ ጀመርኩ እንዴ ለምንድነው እንዲህ ምትይው አለኝ አቤሌ የተፈጠረውን እንዳልተፈጠረ አድርጎ ጠየቀኝ የገዛ ጓደኛዬ በኔ ምክንያት ተጎዳች አንተንም አሰቃየውህ እያልኩ አለቀስኩ ከዛ አቤሌ አንድ ነገር ልንገርህ አልኩት ምንድነው ቃሌ ንገርኝ አለኝ እቤሌ ገና እንዳየውህ የመጀመሪያ ቀን ነበር የወደድኩህ ግን ልነግርህ አልቻልኩም ስለው ስልኬ ጮኽ ማም ነበረች አቤት እማዬ አልኳት ምነው ልጄ ይሄን ሰሞን አልደወልሽም በሰላም ነው አለችኝ ደና ነኝ እናቴ ሰለም ናቹ አልኳት እማ ድምፄ ሲለወጥ ታቃለች ልጄ አሞሻል እንዴ ድምፅሽ ትክክል አይደለም አለችኝ አይ እናቴ ምንም አልሆንኩም ትንሽ ጉንፍን ነገር ይዞኝ ነው አልኳት እሺ በቃ ችግር ካለ ልጄ ደውይ እባክሽ አለችኝ እሽ እማ አታስቢ አልኳት ከዛ እርሷን አናግሬያት ዞር ስል አቤል በቦታው የለም ደነገጥኩ ስደውል ስልክ አያነሳም ከዛም ወደ ዶርም ስሄድ ሜሪ የለችም በቃ ዶርም ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ ከ1 ሰአት በኃላ ሜሪ መጥታ ቃል በጣም ይቅርታ ሳልሰማሽ እንደዛ መሆን አልነበረብኝም አለችኝ ግራ የማጋባት ፊት እያሳየዋት አልገባኝም ሜሪ ይቅርታ አረግሽልኝ አልኳት ሲጀመር ምን አጥፍተሽ አማን ሁሉንም ነገር ነግሮኛል አቤልንም እንደምትወጂው እርሱም እንደዛው አይደል አለችኝ እኔ ግን ምንም ሳልላት ተጠመጠምኩባት ከዛ ኧረ ቀስ ገደልሽኝ አለችኝ እና ተሳስቀን ትላንት እና ዛሬ ምንም እንዳላነበብን ፈተና ከ3 ቀን በኃላ እንደሆነ እረስቼዋለው ግን ጊዜው በጣም ይፈጥናል ትኩረታችንን ሙሉ በሙሉ ጥናታችን ላይ አረግን አቤልን ከዛ ቀን ጀምሮ አይቼው አላቅም በጣም ቢያሳስበኝም ግን አሁን ጥናቴ ላይ ትኩረቴን ማረግ እንዳለብኝ አውቃለሁ እንዲህ እያለ ምርቃታችን ደረሰ አራታችንም ተመራቂ ለመሆን በቃን ማም በጣም ደግሳ ነው የጠበቀችኝ

አሁን ከተመረቅን 2 ሳምንት ሞላን አሁን እኔ ድሬ እናቴ ጋር ነኝ ሜሪም አቤልም አማንም ሀዋሳ ናቸው ከአማን እና ከሜሪ ጋር በስልክ እናወራለን አቤልን ግን አግንቼው አላቅም ግን ዛሬ የማላቀው ቁጥር ተደውሎ ማንነቱን ስጠይቅ አቤል ነበር በጣም ደስ አለኝ ምገባበት አጣው ከዛም ድሬ እንደመጣና ማንንም እንደማያቅ ወጥቼ እንድቀበለው ነገረኝ ትንግርት ነው የሆነብኝ አቤል ድሬ ነው ያለው እሺ መጣው በቃ መጣው አልኩት እና ሊያሳምረኝ የሚችል ልብስ መምረጥ ጀመርኩ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ አርጉ፡፡ክፍል 8 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_8

...🖊ሊያሳምረኝ የሚችል ልብስ መምረጥ ጀመርኩ ግን የትኛውንም ልወደው አልቻልኩም ከዛ ከታናሽ እህቴ ለመበደር ፈለኩ እና ዛሬ ቅዳሜ ስለሆነ ክላስ አልነበራትም ማርቲ 12 ክፍል ተማሪ ናት እናም ማርታ እያልኩ መጮህ ጀመርኩ ከዛም የክፍሌን በር ከፍታ ምንድነው ምትተረተሪው ቀስ ብለሽ አትጣሪም አለችኝ ድንጋጤው ነው መሰለኝ በጣም ጮኬያለው አይ ልብስ እንድታበድሪኝ ነበር አልኳት ምን አይነት ልብስ ፈለግሽ ደሞ የት ልትሄጂ ነው አለችኝ አይ የትም አንድ ጓደኛዬን ላገኘው ነው አልኳት እየሳቀች ኧረ ማነው ባክሽ እንዲህ ማዘንጥሽ አለችኝ ኧረ ዝም ብሎ ኖርማል ጓደኛዬ ነው ልብሴ ዛሬ ቆሽሸዋል ለዛ ነው አንቺን ምጠይቅሽ አልኳት ኮስተር ብዬ ትንሽ ማስመሰል እችላለው እና ወድያው አመነችኝ ግን ማስመሰል በጣም ነው ምጠላው ዛሬ ግን ምንም ባልተወራ ወሬ ነገር ብለኩስ መቀጣጠሉ ስለማይቀር ዝም ማለትን መረጥኩ ከዛም በጣም ምወድላትን ቀይ ትሸርት ከሱሪ ጋር ይዛልኝ መጣች ከዛም ፀጉሬን ወደሀላ ለቅቄ ለአመሉ የውሃ ቻፒስት ከንፈሬን ተቀባው ያው ቀይ መቀባት ብዙም ደስ አይለኝም እና ሸንቀጥ ብዬ ወጣው ከዛም ወደ መናሀሪያ ሄድኩ የሚገርመው አቤልን ከብዙ ሰው መሀል ነበር ነጥዬ ያወኩት ከዛም ደወልኩለት አንስ ያለች ጥቁር ቦርሷ ይዟል ወድያው አነሳው የቱ ጋር ነሽ አልኝ አይቼሀለው ፊትህን አዙር አልኩት ልክ ሲዞር አየኝ ከዛም እጄን አውለበለብኩለት ወድያው ስላወቀኝ ወደ መምጣት ጀመረ እኔም ወደሱ እየሄድኩ ነበር ግን ልቤ እጅግ ይመታ ነበር ከዛም ድርሶ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ ሻንታውን ልቀበለው እጄን ስሰረጋ አይሆንም ብሎ ለትንሽ ጊዜ ከተከራከርን በኃላ ሳይፈልግ ተቀበልኩት ከዛም እየተራመድን እንዴት እንደመጣ ጠየኩት እኔን ለማየት እንደመጣና ማንንም እዚህ እንደማያውቅ ነገረኝ ከዛም እኔን ለማየት በመምጣቱ እጅግ በጣም ደስ አለኝ እና ልክ ወደ ኪሱ እጁን ከተተ ከዛ በጣም የደነገጠ ይመስላል ወደሌላኛው ኪሱ እጁን ሰደደ አሁን ይበልጥ ደነገጠና እስቲ ቦርሳውን ስጪኝ ብሎ ቦርሳውን ተቀበለኝ ከዛ ወይኔ እናቴ ቀለጥኩ አለኝ ምነው ስለው ቃልዬ ተዘረፍኩልሽ አለኝ ምን ብዬ ጮውኩ ምን ምትፈልገው እቃ ነበር አልኩት አይ እቃስ ምንም አልተነካም ግን የነበረኝን ገንዘብ በሙሉ ተወስዶብኛል አለኝ እና ስልክህ እንዴት ተረፈ አልኩት ኧረ በእጃ ይዤው ስለነበር ይሆናል አለኝ በቃ አትጨናነቅ ለማሚ ደውዬ እኛ ጋር እንድታርፍ እጠይቃታለው ከዛም ትንሽ ከሱ ገንጠል ብዬ ለማም ደወልኩ እናም ሁሉንም ስነግራት በጣም ደስ እያላት ይዤው እንድመጣ ነገረችኝ ከዛም ና አንድ ማረፊያ ተገኝቷል አልኩት የት ሲለኝ አይ እዚው ቅርብ ነው ዝም ብለህ ና ብዬ ባጃጅ መጠበቅ ጀመርን ከዛም ከመናሀሪያ እቤት ድረስ አንድ ባጃጅ አደረሰን ከምስጋና ጋር ከንዘቡን ሰጥቼ ላኩት ከዛም ለማርቲ ነግሬያት ስለነበር ወጥታ ደጅ እየጠበቀችን ነበር እና ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ወደ ቤት ገባን ከዛም ማም መጥተናል ስላት ከክችን ወጥታ አቤል እርሱ ነው ተዋወቂው አልኳት ባትይኝም እተዋወቀዋለው ይሄን የመሰለ ቆንጆ ከት አመጣሽ አለችኝ ኧረ እማ አልኳት እንደማፈር ብዬ ከዛ ተቀመጥ ከመንገድ ነው የመጣኸው ደክሞሀል አልችው ወደ ሶፍው እየጠቆመች እሺ ማዘር ብሎ ቁጭ አለና በአይኑ ጠራኝ እ አልኩት አጠገቡ ሄጄ አውቆ ፈገግ እያለ እዚህ እንደምንመጣ ለምን አልነገርሽኝም ብሎ አልኝ እና ወደ እህቴ እያየ ፈገግ አለ ከዛ እ አለኝ ቆጣ እያለ ኧረ አትጨናነቅ ልክ እንደ እቤትህ እየው አልኩት እና ማም ስትጠራኝ ማርቲ አጫውቺው ብያት ሄድኩ ከዛ እጁን አስታጥቢው የሚቀምሰው ነገር አዘጋጅቻለው አልችኝ እሽ ብዬ እጁን ላስታጥበው ስሄድ ማርቲናእቤል በጣም የረጅም ጊዜ ጓደኛማቾች ነው የሚመስሉት ማርቲ ታወራለች አቤል ይስቃል ከዛ በቃ ምንድነው ልጁን ልገይው ነው እንዴ አልኳት ከዛ ጓደኛሽ ደስ ይላል ወድጄዋለው አለችኝ ማርቲ ሲበዛ ፈጣጣ ናት እርስዋ ለምታወራው እኔን ሼም ይይዘኛል እሺ አሁን ይብላ እና እረፍት ያርግ አልኳት እና እኔ መች እጁን ያስኩት አለችኝ ከዛ በአይኔ ተይ የሚል ምልክት ሰጠዋት ማርቲ ቀልቃላና ቀበጥ ብቻ አይደለችም ምትፈልገውን ነገር በእጇ ካላስገባች በጣም ድርቅ ያለች ልጅ ናት በጣም ምትገርም ልጅ ናት እና መጣው ብላ ወጣች ከዛ ሳሎን እኔና አቤል ቀራን አንቺ ካልበላሽ ብቻዬን አልበላም አለኝ ከዛ እሺ ብዬ አብሬው ቁጭ አልኩ የቀረበውን እየበላን ልክ የሆነ ሰአት ላይ ሊያጎርስኝ ሲል...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 9 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@geyone
👉👉👉👉@geyone
👉👉👉👉@geyone
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
🌹🍃🕊...ላያስችል አይሠጥም

ያየሺ ሠዉ በመላ ጨርቁን የጣለ
ተከትሎሺ መጣ ጓዙን ጠቀለለ
አንቺ የተወደድሺ ልብሺ የሚያበራ
ምነዉ ለመናገር ልቤ አንቺን ፈራ
ጠዋትና ማታ ከደጂሺ ለይ ብገኚ
ለመናር ብየ አፌ የሚከዳኚ
አጠገብሽ ስደርስ ቃሉ የሚጠፍኚ
ሌላ ምንም አይደል ወድጄሺ ነዉ እንጂ
ባይኔ የምሼኝሺ ስትመጪ ስትሔጂ
እንዲሁ የማይሺ ስትመጪ ስትሔጂ
እናም ይሔን ሁሉ የነገርኩሽ ለታ
ያንቺ ልብ ባሰቺ ከኔ ልብ ደስታ
ላያስቺል አይሰጥም ለካ የኔ ጌታ።

💖⚘➣ Join ♥️💍
@geyone
@geyone
••●🍃🌹🍃●••
‍ ​​⊶⊷⊶⊷❍ የእብደት ሚስጥሬ ❍⊶⊷⊶⊷


ፍቅሬን በቃላቶች ~ ደርድሬ ባልገልፀው
የኔ ነሽ የምልሽ ~ ያንቺ ነኝ የምለው
ድምፅሽ መዳኒቴ ~ የህይወት እጣዬ
አካልሽ ጉልበቴ ~ የስኬት ማማዬ
ሌላ ማንም የለም ~ ባንቺ ነው ማማሬ
እውነት እልሻለሁ ~ የእብደት ሚስጥሬ

❤️ ❤️
@geyone
━━━━✦🌹
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_9

...🖊ልክ የሆነ ሰአት ላይ ሊያጓርሰኝ ሲል ማርቲ ገብታ ኧረ ጨረሽበት አለችኝ ከዛ እንደማፈር ብዬ አንገቴን አቀረቀርኩ አቤል ለኔ ያነሳውን ጉርሻ እራሱ ጎረሰው የሆነ ሼም ሳይዘው አይቀርም በልተን እንደጨረስን ማም ቡና አፍልታ እስከማታ እየተጫወትን አመሸን ከዛም የት ይደር የሚለው አከራካሪ ሆነ ማርታ እኔ ክፍል ስትል ማም ቃል ክፍል አቤል ሶፋ ላይ በማለት ብዙ ተከራከርን በመጨረሻ ደረቋ ማርታ እርሷ ክፍል እንዲተኛ አሳመነች እኔ የትም ቢተኛ ችግር የለብኝም ዋናው እርሱን ይመቸው እንጂ ከዛ ማርቲ ከማም ጋር አንድ ላይ ማም ክፍል ተኙ እኔ ክፍሌ ተኛው እና ዝም ብዬ facebook ላይ ገባው አማን online ላይ ነበር hi እለኝ እኔም ሰላም ካልኩት በኃላ ወሬ ጀመርን እና ድሬ ለስራ እንደሚመጣ እና በዛው እንደምንገናኝ ነግሮኝ ተሰነባብተን ስልኬን ዘግቼ በጀርባዬ ጋደም አልኩ እና የአማን መምጣት ብዙም ደስ ባይለኝም ትንሽ ቀን ስላልተገናኘን ናፍቆኝም ነበር እና እንዲህ እንዲህ እያልኩ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ከዛ ጠዋት ማም መጥታ ቃል ኧረ ተነሽ አመሸሽው እኮ አለችኝ እየሳቀች እማ ትንሽ ብቻ 5 ደቂቃ አልኳት ደግሞ እህትሽ ጓደኛሽን ይዛ ኮብልላለች ስትለኝ ተስፈጥሬ ተነስቼ የት አልኳት እኔንጃ መጣን ብላ ነው ይዛው የወጣችው አለችኝ የት ይሄዳሉ እዚው ቅርብ ነው ሚሆኑት አለችኝ እሺ ብዬ አልጋዬን አንጥፌ ማም ቁርስ እስክትሰራ እኔ ቤቱን ፏ አርጌ ጠበኳቸው እነ ማርቲ ግን አልመጡም መጠበቁ ሲሰለቸን እኛ በቃ እንብላ አልኳት እሷም ትንሽ እጠብቃቸው ስትለኝ ቆይ እሺ በቃ ልደውውልላቸው ብዬ ለአቤል ስደውል ስልኩን እቤት ትቶት ነው የሄደው ከማርቲ ክፍል ሲጠራ ይሰማል ማርቲ ጋር ስደውል ደግሞ አታነሳም በጣም ተናድጄ እማ አሁን ካልበላሽ ከዚህ በኃላ አልበላም ስላት እያቅማማች እሺ አለች ከዛ ወደ 6:15 አካባቢ አቤል እና ማርቲ መጡ ስልኳን ስላላነሳችልኝ ተናድጄ ለምንድነው ስልክሽን ማታነሽው አልኳት እንደመቆጣት ብዬ እሷ ግን ቀለል አርጋው ደውለሽ ነበር እንዴ አላየውትም አለችኝ ይበልጥ ማላገጥዋ እያናደደኝ እንግዳውን ይዘሽው ሄደሽ ነው አልኳት ማ አቤሌን ነው እንግዳ በቃ እሱ እኮ ቤተኛ ሆኖዋል አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው እንዲህ ምታናግሪኝ አለችኝ እኔም ለራሴ ግራ ገብቶኛል ከዛ ለማስቀየስ ያክል ትላንት ደክሞት መጥቶ በስርሀቱ እንኳን ሳይተኛ የትበለሊት ይዘሽው ትዞሪያለሽ አልኳት እሷም ኧረ ተረጋጊ ሲነሳ ነው የወጣነው ደግሞ ቦታ ላሳየው ነበር አለችኝ ይሄ ሁሉ ሲፈጠር ግን አቤል ዝም ብሎ ነበር የሚያየን በመጨረሻም በቃ አትጨቃጨቁ ይሄ ሁሉ በእኔ ምክንያት ነው አለ እኔም በራሴ አፈርኩ በእርሱ ፊት እንዲህ መሆን አልነበረብኝም ከዛ ማም መጥታ መጣችው ልጆቼ ግቡ ወደቤት ብላ አስገባችን ከዛም ማም እና ማርቲ ምሳ ለማዘጋጀት ክችን ገቡ ትንሽ ቆይቶ ስልኬ ንዝር አረገኝ እየተደወለ ነበር አማን ነበር የደወለው አንሳውት ሄሎ አማን አልኩት አማን ስል አቤል የደነገጠ ይመስል ነበር ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ አቤል እኔ የለውም የሚል ምልክት በእጁ አሳየኝ ለምን እንዲህ እንዳለ ባይገባኝም እሺ አልኩት ትንሽ ካወራን በኃላ ከአቤል ጋር አውርታችው ታቃላቹ አግንቼው አላውቅም አለኝ ከዛ አቤል ያለኝን እረስቼ እቤልማ እኮ....

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 10 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_10
...🖊አቤል ያለኝን እረስቼ አቤልምማ እኮ ብዬ ገና ሳልጨርሰው አቤል ከመቀስፈት መጥቶ አፌን ያዘኝ አፌን የያዘኝ በጣም ተጠግቶኝ ነበር አይኖቼ ከአይኖቹ ጋር አረፉ አቤል በጣም እየተመለከተኝ ነበር የሆነ የሚስለኝ ነበር ሚመስለው ላየው ሰው ግን አሁን ይበልጥ እየተጠጋኝ እንደሆነ ይታወቀኛል ሰውነቴ እየነዛዘረኝ ነው ከዛ አፍንጫዬን በስሱ ሲስመኝ አይኖቼ ሲከደኑ ይታወቀኛል የምሆነውን በሙሉ ከእኔ ቁጥጥር ውጭ ነው ከዛም ቀስ ብሎ ከአጠገቤ ተነስቶ ቦታው ተቀመጠ እና አይኖቼን ቀስ አርጌ ገለጥኳቸው እና ከኔ ፊት ለፊት ተቀምጦ ፈገግ ይላል ከዛ ስልኩን ዘጋውት አማን በድጋሚ ደወለ እና ትንሽ እንደማመንታት ብዬ አነሳውት እና አንቺ ምን ዋጠሽ ገሮሮዬን እኮ እፈልገዋለው አለኝ ከዛ በጣም ይቅርታ አማንዬ ኔቶርክ ትንሽ እያስችገረ ስለሆነ ነው ስለው አቤል ከት ብሎ ሳቀ ድምፁ እንዳይሰማ ብዬ ወደ ውጭ ወጣው ቢሆንም አማን በትንሽውም ቢሆን ድምፁን ሰምቶ ነበር ከዛ ማነው እንዲ ድዱ እስኪታይ የሚስቀው ብሎ ሲጠይቀኝ አይ የጎረቤት ልጅ ነው አልኩት ብዙም ግድ አልሰጠውም ነበር እና ፈልገኸኝ ነበር ስለው ምን ባክሽ ስራዬ ሊያቆየኝ ስለሚችል እቤት እንድፈልጊልኝ ነበር አለኝ እሺ ከተገኘ ችግር የለውም ብዬ ተሰነባብተን ዘጋውት እቤት ስገባ ምሳ ቀርቦ ነበር እጄን ለቅለቅ ብዬ ተቀላቅያቸው በልተን ከጨረስን በኃላ ማም ቡና አፍልታ እየተጫወትን ሳለ ትዙ ደወለች ወዬ ትዙዬ አልኳት የት ነሽ አለችኝ እቤት ስላት ባክሽ ውጪ ከመቅዲ ጋር እየጠበቅንሽ ነው በርጋ አልችኝ መጣው ብያት ስልኩን ዘጋውት ትዙና መቅዲ የሰፈር ጎደኞቼ ናቸው ማም ደግሞ የት ልትሄጂ ነው አለችኝ አይ እነ ትዙ በር ላይ ናቸው አይቻቸው መጣው አለኳት እሺ ቶሎ ተመለሽ እንግዳ አለ አለችኝ እሺ ብዬ ወጣው ትዙ አንቺ ግን አለሽ አልኳት ተጠፍፍተን ስለነበር መች ፈለግሽኝ እና አለችኝ አልሰማሽም እንዴ ስላት የሆነ ትልቅ ነገር ምነግራት መስልዋት ሰፍ ብላ ምን ስትለኝ በየቦታው አፍልጉኝ ፎቶሽን መለጠፌ ስላት ሂ ወረኛ ብላ በስሱ መታችኝ እና መቅዲ ስላት ምን አለችኝ ትንሽ የደበራት ትመስል ነበር ምነው አልኳት ምንም ምነው አለችኝ የውሸት ፈገግታ እያሳየችኝ ከዛ ትዙ እቤት ተፈለጋ መጣው ብላን ባለንበት ጥላን ሄደች ከዛ መቅዲ የሆነ ነገር አለ ንገሪኝ ብዬ ጎተጎትኳት ከዛ ታሪኩ እረጅም ነው ግን እያሳጠርኩ ልነግርሽ እሞክራለው አለችኝ
ችግር የለም ንገሪኝ አልኳት ወክ እያረግን እንድትነግረኝ ነግሬያት በዝግታ እየተራመድን ወሬዋን ጀመረች ከዛ በፊት ግን መቅዲ የ 4ተኛ አመት የዶክትሬት ተማሪ ነች እና ታሪኩን እንዲህ ብላ ጀመረች...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 11 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡vote ስታደርጉ ለኛም ብርታት ነው🙏

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
እንኳን ለናታቸን ለእመቤታችን ማርያም አመታዊ ብዓል አደረሳችሁ



እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕተ ንጹሃን ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ታላቅ አመታዊ በዓል ( ለአስተርእዮ ማርያም) በሰላም በጤና አደረሳችሁ:: አደረሰን!


🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_11
...🖊ታሪኩን እንዲህ ብላ ጀመረች እንድ የክፍሌ ጎበዝ ተማሪ ነበር እና ብታይ ሲበዛ ጢባራም ነው እና መጀመሪያ አካባቢ በጣም ያስጠላኝ ነበር እና አንድ የክፍሌ ጎደኛዬ ሰአዳ የምትባል ልጅ ነበረች እና ለምን ሙድ አንዚበትም ሄደሽ አውሪው አለችኝ ከዛ እኔም ለማፌዝ እሺ አልኳት እና እስክርቢቶም መፅሀፍም በማለት ተግባባውት ከዛ እንድ ቀን አጠገቤ መጥቶ እንዲቀመጥ በአይኔ ነገርኩት እሱ ግን ኮስተር ብሎ አቤት ፈለግሽኝ አልኝ ተቀመጥ አልኩት ከዛ ተቀመጠና አቤት አለኝ ከዛ ፈገግ እንዲል ብዙ ነገር አወራውት እርሱ ግን በስሱ ነበር ፈገግ የሚለው ይበልጥ ያበሽቀኝ ጀመር ከዛ telegram እንደሚጠቀም ጠየኩት አዎ አለኝ እና ለመጀመሪያ ጊዜ ከወንድ ስልክ ስቀበል እና ስልክህን ስጠኝ በዛ እናወራለን አልኩት ከዛ 09 ሲለኝ አላመንኩም ቶሎ ብዬ እስክርቢቶ አንስቼ በእጄ ለመፃፍ እሺ አልኩት 75 እ አልኩት 50 እ አሁንም ስልኩን ለመቀበል ጎጉቼ ስሙኒ አለኝ ከዛ ከት ብዬ ሳቅኩና አትቀልድ ስጠኝ አልኩት ምን ያረግልሻል አለኝ እናወራለና ስለው ትክክለኛ ስልኩን ሰጠኝ ከዛ ተቀበልኩት ከዛ ማታ ብፈልገው ላገኘው አልቻልኩም ለአንድ ሳምንት ያክል ላገኘው አልቻልኩም አንድ ቀን የሆነ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብዬ መጣና አብሮኝ ተቀመጠ እና ለምን online ላይ እንደማይገባ ጠየኩት ከዛ ከዚህ በኃላ ስትገቢ miscall አርጊልኝ ግን መልሼ miscall ካረግኩልሽ አልገባም ማለት ነው አለኝ እሺ ብዬ ማታ ማታ miscall ማድረጌን ቀጠልኩ እናም እኔ እረስቼው ከተውኩት ወይም ከደበረኝ እርሱ ሱስ የሆነበት ይመስል አንድም ቀን አያልፈውም ስትል ስልኬ ጠራ ወይ ማም አልኩ ማም ነበረች አንቺ እንግዳ እቤት አስቀምጠሽ የት ጠፍሽ አለችኝ ውይ እረሳውት እኮ በቃ መጣው ብያት መቅዲን ነገ እናወራለን ብያት ተሰናብቻት እቤት ገባው ስገባ ግን አቤል ሻንጣውን እያስተካከ ነበር እና ወዴት ለመሄድ ነው ስለው ነይ ማወራሽ ጉዳይ አለ አለኝ ብሎ ይዞኝ ወጣ እና እእእ ቃልዬ በመጀመሪያ ይቅርታ ልጠይቅሽ እፈልጋለው አለኝ ግራ በመጋባት ለምኑ አልኩት እእ ድሬ ማንንም አላቅም ስልሽ እና ገንዘቤ ተሰረቀ ያልኩሽ በሙሉ ው.. ሸ ..ቴ ..ን ነ..በ..ር አለኝ በተቆራረጠ ድምፅ ምን አልኩት ለምን ዋሸኸኝ አልገባኝም እየቀልድክ ነው ስለው...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 12 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
👇👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

"አቧራ የጠገበን ምንጣፍ በዱላ የምትመታው አቧራውን ለማራገፍ እንጂ ምንጣፉን ለመጉዳት አይደለም።

የሰውን ድክመት የምትነግረውም ስህተትን እንዲያርም እንጂ ሰውዬው በእራሱ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ አይደለም።"

🙌መልካም ምሽት ይሁንልን🙌
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_12
...🖊በጣም ይቅርታ አርግሊኝ ግን በእኔ እና ባንቺ መሀል ያለውን ችግር ለመቅረፍ በማሰብ ነው እና ደግሞ ትክክል ነው ያረኩት አለኝ ምን መዋሸትህ ትክክል ነው ምንድነው ምትለው ቃልዬ ሁሉንም ነገር እንድታስረጂኝ እኮ እያመቻቸው ነው እሺ አሁን እሱን ተወውና ወዴት ለመሄድ ነው ሻንጣህን የምትሰበስበው አልኩት እሱም እዚህ አክስቴ አለች እና ማም እዚህ መሆኔን ስትነግራት ካልመጣ ብላ ቀወጠችው እና ካልሄድኩ ችግር ትፈጥራለች እና ደግሞ ለአማን እዚህ ነው እንዳትይው አለኝ እና ለምን እንደዛ እንዳለ መጠየቅ ፈልጌ እረስቼው ነበር በዚህ እጋጣሚ ለምን እንዳልነግረው እንደፈለገ ጠየኩት እሱም ሳልነግረው ስለመጣው ይደብረዋል ለዛ ነው አልኝ ወሬ ማብዛት ስላልፈልኩ ነገ ስንት ሰአት ነው የምትሄደዉ አልኩት ወደ 5 ሰአት አልኝ እና ጥሩ በቃ እሸኝሀለው በል እንግባ ብርዱ ከባድ ነው አልኩት እየገባን እያለ አቤል ስልኩ ጮኸ አባቢ አለ ምን ፈልጎ ደወለ አለኝ አንሳና ሚሉህን ስማ አልኩት አቤት አባቴ ከዛም ትንሽ ካወሩ በኃላ ፊቱ እንደመለዋወጥ አለ እና እሺ ብሎ ስልኩን ዘጋው ምንድነው ምን ተፈጠረ ስለው ከ 1 ወር በኃላ ለስራ ድርጅታችን ወደ አሜሪካ እንደምላክ ነው የነገረኝ አለኝ አልገባኝም አልኩት ልክ ገና እንደተመረቅን አባዬ ድርጅቱን እንዳስተዳድር ሀላፊነት ሰጥቶኝ ነበር እና አሁን ወደ ውጭ እንደሚሄድ ነው የነገረኝ አልኝ እስከ መች ትቆያለህ ስለው አላውቅም ግን ብዙ ጊዜ እንደማልቆይ ነው የነገረኝ አልኝ ዱካክ ለቀቀብኝ እና በቃ እሺ እንግባ ተባብለን ውስጥ ገባ እንቅልፍ ምንም አልመጣልሽ አለኝ እንዲሁ መገላበጥ ሆነ ስራዬ በመጨረሻም Facebook ስገባ ሜሪ ኦንላይን ላይ ነበረች ወድያው ነበር ሀይ ያለችኝ ትንሽ ሰላምታ ከተለዋወጥን በሀላ ከአቤል ጋር እንዴት ናችሁ አልችኝ ከሷ ምንም መደበቅ ስላቃተኝ ሁሉንም ነገርኳት ምንም ልታምነኝ አልቻለችም አብሶ እኛ እቤት ነው ስላት ግን ላሳምናት ቻልኩ እና ነገርሽው እንዴ አለችኝ ምኑን ስላት እንደምትወጅው ነዋ ባለፈው ከነገርኩት በኃላ አላወራንም በዚህ እርስ አልኳት እንዴ ለምን ብላ ብዙ የጥያቄ ምልክት ላከችልኝ እኔም እኔንጃ ጊዜ ምንም አልተመቻቸልንም እንደሚሄድም ነገርኳት እሷም እንደምወደው ይሄን አጋጣሚ ተጠቅሜ እንድነግረው ነገረችኝ እሺ ብዬ አምስግኛት ተሰነባብት ከ ኦንላይን ላይ ወጣች የተላኩ ሚሴጆች ወደ 150 ገብተዋል ግን አንዱንም ከፍቼ አይቼ አላውቅም በቃ ማቀው ሰው ኦንላይን ላይ ስለሌላ ሁሉም ስለማላቃቸው ደብሮኝ አጥፍቼ ጋደም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ ነገ ምን ልበለው እያልኩኝ በቃ እንደማወራው ብቻ እርግጠኛ ነበርኩ እንዲህ እንዲህ እያልክ እንቅልፍ አሸልቦኝ ሄደ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 13 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,

@geyone
@geyone
,,📩
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_13
...🖊በጠዋት ተነስቼ ቤታችንን ካስተካከልኩ በኃላ ቁርስ ለመስራት ወደ ክችን ስገባ ማም ጉድ ጉድ እያለች ነበር ልክ ስታየኝ ዛሬ እንዴት በጠዋት ተነሳሽ አለችኝ አይ አቤል ዛሬ የሚሄደው አልኳት እንዴ ወዴት አለችኝ አክ...አልኩ እና አፌን ያዝ አረግኩት ወደ ሀገሩ መሰለኝ አይ አንቺ ትላንት አነግሪኝም ነበር አለችኝ እኔም ማታ ነው የነገረኝ ደሞ ወደ ውጭ ሊሄድ ነው በቅርቡ አልኳት እሷም በድንጋጤ ለመኖር አለችኝ አይ ለስራ አባቱ ልከውት ነው አልኳት አይ ልጁ እኮ በጣም ጥሩ ልጅ ይመስላል በዛ ላይ እረጋ ያለ ነው ግን ልጄ ምንም ነገር ሳትዋሺ ንገሪኝ ምንም ነገር የለም ከእርሱ ጋር ስትለኝ የሌለ ሼም አስያዘችኝ ኧረ ማም ተይ እያሳፈርሽኝ ነው አልኳት ማም ገና ከመጀመሪያው ቀን አንስታ ነበር አይንዋ አቤል ላይ ያረፈው ከዛ ምን ከእኔ ከእናትሽ ምደብቂው ነገር አለ አለችኝ ኧረ ካንቺ ሌላ ምን ህይወት አለኝና ካንቺ እደብቃለው አልኳት እኮ ንገሪኛ አለችኝ ምን ልንገርሽ አልኳት ሁሉንም ነገር አለችኝ ከዛ ግን እኮ እማ ስላት ሳታስጨርሰኝ እንዳትዋሺኝ ልጄ ስትዋሺኝ አቅብሻለው አለችኝ ከዛም ምንም ልደብቃት ስላልፈለኩ ሁሉንም ነገርኳት እንዴት እንደተዋወቅን እንዴት እንደተጣላንና ለምን እንደመጣ ጭምር ሳልደብቅ ነገርኳት እና አሁንም እዚህ አክስት እንዳለው እና እዛ እንደሚሄድ ነገርኳት እርስዋ ግን አንድ ጥያቄ ብቻ ነበር የጠየቀችኝ ደስተኛ ነሽ የሚል አላውቅም አልኳት ከእርሱ ጋር ስትሆኚ ሰላም ይሰማሻል አለችኝ በጣም እንጂ ድምፁን መስማት በራሱ ደስታ ይሰጣል አልኳት እርሷም አይ የሚያስደስትሽ እና የምታምኝበት ከሆነ እኔም ወጌን ልይ አልችኝ ከዛ ሁለታችንም ስንስቅ አቤል ሰምቶ መጣ ከዛ ደና አደራቹ አለ እንደም አደርክ ልጄ ሂድ ፊትህን ታጠብ ቁርስ ደርስዋል አለችው እና ሄዶ ታጥቦ መጣ ቁርስ ለመብላት ተሰብስበን ቁጭ አልን እና እማዬ ወሬ ለማስጀመር ያክል እና ልጄ ስራ እንዴት ነው አለችው ስራ ጥሩ ነው እና ዛሬ ነው ምትሄደው አሉ ስትለው አንገቱን አቀርቅሮ እእእእእ አለ መልስ ምት የሚመስል ነገር እና ለምን በጊዜ አትነግረንም የሆነ ነገር እናዘጋጅ ነበር አለችው ኧረ ችግር የለውም ማዘር አትጨነቂ አላትና በላልተን እንደጨረስን ወደ ውጭ ወጥቶ ለእክስቱ መኪና እንድትልክለት ነገራት ከዛም ሻንጣውን ለማምጣት ማርቲ ክፍል ሲገባ ተከትዬው ገባውና በሩን ዘጋውት አቤል አልኩት አቤት አለኝ ፊቱን ወደ እኔ እያዞረ ባለፈው አንድ ነገር ነግሬህ ነበር አልኩት ምን አለኝ ምንም እንደማያቅ ሰው እንደው ባለፈው የተጣላን ሰሞን አልኩት ይቅርታ ግን አላስታወስኩም ሲለኝ የሌለ አበሳጨኝ ተወው በቃ አልኩትና ልወጣ ስል እጄን ቀበል አደረገና ወደ እኔ እየተጠጋ ለምንድነው ወድያው ምትናደጅው አለኝ አይን አይኖቼን እያየ መናገር አቃተኝ እእእ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 14 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••


━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_14

...🖊እእ እና ታድያ ገብቶህ እንዳልገባህ ስትሆን ነዋ አልኩት እና ከአንደበትሽ መስማት ስለምፈልግ ነዋ አለኝ እንደውም አልነግርህም ስለው ኧረ ወደሽ ነው በግድሽ አልኝ ባልነግርህ ምን ታመጣለህ አልኩት እጮኻለው አልኝ ወንድ ስለው ሊጮህ ሲል እፉን ያዝኩት አበድክ ስለው አዎ አሁን ሳይሆን ገና አንቺን ያየው ቀን አለኝ ወረኛ አሁን አትፈላሰፉ አልኩት እየተፈላሰፍኩ አይደለም እውነት ነው አንቺስ አለኝ አይኖቹን አይኖቼ ላይ ተክሎ ምን ይመስልኸል አልኩት እኔ እራሴን ከምወደው በላይ አብልጠሽ እንደምትወጅኝ እእ ትክክል ነኝ ሲለኝ አዎ ብዬ ገፍትሬው እየሮጥኩ ልወጣ ስል እጄን ይዞ ወደ ደረቱ ልጥፍ አረገኝ እኔም እቅፉ ውስጥ ስገባ ሌላ አለም ውስጥ የገባው መሰለኝ የሆነ የስልክ ጥሪ እኔንም እርሱንም ካለንበት መአበል ፈልቅቆ አወጣን አክስቱ ነበረች መኪናው እንደደረሰና እንዲወጣ ነገረችው እሺ አለና ሻንጣውን ይዞ እንደመውጣት አለና ተመልሶ መጥቶ ግንባሬን ስሞኝ ወጣ ከዛም ተከትዬው ወጣው ማም ልትሄድ ነው ስትለው አዎ ማም በቃ ቻው እየመጣው እጠይቃችኃለው አልና ተሰናብቶን ወጣ በአይኔ መኪና ውስጥ ገብቶ እስኪሄድ ከሸኘውት በኃላ እቤት ገባው እና ቁጭ እንዳልኩ ለካ ትላንት መቅዲ ያስከፉትን ነገር ሳትጨርስልኝ ነበር ስደውል ስልክ አታነሳም ድግሜ ስደውል ተይዝዋል ይለኛል በቃ ሚስኮል አይታ ትደውላለች አልኩና ስልኬን ቁጭ አረኩት ብዙም ሳትቆይ ደወለች ምንድነው ስልክ ማታነሽው አልኳት ኧረ ስደውል ተይዝዋል ብሎኝ እኮ ነው አለችኝ የት ነሽ ስላት እቤት ነኝ ፈለግሽኝ ስትለኝ አዎ መምጣት ትችያለሽ አልኳት የት እቤት አለችኝ አይ ሰፈር ወጣ በይ እኔም ንፍስ መቀበል አምሮኛል አልኳት እሺ በቃ ውጭ መጣው አልችኝ እና ተሰነባብተን ስልኩን ዘጋነው ከዛ ከ 15 ደቂቃ በኃላ ውጭ አለችኝ ደውላ እሺ ብያት ወጣን ከዛም በማርያም ቤተክርስቲያን በኩል ወክ እያረግን ማውራት ጀመርን ከዛም ከአንዱ መቀመጫ ድንጋይ ላይ ሄደን ቁጭ አለን እና መቅዲዬ የባለፈውን ቀጥይልኝ እንጂ አልኳት እሷም ለማውራት ትንሽ ካንገራገረች በኃላ ለመናገር ጉሮረዋን ጠረግ ጠረግ አርጋ በቃ ከናቲ ጋር በቴሌግራም ማውራታችን ቀጠልን ግን እኔ ምንም አይነት ነገር ለእርሱ አልነበረኝም ያው ጉረኛ ስለሆነ ትንሽ ላስተንፍሰው ብዬ እንጂ አንድ ቀን ግን ምሳ ሰአት ላይ ኪሩቤል የሚባል ልጅ ሊያወራኝ እንደሚፈልገኝ ነገረኝ እኔም እሺ ብዬው የምንገናኝበትን ቦታ ነግሮኝ እርሱን ለማግኘት ሄድኩ ኪሩቤል በጣም ደስ የሚል ተጫዋች የደስ ደስ ያለው ልጅ ነው ደግሞ ሲስቅ ድምፒሉ እንዴት እንደሚያምር እና እርሱ ጋርም እንደደረስኩ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ በጣም ትልቅ ነገር እንደሚነግረኝ ነገረኝ ምን እንደሚነግረኝ ብዙ ነገር እያወጣው እያወረድኩ ምን ሊነግረኝ እንደፈለገ ጠየኩት እርሱም እንዲህ በማለት ጀመረ ብዙ የፍቅር ጥያቄዎች ደርሰውሽ ይሆናል ብዙ ሰዎችንም ተተዋውቀሽ ይሆናል ግን አሁን የምነግርሽ ሰው በጣም ከልቡ የሚወድሽ እራሱን እስከመጣል የደረሰልሽ ሰው ነው ከአንቺ በፊት ብዙ ሴት ቢያቅም ነገር ግን የትኛዋንም ልክ እንዳንቺ ወድዶ አያውቅም አለኝ ምንም ማለት አቅቶኝ ዝም ብዬ እሰማው ነበር አሁን ላይይ አንቺ ለእርሱ ምንም ስሜት ባይኖርሽም እስከ መጨረሻው እንደሚጠብቅሽ እርግጥኛ ነኝ አለኝ እኔም በመደንቅ ይሄን ያክል ልጁ ማን ቢሆን ነው እንዲህ ስለሱ እርግጥኛ ሆኖ የሚያወራው አልኩና ማነው እርሱ አልኩት ከዛም መናገር ያቃተው ይመስል ዝም አለ እኔም አላስችል ብሎኝ ንገረኛ ማነው አልኩት አሁንም ምላሹን እየጠበኩ እእእ እባክሽ ስሙን ስነግግሽ እንዳደነግጭ ግን አንድ ነገር እወቂ መልስሽ ምንም ቢሆን እርሱ ከምታስቢው በላይ እንደሚወድሽ እሺ አለኝ እኔ ትዕግስቴ እያለቀ ማነው እርሱ አልኩት እእእ እሺ እነግርሻለው ግን ባትወጂው እንኳን አትጥይው አለኝ ሳላውቀው በመጀመሪያ ልጁ ማነው አልኩት እርሱም በጣም በመጨነቅ ስሜት ሆኖ እእእ እኔ እራሴ ነኝ አልኝ ድርቅ ብዬ ቀረው ምን አልኩት አዎ እኔ ነኝ መቅዲ አንቺ ሳታቂ ለብዙ ጊዜ ወድጄሻለው አንቺን ለመርሳት ከብዙ ሴት ጋር ሆኛለው ግን አልቻልኩም አንዴ ልቤ ላይ ተፅፈሽ የማይጠፍ እስክርፒቶ ሆነሽብኛል መቅዲ መልስሽ ምንም ቢሆን አንቺን መውደዴን አላቆምም አለኝ እልሻለው ስትለኝ የሆነ ፊልም የምትነግረኝ ነበር የመሰልኝ ቀጥይ በሚል አስተያየት እያየዋት ቅንድቤን ከታች ወደላይ ከፍ በማድረግ ቀጥይ አልኳት እርሷም ይሄን ነገር ኪሩቤል ከነገረኝ ቀን ጀምሮ ስለሱ ማሰብ ጀመርኩ ከዛ ግን ስልኬን ማን እንደሰጠው ባላውቅም ቴሌግራም ላይ ሀይ ብሎ ላከ እኔ መልስ ከመመለሴ በፊት ፕሮፍይል አይ ስለነበር የእርሱ መሆኑን አውቅኩ እና ከትንሽ ቀን በኃላ እኔም ሀይ ብዬ መለስኩለት ከዛ ለረጅም ጊዜ ማውራት ጀመርን ቀስ በቀስ በጣም እወደው ጀመር እና በመሀል ስለ እኔ እና ናቲ መወራት ጀመረ እኔ እና ናቲ አንድ ላይ እንደሆንን ማውራት ጀመሩ አንድ ቀን ግን ክፍል ውስጥ ያለመደባቸውን ትዕዛዝ እንጫወት ብለው ናቲ እኔን እንዲስመኝ ታዘዘ ከዛ ልሳምሽ አለኝ ላሳፍረው ስላልፈለኩ እሺታዬን አንገቴን በመነቅነቅ ገለፅኩለት ከዛ ልክ ገና ሲስመኝ የክላስ ተማሪዎች በጩኸት ክፍሉን ቅውጥ ግማሾቹ ፎቶ አነሱንና ቴሌግራም ላይ የአመቱ ምርጥ ፍቅረኛማቾች ብለው ግሩብ ላይ በተኑት ይመስለኛል ናቲ ጎበዝ እና ቆንጆ ጉረኛ ስለሆነ ይመስለኛል እንዲህ ያካበዱት ከዛ ግን...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 15 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_15
...🖊ከዛ ግን ወሬው ስለኛ ሆነ ኪሩቤል ይሄን ሲሰማ እንደ እብድ ነው ያረገው እና በስልክ መገናኘት አልብን አልኝ እና የምንገናኝበትን ቦታ ነግሮኝ መልሴን ሳይጠብቅ ዘጋው አሁን በእኔ እና በእርሱ መሀል አንዳች ነገር እንደሚፈጠር እያሰብኩ እንገናኝ ካለኝ ቦታ ሄድኩ ስሄድ ግን ከቦታው ላይ ደርሶ ጀርባውን ሰጥቶ ቆምዋል እና ትንሽ ከእርሱ ሁለት እርምጃ ቆሜ ኪሩቤል አልኩት ከዛ ዞር አለና እኔ መሆኔን ሲያቅ ዘሎ አቀፈኝ ያለቀሰ ይመስል ነበር ከዛ ምነው ምን ሆነህ ነው አልኩት እባክሽ መቅዲዬ ለትንሽ ደቂቃ ዝም ብለሽ እቀፊኝ አለኝ እኔም አግንቼ ነው በሚል አስተቃቀፍ አቅፍኩት ከዛ ከትንሽ ደቂቃ በኃላ ግን ትወጂኛለሽ አልኝ በመደንገጥ ስሜት እጄን ከትከሻው ላይ ቀስ ብዬ ማንሳት ጀመርኩ ከዛ እንደለቀቅኩት ሲገባው ቀና አለ እና ይመለከተኝ ጀመር እኔም ለምን ጠየከኝ አልኩት መቅዲ እኔ እንደምወድሽ ከነገርኩሽ ቀን እራሱ ስንት ጊዜ ሆነኝ እባክሽ የማትወጅኝ ከሆነም ንገሪኝ ቁርጤን አውቄ ልቀመጥ አልኝ ከዛ ምንም መናገር አቃተን ላወራ ፈልጌ አፌን የሆነ ነገር ያዘኝ ከዛ በቃ ተይው ዝምታሽ ነግሮኛል ከአሁን በኃላ አላስቸግርሽም አጠገብሽም አታይኝም ብሎ ጥሎኝ እስኪሄድ ድረስ አንደበቴ አልከፈት አለኝ እና ባለውበት ጥሎኝ ሄደ ስትለኝ አቤል ደወለ ከዛ ደርሻለው ሊለኝ ነበር የደወለው ከመቅዲ ጋር ሳወራ አቤልን እርስት አድርጌዋለው ውይ እቤሌ ይቅርታ ከጓደኛዬ ጋር ሆኜ እረሳውህ ይቅርታ አልኩት ከዛ ኧረ ችግር የለም አትጨነቂ አለኝ እና ትንሽ ካወራን በኃላ በቃ ቻው እወድሻለው ብሎ ሲለኝ እኔ በጣም ስለው መቅዲ ቁንጥጥ አርጋኝ በአንገቷ ማነው የሚል ምልክት አሳየችችኝ እኔ እሺ በቃ ቻው ብዬ ስልኩን ዘጋውት ከዛ መቅዲ ማንው ስትለኝ ታሪኩን እየሄድን ልንገርሽ ሰአቱ እየሄደነው አልኳት እና ሁሉንም ነገር ነገርኳት ልክ ሰፈር ስንደርስ ታሪኬን ባጭሩ ስነግራት ዋው ደስ ይላል እና በቃ እናወራለን አልችኝ እና ተሰነባብተን ተለያየን ከዛ እቤት ልክ ስግባ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 16 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
👎👎👎👎👎👎🤞🤞🤞🤞🤞
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone

━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_16
...🖊ልክ እቤት ስገባ ማንም እቤት ውስጥ አልነበረም ከዛ ሰአት ስመለከት 9:30 ይላል ምሳ እስካሁን አልበላውም ብዬ ምሳ ላቀርብ ወደ ክችን ስገባ ምንም ሚላስ ሚቀመስ የለም ከዛ በቃ እስከ እራት ልስራ እና ልብላ ብዬ ምስር መልቀም ጀመርኩ ከዛም አጥቤው ሽንኩርቴን ከትፌ አቁላልቼ ምናምን ሰራው ልክ 10:30 አካባቢ ምሳዬን አቅረብኩ ለነገሩ መክሰስ ልበለው እንጂ ሰአቱ ሄድዋል ከዛ በልቼ እንድጨረስኩ ክፍሌ ገብቼ ግጥም ለመሞነጫጨር ሞከርኩ ግን ትንሽ እንደመፃፍ ስል ስልኬ ጠራ አማን ነበር እ ሴትዬዋ እንዴት ነሽ አለኝ አለውልህ አማንዬ ሰላም ነው አልኩት አለውልሽ ጠፍሽ አለኝ ኧረ አለው አልኩት ገምቺ የት እንዳለው አለኝ የት ነህ አልኩት ገምቺ ሲለኝ እመጣለው ያልኝ ትዝ አለኝ እና አላምንም ድሬ ነኝ እንዳትል ስለው እልሻለሁ አልኝ ከዛ ደስ ይላል እና አሁን የት ነህ ሆቴል ነኝ ነገ አገኝሻለው አለኝ እስቲ እሺ አልኩት ምነው የያዝሽው ቀጠሮ አለ እንዴ ሲለኝ አይ በቃ እንገናኛለን ብዬው ስልኩን ዘጋውት አማን ሲደውል ሜሪ ትዝ አልችኝ እና ደወልኩላት እና ሞቅ ያለ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ ብዙ ነገር አወራን እንደናፈቅኳት እያነገረችኝ እየተሳሳቅን የሆነ ሰአህ ላይ ከአማን ጋር እንዴት ናችሁ አሁን ላይ አልኳት ያው ከአማን ፍቅር ከያዛት በኃላ ሜሪ እንደ ድሮ አትቅለበለብም ደስ የሚል ፀባይ አምጥታለች ቢሆንም እንደ ድሮ እንዳልሆኑ በደፈናው ነገረሽኝ እና እኔም ብዙ ካወራው ማስከፍት ስለመሰለኝ እሺ ብዬ ተሰነባብተን ዘጋውት ከዛ ጥቅልል ብዬ ተኛው ማታ ቃል ተነሽ እራት ቀርቧል የሚል ድምፅ ይሰማኛል በህልሜ ይሁን በእውኔ መለየት ተስኖኛል በህልም ስለመሰለኝ ግድ አልሰጠውት ከዛ ድምፁ ወደ እኔ በይበልጥ ይጠጋ ጀመር ማም ናት ቃል ተነሽ እራት በልተሽ ትተኛለሽ አልችኝ ም ን ን አልኳት በተቆራረጠ ድምፅ ተነሽ በልተሽ ትተኛለሽ አለችኝ በልቻለው ማም ልተኛ አልኳት መቼ ነው የበላሽው ተነሽ አለችኝ ከዛ ኧረ እማ በጌታ ልተኛ በልቻለው ስላት እሺ ካልሽ ምን ይደረጋል ጎትቼ አላነሳሽ ነገር ልጅ አይደለሽ በይ ተኚ አለችኝ ከዛም ብዙ ሳይቆይ እንቅልፍ ወሰደኝ ጠዋት ስነሳ ማንም እቤት የለም ከዛም የውጭ በር ይንኳኳ እና እርሱን ለመክፈት ልክ ከሶፍ ተነሳው እና በሩን ስከፍተው አቤል ቀይ አበባ ታቅፎ ከኃላው አንድ ሴት እና ወንድ በእድሜ ገፋ ያሉ እንደሆኑ ያስታውቃል ግርማ ሞገስ ያላቸው ሰዎች ቆመዋል በጣም ተደናገጥኩ አቤል አልኩ በግርምት አስተያየት እያየውት ግቡ እንኳን አላልኳቸውም ለምን እንዳላልኳቸው እኔም አላውቅም ወዬ ፍቅሬ አለኝ ይባስ ፍቅሬ ሲለኝ ድንጋጤ ሰውነቴን ሲወር ይሰማኛል ከዛም ማናቸው በዚህ ጠዋት ምን ትሰራለህ አልኩት በድንጋጤ እናት እና አባቴ ናቸው አለኝ አሁን በቃ ላቤ እንደውሃ ይወርድ ጀመረ አልገባኛም ምንድነው እርሱ ስለው ቆይ አለና
ከሱሪው ኪስ ውስጥ አንድ ብልቃጥ ምትመስል ምታምር ነገር አወጣ እና ሲከፍታት...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 17 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​❥❥❥❥



​ ፍቅር ጠላቴ ነው
.

በእርግጥ ለታደለው
አፍቅሮ ላገኘው
ፍቅር ጠላት አይደል
ጓደኛ ወዳጅ ነው…
.

ለኔ ግን ጠላቴ
ባለጋራዬ ነው
አዋዶ ትቶኛል
ልቤን ቀምቶኛል
ገንዘቤን ንብረቴን
ሁሉን ወስዶብኛል
በመውደድ አኑሮ
በናፍቆት ገሎኛል
.

ታዲያ ከዚ በላይ
የቀረው ምንድነው
ተውኝ አታንሱብኝ
ፍቅር ጠላቴ ነው።

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
❥❥❥❥
እየቆረቆረኝ
tewodros tadesse
Title ➲ እየቆረቆረኝ

Song ➲ Tewedros Taddese

Size ➲ 1.4 mb

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone

ሼር 🙏🙏
የ12ኛ ክፍል ፈተና የካቲት 29 ይሰጣል።

የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2013 ዓ.ም የዲጂታል መታወቂያ ይሰራጫልም ብሏል።

የፈተናው ገለጻ የካቲት 26 ቀን ተካሂዶ ፈተናው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥም ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በቀጥታ (ኦንላይን) ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone