የልቤ ትርታ
202 subscribers
473 photos
4 videos
10 files
422 links
Download Telegram
ውድ የልቤ ትርታ ተከታታዮቻችን
እነሆ
ፍቅር ሲፈርድየተሰኘ ልብ አንጠልጣይ
የፍቅር ታሪክ ይዘንላቹ መተናል
ታሪኩ እንዲጀምር ምትፈልጉ
Jion ሽር አድርጉት
👇👇👇👇👇👇

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
❤️❤️❤️ ❤️❤️❤️

​​ፍቅር_ሲፈርድ

ክፍል_አንድ 1⃣

በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ ታሪክ


ሳራ ትባላለች የሀረር ልጅ ናት እዚህ ከተማችን አዲስ አበባ መኖር የጀመረችው አባቷ በስራ ምክንያት ሀረርን ለቆ ሸገር ሲገባ ነው ... ታድያ ሳራ እድሜዋ 13ን ሲያልፍና ከህፃንነት ወደ ታዳጊ ወጣት ስትሸጋገር ውበቷ እንደልጅነቷ እዩኝ እዩኝ አይልም ነበር ሳራ በአንፃሩ ... አፍንጫዋ ጎራዳ ፀጉሯ ገባ ገባ ያለ ከመሆንም አልፎ ከርዳዳና ከለሯ የቀይ ዳማ የማይሉት ወደ ነጭነት ያደላ ነበር በዚህም ሁሌም ቢሆን ከቆንጆዋ የትምህርት ቤት ጓደኛዋ ቤቲ ጋር ስትሆን ብዙ ተማሪዎች ሙድ ይይዙባት ነበር ...

ሳራ በራሷ የማትተማመን ሴት ናት 7ኛ ክፍልን ተፈትነው ክረምት ሲገባ ሳራ ደስታዋ ወደር አልነበረውም ከቤት ለመውጣት ምክንያቷ ትምህርት ስለነበር ትምህርት አለመኖሩ ለሷ ትልቅ ደስታ ነው አባቷ ይህን ቢያውቅም ምንም ማድረግ አልቻለም እናቷን አታውቃትም ይሄ ተፅኖ አሳድሮባት ይሆናል ሲል አባቷ በስተርጅና ሚስት ለማግባት ወስኖ አንዲት በእድሜ በሰል ያለች ግን ስራዋ ገና የሀያቤቶች መጀመርያ ላይ ያለች ልጃገረድ የምትመስል ሴት አመጣ ... መጀመርያ ያየቻት ቀን ሳራ ደስ አላላትም ቢሆንም ግን አባቷን ስለምታከብር በይሁንታ ተቀበለች...

ወራቶች አለፉ የስምንተኛ ክፍል ሩብ አመት ፈተና ደርሶ ሳራ ለሊት ተነስታ ለማጥናት ከመተኛ ክፍሏ ወደሳሎን አመራችና መብራቱን አበራች ይሄኔ ያየችውን ማመን አልቻለችም አባቷ በደም ተነክሮ መሃል ወለሉ ላይ ተዘርሯል የእንጀራ እናቷ ማርታ አፏ ታፍኖ ከበሩ ስር ካለው አግዳሚ ላይ ታስራለች ... ሳራ መጮህ ጠፋባት ድንጋጤ ጭር ካለው ለሊት ጋር ተደምሮ በፍርሃት ራደች አባ ብላ ልትቀሰቅሰው ሞከረች ግን ያለናት ያሳደጋት አባቷ ላይመለስ እስከወዲያኛው አሸልቧል ...

ሳራ የአባቷ ገዳዮች ሌቦች እንደሆኑ ፖሊስ መረመርኩ ሲል አሳወቃት ውስጧ ግን አንድ ነገር ይላታል የእንጀራ እናትሽ ማርታ እንዴት ተረፈች ስለምንስ ይህ ሁሉ ሲፈፀም ድምፅ አልሰማሁም ቤት ውስጥም የጠፋ አንድም ንብረት የለም ይህ ሁሉ ፈች አልባ እንቆቅልሽ በሳራ አይምሮ ውስጥ ይመላለሳል የአባቷ አርባ አልፎ ትምህርቷን ቀጠለች የእንጀራ እናቷ ማርታም እንደእናት ሆኜ አስተምራለው ስትል ቃል ገብታ ኑሮ ቀጠለ... ሳራ ህልሟ አንድ ሆነ ተምራ ስትጨርስ የተበዳዮች ጠበቃ መሆን ህግ አጥንቶ ወንጀለኛን ፈልፍሎ ለህግ ማቅረብ!!!

ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ሀሙስ ቀን እሷና ቆንጂዬዋ ጓደኛዋ ቤቲ ወደቤት እያመሩ ሳለ የግቢው ቆንጆና ቀለሜ ተማሪ ቤቲን ለመጀንጀን ወደነሱ ተጠግቶ ሰላምታ ሰጣቸውና ተቀላቀለ ... ሶስቱም ስለትምህርት ሲያነሱ ና ስለወደፊት እቅዳቸው ሲነጋገሩ በመሀልም ቀልድ ቢጤ ጣል ሲያደርጉ ሰፈራቸው ደርሰው መለያየት ግድ ሆነና ወደየቤታቸው ሄዱ ... በሁለተኛውም ቀን አንድላይ ሄዱ ከዛማ ሶስቱም ጥሩ ጓደኛሞች ለመሆን በቁ...

ይህ በዚ ብቻ አላበቃም ልኡል በቤቲ ውጫዊ ውበት ተማርኮ የነበር ቢሆንም ሳያስበው ለካ ሳራን ወዷታል ሳራ ስትስቅ ስታወራ ስታኮርፍ ... ብቻ ምንም ስትሆን ለሱ ስሜት ይሰጠዋል ካላገኛት ይከፋዋል ይህን ስሜቱን ግን ሸሽጎ መዝለቅ አልቻለም ለሳራ ፊት ለፊት ከምነግራት ብሎ ለቤቲ እንድትነግርለት ነገራት ይሄኔ ቤቲ በጓደኛዋ መበለጧ ውስጧን ቅናት አናወፀው እሷ ቆንጆ ሆና በልኡል ሳትፈቀር ሳራ መፈቀሯ አበሳጫት ... ሳራንም ከዚ ልጅ ጋር መሄድ እናቁም ስትል ስለሱ መጥፎ ነገር አልፎም በመልኳ እንደሚቀልድ ነገረቻት ሳራም ቤቲና ታምናትና ትወዳት ስለነበር ልኡልን አይንህን ላፈር አለችው ልኡልም ቤቲን ምን ሆና ነው ብሎ ሲጠይቅ እንዴት የፍቅር ጥያቄ ይጠይቀኛል ብላ ነው ስትል አራራቀቻቸው ... በትምህርቱ ጎበዝ የነበረ ልጅ ፈዘዘ ሳራም ልኡልን እንደወደደችው የገባት ሲራራቁ ኖሮ መልኳን የፈጠረውንና አባቷን ያሳጣትን አምላክ እያማረረችና የማታውቃትን እናቷ ፎቶ ላይ አፍጥጣ ማደር ጀመረች...

አንድ እለት ሳራ ትምህርት ቤት ሄዳ ራሷን በጣም ሲያማት ግማሽ ቀን ላይ አስፈቅዳ ወደቤት አመራች የውጪው በር በሰራተኛ ተከፍቶላት ገብታ በረንዳ ላይ ጫማዋን ስታወልቅ ቤት ውስጥ ብዙ ሰው እንዳለ ተረዳች ይሄኔ ድንገት አንድ አረፍተ ነገር ጆሮዋ ውስጥ ጥልቅ አለ "እሷንም እንዳባቷ ቀብረን በነፃነት እንኖራለን!!" ካካካካ( እረጅም ሳቅ)

ክፍል 2
ይቀጥላል..
ሼር ና Join ያድርጉን

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
‍ ​​❤️ፍቅር_ሲፈርድ....

❤️ክፍል_ሁለት 2⃣

❤️❤️ መልካም ንባብ❤️❤️❤️
❤️እውነተኛና_____አሳዛኝ_____እንዲሁም_____አስተማሪ...
።።።።።።


ሳራ አሁን ሁሉም ነገር ገባት የእንጀራ እናቷ አባቷን ማስገደሏን አረጋገጠች በረንዳ ላይ ተቀምጣ ለረጅም ሰአት በንዴት ተንገበገበች ምን አይነት እድለ ቢስ ነኝ ግን ስትል እራሷን አማረረች ይሄኔ ሳታስበው "ሳራ መቼ መጣሽ" አለች ማርታ ሳራም ለምን ይሁን ባታውቅም ድንግጥ ብላ ቆመች ነይ ሰው ላስተዋውቅሽ አለችና ተመልሳ ገባች ድንጋጤዋን ልብ ያለችውም አትመስልም ነበር ... ሳራ ግራ ገባት ማን ይሆን እያለች በውስጧ ተከትላት ወደውስጥ ገባች ስትገባ ሁለት ሴትና አንድ ወጣት ወንድ ሶፋው ላይ ተቀምጠዋል በየተራ ጨበጠቻቸውና ቆመችኝ ...

ሳራ ማለት እሷ ናት አለች እሷን እያስተዋወቀቻቸው ትመስላለች እነሱ ጓደኞቼ ናቸው እሱ ደግሞ... ብላ ንግግሯን ሳጨርስ ስልኳ ጠራ ይሄኔ ሳራ ወደመኝታ ክፍሏ ገብታ ጋደም አለችናና የማታውቃትን እናትንና ሳትጠግበው ያጣችውን አባቷን ፎቶ እያየች ማልቀስ ጀመረች ፈጣሪ የረሳት አልፎም የማያውቃት መሰላት... በመሃል ደሞ ልኡልን ስታስታውስ ሉሌ ምናለ ባላውቅህ ትላለች... እንዲው እያለች እንቅልፍ ይዟት ተኛች ግን ከወትሮው በተለየ ፈርታለች በየደቂቃው ትባንናለች ልክ እንደአባቷ እሷንም ልትገላት ማቀዷ እርግጥ በመሆኑ ቀኗን መጠበቅ ወይስ ቤቱን ጥላ መጥፋት ሁለቱም ለሷ አደጋ ነው ብትጠፋም መሄጃ ስለሌላት ብትኖርም ሞት ስለታቀደላት ምርጫ የላትም ... ሳራ ከቀን ወደቀን ዝም ፍዝዝ ማለት ጀመረች ይባስ ብላ ማርታ ባልዋ(የሳራ አባት) ከሞተ 4ወር ሳይሞላው እንኳ በእድሜ ግማሽ የሚያንሳትን ባል አገብታ አረፈችው...

ባል ተብዬው ሳራን ያስጠናታል ልክ እንደ ታላቅ ወንድምም ይንከባከባት ጀመር ሳራ ይበልጥ ግራ ገባት ይህ በንዲህ እንዳለ የሚኒስትሪ ፈተና ደረሰ ይሄኔ ልኡል ለሳራ የተወጋ ልብ የሚል ልቦለድ መፅሃፍ ሰጣት ሳራም።ቤት ገብታ እስክታነበው ጓጓች ... ልክ እቤት ስትገባ የመጀመርያ ስራዋ መፅሃፉን መግለጥ ነበር ይሄኔ በጥንቃቄ የተጣጠፈች ወረቀት ከውስጡ አገኘች ከፍታ ማንበብም ጀመረች...
"ሳሪቲ ትምህርት ተዘግቶ ከመለያየታችን በፊት ስላለፉት ስህተቶቻችን ይቅር እንባባል!! ይገርማል እኔ አንቺን አፈቀርኩ ማፍቀሬ ልክ ነበር ባንቺ እይታ ደግሞ ስህተት ነበር የሰጠሁሽ መፅሃፍ ቆንጆ የፍቅር ህይወትን ያስተምርሻል የኔ ውድ ማፍቀሬ ቢያስከፋሽም ማቆም አልችልምና አሁንም ወደፊትም አፈቅርሻለሁ ...." ይላል አምብባ ስጨርስ የደስታም የሀዘንም ስሜት ተፈራረቁባት ደስታዋ ልኡል ሲሆን ሀዘኗ ደግሞ ጓደኛዋ ቤቲ ናት...

ሳራ ለልኡል መልስ መፃፍ አልፈለገችም በነጋታው የፈተና ፈረቃቸው ይለያይ ስለነበር ሳይገናኙ ቀሩ ከ2ቀን በላይ ግን መታገስ አልቻለችም ሰፈሩ ድረስ ሄዳ ከቤቱ አስጠራችው ልኡል ልክ ሲያያት ደንግጦ ቆመ ከዛ ግን አይኖቻቸው ተግባቡ ቃል ሳይወጣቸው ልቦቻቸው ፍቅርን ተጋሩ... ከዚ ቀን ጀምሮ ሳራና ልኡል አንድ ሆኑ ሳራ ብሞት እንኳ ብላ ለልኡል ስለአለፈው ሁሉ ህይወቷ አጫወተችው ቅስሙ ተሰበረ በቅርብም ከዛ ቤት መውጣት እንዳለባት አብረው ወስነው ነገሮችን ማመቻቸት ጀመሩ...

ሀምሌ አልቆ ነሀሴ ተራውን ሊረከብ ደርሷል አንድ ክፉ ጠዋት ማርታ ከቤት ወጥታለች በቤት ውስጥ ያሉት ሳራና የማርታ ባል ነበሩ ሳራ ሰውየውን ባታምነውም ትወደዋለች ለዛም እሷን እንጂ እሱን አትፈራውም ያን ቀን ግን ይህ ወጣት ሳራን ለስጋዊ ስሜቱ ተመኛት ተመኝቶም አልቀረም በብዙ ልፋት የእንቅልፍ ኪኒን እንድትውጥ አረገ ሳራም ድብን ያለ እንቅልፍ ተኛች ይሄኔ ሊደፍራት ልብሶቹን ለማውለቅ ይጣደፍ ጀመር...


3, #ይቀጥላል.....👈

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቢያንስ ለ 5 ሰዉ ሼር ያድርጉ

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
‍ ​​🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒

❤️ ፍቅር ሲፈርድ ❤️

ክፍል 3⃣


❤️እውነተኛ___አሳዛኝና__አስተማሪ.....



አወላልቆ ሊደፍራት የሷን ልብስ ማውለቅ ሲጀምር በሩ በሀይል ተንኳኳ ደንግጦ እላይዋ ላይ ዘግቶባት ልብሱን ሰብስቦ ወደሻውር ቤት ገባና መታጠብ ጀመረ ሰራተኛዋ በር ከፍታላት ማርታ ገባች ባሌ ዛሬ ደሞ እንዴት ቀደምከኝ አለች የሻውሩን ድምፅ ሰምታ ስላልሰማት መልስ ሳይሰጣት ቀረ... ብቻዋን እያወራች ኪችን ገብታ ምግብ አቅርባ እየበላች ሰራተኛዋን ስሚ ሳራ አልመጣችም እንዴ? ስትል ጠየቀቻት ሰራተኛዋም የሳራን መግባት ተናገረች ...

ሳራ ለሰአታት ተኛች ማርታ ግራ ገብቷት እየከፈተች ታያት ጀመር ባልየውም ስራውን ስለሚያውቅ ፈራ ከ10 ሰአታት ቡሃላ ነቃች ስትነሳ እራሷ በጣም ከበዳት ማርታም ምን ሆነሻል አንቺ ስትል ጠየቀቻት ሳራም ለማርታ ምንም ሳትመልስላት መታጠብያ ቤት ገብታ ለማስታወስ ጥረት ታደርግ ጀመር ይሄኔ ውሃ ሳይጠማት ውሃ ካልጠጣሽ ብሎ ያስጠጣት ያለምክንያት አለመሆኑ ገባት ይህን ለማረጋገጥም አንድ ዘዴ ፈጠረች ማርታ ዞር ስትልላት ልትደፍረኝ እንደነበር ለማርታ ልናገር አለችው ደንግጦ አይ እባክሽ ይቅርታ.... ቀባጠረ አሁን እርግጠኛ ሆነች ለማርታ መናገሩንም ተወችውና ለፍቅረኛዋ ልኡል ልትነግረው ወሰነች...

ልኡል ይሄን ሲሰማ አበደ እረጅም ሰአት ራሱን አመመው በሳምንት ውስጥም ቤተሰቦቹን አሳምኖ ሳራን እነሱ ቤት እንድትኖር አመቻቸ በሰአቱ ፍቃደኛ አልሆነችለትም ነበር ቡሃላ ግን እናቱ ለምለምንና ታናሽ እህቱን ልእልና ሲያስተዋውቃት እነሱም በደስታ ከነሱ ጋር እንድትኖር ሲጋብዟት የፍቅረኛዋ ቤተሰብ ሳይሆን የራሷ መሰሏት በሀሳባቸውም ተስማምታ ከነሱ ጋር ለመኖር የአባቷን ቤት ለእንጀራ እናቷ ጥላላት ወጣች ...

ልኡል ያደገው ከእናቱ ጋር ነው በጣም ሀብታም ስለሆኑ ስለምንም መጨነቅ አይወዱም እናቱ ስለልጇ ልኡል አብዝታ ትጨነቅለታለች ፈፅሞ ያለው መሳካት አለበት ብላ ነው የምታምነው አባቱ አሜሪካ ነው ያለው እህቱን በአንድ አመት ቢበልጣትም እሷ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ናት በርግጥ እሱ ትንሽ እያለ አቋርጦ ስለነበር ነው የቀደመችው ያቋረጠበት ምክንያትም ታሞ ስለነበር ነው። ስለልኡል ይህን ካልኩ ይበቃል ወደዋናው ታሪክ ስገባ...

ሳራና ልኡል 9ኛ ክፍልን ጨርሰው 10ን መማር ቀጥለዋል ሁለቱም የማይነጣጠሉ ጥንዶች ናቸው እነሱን አይቶ ያልቀና የለም አብረው እስፖርት ይሰራሉ ፊልም ያያሉ ያጠናሉ... ሳራ ለመጀመርያ ግዜ ደስተኛ ሆነች ደምግባቷ ወጣ ቅርጿ ደግሞ ሞዴል ያስብላት ጀመር የወንዶች አይን ውስጥ በቀላሉ መግባት ጀመረች አላማዋ ላይ ትኩረት አድርጋ በደስታ ኑሮን ቀጣለች ... የሚያሳዝነው ግን ደስታዋ ከወራት አልዘለለም ያቺ ክፉ ማርታ አፈላልጋ የልኡልን እናት በማግኘት ስለሳራ መጥፎ ነገር ነገረቻት ከዛም አልፋ እቤቷ እንድትመለስ ካላረገቻት ልጄን ሰረቀች ብላ እንደምትከሳት አስጠነቀቀቻት በዚ ግራ የተጋባችው ለምለም ጭንቀቷ ልክ አጣ ልኡል እግሩ ሲወጣ ጠብቃም ሳራን አስጠርታ መኝታ ቤት ዘግታ ታወራት ጀመር...

ሳራ ለልጄ ስል እንደሆነ እቤቴ የምትኖሪው ገብቶሻል? ልጄ በጣም ካዘነ ወይ ከተናደደ ወይ ከተጨነቀ አልያም በጣም ከተደሰተ እራሱን ይስታል ይሄ ብቻ አይደለም ይሞትብኛል ለዚ ነው ያለው ሁሉ የሚደረግለት በቅርብ አባቱ ነገሮችን አመቻችቶ ይወስደናል ከዛም ይታከማል እስከዛ ግን ልጄ አንድ ነገር እንዲሆንብኝ አልፈልግም አንቺ ለአባትሽ መሞት ምክንያት እንደሆንሽ አሳዳጊሽ ማርታ ነግራኛለች ግን በልጄ ቀልድ አላውቅምና እንዲጠላሽ አርገሽ በቶሎ ቤቴን ለቀሽ ሂጂልኝ ስትል የሳራን ልብ ሁለት ቦታ ከፈለችው በመጨረሻዎቹ አረፍተ ነገሮች እንባዋ ባይኗ እየሞላ ፈሰሰ ይህች አለም የአጭበርባሪዎችና የውሸታሞች ብቻ ናት አለች በውስጧ ይሄኔ እንባሽን ጥረጊ ልጄ ያስከፋሁሽ መስሎት ደግሞ ... ብላ ተነስታ ወጣች...

ከዛ ቀን ቡሃላ ህይወት ጭልምልም አለባት ማትሪክን እንደምንም ተፈተነችና እንደተባለችው እንዲጠላት እያያት ከወንዶች ጋን መላፋት አልፎም መሳሳም ጀመረች ልኡልም በተደጋጋሚ እንደዛ የምታፈቅረ ልጅ በመቀየሯ ምክንያቷን ማጣራት ጀመረ ግን ምንም ፍንጭ አላገኘም ሳራም ብቻዋን ስትሆን ደም እምባ እያለቀሰች ልኡሌ ላንተ ስል ነው ትላለች በሆዷ...
ታድያ አንድ ቀን ልኡልና እናቱ እቃ ሊገዙ ወጡ ይሄኔ እህቱ አንድ ጎረምሳ እቤት በማምጣት ሳራን ልክ ማሚና ሉሌ ሲገቡ እቅፍ አርገሽ ጭኑ ላይ ተቀመጪና የምትስሚው ምሰይ አለቻት ሳራም የተባለችውን ለማድረግ ሳትወድ በግዷ ተስማማች እንደተባለውም ልክ ሲመጡ የተባለችውን አረገች ልኡል ያየውን ማመን አቃተው ሳራን ጎትቶ ከልጁ ላይ በማንሳት ስሚ ሳራ ካሁን ቡሃላ ላይሽ አልፈልግም ጭራሽ ከቤተሰቤ ከእናቴ ፊት??? ሲል ጮኸባት ሳራም ምንም ሳትመልስለት ስልኳን ይዛ እምባዋን እያዘራች ቤቱን ለቃ እግሯ ወደመራት መጔዝ ጀመረች...

ይቀጥላል ......!
ከወደዱቱ ለሚወዱት
ሼር ማድረግ አትርሱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
ለሰዎች ልንሰጣቸው የምንችለው ትልቅ ስጦታ ካለ...ስሙ ጓደኝነት ይባላል።...ማንንም ሰው ከጓደኝነት በላይ ልናቀርበው አንችልም።...ጓደኝነት አብሮ በመኖር ድር ተገምዶ..በውጣ ውረዶች ተነጥሮ..በፍቅር ተቀሽሮ...በእኩልነት እርካብ ተሞሽሮ..የተሰራ አሸንክታብ ነው።
ወዳጅ ለመሆን join ያድርጉት
@geyone
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_4

...🖊እርሷ ግን ምንም መናገር እልፈለገችም ግን ምንም ቢሆን ጓደኛሽ ነኝ ብላት ብሰራት ምንም ልትመልስልኝ አልቻለችም የማትነግረኝ ከሆነ ደግሜ እንደማላናግራት ነግሬ ላስፈራራት ሞከርኩ ግን ተሳክቶልኛል እሺ እነግርሻለው ግን እባክሽ የምነግርሽን ለማንም እንዳትናገሪ እባክሽ አብሶ ለአማን እና ለአቤል አለችኝ በጣም ደነገጥኩ ከእነርሱ ምን ልትደብቅ ትችላለች ብዬ ደነገጥኩ ከዛ እኔ ፍቅር ይዞኛል ብላ ስቅስቅ ብላ አቀሰች ልቤ ቀጥ ብላ ቀረች በጣም ደነገጥኩ ለአማንም ለአቤልም አትናገሪ ያለችኝ ከእነርሱ አንዳቸው ናቸው ብዬ ደነገጥልኩ አንድም ቀን ለአቤል ልዩ ስሜት እንዳለኝ ነግሬአት አላውቅም የመሸነፍ ያክል ተሰማኝ ተቀደምኩ ብዬ አሰብኩ ግን ከጓደኛዬ አይበልጥም ብዬ መልሼ አሰብኩ ከዛም እርሷን ላማረጋጋት እየሞከርኩ ከማን ፍቅር እንደያዛት ስጠይቃት ይባስ ብላ በጣም ማልቀስ ጀመረች ከዛም ትንሽ እንደቆየን ልክ ልትንግረኝ አ... እንዳለች ስልኬ ጠራ ከዛ አቤል ነበር የደወለው ልቤ ክፍል አለ ላንሳው አላንሳው እያልኩ እያለ ሜሮን አንሽው እንጂ ስልኩን ስትለኝ እ እ እ እሺ እልኩ እና አነሳውት አቤት እቤል አልኩት ቃልዬ የት ነሽ አለኝ ዶርም ነኝ ፈልገኸኝ ነበር አልኩት አዎ በፍጥነት ነይ እፈልግሻለው ምን የሚያስቸኩል ጉዳይ ተገኘና ነው እንዲህ የምታጣድፈኝ ስለው እርሱ ስትመጪ ይነገርሻል አሁን እታች እየጠበኩሽ ነው አታስቁሚኝ ፈጥነሽ ውረጂ አለኝ ከዛም እሺ አሁን መጣው በቃ ብዬ ስልኩን ዘጋውት ሜሮን በቃ ሂጂ ስትምጪ እናወራለን አለችኝ ትንሽ አረጋግቻት ሄድኩ በጣም ጨንቆኛል አሁን አቤልን ነው ምወደው ብትለኝ ምን ይዉጠኛል ደግሞስ እርሱ ለምንድን ነው እንዲህ እያጣደፈ የጠራኝ እርሱም እንደሚወዳት ሊነግረኝ ይሁን እያልኩ እያሰላሰልኩ ሳላስበው አቤልን አልፌው ሄድኩ አቤል አውቆ አይቶኝ ዝም አለና ከኃላዬ ይከተለኛል እኔ ግን ከገባውበት ውስብስብ ሀሳብ መውጣት አልቻልኩም ከዛ ትንሽ ከቆየ በኃላ ጃስ ሲለኝ በጣም ደንግጬ በስመአብ ብዬ አቀፍኩት ከዛ የልብ ምቱ ይሰማኝ ነበር ልቡ በጣም ይመታል ከዛ ቀና ብዬ ስመለከተው ቁልቁል ወደኔ በስስት እያየኝ ለምን ግን አወኩሽ ባላቅሽ ይሻለኝ ነበር አለኝ በጣም ደንግጬ ለምን ምን አጠፍው ስለው አይ ምንም ብሎ ለቀቀኝ ከእቅፉ ባልወጣ ደስ ይለኝ ነበር ግን ግድ መውጣት ነበረብኝ ከዛም ለትንሽ ሰአታት በመሀከላችኝ ዝምታ ሰፈነ ዝምታውን ለመስበር ያክል ለምን ነበር እንዲህ በአስቸኳይ የፈለከኝ አልኩት እርሱም ጥቂት እንደማሰብ አለና ይኸውልሽ ቃል ልነግርሽ የምፈልገው ነገር አለ አለኝ እኮ እሱን አቃለው ግን ምንድነው ልትነግረኝ ምትፈልገው ነገር አልኩት በጣም የተጨናነቀ ቃላቶቹን እያወጣ ቃል በመጀመሪያ ስለ እኔ ምታስቢውን ነገር ንገሪኝ አለኝ እኔም በጣም ደነገጥኩ እ እ እ ምን ማለት ፈልገህ ነው ምትነግረኝን ነገር በግልፅ ንገረኝ አልኩት ከዛ ከመች ጅምሮ እንደሆነ ባላውቅም አንቺን ማሰብ ከጀመርኩ ግን ቆይቻለው ቃልዬ በጣም ነው ማፈቅርሽ አለኝ አንደበቴ ቁልፍልፍ አለ መናገር አቃተኝ....

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 5 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡vote ስታደርጉ ለኛም ብርታት ነው 🙏

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

👍 @geyone
❤️ @geyone
🤳 @geyone
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
5 ይቀጥላል ለምትወዱት ሽር አድርጉት.......
"ለጠላቶችክ ደስታ ብለክ ሳይሆን መሸነፍክ ለሚያስከፋቸው ሰዎች ብለክ ጠንካራ ሁን"

ዛሬ ውስጥህ ሰላም አጥቶ መኖር አስጠልቶካል? ተስፋ እንዳትቆርጥ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ዛሬ ሰዎች ከሰው ክብር ዝቅ አርገውክ በሚጠሉክ ሰዎች ተከበሀል? የሚወዱክ ይመጣሉ፤ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ዛሬ ስንት የደከምክበት ቢዝነስ ብልሽትሽቱ ወጥቷል? ቀና በልና አማራጮችን ተመልከት፤ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ዛሬ በትዕምርትህ የተዘጋጀከውንና የደከምክበትን ያህል ውጤት አላመጣህም? ትምርት በቃኝ እንዳትል፤ ነገ ሌላ ቀን ነው።

የተሸነፍከው የወደክ ፣ የተሰበርክ ቀን አይደለም። የተሸነፍከው በወደክበት ለመቅረት አምነክ የተቀመጥክና ዳግም መሞከር ያቆምክ ዕለት ነው።

በል ተነስ የእኔ አንበሳ፤ ይቺ ምድር ለተሸናፊ ቦታ የላትምና "ለችግሮችህ በሙሉ ትልቅ ችግር ሁንባቸው።"

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌

Join
@geyone
@geyone
@geyone
ጥምቀት በባህርዳር ጣና ዳር
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_5

...🖊ቃልዬ በጣም ነው ማፈቅርሽ አንደበቴ ቁልፍልፍ አለ መናገር አቃተኝ በወቅቱ ምን እንደሚሰማኝ አላውቅም በጣም ደስ እንዳለኝ አቃለው ግን ቅር ቅር የሚለኝ ነገር አለ ምንድን ነው እንዴ እረስቼው ሜሮን አ.... ስትል ነበር ስልኬ ጮሆ ማንን እንደነበር ሳልጠይቃት ነበር የመጣውት አሁን ለአቤል እንደምወደው ከነገርኩት እርሷም እርሱን ከወደደችው ትጎዳለች ታዳ ምን ልበለው በጣም ጨነቀኝ ዝምታዬ ያስጨነቀው አቤል ቃልዬ ምነው ዝም አልሽ አንድ ነገር በይ ማፍቀሬ ስህተት ሆኖ ከታየሽ ስደቢኝ ምችኝ ብቻ አላውቅም ቅጪኝ ግን እባክሽ ዝም አትበይኝ ዝምታሽ ያስፈራል አለኝ እኔም እንደማንገራገር አልኩና ትንሽ ጊዜ ስጠኝ ማሰብ እፈልጋለው አልኩት እርሱም ችግር የለውም የፈለግሽውን ያክል ጊዜ ወስደሽ አስቢበት አለኝ እሺ ብዬው ቻው ተባብለን ተለያየን ከአቤል አፍ ይሄ ይወጣል ብዬአንድም ቀን አስቤው አላውቅም ግን በጣም ደስ ብሎኛል አሁን ችግሩ ሜሪ ማንን ነው ምትወደው ነው ከራሴ ጋር እንዲህ እየታገልኩ ዶርም ደረስኩ ስደርስ ግን ሜሪ ብዙ ከማልቀስዋ የተነሳ እራስዋን አሟት ተኝታለች አስተኛኘቷ ልክ እንደህፃን ነው ታሳሳለች በቃ ነገ አወራታለው ብዬ ወደ መኝታዬ ሄድኩ ለመተኛት ብሞክርም ምንም እንቅልፍ አልመጣም አለኝ ላነብ ብልም እንኳ በቃ ቅዥብ ብያለው አይነጋ ነገር ለሊቱ አመታት ሆኖብኝ ነጋ ጠዋት ገና እንደተነሳን በደንብ እንኳን ሳትነቃ ከማን ፍቅር እንደያዛት ጠየኳት ትንሽ እንደመሽኮርመም ብላ አ አ አ ስትል ኧረ በፈጣሪ ይሁንብሽ ንገሪኝ ስላት በቃ እሺ አማንን ነው የወደድኩት አለችኝ ምን አማን አልኳት አዎ አማን አለችኝ እርግጥኛ ነሽ አልኳት ያምሻል ምን ማለት ነው ስትለኝ እውንትም ያመኛል ምን አይነት ጥያቄ ነው የጠየኳት

ግን አቤል ትላንት እንደሚያፈቅረኝ ከነገረኝ በላይ ዛሬ ደስተኛ ሆንኩ ከዛ የስ ምናምን እያልኩ ሳብድ ምን ሆነሽእንዴት ነው ዛሬ ግን በሰላም ነው አለችኝ በጣም ደነገጥኩ የማደርገው ነገር ለራሴም ገርሞኛል ወደ ማታ አካባቢ እኔና ሜሪ ቁጭ ብለን እያወራን እንደወደደችው እና ብዙ ነገር ነገረችኝ ከዛም ቃል ግን እስኳሁን በፍቅር ያሰብሽው ሰው የለም ስትለኝ አሁን አልነግርሽም ሰርፕራይዝ ነው አልኳት እንድነግራት ብዙ ብትለምነኝም አልነገርኳትም የምንመረቅበት ጊዜ ደርስዋል ለፈተና በጣም እየተዘጋጀን ነው በብዛት ላይብረሪ ነው ምናሳልፈው ለአቤልም ልክ ፈተና እንደጨረስን ሁሉንም ነገር ልነግረው አስቤያለው ይህንኑ ሀሳቤን ስለነገርኩት እርሱም እየተጫነኝ አይደለም ዛሬ ግን በጣም የሚያስጠላ የሚያናድድ ነገር ተፈጠረ አማን ደውሎ ሊያገኘኝ እንደሚፈልግና በጣም አስቸኳይ እንደሆነ ነገረኝ ከዛም እኔ ጋር እንደምትመጪ ለማንም እንዳትናገሪ ብሎኛል ከዛም አስቸኳይ ነው ስላለኝ ፍንጥር ብዬ ስወጣ ሜሪ ወዴት ነው ስትለኝ ማሚ ጋር ልደውል ነው እዚህ ኔቶርክ የለም አልኳት ያልኳት ነገር ባይዋጥላትም እሺ አለችኝ ከዛም አማን ከርቁ ሆኖ እየተንጎራደደ አየውት በቻልኩት ፍጥነት ደርሼ ምን ተፈጠረ ችግር አለ አቤል ምን ሆነ አልኩት አይ ማንም ምንም አልሆነም እኔ ለራሴ ጉዳይ ፈልጌሽ ነው አለኝ ምነው ምን ሆንክ አልኩት ይኸውልሽ ቃል ችግር ውስጥ ነኝ አለኝ የምን ችግር አልኩት ፍቅር ያዘኝ አለኝ እኔም ሜሪን ወደዳት ማለት ነው በቃ ጎደኝነታችን ወደ ፍቅር ሊለውጥ ነው ደስ ይላል እያልኩ እና ጥሩ እኮ ነው ግን ከማን እልኩት አማን ዛሬ አስተያየቱ ተቀይሮብኛል ወደ እኔ ቀስ እያለ መጠጋት ጀመረ ቀስ እያለ በጣም ተጠጋኝ ከዛም ካንቺ ሲለኝ ልቤ ቀጥ አለ መናገር አቃተኝ ደርቄ ቀረው አማን ግን ቀስ ብሎ ልክ ሊስመኝ ሲል ዋው ዋው ስታምሩ የሚል ከጭብጨባ ጋር...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 6 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
መልካም ንባብ
@geyone
@geyone
@geyone
@geyone
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_6
...🖊በጣም ተጠጋኝ ከዛም ካንቺ ሲለኝ ልቤ ቀጥ አለ መናገር አቃተኝ ደርቄ ቀረው አማን ግን ቀስ ብሎ ልክ ሊስመኝ ሲል ዋው ዋው ስታምሩ የሚል ከጭብጨባ ጋር ድምፅ ሰማው ስዞር ሜሪ እና አቤል ናቸው በጣም ደነገጥኩ ግን ስረዳ አቤል እኔ ጋር ሲደውል ሜሪ አንስታ እየተጣደፍኩ እንደወጣው እና የሆነ ነገር እንዳለ ስትነግረው ነው ተከታትለው የመጡት ግን አቤል በጣም እንደተናደደ ያስታውቃል በቃ ለዚህ ነበር ምላሽ መስጠት ያቃተሽ ብትነግሪኝ እኮ ችግር አልነበረውም ለምን ለምን ታሰቃይኛለሽ ቆይ ምን ጋር ጥፍቴ አንቺን ማፍቀሬ ግን እንደዚህ አይነት ሴት አልመሰልሽኝም ነበር ብሎኝ ምላሼን ሳይጠብቅ ሄደ ላስቆመው ሞክሬ ነበር ግን አልቻልኩም ይሄ ሁሉ ሲፈጠር ሜሪ ከማልቀስ ውጪ ያወራችው ነገር አልነበረም አሁን ግን ተራዋ የደረሰ ይመስል ቃል አንቺ እኔን እንዲህ ታረጊኛለሽ የውስጤን ስለነገርኩሽ ትረጂኛለሽ ብዬ አንቺ እኮ ጓደኛዬ ሳትሆኚ ልክ እንደህቴ ነበር ማይሽ አሁን ግን እምነቴን ሙሉ በሙሉ አጥፍተሽዋል ክፉ ክፉ ነሽ እያለች እያለቀሰች ወደ ዶርም ሄደች የሚሆነው ሁሉ በህልም ነበር የመሰለኝ ደርቄ ቀረው የቆምኩበት መሬት ላይ ወደኩ ልክ እኔ ስወድቅ አማን ተንበረከከ ምን ሆንሽ ምንድን ነው የተፈጠረው እነ ሜሪ ምን ሆነው ነው እለኝ ምንም ማለት አልቻልኩም አሁን ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ ነገ ስረጋጋ ሁሉንም እነግርሀለሁ አልኩት ሊያስጨንቀኝ ስላልፈለገ እሺ ወደ ዶርም ልሸኝሽ አለኝ አይ እራሴ እሄዳለው ደና ነኝ እልኩት እባክሽ እንዲ ሆነሽ ብቻሽን ትቼሽ መሄድ አልችልም ሲለኝ እባክህ እማን ተወኝ እራሴ መሄድ እችላለሁ ብዬ ጮኩበት እስከዛሬ ስስቅ እንጂ እንዲህ ስሆን አይቶኝ ስለማያቅ በጣም ደነገጠ እሺ በቃ እሺ ተረጋጊ እሄዳለው ብሎኝ ቀስ እያለ መሄድ ጀመረ የሜሪን አይን እንዴት እንደማየው ምን ብዬ እንደማስረዳት ግራ ገብቶኛል ግን ዶርም ስገባ ጥቅልል ብላ ታለቅሳለች ላናግራት አልቻልኩም በቃ ስትረጋጋ አናግራታለው ብዬ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩ በቃ ከአቤል ጋር እስከመጨረሻው ተጣላን ብዬ አለቀስኩ በጣም በሸኩ ከሁሉም በላይ ከአቤል በፊት የማቃትን ጓደኛዬን ጎዳዋት በእርሷ ዘንድ ታማኝነቴን አጣው ሁሉም ቀርቶብኝ ብያንስ ባናግራት ደስ ይለኛል ግን እርሷ አይኔን ማየት አትፈልግም እንደምንም እየተሟዘዘ ነጋ ገና ሲነጋ አማ ደውሎ ላግኝሽ አለኝ እኔም ትላንት ስላስከፍውት በዛው ይቅርታ እለዋለው ብዬ እሺ አልኩት ከአማን ጋር ተገናኝተን ስለተፈጠረው ነገር በሙሉ ነገርኩት አቤል እንደማፈቅረው ሜሪ ደግሞ እርሱን እንደምትወደድ ብቻ ሁሉንም ነገርኩት ሆድ ብሶኝ ስለነበር ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ከዛም እንድረጋጋ ብሎ አማን እቅፍ ውስጥ አስገባኝ ክፍቶኝ ስለነበር ምንም አላልኩም ማታ አቤል እንደዛ ስለተናገረኝ ይቅርታ ሊጠይቀኝ እና ምን እንደተፈጠረ ላስረዳው ፈልጎ ሲመጣ እኔን እና አማንን ተቃቅፈን አየን ከዛ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 7 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

━━━━━━━✦🌹
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
🌹✦━━━━━━━
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_7

...🖊ማታ አቤል እንደዛ ስለተናገረኝ ይቅርታ ሊጠይቀኝ እና ምን እንደተፈጠረ ላስረዳው ፈልጎ ሲመጣ እኔን እና አማንን ተቃቅፈን አየን ከዛ ቃል አለኝ እያለቀስኩ እንደነበር አይቷል እና አማንን ጥሎን ሄደ አቤል አማን የተቀመጠበት ቦታ ላይ ቁጭ አለና ልትነግሪኝ ምትፈልጊው ነገር አለ ብሎ ጠየቀኝ እኔም ከምላሼ ይልቅ እንባዬ ነበር የቀደመኝ ከዛም ሊያረጋጋኝ ሞከረ ግን ባሰብኝ እኔ አልጠቅምም እያልኩ ማልቀስ ጀመርኩ እንዴ ለምንድነው እንዲህ ምትይው አለኝ አቤሌ የተፈጠረውን እንዳልተፈጠረ አድርጎ ጠየቀኝ የገዛ ጓደኛዬ በኔ ምክንያት ተጎዳች አንተንም አሰቃየውህ እያልኩ አለቀስኩ ከዛ አቤሌ አንድ ነገር ልንገርህ አልኩት ምንድነው ቃሌ ንገርኝ አለኝ እቤሌ ገና እንዳየውህ የመጀመሪያ ቀን ነበር የወደድኩህ ግን ልነግርህ አልቻልኩም ስለው ስልኬ ጮኽ ማም ነበረች አቤት እማዬ አልኳት ምነው ልጄ ይሄን ሰሞን አልደወልሽም በሰላም ነው አለችኝ ደና ነኝ እናቴ ሰለም ናቹ አልኳት እማ ድምፄ ሲለወጥ ታቃለች ልጄ አሞሻል እንዴ ድምፅሽ ትክክል አይደለም አለችኝ አይ እናቴ ምንም አልሆንኩም ትንሽ ጉንፍን ነገር ይዞኝ ነው አልኳት እሺ በቃ ችግር ካለ ልጄ ደውይ እባክሽ አለችኝ እሽ እማ አታስቢ አልኳት ከዛ እርሷን አናግሬያት ዞር ስል አቤል በቦታው የለም ደነገጥኩ ስደውል ስልክ አያነሳም ከዛም ወደ ዶርም ስሄድ ሜሪ የለችም በቃ ዶርም ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ ከ1 ሰአት በኃላ ሜሪ መጥታ ቃል በጣም ይቅርታ ሳልሰማሽ እንደዛ መሆን አልነበረብኝም አለችኝ ግራ የማጋባት ፊት እያሳየዋት አልገባኝም ሜሪ ይቅርታ አረግሽልኝ አልኳት ሲጀመር ምን አጥፍተሽ አማን ሁሉንም ነገር ነግሮኛል አቤልንም እንደምትወጂው እርሱም እንደዛው አይደል አለችኝ እኔ ግን ምንም ሳልላት ተጠመጠምኩባት ከዛ ኧረ ቀስ ገደልሽኝ አለችኝ እና ተሳስቀን ትላንት እና ዛሬ ምንም እንዳላነበብን ፈተና ከ3 ቀን በኃላ እንደሆነ እረስቼዋለው ግን ጊዜው በጣም ይፈጥናል ትኩረታችንን ሙሉ በሙሉ ጥናታችን ላይ አረግን አቤልን ከዛ ቀን ጀምሮ አይቼው አላቅም በጣም ቢያሳስበኝም ግን አሁን ጥናቴ ላይ ትኩረቴን ማረግ እንዳለብኝ አውቃለሁ እንዲህ እያለ ምርቃታችን ደረሰ አራታችንም ተመራቂ ለመሆን በቃን ማም በጣም ደግሳ ነው የጠበቀችኝ

አሁን ከተመረቅን 2 ሳምንት ሞላን አሁን እኔ ድሬ እናቴ ጋር ነኝ ሜሪም አቤልም አማንም ሀዋሳ ናቸው ከአማን እና ከሜሪ ጋር በስልክ እናወራለን አቤልን ግን አግንቼው አላቅም ግን ዛሬ የማላቀው ቁጥር ተደውሎ ማንነቱን ስጠይቅ አቤል ነበር በጣም ደስ አለኝ ምገባበት አጣው ከዛም ድሬ እንደመጣና ማንንም እንደማያቅ ወጥቼ እንድቀበለው ነገረኝ ትንግርት ነው የሆነብኝ አቤል ድሬ ነው ያለው እሺ መጣው በቃ መጣው አልኩት እና ሊያሳምረኝ የሚችል ልብስ መምረጥ ጀመርኩ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ አርጉ፡፡ክፍል 8 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_8

...🖊ሊያሳምረኝ የሚችል ልብስ መምረጥ ጀመርኩ ግን የትኛውንም ልወደው አልቻልኩም ከዛ ከታናሽ እህቴ ለመበደር ፈለኩ እና ዛሬ ቅዳሜ ስለሆነ ክላስ አልነበራትም ማርቲ 12 ክፍል ተማሪ ናት እናም ማርታ እያልኩ መጮህ ጀመርኩ ከዛም የክፍሌን በር ከፍታ ምንድነው ምትተረተሪው ቀስ ብለሽ አትጣሪም አለችኝ ድንጋጤው ነው መሰለኝ በጣም ጮኬያለው አይ ልብስ እንድታበድሪኝ ነበር አልኳት ምን አይነት ልብስ ፈለግሽ ደሞ የት ልትሄጂ ነው አለችኝ አይ የትም አንድ ጓደኛዬን ላገኘው ነው አልኳት እየሳቀች ኧረ ማነው ባክሽ እንዲህ ማዘንጥሽ አለችኝ ኧረ ዝም ብሎ ኖርማል ጓደኛዬ ነው ልብሴ ዛሬ ቆሽሸዋል ለዛ ነው አንቺን ምጠይቅሽ አልኳት ኮስተር ብዬ ትንሽ ማስመሰል እችላለው እና ወድያው አመነችኝ ግን ማስመሰል በጣም ነው ምጠላው ዛሬ ግን ምንም ባልተወራ ወሬ ነገር ብለኩስ መቀጣጠሉ ስለማይቀር ዝም ማለትን መረጥኩ ከዛም በጣም ምወድላትን ቀይ ትሸርት ከሱሪ ጋር ይዛልኝ መጣች ከዛም ፀጉሬን ወደሀላ ለቅቄ ለአመሉ የውሃ ቻፒስት ከንፈሬን ተቀባው ያው ቀይ መቀባት ብዙም ደስ አይለኝም እና ሸንቀጥ ብዬ ወጣው ከዛም ወደ መናሀሪያ ሄድኩ የሚገርመው አቤልን ከብዙ ሰው መሀል ነበር ነጥዬ ያወኩት ከዛም ደወልኩለት አንስ ያለች ጥቁር ቦርሷ ይዟል ወድያው አነሳው የቱ ጋር ነሽ አልኝ አይቼሀለው ፊትህን አዙር አልኩት ልክ ሲዞር አየኝ ከዛም እጄን አውለበለብኩለት ወድያው ስላወቀኝ ወደ መምጣት ጀመረ እኔም ወደሱ እየሄድኩ ነበር ግን ልቤ እጅግ ይመታ ነበር ከዛም ድርሶ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ ሻንታውን ልቀበለው እጄን ስሰረጋ አይሆንም ብሎ ለትንሽ ጊዜ ከተከራከርን በኃላ ሳይፈልግ ተቀበልኩት ከዛም እየተራመድን እንዴት እንደመጣ ጠየኩት እኔን ለማየት እንደመጣና ማንንም እዚህ እንደማያውቅ ነገረኝ ከዛም እኔን ለማየት በመምጣቱ እጅግ በጣም ደስ አለኝ እና ልክ ወደ ኪሱ እጁን ከተተ ከዛ በጣም የደነገጠ ይመስላል ወደሌላኛው ኪሱ እጁን ሰደደ አሁን ይበልጥ ደነገጠና እስቲ ቦርሳውን ስጪኝ ብሎ ቦርሳውን ተቀበለኝ ከዛ ወይኔ እናቴ ቀለጥኩ አለኝ ምነው ስለው ቃልዬ ተዘረፍኩልሽ አለኝ ምን ብዬ ጮውኩ ምን ምትፈልገው እቃ ነበር አልኩት አይ እቃስ ምንም አልተነካም ግን የነበረኝን ገንዘብ በሙሉ ተወስዶብኛል አለኝ እና ስልክህ እንዴት ተረፈ አልኩት ኧረ በእጃ ይዤው ስለነበር ይሆናል አለኝ በቃ አትጨናነቅ ለማሚ ደውዬ እኛ ጋር እንድታርፍ እጠይቃታለው ከዛም ትንሽ ከሱ ገንጠል ብዬ ለማም ደወልኩ እናም ሁሉንም ስነግራት በጣም ደስ እያላት ይዤው እንድመጣ ነገረችኝ ከዛም ና አንድ ማረፊያ ተገኝቷል አልኩት የት ሲለኝ አይ እዚው ቅርብ ነው ዝም ብለህ ና ብዬ ባጃጅ መጠበቅ ጀመርን ከዛም ከመናሀሪያ እቤት ድረስ አንድ ባጃጅ አደረሰን ከምስጋና ጋር ከንዘቡን ሰጥቼ ላኩት ከዛም ለማርቲ ነግሬያት ስለነበር ወጥታ ደጅ እየጠበቀችን ነበር እና ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ወደ ቤት ገባን ከዛም ማም መጥተናል ስላት ከክችን ወጥታ አቤል እርሱ ነው ተዋወቂው አልኳት ባትይኝም እተዋወቀዋለው ይሄን የመሰለ ቆንጆ ከት አመጣሽ አለችኝ ኧረ እማ አልኳት እንደማፈር ብዬ ከዛ ተቀመጥ ከመንገድ ነው የመጣኸው ደክሞሀል አልችው ወደ ሶፍው እየጠቆመች እሺ ማዘር ብሎ ቁጭ አለና በአይኑ ጠራኝ እ አልኩት አጠገቡ ሄጄ አውቆ ፈገግ እያለ እዚህ እንደምንመጣ ለምን አልነገርሽኝም ብሎ አልኝ እና ወደ እህቴ እያየ ፈገግ አለ ከዛ እ አለኝ ቆጣ እያለ ኧረ አትጨናነቅ ልክ እንደ እቤትህ እየው አልኩት እና ማም ስትጠራኝ ማርቲ አጫውቺው ብያት ሄድኩ ከዛ እጁን አስታጥቢው የሚቀምሰው ነገር አዘጋጅቻለው አልችኝ እሽ ብዬ እጁን ላስታጥበው ስሄድ ማርቲናእቤል በጣም የረጅም ጊዜ ጓደኛማቾች ነው የሚመስሉት ማርቲ ታወራለች አቤል ይስቃል ከዛ በቃ ምንድነው ልጁን ልገይው ነው እንዴ አልኳት ከዛ ጓደኛሽ ደስ ይላል ወድጄዋለው አለችኝ ማርቲ ሲበዛ ፈጣጣ ናት እርስዋ ለምታወራው እኔን ሼም ይይዘኛል እሺ አሁን ይብላ እና እረፍት ያርግ አልኳት እና እኔ መች እጁን ያስኩት አለችኝ ከዛ በአይኔ ተይ የሚል ምልክት ሰጠዋት ማርቲ ቀልቃላና ቀበጥ ብቻ አይደለችም ምትፈልገውን ነገር በእጇ ካላስገባች በጣም ድርቅ ያለች ልጅ ናት በጣም ምትገርም ልጅ ናት እና መጣው ብላ ወጣች ከዛ ሳሎን እኔና አቤል ቀራን አንቺ ካልበላሽ ብቻዬን አልበላም አለኝ ከዛ እሺ ብዬ አብሬው ቁጭ አልኩ የቀረበውን እየበላን ልክ የሆነ ሰአት ላይ ሊያጎርስኝ ሲል...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 9 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@geyone
👉👉👉👉@geyone
👉👉👉👉@geyone
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
🌹🍃🕊...ላያስችል አይሠጥም

ያየሺ ሠዉ በመላ ጨርቁን የጣለ
ተከትሎሺ መጣ ጓዙን ጠቀለለ
አንቺ የተወደድሺ ልብሺ የሚያበራ
ምነዉ ለመናገር ልቤ አንቺን ፈራ
ጠዋትና ማታ ከደጂሺ ለይ ብገኚ
ለመናር ብየ አፌ የሚከዳኚ
አጠገብሽ ስደርስ ቃሉ የሚጠፍኚ
ሌላ ምንም አይደል ወድጄሺ ነዉ እንጂ
ባይኔ የምሼኝሺ ስትመጪ ስትሔጂ
እንዲሁ የማይሺ ስትመጪ ስትሔጂ
እናም ይሔን ሁሉ የነገርኩሽ ለታ
ያንቺ ልብ ባሰቺ ከኔ ልብ ደስታ
ላያስቺል አይሰጥም ለካ የኔ ጌታ።

💖⚘➣ Join ♥️💍
@geyone
@geyone
••●🍃🌹🍃●••
‍ ​​⊶⊷⊶⊷❍ የእብደት ሚስጥሬ ❍⊶⊷⊶⊷


ፍቅሬን በቃላቶች ~ ደርድሬ ባልገልፀው
የኔ ነሽ የምልሽ ~ ያንቺ ነኝ የምለው
ድምፅሽ መዳኒቴ ~ የህይወት እጣዬ
አካልሽ ጉልበቴ ~ የስኬት ማማዬ
ሌላ ማንም የለም ~ ባንቺ ነው ማማሬ
እውነት እልሻለሁ ~ የእብደት ሚስጥሬ

❤️ ❤️
@geyone
━━━━✦🌹
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_9

...🖊ልክ የሆነ ሰአት ላይ ሊያጓርሰኝ ሲል ማርቲ ገብታ ኧረ ጨረሽበት አለችኝ ከዛ እንደማፈር ብዬ አንገቴን አቀረቀርኩ አቤል ለኔ ያነሳውን ጉርሻ እራሱ ጎረሰው የሆነ ሼም ሳይዘው አይቀርም በልተን እንደጨረስን ማም ቡና አፍልታ እስከማታ እየተጫወትን አመሸን ከዛም የት ይደር የሚለው አከራካሪ ሆነ ማርታ እኔ ክፍል ስትል ማም ቃል ክፍል አቤል ሶፋ ላይ በማለት ብዙ ተከራከርን በመጨረሻ ደረቋ ማርታ እርሷ ክፍል እንዲተኛ አሳመነች እኔ የትም ቢተኛ ችግር የለብኝም ዋናው እርሱን ይመቸው እንጂ ከዛ ማርቲ ከማም ጋር አንድ ላይ ማም ክፍል ተኙ እኔ ክፍሌ ተኛው እና ዝም ብዬ facebook ላይ ገባው አማን online ላይ ነበር hi እለኝ እኔም ሰላም ካልኩት በኃላ ወሬ ጀመርን እና ድሬ ለስራ እንደሚመጣ እና በዛው እንደምንገናኝ ነግሮኝ ተሰነባብተን ስልኬን ዘግቼ በጀርባዬ ጋደም አልኩ እና የአማን መምጣት ብዙም ደስ ባይለኝም ትንሽ ቀን ስላልተገናኘን ናፍቆኝም ነበር እና እንዲህ እንዲህ እያልኩ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ከዛ ጠዋት ማም መጥታ ቃል ኧረ ተነሽ አመሸሽው እኮ አለችኝ እየሳቀች እማ ትንሽ ብቻ 5 ደቂቃ አልኳት ደግሞ እህትሽ ጓደኛሽን ይዛ ኮብልላለች ስትለኝ ተስፈጥሬ ተነስቼ የት አልኳት እኔንጃ መጣን ብላ ነው ይዛው የወጣችው አለችኝ የት ይሄዳሉ እዚው ቅርብ ነው ሚሆኑት አለችኝ እሺ ብዬ አልጋዬን አንጥፌ ማም ቁርስ እስክትሰራ እኔ ቤቱን ፏ አርጌ ጠበኳቸው እነ ማርቲ ግን አልመጡም መጠበቁ ሲሰለቸን እኛ በቃ እንብላ አልኳት እሷም ትንሽ እጠብቃቸው ስትለኝ ቆይ እሺ በቃ ልደውውልላቸው ብዬ ለአቤል ስደውል ስልኩን እቤት ትቶት ነው የሄደው ከማርቲ ክፍል ሲጠራ ይሰማል ማርቲ ጋር ስደውል ደግሞ አታነሳም በጣም ተናድጄ እማ አሁን ካልበላሽ ከዚህ በኃላ አልበላም ስላት እያቅማማች እሺ አለች ከዛ ወደ 6:15 አካባቢ አቤል እና ማርቲ መጡ ስልኳን ስላላነሳችልኝ ተናድጄ ለምንድነው ስልክሽን ማታነሽው አልኳት እንደመቆጣት ብዬ እሷ ግን ቀለል አርጋው ደውለሽ ነበር እንዴ አላየውትም አለችኝ ይበልጥ ማላገጥዋ እያናደደኝ እንግዳውን ይዘሽው ሄደሽ ነው አልኳት ማ አቤሌን ነው እንግዳ በቃ እሱ እኮ ቤተኛ ሆኖዋል አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው እንዲህ ምታናግሪኝ አለችኝ እኔም ለራሴ ግራ ገብቶኛል ከዛ ለማስቀየስ ያክል ትላንት ደክሞት መጥቶ በስርሀቱ እንኳን ሳይተኛ የትበለሊት ይዘሽው ትዞሪያለሽ አልኳት እሷም ኧረ ተረጋጊ ሲነሳ ነው የወጣነው ደግሞ ቦታ ላሳየው ነበር አለችኝ ይሄ ሁሉ ሲፈጠር ግን አቤል ዝም ብሎ ነበር የሚያየን በመጨረሻም በቃ አትጨቃጨቁ ይሄ ሁሉ በእኔ ምክንያት ነው አለ እኔም በራሴ አፈርኩ በእርሱ ፊት እንዲህ መሆን አልነበረብኝም ከዛ ማም መጥታ መጣችው ልጆቼ ግቡ ወደቤት ብላ አስገባችን ከዛም ማም እና ማርቲ ምሳ ለማዘጋጀት ክችን ገቡ ትንሽ ቆይቶ ስልኬ ንዝር አረገኝ እየተደወለ ነበር አማን ነበር የደወለው አንሳውት ሄሎ አማን አልኩት አማን ስል አቤል የደነገጠ ይመስል ነበር ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ አቤል እኔ የለውም የሚል ምልክት በእጁ አሳየኝ ለምን እንዲህ እንዳለ ባይገባኝም እሺ አልኩት ትንሽ ካወራን በኃላ ከአቤል ጋር አውርታችው ታቃላቹ አግንቼው አላውቅም አለኝ ከዛ አቤል ያለኝን እረስቼ እቤልማ እኮ....

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 10 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

♥️አስተማሪ የፍቅር ታሪክ♥️

#ክፍል\_10
...🖊አቤል ያለኝን እረስቼ አቤልምማ እኮ ብዬ ገና ሳልጨርሰው አቤል ከመቀስፈት መጥቶ አፌን ያዘኝ አፌን የያዘኝ በጣም ተጠግቶኝ ነበር አይኖቼ ከአይኖቹ ጋር አረፉ አቤል በጣም እየተመለከተኝ ነበር የሆነ የሚስለኝ ነበር ሚመስለው ላየው ሰው ግን አሁን ይበልጥ እየተጠጋኝ እንደሆነ ይታወቀኛል ሰውነቴ እየነዛዘረኝ ነው ከዛ አፍንጫዬን በስሱ ሲስመኝ አይኖቼ ሲከደኑ ይታወቀኛል የምሆነውን በሙሉ ከእኔ ቁጥጥር ውጭ ነው ከዛም ቀስ ብሎ ከአጠገቤ ተነስቶ ቦታው ተቀመጠ እና አይኖቼን ቀስ አርጌ ገለጥኳቸው እና ከኔ ፊት ለፊት ተቀምጦ ፈገግ ይላል ከዛ ስልኩን ዘጋውት አማን በድጋሚ ደወለ እና ትንሽ እንደማመንታት ብዬ አነሳውት እና አንቺ ምን ዋጠሽ ገሮሮዬን እኮ እፈልገዋለው አለኝ ከዛ በጣም ይቅርታ አማንዬ ኔቶርክ ትንሽ እያስችገረ ስለሆነ ነው ስለው አቤል ከት ብሎ ሳቀ ድምፁ እንዳይሰማ ብዬ ወደ ውጭ ወጣው ቢሆንም አማን በትንሽውም ቢሆን ድምፁን ሰምቶ ነበር ከዛ ማነው እንዲ ድዱ እስኪታይ የሚስቀው ብሎ ሲጠይቀኝ አይ የጎረቤት ልጅ ነው አልኩት ብዙም ግድ አልሰጠውም ነበር እና ፈልገኸኝ ነበር ስለው ምን ባክሽ ስራዬ ሊያቆየኝ ስለሚችል እቤት እንድፈልጊልኝ ነበር አለኝ እሺ ከተገኘ ችግር የለውም ብዬ ተሰነባብተን ዘጋውት እቤት ስገባ ምሳ ቀርቦ ነበር እጄን ለቅለቅ ብዬ ተቀላቅያቸው በልተን ከጨረስን በኃላ ማም ቡና አፍልታ እየተጫወትን ሳለ ትዙ ደወለች ወዬ ትዙዬ አልኳት የት ነሽ አለችኝ እቤት ስላት ባክሽ ውጪ ከመቅዲ ጋር እየጠበቅንሽ ነው በርጋ አልችኝ መጣው ብያት ስልኩን ዘጋውት ትዙና መቅዲ የሰፈር ጎደኞቼ ናቸው ማም ደግሞ የት ልትሄጂ ነው አለችኝ አይ እነ ትዙ በር ላይ ናቸው አይቻቸው መጣው አለኳት እሺ ቶሎ ተመለሽ እንግዳ አለ አለችኝ እሺ ብዬ ወጣው ትዙ አንቺ ግን አለሽ አልኳት ተጠፍፍተን ስለነበር መች ፈለግሽኝ እና አለችኝ አልሰማሽም እንዴ ስላት የሆነ ትልቅ ነገር ምነግራት መስልዋት ሰፍ ብላ ምን ስትለኝ በየቦታው አፍልጉኝ ፎቶሽን መለጠፌ ስላት ሂ ወረኛ ብላ በስሱ መታችኝ እና መቅዲ ስላት ምን አለችኝ ትንሽ የደበራት ትመስል ነበር ምነው አልኳት ምንም ምነው አለችኝ የውሸት ፈገግታ እያሳየችኝ ከዛ ትዙ እቤት ተፈለጋ መጣው ብላን ባለንበት ጥላን ሄደች ከዛ መቅዲ የሆነ ነገር አለ ንገሪኝ ብዬ ጎተጎትኳት ከዛ ታሪኩ እረጅም ነው ግን እያሳጠርኩ ልነግርሽ እሞክራለው አለችኝ
ችግር የለም ንገሪኝ አልኳት ወክ እያረግን እንድትነግረኝ ነግሬያት በዝግታ እየተራመድን ወሬዋን ጀመረች ከዛ በፊት ግን መቅዲ የ 4ተኛ አመት የዶክትሬት ተማሪ ነች እና ታሪኩን እንዲህ ብላ ጀመረች...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 11 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡vote ስታደርጉ ለኛም ብርታት ነው🙏

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
እንኳን ለናታቸን ለእመቤታችን ማርያም አመታዊ ብዓል አደረሳችሁ



እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕተ ንጹሃን ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ታላቅ አመታዊ በዓል ( ለአስተርእዮ ማርያም) በሰላም በጤና አደረሳችሁ:: አደረሰን!


🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏