Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
6.25K subscribers
2 photos
4.79K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
468 የቆሙ የወይን ብርጭቆዎችን በጭንቅላቱ በመሸከም የደነሰው ቆጵሮሳዊ ዳንኪረኛ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16606/

#Ethiopia | 468 ያህል የተደረደሩ የወይን ብርጭቆዎችን በራሱ ላይ አስቀምጦ የጨፈረው ቆጵሮሳዊ ዳንኪረኛ ድርጊት በርካቶችን አስገርሟል።

ዲኖስ ካንቲስ የተሰኘው ይህ ሰው በዕለተ ማክሰኞ በአራዲፖ ከተማ በተዘጋጀ ባሕላዊ ድግስ ላይ በስምንት ትሪዎች (ዝርግ ሳህኖች) ላይ የተደረደሩ የወይን ብርጭቆዎችን ያለምንም ድጋፍ ተሸክሞ የመጨፈር አስገራሚ ትርዒት አሳይቷል።

የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ አርስቶቴሊስ ቫላኦራይትስ የተሰኘ ሌላ ቆጵሮሳዊ 319 ብርጭቆዎችን ተሸክሞ በመጨፈር ይዞት የነበረውን ክብረወሰን እንዳሻሻለውም ተነግሯል።

ክብረ ወሰን መዝጋቢው ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ የካንቲስን የእንቅስቃሴ ቪዲዮ እና ሌሎች ማስረጃዎችን ከመረመረ በኋላ በይፋ እውቅና የሚሰጠው ይሆናል።

በሰባት ትሪዎች ላይ ተደራርበው 80 ኪሎ ግራም የመዘኑት 468 ብርጭቆዎች፣ በዳንኪረኛው ጭንቅላት ላይ ቢያንስ ለ10 ሰከንድ ሚዛናቸውን እንደጠበቁ መቆየታቸውን አረጋግጠው እውቅናውን ይሰጡታል ተብሎ ይጠበቃል። መረጃው የዩናይትድ ፕሬስ ኢንተርናሽናል ነው።
#etv

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ስራ ያቆሙ 518 ኢንደስትሪዎች ወደ ማምረት እንዲገቡ ተደርጓል ተባለ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16608/

#Ethiopia | ሁለት መቶ አምስት ኢንደስትሪዎችን ደግሞ በገጠር ማቋቋም መቻሉ ተገልፆል።

ይህ የተባለዉ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የዘጠኝ ወራቱን የስራ አፈፃፀምን በተመለከተ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነዉ።

ተቋሙ በተለያየ ምክንያቶች ስራ አቁመዉ የነበሩ አምራች ኢንደስትሪዎችን ወደ ስራ ለማስገባት መቻሉን ተናግሯል።

የኢንተርፕራይዙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በሰጡት የጋዜጣዊ መግለጫ ለዘርፉ ፈታኝ የሆነዉን የፋይናንስ አቅርቦት ለመፍታት ጥረት መደረጉን አንስተዋል።

6 ቢሊየን ብር ለአምራች ኢንተርፕራይዞች የቀረበ የስራ ማስኬጃ ብድር አቅርቦት ተሰቷል ተብሏል።

ከተወሰደዉ ዉስጥ 95 በመቶ ያህሉ የተወሰዱ ብድሮች መመለስ መቻላቸዉን ተቋሙ ገልጿል ።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት በገጠር የኢንዱስትሪ መስፋፋት ላይ ስራዎች ነበሩት ያሉት አቶ አብዱል ፈታህ የሱፍ በዘጠኝ ወራቱ አፈፃፀም ለ 151 ሺህ ሰዎች የስራ እድል ፈጥረናል ብለዋል።

አዳዲስ ኢንደስትሪዎች በመክፈት ረገድ 2 ሺህ 7 መቶ ሀምሳ ሁለት ኢንደስትሪዎች ማቋቋም ችያለሁ ብሏል።

የአምራች ኢንተርፕራይዞች የደረጃ ሽግግር እያደረኩ ነዉ የሚለዉ ተቋሙ በዚህም በገበያ ትስስር እንዲገኝ ተሰርቷል ተብሏል።

የአምራች ኢንደስትሪዎችን ስራ በተመለከተም ከዉጪ ይገባ የነበረን ምርት በተኪ ምርቶች 1.6 ቢሊየን ዶላር ማዳን መቻሉን ከኢንተርኘራይዙ ሰምተናል።

በተቃራኒው 57 ሚሊየን ዶላር የዉጪ ምንዛሬ ምርቶችን በመላክ ማስገባት መቻሉን ተያያዞ በመግለጫዉ ተገልፆል።
#ethioFm

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በአዋሽብር ፕሮ መገበያየት ያሸልማል!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16610/

ወርቃማውን ፕሮኮይን በመሰብሰብ ሲያሻዎ ወደ ገንዘብ ቀይረው ይገበያዩ አልያም ለወዳጅ ዘመድ በስጦታ ያስተላልፉ።

ወርቃማውን ፕሮኮይን ለመሸለም

• ቢል እና የትምህርት ክፍያ ሲፈፅሙ
• ወደ ዋሌት ገንዘብ ሲያስተላልፉ
• ወደ አዋሽ አካውንት ገንዘብ ሲያስተላልፉ
• የአየር ሰዓት ሲሞሉ

የአዋሽብር ፕሮን ሰው እንዲመዘገብ ሲጋብዙ ወርቃማዋን ፕሮኮይን ይሸለማሉ ለበለጠ መረጃ https://awashbank.com/loyalty-program/ ይግብኙ!

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ሳያውቅ የራሱን የተሰረቀ መኪና መልሶ የገዛው ግለሰብ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16612/

#Ethiopia | ነገሩ እንዲህ ነው ኢዋን ቫለንታይን የተባለ የ36 ዓመት እንግሊዛዊ፤ ጥቁር ቀለም ያለው 2016 Honda Civic Type-R መኪናን በአንድ ሌሊት ከመኪና ማቆሚያ ቦታ ይሰረቃል።

ታዲያ ቫለንታይን በደረሰበት ኪሳራ በጣም አዘነ፤ ነገር ግን መኪናውን በሚመስል ሌላ ተመሳሳይ ሞዴል ተሽከርካሪ ሊተካው እንደሚችል ተስፋ ያደርጋል።

ከዛም ይህ ግለሰብ አንድ ለሽያጭ የቀረበ መኪና በማኅበራዊ ሚዲያ ቀርቦ ይመለከታል። የመኪናው ቀለም፣ የተመረተበት ዓመት እና የጭስ ማውጫ ስርዓት ከተሰረቀበት መኪና ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ደሞ ቀልቡን ይስበዋል።

የጠፋው መኪና እና አዲስ ሊገዛ ያሰበው መኪና ታርጋዎች የተለያዩ ስለነበሩ መኪናውን ለመውሰድ ከ26 ሺህ ዶላር በላይ እስኪከፍል ድረስ ስለ ተመሳሳይነቱ ብዙ አላሰበም ነበር።

እናም ቫለንታይን መኪናውን ከገዛ በኋላ ወደ ቤት ሲደርስ አንዳንድ ያልተለመዱ ነገሮችን ማስተዋል ይጀምራል። መኪና ውስጥ የድንኳን ሚስማር እና አንዳንድ የገና ዛፍ ጽዶችም ይመለከታል፤ በዚህ ጊዜ ታዲያ ሁሉም ነገር ከተሰረቀ መኪናው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ያስተውላል።

በመሆኑም ቫለንታይን የመኪናውን የቦርድ ጂ.ፒ.ኤስ ለመፈተሽ አስቦ ይህን አደረገ እናም ከዚህ በፊት የነበረችው የጠፋችው መኪናው መሆኗን ለማወቅ አስተማማኝ መረጃ ሳያገኝ ይቀራል።

ነገር ግን ግለሰቡ ጥርጣሬው እረፍት ሊሰጠው ባለመቻሉ፤ በመጨረሻም ግለሰቡ ተሽከርካሪውን ወደ ሆንዳ (Honda) መኪና አከፋፋይ ወሰደው።

እዚያ ያሉ ባለሙያዎችም መኪናውን ፈትሸው የተሽከርካሪ መለያ ቁጥሩ የተቀየረና የውሸት መሆኑን እንዲሁም መኪናው ከቫላንታይን የተሰረቀው መኪና መሆኑን ያረጋግጣሉ።

መኪናው በአሁኑ ጊዜ በፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን ምርመራው ሲጠናቀቅ መኪናው ለቫላንታይን ኢንሹራንስ ኩባንያ ይሰጣል መባሉን ዩፒአይ ዘግቧል።
#etv
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ዜና እረፍት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16614/

#Ethiopia | አቶ ግርማ ደምሴ ዲነግዴ ከአባታቸው ከአቶ ደምሴ ዲነግዴ ከእናታቸው ከወይዘሮ ዘነቡ ዳኜ በቀድሞ አጠራር በአርሲ ክፍለ ሀገር በዲገሉና ጢጆ ወረዳ ቡርቁቱ ቀበሌ ገበሬ ማኀበር ታህሳስ 29 ቀን 1949 ዓ.ም ተወለዱ።

አቶ ግርማ ደምሴ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በሀገር ውስጥ ከፍተኛ ህክምና ሲረዱ ቆይተው ሚያዝያ 19 ቀን 2017ዓ.ም ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል።

የቀብር ስነ- ስርዓታቸው ረቡዕ ሚያዝያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በአሠላ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6:00 ሰዓት ቤተሠቦቻቸው ፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የቅርብ ጓደኞቻቸው በተገኙበት ይፈጸማል።

ቤተሠቦቻቸው

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ሊቨርፑል የዋንጫ ድሉን ከደጋፊው ጋር ያከብራል !

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16616/

#Ethiopia | የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ትላንት ምሽት ሀያኛ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫውን ማሳካቱን በይፋ አረጋግጧል።

ሊቨርፑል የፕርሚየር ሊግ ዋንጫ ድሉን ከደጋፊው ጋር በሚያዘጋጀው የጎዳና ላይ ዝግጅት ለማክበር ማሰቡን አስታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ተጨዋቾቹ በክፍት ባስ ሊቨርፑል ከተማን እየተዟዟሩ ድሉን ከደጋፊዎቻቸው ጋር እንደሚያከብሩ ተገልጿል።

በጎዳና ላይ ክብረበዓሉ የቀድሞ የቡድኑ ታሪካዊ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የድል ክብረበዓሉ ሊጉ በተጠናቀቀ ማግስት ግንቦት 18/2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተነግሯል።
#Tikvah

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ቭላድሚር ፑቲን የተኩስ አቁም አወጁ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16618/

#Ethiopia | የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንከዩክሬን ጋር እየተደረገ ባለው ጦርነት ለሦስት ቀናት የሚቆይ የተናጠል ተኩስ አቁም ማወጃቸው ተሰምቷል።

ፑቲን ያወጁት የተናጠል ተኩስ አቁም ከ10 ቀናት በኋላ ከፈረንጆቹ ግንቦት 8 ቀን እስከ ግንቦት 11 ቀን ድረስ ይቆያል ተብሏል።

የተኩስ አቁሙ የሩሲያ ጦር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚን ጦር ካሸነፈበትመታሰቢያ ጋር የተያያዘ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በተጨማሪም ተኩስ አቁሙ ሰብአዊ ሥራዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት መደረጉን ፑቲን አስታውቀዋል።

ከክሬምሊን የወጣ መግለጫም ዩክሬን ተመሳሳዩን እርምጃ ልትከተል እንደሚገባ ገልጿል።

#aradaFm

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን መነሻ ያደረገ የንግድ ስርአት እንዳይኖር ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ነጋዴዎች ላይ በተወሰደ እርምጃ ከ42 ቢሊዮን በላይ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ መደረጉ ተገለጸ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16620/

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በተያዘው የበጀት አመት በዘጠኝ ወራት አፈፃፀም በስፋት ከሰራኋቸው ስራዎች አንዱ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን መቆጣጠር ነው ብሏል ።

በዚህም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን መነሻ ያደረገ የንግድ ስርዓት እንዳይኖር ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 9 ሺሕ 134 የንግድ ተቋማት ላይ በተደረገ ቁጥጥርና ነጋዴዎች ላይ በተወሰደ እርምጃ ከ42 ቢሊየን በላይ ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና ገቢ መደረጉ ተገልጿል ።

ቢሮው ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ህገወጥ ነጋዴዎችንና ብልሹ አሰራር ብሎም የጎዳና ላይ ንግዶችን መቆጣጠሩን የገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ናቸው።

በተለይም አላግባብ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ብሎም ሃሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን በመጠቀም ህብረተሰቡን በማጭበርበር ላይ የተሰማሩ እንዲሁም ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ላይ የቁጥጥርና እርምጃ የመዉሰድ ስራዎች በስፋት መሰራታቸውን አመላክተዋል። የኮሪደር ልማቱ ላይ ያሉ የህግ ጥሰቶችንና ህጋዊ ያልሆኑ ነጋዴዎችንም በመቆጣጠር ወንጀልና ደንብ ጥሰትን መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል ።

ቢሮው በኑሮ ማረጋጋትና በህገ-ወጥ ንግድ ዙሪያ ክትትልና ቁጥጥር ላይ ትኩረት ሰጥቷል ያሉት ሃላፊዋ፤ ወደ ፊትም ህግና ስርዓት ከማስከበርና የነዋሪውን ሰላምና ደህንነት ከዚህ በተሻለ ለማስጠበቅ በተሻለ የቴክኖሎጂ አሰራር ለመስራት መታቀዱን አመላክተዋል ።
#MenahriaFm

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ከኮስሞ ትሬዲንግ ጋር በተያያዘ በከባድ እምነት ማጉደልና በሌሎች ወንጀሎች የተከሰሱ ግለሰቦችና ድርጅቶች በነፃ ተሰናበቱ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16622/

#Ethiopia | የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀ እና ለ)፣ አንቀጽ 676 (2ሀ)፣ አንቀጽ 34፣ አቀንጽ 702 (1) እና 703 (1)፣ አዋጅ ቁጥር 592/2000 አንቀጽ 3(1) እና አንቀጽ 58 (1 እና 3)፣ አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 (1ሀ እና 2መ) እና አንቀጽ 33 (1ሀ) ድንጋጌዎችን በመተላለፍ፣ ኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተባለ ድርጅት ላይ ከባድ የእምነት ማጉደል፣ ፈቃድ ሳይኖራቸው በባንክ ሥራ ላይ መሰማራት፣ በሕገወጥ ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በሌላ ሰው ጥቅም የሥራ አመራር ላይ ጉዳት በማድረስ ወንጀሎች ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩ አራት ግለሰቦችና ሦስት ድርጅቶች የተመሠረተባቸውን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ችሎት ባለፈው ሳምንት በሰጠው ብይን በነፃ ያሰናበታቸው ተከሳሾች ወ/ሮ አዜብ ምሕረተዓብ፣ አቶ ተመስገን ይልማ፣ አቶ አደፍርስ ሀብቴ፣ አቶ መስፍን አስማማው፣ ጄጄ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ቲቲኤች ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርና ቦስተን ሪል እስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ናቸው፡፡

ተከሳሾቹ የኢፌዴሪ ወንጀል ሕግ ድንጋጌዎችን፣ የባንክ ሥራ አዋጅ ድንጋጌዎችን፣ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣን አዋጅ ድንጋጌዎችን ተላልፈዋል በሚል፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መሥርቶት የነበረው ክስ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ በግለሰቦቹና ድርጅቶቹ ላይ የመሠረተውን ክስ በሰው ምስክሮችም ሆነ በሰነድ ማስረጃዎች በብቃት ማስረዳት አለመቻሉን በብይኑ ጠቅሶ፣ ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 141 ድንጋጌ መሠረት በነፃ እንዲሰናበቱ ብይን መስጠቱን አስታውቋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ ለክሱ ዋና መነሻ ያደረገውና ክስ የመሠረተው፣ ወ/ሮ አዜብና አቶ ተመስገን የተባሉት ተከሳሾች ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሳቸው ለማግኘትና ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ፣ የግል ተበዳይይ የሆነው የኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሳለ፣ የዋና ሥራ አስኪያጁ ሙሉ ሥልጣን እንዲኖራቸው አድርገዋል፡፡ በዚህም ራሳቸው ለራሳቸው በሰጡት ሹመት ድርጅቱን እንዲያስተዳድሩ በማድረግ፣ ድርጅቱን በማስያዝ 61 ሚሊዮን ብር ከአዋሽ ባንክ በመበደር፣ ኮስሞ ትሬዲንግ ቀደም ብሎ ከኅብረት ባንክ የተበደረውን 21 ሚሊዮን ብር መክፈላቸውን የብይን ሰነዱ ያስረዳል፡፡ ተከሳሾቹ ቀሪውን 40 ሚሊዮን ብር ወደ ኮስሞ ትሬዲንግ የሒሳብ ቋት ገቢ ካደረጉ በኋላ፣ ለድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አሥር ሚሊዮን ብር ማበደራቸውንና ተጨማሪ 32,500,000 ብር ደግሞ ንብረትነቱ የወ/ሮ አዜብ ለሆነውና አቶ ተመስገን በውክልና ለሚያስተዳድሩት ጄጄ ፕሮርቲ ድርጅት ማስተላለፋቸውንም የዓቃቤ ሕግ ክስ ይዘረዝራል፡፡ የወ/ሮ አዜብ ድርጅት ለሆነውና እራሳቸው ለሚያስተዳድሩት ቦስተን ሪል እስቴትም 7000,000 ብር ማስተላለፋቸውንም ክሱ ይገልጻል፡፡ ከብድሩ ላይ በተለያዩ ቀናት 11,014,000 ብር እና 5000,000 ብር ደግሞ ንብረትነቱ የአቶ ተመስገን ለሆነው ቲቲኤች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ላለበት የባንክ ብድር ክፍያ ማዋላቸውንም የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ከባንክ የተበደሩትን ቀሪ ገንዘብ በግል ግንኙነት ላላቸው በክፍያ መስጠታቸውንም አክሏል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንዳብራራው አቶ ተመስገን ኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ‹‹ዋን ሃው›› ለተባለ ሆቴል ያከራየውን ሕንፃ ገቢ 14,400,000 ብርና ከአንድ ግሬደር ተሽከርካሪ ሽያጭ የተገኘ 1,410,000 ብር ለግል ጥቅማቸው ማወዋላቸውን በመግለጽ፣ ኮስሞ ትሬዲንግን በመመሥረቻ ጽሑፉ መሠረት በሕጋዊ የንግድ ተግባር እንዲመሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው፣ የድርጅቱን ሕንፃ ለባንክ መያዣ በማድረግና ከፍተኛ ገንዘብ በመበደር ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው፣ ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶባቸው ነበር፡፡

ዓቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዜብ፣ አቶ ተመስገንና አቶ አደፍርስ የባንክ ሥራን በመተካት ፈቃድ ሳይኖራቸው በተለይ ወ/ሮ አዜብ በአሜሪካና አውሮፓ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን የውጭ ምንዛሪ በመሰብሰብ፣ በኢትዮጵያ ብር መንዝረው ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ ግለሰቦች የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ የማስተላለፍ ሥራ መሥራታቸውንና አቶ ተመስገን ደግሞ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ሆነው ከቀረቡትና የኮስሞ ትሬዲንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከነበሩት አቶ ገመቹ ዲንቃ ከተባሉ ግለሰብ ጋር በመሆን፣ የተላከው ገንዘብ ወጪ በማድረግ ለተለያዩ ግለሰቦች (ግለሰቦቹ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሆነዋል) መስጠታቸውን ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ በክሱ ዘርዝሮ በማቅረብ፣ ተከሳሾቹ ፈቃድ ሳይኖራቸው የባንክ ሥራ በመሥራት ወንጀል ክስ መሥርቶባቸው ነበር፡፡

ዓቃቤ ሕግ በወ/ሮ አዜብና አቶ ተመስገን ላይ ያቀረበው ሦስተኛ ክስ፣ ተከሳሾቹ በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስለውና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት፣ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ተላልፈው ወንጀል ፈጽመዋል የሚል መሆኑን ክሱ ያብራራል፡፡ ተከሳሾቹ አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 (1ሀ እና 2መ) ድንጋጌዎችን ተላልፈው፣ ኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርን እንዲያስተዳድሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው፣ ከአዋሽ ባንክ 61,000,000 ብር በመበደር፣ ገንዘቡን ለግለሰቦችና ድርጅቶች በማዘዋወር፣ ዕዳ በመክፈልና ለተለያዩ ግለሰቦች በመክፈል በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስለው የማቅረብ ወንጀል መፈጸማቸውን፣ በክሱ በዝርዝር ጠቅሶ ማቅረቡን ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን ላይ ገልጿል፡፡

ዓቃቤ ሕግ አቶ መስፍን አስማማው በተባለው ግለሰብ ላይ የመሠረተው ክስ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 702 (1) እና 703 (1) ድንጋጌዎችን መተላለፍ፣ ግለሰቡ ለሌላ ጥቅም በሥራ አመራር ላይ ጉዳት የማድረስ ወንጀል ፈጽሟል የሚል ሲሆን፣ ተከሳሹ በውል ግዴታ ተቀብሎ በሥራ አስኪያጅነት በሚመራው ድርጅት (ኮስሞ ትሬዲንግን) በማንኛውም ፍርድ ቤት ከሳሺ፣ ተከሳሺ ወይም ጣልቃ ገብ ሆኖ አስፈላጊውን ሁሉ እንዲፈጽም ግዴታ የገባ ቢሆንም፣ የግል ተበዳይ (ድርጅቱ) የ50,,000,000 ብር ክስ ተመሥርቶበት ሳለ፣ በፍርድ ቤት ቀጠሮ እያለበት ባለመቅረቡ በድርጅቱ ላይ እንዲወሰንበት በማድረጉ መከሰሱን የክስ ሰነዱ ያብራራል፡፡

ዓቃቤ ሕግ ከላይ በዘገባው ለተዘረዘሩት ክሶች ዘጠኝ ምስክሮችን ፍርድ ቤት አቅርቦ ያሰማ ሲሆን፣ አንደኛ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ሆነው የቀረቡት አቶ ኃይለየሱስ መንግሥቱ የተባሉ ምስክር መሆናቸው በብይኑ ተገልጿል፡፡ ምስክሩ በሰጡት ምስክርነትም ከወ/ሮ አዜብ ጋር እንደሚተዋወቁና ገንዘብ ከእሳቸው በአራጣ እየተበደሩ 100,000 ብር እና 200,000 ብር እየጨመሩ ይመልሱ እንደነበር አስረድተዋል፡፡…
በበርካታ ሙዚቃዎቹ እና በድምፁ የምንወደውና የምናከብረዉ አብዱ ኪያር በዱባይ ካሉት የቅንጦት ቪላዎቻችን አንዱን ለማስጎብኘት እድል ነበረን። እሱም በዚህ ቤት እጅግ ደስተኛ እንደሆነ እርግጠኛ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16625/

በበርካታ ሙዚቃዎቹ እና በድምፁ የምንወደውና የምናከብረዉ አብዱ ኪያር በዱባይ ካሉት የቅንጦት ቪላዎቻችን አንዱን ለማስጎብኘት እድል ነበረን። እሱም በዚህ ቤት እጅግ ደስተኛ እንደሆነ እርግጠኛ ነን።

ኑ ዛሬ በዱባይ ቤት ይግዙ እና ትርፋማ ይሁኑ። ከከፍተኛ ጥራት፥ በፈጠነ ጊዜ እንዲሁም በቀላል የአከፋፈል ስርዓት ቤቶችን ለእናንተ ለቤት ገዢዎች ይዘነኝሁ መትዋል።

ይህንን ትልቅ አማራጭ ለመጠቀም ወደ ብሩክ ሪል እስቴት አሁኑኑ ይደውሉ

Contact us for journey of ownership and investment in the heart of Dubai . 🌟🔑

Brook Real Estate
www.brookrealestate.ae
+971 527 866251

#Dubai #eritrea #ethiopia #habesha #eritrean #ethiopian #ethiopiarealestate #ethiopiagirls #ethiopianwomen #habeshabeauty #habeshawedding #eritreanwomen #habeshastyle #habeshafashion #ethiopianfood #habeshagirl #habeshaqueens #eritreangirl #ethiopians #amharicmuisc #ethiopianmusic #newamharicmusic #abdukiyar #ethiopianmusic #ethiomusic

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የአባቶች የቡራኬ እና የአንልኮ ድግስ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16640/

አያት ዞን 5 መንገድ 16

ለበለጠ መረጃ ስልክ
0993103051/0982936412

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የደጃዝማች ኩምሳ ሞረዳ ቤተ መንግስት የጥገናና የመልሶ ማልማት ስራ የውል ስምምነት ተደረገ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16642/

#Ethiopia | ኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የደጃዝማች ኩምሳ ሞረዳ ቤተመንግስት የጥገናና የመልሶ ማልማት ስራ ለማከናወን ከቢዋይ ኤም ቲ ኮንትራክተር ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በውል ስምምነቱ ላይ እንደገለፁት ቤተ መንግሥቱ ጥንታዊና ታሪካዊ መሆኑን ጠቅሰው ለረዥም ዓመታት እድሳት ሳይደረግለት ፣ በቱሪዝሙ ዘርፍ አገልግሎት ሳይሰጥ መቆየቱ አብራርተዋል ። ቅርሱ ከጥንት የኢትዮጵያ ታሪክ ጋር የተያያዙ ስፍራዎችን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ከተመረጡ ስፍራዎች አንዱ መሆኑን ፣ጥገናው ቅርሱ የነበረውን አሻራና ይዘት በጠበቀ መልኩ የቅርስ ጥገና መርሆዎችን በተከተለ መንገድ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት የጥገና ስራው በተያዘለት የሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ጥራቱን ጠብቆ መጠገንና ለሃገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መሆን እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡

እንዲሁም በውል ስምምነቱ ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉት ክብርት ወ/ሮ ህይወት ኃይሉ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ይህ የጥገና ስራ ቤተመንግስቱ ያለበትን የጥገና ችግር የሚፈታና ኮንትራክተሩ የተሳካ ስራ የሚያሳይበት እንደሚሆን ተመኝተው የቤተመንግስቱ እንዲሁም የምድረ ግቢው ጥገና በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለሀገራችን ተጨማሪ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡

አቶ በዛብህ መለሰ የቢዋይ ኤም ቲዋና ስራ አስኪያጅ ይህን ታሪካዊ ቤተመንግስት ጥገና ለማድረግ ጨረታ በማሸነፋቸው መደሰታቸውን ገልጸው ስራውን በተፈለገው ጊዜና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ አከናውነው እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል፡፡
መረጃዎች እንደሚያሳዩት ደጃዝማች ኩምሳ ሞረዳ በከሬ ከ1881ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 1916 ዓ.ም. ድረስ የቀድሞ ወለጋ ጠቅላይ ግዛትን ያስተዳድሩ ነበር ፡፡ ንጉሡ ቤተመንግስታቸውን የመሠረቱት 1830 ዓ.ም. ሲሆን ይህ አስደናቂ ቤተመንግስት ያረፈበት ቦታ ስፋቱ 2.5 ሄክታር የሚያካልል ነው፡፡ በቅጥር ግቢው ሌሎች አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ተደርገው የተገነቡ የተለያዩ ቤቶች ሲኖሩ በአጠቃላይ ቅጥር ግቢው አምስት በሮች አሉት፡፡

ይህ ቤተ መንግስት ከአዲስ አበባ በስተ-ምዕራብ በኩል 319 ኪሎ ሜትር ርቀት ነቀምቴ ከተማ ነው የሚገኘው፡፡ ይህም ከከተማዋ መሃል መነሻ ሆኖ በስተ-ምዕራብ በኩል 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከፍ ባለ ውብና ማራኪ ሥፍራ ተንጣሎ ይታያል፡፡
(ኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን)

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
እስራኤል ከሁለት ወራት በላይ በጋዛ የእርዳታ ድጋፍ እንዳይገባ መከልከሏ ተነገረ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16644/

#Ethiopia | እስራኤል ምግብ፣ ውሃ፣ መድሃኒት፣ የህክምና ቁሳቁሶችን እና ነዳጅን ወደ ጋዛ ከሁለት ወራት በላይ እንዲገባ አልፈቀደችም፣ የእስራኤል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንን ፖሊሲ በመደገፍ በርካታ የእርዳታ ጥያቄዎችን ውድቅ በማድረግ፣ ሰው ሰራሽ የሆነ የሰብአዊ ጥፋት፣ ረሃብ ሞትን ጨምሮ እንዲፈጠር ምክንያት መሆኗን በኔዘርላንድስ የፍልስጤም አምባሳደር የሆኑት አማር ሂጃዚ በሄግ የቃል ክርክራቸውን አቅርበዋል።

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ ጋዛን እንደ “ገዳይ ሜዳ” ገልፀዋል። ይህንን ጉዳይ ለመስማት የፍርድ ቤቱ ስልጣን ምንም ጥርጥር የለውም፤ የህግ ጥያቄዎች በአለም አቀፍ ህግ መሰረት የሚሰሩ ናቸው እናም የፍልስጤም ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮ ውስጥ ማዕከላዊ ነው፤ ይህም ቀደም ባሉት የአማካሪ አስተያየቶች ላይ በድጋሚ ተረጋግጧል።

የፍልስጤም ግዛት የእስራኤል ድርጊት በጋዛ እና በዌስት ባንክ (ምስራቅ እየሩሳሌምን ጨምሮ) ለዘለቄታው መቀላቀልን፣ የዘር ማጽዳት እና የፍልስጤማውያንን መሰረታዊ መብቶች እና ህልውና እንደሚጥስ የሚያሳይ ማስረጃ ቀርቧል። እስራኤል በዘር ማጥፋት ወንጀል የተከሰሰች ህገ-ወጥ የስልጣን ባለቤት ነች እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው ይፈለጋሉ። እስራኤል የፍልስጤምን ህዝብ ለማጥፋት እና ፍልስጤምን ለማጥፋት እየሞከረች ነው፣የሰብአዊ ድርጅቶችን በመከልከል እና በማደናቀፍ፣በዚህም በተባበሩት መንግስታት ቻርተር እና ሌሎች የአለም አቀፍ ህግ ሰነዶች ላይ ያላትን ግዴታዎች በመጣስ ላይ ትገኛለች በሚል ክስ ይቀርብባታል።
#ዳጉ_ጆርናል
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በኡጋንዳ አዲስና ደማቅ ታሪክ በማፃፍ ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16646/

📌

#Ethiopia | ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚለው ስም ከሌሎች ስሞች በበለጠ በኡጋንዳ ከፍ ብሎ እየተውለበለበ የሚገኝ ከስኬት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ስም ከሆነ ከ180 ቀናት በላይ ተቆጥረዋል፤አዎን የኡጋንዳ ካምፓላ ኩዊንስ የሴቶች ቡድን ዋና አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል በኡጋንዳ ሠማይ ስር ደምቆ እያበራ ነው፤ በግርምት እጃቸውን አፋቸው ላይ እንዲጭኑ በውጤቱ ያስገደደው አሠልጣኝ ፍሬው የሴቶች ብ/ቡድንን ይረከብ የሚሉ ድምፆች እንዲበረክቱም አድርጓል።የአሠልጣኙ የኡጋንዳ 6 ወራቶች ወይም 180 ቀናት በወፍ በረር ከዚህ በታች ያለውን ይመስላሉ።

👉በተደጋጋሚ የጨዋታው ኮከብ አሠልጣኝነት ክብርን ተጎናፅፏል

👉በኡጋንዴ ለስልጠናውም ለእግር ኳሱም ለባህሉም እንግዳ ቢሆንም ውጠታማ ከመሆን አላገደውም፤በሀገር ውስጥ የነበረውን ስኬታማ ጉዞ በኡጋንዳም አስቀጥሏል

👉ኡጋንዳ ገብቶ ካምፓላ ሲቲ የሴቶች ቡድንን በያዘ በወራት ውስጥ የጥሎ ማለፍ ዋንጫን ከፍ አድርጎ በማንሳት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ለመሆንም በቅቷል

👉ዋንጫ አይምሬ የሆነው ፍሬው ኃይለገብርኤል በዚህ ሳያበቃም FINANCE TRUST BANK WOMENS SUPPER LEAGUE አሸናፊ በመሆን የራሱንም የሀገሩንም ስም ለማስጠራት በጣም ተቃርቧል

📌ኢትዮጵያዊው አሠልጣኝ ፍሬው በኡጋንዳ የሀገሪቱ ሀያል ክለብ ከሆነው የካምፓላ ኩዊንስ የሴቶች ቡድን አሠልጣኝ ሆኖ

👉15 ጨዋታዎችን አድርጎ 13 አሸንፏል
👉በሁለት ጨዋታ አቻ ተለያይቷል
👉በ12 ጨዋታ አንድም ጎል ሳይቆጠርበት አሸንፏል
👉 30 ጎሎችን በተጋጣሚዎቹ ላይ አስቆጥሯል
👉በ6 ወር ቆይታው የገባበት ሶስት ጎል ብቻ ነው

እነዚህን ሁሉ ስኬቶች በምስራቃዊቷ ሀገር ኡጋንዳ ምድር ያስመዘገበው፣የራሱንም የሀገሩንም ስም ከፍ አድርጎ እያስጠራ የሚገኘው፣በሌሎች ኢትዮጵያዊያን አሠልጣኞች ላይ ዕምነት እንዲጣል የሚያደርግ ስኬታማ ስራን እየሠራ የሚገኘው ኢትዮጵያዊው ፍሬው ኃይለገብርኤል ነው።

✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ሚኬል አርቴታ ለደጋፊው ጥሪ አቅርበዋል !

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16648/

#Ethiopia | የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በነገው የፒኤስጂ ጨዋታ “ አብራችሁን ተጫወቱ “ ሲሉ የክለቡን ደጋፊዎች ጠይቀዋል።

ኤምሬትስ ስታዲየም ለሚሄዱ ደጋፊዎች መልዕክት ያስተላለፉት አርቴታ “ ሙሉ ትጥቃችሁን አድርጋችሁ እያንዳንዱን ኳስ አብራችሁን ተጫወቱ “ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

“ ታሪክ እየፃፍን ነው “ የሚሉት አርቴታ የበለጠ እንፈልጋለን ነገ ከደጋፊው በማድሪድ ጨዋታ ከነበረውም የበለጠ ትልቅ ድባብ እንፈልጋለን ብለዋል።

ቦታውን የተለየ ማድረግ ከፈለጋችሁ ማድረግ ትችላላችሁ ከዚህ በፊት ያልታየ ነገር ይኖራል ሲሉ አርቴታ ተናግረዋል።
#Tikvah
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የትራንስፖርት ሚኒስቴር ለአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ረቂቅ ፖሊሲ አዘጋጀ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16650/

#Ethiopia | የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ራሱን የቻለ ረቂቅ ፖሊሲ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

ይህ አዲስ ረቂቅ ፖሊሲ ከዚህ ቀደም የነበረውን ክፍተት ለመሙላትና ለኢንዱስትሪው ዕድገት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው ተብሏል።

የሚኒስትሩ አማካሪ የሆኑት አቶ ከድልማግሥት እንደተናገሩት ፓሊሲው የአገሪቱን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ መነሻ በማድረግ ተዘጋጅቷል ። ረቂቅ ፖሊሲው የኢትዮጵያን አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ የወደፊት ዕጣ ፋንታ፣ የእድገት ዕቅዶችና ተያያዥ ጉዳዮችን በግልጽ ያስቀምጣል ብለዋል።

በተጨማሪም ፖሊሲው ነዳጅ እና ኤሌክትሪክን (ታዳሽ ኃይልን) የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ሲሆን፣ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡበትን ሁኔታ፣ ሊያሟሏቸው የሚገቡ የጥራት ደረጃዎች እንዲሁም የአምራች ኩባንያዎች በአገር ውስጥ ምርትና መገጣጠሚያ እንዲገነቡ የሚበረታቱበትን መንገዶች በዝርዝር ማካተቱን ሪፖርተር ዘግቧል።
#ቅዳሜገበያ

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ፖርቹጋል እና ስፔን ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ አጋጠማቸው

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16652/

#Ethiopia | በፖርቹጋል እና ስፔን አብዛኛው ክፍሎች ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ካጋጠማቸው ሰዓታት የተቆጠሩ ሲሆን፣ የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ መንስኤው አሁንም እየተመረመረ እንዳለ ተናግረዋል።

ሳንቼዝ ሰዎች ግምታዊ አስተያየቶችን ከመስጠት እንዲቆጠቡ ያስጠነቀቁ ሲሆን፤ በደቡብ ስፔን በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ኃይል ተመልሶ መምጣቱን ተናግረዋል ።

የፖርቹጋል ጠቅላይ ሚኒስትር ሉዊስ ሞንቴኔግሮ በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት የኃይል መቋረጡ የሳይበር ይሁን ሌላ ጥቃት ጠቋሚ መረጃ የለም ብለዋል።

የቢቢሲ ዘጋቢዎች በፖርቹጋል ዋና ከተማ ሊዝበን ጎዳናዎች ላይ በትራፊክ መጨናነቅ ማስተዋላቸውን ጠቅሰው፣ የፖሊስ አባላት በትራፊክ መብራት ምትክ በፉጨትና በእጅ ምልክት እየተጠቀሙ ሲያሰተባብሩ ማየታቸውን ገልፀዋል።

የሊዝበን ሁምበርቶ ዴልጋዶ አውሮፕላን ማረፊያ በኃይል መቆራረጥ ምክንያት የእንግዶች መግቢያ አዳራሾችን ለመዝጋት መገደዱንም ሪፖርቶች ያመላክታሉ።

በስፔን አንዳንድ አካባቢዎች የስልክ መስመሮች ላይ እክል አያጋጠመ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝም ሕዝቡ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ስልኮችን በኃላፊነት እንዲጠቀም ጠይቀዋል።

አርቲ በማኅበራዊ ትስስር ገጾቹ ያወጣቸው ምስሎች ፖርቹጋል በጨለማ መዋጧን የሚያሳዩ ሲሆን፣ የሀገሪቱ የመብራት ግሪድ ኦፕሬተሮች መብራት ተመልሶ ሊመጣ የሚችልበትን ጊዜ መተንበይ የማይቻል መሆኑን መግለጻቸውን ጠቅሷል።

በለሚ ታደሰ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ከትኬት ሽያጭ የሚገኘዉ ገቢ ለመቄዶንያ ገቢ ይሆናል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16654/

አርቲስቶች – ከድምፃውያን
ጋዜጠኞች – ከቲክቶከሮች ሀሙስ ሚያዚያ 23 ለዋንጫ ለማለፍ ይፋለማሉ

ዋንጫዉ ከኛ አያልፍም የሚለዉ የአራቱ ቡድኖች ፉክክር ዉድድሩን አጓጊ አድርጎታል

የመግቢያ ትኬቱን አሁኑኑ ከቴሌ ብር ላይ ይግዙ እና ተወዳጅ ኮከቦችን በኳስ ሜዳ ያግኟቸዉ፡፡
ዉድድሩ ከልደታ ቤተክርስቲያን ጀርባ በሚገኘዉ በብሪሞ ሜዳ ይደረጋል።

Celebrity sports festival powered by Pepsi
የታዋቂ ሰዎች ስፖርታዊ ዉድድር ከፔፕሲ ጋር

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet