Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
6.18K subscribers
2 photos
4.75K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
ሩሲያ የጄኔራሏን ገዳይ በቁጥጥር ስር አዋለች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16575/

#Ethiopia | ሞስኮ በመኪና ላይ የቦምብ ጥቃት የተገደለባትን ጄኔራል ገዳይ በቁጥጥር ስር አዋለች።

በዩክሬን የስለላ ድርጅት ተመልምሏል የተባለው በቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ ባለፈው ሳምንት የሩሲያ ጄኔራል በመኪና ላይ ከደረሰው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ በሩሲያ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት ኤፍ.ኤስ.ቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በቁጥጥር ስር የዋለው የ41 ዓመቱ የዩክሬን ነዋሪ ኢግናት ኩዚን በኤፍ.ኤስ.ቢ የተያዘው የሩሲያን ጄኔራል ያሮስላቭ ሞስካሊክን የገደለውን ፈንጂ አጥምዷል ተብሎ ነው። በዚህም ክስ እንደቀረበበት የሩስያ ኤጀንሲ በመግለጫው አሳውቋል።

ዓርብ ዕለት በተከሰተው ፍንዳታ የሩስያ ጦር ኃይሎች ዋና ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ኃላፊ ከመኖሪያ ቤታቸው በመውጣት ላይ እያሉ የተገደሉ ሲሆን፤ በጉዳዩ ተጠርጥሮ የተያዘው ኩዚን በሽብርተኝነት እና በህገ ወጥ የፈንጂ ንጥረ ነገሮች ክምችት ተከሷል።
#Gazette_plus

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዓለም ባንክ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ሊቀበል ነው

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16577/

#Ethiopia | መንግስታዊዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአለም ባንክ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ ድጋፍ በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለመቀበል በዝግጅት መሆኑ ተጠቆመ ።

ከ650 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከተመደበው ገንዘብ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በዚህ የመጀመሪያ ዙር ዝውውር እንደሚካተት ይጠበቃል።

ይህ በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ የገንዘብ ድጋፍ የአለም ባንክ የፋይናንስ ሴክተርን የማጠናከር ፕሮጀክት አካል ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፋይናንስ አቅሙን እንዲያሳድግና የኢትዮጵያን ሰፋ ያሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እንዲደግፍ ያለመ ነው።

ባንኩ ይህንን ድጋፍ ለማግኘት መንግስት ቦንድ ማውጣትንና የቦርድ ስብጥርን ማስተካከልን ጨምሮ የተወሰኑ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቷል።

ይህን ተከትሎ በሚቀጥለው ሳምንት ቢያንስ 350 ሚሊዮን ዶላር መቀበል እንደሚችል ይጠበቃል። ይህ የገንዘብ ድጋፍ በተለይም ባንኩ ቀደም ሲል ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በሰጠው ያልተመለሰ ብድር ምክንያት ያጋጠሙትን የፋይናንስ ተግዳሮቶች ለማቃለል ትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት የንግድ ባንኩን ካፒታል ለማጠናከር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተገልጿል። ባለሙያዎች ይህ የዓለም ባንክ ድጋፍ የሀገሪቱን የፋይናንስ ሴክተር ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ይስማማሉ።

(Capital)

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16579/

#Ethiopia | በአንድ ስፍራ 12 ተቋማት 41 አገልግሎቶች ይሰጣሉ፤

✍️የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት

✍️ የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት

✍️ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሌት

✍️ የገቢዎች ሚኒስቴር

✍️ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

✍️ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር

✍️ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

✍️ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

✍️ የትምሀርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት

✍️ የኢትዮ ፖስታ

✍️ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

✍️ ኢትዮ ቴሌኮም ሲሆኑ ሁሉም ተቋማት በቴክኖሎጂ አማካኝነት በትስስር አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።

በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው።

አሁን ሥራ ለጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት አስራ ሁለት የፌደራል መንግስት ተቋማት አርባ አንድ የሚሆኑ የህዝብ አገልግሎቶችን አቅርበዋል፡፡ አገልግሎቶቹ ከፈቃድ አሰጣጥ ጀምሮ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባንም አካትተዋል።
#press

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በመዲናዋ በያዝነው በጀት ዓመት ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣትና ከጨረታ ሽያጭ ከ290 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16581/

#Ethiopia | በ2017 በጀት ዓመት በ9 ወራት ውስጥ ከደምብ ተላላፊዎች ከተወረሱ ቁሳቁሶች የጨረታ ሽያጭ እና ከደምብ ተላላፊዎች ቅጣት በድምሩ ከ290 ሚሊዮን 543 ሺሕ ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ከዚህም መካከል ደንብ ቁጥር 167፣ 150 እና 180/2017ን ተላልፈው ከተገኙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ከ258 ሚሊዮን 800 ሺሕ ብር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን፤ ከ17 ሚልዮን 200 ሺሕ ብር በላይ የሚሆነው ደግሞ ከደንብ ተላላፊዎች ተወርሰው በጨረታ ከተሸጡ ንብረቶች የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ ባለፉት 9 ወራት ከጨረታ ሽያጭና ከቅጣት ከ290 ሚሊዮን 543 ሺሕ ብር በላይ ተሰብስቧል።

ከተሰበሰበው ገንዘብ ከ268 ሚሊዮን 322 ሺሕ ብር ለፋይናስ ገቢ ሲደረግ፤ ከ22 ሚልዮን 221 ሺሕ ብር በላይ የሚሆነው ደግሞ በሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት ባለስልጣኑ ሕገ-ወጥ የጎዳና ንግድ ሲያከናውኑ የተገኙ 34 ሺሕ 260 አካላት ላይም እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

በቅርብ ጊዜያት ደምብ ተላላፊዎች ላይ የቅጣት እርምጃ የሚወስዱ በርካታ ሕግና ደንቦች መውጣታቸውን ያነሱት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፤ በተለይም በደንብ ቁጥር 167 ላይ የተመለከተው ከፅዳት ጋር የተያያዘ መመሪያ ከፍተኛ ቅጣት የሚያስከትል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም የወንዞችንና የወንዝ ዳርቻዎችን ከቆሻሻና ብክለት ነፃ ለማድረግ የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 በሚገባ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም ሕግና ደንቦች በሚወጡበት ሰዓት ገቢ ለመሰብሰብ ሳይሆን፤ ትልቁ ነገር የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሕግና ደንብን ለማስፈፀም ከጸጥታ መዋቅርና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝና ደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
#ahaduRadio

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
መጋቢት 20፤2017 – አልሻባብ እየተጠናከረ መምጣቱን ተከትሎ ሶማሊያ አዲስ የመከላከያ ሚኒስትር ሾመች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16583/

#Ethiopia | የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የካቢኔ ማሻሻያ ያደረገ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን አህመድ ሙአሊም ፊቂን በመከላከያ ሚኒስቴርነት ሾመዋል። በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሁለተኛው የመከላከያ ሚኒስትር ለውጥ ሲሆን የአልሸባብ ታጣቂዎች ጥቃቱን እያጠናከሩ በመምጣታቸው የፀጥታው ሁኔታ እያሽቆለቆለ መሆኑን ተከትሎ ነው።

ይህ እርምጃ ከሳምንታት በፊት የሶማሊያን የረጅም ዓመታት የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩትን አብዱልቃድር መሀመድ ኑርን ተክተው የነበሩትን ጅብሪል አብዲራሺድን ዳግም በሌላ ሚኒስትር እንዲተኩ ያደርፋል ። ባሬም ምክትላቸውን አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርጎ ለመሾም እያሰበ መሆኑን ምንጮች ለሶማሊያ ጋርዲያን ተናግረዋል። ሆኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ የቅርብ ሰው ከዋሽንግተን ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ከዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ጋር ግንኙነት ያላቸውን እጩ እንዲቀርብ እየተማፀኑ ይገኛል ተብሏል።

በተመሳሳይ የሹም ሽር መረጃ፣ የሶማሊያ መንግሥት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ኤጀንሲ (ኒሳ) ኃላፊ የሆኑትን አብዱላሂ መሐመድ ሳንባቦሎሼን ከኃላፊነት እንደሚያሰናብት ይጠበቃል። የቀድሞ የስለላ ተቋም ጉድለትን ተከትሎ ከስልጣናቸው የተነሱት የቀድሞ ዳይሬክተር ማሃድ ሳላድ ወደ ስራቸው እንዲመለሱ እየታሰቡ ይገኛል። ይህ እርምጃ የፀጥታ መስተጓጎል እየተባባሰ በመጣበት ወቅት የተወሰደ ነው።
#BisratFm

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ አፍሪካውያን ለምን እርስበርስ ለመዋደድ እንደሚቸገሩ ሀሳባቸውን በቅርቡ አካፍለዋል።

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16585/

🗣️🗣️ “አፍሪካን ስንመለከት ፈጣሪ ከባረካቸው እጅግ ሰላማዊ አህጉራት አንዷ ነች። አሁን ላይ በመካከላችን የምናያቸው ግጭቶች በዋናነት አውሮፓውያን አንዱ ሀገር ከሌላ ሀገር እንዳይዋደድ፣አብሮ እንዳይሰራ እና እንዳያድግ የመለያየት ዘር ስለዘሩ ነው።

እራሳችንን መጠየቅ አለብን፡ ለምንድነው አውሮፓውያን በአፍሪካውያን ዘንድ እንደምናየው እርስበርስ ሲጠላለፉ የማናየው? እነሱ እኛን ሆን ብለው እርስ በርሳችን እንድንጋጭ ስላደረጉን ነው። እነሱ አንድ ሆነው ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን እንድንጠላ አስተምረውናል።

በአውሮፓ ውስጥ እንዲህ ዓይነቱን ክፍፍል ማየት ብርቅ ነው። ይህንን ተገንዝበን ጥላቻን ማቆም እና የተሻለች አፍሪካን ለመገንባት በጋራ መስራት አለብን”
#ayu

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የዲ/ን ዘማሪ ነቢዩ ሳሙኤል መልዕክት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16587/

የዲ/ን ዘማሪ ነቢዩ ሳሙኤል መልዕክት👇

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አሜሪካ በየመን የአፍሪካ ስደተኞች ማቆያ ላይ በፈጸመችው የአየር ድብደባ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ቢያንስ 68 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16590/

#Ethiopia | አሜሪካ በሰሜን ምዕራብ የመን የሁቲ ቁጥጥር ሥር በሚገኘው የአፍሪካ ስደተኞች ማቆያ ጣቢያ ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት፤ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ቢያንስ 68 ሰዎች መሞታቸውን የታጣቂው ቡድኑ የቴሌቪዥን ጣቢያ ገለጸ።

የሁቲዎች ምሽግ በሆነው በየመን ሰአዳ ከተማ ውስጥ በተደረገው ጥቃት በጎረቤት ሀገር ሳውዲ አረቢያ ‘የሥራ ዕድል ለማግኘት’ ሲሉ ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች ሀገራት ድንበር አቋርጠው የመጡ አፍሪካውያን ስደተኞች መገደላቸው የኤፒ ዘገባ አመላክቷል፡፡

በሰአዳ ግዛት የሚገኘው የአፍሪካ ስደተኞች ማቆያ ጣቢያ በቦምብ መመታቱን ተከትሎም፤ ከሟቾች በተጨማሪ 47 ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል።

ይህንንም ተፈትሎ በሕንጻዎች ፍርስራሽ ውስጥ የተሸፈኑ በርካታ አካላትን የሚያሳዩ ምስሎችን አል ማሲራህ የተባለው የቡድኑ የቴሌቪዥን ጣቢያ ለቋል።

ከአሜሪካ ጦር በኩል እስካሁን የተሰጠ አስተያየት የለም።

ነገር ግን የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ መጋቢት 15 በሃውቲዎች ላይ የአየር ዘመቻ እንዲጠናከሩ ካዘዙ በኋላ፤ ጦሩ ከ800 በላይ የሁቲ ኢላማዎችን መምታቱን አስታውቋል።

ጥቃቱ የሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የሚቆጣጠሩ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ “በመቶ የሚቆጠሩ የሃውቲ ተዋጊዎችን እና በርካታ የሃውቲ መሪዎችን ገድሏል” ብሏል።

የሁቲ ባለስልጣናት በተደረጉት ጥቃቶች በደርዘን የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች መሞታቸውን ቢናገሩም፤ በቡድኑ አባላት ላይ የደረሰው ጉዳት ግን አነስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በሃውቲ የሚመራው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ በቀይ ባህር ዳርቻ በሚገኘው ራስ ኢሳ የነዳጅ ማደያ ጣቢያ ላይ የአሜሪካ ጦር ባደረገው ተከታታይ የአየር ጥቃት በትንሹ 74 ሰዎች ሲገደሉ 171 ሰዎች ቆስለዋል።

ባለፈው ወር ትራምፕ በሃውቲዎች ቁጥጥር ሥር ባሉ ቦታዎች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት እንዲካሄድ ትዕዛዝ የሰጡ ሲሆን፤ ታጣቂዎቹ “ሙሉ በሙሉ ይጠፋሉ” ሲሉም መዛታቸው ይታወሳል።

ከአውሮፓዊያኑ ሕዳር ወር 2023 ጀምሮ ሁቲዎች በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ በሚሳኤል፣ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና በትንንሽ ጀልባዎች በሚያደርሷቸው ጥቃቶች በደርዘን የሚቆጠሩ የንግድ መርከቦችን ኢላማ በማድረግ አውድመዋል።

በተጨማሪም ሁለት መርከቦች በማስጠም ሦስተኛውን በቁጥጥር ሥር ያዋሉ ሲሆን፤ አራት የበረራ አባላትን ገድለዋል።

በዚህም ሁቲዎች በእስራኤል እና በጋዛ ሃማስ መካከል በተደረገው ጦርነት ፍልስጤማውያንን ለመደገፍ እየሰሩ መሆኑን ያስታወቁ ሲሆን፤ ኢላማ ያደረጉትም “የእስራኤል፣ የአሜሪካ ወይም የእንግሊዝ ንብረት የሆኑ መርከቦችን ብቻ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ባለፉት አስርት ዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት የምታመሰው የመን ከፍተኛ የሆነ ውድመትን በማስተናገድ ላይ ትገኛለች፡፡

በዚህም ሃውቲዎች የሀገሪቱን ሰሜናዊ ምዕራብ ዓለም አቀፍ እውቅና ካለው መንግሥት አስለቅቀው የተቆጣጠሩ ሲሆን፤ በአሜሪካ የሚደገፈውና በሳዑዲ የሚመራው ጥምር ጦር በሳውዲ በስደት ላይ የሚገኘውን መንግሥት ወደ ቦታው ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ጣልቃ ገብቷል።

በጦርነቱ ከ150 ሺሕ ላይ ሰዎች መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን፤ አስከፊ ሰብዓዊ ቀውስ ማስከተሉም ተነግሯል፡፡ በዚህም 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሰዎች ሲፈናቀሉ፤ 19 ሚሊዮን 500 ሺሕ የሚሆኑ የሀገሪቱ ዜጎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተመላክቷል።

በኢዮብ ውብነህ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ቲሸርቱን ፈጥነው ይግዙ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16592/

ታላቁ የኢትዮጲያ የተራራ ጉዞ(ሀይኪንግ) ውድድርና ፌስቲቫል🏋️🪂🤸🏇🏃
🎯በእንጦጦ ፖርክ
🗓 ሚያዝያ 23 2017 ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ ይካሄዳል
🏃‍♀️5 ኪሜ ይሸፍናል
👯‍♂️ራሳችንን የምና ዝናናበት
💪ብርታታችን የምንፈትሽበት
🎁ሽልማት የምንሸለምበት
ሁሉንም ዝግጅት ያጠናቀቅን ሲሆን 10,000 ቲሸርት ተዘጋጅቷል ፈጥነው በቴሌ ብር / cbe1000009631198 ወይም ቢሮ ደውለው ይመዝገቡ
📞 O909 57 0000, 0909 67 0000

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የአሜሪካ የስለላ ድርጅት(ሲአይኤ) ከፍተኛ ባለስልጣን ልጅ ለሩሲያ ወግኖ ሲዋጋ በዩክሬን መገደሉን አንድ ሪፖርት አመላከተ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16594/

#Ethiopia | የሲአይኤ ቃል ​​አቀባይ አርብ ዕለት ከኤን ቢ ሲ ጋር በነበረው ቆይታ እንደተናገረው አንድ ከፍተኛ የሲአይኤ ባለስልጣን ልጅ ባለፈው አመት “በዩክሬን ግጭት ውስጥ እያለ” መሞቱን ይፋ አድርጓል። የሲአይኤ የዲጂታል ይዘት ፈጠራ ምክትል ዳይሬክተር የሆነው የጁሊያን ጋሊና የ21 አመቱ ልጅ ሚካኤል ግሎስ እ.ኤ.አ. በ2024 የጸደይ ወቅት መሞቱን ቃል አቀባዩ ተናግሯል።

ኤጀንሲው ሞትን “የግል ቤተሰብ ጉዳይ” ሲል ገልጾ ግሎስ ከአእምሮ ጤና ጉዳዮች ጋር ታግሏል ብሏል። ቃል አቀባዩ መላው የሲአይኤ ቤተሰብ “በደረሰሰው ጥፋት ልባቸው ተሰብሮ ነው” ያሉ ሲሆን ጉዳዩ የብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ተደርጎ እንደማይወሰድም አፅንዖት ሰጥተዋል። ኤንቢሲ እንደዘገበው የግሎስን ሞት ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ያደረገው የሩሲያ ሚዲያ ሲሆን የሩሲያ መንግስት ሰነዶችን እና የማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፎቹን ለዋቢነት ጠቅሷል።

ግሎስ ከሩሲያ ኃይሎች ጋር ከመቀላቀሉ በፊት ወደ ሞስኮ ተጉዟል ሲል ዘገባው አካቷል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ግሎስ በሞስኮ ቀይ አደባባይ ላይ ፈገግ ብሎ የሚያሳይ ፎቶ አጋርቶ ለሩሲያ ጦር ያለውን ርኅራኄ ገልጾ ከዩክሬን ጋር እንደሚዋጋ በፅሁፉ አጋርቶ ነበር። በተጨማሪም የምዕራባውያን ሚዲያዎች ስለ ጦርነቱ እውነቱን ደብቀዋል በማለት የዩክሬን ጦር “ሙሰኛ” እና “የተጨናነቀ” ሲል ገልጿል።
#ዳጉ_ጆርናል

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለቤቶች ልማት 15 ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16596/

#Ethiopia | ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለቤቶች ልማት 15 ነጥብ ስድስት ቢሊየንብ ብር ወጪ መደረጉን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እንደተናገሩት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመንግሥት አስተባባሪነት ለሚከናወኑ ቤቶች ልማት መንግሥት ስድስት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር አቅርቧል፡፡

በግል ዘርፍ ደግሞ ከዘጠኝ ቢሊዮን ብር በላይ ሥራ ላይ ውሏል ብለዋል፡፡

በመንግሥት አስተባባሪነት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ቀጥተኛ በጀት በመመደብ 14 ሺህ 032 ቤቶች፣ ተቋማትንና ባለሀብቶችን በማስተባበር 14 ሺህ 670 ቤቶች እንዲሁም በመልሶ ማልማት ስምንት ሺህ 612 አዲስ ቤቶች መገባታቸውን አመልክተዋል።

በአጠቃላይ በመንግሥት አስተባባሪነት 37 ሺህ 314 ቤቶች መገንባታቸውን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በግል ዘርፍ 210 ሺህ 184 ቤቶች የተገነቡ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዚህ ውስጥ 27 ሺህ 799 ቤቶች በሪል ስቴት ልማት፤ 44 ሺህ 568 ቤቶች በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት እንዲሁም 137 ሺህ 817 ቤቶች ግለሰቦች ባላቸው ይዞታ ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የቤት ፋይናንስ አማራጮችን ለማስፋት ታስቦ የቤት ፋይናንስ የአቅርቦት ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል ጥናት እንደተከናወነ አንስተዋል። ጥናቱን ተከትሎ በረቂቅ ደረጃ የሕግ ማሕቀፍ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል።
Gazette Plus

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የሰሜን ኮሪያ ተዋጊዎች ጀግንነትን ህዝባችን ፈፅሞ አይረሳውም አሉ ፑቲን

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16598/

#Ethiopia | በሩሲያ ኩርስክ የዩክሬን ኃይሎች ሽንፈት ላይ የተሳተፉትን የኮሪያ ተዋጊዎች ጀግንነትን ህዝባችን ፈፅሞ አይረሳውም ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ

“የኮሪያ ወታደሮች ሩሲያን እንደ ሀገራቸው በመቁጠር ሀገራችንን ለመከላከል ከጦር ኃይላችን ጎን ለጎን በመቆም ያሳዩትን ጀንነትና ወዳጅነት እናከብራለን” ሲሉ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።

የኮሪያ ወታደሮች ሃላፊነታቸውን በክብርና በጀግንነት በመወጣት ዘላለማዊ ታላቅነት ተጎናፅፈዋል ሲሉ ፑቲን አጽንኦት ሰጥተዋል ።

“የኮሪያ ወዳጆቻችን በትብብር፣ በፍትህ እና በእውነተኛ የወዳጅነት ስሜት በመነጨ መልኩ ሃላፊነታቸውን ተወጥተዋል። ይህንን በእጅጉ እናደንቃለን፤ እንዲሁም የሀገሪቷን መሪ ክቡር ኪም ጆንግ-ኡን፣ መላው አመራርቸው እና የሰሜን ኮሪያን ህዝብ ከልብ እናመሰግናለን” ብለዋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል ።

በሌላ ዜና ሰሜን ኮሪያ ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው ዩክሬንን የሚዋጉ ወታደሮችን መላኳን ለመጀመሪያ ጊዜ አረጋግጣለች፡፡

በመንግሥታዊው የዜና ወኪል ኬሲኤንኤ ላይ አገሪቱ ጦር ባሠራጨው ዘገባ ወታደሮቹ በመሪው ኪም ጆንግ ኡን ትዕዛዝ የኩርስክን ክልል “ሙሉ በሙሉ ነጻ እንዲያወጡ” ረድተዋል ሲል ገልጿል።

የፒዮንግያንግ ይህንን ያሳወቀችው የሩሲያ አዛዥ ቫለሪ ጌራሲሞቭ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮችን “ጀግንነት” ካደነቁ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሲሆን፣ ይህም ሞስኮ ተሳትፏቸውን በይፋ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳወቀችበት ሆኗል።

ከሰሜን ኮሪያ ከተላኩት 11 ሺህ ወታደሮች መካከል ቢያንስ አንድ ሺህ ያህሉ በሦስት ወራት ውስጥ መገደላቸውን እንደሚያምኑ ቀደም ሲል የምዕራባውያን ባለሥልጣናት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሄራሲሞቭም አክለውም ሞስኮ የኩርስክ ግዛትን ሙሉ በሙሉ መልሳ መቆጣጠሯን ተናግረዋል። ይህ ግን በዩክሬን ውድቅ ተደርጓል።

ለመግለጫው ምላሽ የሰጠችው አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ ጦርነቱን በማስቀጠሏ ኃላፊነቱን መሸከም አለባት ብላለች ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
#ethioFm

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ለ 1 ሳምንት ብቻ የወጣ ታላቅ ቅናሽ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16600/

❗️

106 ካሬ ባለ 3 መኝታ

ጠቅላላ ዋጋ – 11,342,000 ብር
10% ቅድመ ክፍያ – 1,134,200 ብር
ቀሪው 90% በ 3 ዓመት የሚከፈል

ሙሉ ለሚከፍል 40% ቅናሽ ተደርጎለት በካሬ 64,200 ይሆናል ይሄ ማለት

ከቅናሽ በኋላ ጠቅላላ ዋጋ – 6,805,200 ብር

ሙሉ በመክፈልዎ ያገኙት የቅናሽ መጠን – 4,536,800 ብር

📱📞 +251908770077
+251982770077

ወይም በዋትሳፕ ያውሩን – https://wa.me/251908770077?text

N:B ሳርቤት አካባቢ አሁን ያለው የካሬ ዋጋ ከ 130,000 ብር በላይ ነው!

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በከተማ አስተዳደሩ ሥር ለአደጋ ተጋላጭ ተብለው የሚለዩ ችግሮች ጊዜያዊ መፍትሄ የሚሰጣቸው በመሆናቸው በቋሚነት መፍታት እንዳልተቻለ ተገለጸ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16602/

👉 በዝናብ ወቅት በሚፈጥሩ ውሃ ያቆሩ ጉድጓዶች ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ተብሏል

#Ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክረምት በሚመጣበት ወቅት ለጎርፍ፣ ለመሬት መንሸራተት እና ለኤሌክትሪክ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች በየጊዜው ተለይተው ለባለ ድርሻ አካላት እንደሚሰጡ የከተማ አስተዳደሩ የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

“ኮሚሽን መስሪያ ቤቱ በየጊዜው የሚለያቸው አደጋዎች በቋሚነት ይፈታሉ ወይ በተለይም የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ማህበረሰቡ ላይ የሚያደርሱት ችግር ከፍተኛ በመሆኑ ምን እየተሰራ ነው?” ሲል አሐዱ ጠይቋል፡፡

የኮሚሽን መስሪያ ቤቱ ዋና ኮሚሽነር አህመድ መሃመድ በሰጡት ምላሽ “አብዛኞቹ ችግሮች ተሻጋሪ ናቸው” ያሉ ሲሆን፤ “ጊዜያዊ የሆኑ መፍትሄዎች እየተሰጡ በመሆኑ ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት አልተቻለም” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ሆኖም በከተማዋ ከጎርፍ እና መሬት መንሸራተት ጋር በተያያዘ የተለዩ ቦታዎች መኖራቸውን ገልፀው፤ ከእነዚህ ቦታዎች ውስጥ ሳይሰሩ ከአንደኛው ዓመት ወደ ሌላኛው የሚሸጋገሩ መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ዓመት ከተለዩት 300 ለአደጋ አጋላጭ ሁኔታዎች ውስጥ 170 የሚሆኑት መፈታታቸውንም አክለው ገልጸዋል፡፡

“አደጋዎችን መከላከል ላይ መስራት ይገባናል” ያሉት ኮሚሽነሩ፤ “እዚህ ላይ የማንሰራ ከሆነ አደጋዎች መፈጠራቸው እና ጉዳት ማድረሳቸው ግልጽ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቂርቆስ እና ሌሎችም ክፍለ ከተሞች ላይ ችግሮች አሉ” የተባለ ሲሆን፤ የኮሪዶር ልማት የሚካሄድባቸው ቦታዎች ላይ ያሉ ችግሮች ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል፡፡

ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ አክለውም፤ በከተማዋ የዝናብ ወቅት በሚፈጠሩ ዉሃ የሞሉ ጉድጓዶች ውስጥ አደጋዎች እየተፈጠሩ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በውሃ በተሞሉ ጉድጓዶች ውስጥ ለመዋኘት ብለው የሚገቡ ሕጻናትና ወጣቶች ለህልፈት መዳረጋቸውን ገልጸው፤ የጎርፍ አደጋም ቢሆን ትኩረት የሚፈልግ መሆኑን ተናግረዋል።

“ይህን ለመከላከል ሥራዎች እየተሰሩ ቢሆንም በሁሉም ቦታዎች ላይ መድረስ የማይቻል በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል” ብለዋል።

ለአብነትም የእሳት አደጋ፣ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ ቢከሰት ጉዳቱን ለመቀነስ የሚያስችል መግቢያ የሌለው በሚል እንዲሁም፤ ለሁሉም አደጋዎች ተጋላጭ የሆኑ በሚል በጥናት መለየቱን ገልጸዋል።

“በከተማዋ ውስጥ በወንዞች አቅራቢያ የተሰሩ ቤቶች ላይ የመሬት መንሸራተት አደጋ ያጋጥማል” ያሉት ኮማንደር አህመድ፤ አስቀድሞ መነጋገርና ሌላ ተለዋጭ መፍትሄዎችን ማሰብ እንዲሁም ለአደጋ ተጋላጭ የሆነው አካል ከቦታው ለመዘዋወር ፈቃደኛ መሆን እንዳለበት አንስተዋል።

ለዚህም ለአደጋ ተጋላጭ ቦታዎች ላይ ሆነው ‘ምንም አይፈጠርም’ በሚል በመዘናጋት ለአደጋ የሚጋለጡ መኖራቸውን የገለፁ ሲሆን፤ “ይህም መታረም አለበት” ብለዋል።
#ahaduRadio

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ተጀመረ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16604/

ቃላችን በተግባር የምናሳይበት ጌዜው ደርሷል፦ ኦቪድ ሪልስቴት

#Ethiopia | አንድ ከተማ እየገነባ የሚገኝው ኦቪድ ሪልስቴት የ90ሺህ መኖርያ ቤቶች ሽያጭ በይፋ መጀመሩን አስታወቀ።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገነባው እና “ኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ” የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው ፕሮጀክቱ፤ ኦቪድ ግሩፕ በተሰኘ የግል ድርጅት የሚገነባ ነው።

ኦቪድ ሪል ስቴት በልዩነት ያዘጋጀውና እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የዋጋ ቅናሽ የሚያስገኘው ታላቅ የቤቶች ሽያጭ ኤክስፖ ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ፕሮጀክት የሽያጭ ቢሮ ተጀምሯል።

የኦቪድ ሆልዲንግ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ ታደሰ እና የሌሎች እህት ኩባንያዎች ዋና ስራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት ዛሬ ማለዳ የው ልዩ የዋጋ ቅናሽ የቤቶች ሽያጭ ኤክስፖ እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።

የመጀመሪያዎቹ 100 ቤት ገዢዎች ከ1 ሚሊዮን ብር ቅናሹ ተጨማሪ ልዩ የዋጋ ቅናሽ የተደረገላቸው ሲሆን፣
በኦቪድ ልዩ የቤቶች ሽያጭ ኤክስፖ በዋል።

በዕለቱ ወደ ሽያጭ ቢሮው ጎራ ያሉ ደንበኞች ሞዴል ቤቶችን ተዘዋውረው በመጎብኘትና በቂ መረጃ በመያዝ ከስቱዲዮ ጀምሮ ባለ 1፣ ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ ቤቶች በአማራጭ የቀረቡላቸውን ቤቶች በከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ ሲሸምቱ ውለዋል።

ከቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በ8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ፕሮጀክት ቢሮ
ለአስር ቀናት በሚቆየው ኤክስፖ ለሚሳተፉ ደንበኞች ነጻ የትራንስፖርት፣ የምግብና መጠጦች አቅርቦት ተሟልቷል።

ለደንበኞች ከቡልቡላ ሪፌንቲ እና ከኮዬ ፈጬ አደባባይ ወደ ሽያጭ ቢሮው የደርሶ መልስ ነጻ የትራንስፖርት አቅርቦት ከጠኋቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

በዚህ ፕሮጀክቱ 90ሺህ መኖርያ ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል።

ኦቪድ ግሩፕ የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ጥያቄ ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጾ፤ ለዚህም በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ አስታውቋል።

“ባለፉት ዓመታት ቃላችንን በተግባር ማሳየት ችለናል” ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው “ዛሬም የገባነውን ቃል በተግባር አሳይተን እናረጋግጣለን” ሲሉ ገልጸዋል።

በ565 ሄክታር ላይ የሚያርፈው የመኖርያ ቤት ግንባታው፤ ከ400 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ያሉት የኦቪድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዮናስ ታደሰ ናቸው።

ኦቪድ ለዚህ ፕሮጀክት 5 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚያደርግም ነው የገለጸው።

በዚህ ግንባታ የተለያዩ አገልግሎቶች ያሉ ሲሆን ከ80በላይ ትምህርት ቤቶች ሆስፒታሎች የገበያ ማዕከላትና ሌሎችም አገልግሎቶች እንዳሉት ነው የተገለጸው።

ኦቪድ አላማው የገባውን ቃል በተግባር ማሳየት ነው ያሉም ሲሆን ሁሉም ነዋሪ የአንገት ማስገቢያ ማበጀት ነው ተቀዳሚ ስራችን ብለዋል።

ኦቪድ ሆልዲንግ በዘርፉ የ12 አመታት ልምድ ያለው፣ በስሩ ከ30 በላይ ኩባኒያዎችን ያቀፈ ተቋም መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከ10ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የስራ ዕድል መፍጠሩ አስታውቋል።

ኦቪድ ባሁኑ ሰአት 15 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ ነው ያስታወቀው።

ኦቪድ ሆሊዲንግ የህዝብ ሀብት እንደመሆኑ መጠን መልሶ ለማህበረሰቡ በማበርከት በአዲስ አበባና በመላ ኢትዮጵያ የማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ተብሏል።

==
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክ ቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet