🔆ራስህን በማንበብ ውስጥህን አጽዳ፣ ሠላምህን ተጎናጸፍ፣ ደስታህን ተቀዳጅ!
(እ.ብ.ይ.)
⚜ወዳጄ ሆይ…. ራስን ከማንበብ በላይ አዋቂነት የለም፡፡ ራስን፣ ውስጥን፣ ስሜትን፣ መንፈስን፣ ነፍስያን፣ ደመነፍስን፣ ልቦናን፣ ዝንባሌን፣ ፍላጎትን፣ ፍርሃትን የማወቅ ከፍታ የከፍታዎች ሁሉ ታላቁ ከፍታ ነው፡፡
〽️ራስን ማወቅ የሚጀመረው ራስን ከማንበብ ነው፡፡ ብዙዎች መጽሐፍ ያነባሉ፣ የሠዎችን ተሞክሮ ይኮርጃሉ፣ ዕውቀታቸውን ይጋራሉ፡፡ ይሄ በራሱ ታላቅ ነገር ነው፡፡ ከሁሉ ከሁሉ ግን ራስን አንብቦ፣ ራስን መርምሮ፣ ራስ ላይ ጥናት አድርጎ ራስን አብጠርጥሮ ማወቅ እጅግ ይልቃል፣ ይረቅቃል፣ ይጠልቃል፣ ይበልጣል፡፡ በዚህም ምክንያት በራሳችን ላይ በሚኖረን ዕውቀት የሌሎችን ተሞክሮና ዕውቀት እንዴትና መቼ ከእኛ መንፈስ ጋር ማጋባትና ማዋሃድ፣ መዋጀትና ማቀናጀት እንደምንችል ብልሃት ይፈጥርልናል፡፡
💎ለዚህ ነው ሶቅራጦስ በግሪክ ደልፊን ቤተመቅደስ ላይ ‹‹ራስህን ዕወቅ (Know thyself)›› የሚለውን ታላቅ ምክር ሠቅሎ የነበረው፡፡ ራስን ማወቅ ሌሎችንም ለማወቅ መሠረት ነው፡፡ ራስን ማንበብ ዓለሙን ለማንበብ ሀሁ ነው፡፡ አልያ ራሱን ሳያነብ ሌላውን የሚያነብ ጊዜያዊ ሸምዳጅ እንጂ በሕይወቱ ሙሉ ተጠቃሚ የሚሆን አንባቢ አይሆንም፡፡
🔆ወዳጄ ያለህን ገንዘብ ከአንተ በላይ ላሉ ሠዎች በማሣየት የምትሞክር ከሆነ ሠዎቹ ይንቁሃል፣ ይሣለቁብሃል፡፡ ከአንተ በታች ላሉ ሠዎች የምታሣይ ከሆነ ደግሞ ይቀኑብሃል እንጂ የምታተርፈው ነገር የለም፡፡ ከፍ ያለ ገንዘብ ብቻውን የትም አያደርስህም፡፡ በእያንዳንዱ ሠው መካከል እኩል መንሣፈፍ የምትችለው ክፍትና ንፁህ ልብ ካለህ ብቻ ነው፡፡ ይሄንን ንፁህ ልቦና፣ በጎ ህሊና፣ ቅዱስ መንፈስ የምታገኘው ራስህን በጥልቀትና በርቅቀት አንብበህና ተረድተህ ስታውቅ ብቻ ነው፡፡
🌊ብዙዎቻችን ኑሯችን የችኮላ፣ ስሜታችን የደመነፍስ፣ ሩጫችን የፉክክር፣ ህይወታችን ጣዕም ያጣና እርካታ የሌለው የሚሆነው እውነተኛ ፍላጎታችንን፣ ዝንባሌያችንን፣ ውስጣዊ ፈቃዳችንን፣ ነፍስያችንን፣ ልቦናችንን ጥለን በስሜታችን ስንመራ፣ በደመነፍስ ስንጓዝ ነው፡፡ ራሳችንን በጥልቀት አለማወቃችን ለድንግዝግዝ ሕይወት፣ ለፈራ ተባ ኑሮ፣ ለአስፈሪ ተስፋ ዳርጎናል፡፡ ደስታችን የሠከንድ የሚሆነው፣ ሐዘናችን፣ ፀፀታችን፣ ቁጭታችን ደግሞ ለብዙ ዘመን የሚረዝመው ውስጣችንን ባለማግኘታችንና ደስታን፣ ሠላምን፣ ፍቅርን፣ ተቀባይነትን የምንፈልገው ከውስጣችን ሳይሆን ከውጪው ዓለም በመሆኑ ነው፡፡ ደስታ፣ ፍቅር፣ ሠላም፣ እርካታ፣ ወዘተ እኮ ከልባችን የሚቀዱ፣ ከነፍሳችን የሚፈልቁ፣ በመንፈሳችን የሚባረኩ፣ በውስጣችን ሞልተው የሚፈሱ እንጂ ከውጪው ዓለም ቁሳዊ ዝባዝንኬ የምናገኛቸው አይደለም፡፡ ቁሳዊ ደስታ ከመንፈሳዊው ፍስሃ በኋላ የሚመጣ እንጂ የሚቀድም አይደለም፡፡
⚜ወዳጄ ሆይ… ራስህን አንብበህ፣ ሕሊናህን አጥንተህ፣ ውስጠትህን አውቀህ፣ የልቦናህን ውቅር አስተካክለህ ከልብህ የፈለቀ ነገር ስራ፡፡ ያንን ስታደርግ እርካታ የለሽ አትሆንም፡፡ አትቀናም፡፡ የሌሎችን ንብረት አትመኝም፡፡ ተስፋህ እውን ይሆናል፤ መንገድህ ያምራል፣ መድረሻህ ጥርት ብሎ ይታይሃል፤ በተቃራኒው ተመልሶ ወዳንተ በሚመጣ ነገር ትጥለቀለቃለህ፡፡
🔱ወዳጄ ሆይ… እውነተኛ ሠላም የሚመጣው ከውስጥህ ነው፡፡ ይሄ ሠላም በውጫዊ ሁኔታዎች ላይ ጥገኛ አይደለም፡፡ ውስጣዊ ሠላም አዕምሮን ለትንሽ ጊዜ በፀጥታና በሠላማዊ ዕረፍት በማረጋጋት ሃሳባችንን በሙሉ በቁጥጥር ስር የምናደርግበት ድንቅ ቆይታ ነው፡፡ ታዲያ ይሄ ሁሉ የእውቀት ከፍታ፣ የመንፈስ ርቅቀት፣ የጥበብ ጥልቀት ዕውን የሚሆነው ራስህን በደንብ አንብበህ ራስህን በጥልቀት ማወቅ ስትችል ብቻ ነው፡፡
🌊ራስህን በማንበብ ውስጥህን አጽዳ፡፡ አጽድተህም ልቦናህን በተሻለ ሃሳብ ገንባ፡፡ ሕሊናህን በመልካምና በቅን አመለካከት አትጋው፡፡ አዕምሮህን የግል ሠራተኛህ አድርገው፡፡ ህሊናህን ባሪያህ ካደረግክ ስትፈልግ የምታበራውና የምታጠፋው በአንተ ቁጥጥር ስር ያለ ባልቦላህ ይሆናል፡፡ ስትፈልግ የምትጠቀምበት፤ ማሠብ ባልፈለግክ ጊዜ ደግሞ ልታጠፋ የምትችልበትን ችሎታ ትጎናፀፋለህ፡፡
ራስህን በማንበብ እወቅና ውስጥህን አጽዳ፣ ሠላምህን ተጎናጸፍ፣ ደስታህን ተቀዳጅ! ከዚህ በላይ ስኬት ምንም ነገር የለምና!
✍ እሸቱ ብሩ ይትባረክ
መልካም ምሽት❤️
🌊🔆🌊🔆🌊🔆🌊🔆🌊🔆🌊🔆🌊❄️
https://telegram.me/geyone

Forwarded from የልቤ ትርታ
💌💌ተመልሼ ተውኩት💌💌
ፅፌልሽ ነበረ ሁለት ወረቀት፣ አንዱም የፍቅር ነው አንዱም ይናፍቆት፣
ይናፍቆት መንስዔው ጊዜ ነው ይሉኛል ፣
እኔ በበኩሌ ፍቅር ይመስለኛል
ብዬ ልፅፍልሽ ብዕሬን አንስቼ ፣
ተመልሼ ተውኩት ምላሹን ፈርቼ።።
💌💌👇👇👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
💌💌💌💌💌💌

እማየውን እንጅ እምሰማውን ኣላምንም
------------
አርትን ከኔ በላይ ጠለቅ ብለው እሚያውቁ እንዳሉ ባውቅም የሚኖሯት ግን ጥቂቶች መሆናቸውን አውቃለሁ እኔ ግን ከማየው ተነስቸ ትንሽ ነገር ልበል አሁን ካለው የሃገራችን አንፃራዊ ሁኔታ ተነስቸ ሚዛናዊ በሆነ እይታ "የአገር ልጅ የማር እጅ" በሚል የተጀመረውን እርዳታ መሰብሰብ አልደግፍም/አላምንበትም።
እኔ በተፈጥሮየ የማየውን እንጅ የምሰማውን አላምንም ከዚህ ተነስቸ ደግሞ እርዳታ ለመርዳት ምክንያታዊ ሆኘ ስናገርና እውነት ኣርትን ሃብታችን ለምንለው ህዝባችን ለመድረስና ድጋፍ ለማድረግ እረፍዶብናል።
እኔ ዛሬ ተነስቸ ትግራያዊት ስለሆንኩ ወይም በሌላ ምክንያት በትግራይ ለተፈናቀሉ እርዳታ ለመጠየቅ ሞራሉ የለኝም ምክንያቱም በኢትዮጲያ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ አንፃራዊ ሰላም አልነበረም በዚህም ምክንያት
ዛሬ ለተከሰተው ችግር እጀን ከመዘርጋቴ በፊት ከአሁን በፊት ልዘረጋላቸው የሚገባኝ ንፁሃን ነበሩ
____
፩-በሻሸመኔ ቤተሰቦቻቸውን ላጡና ንብረታቸው ወድሞና ጥለው ለተሰደዱ መድረስ ነበረብኝ
፪-በጉራፈርዳ ቤተሰቦቻቸውን ላጡና ንብረታቸው ወድሞና ጥለው ለተሰደዱ መድረስ ነበረብኝ
፫-በቤኒሻንጉል ዛሬም ድረስ መፍትሄ አልባ ለሆነውና
ቤተሰቦቻቸውን ላጡና ንብረታቸው ወድሞና ጥለው ለተሰደዱ መድረስ ነበረብኝ
፬-በኮንሶ በተመሳሳይ ሁኔታ ቤተሰቦቻቸውን ላጡና ንብረታቸው ወድሞና ጥለው ለተሰደዱ መድረስ ነበረብኝ
፭-በማይካድራ በቅርብ ለሆነው ነገር ቤተሰቦቻቸውን ላጡና ንብረታቸው ወድሞና ጥለው ለተሰደዱ መድረስ ነበረብኝ
ይህን እንኳ ማድረግ ባንችል ለትምህርት እንደወጡ የቀሩትን ሴት እህቶቻችን የት ደረሱ ብለን ለመጠየቅ ያልደፈርን እኛ አሁን ብንጮህ ትርጉም ያጣብናል።
በተቀደደልን ቦይ አብረን እምንፈስ ከሆነ ሃብታችን እምንለውን ህዝብ ጋ አብረን መቀጠላችን ጥያቄ ውስጥ ከመውደቁ በተጨማሪ ኣርትም ቁማር ይሆናል።
*** እ ረ ፍ ዶ ብ ና ል ***

💚💚💚💚
💛💛💛💛💛💛
ሰላም እዴት አደርሽ ኢትየጵያን
♥️♥️♥️♥️♥️♥️♥️
🙏🙏Join
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
💛💛💛💛💛💛
ሰላም እዴት አደርሽ ኢትየጵያን
♥️♥️♥️♥️♥️♥️♥️
🙏🙏Join
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
Min Atefahu (ምን አጠፋሁ) 1995 E.C.
Tibebu Workiye
Join Us _oldies_music
══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══
══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══