Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
6.39K subscribers
2 photos
4.9K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
በመጪዎቹ አስር ቀናት በአዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል ተባለ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16794/

#Ethiopia | በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ከፍ ያለ ከባድ መጠን ያለው #ዝናብ ሊመዘገብ እንደሚችልም ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በመጪዎቹ 10 ቀናት የሚኖረውን የአየር ሁኔታ ትንበያ መረጃን ይፋ አድርጓል፡፡

በኢንስቲትዩቱ አሃዛዊ የትንበያ መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረሪ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የኦሮሚያ፣ የሶማሌ፣ የአማራ፣ ትግራይ እና ጋምቤላ አንዳንድ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ዝናብ በቀጣዮቹ ቀናት ይኖራቸዋል፡፡

በደቡብ ፣ በደቡብ ምስራቅ ፣ በምስራቅ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ለመዘገብ ይችላልም ብሏል የተቋሙ መረጃ፡፡

አሃዛዊ የአየር ትንበያ መረጃው ከነገ ሚያዚያ 23 ቀን እስከ ግንቦት 2 ያሉትን 10 ቀናት የተመለከተ ነው ተብሏል፡፡
#shegerFm

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ፍሬ ከናፍር

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16796/

#Ethiopia | ‹‹ ከፍቅር ጋር ለመጣበቅ ወስኛለሁ፡፡ ምክንያምቱም ጥላቻ ሊሸከሙት የማይችሉት ታላቅ ቀንበር ነውና፡፡ ››

ዶ/ር ማርቲን ሉተርኪንግ

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ለዓባይ ህዳሴ ግድብ ተምሳሌታዊ አሻራ ያኖሩት ጀግና አርፈዋል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16798/

💔

#Ethiopia | ከዓባይ ህዳሴ ግድብ ጅማሮ አንስቶ እስከ ህልፈታቸው ድረስ፣ ፕሮጀክቱም ከዘጠና ስምንት በመቶ በላይ እስከደረሰበት እለት ድረስ በዬወሩ ከሚያገኙት የጡረታ ደሞዝ ላይ ተከታታይ ወርሃዊ ቦንድ በመግዛት ላለፉት 14 ዓመት ሳያቋርጡ ለግድቡ ተምሳሌታዊ አሻራቸውን ያኖሩት አቶ ፋንታ መስተሳዕል መሰረት በተወለዱ በ 77 ዓመታቸው የማረፋቸው አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል።

ጡረተኛ አቶ ፈንታ መስተሳዕል ነዋሪነታቸው በደብረ-ማርቆስ ከተማ ሲሆን፣ በመንግስት ሰራተኝነት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ተቀጥረው በተለያዩ አካባቢዎች የሚጠበቅባቸው ሀላፊነት በታማኝነት የተወጡ መሆናቸውን የግድቡ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት መረጃ ይጠቁማል፡፡

በመጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ታላቁ የዓባይ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሲጀመር በአርአያነቱ የሚጠቀስ አሻራቸውን በታሪካዊው ግድብ ፕሮጀክት ላይ ህይወታቸው እስካለፈበት ዕለት ድረስ ሳያቋርጡ የግድቡን ቦንድ በመግዛት በድምሩ አንድ መቶ ስልሳ ስምንት ሺ (168,000) ብር ማበርከት ችለዋል፡፡

አቶ ፈንታ መስተሳዕል መሰረት ግድቡ ተፈፅሞ ለማየት ያላቸው ጉጉት ሊሳካ ጥቂት ሲቀረው ሚያዚያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል፡፡ ቀብራቸውም ሚያዝያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በደብረ ማርቆስ ከተማ በወንቃ ቀበሌ በወንቃ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል፡፡

የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በአመራሩ እና በሰራተኞች ስም የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
ለመላ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው መፅናናት ይሁን

#የዓባይልጅ
#GERD
#ኢትዮጵያ

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በአገዉ ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል ከፍተኛና ዉስብስብ ቀዶ ህክምና ተሠራ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16800/

#Ethiopia | በአንገቱ ላይ በግራ በኩል በወጣ እብጠት ከ10 ዓመት በላይ ሲሰቃይ የነበረ ወጣት የቀዶ ህክምና እና ከአንገት በላይ ህክምና ስፔሻሊስቶች በተመራ የህክምና ቡድን ለዓመታት ሲሰቃይ ከነበረበት ስቃይ ሊገላገላገል የቻለ ሲሆን እብጠቱ በቀኝ ካሮቲድ ስፔስ (carotid space) ውስጥ የተነሳ እና የደም ስሮችን ገፍቶ የተጫነ ነበር::

በአሁኑ ሰዓት ታካሚያችን በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኝ ሲሆን ታካሚዉና ቤተሰቦቹ ባገኙት የህክምና አገልግሎት እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል

ሆስፒታሉም በዚህ ከፍተኛ ኦፕራሲዮን ለተሳተፈዉ የህክምና ቡድን ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል።

በቀዶ ህክምናው የተሳተፉ አባላት
1. ዶ/ር እንየው መብራቱ – የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት
2. ዶ/ር ዮሐንስ አዳሙ- ከአንገት በላይ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት
3. አቶ አቡኑ – አንስቴቲስት
4. አቶ ዘመን – አንስቴቲስት
5. ሲ/ር መዲና ሀሰን – ስክራብ ነርስ
6. አቶ መብራቱ ና መልካሙ – ሰርኩሌት ነርስ
7. እንዲሁም የሆስፒታሉ ዲያግኖስቲክ ባለሙያዎች በሙሉ::

አገዉ ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል
የጤንነትዎ ቋሚ ካፒታል !!
https://www.facebook.com/share/p/15aYFbc5rg/

ማሳሰቢያ ምስሉ በታካሚያችን ፈቃደኝነት የተለጠፈ ነው ፡ ፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
“ባለፉት 8 ዓመታት እንደ ላሚን ያማል ዓይነት ድንቅ ተጫዋች አይቼ አላውቅም” – ሲሞን ኢንዛጊ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16803/

#Ethiopia | “ባለፉት 8 ወይም 9 ዓመታት እንደ ላሚን ያማል ዓይነት ድንቅ ተጫዋች አይቼ አላውቅም” ሲሉ የኢንተር ሚላን አሠልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ ለተጫዋቹ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ዛሬ ምሽት በተደረገው የሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ባርሴሎና ኢንተር ሚላንን በሜዳው አስተናግዶ 3 አቻ ተለያይቷል።

በጨዋታው የባርሴሎናው አዳጊ ተጫዋች ላሚን ያማል ድንቅ ብቃቱን ያሳየ ሲሆን ጠንካራ የሚባለውን የኢንተር ሚላን የተከላካይ መስመር አታልሎ በማለፍ ለክለቡ አንድ ግብ አስቆጥሯል።

የ17 ዓመቱ ላሚን ያማል በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ታሪክ በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ግብ ያስቆጠረ በዕድሜ ትንሹ ተጨዋች ሆኗል።

በዚህ ብቃቱ የተደነቁት የኢንተር ሚላኑ አሠልጠኛል ሲሞን ኢንዛጊ፣ “የእሱን እንቅስቃሴ ለመግባት ሁለት እና ሦስት ተጫዋችን መመደብ ነበብን” ሲሉ ከጨዋታው በኋላ ተናግረዋል።

“እንደ ላሚን ያማል ያሉ ባለድንቅ ተሰጥኦ ተጫዋቾች በየ50 ዓመቱ አንዴ የሚከሰቱ ናቸው” ሲሉም ነው አድናቆታቸውን የገለጹት።

የባርሴሎናው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ላሚን ያማል በ17 ዓመቱ ዛሬ 100ኛ ጨዋታውን ማድረግ ችሏል።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
#ታሪክ_ተሰርቷል_የአባቶቻችን_ቃል_በልጆቻቸው_ተፈጽሟል_እንኳን_ደስ_አላችሁ_እንኳን_ደስ_አለን

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16805/

የታሪካችን ማሳያ ማኅደር፣የከፍታችን ፈርጥ የሆነው ደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ ማብሰሪያ መርሐ ግብር እሁድ ሚያዝያ 26/2017 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በጉተራ አዳራሽ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በድምቀት ይካሄዳል

በዚህ ታላቅ የምረቃ ማብሰሪያ መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ተጋባዥ መምህራን ፣ዘማርያንና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት #የምረቃው_ብስራት_ችቦ_ይለኮሳል
በዚህ ታሪካዊ መርሐ ግብር ላይ እርሶም እንዲገኙ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።
የመግቢያ ትኬት በደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እና በሁሉም አድባራትና ገዳማት ንዋየ ቅድሳት መሸጫ ቦታዎች ያገኛሉ።

ኢትዮጵያዊ ሱራፊ፣ ሐዲስ ሐዋርያው ጻዲቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የቀጠሮ ሰው ይበሉን

እሁድ ሚያዝያ 26/2017ዓም ከ6:00 ሰዓት ጀምሮ በወላይታ ሶዶ ጉተራ አዳራሽ እንገናኝ
የደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም
ትኬቱን ለማግኘት :- 0910700835
:- 0924030101
:- 0904825039

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አዲሱ የአውሮፕላን ማረፊያ ምን በረከት ይዞ ይመጣል?

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16807/

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ግዙፍ ያለውን የአውሮፕላን ማረፊያ በሰባት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ሊገነባ መሆኑን አስታውቋል።

አየር መንገዱ ግንባታውን ለማስጀመር ዳር ከተባለ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ጋራ የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፤ ግንባታው በሁለት ምዕራፎች ተከፍሎ እንደሚገነባም ገልጿል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ 60 ሚሊዮን ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችለው የአውሮፕላን ማረፊያ ይገነባል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ ደግሞ 50 ሚሊዮን ተጓዦችን የሚያስተናግደው ሁለተኛው ምዕራፍ ይገነባል። የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ በአምስት ዓመት ውስጥ ማለትም እስከ 2022 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በቢሾፍቱ አቅራቢያ ይገነባል የተባለው ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሦስት ሺህ 500 ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፍ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ግዙፍ የአየር መንገድ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ስኩዌር ሜትር ላይ የሚያርፍ የመንገደኞች ተርሚናል፣ 126 ሺህ 190 ስኩዌር ሜትር ላይ የሚያርፍ ለአየር መንገዱ ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማት እንዲሁም 100 ሺህ ስኩዌር ሜትር ላይ የሚያርፍ የጭነት አገልግሎት መስጫ እንደሚያካትት ገልጸዋል።

አዲሱ በቢሾፍቱ አቅራቢያ የሚገነባው አውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ጋር በፈጣን መንገድ እንዲሁም በፈጣን ባቡር እንደሚገናኝ ተናግረዋል።

የሚገነባውን የኤርፖርት ሲቲ ስፋት እና ጠቀሜታ ለመረዳት አሁን ያለውን የቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን የመሠረተ ልማት ውስንነት ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው ያሉት አቶ መስፍን፤ የአየር መንገዱ ዕድገት በጨመረ ቁጥር ለአውሮፕላን ማረፊያው የተለያዩ የማስፋፊያ ሥራዎች ሲከናወኑ ቢቆይም፤ በዓመት 25 ሚሊዮን ተጓዦችን ማስተናገድ በሚችልበት የመጨረሻ አቅሙ ላይ መድረሱን አቶ መስፍን አስታውቀዋል።

ከእዚህ መነሻነትም የአየር መንገዱን እድገት እና የመንገደኞችን ቁጥር መጨመር ታሳቢ ያደረገ ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ (ኤርፖርት ሲቲ) መገንባት የግድ መሆኑን በማመን ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረው፤ አውሮፕላን ማረፊያው ከትራንስፖርት አገልግሎት ባለፈ ሆቴሎችን፣ የገቢያ ማዕከሎችን፣ የቢሮ ቦታዎችን እና የመኖሪያ አካባቢዎችን የሚያጠቃልል ትልቅ “የኤርፖርት ሲቲ” ዋና አካል እንዲሆን ታስቦ የሚገነባ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለመሆኑ የኤርፖርት ሲቲው መገንባት ከንግድ አንፃር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ምን ሊሆን ይችላል? ስንል የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችን ጠይቀናል።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ሞላ አለማየሁ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ኤርፖርት ሲቲው ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ በዓመት 125 ሚሊዮን መንገደኞችን በአየር ትራንስፖርት ማስተናገድ ትችላለች። 100 ሚሊዮኑ በኤርፖርት ሲቲው የሚስተናገዱ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 25 ሚሊዮን ደግሞ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ይስተናገዳሉ።

ይህም ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላት የንግድ ግንኙነት እንዲቀላጠፍና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንድትሆን ያደርጋታል ያሉት ሞላ (ዶ/ር)፤ በእዚህም ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች የሀገሪቱን እምቅ አቅም እንዲመለከቱ በማድረግ የንግድ አማራጮች በግልጽ እንዲታዩ ሰፊ እድል ይፈጥራል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ በቀላሉ የሚበላሹ የግብርና ምርቶችን ወደ ሌሎች ሀገራት የምትልከው በአየር ትራንስፖርት ነው። ከእዚህ አንፃር የቢሾፍቱ ኤርፖርት ሲቲ መገንባት የካርጎ አቅምን የሚጨምር በመሆኑ የሚበላሹ ምርቶችን በብዛት ወደ ውጭ ሀገር ለመላክና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት ይረዳል ብለዋል።

ከቡና ምርት ቀጥሎ አበባን ወደ ውጭ የመላክ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን አንስተው፤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ ተወዳዳሪ በሆነችባቸው ምርቶች ላይ በልጣ እንድትገኝ የኤርፖርት ሲቲው መገንባት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው ምርት ወደ ውጭ ከሚላከው አንፃር ዝቅተኛ ነው። ይህም ሀብት ወደ ውጭ ሀገራት እንዲሄድ በማድረግ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል ያሉት ሞላ (ዶ/ር)፤ ኤርፖርት ሲቲው አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ውጪና ገቢ ንግድን ለማመጣጠን እንደሚረዳ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን እያሳደገች ትገኛለች። ይህም የግብርና ምርቶችን ወደ ውጭ ሀገራት የሚልኩ አርሶ አደሮችን በተለይ በቡናና በአበባ ምርት ላይ የተሰማሩትን እንደሚጠቅም ገልጸው፤ አርሶ አደሮችና ነጋዴዎች ሌሎች የኤክስፖርት አማራጮችን እንዲመለከቱ እድል እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

አሁን ያለው የቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ያለው አቅም ኢትዮጵያ ወደፊት ከሚያስፈልጋት አቅም ጋር ሲነፃጸር ዝቅተኛ እንደሚሆን ገልጸው፤ አሁን ላይ የኢትዮጵያን የወደፊት አቅም የሚመጥን አየር ማረፊያ ለመገንባት የሚደረገው ጥረት ጊዜውን የዋጀ እና ሀገሪቱን የሚመጥን ተግባር መሆኑን ነው የተናገሩት።

የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኤርፖርት ሲቲው በዓመት መቶ ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ ይችላል ማለት በንግድ ዘርፉ ላይ የሚኖረው ሚና ቀላል የሚባል አይደለም። ከእዚህ አንፃር ኤርፖርት ሲቲው ራሱን የቻለ የኢኮኖሚ ዞን የመሆን እድል እንዳለው ጠቁመዋል።

በተለይ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና እየተስፋፋ በሚሄድበት ጊዜ የአየር ትራንስፖርት ተፈላጊነት ይጨምራል ያሉት ቆስጠንጢኖስ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ባለበት ሁኔታ ወደ ኢትዮጵያ ስድስት ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የንግድ እንቅስቃሴ እንደሚያመጣ መረጃዎች ያሳያሉ ነው ያሉት።

ከእዚህ በመነሳት ኤርፖርት ሲቲው የኢትዮጵያን የንግድ እንቅስቃሴን በእጥፍ ሊያሳድግ እንደሚችል የጠቆሙት ቆስጠንጢኖስ (ዶ/ር)፤ ኤርፖርት ሲቲው በውጭ ምንዛሪ ግብይት የሚፈጸም በመሆኑ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እንደሚያስገኝ ተናግረዋል።

ይህም ሀገሪቱ በውጭ ንግድ ላይ ተወዳዳሪ እንድትሆን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረው፤ በተለይ የሕክምና ቁሳቁሶችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማንቀሳቀስ የአየር ትራንስፖርት ተመራጭ መሆኑን አንስተው፤ በእዚህ ረገድ ኤርፖርት ሲቲው ተመራጭ እና አትራፊ የሚሆንበት እድል እንዳለ ገልጸዋል።

በኤርፖርት ሲቲ ውስጥ ተሳፋሪዎች ጊዜ ሲኖራቸው ተዘዋውረው እቃ የሚገዙበት ሁኔታ ይፈጥራል። በተለይ ደግሞ በኤርፖርት ሲቲው በርካታ አውሮፕላኖች የሚኖሩ ከሆነ የአየር ትራንስፖርት እና የጭነት የማጓጓዣ ዋጋ የሚቀንስ በመሆኑ ከመርከቦች ክፍያ ጋር ተቀራራቢ ሊሆን ይችላል ነው ያሉት።

የኤርፖርት ሲቲ መሠረተ ልማት መገንባት ከፍተኛ በጀት የሚፈልግ ፕሮጀክት ነው። ወደ ፊት ከሚገኘው ጠቀሜታ አኳያ ፕሮጀክቱን በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚገባ አመላክተው፤ ኤርፖርት ሲቲው የኢትዮጵያን የአቪዬሽ አቅም በሦስት እጥፍ ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት።

እንደ ምሁራኑ አገላለጽ፤ አውሮፕላን ማረፊያው የኢትዮጵያን የንግድ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ ዓይነተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንደ ማግኔት ጎትቶ የሚሰብ ነው፡፡ ይህም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ዕድገት ዘላቂና አስተማማኝ…
#ግሩም_ድግስ_በሀዋሳ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16809/

#አድቬና_ሽር_ጉዱን ጨርሶ እርስዎን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

#አድቬና ቁርጥ እና ላውንጅ
Adveena Bura Maalanna Lawunji

” ሚያዝያ 25 እና 26 ቀን 2017 ዓ. ም ቅዳሜና ዕሁድ በዓይነቱ ለየት ባለ ዝግጅት ይመረቃል ።

#እንኳን_ደስ_አላችሁ ተጋባዥ እንግዶች እና
ዝነኞቹ ድምፃዉያን ሀዋሳ ይከትማሉ። ሸብ ረብ ሞቅ ደመቅ ሽብርቅ ያለ ድግስ በአድቬና ተሰናድቷል::

ቁርጥ ይቆረጣል ጥብስ ይጠበሳል በዓይነት በዓይነቱ የሚበላዉ የሚጠጣዉ ሁሉ ተሰናድቷል። ወገብ ይፈተሻል ጭፈራዉ ይደምቃል ።

ምሽቱን ሊያደምቁልን ተወዳጆቹ ድምፃዊያን
1. ጌዲዮን ዳንኤል
2. ኤደን አይሸሹም
3. ታዴ
4. ወንጊ
5,ብስራት
6,አቡዲ
7,መለሰ እንዲሁም ሌሎችም
ልምምዳቸዉን ጨርሰዉ በፍቅር ከተማዋ ሀዋሳ በሸነና ሊሉ ለእናንተ እየተዘጋጁ ነዉ
#አድቬና ታድሷል ስንል አንቀልድም ።

#ታድሶስ መች ቀረ አድቬና በድምቀት ይመረቃል ….. እርስዎም በክብር ተጋብዘዋል 👇
ዉድ የከተማችን ነዋሪዎች
በዕለቱ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ በመገኘት እየተዝናኑ የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ በክብር ጠርተንዎታል::

#ጠሪዎች
የእናንተዉ
ኢንጂነር አሸናፊ ጉልማ እና ወ/ሮ ሀና ሀይሉ

አዘጋጅ: ፕሮሞተር ቤቲ ሀዋሳ

አድራሻ ሀዋሳ ዋናው ፖስታ ቤት አጠገብ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2026 አሸናፊዎች ቅዳሜ ሚያዚያ 25/2017 ዓ/ም ይፋ ይደረጋሉ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16811/

#Ethiopia | ለዲቪ (Diversity Visa) 2026 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።

NB. የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation Number በማለት አስፈለጊ መረጃ በመሙላት በኢሜል አዲስ ቁጥር ማግኘት ይቻላል።

ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የሚደርስ የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ተዘጋጅቷል። ይህ ቁጥር ብቁ የሆኑ ሀገራትን ሁሉ የሚጠቃልል ሲሆን #ኢትዮጵያም አንዷ ናት።

የዲቪ ሎተሪ መውጫ መድረሱን ተከትሎ ” የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል ፣ ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው ምንደውለው / ይህን ኢሜል / ቴክስት የምንልከው ” በማለት የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች ሊጠነቀቁ ይገባል።

አንድ አመልካች ዲቪ 2026 ደርሶት እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማወቅ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ከላይ የተጠቀሰው ድረገጽ ብቻ ነው።

አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ (ኢትዮጵያ ጨምሮ) ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 55 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።
#Tikvah

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በመኪና አደጋ የሥድስት ሰዎች ሕይዎት አለፈ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16813/

#Ethiopia | በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዋጫሌ ወረዳ ሙከጡሪ ከተማ አቅራቢያ መቼላ ቀበሌ ቄሌምቶ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ እስከ አሁን የሥድስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

ከሟቾች በተጨማሪ በ21 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በሌሎች 17 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ታከለ ቶሌራ ተናግረዋል፡፡

አደጋው የደረሰው ከሙከጡሪ ወደ ጂዳ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ አይሱዚ ተብሎ የሚጠራው ቅጥቅጥ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከለሚ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው ነው ብለዋል፡፡

አደጋው 7 ሠዓት 30 ላይ መድረሱን ለፋና ዲጂታል ያረጋገጡት ኃላፊው፤ የአደጋውን ክብደት ጠቅሰው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመላክተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የደረጃ ‘ሀ’ እና ‘ለ’ ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ ካላቀረቡ አገልግሎት አይሰጣቸውም ተባለ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16815/

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከመጪው በጀት ዓመት ጀምሮ ሁሉም የደረጃ ‘ሀ’ እና ‘ለ’ ግብር ከፋዮች ሥርዓት ያለው የሒሳብ መዝገብ ካላቀረቡ እንዳይስተናገዱ የሚያስገድድ ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ።

የቢሮው የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ዋቢ አድርጎ ሪፖርተር እንደዘገበው የአዋጅ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 እነዚህን ግብር ከፋዮች የሒሳብ መዝገብ እንዲይዙ ያስገድዳል። ሆኖም በርካታ በተለይም የደረጃ ‘ለ’ ግብር ከፋዮች ገቢያቸው በግምት እንዲወሰንላቸው እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የሒሳብ መዝገባቸውን በአግባቡ ያላቀረቡ ነጋዴዎች ከቢሮው ምንም ዓይነት አገልግሎት እንደማያገኙ አቶ ሰውነት አስጠንቅቀዋል።

#ቅዳሜገበያ

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
መጪውን የ ፋሲካ በዓል አስሞልክቶ ከ 2,000,000 ብር በላይ ቅናሽ ይጠቀሙ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16817/

ይህ የምስራች ለውድ ደንበኞቻችን ስናቀርብ በታላቅ ደስታ ነው::

📌📌 በ ቁጥር 3ሳይት በሳርስ ዓደይ አበባ B+G+7
የሆነው ህንፃችን ላይ ከረጅም አከፋፈል ጋር እንጠብቆታለን!
ያስተውሉ ብልሆች የ እድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ለውስን ቤቶች ብቻ የቀረበ ዕድል ሞሆኑ ይገንዘቡ!

‘አልቲማ ሪል እስቴት’

“ህልምዎን ይኑሩ!”

“Live Your Dreams!”

ለበለጠ መረጃ :-. ☎️0996000000 / 0995222222

➡️Website: http://www.ultimaet.com

➡️Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61568957484689

➡️Whatsapp: https://whatsapp.com/channel/0029VawOxno545uoGPoLfH3X

➡️Telegram: https://t.me/ultimarealestate1

➡️YouTube: https://www.youtube.com/@UltimaRealestate

➡️ TikTok: tiktok.com/@ultimareal.estate

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በተለያዩ የመዋብያ ዓይነቶች እና አርቴፊሻል ፀጉር በመጠቀም እራሱን ወደ ሴት ቀይሮ የማጭበርበር ተግባር ሲፈፅም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16819/

#Ethiopia | በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ገለምሶ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በተለያየ የመዋብያ ዓይነቶች እና አርቴፊሻል ፀጉር በመጠቀም እራሱን ወደ ሴት ቀይሮ የማጭበርበር ተግባር ሲፈፅም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታዉቋል፡፡ብስራት ሬዲዮ ከምዕራብ ሀረርጌ ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮምኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንዳመለከተው ተጠርጣሪ ስንታየሁ አስቻለው የተባለው የ20 ዓመት ወጣት በተለያዩ የመዋቢያ አይነቶች እና አርቴፊሻል ፀጉር በመጠቀም እንደዚሁም የሴት ረጅም ቀሚስ በመልበስ የማጭበርበር ተግባር ሲፈፅም በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉ አመላክቷል፡፡

ተጠርጣሪው ረጂም ቀሚስ በማድረግ የሴት ቦርሳ በማንጠልጠል እራሱን በመዋቢያ ወደ ሴትነት ቀይሮ ከፍተኛ የማጭበርበር ተግባር ሲፈፅም እንደነበረ ተገልጿል። ተጠርጣሪው ለምን እራሱን ወደ ሴትነት እንደቀየረ ሲጠየቅ ከሚከታተሉኝ ሰዎች ለማማምለጥ ነው ቢልም ፖሊስ ግን ተጠርጣሪው በተለያየ መዋቢያዎች እና የአርቴፊሻል ፀጉር እና ረጅም ፀጉር በመልበስ ሙሉ በሙሉ ሴት መስሎ ወንድን በመቅረብ ካማለለ በኋላ አብረው እንዲያሳልፉ በማድረግ የእጅ ስልክ እና ቦርሳቸውን ነጥቆ በመሠወር ተግባር ላይ በትላልቅ ከተሞች ላይ ተሰማርቶ ድርጊቱን ሲፈፅም አይቀርም በሚል የፖሊስ ጥርጣሬ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ተገልጿል።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ሲውል በቦርሳ ውስጥ በርካታ የሴት መዋቢያ ቁሳቁሶች እና ሽቶ ፣ ቅባቶች የተገኙ ሲሆን ባጃጅ ውስጥ የተሳፈሩ ተሳፋሪዎች እና አሽከርካሪው ተጠርጣሪው ድምፁን ወደ ሴት ለመቀየር በሚያደርገው ሙከራ ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ በቁጥጥር መያዙን ብስራት ሬዲዮ ያገኘዉ መረጃ አመላክቷል። ይህ በመዋቢያ እና በአርቴፊሻል ፀጉር እንደዚሁም ረጅም ቀሚስ በመልበስ እና ቦርሳ በማንጠልጠል ራሱን ወደ ሴትነት የቀየረው ግለሰብ ላይ አስፈላጊው ምርመራ ተጣርቶ በቅርብ ቀን ለፍትህ አካል እንደሚላክ ተገልጿል፡፡

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
እንኳን ለላባደሮች ቀን አደረሳችሁ!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16821/

የሚሰሩ እጆች ሁሉ ጥበበኞች ናቸው!!

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ልብሶችን ለመግዛት እቀያየር ሲለካ የነበረ ሰው ከበድ ባለ ቆዳ በሽታ ተያዘ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16823/

#Ethiopia | ልብሶቹን ከገዛ በኋላ ሳያጥብ ከለበሳቸው በኋላ ቆዳው በሽፍታዎች እና በእባጮች ተሸፈነ።

የቆዳ ሐኪሞች ሁሉም ልብሶች ከተገዙ በኋላ መታጠብ እንዳለባቸው ያስጠነቅቃሉ።

በፋብሪካ ውስጥ የሚመረቱ ጨርቆች የቆዳ መቅላት እና ማሳከክ ሊያስከትሉ በሚችሉ የተለያዩ ቆሻሻን እና ውሃን መከላከያ ኬሚካሎች ይታከማሉ።

እንዲሁም ከእርስዎ በፊት ልብሱን ለመግዛት ለክቶት የነበረው ሰው ብዙ የቆዳ በሽታዎች ሊኖርበት ይችላል – ለምሳሌ በቀላሉ የቆዳ ፈንገስ ሊይዝዎት ይችላል።
#FidelPost
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ታዳጊዋ የዲጂታል ዓለም ተስፋ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16825/

#Ethiopia | ተማሪ ክርስቲና ጳውሎስ ትባላለች፡፡ የልደታ ካቶሊክ ትምህርት ቤት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ናት፡፡

ተማሪ ክርስቲና ትምህርት ቤቷን ወክላ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በ10ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ የተሳተፈች ታዳጊ ናት።

አሁን ላይ የሳይበር ደህንነት ዓለም አቀፍ ስጋት መሆኑን የምትገልፀው ተማሪ ክርስቲና የፈጠራ ስራዋ ‘ጉድ ፕራይቬሲ ፕላትፎርም’ የተሰኘ መረጃን መደበቅ የሚያስችል ሲስተም መሆኑን ትገልፃለች፡፡

አሁን ባለንበት ዘመን ሁሉም ሰው የዲጂታሉን ዓለም ተቀላቅሏል የምትለው ተማሪ ክርስቲና ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር ለተያያዙ ጥቃቶች መፍትሔነቱን ትጠቁማለች፡፡

ከዚያ ባሻገር ለትምህርት ቤቶች፣ ለትምህርት ቢሮዎችና ሀገር አቀፍ ፈተና አዘጋጅ ድርጅቶች ጠቀሜታ ያለው ሶፍት ዌር መሆኑን ታስረዳለች፡፡

ፈተና ተሰረቀ ሲባል እንደሚሰማ ጠቁማ ይህን ችግር ለመቅረፍ የእርሷ የፈጠራ ስራ አይነተኛ ሚና እንዳለው ትገልፃለች፡፡

የሳይበር ጥቃት ቢደርስ ጥቃቱን ያደረሰው ሰው መረጃን ማግኘት እንዲችል እንደማያደርገው ትናገራለች፡፡

በሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይ ስትሳተፍ ሁለተኛዋ መሆኑን የምትገልፀው ተማሪ ክርስቲና የአምና ተሞክሮዋ ለዘንድሮ ጥሩ መሻሻል እንዳመጣላት ትገልፃለች፡፡

እንደእኔ የፈጠራ ስራ ያላቸው ተማሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ነገሮችን መሞከር አለባቸው የምትለው ተማሪ ክርስቲና፤ ተማሪዎች የፈጠራ አቅማቸውን ትምህርት ቤት እያሉ ማውጣት እንደሚኖርባቸው ትመክራለች፡፡

#Gazette_Plus

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
“መኖር በጊፍት መንደር” በሚል መሪ ቃል ሁለተኛው የሽያጭ ኤክስፖ ተከፈተ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16827/

📌 4.5 ሚሊዮን ብር ቅናሽ ተደርጓል

#Ethiopia | ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ተወዳዳሪ የሆነው ጊፍት ሪል ስቴት “መኖር በጊፍት መንደር” በሚል መሪ ቃል ሁለተኛው የሽያጭ ኤክስፖ ከዛሬ ሚያዝያ 23 እስከ ሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሄድ አሳወቀ።

የጊፍት ሪልስቴት የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ብርቁ ይርጋ እንደገለጹት ጊፍት ሪል ስቴት ለገዢዎች እስከ 30 በመቶ የሚደርስ የአጭር ጊዜ ቅናሽ ያቀረበ ሲሆን ከ9 በመቶ እስከ 25 በመቶ ቅድመ ክፍያ በመክፈል የቤቶቹ ባለቤት መሆን እንደሚቻል እና የዚህን ታላቅ ቅናሽ ተጠቃሚ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል።

የጊፍት ሪል ስቴት የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ምክትል ዳይሬክተር ወይዘሪት ሮዛ ዘውዱ በበኩላቸው በለገሃር በተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ሽያጭ ከአንድ መቶ በላይ ቤቶች መሸጣቸውን ጠቁመው ሁለተኛው ዙር ሽያጭ በመካሄድ ላይ በመሆኑ ሁሉም ሰው የቤት ባለቤትነት ህልሙን እውን ለማድረግ እና ትርፋማ የሆነ የዕድሜ ልክ ኢንቨስትመንት ባለቤት ለመሆን ወደ ሽያጭ ቢሮዎቻቸው በመምጣት እንዲጎበኝ ጥሪ አቅርበዋል።

ጊፍት ሪል ስቴት አዳዲስ ሦስት መንደሮችን ጨርሶ ለቤት ባለቤቶች ካስረከበ በኋላ በአራተኛው የጊፍት ሜትሮፖሊታን መንደር በለገሃር 4 ሺህ ቤቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም በሁለተኛና ሶስተኛ ዙሮች የሚገነቡ 8 ሺህ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን እንዲሁም በ6 ኪሎ፣ በቦሌ መድሃኒዓለም፣ በፊጋ፣ በ22 ማዞሪያ፣ በተክለሃይማኖት፣ በሲኤምሲ እና በሌሎች አካባቢዎች 4 ሺህ ቤቶችን በአጠቃላይ ከ16 ሺህ በላይ ቤቶችን ለሽያጭ አቅርቧል።

እነዚህ ግንባታዎች በሚከናወኑባቸው መንደሮች ትምህርት ቤቶች፣ የህክምና ተቋማት፣ የገበያ ማዕከላት፣ የሀይማኖት ተቋማት ፣ የመዝናኛ ስፍራዎች እና የመኪና ማቆሚያዎች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

ጊፍት ሪል ስቴት እስካሁን በ165 ሺህ ካሬሜትር ላይ በሲኤምሲ እና ፈረስ ቤት ሦስት ትላልቅ መንደሮችን ገንብቶ ለማኅበረሰቡ ማስረከብ መቻሉ የተመላከተ ሲሆን ዓለም የደረሰበትን የግንባታ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ዘመናዊ እና ቅንጡ የመኖሪያና የንግድ አፓርትማ መንደሮችን እየገነባ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
“የቤት ስራ አልሰራሽም” በሚል በአንዲት ተማሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ ቅጣት የፈጸመችው መምህርት በቁጥጥር ስር ዋለች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16829/

#Ethiopia | በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በሰላም በር ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2ኛ ክፍል ተማሪን “የቤት ስራ አልሰራሽም” በማለት ተገቢ ያልሆነ ቅጣት በፈጸመችው መምህርት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለEBC DOTSTREAM አስታውቋል።

ቢሮው ጥፋቱ ሰለመፈፀሙ መረጃ እንደደረሰው አፋጣኝ እርምጃ መውሰዱን የትምህርት ቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነግሮናል።

ትውልድን ከመቅረፅ፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ተተኪ ዜጋን ከመፍጠርና የቀለም እናት ከመሆን ባለፈ ከእናት የማይጠበቅ፤ ያለንበትን ዘመንና ወቅት የማይዋጅና የማይመጥን መሰል ድርጊት መፈጸም ተገቢ አይደለም ብሏል።

ድርጊቱ እንደተፈጸመ ጥብቅ ክትትል በማድረግ ወዲያውኑ የማጣራት ስራዎች እንዲሰሩና መምህርቷ በህግ ከለላ ውስጥ እንድትሆን መደረጉም ተገልጿል።

ጉዳዩም በህግ አግባብ እንዲታይና ፍትህ እንዲያገኝ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ጉዳቱ የደረሰባት ተማሪም ህክምና አግኝታ በጥሩ የጤንንነት ሁኔታ ላይ የምትገኝ ሲሆን በነገው እለትም ትምህርቷን ትጀምራላች ተብሏል፡፡

መሰል ችግሮች እንዳይፈጸሙና ለሌሎችም ትምህርት እንዲሆን ይህ ርምጃ መወሰዱም ነው የተገለጸው።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በ27 ዓመታት ቆይታ አንድም ቀን ከስራዉ ያልቀረዉ ግለሰብ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16831/

#Ethiopia | ኬቨን ፎርድ የተሰኘዉ አሜሪካዊ ጎልማሳ ለ27 አመታት በስራ ገበታዉ ላይ ሲቆይ ለአንድም ቀን ቀርቶ አያዉቅም::

የ54 ዓመቱ ኬቪን ፎርድ የእድሜዉን ግማሽ የሰራበት መስሪያ ቤት ደግሞ የበርገር እና ሌሎች ምግቦች አቅራቢ የሆነው በርገር ኪንግ ነው::

ፎርድ ለ27 አመታት በስራዉ ላይ ሲቆይ ታድያ አንዲትም ቀን በእረፍትምም ይሁን በህመም ምክንያት ከስራ ገበታዉ ዉጭ ሆኖ አያውቅም ይላል ከዩ .ኤስ.ቱዳይ (USTODAY) የተገኘው መረጃ::

በነዚህ አመታት ኬቨን ፎርድ ከባድ ህመም አጋጥሞት የማያዉቅ ሲሆን የህመም ስሜቶች ቢኖሩም በዛው በስራ ቦታ መቆየትን ይመርጣል::

ሰዉ የዘራዉን ያጭዳል እንዲሉ ታድያ የታታሪዉን ሰራተኛ ኬቨን ፎርድ ትጋት የተመለከተዉ መስሪያ ቤቱ እና የስራ አጋሮቹ በስራዉ ላይ ላሳያዉ ጥንካሬ እና ብርታት እዉቅና ሊሰጡት ይወስናሉ::

በጎርጎሮሲያኑ 2022 መጀመሪያዎቹ ወራት አካባቢ ህይወቱን የቀየረዉ አጋጣሚ ተከሰተ::

በጥቃቅን የስጦታ እቃዎች የተሞላ አነስተኛ ቦርሳ ነበር የተሰጠዉ::

ኬቨን ተንቀሳቃሽ ስልኩን ያነሳና ይህንን ስጦታ ለአለም ለማሳየት ይወስናል::

የፊልም መመልከቻ ትኬቶች እና ሌሎችም የሚገኙበትን ይህን ቦርሳ እየከፋፈተ ምስጋናዉን በፈገግታ እየገለጸ ይታያል::

ይህንን ተንቀሳቃሽ ምስል ኢንተርኔት ላይ ይጭነዋል:: ይህንን ምስል ታድያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይመለከቱታል::

ነገር ግን በኢንተርኔት ላይ በተንቀሳቃሽ ምስል የተመለከቱት ሁሉ እዉቅናዉ የሱን ትጋት እና ልፋት የሚመጥን እንዳልሆነ የብዙዎች እምነት ነበር::

ብዙዎችም ለትጋቱ እና ታማኝነቱ ልናበረታታዉ ይገባል በማለት ድጋፍ ለማድረግ ይወስናሉ::

የኬቨን ፎርድ ልጅ የሆነቸው ሴሬና የገቢ ማሰባሰቢያ ( ጎፈንድሚ ) ገፅ ከፈተች::

በዚህ ድጋፍ በ2022 አመት አጋማሽ ላይ ከአሜሪካውያን እና ሌሎች ሃገርት ዜጎችም በተደረገ ርብርብ 450 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ገንዘብ ተሰበሰበለት::

የገንዘብ ችግር ለነበረበት ኬቨን ፎርድ ይህ ትልቅ አጋጣሚ ህይወቱን ቀይሮለታል::

#የኢትዮጵያ_ሬድዮ

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ለእግር ኳስ ተጫወችነት ብቻ የተፈጠረች ነፍስ !

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16833/

#Ethiopia | ልብ በሉ ! ድፍን አለም የሚያወራለት ፣ ይገልጹበት ቃላት የጠፋለት ልጅ ገና 17 አመቱ ነው። መታወቂያና መንጃ ፈቃድ ለማውጣት የማይፈቀድለት ልጅ ነው እንደማለት።

የእግር ኳሱ አለም ሰዎች ከምንጊዜም ኮከቦቹ ክርስቲያኖ ሮናልዶና ሊዮኔል ሜሲ ጋር ያነጻጽሩታል። እሱም ከማንም ጋር አታወዳድሩኝ ይላል። ራሴን መሆነ ፣ የራሴን ብቃት ማሳዬት ፣ ትላልቆቹ ያስመዘገቡትን ታሪክ ለመጻፍ ተግቸ መስራት ብቻ እፈልጋለሁ ብሏል።

ላሚን ያማል ከሜሲም ሆነ ከሮናልዶ ጋር ቢነጻጸር ስህተት አይሆንም። ምክንያቱም እሱ በዚህ እድሜ የሰራው ጫፍ ላይ ያልደረሱ ስለነበሩ። ንፅፅሩን 17 አመት ላይ አቁመን እንመልከተው።

ላሚን በ17 አመቱ 100 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፏል። ያውም ተአምር በሰራበት ምሽት ድፍን 100ኛ ጨዋታ። 22 ግቦችንና 27 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አስመዝግቧል።

ሊዮኔል ሜሲ በዚህ እድሜ ያደረጋቸው ጨዋታዎች ከላኒን በ91 አንሶ 9 ጊዜ ብቻ ተሰልፏል። ያስቆጠረው ግብ ብቻ 1 ሲሆን ያቀበለው ኳስ የለም።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ 18 አመት ሳይሞላው ያደረጋቸው ጨዋታዎች ከላሚን በ81 ያነሱ ናቸው። ፖርቱጋላዊው በ19 ጨዋታ 5 አግብቶ 4 አመቻችቶ አቀብሏል።

ላሚን 17ኛ አመት ልደቱን ባከበረ ማግስት ከሀገሩ ስፔን ጋር የአውሮፓ ዋንጫን አሸንፏል። በጀርመኑ ውድድር ያሳየው ድንቅ ብቃትና ድሉ የልደቱ ስጦታ ነበር።ሜሲም ሆኑ ሮናልዶ ግን በ18 አመታቸው ለብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ያላደረጉ ተጫዎቾች ናቸው።

ይህ ታዳጊ የሰባበራቸው ሪከርዶች የበረከቱ ናቸው። ለባርሴሎና በላ ሊጋው በትንሽ እድሜው የተጫወተ ገና በ15 አመቱ ፣ በትንሽ እድሜው የላ ሊጋው ግብ አስቆጣሪና አቀባይ ነው ፣ በቻምፒየንስ ሊግ በቋሚ አሰላለፍ የገባ ትንሹ ልጅ ነው ፣ በዚሁ መድረክ በጥሎ ማለፍ ፣ ሩብና ግማሽ ፍጻሜ ላይ ግብ ያስቆጠረ ባለ ትንሽ እድሜ ነው።

ላሚን በትንሽ እድሜው ለስፔን ብሄራዊ ቡድን የተጫወተና ግብ ያስቆጠረ ፣ በአውሮፓ ዋንጫ ላይም ግብ ያስቆጠ በእድሜ ትንሹ ተጫዎች የሚሉ ክብሮችን ይዟል።

እናም ሮናልዶም ሆኑ ሜሲ በእሱ እድሜ ያልሰሩትን ያሳካውን ተጫዎች ከነሱ ጋር ማነጻጸሩ ስህትተ አይሆንም። ለልጁ የወደፊት ስኬት መሰናክል እንዳይሆን ከመስጋት ውጪ ። የወደፊቱን ጊዜው ሲደርስ ማየት ነው።

ሜሲና ላሚን ችሎታ ብቻ ሳይሆን የሚያገናኛቸው ብዙ ምክንያት አለ። ሁለቱም በእግር ኳስ ማህጸኑ ላ ማሲያ የተሰሩ ፣ ሁለቱም በግራ እግራቸው ተአምር የሚፈጥሩ ፣ ሁለቱም ከቀኝ ክንፍ እየተነሱ ተጋጣሚን የሚያሸብሩ ናቸው።

ሜሲ የ20 አመት ታዳጊ እያለ አንድ ጨቅላ ህጻን ልጅ ገላ ሲያጥብ የሚያሳይ ፎቶ አለ። ላሚን ነበር። አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ጥበቡን ሁሉ ያወረሰው ያኔ ነው ይባልለታል። ለእግር ኳስ ተጫወችነት ብቻ የተፈጠረች ህይወት ላሚን ያማል።

የኢንተር ሚላኑ አሰልጣኝ ሲሞኒ ኢንዛጊ በ50 አመት አንድ ጊዜ የሚፈጠር ተሰጥኦ ብሎታል። አሰልጣኙ ሀንሲ ፍሊክ ቃላቶቼን ጨርሻለሁ ኢንዛጊ እንዳለው ከሆነም ይህ የተከሰተው በባርሳ ብቻ ነው ብለዋል።

በሁሴን ግዛው

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet