የልቤ ትርታ
203 subscribers
473 photos
4 videos
10 files
422 links
Download Telegram
​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል_8
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄


ዮሚፍ አለችኝ አቤት ብዬ ዞር አልኩ እህቷ ድንግጥ አለች ዮሚፍ እሱ ነው
አለች አዋ እሱ እኮ ነው አለቻት
በጣም ደስ ይላል አለች ምኑ አልኳት አይ ሰለረዳሃት አለችኝ እረ ግድ የለም
አልኳትኝና ወደ ቤት ሄድኩኝ
የገረመኝ ባህሪያቸው ተመሳሳይ ነው ሁለቶችም ረጋ ያሉ ናቸው በቃ ለሰከንድ
ትረሀስን ከእቅፏ አታወጣትም
እንደዚህች አይነት እህትም አለች ያስብላል በዚህ
መሀል ወይኗ ደወለችልኝ ለምንድነው ማታመጣው አለችኝ መጥቻለው እኮ
አላየሽኝም አልኳት መቼ ምናምን ቀባጣረች እኔምልሽ ነይ እንጂ ቅበሪያት
ገድለሻት የለ እልኳት ስልኩን ጆሮዬ ላይ ዘጋችው
ወይኗ ማለት እስስት ናት እኔ ጋር እንዴት ጓደኛ እንደ ሆነች ራሱ አላውቀውም
ብዙን ግዜ ክፋቷን ጓደኞቿ ሲነግሩኝ እንዴት እንደዚህ ታደርጊያለሽ ከማለት
ውጪ
ምንም ነገር ብያት አላውቅም እዛኔ ዝም በማለቴ ግን
ዛሬ በምወዳት ልጅ ላይ ስራዋ ደረሰ ለካስ ዝምታም ያስቀጣል ይበለኝ
የስራዬን ነው ያገኘው
ትረሀስ ከበፊቱ በጣም እየተሻላት ነው ጋሼ ሚሉት ዘመዳቸው ለነትረሀስ
ከቤት ዕቃ ውሰድላቸው እኔም መጣሁ አለኝ እሺ ብዬ የተቋጠረ ነው ይዤው
ሄድኩኝ በዬት እንደ መጣ ባለውቅም መንገድ ላይ ደረሰብኝ ጋሼ
ግርማሞገሱ ብቻ ያስፈራል እዛ እንደ ደረስን ጋሼ ትረሀስ ጋር ቁጭ አለ እኔና
የትረሀስ እህት እንድን ርቅለት
በእጁ ምልክት ሰጠን እኛም ቶሎ እጥፍ አልን የሚገርመው እህቷን ሳወራ
ትረሀስን የማናግራት ነው የሚመስለኝ ሁሉ ነገራቸው አንድ ነው ተጫዋች
ናት በመሀል እያወራን እያለ ስለ ቤተሰብ አንስተን እያወራን
እናታቸው በህይወት እንደ ሌለች ነገርችን ግን ያው እንደ እናት የሚያዩዋት
የእናታቸው ጓደኛ እንዳለች ነገረችኝ እኔም ለምን ይቅርብኝ ብዬ እዚህ አጎቶቼ
እንዳሉ አ/አ እህቶቼ ወንድሞቼ አንዳሉ እናቴ ግን የት አንዳለች አንደ
ማላውቅ ነገርኳት እናቴ የት እንዳለች አለማወቄ ገረማት
ሁሉንም ነገር ነገርኳት አባቴ ወታደር እንደ ነበር እናቴ ጋር ግን እኛ ህፃን እያለን
አንደ ተፋቱ እና ከቤት እንዳባረራት ብቻ ብዙ ነው ታሪኩ አልኳት ለምን
ያለችበትን አታፈላልጓትም አለች በርግጥ ያልደረስንበት ቦታ የለም አጣናት
አባታችን ብቻ ነው የት እንዳለች የሚያውቀው እሱን እናታችን የት
እንዳለች መጠየቅ ማለት ቤት ውስጥ ጦርነት ማወጅ ነው ያ ስለሆነ ማንም
አያነሳበትም ፈጣሪ በፈቀደ ቀን ትገናኛላቹ አለች አሜን ያድርግልን አልኩኝ
ስልክ ተደውሎላት ልታናግር ትንሽ ራቅ አለች እኔ ባለሁበት ቁጭ አልኩ
ከትንሽ ደቂቃዋች በኋላ መጣች እመዬ ደውላልኝ እኮ ነው አለች የእናትሽ
ጓደኛ አልኳት አዋ ብላ ሳቀች ቆይ ላሳይህ ብላ ከሞባይሏ ላይ ፈልጋ ይህቺ
ናት አመዬ ማለት ብላ
ስልኩን ሰጠችኝ ያየሁት ነገር ማመን አቃተኝ…


#ክፍል ዘጠኝ ይቀጥላል ...
#ሼር ላይክ አትርሱ 🙏


​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 የፍቅር ቤት🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺̶̥✽̶┄┄

https://telegram.me/geyone
​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል_9
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄


ይህቺ ናት አመዬ ማለት ብላ
ስልኩን ሰጠችኝ ያየሁት ነገር ማመን አቃተኝ ሰንት አመት ፈልገን ያጣናት
እናቴ ነች እንዳልጨው አፌን ያዘኝ በቃ ውስጤ ውጥርጥር አለ ታቃተለህ
እንዴ አለችኝ ዘልዬ አንገቷ ላይ ተጠመጠምኩባት በቃ በደስታ እንባ ታጠብኩ
ነገሩ አልገባትም ነበር ዋሌቴን አውጥቼ የእናቴን ፎቶ አሳየኋት ያየችው ነገር
ግራ አጋባት ከእኔ በላይ ተደሰተች እናትህ እኮ ግን ለዘመናት ብቻዋን ነው
ስታለቅስ የኖረችው አለችኝ አንጀቴን በላችኝ ግን እኮ
ግን ምን አልኳት እናት በአሁን ሰአት የራሷ ኑሮ እየኖረች ነው አለችኝ በርግጥ
ስለእናቴ የማውቀው ነገር የለኝም
እስቲ ምታውቂውን ነገሪኝ አልኳት በቃ ምኑን እነግርሀለው አንተ የነገረከኝ
ታሪክ እኮ ነው አባት ከቤት እንዳባረራት አባቷ ወደ ውጭ ሀገር እንደወጣች
ነገረችኝ
አባትህ በዚህ ምክንያት ለብዙ ዘመን ብቻውን ቤተ ዘግቶ እንዳለቀሰ እዛም
ሂዳ ትደውልለት ስለነበረ አባታቹ ከባድ ሀዘን ውስጥ ነው የእናትህ አባት እዛ
ውጭ ሀገር ለአንድ ባለፀጋ ነበር የዳራት እናቴ ጋር በጣም ጓደኛ ነበሩ ሁሌም
ስለናተ ታስብ ነበረ አባታቹም እሷ ካገባች በኋላ ምን ብዬ ነው ልጆቼን እናታቹ
አግብታለች ብዬ ምነግራቸው ብሎ ለብዙ አመት ብቻውን እንዳለቀስ አንድ
በአንድ ነገረችኝ የምሰማው ነገር በጣም ግራ ገባኝ በቃ ተምታታብኝ
አባታችንን
ስንወቅሰው ነው የኖርነ ለካስ እውነቱ ይሄ ሰለሆነ ነው ስሟ ሲነሳ
የማይወደው ሁሉም ነገር ግራ ሆነብኝ እናቴ በህይወት እንዳለች ሳውቅ
ለመጀመሪያ ግዜ ልቤ በእናቴ ደስ አለው እህትና ወንድሞቼ ስለ እናቴ
ሚሰማቸውን ያወራሉ እኔ ግን ሙታለች ብዬ ነበር
በዚህ መሀል ጋሼ ደወለልን ስንሄድ ትረሀስ ጋር ወደ እኛ እየመጡ ነበር ጋሼ
ዮሚፍ እኔና አንተ ወደ ቤት እንሂድና ዕቃ ይዘህላቸው ትመለሳለህ አለኝ እሺ
ስለው እሙቲ ደግሞ የምትቀባውን እምነት አምጪላት አለ ስሟን ራሱ
አላውቀውም ነበር እኔ አብሬህ ልሂድ ከቤት የማመጣው ዕቃ አለኝ አለች እሺ
በቃ አንተ ቆይ ብሎን ሄድነ
እምነቱን ይዤላት መጣሁ ወደ ሜዳው እንሂድ አለችኝና ተያይዘን ሄድን ዮሚፍ
አንድ ያልነገርኩህ ነገር አለ ስለ እህቴ አለችኝ ምነበር እልኳት ሰላንተ በፊት
ነግሪያት ነበር እና ዛሬ ስላገኘችህ በጣም ደስ ብሏታል ወሬዋ ምንም
አልጥመኝ አለ አዋ እህትሽ ጥሩ ልጅ ናት ደስ ምትል እህት አለሽ አልኳት አዋ
ባንተ ወጣ እኮ ነው ብላ ተሳሳቅነ እና ምን ልልህ ፈልጌ ነበረ እህቴ…



#ይቀጥላል ክፍል አስር ከ 100በኃላ
#ሼር ቮት ማድረግ አይርሱ



​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 የፍቅር ቤት 🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺̶̥✽̶┄┄
ለሰንበታችን!
💚

እንደ ሰው ለመኖር ሁለት መንገዶች ብቻ አሉን
ስላሉን ነገሮች በሙሉ አመስጋኞች በመሆን ምስጋናችንን ለፈጣሪ በማቅረብ በምስጋና
ሕይወት መኖር
ወይም የሌሉንን ነገሮች በማሰብና ያሉንን ነገሮች ዝቅ አድርጎ በመመልከት የቅናት
ሕይወት መምራት።

መልካም እለተ ሰንበት
​​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል_10
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄


አዋ እህትሽ ጥሩ ልጅ ናት ደስ ምትል እህት አለሽ አልኳት አዋ ባንተ ወጣ እኮ
ነው ብላ ተሳሳቅነ እና ምን ልልህ ፈልጌ ነበረ እህቴ ላንተ ያላት አመለካከት
በጣም
የተለየ ነው አባክህን እንዳትጎዳት አለችኝ አልገባኝም
ምን ለማለት ፈልገሽ ነው አልኳት ዮሚ ተረዳኝ እንጂ ለምን እንዳልገባህ
ትሆናለህ ምንም እኮ የተካበደ ነገር የለውም አለችኝ እንደ እሷ አባባል እኮ
እህቴ ወዳሀለች እያለችኝ ነው ምን አይነት ጣጣ ነው የገባሁ አምላኬ
እኔ ግን መቼ ይሆን የፈለኩትን የማገኝ አልኩ በልቤ
ትረሀስን መወድድ ብቻ አይደለም በፍቅሯ ወድቄላታለሁ
በዚህ መሀል እንደዚህ አይነት ነገር መፈጠሩ እጅግ በጣም አዘንኩ ትረሀስ
በእህቷ አትደራደርም እህቷም ልክ እንደሷ እንደዛ ካለችኝ በኋላ ቅስሜን
ሰበረችው መሰለኝ ዝም አልኩኝ ተጨዋት እንጂ ምነው ዝም አልክ አለችኝ እ
…ብዬ ፈገግ አልኩ ውስጤ ምስቅልቅሉ ወጧል ከሰአታት በኋላ እህቷ
መጣች ቁጭ ብለን ነበር
ወደ እሷ ሄድነ ያልገባኝ ነገር ትረሀስ እና እህቷ በአይን የሚያውሩት ነገር አለ
ምንም አለገባኝ አለ ሲታያዩ በአይናቸው እንቅስቃሴ ብቻ ይግባባሉ የሆነ ነገር
እንዳል ገብቶኛል በዚህ መሀል አባቴ ደወለለኝና ከእነሱ ራቅ አልኩኝ ምንድ
ነው እስካሁን የቆየህ አለኝ ስለተመቸኝ ነው አልኩት በል በዚህ ሳምንት
እንድትመጣ አለኝ እረ አባቢ ፀበል ጀምሬ ነው አልኩኝ ደነገጠ ምን ሆንክ
አለኝ
ምንም አልሆንኩም ልጆች ጋር ልጠመቅ ብዬ ነው አልኩኝና ሽፍንፍን አደረኩ
በል እንደ ጨረስክ ቶሎ ና አለኝ እሺ ብዬ ስልኩን እንደ ዘጋሁ የትረሀስ እህት
ከኋላዬ ትክሻዬን ያዝ ስታደርገኝ ቀልቤን ነበር የገፈፈችው ወደ አ/አ ልሄድ
ነው አባቢ ናብሎኛል እልኳት በጣም ደነገጠች እህ እይሆንም አትሄድም
አለች ሁኔታዋ አሳቀኝ በዚህ መሀል አንድ የቆሎ ተማሪ አባ እየፈለገህ ነው
አለኝ እሺ ብዬ እሱ ጋር ሄድኩ እንደ ደረስኩ ሰው ጋር ነበሩ
ውጭ ጠበኳቸው አባ ማለት ሲበዛ ቅን እና ትሁት አባት ናቸው በጣም
የሚገርመው አባ
#የቤሩት_ሊባኖስ_ደብረ_ሲና_ቅዱስ_ገብርኤል_ካቴድርያል ነበር
የሚያገለግሉት ሁሉም በቃኝ የገጠር ቤተክርስትያንን ባስተዳድር ይሻለኛል
ብሎ ነው የመጡት
አባ እንደ ወጣ ሰላምታ ተለዋውጠን ያለችበትን ሁኔታ
ከጠየቀኝ በኋላ ወደ ወንቀሽት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም
እንድን ሄድ አዘዘን እኔም እሺ ብዬው ያለውን ነገር ለትረሀስ እህት አባ ያለኝን
ነገርኳት እሺ አለችኝና ወደ ትረሀስ ሄድነ መጀመርያ ላይ አባቴ ሲደውልልኝ
ነበር ላናግረው ብዬ የተለየኋት እንደ ሄድኩ ዮሚ አባትህ ምን አለህ አለች
በናትሽ ወደ አ/አ ልሄድ እኮ ነው ስላት …


#ይቀጥላል ክፍል አስራ አንድ
#ሼር ቮት ማድረግ አትርሱ


​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 የፍቅር ቤት🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺̶̥✽̶┄┄

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል_11
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄

ውዶቼ ድርሰቱ ተወዳጅነተን እንዳተረፈ እርግጥ ነው ከታች ሼር የምለውን በመንካት ሼር አድርጉልን ስንል በ ክብር እና በትህትና ነው🙏


መጀመርያ ላይ አባቴ ሲደውልልኝ ነበር ላናግረው ብዬ የተለየኋት እንደ ሄድኩ
ዮሚ አባትህ ምን አለህ አለች በናትሽ ወደ አ/አ ልሄድ እኮ ነው ስላት
ከተቀመጠችበት
ተስፈንጥራ ተነሳች አትሄድም አለች እህ ተይ እንጂ ቆንጅዬ ፋዙ እኮ ነው
የጠራኝ አልኳት አልሰማህም አለች
እኛ ተሳስቀን አባ ያለኝን ነገርኳት እሺ ግን ለምን እዛ እዚህ አይሻልም ነበር
አለች ውስጤ ፍረሀት ፍረሀት አለኝ አለች ሚያስፈራ ነገር የለውም እኮ ብዬ
እቅፍ አደርኳት ውስጧ እየስጨነቃት እንደ ሆነ ገባኝ ሶስት ቀን በኋላ ልንሄድ
ስንነሳ በቃ ሆዷዋን በጣም አመማት መቆም አቃታት በቃ ሲነኳት መጨሁ
እኔና ጋሼ
እንደምንም ተጋግዘን ወደ መንገድ አወጣናት እውነት ለመናገር በቃ ምትሞት
መስሎኝ ነበር አይኗ ግልብጥብጥ ብሏል ጨንቆኛል እህቷ ቤቲ ታለቅሳለች
እንደ ምንም ብለን #ወንቅሸት_ቅዱስ_ገብርኤል_ገዳም ደረስን እውነት
ለመናገር እኔ በህይወቴ ለመጀመሪያ
ግዜ ነው እንደዚህ አይነት ነገር የገጠመኝ ሰው ታሞ
ፀበል ሲገባ እሰማለሁ አንጂ ገብቼ አላቅም ወደ ገዳማትም ቢሆን ለክብረ
በአል ነው ብዙን ግዜ የምሄደው ለፀበል ሂጄ አላውቅም እዛ ያለው ህዝብ
ይሄ ነው ለማለት ይቸግራል የሰው ልጅ በህይወት ሲኖር
ትልቁ ፈተናው ሰው ነው ይባላል ግራ ይገባኝ ነበር
ፀበል ቦታ የሄደው ሰው እውነቱን ተረድቶ ይመጣል
በቅናት መንፈስ የገዛ ወንድሙን በመተት ደም የሚያሰተፋ ለእላቂ ገንዘብ
የሰውን ህይወት ሲያበላሹ
ለሰው ያስቀመጡት ወጥመድ የገዛ ለጃቸውን
አጥምዶባቸው አሳር መከራቸውን ሲያዩ ሁሉም የእጁን እንደሚያገኝ ያሰየናል
እኔ በውስጤ ሰለ ፈጣሪ ትዕግስት
የማስበው ልክ እንደ ሰማይ የተዘረጋ ነው በዚህ መሀል የማውቃቸው ጓደኞቼ
የአ/አ ልጆች አግቼ በጣም ደስ
አለኝ ብዙም ሳንቸገር እነሱ ቦታ ሰጡን ትረሀስ እህል በሁለተኛ ቀኗ ቀመሰች
በጣም አሳዘነችኝ በአንድ ሰው ምክንያት እንደዛ መሆኗ ውስጤ በጣም
ይወቅሰኛል ፀበል ቦታ ያገኘዋቸው ጓደኞቼ ትረሀስን ከእኔ በላይ ተንከባከቧት
በሳምንቱ ትንሽ ሲሻላት ወደ ተራራው ወጣን
ቤቲ ስልክ ላናግር ብላ ራቅ አለች ትረሀስ እኔ ላይ ተደግፋ እያወራን እያለ
አንተን እኮ ግን ማጣት አልነበረብኝም አለች ልዝዝ ባለ ድምፅ ምን አልሽኝ
አልኳት አንተ እኮ ጥሩ ሰው ነህ አለች መጀመርያ
ያለችውን ሰምቻለው ግን ባልሰማ አለፍኩ እ…አደል አልኳት ቤቲ መጣችና
ቁጭ አለች ፊቷ ልክ አይደለም ችግር አለ እንዴ አልኳት ትረሀስ ቶሎ
መመለስ እንዳለባት እሷ ምትሰራበት ድርጅት …



#ይቀጥላል ክፍል አስራ ሁለት
#ሼር እንደማታደርጉ ደርሶናል ሼር በተኑን ንኩልን 🙏



​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 የፍቅር ቤት 🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺̶̥✽̶┄┄

https://telegram.me/geyone
ሲፈጀኝ ይኖራል ልክ እንደሚጥሚጣ፣
እድሜሽ የወይዘሮ አመልሽ የሚጣ! 😔😁

@geyone
@geyone
@geyone
​​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል_12
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄

አባላትን ለማብዛት ማስታወቂያ እንዳበዛን ይገባናል ሳትሳላቹ እንድትከታተሉን እንጠይቃለን እንዲሁም ሼር ቮት አትርሱ



ትረሀስ ቶሎ መመለስ እንዳለባት እሷ ምትሰራበት ድርጅት በኢሜል
የተፈቀደላት ቀን እየተገባደደ እንደሆነ እና እንደ አሳወቋት ነገረችኝ ትረሀስ
አንገቷን አቀረቀረች እኔም በጣም ተሰማኝ ምን እንደ ሆነ ባላውቅም ነገሮቸ
ሁሉ ጠበቡኝ እንደምንም
ብዬ ተስፋ ሰጠኋት # ወይኔ_አምላኬ_እባክህ_እኔንም
#አበርታኝ_አልኩ_በልቤ እኔ ራሱ አቅም አጣሁ እንደ ምትሄድ ሳውቅ እሷ
ከእኔ ርቃ ምን ሊፈጠር እንደ ሚችል አውቃለሁ በዚህ መሀል ከሳምንት በኋላ
ቤቲ ወደ ተራራው ወጣ ነበር በጣም ደስ ብሏት መጣች
ምንድነው ደስታው አልኳት ምክንያቷን ተቀበሉ አለች የምን ምክንያት ስላት
ትረሀስ ለምትሰራበት ድርጅት በኢሜል ያለችበትን ችግር ትረሀስ አስመስላ
እንደ ፃፈች ነገረችኝ በጣም ደስ አለኝ በዚህ መሀል ግን ያልጠበኩት ነገር
መጣ ትረሀስ በሶስተኛው ሳምንት ላይ ልክ በገብርኤል ቀን ስብከት አልቆ
የደህነት ሰአት ላይ እንደ
ምንሜና አደረጋት እንዴት አድርገን ችለን እንያዛት በጣም ተወራጨች ለመጓዝ
አቅም ያጣች ልጅ እንደዛ ስትሆን ላየ ሰው ትንግርት ነው በቃ ጆሮዬ
ከመስማት አልፎ እኔንም አዙሮ ሊጠለኝ እስኪደርስ ለፈለፈች በቃ እንደ
ተደገመባት ወይኗ እንዳስደገመችባት በሚበላ ነገር እንዳሰጠቻት
በቃ እውነት ለመናገር ሰው መሆኔን ጠላሁ አንደዛ ሁና ተፈወሰች ተደግፋን
ምትሄድ ልጅ እንደ ፈለገች ዘለለች
አምላኬን አመሰገንኩ እኛም ሳምንት በኋላ ጨርሰን
ወጣን ልክ እንደ ደረስን ጋሼ ሲያየን ከደስታ ብዛት አለቀስ ከአንድ ወር በፊት
በጣም እንደ ታመመች አከባቢ ጋሼ ጋር ወደ እሷ እየሄድን ዮሚፍ ግን
ምትድን ይመስልሀል አለኝ እንዴ ጋሼ እንዴት እንደዛ ታስባልህ
ስለው እኔጃ ፈራሁ አለኝ እኔ እንደዛ ሲለኝ እንባዬን እንዴት ልቻለው ዛሬ ግን
ያሁሉ አልፎ ደግፈናት ያለፍንበትን ሜዳ ሮጠችበት # እያዳነ_ሄድ … አለ
ዘማሪው አልኩ በልቤ ቤተሰብ ዘንድ ሳምንት ቆየንና
እኔ ወደ አ/አ ልመለስ አልኳቸው በቃ ከእሷ መለዬትን
ባልፈልግም ግድ ሆነብኝ ትረሀስ ገና ተናግሬ ሳልጨርስ እንባዋ ይወርድ
ጀመር ወደ ሜዳ ብቻዋን ይዣት ወጣሁ ግን ምንም ልትረዳኝ አልቻለችም
ቆይ እኔ ያልገባኝ አሁን አንቺ እኮ ወር በኋላ ልትሄጂ
አይደል ደግሞ አ/አ ስትመጡ እንገናኛለን አልኳት
ቢሆንም ትላለች ይሄነው መልሷ እኔ እኮ ወንድ ልጅ
ጋር ብዙም ቅርርብ የለኝም ታድያ ለምን ውስጤ አንተን
ብቻ የለኛል ዮሚ እኔ እኮ ውስጤ ያለውን ስሜት እንዴት
አድርጌ ልንገርህ… በቃ ሲቃእየተናነቃት እንዴት አድርጋ ታውራኝ ሳልረዳሽ
ቀርቼ አይደለም ብዬ አቀፍኳት በዚህ መሀል እኔ እኮ አንተን ብላ ቀና ስትል
አይናችን አኩል ተጋጨን ከንፈሯ ይነቀጠቀጣል እኔም ተጠጋኋት እሷም
ተጠጋችኝ…



#ይቀጥላል ክፍል አስራ ሶስት ከ 100 ቡኃላ
#ሼር ላይክ አድርጉ

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል_13
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄



በመሀል እኔ እኮ አንተን ብላ ቀና ስትል አይናችን አኩል ተጋጨን ከንፈሯ
ይነቀጠቀጣል እኔም ተጠጋኋት እሷም ተጠጋችኝ እኔም በድፍረት ሳምኳት
ሰውነቴ እንዴት እንደነዘረኝ እኔ ነኝ የማውቀው ወይኗ ጋር ብዙ ነገር
አሳልፍያለሁ ግን ዛሬ ትረሀስን ስስም እንደ ሰጠኝ ስሜት
ጭራሽ ወይኗ ጋር እንደዚህ አይነት ነገር ተሰምቶኝ አያውቅም በቃ ልገልፀው
የማልችለው ደስታ ነበር
ውሰጤ ላይ በቃ እዛው ተያይዘን አንላቀቅ አልን
ለካስ ልጆች ገርሟቸው እያዩን ነበር ሳቃችንን እንዴት
እንቻለሁ ነገራችን ግራ ስለገባቸው እጃቸውን አፋቸው
ላይ ጭነው በግርምት ያዩን ነበር ትረሀስ አግሬ ላይ ተኝታ እያወራን በመሀል
ቤቲ መጣች እናተ ሳጠሩኝ አይደብራቹም አለች እና በዋትስ አፕ አንድ ሰው
ላስተዋውቅህ አለችኝ ደስ ይለኛል ግን ቺክ ብትሆን
የበለጠ ደስ ይለኛል ስል ትረሀስ አንተ ብላ በጥፊ መታችኝ ሁላችንም
ተሳሳቅን
ከትንሽ ደቂቃ በኋላ አግቼዋለሁ አናግረው እስኪ ስትል
እንዴ ወንድ ነው እንዴ እኔ ሰፍ ብዬ ስጠብቅ ስል ከቅድሙ የባሰ ሳቁ ትንሽ
ራቅ በልና አናግረው ብላ ስልኳን ስሰጠኝ እሺ ብዬ ተቀበልኩና ትንሽ ራቅ
አልኩ ሄሎ አለችኝ ቀልቤን ገፈፈችው ሳላም ነው እልኩኝ
በስማም አንተ አድገህ የለ ድምፀህ ራሱ ጎረነነ አለችኝ ታድያ የቀፊራ ግንብ
ነኝ ወይስ የአክሱም ሀውልት ነኝ ባለሁበት የምቀር አልኳት በቃ ከሳቋ የተነሳ
እንዴት ታናግረኝ በጣም ቀልደኛ ነህ እንተ እናትህን እንደዚህ ትላለህ ስትለኝ
በቃ ወገቤን የተያዝኩ ነው የመሰለኝ ከዬት መጣ ያላልኩት እንባዬ ሲፈስ
ይታወቀኛል እንዴት አድርጌ
ላውራት ሲቃ ተናነቀኝ በእናቴ እጅ አላደኩም ግን ለእናት
ያለኝ አመለካከት ላየ ሰው በእናት ፍቅር ያደኩ ነው የሚመስለው ሳናስበው
ወደ ሁለት ሰአት የሚሆን አወራን መጨራሻ ላይ ስልኳን ይዤው ምናምን
ተላየየን
በቃ ሁሉ ነገር በእጄ የገባ መሰለኝ የምውዳትን ልጅ
እንደዛ ስሜ ስንት አመት የናፈቀችኝን እናቴ ድምፇን ሰምቼ በቃ ደስታዬ ገደብ
አጣ ወደነ ትረሀስ ስመለስ ቤቲ እኔምልክ
ዮሚፍ ቺኳ እንዴት ናት ተመቸችህ ስትል በቃ በሳቅ የተነሳ ሆዴን አመመኝ
እንደዛ የሳኩበትን ቀን አላስታውስም እንደዛ ስንቀላለድ ቆየንና
ባ/ዳር ላሉት ጓደኞቼ ደውዬ ወደ አ/አ የመጨረሻ በረራ ስንት ሰአት ላይ እንደ
ሆነ እንዲጠይቁልኝ ነገርኳቸው ወደ ቤት ተመለስንና እኔም ልብሴን
እየሰበሰብኩ እያለ ትረሀስ መጣች በቃ ልትሄድ ነዋ አለችኝ አይን አይኔን
እያየች እህ ምን እያልሽ ነው
#ቆንጂዬ ተነጋግረን ጨረሰን ስላት አዋ አብረን ብንሄድ በዬ ነበር ምናምን
ስትል ጓደኛዬ ደወለልኝና የመጨረሻው 12:30 ላይ ነው አለኝ ትኬት
እንዲቆርጥልኝ ነገርኩት እሺ አለኝ ትረሀስ በጣም ደብሯታል ከቀኑ ወደ አስር
ሰአት እየሆነ ነው እሺ
እንሸኝህ ስትለኝ አያስፈልግም የናተ ዘምድ አሁን
በሞተር ስለ መጣ ዋናው መንገድ ድረስ አብረን እንሂድ ብሎኛል እኔን
እየጠበቀኝ ነው ልሂድ ቻው ብዬ እጄን ስዘረጋላት አንገቷን አቀረቀረች ምንነው
የቅድሙ ነገር ወሰወሰሽ እንዴ እንድገመው እንዴ አልኳት ሳቄ መጦኛል…



#ይቀጥላል ክፍል አስራ አራት...
#ሼር ቮት ማድረግ አይዘንጉ


​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 የፍቅር ቤት 🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺̶̥✽̶┄┄
https://telegram.me/geyone
👫👫👫👫😢👫👫💝💝👄♥️
ተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳይ ላይ ስሜቱን የገለጸበት አዲስ ሙዚቃ ተሰርቆ ወጣ😱😱😱😱😱 አቦ ያበደ ሙዝቃ ነው ከስር ያለውን ሊንክ በምጫን ያዳምጡ 👇👇

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል_14
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄



ቻው ብዬ እቼን ስዘረጋላት አንገቷን አቀረቀረች ምንነው የቅድሙ ነገር
ወሰወሰሽ እንዴ እንድገመው እንዴ አልኳት ሳቄ መጦኛል ክትክት ብላ ሳቀች
ደስ ይለኛል አለች ሁለታችንም በጣም ሳቅነ እኔ ምተኛበት ቦታ ማንም
ስላለነበረ ጥግ ድረስ ሳምኳት ፍቅርን የቀመስ ሰው
የህግ ፍፃሜ ፍቅር መሆኑ ይገባዋል
ብቻ የዛን ቀን ደስታ ልዩ ነው አ/አ ስትመጪ እንገናኛለን እልኳት እሺ ብላ
አንዴ ልደገምህ አለች እየፈራች በለው አንቺ ልጅ ባክሽ በአንድ ቀን እንደዚህ
የሆንሽ እኔ ጋር ውለሽ ብታድሪ ምን ልትፈጥሪ ነው አልኳት እሱን እዛኔ
የምናየው ይሆናል አለች ሁለተኛ ላይ ስስማት የአጎቴ ልጅ እኛ የለንበትን
ስትከፍተው ደነገጥነ ትረሀስ እኔ ላይ ቁጭ ብላለች ስታየን እንደ ማፈር
አለችና እሯ ምንድነውሳ ባልጠፋ መቀመጫ አለች ሁለታችንም ሳቃችንን
ለቀቅነው ትረሀስ እንደ ማፈር አለች እኔም ሳላስጠጣ
ተያይዘን ወደ ውጭ ወጣን ቦርሳዬን ይዛዋለች
ቤቲን ጠርቼ ተሰናበትኳት ትረሀስ አይኗ እንባ ሞላው
እኔም አልቻልኩም ግን እንደ ምንም ብዬ ቻልኩት
ወደ ባ/ዳር በግዜ ገባሁ ጓደኛዬ ጋር ወደ ኤርፖርት
ሄድኩ በቃ ልቤ ሲርድ ይታወቀኛል ሰው መልመድ በጣም እንደሚያስደስት
ሁሉ በዛው ልክ ይጎዳል
#መለያየት_ባይኖር_መተዋወቅ_ጥሩ_ነበር አለ የሀገሬ ሰው ወዶ አይደለም
ደርሶበት እንጂ ወደ አ/አ
እንደ ገባሁ ለትረሀስ ደወልኩላት ደስ አላት ግን ድምፇ ልክ አይደለም
ያለቀሰች መሰለችኝ በጣም ቅር አለኝ በሁለተኛው ቀን እህቷ ቤቲ
ደወለችልኝ እያወራን በመሀል ትረሀስ የለችም ደህና ናት አጠገበሽ አለች
አልኳት ወደ ሜዳ ብቻዬን ወጥቼ ነው ያለሁ አለችኝ
ነው እንዴ ብዬ እያወራን ወሬዋ ግራ እያጋባኝ መጣ የባለፎውን አሰብክበት
አለችኝ የእውነት ደነገጥኩ ምኑን አልገባኝም ስላት ሙድ ያዝክ ማለት ነው
አለችኝ እህ
ቤቲ ከምሬን እኮ ነው ስላት ምነው በሴትነቴ ስለ ጠየኩህ ነው አለች መልሳ
አሳጣችኝ ፀበል ቦታ እያለን
ትረሀስ እህቴ ተመችተሀታል ስትለኝ ምንም አልመሰለኝም ነበር ቀጥላ ደግሞ
አንተን ማጣት
አልነበረብኝም ያለችኝ ትዝ አለኝ ዮሚፍ ምነው ዝም አልክ ስትል ይቅርታ
ልደወልሽ መልሼ ብዬ ዘጋሁባት ለሰአታት በጣም ተናደድኩ ትረሀስን እንደ
ምወዳት አሳምራ ታቃለች ማታ ላይ ትረሀስ ደወለችልኝ
በጣም እንደ ደበራት ነገረችኝ በዛላይ ለመመለስ ወደ
ሶስት ሳምንት አለን አለች አንደ ምንም ብዬ ተስፋ ሰጠኋት እሁድ ቀን ትረሀስ
ደወለችና ቦሌ አከባቢ ከሰው ህቃ ተቀበልልኝ ብላ የሰውዬውን ስልክ
ላከችልኝ እሺ ብዬ ወዲያው ሄድኩ ደርሼ ስደውልለት ሰውዬው
የሆቴሉን ስም ነግሮኝ እዛ ነኝ ስትደርስ ደውልልኝ አለ እዛው እዛው ውጭ
ላይ ነኝ አልኩት ግባ አለኝ ወደ ውስጥ ስገባ በጣም ቀብረር ያለ ሰውዬ ነው
ከጫማዬ እስከ ፀጉሬ ድረስ አየኝ ምን አባቱ አስቦ ነው አልኩ በልቤ አረፍ
በል ዕቃውን ላምጣልህ በሎ ወደ ደረጃው ወጣ የሚገርመው ሳላስበው
ከኃላዬ…



#ይቀጥላል ክፍል አስራ አምስት ከ 100ቡኃላ
#ሼር ቮት አይርሱ


​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 የፍቅር ቤትሽ🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺̶̥✽̶┄┄

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
​​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል_15
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄



በጣም ቀብረር ያለ ሰውዬ ነው ከጫማዬ እስከ ፀጉሬ ድረስ አየኝ ምን አባቱ
አስቦ ነው አልኩ በልቤ አረፍ በል ዕቃውን ላምጣልህ በሎ ወደ ደረጃው
ወጣ የሚገርመው ሳላስበው ከኃላዬ ትክሻዬን መታ ስደረግ
ከተቀመጥኩበት ነው ያስነሳኝ ድንጋጤዬ ዞር ስል
ወይኗ ናት ምንም መልስ አልሰጠኋትም ቦታ ልቀይር ብዬ
ወደ ፊት ስሄድ ምን ያስኮፍስሀል አታውራም እንዴ አለችኝ
በቃ ሁሉ ነገር ፊቴ ድቅን አለ ወይስ የወደድካት ልጅ
ለገና ታመመች ብለህ ነው ስትለኝ ምሆነው አጣሁኝ
ፈጣሪ ትዕስቱን ስጠኝ አልኩ በልቤ ሰውዬው ወዲያው መጣ ዕቃውን
ተቀብዬው እንደ ወጣሁ ተከትላኝ ወጣች የሚፍ ጠብቀኝ አታሩጠኝ እንጂ
አለችኝ በጥፊ
ነበር መወልወል አለ ስወዬው ወዶ ነው እንደ ምንም ንዴቴን ችዬው ቆምኩ
ተቀየምከኝ እንዴ አለች በምኑ አልኳት ምን አውቃለሁ ከመጣህ እንኳ
አልደወልክልኝም
ብላ ቀባጠረች ትረሀስ እንዴት ሆነች ተሻላት አለች
ወይ አምላኬ ስንቱን ችለኸዋል አልኩት በልቤ ሰውን ገሎ ደህነቱን መጠየቅ
ምን ይባላል አልኩኝ በልቤ
አዋ ደህናናት በቅሩብ እንጋባለን የሰርግ ጥሪ ይደርስሻል እንዳትቀሪ አልኳት
ፈገግ ብዬ መልስ
አልሰጠችኝም እኔም በቆመችበት ጥያት ሄድኩ
የተቀበልኩትን ዕቃ በፖስታ ቤት ወደ ባህር ዳር ላክልኝ አለች እኔም ወዲያው
ላኩላት በሁለተኛው ቀን የትረሀስ ስልክ አይሰራም ለቤቲ ስደውል አ/አ ዛሬ
መጣሁ የትነህ
አለችኝ በጣም ነበር የደነገጥኩኝ መጨረሻ ላይ ተቀጣጥረን ተገናኘን እና እሷ
በረራ ለማድረግ ሳምንት ስለቀራቸው መጨረስ ያለባት ነገር ስላለ
እንደመጣች ነገረችኝ ደስ ይላል ብዬ እየወራኋት ከኋላዬ ትረሀስ
አይኔን ያዝ አደረገችው ድምፇን ጎርነን አድርጋ እኔ ማነኝ
አለች በቃ መጮህ ብቻ ነው የቀረኝ ደስታውን መሸከም ከበደኝ ጠረኗ ራሱ
ናፍቆኝ ነበር ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እንደ ማስቲሽ ተላተምኩባት ትረሀስ
ማለት ፍቅርን በስሱ አሳይታኝ በምእናብ የተከተልኳት ልጅ ናት ሳቅፋት
ጉያዬ ውስጥ ገባች በመሀል ቤቲ እህ ቁጭ በሉ እንጂ ይሄናፍቆት ውይስ
ብላ ፈገግ አለች አንተ እንደዚህ ትናፈቀኛለህ በሁለት ሳምንት ውስጥ አለችኝ
የእኔን ማን በነገረሽ አልኩኝ በልቤ ትረሀስ ጎኔ ቁጭ ብላ እየተጫወትን እያለ
ቤቲ ፊት ለፊቴ ነበር የተቀመጠችው
በመሀል ቤቲ አትኩራ አየችኝ አይኗ እኔ ላይ እንደ ሆነ ገባኝ ቀስ ብዬ ሳያት በዛ
ፍጥነት…


#ይቀጥላል ክፍል አስራ ስድስት...
#ሼር ቮት አድርጉ ሊያልቅ ሶስት ክፍል ቀረው



​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 የፍቅር ቤት 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
ለውብ ቀን!
💚

ወጣትነት ባህር ነው ። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው ። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው ።
ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው ። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን
መሞላት ነው ። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው ። ወጣትነት በዘረኝነት
ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ
ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ
እይታን ማስፋት ነው ።

ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው ። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ
ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው ። ወጣትነት ብርሃን ነው ። ወጣትነት
ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው
ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው ። ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት
መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ
መጠማት ነው ። ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው ። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ
ራስን መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው ። ወጣትነት
እሳት ነው ። ወጣትነት ቤንዚል ነው ። ወጣትነት ቅጠል ነው ። ወጣትነት ጤዛ ነው ።
ወጣትነት ታክሲ ነው ። ወጣትነት ምርጫ ነው ። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን
ነው ። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው ። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ
ማጀገን ነው ። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ
ማለፍ ነው ። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ... ።

ኤጭ ከሚለው መፅሐፍ ላይ የተቆነጠረች...! "

ውብ ቀን!💚

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
ዒድ ሙባረክ!

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አል አድሀ በአል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

ኢድ ሙባረክ!

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
​​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል_16
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄




በሁለት ሳምንት ውስጥ አለችኝ የእኔን ማን በነገረሽ አልኩኝ በልቤ ትረሀስ ጎኔ
ቁጭ ብላ እየተጫወትን እያለ ቤቲ ፊት ለፊቴ ነበር የተቀመጠችው
በመሀል ቤቲ አትኩራ አየችኝ አይኗ እኔ ላይ እንደ ሆነ ገባኝ ቀስ ብዬ ሳያት በዛ
ፍጥነት ጠቀሰችኝ ደነገጥኩ
እህቷ ጋር ቁጭ ብዬ እንኳ እንዴት እንደዚህ የሚያሳፍር ስራ ትሰራለች
አልኩኝ በልቤ በዚህ መሀል እኔ ልሂድ ምጨርሰው ጉደይ አለኝ እናተ አብራቹ
ቆዩ ብላ ጥላን ሄደች ተመስገን አልኩ ትረሀስን ይዤ ወደ ቤት ሄድኩኝ
አባቴ ጋር ላስተዋውቃት ብዬ ምክንያቱም ከዛሬ ውጭ
ግዜ ላላገኝ እችላለሁ ብዬ አሰብኩ አቤት ስንሄድ አባቢ ብቻ ነው ያለ ማንም
የለም ደስ አለኝ አስተዋውቂያቸው ምን ብዬ ብዙ ተጫውተን አባቢ ቡና
አፍይልኝ እስኪ ልጄ አላት በአንድ አፍ እሺ አለች እንዴ አባቢ እንግዳ እኮ ናት
ባይሆን እኔ ላፍላ ስል ቀድማኝ ተነሳች እሳ ቡናውን
ስትቆላ እኔ እቤቱን አስተካክዬው ሲኒ አጥቤላት ምናምን ወደ እሷም ቡናውን
አድርሳ ነበር ጤና አዳም
እና ቀረፋ ይኖራል አለች አዋ አለ ግን ምን ልታደርጊ ነው አልኳት ዝም ብለህ
ስጠኝ አለች እሺ ብዬ ሰጥቻት አባቢ ጋር ቁጭ አልኩ ቡናውን ቀድታ ለአባቢ
ስትሰጠው
ግር አለው ትንሽ ጎደል ብሏል ግርምት ነገር ፊቱ ላይ አለ የእኔ ደግሞ እስከ
ስኒው ጫፍ ሙሉ ነው ለምን ጎዶሎ ቀዳችለት ብዬ ትንሽ ቅር አለኝ አባቢ
ቡናውን ሳይጠጣ አሽትቶት ክትክት ብሎ ሳቀ እኔ ምንም ሊገባኝ አልቻለም
ሲጠጣው ደግሞ በቃ አባቴን ከማውቀው ቀን ጀምሮ እንዲህ ያለ ፈገግታ
አይቼበት አላውቅም ከተቀመጠበት ተነስቶ ግንቧሯን ሳማት እሷም ምንም
አልገረማትም
ምድነው ነገሩ አልኩኝ ከአመታት በፊት ከእናትህ እጅ ተቀብዬ የጠጣሁትን
ቡና ዛሬ ደገምኩ አለ እንባው በጉንጩ ይፈሳል ደስታም አለ ትዝታም አለበት
ትረሀስ
ከዚህ በፊት ስለ አባቴ ባህሪ የነገረችኝ ትዝ አለኝ እናቴ ጋር ስለ ምትውል
የአባቴን ባህሪ ጠንቅቃ ታቃለች አባቢ
አብዝቶ መረቃት እኔ እስከ ማውቀው ድረስ አባቢ ሰው ሲረግም እንጂ ሰው
ሰው ሲመርቅ አይቼ አላውቅም
ወደ ማምሻ ላይ ቤቲ ስትደውልልን ሄድነ ትረሀስን ከምገልፃት በላይ
በውስጤ ላይ ትልቅ ቦታ ሰጥቻታለሁ
መወደዴን ግን ምን ብዬ ልንገራት በዛ ላይ ልትሄድ ነው
ብቻ ሁሉም ነገር ጨንቆኛል ለመሄድ አንድ ቀን ሲቀራቸው ትረሀስ ጋር
ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ወደ አንጦጦ ተራራ ወጣን አየሩ በጣም ደስ ይላል
ትረሀስ ጋር ሰሆን ልቤ ያረፈ ያህል ይሰማኛል በዚህ መሀል
ቤቲ ደወለች እኔ ላነሳው ስል አታንሳው አለች ባክሽ አነሳዋለሁ ይደብርታል
ብዬ ላነሳው ስል ስልኩን እጄ ላይ ያዘችው እኔም ለጫዋታ ያህል እንጂ
ማንሳቱን አልፈልግም ከሰላምታ በፊት የትናቹ የሚለው ቃሏ ይቀድማል
ስንታገል ሁለታችንም ሌላ ሙድ ውስጥ ገባን …


ክፍል አስራ ሰባት ከ100ቡኃላ #ይቀጥላል … ሊያልቅ 2 ክፍል ብቻ ቀርቷል
#ሼር ማድርግ አይርሱ


​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 የፍቅር ቤት 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
​​#አራቱ_ሚስቶች


🔐አራት ሚስቶች የነበሩት አንድ ሀብታም ነጋዴ ነበር፡፡

🔓አራተኛ ሚስቱን
ከሌሎች አብልጦ በእጅጉ ይወዳታል፡፡ ስለሚወዳትም ጥሩውን ሁሉ ለእርሷ በመስጠት ይንከባከባታል ያስደስታታል፡፡

🔓ሦስተኛ ሚስቱን መውደድም ብቻ አደለም ይኮራባታል፣ ይመካባታልም ጭምር ይዟት በአደባባይም ለመታየት ይፈልጋል ነገር ግን ጥላው እንዳትሄድ በጣሙን ይሰጋል፡፡

🔒ሁለተኛ ሚስቱንም እንዲሁ ይወዳታል ይች ሁለተኛ ሚስቱ በነገሮች አስተዋይና ብልህ ታጋሽም በመሆኗ ይመካባታል፡፡ ነጋዴው አንዳች እክል ከገጠመው እንዲሁ ችግሩን ታቅፎ እሚያመራው ወደ ሁለተኛ ሚስቱ ነው እሷም በአስቸጋሪው ሰዓት ከጭንቀቱ ትገላግለዋለች፡፡

🔓የመጀመሪያ ሚስቱ በጣም ታማኝ አጋሩ ናት ቤቱንና ንግዱን
የምትመራለትና የምታስተዳድርለት እሷው ነች እሷ በጣም የምታፍቅረውዐቢሆንም እሱ ግን ስለማያፈቅራት አንድም ቀን በትውስታው ውስጥ ቦታ ሰጥቷት አያውቅም ነበር፡፡

🖤ታዲያ አንድ ቀን ህመም ተሰማውና ማለፉን ባሰበ ጊዜ የተድላ ዓለሙን እያስታወሰ እንዲህ አሰበ “አራት ሚስቶችና የተትረፈረፈ ሀብት አለኝ ነግር ግን በሞት ጊዜ ብቻዬን እሆናለሁ፡፡ እንዴት ብቻዬን እሆናለሁ?” በማለት አራቱንም ሚስቶች በማስጠራት ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡
ሁላችሁንም በጣም እወዳችኋለሁ የሚያምሩ አልባሳትንም እያለበስኩ ሳስጌጣችሁ ኖርኩ አሁን ግን ልሞትናውና ከብቸኝነቴ ታድኑኝ ዘንድ ተከተሉኝ አላቸው፡፡

🔓አራተኛው ሚስቱ “በፍጹም አይሆንም” ስትል መልሱን ሰጥታው
ከአካባቢው ተሰወረች፡፡ ነጋዴው በሰማው ምላሽ ልቡ ተነካ፡፡

🔓ለሦስተኛዋ ሚስቱ “በሕይዎቴ ሙሉ ስወድሽ ኑሪያለሁ አሁን አብረሽኝ ልትሆኝና ወደምሄድበት ልትከተይኝ ትፈቅጃለሽ?” አላት በአዘኔታ ሆኖ መልስ ሲጠባበቅ “አይሆንም ሕይወት አትጠገብም፡ እዚህ መኖር መልካም ነው እናም ከአንተ ሞት በኋላ አግብቼ መኖር እሻለሁ” አለችው፡፡

💔ይህ ሀብታም ነጋዴ ልቡ ዝቅ ሲልና ወደ ቀዝቃዛነት ሲለወጥ ተሰማው፡፡
አሁንም በተስፋ መቁረጥ ሁኖ “በሕይዎቴ ሙሉ እርዳታን ስፈልግ ወደ አንች ስመላለስ ኖሪያለሁ ስትረጅኝም ነበር አሁንም እርዳታሽን ፈልጊያለሁና እርጅኝ” ሲል ሁለተኛ ሚስቱን ጠየቃት፡፡
“በዚህ ሰዓት ልረዳህ ባለመቻሌ አዝናለሁ ማድረግ የምችለው አንተን ወደ መቃብርህ መሸኘት ብቻ ነው” ስትለው መብርቅ የመታው ያህል ክው አለ፡፡
በድንጋጤ ስሜት ተውጦ እያለ “የትም ብትሄድ እከተልሃለሁ፤ አንተጋ እሆናለሁ!” የሚል ድምጽ ሲያስተጋባ ተሰማው ዓይኑን ሲያነሳ የተጎሳቆለ እይታ ያላት የመጀመሪያ ሚስቱ ነበረች ነጋዴው እየተናነቀው “ሲኖረኝና ስችል ልንከባከብሽ ይገባኝ ነበረ” በማለት እቅፍ አድርጎ ወደሰውነቱ አስጠጋት፡፡💔

🤍በመሠረቱ ሁላችንም በሕይዎታችን አራት ሚስቶችን አኑረን ይሆናልና የእኛም ታሪክ ሊሆን ይችላል፡፡

💝አራተኛው ሚስታችን ፈራሹ ስጋችን ነው ለምቾቱና ለውበቱ
ተጨንቀን ብንደክምም ቀሪ እንጅ ተከትሎን አይሄድም፡፡

💛ሦስተኛው ሚስታችን አለን የምንለው ነገር ንብረት ሀብትና ክብራችን ነው ይሄም እኛ ስንሞት ወደሌሎች የሚተላለፍ ነው፡፡

💖ሁለተኛው ሚስታችን ቤተሰቦቻችንና ጓደኞቻችን ናቸው፡፡ በሕይወት ዘመናችን የቱንም ያህል ቀረቤታና ቁርኝት ቢኖረንም ማድረግ የሚችሉት እስከ መቃብር መሸኘት ብቻ ነው፡፡

💚የመጀመሪያዎ ሚስታችን ሕያው ነፍሳችን ናት፡፡ በመልካም ስራ እናድሳት ነገ አብራን ትኖራለች ቁስና ሀብት ስናሳድድ ወደ ጎን ገፍተናት ቢሆንም አብራን የምትሆነው እሷው ነችና በመጨረሻው ሰዓት
ሳይሆን #አሁኑኑ_እንድናለመልማት_ያስፈልጋል፡፡

ታሪኩ አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር ያርጉት

❤️ፍቅር
https://telegram.me/geyone
የተፈፀመ የዘር ማጥፋት እንጂ የተፈጠረ የብሔር ግጭት የለም!
****
በአማራነታቸው ተለይተውና ተመርጠው ስማቸው እየተጠራ ጅምላ ግድያ ለተፈፀመባቸው ወገኖቻችን ፍትኅ ማስፈን የሚጀምረው የተፈፀመባቸውን ወንጀል በስሙ ከመጥራት ነው። ሰኔ 22፣ 2012 ዓ/ም ምሽት በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በአርሲ ልዩ ልዩ ከተሞች አማሮች ላይ የተፈፀመው ጅምላ ግድያ የዘር ማጥፋት ከሚለው ውጭ ሌላ ስያሜ የሚገልፀው አይደለም። የገዥው ፓርቲ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ጭምር የተሳተፉበት፣ ለዜጎች ደኅንነት መከበር በሚል ለ32 ዙር በሰለጠኑ የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ አካላት ፊት የተፈፀመ፣ አማሮች በአማራነታቸው ተለይተውና ተመርጠው ጅምላ ግድያና የንብረት ማውደም የተፈፀመበትን አሳዛኝና አሳፋሪ ድርጊት ከማውገዝ ባለፈ ሁላችንም ወንጀሉ የዘር ማጥፋት መሆኑን በመገንዘብ በስሙ ልንጠራው ግድ ይለናል።

የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ቀዳሚ ኃላፊነት ያለበት መንግሥት የተፈፀመውን ወንጀል በስሙ ከመጥራት ጀምሮ በዚህ ድርጊት የተሳተፉ አካላትን፣ የዘር ማጥፋቱ እንዲስፋፋ የሞራል ድጋፍን ጨምሮ ተሳትፎ የነበራቸውን አካላትና ይህን ዘር ተኮር እልቂት በመከላከልና መቆጣጠር ረገድ ተገቢውን መንግስታዊ ኃላፊነታቸውን ባልተወጡ የፌዴራል፣ ክልል፣ ዞን፣ ከተማ አስተዳደር፣ ወረዳና የቀበሌ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ላይ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል።

አንዳንድ ሚዲያዎች በግላጭ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት «የብሔር ግጭት» አስመስለው ማቅረባቸው ኢሞራላዊና የተፈፀመውን እጅግ ዘግናኝና ዓለምአቀፋዊ ወንጀል በማድበስበስ ለወንጀለኞች ሽፋን የመስጠት ሌላ ወንጀል ነው። በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረ የብሔር ግጭት አልነበረም፤ የነበረው አማሮችን በማንነታቸው ነጥሎ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ነው። ከዚህ አንፃር ሁላችንም ከቃል አጠቃቀም ጀምሮ በታሪክ ፊት ድንክ ከሚያደርጉን ከሕግም ከሞራልም ውጭ ከሆኑ አሰላለፎችና አካሄዶች ራሳችንን እንድናርቅ ማስታወስ እንፈልጋለን።

ስለሆነም መንግስት፦
1) ወንጀሉ የዘር ማጥፋት መሆኑን እውቅና ሰጥቶ በዚያው ልክ እንዲንቀሳቀስ፣
2) የዘር ማጥፋት ለተፈፀመባቸው ወገኖቻችን ብሔራዊ የኃዘን ቀን እንዲያውጅና ቋሚ መታሰቢያም እንዲያደርግ፣
3) የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያጣራና የሚመረምር ልዩ የምርመራ ኮሚሽንና አቃቤ ሕግ ጽ/ቤት እንዲያቋቁምና ወንጀለኞች የሚዳኙበት ልዩ ችሎት እንዲሰይም፣
4) ለተፈፀመው የዘር ማጥፋት ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣
5) የዘር ማጥፋት ለተፈፀመባቸው ወገኖች ቀሪ ዘመዶች የካሳና መልሶ ማቋቋሚያ ልዩ ፈንድ በመክፈት ወደ ሥራ እንዲገባ እንዲሁም
6) የዘር ፍጅቱ ሥርወ ምንጭ የሆኑ ሕጋዊና መዋቅራዊ ጉዳዮችን የመፈተሽና በዘላቂነት መፍትሔ የሚያገኙበትን ሁኔታ እንዲያመቻች፣

ሁላችንም የተጠናከረ ትግል ልናደርግና ጫና ልሳድር ይገባል።

መንግስት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፃሚዎችንና ተባባሪዎችን ወደ ሕግ ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረትም ሁላችንም ልንደግፍና ፍትኅ እንዲሰፍን በጽናት ልንቆም ይገባል።

ፍትኅ የዘር ማጥፋት ለተፈፀመባቸው ወገኖቻችን!
@ክርስቲያን ታደለ

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
​​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል_17
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄


#የመጨረሻ_ክፍል_ከ 100🀄️ጥላል


ቤቲ ደወለች እኔ ላነሳው ስል አታንሳው አለች ባክሽ አነሳዋለሁ ይደብርታል
ብዬ ላነሳው ስል ስልኩን እጄ ላይ ያዘችው እኔም ለጫዋታ ያህል እንጂ
ማንሳቱን አልፈልግም ከሰላምታ በፊት የትናቹ የሚለው ቃሏ ይቀድማል
ስንታገል ሁለታችንም ሌላ ሙድ ውስጥ
ገባን በተቀመጥንበት ተያይዘን ተጋደምን በርግጥ እኔ ሴት ልጅ ጋር ስሳሳም
የመጀመሪያዬ ባይሆንም ግን በፍፁም ትረሀስ ጋር እንዳለኝ ስሜት ተሰምቶኝ
አያውቅም እሷ ግን ወንድ ልጀ ጋር እንደዚህ አይነት ነገር የመጀመሪያዋ ነው
እንዴት እንደ ምለያት አላውቅም
እሷም ብትሆን በጣም ከብዷታል ምክንያቱም ነገሮች አንዳሰብነው አልሆነም
በአጭር ግዜ ውስጥ ከመግባባት አልፎ ለፍቅር መተሳሰብ ደርጃ ላይ
ደርሰናል
ማታ ላይ እህቷ እራት ጋበዘችንና እዛው ሆቴል ውስጥ
መጠጥ ወዳለበት ክፍል ሄድነ እኔም ደስ አለኝ ባይሆን መጠጡ ጭንቀቴን
ቢያስረሳኝ ብዬ አሰብኩ ቤቲ ከትንሽ ሰአት በኋላ በቃ በመጠጥ ራሷን
መቆጣጠር አቃጣት ትረሀስ በመጠኑም ቢሆን ሞቅ ብላለች እኔም ብሆን
በጣም ከብዶኛል የግዴን ቤቲን ትረሀስ ጋር
ለሁለት ይዘን ያየዙት ክፍል ወስድናት በቃ ከስካር የተነሳ ሬሳ ሁናለች አልጋ
ላይ አስተኝተናት ልወጣ ስል ደብል አልጋ ነበር የያዙ ትረሀስ አንተ እሱላይ ተኛ
እኔ እሷ ጋር ልተኛ ስትለኝ እኔም እኮ ክላስ ይዣለሁ አልኳት ሰላም እደሩ ብዬ
ጉንጯን ስሜ ወደ ክላሴ ሄድኩ ትንሽ ስለከበደኝ ሻወር
ገባሁ ልክ ጨርሼ እንደ ወጣሁ ክለሴ ተንኳኳ ስከፍተው ትረሀስ ናት
ደነገጥኩኝ ችግር አለ ስላት እረ የለም ሰአት ገና ሰለሆነ ትንሽ እንጫወት ብዬ
ነው አለች እሺ ግቢ ብያት ክላስ መጠጥ እንዲያመጡልን ደወልን ወዲያው
ብላክ ሌብል ይዞልን መጡ ብዙ ተጫወትነ
ሁለታችንም የስካር መንፈስ ውስጥ ገብተናል እውነት ለመናገር ከዛን በኋላ
የተፈጠረውን አላውቅም ምን እንደ ሰራን ባውቅም እንዴት ስሜታችንን
መቆጣጠር እንዳቃተን ግራ ገብቶኛል ሊነጋ አስራ አንድ ሰአት አከባቢ ትረሀስ
ሻወር ቤት ውስጥ ናት የተኛንበት አልጋ አምሶላው እንዳለ በደም ተበላሽቷል
በቃ ከደንጋጤ የተነሳ ተሸማቅቂያለሁ ትረሀስ ጨርሳ ስትወጣ አንገቴን ደፋው
በምን አይኔ ልያት እግሬ ስር መጣ ቁጭ አለች
ትረሀስ ይቅርታ ብዬ ልጀምር ስል ሁሉንም ፈልጌ ነው ያደረኩት አለችኝ
ተጠመጠምኩባት ወደ ቤቲ ክላስ ሄደች እኔም ሻወር ወስጄ ወጣሁ ወደ
ክላሳቸው ስሄድ
ቤቲ እንደ ተኛች ነው ቁርስ እዛው ክለስ ውስጥ እንዲመጣ አደርኩኝ ቤቲ
የግዷን ቀስቅሰናት ሻወር ገባች ቁርሰ እየበላን እያለ ድንገት እኔና ትረሀስ
እኩል
ተያየን እንደ ማፈር ብላ ዝቅ አለች እኔ ግን ውስጤ በሀዘን ጨለሞብኛል እሷ
ለአንድያው ጥላኝ ልትሄድ ነው እንዴት አድርጌ ልደሰት እሁድ ቀኑን ሙሉ
አብረን ዋልነ ወደ ማታ ላይ በረራ ስላላቸው ወደ ኤርፖርት ሄድነ በቃ የልቤ
ምት ጨምሯል ትረሀስ ልትለየኝ ነው ኤርፖርት ውስጥ ተቀምጠን እያለ
ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ወደ በረራ ክፍሉ እንዲ ገቡ ተነገረ እንባዬ
ሊመጣኝ ነው እንዴት ልቻለው ቤቲ ጠጋ አለችና እባክህና ፊትህን አንደዚህ
አታድርግ እየለቀሰች ነው እዛ ምትደርስ አለችኝ እንደምንም ብዬ ቻልኩት
ትረሀስ ቤቲ እያየችን ግጥም አድርጋ ሳመችኝ ቤቲ ፈገግ አለችና ጠቀሰችኝ
እንዴ እቺ ልጅ ሙዷ ነው እንዴ ሰው መጥቀስ አልኩ በልቤ ለአንዴና
ለመጨረሻ ግዜ…



#ይቀጥላል#የመጨረሻ_ክፍል_ከ 100 ቡኃላ
#ሼር ቮት ማድረግ አይርሱ


​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 የፍቅር ቤት 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄

https://telegram.me/geyone
ባገኘኸው ቦታ ብቀል…..




ይህች አበባ ከቤቴ በራፍ ላይ ያለች አበባ (አበባ መሳይ ቅጠል) ናት። ዘወትር ደረጃውን ስውጣም ሆነ ስወርድ እንዳልረግጣት እጠነቀቃለው።

ጥንቃቄዬ የመጣው ግን ከብዙ ጊዜ በኋላ በተለየ አይን ስለተመለከትኳት ነው። አንድ ቀን በሬን ቆልፌ ወደታች ስወርድ፤ ድንገት ቁልፌ ከመሬቱ ላይ ወደቀ። ቁልፌ ወድቆ ያረፈው፤ ከዚህች ትንሽ አበባ መሳይ ቅጠል ጎን ነበር። ቁልፌን ከማንሳቴ በፊት፤ ይህችን ቅጠል አስተውዬ ተመለከትኳት።

ዙሪያዋን በድንጋይ የተከበበች፤ ብቸኛ ነፍስ። አፍር ለአይን በማይታይበት፤ ድንጋይ ላይ፤ ያገኘችው የስንጥር ያህል ቀዳዳ ተጠቅማ በድፍረት የበቀለች ህይወት መሆኗን አስተዋልኩኝ። እንደልቤ አፈር ካላገኘው አልበቅልም ብላ ያላመጸችውን ይህችን ቅጠል ሳይ፤ መንፈሴ እንደልማዱ አፈንግጦ ሌላ ነገር ማሰብ ጀመረ።


ብዙዎቻችን ለህይወታችን መሰናከል፤ ዙሪያችንን መውቀሱ ይቀናናል። ለህይወታችን መበላሸት፤ ለውድቀታችን ሌላው ላይ እጣታችን መቀሰሩ የተለመደ መልሳችን ነው።

ነፍስ ዘርተን ለመብቀል፤ ዙሪያው በሙሉ አፈር እንዲሆን እንሻለን።

ህይወትን አጣጥመን ለመኖር፤ ዙሪያችን ሁሉ መልካም እስኪሆን እንጠብቃለን። በቤተሰብ ጥፋት፤ በማህበረሰብ ስህተት፤ በሃገር ውድቀት፤ ዙሪያው ድንጋይ ነው ብለን ሳንበቅል እንቀራለን። ምንም እንኳን መብቀያ ቦታ ብናገኝም፤ በዙሪያችን ነፍስ ስላላየን የማይቻል ይመስለናል። ለዚህ ነው ይህች አበባ፤ ያላሰብኩትን ያሳሰበችኝ። እኔ በተፈጥሮ አምናለው፤ የሰው ልጅ አይኖቹን ከፈቶ ማየት ከቻለ፤ ከተፈጥሮ የላቀ መምህር ያለም አይመስለኝም። ተሳስቼ ሊሆንም ይችላል።


በእድል የሚያምኑ ብዙ ሰዎች አሉ፤ እድል ሁሌም ዝግጁ ሆኖ ለሚጠብቅ የምትሰጥ ሙሽራ ናት። የእድል እውነተኛ “ትርጉም ጥረት ከአጋጣሚ ጋር ሲገናኝ” የሚል ነው።

ማንም ሰው እጅ እና እግሩን አጣጥፎ እድልን ቢጠብቅ፤ በእድሜው እያሾፈ ነው። እድለኛ የምንላቸው ሰዎች፤አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት ተዘጋጅተው የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው።


ማድረግ የምትፈልገው ነገር ካልህ፤ ትክክለኛው ሰዓት እስኪመጣ ብለህ አትዘናጋ። በህይወት ውስጥ ትክክለኛዋ ሰዓት የአሁኗ ደቂቃ ብቻ ናት። ሁኔታዎች እስኪመቻቹ መጠበቅ፤ አሁን ያለህን አጋጣሚዎች ማባከን ነው።

ለዚህ ነው ይህችን በደጃፌ ፤ ከደንጋዮቹ መሃከል የስንጥር ያህል ቦታ ላይ የበቀለችው አበባ ዘወትር የምቃኛት፤ ባየትኋት ቁጥርም ለራሴ እንዲህ እያልኩኝ እነግረዋለው “ለወቀሳ ጊዜ አልሰጥም፤ በገኘሁት ቦታ እበቅላለው፤ ባለችኝ አፈር ላይ አብባለው”

ያለህ ከበቂ በላይ ነው፤ ምንም የሌለህ የሚመስልህ፤ አሳብህ እና ጭንቀትህ በሌሉህ ነገሮች ላይ ስለሆነ ብቻ ነወ^

https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
​​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል18
#የመጨረሻ_ክፍል
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄


ቤቲ ጠጋ አለችና እባክህና ፊትህን አንደዚህ አታድርግ እየለቀሰች ነው እዛ
ምትደርስ አለችኝ እንደምንም ብዬ ቻልኩት ትረሀስ ቤቲ እያየችን ግጥም
አድርጋ ሳመችኝ ቤቲ ፈገግ አለችና ጠቀሰችኝ እንዴ እቺ ልጅ ሙዷ ነው እንዴ
ሰው መጥቀስ አልኩ በልቤ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ትረሀስ ጋር ተያየን
እንባዋ ቀደማት እኔ
ተሰናብቻቸው ወደ ቤት ሄድኩኝ ክላሴ ገብቼ እስኪበቃኝ
አለቀስኩ አባቢ ምን እንደ ሆንኩ ቢጠይቀኝም መናገር ግን አለፈለኩም
ጥላህ ሄደች እንዴ አለኝ ደነገጥኩ እንዴት ሊያውቅ ቻለ ብዬ ገርሞኛል አንተ
ጋር ከመጣች በኋላ እኮ በሁለተኛው ቀን ብቻዋን መጣለች አለኝ
ትዝ አለኝ አብረን የመጣን ቀን በኩንትራት ታክሲ ነበር
ስልኬ ባላንስ ጨርሶ ስለነበረ ለባለታክሲው የደውልኩለት በሷ ስልክ ነበረ
ቁጥሩን ይዛው ማለት ነው አልኩኝ በልቤ ሁሉንም ነገረኝ እናቴን በስልክ እንደ
አገናኘችው በቃ ለመናገር ከቃል በላይ እንደ ሆነበት
እኔም በሰአቱ ተሰምቶኝ ነበር ትረሀስ ጋር በስልክ
መገናኘት ጀመርነ ሆዷን እንደ ማም ብሏት እንደ ነበረ ነግራኝ ነበር ተሻለሽ
አልኳት እ… ብላ ዝም አልች ንገሪኝ እንጂ ችግር አልኳት ስልኩን ዘጋችብኝ
በቃ የምሆነው አጣሁኝ የቤቲ ስልክ አይሰራም መጨረሻ ላይ ሳምንት በኋላ
ቤቲ ደውላ የሶስት ወር እርጉዝ እንደ
ሆነች ነገረችኝ በጣም ነው የደነገጥኩኝ እነሱ ከሄዱ
ሶስት ወር ሁኗቸዋል ምን ልመልስላት አትጨናነቅ የሚፍ አለች ይባስ ብላ
ሆቴል ውስጥ ያደርን እለት እኮ አንድ ላይ እንደ አደራቹ አውቂያለሁ አለች
ይበልጥ ደነገጥኩ ታድያ እንዴት ዝም አልሽን አልኳት ፈተናውን ስላለፍክ
አለችኝ የምን ፈተና ስላት እኔ ጋር ወደ ፍቅር
እንድትገባ የጠየኩህና የፈለኩ ልብህ ከእህቴ ውጭ ምን ያህል ታማኝ እንደ
ሆነ ለማወቅ ነበር አለኝች ትረሀስ ደግሞ ይሄን ነገር አንተጋር ማድረግ ትፈልግ
ነበር ለዛ ነው ብላ ብዙ አዋራችኝ ትረሀስን እንደምንም ብዬ አናገርኳት ቤቲ
ጋር በስልክ መገናኘታችን ቀጠልን ወራት
አለፉ ትረሀስ የምትወልድበት ቀን ደረሰ እኔም ቤቲ ጋር ከብዙ ልፋት በኋላ እኔም ቪዛዬን ጨርሼ ወደ አውስትራሊያ አቀናሁ ሚገርመው ፈጣሪ ረድቷት እሷ ሴት ልጅ ተገላግላ ወደ ቤት እንደ ገባች እኔ ደረስኩ የእኔን መምጣት ከቤቲ ውጭ ማንም አያውቅም ይሄን ሀሳብ ያመጣችው እሷ ነበረች ቤቲ ማለት ለትረሀስ ደስታ ስትል የማታደርገው ነገር የላትም ልክ እንደ ደረስኩ ቤቲ በስተ ጀርባ በኩል ነበር የወሰደችኝ እናቴ ስታየኝ የያዘችውን ዕቃ ነበር የለቀቀችው ቤቲ አፏን ያዘቻት ቀድማ እንዳትጨው ብላ እናቴ ጋር ሰላምታዬን ጨርሼ ወደ ትረሀስ ልሄድ ስል ቤቲ ቆይ አንዴ ዋትስ አፕ ላይ ግባ አለችኝና ወደኔ ደወለች ስልኩን ሳነሳው ሂጄ በስልክ ላገናኝህ ስትለኝ ሳቄ ቢመጣኝም እሺ እልኩ ቤቲ ወደ ትረሀስ ሄደችና እንኪ ዮሚፍ ይፈልግሻል አለቻት እኔም ኢትዮጲያ እንዳለው አድርጌ አወራኋት በመጨረሻ ላይ ቻው ብዬ ምናምን ልዘጋው ስል እንደ ማልቀስ አለች #እናትዬ ዛሬም ታለቅሻለሽ አልኳት ከአሁን በኋላ እንኳ ብታለቅሺ በጥፊ ነው ማከናንብሸ አልኳት ከቻልክ አድርገው አለችኝ እረ አንቺ ልጅ ተደፋፈርሽኝ ስላት ይልቅ ዮሚ ናፍቀህኛል አለች ታድያ ደርሻለሁ በር ላይ እኮ ነኝ ጠብቂኝ #እናትዬ ስላት ሳቀችብኝ ቀስ ብዬ ገባሁ አንቺ ምን አድርግ ነው ምትይኝ አልኳት ፊቷ ላይ ቁሜ ዮሚ ብላጨወች በቃ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች እኔም ልጄን አቅፌ አንባዬን አወረድኩ የልጃችንን ስም #ቤሮኒካ አልናት በመጨራሻው ሰአት ሁሉንም አገኘው ፍቅረኛቹ ምንም ያህል መጥፎ እና ጨካኝ ቢሆን እናንተ ግን ፀለዩላቸው የእናተ ፀሎት አንድም ፍቅራቹን ይባርከዋል እንድም
የተሻለ እና አስተዋይ ይሰጣቹዋል ሁሌም ለወይኗ እፀልይ ነበር አምላክ
ሁሉንም ነገር ቀየረው ሰዋች መቀየር
ባይፈልጉም እንኳ ለእናተ ግን ፈጣሪ ያስባል ከመወሰናቹ በፊት ከውሳኔ
በኃላ ለሚመጣው ችግር ሀላፊነት ለመውሰድ ዝግጁ ሁኑ ዛሬ ሁሉም ነገር ተሳክቶልኛል የምወዳት ፍቅረኛዬን እና እድሜ ልኬን የናፈኳትን እናቴ ከጎኔ አድርጌ መሀል ላይ ነኝ ሁሌም
ለምትፈልጉት ነገር ተስፋ መቁረጥ የለባቹም ።



ይህ አሳዛኝ እና አስተማሪ የሆነውን ቤሮኒካ🌺 የተሠኘው አጭር ልብ ወለድ ዛሬ በዚህ መልኩ ተፈፀመ እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለው በሌላ ታሪክ እስከምንገናኝ 🌺መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ ስለ ታሪኩም ሆነ ስለ ቻናሉ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት በውስጥ መስመራችን እንድትልኩልን ስንል በ ቻናላችን ስም እንጠይቃለን፡፡📩

@YefkrBet1Bot

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share የፍቅር ቤት
የፍቅር ቤት
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
ተፈፀመ ቤሮኒካ
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥🌺 ቤሮኒካ 🌺🌺̶̥✽̶┄┄
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ከተመቻቹሁ ለጓደኞቻቸሁ ሽር አድርጉ በሌላ ታሪክ እስከ ምንገናኝ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone
❤️❤️❤️❤️ፍቅር ይስጠን😍
https://telegram.me/geyone
https://telegram.me/geyone