Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
6.17K subscribers
2 photos
4.7K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
በ ኤሌጋንስ ኮንሰርት እየተዝናኑ ዕድለኛ ይሁኑ!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16481/

በዕለቱ 50ሺ ብር ለማሸነፍ፤
Ethiolottery.et ላይ አሁኑኑ ይመዝገቡ፤
የ50 ሚሊየን ብር ሎተሪ ይቁረጡ!

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የሪፖርተር ጋዜጠኛ ከእስር ተፈታ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16483/

#Ethiopia | ለዘገባ ሥራ ወደ ልደታ ክፍለ ከተማ በሄደበት ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በቁጥጥር ስር ውሎ በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጌጃ ሠፈር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ላለፉት ሦስት ቀናት በእስር የቆየው የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አበበ ፍቅር፣ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርቦ በ10‚000 ብር ዋስ ከእስር ተፈታ፡፡

ጋዜጠኛ አበበ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማ ነክ ፍርድ ቤት የቀረበው ከሰዓት በፊት ሲሆን፣ ፖሊስ ጋዜጠኛውን ለምን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለው ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

ፖሊስ ለችሎቱ እንዳስረዳው ጋዜጠኛ አበበ ፍቅር ፈቃድ ሳይጠይቅና ጋዜጠኛ መሆኑንም የሚያስረዳ ምንም ዓይነት መገለጫ (መታወቂያ) ሳይኖረው፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ኃላፊዎችንና መሥሪያ ቤቱን ቪዲዮ ሲቀርፅና ፎቶ ሲያነሳ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ተናግሯል፡፡ ሁከትና ረብሻ ለማስነሳት እየተንቀሳቀሰ እንደነበርና ከበስተጀርባው ያለውን ማጣራት አስፈላጊ በመሆኑ፣ የዋስትና መብቱ ቢከበር መረጃ ሊያጠፋና እሱም ላይቀር ስለማይችል ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

የተጠርጣሪ ጋዜጠኛ አበበ ጠበቃ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት፣ ደንበኛቸው ጋዜጠኛ መሆኑን ተናግረው፣ ጋዜጠኛ ስለመሆኑ የሚገልጽ ምንም ዓይነት ሰነድ የለውም በሚል ፖሊስ ስላቀረበው ክስ የሚሠራበትን ተቋም በችሎት ጭምር ደውሎ ማረጋገጥ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

ጋዜጠኛ አበበ በክፍለ ከተማ የተገኘው፣ በመሥሪያ ቤቱ ተገኝተው በክፍለ ከተማው የደረሰባቸውን ቅሬታ ያሰሙ ሰዎች ስለነበሩ፣ ዘገባው ሚዛናዊ እንዲሆንና ከአንድ በኩል ብቻ እንዳይሆን፣ የክፍለ ከተማውን ኃላፊዎች ለማነጋገር መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ ዘገባው ገና በሒደት ላይ የነበረና ያልተሠራጨ በመሆኑ፣ እንዲሁም ከአዋጅ 1238/2013 ድንጋጌ አንፃር ሊታሰር እንደማይገባ አስረድተው፣ ይህ እንኳን ቢታለፍ የዋስትና መብቱ እንዲከበር ጠይቀዋል፡፡ ጋዜጠኛው መረጃ ሊያሸሽና እራሱም ላይቀርብ ይችላል ለተባለው፣ የሚሠራበት ድርጅት ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡

ጋዜጠኛ አበበ የሚናገረው ካለ ፍርድ ቤቱ ሲጠይቀው” እኔ ቪዲዮ አልቀረጽኩም። ድምጽም ሪከርድ አላደረኩም” በማለት አስረድቷል።

የሁለቱን ወገኖች ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ፣ ጋዜጠኛ አበበ በ10‚000 ብር ዋስ እንዲለቀቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡(ሪፖርተር)

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ዘመን ጠቀስ ዘመነኛ ዕድል!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16485/

http://xn--ethiolotterey-ok6c.et/ ይመዝገቡ፤

የ50 ሚሊየን ብር ሎተሪ ይቁረጡ!

ሲመዘገቡ በሚሊኒየም፣ በማሪዮት እና ግዮን ኮንሰርቶች ዘና ፈታ እያሉ በእያንዳንዱ ኮንሰርቶች 50 ሺህ ብር ያሸንፉ!

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የአዲስ አበባ ፖሊስ ያመከነው አደገኛው የዝርፊያው ወንጀል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16487/

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ፖሊስ በተቀናጀ መልኩ ባደረገው ዘመቻ በርካታ የቅሚያ ወንጀል የፈጸሙ አካላትን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ አድርጎባቸዋል።

ፖሊስ ይዞ ምርመራ ያደረገባቸው የዝርፊያ ወንጀል የፈጸሙትን ብቻ ሳይሆን የሌቦቹ ተባባሪ የሆኑትንም ጭምር ነው።

በዚህም መሰረት ፖሊስ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሰዎች ራሳቸውን ለመከላከል በማይችሉበት ደረጃ አፍነው ዝርፊያ የፈጸሙ 34 ተጠሪጣሪዎች እና ንብረቶችን ሲገዙ የነበሩ 8 ተቀባዮቻቸውን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ አጠናቅሮባቸዋል።

ይህን ዘራፊዎቹ ራሳቸው ቃላቸውን በሰጡበት ጊዜ ያረጋገጡት መሆኑን የፖሊስ ማስረጃ ያሳያል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ምክትል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ፥ ዘራፊዎቹ እንዴት ተደራጅተው ሰዎችን እንደሚቀሙ ይናገራሉ፡፡

ምክትል ኮሚሽነር እንደሚሉት እነዚህ ዘራፊዎች መሣሪያ እና ተሽከርካሪን በመጠቀም፣ እንዲሁም አልፎ አልፎ ያለ ተሸከርካሪ እየተንቀሳቀሱ በቡድን ሰዎች ራሳቸውን እንዲስቱ ካደረጉ በኋላ የሚፈልጉትን ዘርፈው ከአካባቢው ይሰወራሉ።

ሌላው የዝርፊያቸው ስልት የአዲስ አበባ እና የፌዴራል ፖሊስ በመምሰል የሚፈጸም እንደሆነ የሚናገሩት ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን፣ የፀጥታ አካላቱን የደንብ ልብስ በመልበስ እና መታወቂያዎችን በመጠቀም የባለሀብቶችን ቤቶች እየመረጡ ለፍተሻ ተልከው እንደሄዱ በማስመሰል በመግባት የሚፈልጉትን ዘርፈው ይሰወራሉ።

እንደዚህ ዓይነት የተደራጀ የዝርፊያ ስልት የመጀመሪያው ምልክት የታየው በቦሌ ክፍለ ከተማ እንደሆነ የሚጠቅሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ክትትሉ ሲቀጥል በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች ተመሳሳይ ድርጊቶች እንደሚፈጽሙ እንደተደረሰበት ያወሳል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አድማሱ ኢፋ እንሚናገሩት፥ ከሕብረተሰቡ የሚገኙ ጥቆማዎችን በመጠቀም የወንጀለኞቹን ማንነት እና የት እንደሚገኙ ሊደረስበት ችሏል።

ተበዳዮችም ዘራፊዎቹ በፈርጣማ ክንዳቸው እንደሚይዟቸው እና ራሳቸውን ለመከላከል እንዳይችሉ አድርገው ጥቃት እንደሚሰነዝሩ ገልጸው፣ ምንም ጥንቃቄ ቢያደርጉ እንኳን ከነሱ ማምለጥ እንዳልቻሉ ይጠቅሳሉ።

ተበዳዮቹ እንደሚሉት ክስተቱ ከተፈጸመባቸው በኋላ ራሳቸውን ስተው ምን እንደተፈጸመባቸው እንኳን የሚያውቁት ሰዎች መጥተው ከቀሰቀሷቸው በኋላ ነው።

ከዘራፊዎቹ የተደረጃ አካሄድ እና ዱካ ማጥፋት አንጻር ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ ከፍተኛ መስዋዕትነት እንደከፈለ ገልጿል።

ከእነዚህ ዘራፊዎች መካከል የቁስ ዝርፊያ ከመፈጸም ባለፈ የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ እንደሚገኙበት ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን ተናግረዋል።

ከመካከላቸው ሀገርን ሲያውኩ ከነበሩ ወገኖች ጋር የፀጥታ አካላትን ሲያጠቁ የነበሩ እንዳሉበት የጠቀሱት ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ፥ ከዚህ በኋላ በከፍተኛ ደረጃ ስጋት በማይሆኑበት ደረጃ ከያሉበት ከተያዙ በኋላ በቂ ፍርድ የሚያገኙበት ማስረጃ መደራጀቱን ገልጸዋል።

ይህ በአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው ውጤት ማንም ሰው ከሕግ በላይ እንደማይሆን እና ወንጀል ሠርቶ ተሰውሮ መቅረት እንደማይቻል ማሳያ እንደሆነ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል።

በለሚ ታደሰ
Via EBC

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ከ20 ዓመት በኋላ ተገናኝተዋል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16489/

ሃምሳ ቴብሎች ብቻ ተዘጋጅተዋል!
አንዱ ቴብል ላይ አምስት የክብር ሰዎች ብቻ ይገኛሉ።

ቡክ የሚደረገው
በዚህ ስልክ ብቻ ነው።
0911225998

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16491/

#Ethiopia | 12 የፌዴራል ተቋማት በአንድ ቦታ የተሰባሰቡበት የአንድ ማዕከል አገልግሎት በፓይለት ፕሮግራም ሥራ መጀመሩ ተነገረ።

” ” በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው ተብሏል።

የአሰራር ስረአቱ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያስችል ተመላክቷል።

ይህም ባለጉዳዮች ወደ ተለያዩ ቢሮዎች የሚያደርጉትን ምልልስ፣ ረጅም የወረፋ ጥበቃ እና ከወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን የሚያሰቀር እንደሆነ ተገልጿል።

አሁን ሥራ ለጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት 12 የፌደራል መንግስት ተቋማት የተቀላቀሉ ሲሆን 41 የሚሆኑ የህዝብ አገልግሎቶችን እንዳቀረቡ ይፋ ተደርጓል።

አገልግሎቶቹም ከፈቃድ አሰጣጥ ጀምሮ ፋይዳ ድጅታል የመታወቂያ ምዝገባና ሌሎችንም አካትተዋል።

በአጠቃላይ በፓይለት ፕሮግራም በአንድ ስፍራ 41 አገልግሎቶች በመሰጠት ላይ የሚገኙት 12 ተቋማት ፦

1. የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት
2. የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት
3. የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሌት
4. የገቢዎች ሚኒስቴር
5. የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
6. የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር
7. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
8. የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
9. የትምሀርት ምዘና እና ፍተናዎች አገልግሎት
10. የኢትዮ ፖስታ
11. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
12. ኢትዮ ቴሌኮም ናቸው።

ሀሉም ተቋማት በቴክኖሎጂ አማካኝነት በትስስር አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የጠ/ሚ ፅ/ቤት ገልጿል።

#PMOEthiopia

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ለአራህማን እንግዶች የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16493/

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በወረደለት አቅጣጫ መሠረት የ1446ኛውን የሐጅ ምዝገባ እንግልት አልባ በሆነ መንገድ አጠናቆ ወደ ቀጣዩ የጉዞ ቅድመ ዝግጅት ለመሸጋገር በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል።

ከፍተኛ ምክር ቤታችን በዕቅድ ካስቀመጠው የሀጅ ምዝገባና ተያያዥ የአገልግሎት ስራ ውስጥ አብዛኛውን በማጠናቀቅ ለሁጃጆች አስፈላጊውን አገልግሎት በማቅረብ ቪዛ እጃቸው ላይ እንዲገባ ማድረግም ችሏል፡፡

በመሆኑም ክፍያ ፈጽማችሁ እና የፓስፖርት ሂደት አጠናቃችሁ ቪዛ ያልወሰዳችሁ ሁጃጆች እስከ ሰኞ ሚያዚያ 20/2017 ድረስ በአዲስ አበባ መጅሊስ የምዝገባ ጣቢያ እንድታመለክቱ በጥብቅ እያሳሰብን ይህ ካልሆነ ግን እንደሌላችሁ ተቆጥሮ በምትካችሁ ተጠባባቂ ሁጃጆች የሚተኩ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለሁጃጆቻችን ሀጀን መብሩር፣ ወሳዕየን መሽኩር ወቲጃረተን ለንተቡር እንዲሆንላችሁም በዚሁ አጋጣሚ ዱዓችንን እንገልፃለን።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በጀርመን በተካሄደው የአዲዳስ ውድድር ዮሚፍ ቀጀልቻ እና መዲና ኢሳ አሸነፉ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16495/

#Ethiopia | ዛሬ በጀርመን በተካሄደው የአዲዳስ አዲዜሮ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀዳጅቷል ።

በ5 ኪሎ ሜትር ሴቶች ውድድር አትሌት መዲና ኢሳ ስታሸንፍ በወንዶቹ ዮሚፍ ቀጀልቻ በቀዳሚነት አጠናቋል ።

ከፍተኛ ፉክክር የተደረገበት የሴቶች 5 ኪሎ ሜትር የባለፉት ሁለት አመታት አሸናፊዋ አትሌት መዲና ኢሳ በ14:48 በመግባት በቀዳሚነት አጠናቃለች ።

አትሌት ፎትየን ተስፋይ 14:50 በመግባት ሁለተኛ ስትወጣ ፣አትሌት ገላ ሀምበሴ ሶስተኛ ደረጃ ይዛለች ።

በወንዶች 5 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በ12:54 በመግባት አሸንፏል።

በሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ፋንታዬ በላይነህ በ30:30 ሁለተኛ ስትወጣ፣አትሌት ሰናይት ጌታቸው በ30:31 ሶስተኛ ፣አትሌት ግርማዊት ገብረእግዜር በ30:41 አራተኛ ፤ አለምአዲስ እያዩ በ31:15 አምስተኛ ፤ አትሌት ለምለም ንብረት በ 31:40 ስድስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል ።

በወንዶቹ ውድድር አትሌት ገመቹ ዲዳ በ26: 54 ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል ።

#ዳጉ_ስፖርት

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ግማደ መስቀሉ ያረፈበት መስቀለኛ ቦታ — ግሸን ደብረ ከርቤ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16497/

✍️ ግሸን ደብረ ከርቤ በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ከደሴ ከተማ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 82 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

✍️ ግሸን ደብረ ከርቤ አስደናቂ የተፈጥሮ ገጽታን የተላበሰ፣ ተራራማ፣ 360 ዲግሪ ዙሪያውን ገደላማ የሆነ እና የመስቀል ቅርፅ ያለው አምባ ላይ ያለ ልዩ ስፍራ ነው።

✍️ የግሸን ደብረ ከርቤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፄ ካሌብ ዘመነ መንግስት አባ ፈቃደ ክርስቶስ በሚባሉ አባት ለቤተ ክርስቲያን መስሪያ እንደተመረጠ ይታመናል፡፡

✍️ አባ ፈቃደ ክርስቶስ በንጉሡ ይሁንታ በ517 ዓ.ም የመጀመሪያውን የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን የሰሩት ሲሆን አሰራሩም በገጠሩ የአማራ ምድር በተለመደው የሳር ክፍክፍ ነበር፡፡

✍️ የእግዚአብሔር አብ ታቦት ያለበትን ቦታ የወንዶች ገዳም ሲያደርጉት የእመቤታችን ታቦት ያለችበትን ደግሞ የሴቶች ገዳም አድርገው ሲያገለግሉበት እንደነበር በገዳሙ ያሉት አባቶች ያስረዳሉ።

✍️ የግሽን አምባ የመጀመሪያ የመጠሪያ ስም “ደብረ-ነጎድጓድ” እንደነበር ይነገራል፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ወደ ግሸን መጥተው በአምባው ቤተ ክርስቲያን ለመፈልፈል እንዳሰቡ በሚነገርበት ዘመን ደግሞ የግሸን መጠሪያ ወደ “ደብረ- እግዚአብሔር” በሚል ተቀይሯል፡፡

✍️ ብዙም ሳይቆይ ደብረ እግዚአብሔር የተባለችው ግሸን በንጉሥ ይኩኖአምላክ ዘመነ መንግስት ድጋሚ ስሟ ተቀይሯል፡፡

✍️ በዘመኑ አምባው ከእምነት ቦታነቱ በተጨማሪ የአስተዳደር ቦታ በመሆን የነገሥታት ልጆች እንዲማሩና በዚያው እንዲኖሩ በመደረጉ አምባው “ደብረ ነገሥት” በመባል ተጠራች፡፡

✍️ በኋላም አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉን ከሲናር ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት በዚህ አምባ ሲያሳርፉ አምባው ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል መገኛ ነው በማለት “ደብረ ከርቤ” ብለው እነደሰየሟት በገዳሙ ከሚገኙት የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡

✍️ “ደብረ ከርቤ” ማለትም “መስቀሌን በመስቀል ተራራ ላይ አስቀምጥ” ከሚለው የፈጣሪ ትዕዛዝ የመጣ ሲኾን የመስቀል ተራራ ማለት እንደሆነም ይነገራል።

✍️ በክርስትና ሐይማኖት ዘንድ ለሰዎች ኃጢያተ-ድህነት ሲል የእየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ግማደ መስቀል መገኛ በመሆኗ የተቀደሰች ቦታ እንደሆነችም ይታመናል።

✍️ የግሸን አምባ በተፈጥሮ በመስቀል ቅርጽ የተፈጠረ ሲሆን ዙሪያውን ቀጥ ባላ ገደል የተከበበና ወደ አምባው ሰውም ሆነ ማንኛው ዕቃ የሚጓጓዝበት መግቢያ አንድ በር ብቻ ያለው ነው፡፡

✍️ የነገሥታት ስጦታዎች፣ የብራና መጻሕፍት፣ መስቀሎች እና የተለያዩ ቅርሶች በሙዚየሙ ይገኛሉ፡፡ ሙዚየሙ በአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ በህብረተሰቡ ተሳትፎ እና በገዳሙ በጋራ የተገነባ ነው። ግሸን ደብረ ከርቤ አምባ መጽሐፈ ጤፉት የተባለችው ውድ የብራና መጽሐፍም ይገኛል፡፡

✍️ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ልዩ ቃልኪዳን እንደተገባላት የሚታመነውና “ዳግማዊት ኢየሩሳሌም” በመባል የምትታወቀው ግሸን ደብረ ከርቤ በእምነት እና አሥተዳደር ቁርኝት የፈጠሩባት; ተፈጥሮ ያከበራት ድንቅ ምድር ናት፡፡

✍️ በግሸን ደብረ ከርቤ አምባ የእግዚአብሔር አብ፣ የቅድስት ማርያም፣ የቅዱስ ሚካኤል፣ የቅዱስ ገብርኤል እና የቅዱስ ኡራኤል አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ሲሆን በዋናነት መሰከረም 21 እና ጥር 21 ታላቅ ዓመታዊ የንግስ በዓላት ሆኖ በዓሉ ይከበራል፡፡

✍️ በአሁኑ ሰዓት ከደሴ ወደ ዋድላ ደላንታ የአስፓልት መንገድ በመሰራቱ በእግር እና ተሽከርካሪ የአንባሰል የተራራ ሰንሰለት አካል ከሆነው የግሸን አምባ በቀላሉ መድረስ እና መጎብኘት ይቻላል፡፡

Amhara Culture & Tourism Bureau

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ከምድር በጠፋው ዳይኖሰር ቆዳ የተለያዩ የቆዳ ምርቶች ተሰርተው ለገበያ ሊቀርቡ ነው

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16499/

#Ethiopia | ቲሬክስ የተባለ የዳይኖሰርን ቆዳ በመጠቀም የተሰሩ የቆዳ ውጤቶችን በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት ማገባደጃ ላይ ለገበያ ሊቀርብ መሆኑ ተሰምቷል።

መቀመጫውን በእንግሊዝ ኒውካስትል ያደረገው እና በላብራቶሪ የቆዳ ውጤቶችን የሚያመርተው ድርጅት ከኦርጋኖኢድ ከተባለ ድርጅት ጋር በመሆን የጠፋውን የዳይኖሰር ዘረመልን በመጠቀም የቆዳ ምርቱን ለማምረት መቻላቸውን አስታውቀዋል።

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዳይኖሰር ከምድር ላይ ከጠፋ እጅግ ከመቆየቱ የተነሳ የዳይኖሰርን ዘረመል ከቅሪተ አካል ላይ ማግኘት አይቻልም የሚል አመለካከት ነበር።

ቢሆንም ባለፈው አስርት ዓመታት ውስጥ በተደረገ ምርምር ሳይንቲስቶች ከጠፋ 80 ሚሊዮን ዓመታት አድሜ አስቆጥሯል የሚባለውን የዳይኖሰር ዘረመል ከቅሪተ አካሉ ላይ ማግኘት ችለዋል።

በ2023 ዘረመልን በመጠቀም ብቻ በላብራቶሪ ውስጥ የእንስሳትን ቆዳ መስራት የቻለው ይህ ድርጅት አሁን ላይ ደግሞ የዳይኖሰርን ቆዳ መመለስ እንደሚችሉ ተስፋ ተጥሏል ።

ይህን ቆዳ በመጠቀም የተሰሩ የተለያዩ የቆዳ ምርቶችም እጅግ ጠንካራ እና ለብዙ ጊዜ ይቆያሉ የተባለ ሲሆን በዓመቱ መጨረሻ ላይ ለገበያም ይቀርባሉ ሲል ዘ ቴሌግራፍ አስነብቧል።
#etv

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
*ታላቅ የቤቶች ሽያጭ ኤክስፖ በኦቪድ ገላን ጉራ!*

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16501/

🌸 _እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ!
🌸 ለ10 ቀናት ብቻ!_

ኦቪድ ሪል ስቴት ከቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በ8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እየተከተመ በሚገኘው የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ፕሮጀክት የሽያጭ ቢሮ ከሚያዝያ 20 – 30 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ የሚቆይና እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የዋጋ ቅናሽ የሚያስገኝ ታላቅ የቤቶች ሽያጭ ኤክስፖ ተዘጋጅቶልዎታል!

ከመጀመሪያዎቹ 100 ገዢዎች አንዱ ከሆኑ፣ ከ1 ሚሊዮን ብር ቅናሹ ተጨማሪ ልዩ የዋጋ ቅናሽ ይደረግልዎታል!

ከስቱዲዮ ጀምሮ ባለ 1፣ ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ ቤቶች በአማራጭ ቀርበውለዎታል!

በአስሩ ቀናት ቤትዎን በታላቅ ቅናሽ፣ ትራንስፖርትና ምግብ መጠጥዎን በነጻ እናቀርብልዎታለን! ከቡልቡላ ሪፌንቲ፣ ከኮዬ ፈጬ አደባባይ ወደ ሽያጭ ቢሯችን በምቾት አድርሶ የሚመልስዎት ነጻ የትራንስፖርት አቅርቦት ከጠኋቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ዝግጁ ሆኖ ይጠብቅዎታል!

በልተው ጠጥተው ተዝናንተው፤ ማሳያ ቤቶቻችንን ተዘዋውረው ጎብኝተው፣ ቤትዎን መርጠው ሸምተው ይመለሱ!

*ኦቪድ ሪል ስቴት – ራዕያችን ልማት ነው!*

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ጄኔራል ታመነ ድልነሳው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16503/

#Ethiopia | ኢትዮጵያ ካፈራቻቸዉ ምርጥ ጄኔራሎች አንዱ ሰለነበሩ ሐገራችንን በሐይል ለመደፈር የመጡበንን ጠላቶች በመደምሰ ድል አስመዘገበዉ ደማቅ ታሪክ ከሰሩት የቀድሞ ጄኔራሎች ዉስጥ ጄኔራል ታመነ ድልነሳው አንዱ ነበሩ ::

ለሀገራቸው በዋሉት ውለታ ከወታደራዊ አዛዠነት በተጨማሪ በዉጭ ጉዳይ ሚ/ር ከሚኒተሪ አታሸነነት እሰከ አምባሳደርነት ሙሉ ህይወታቸውን ለሀገራቸው የሰጡ ጀግና ናቸዉ።

ጀግና አዋጊና ተዋጊ የጦር መሪና ድፕሎማቱ ጄኔራል ታመነ
ድልነሳዉ ሠኞ (Monday) April 21 ለረጅም ጊዜ በስደት በኖሩበት በለንደን ከተማ በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል::

በበርካታ የጦር ሜዳ ውጊያዎች ተሳትፈው የሀገርን ሉዓላዊነት፣ የህዝብን ነፃነት ያስከበሩና ደማቅ ድል ያሰመዘገቡት ብርጋዲየር ጄኔራል ታመነ ድልነሳዉ የቀብር ሥርአታቸዉ የሚፈፀመው ለረዠም አመት በስደት በኖሩበት በእንግሊዝ አገር በለንደን ከተማ መሆኑን ቤተሠቦቻቸው ገልፀውልኛል ።

ብሔራዊ ስሜት የታጠቁ ፡፡ የሀገር ክብር፡፡ የዜግነት ኩራትን የተረዱት፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክና ቅርስ ተቆርቋሪና ምርኩዙ በመሆን ከኔ ጋር አብረዉ በየ ኮለጁና በዮኬ ዮኒቨርሰቲወች እየተዘዋወሩ ኢግዚቨሸኖችን አሳይተዋል።

የሀገር ፍቅር አቀንቃኝ ጀኔራል ታመነ ድልነሳዉ የኢትዮጵያ ፣ ባህል የጥንታዊነት ታሪክ ተንተኝ የአርበኝነትን አዋጅ ነጋሪም ነበሩ ::
ነፍስ ይማር ::

የኢትዮጵያ ቅርሰ ማበልፀጊያ ማሕበር ጄኔራል ታመነ ድልነሳው ከዚህ አለም በሞት መለየት የተሠማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለፅን
ለመላዉ ቤተሰቦቻቸዉና ወዳጅ ዘመዶቻቸዉ በሙሉ መፅናቱን እንዲሠጥልን ፈጣሪን እንለምናለን።

አሜን::
አለባቸዉ ደሳለኝ አበሻ (ለንደን) 🇬🇧

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ሐበቫ ቁርጥ እና ሬስቶራንት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16505/

ለምርቃት በክብር ተጠርተዋል

#Ethiopia | በሀዋሳ ከተማ ስመጥር የሆነው ሀበሻ ሆቴል የስራ አድማሱን በማስፋት ቁጥር 2 ቁርጥና ሬስቶራንት በአዲስ አበባ ከፍቶ ለምርቃት ዝግጁ ሆኗል።

የዚህ ስኬታችን ተቋዳሽ ይሆኑልን ዘንድ ከቤተሰብዎ እና ከወዳጆችዎ ጋር በምርቃቱ ላይ እንዲገኙልን በማክበር ጠርተንዎታል።

የምርቃቱ ቀናት

ሚያዚያ 25 ቀን 2017ዓ.ም
ሚያዚያ 26 ቀን 2017ዓ.ም
ሚያዚያ 27 ቀን 2017ዓ.ም

በምርቃቱ ላይ እንዲገኙልን በአክብሮት ጠርተንዎታል።

አድራሻ
ቦሌ ስካይ ላይት ሆቴል ጀርባ፤
የቀድሞው አምስተርዳም ሬስቶራንት የነበረው

ጠሪ አክባሪዎ
ወ/ሮ ማህሌት ዘገየ

+251916171723
+251911428744

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የአፍሪካ ካሚሎት!..

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16507/

#Ethiopia | “ኑ ጎንደርን እንሞሽር” በሚል ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል የሚዘጋጀውን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ሊከናወን ነው።

ጎንደር ኢትዮጵያዊ ከተማ ግን ደግሞ የአፍሪካ ካሚሎት በሚል ታሪክ የሚገልፃት መናገሻ ናት።

ኢትዮጵያዊያን በአንድነት የገነቧት መኩሪያቸውና ማገጫቸው ጥንታዊ ከተማ ነች ይሁን እንጂ ታሪካዊ ስሟ የገነነውን ያህል በልማት ያልገፋች የዕድገት ግስጋሴዋ ደግሞ የቀጨጨ ነበር፤ በመሆኑም ኢትዮጵያዊያን በስነ-ጥበብና በስነ-ኪነት ታሪኳ ሞገስ የተላበሱባትን ያህል በዕድገቷ ዘገምተኝነት ደግሞ ኑዋሪዎቿ ቅሬታቸውን ሲገልፁ ቆይተዋል።

አሁን ላይ ጎንደርን ወደ ቀደመ ከፍታዋ ለመመለስ እና በሚመጥናት ታሪኳ ልክ በጋራ ለማሳደግ ብሎም ተተኪው ትውልድ የሚኮራበት ታሪክ ስርቶ ለማስረከብ ብሎም ጥንታዊቷን ከተማ በማዘመን የቱሪስትና የባህል ማዕከል ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ሚያዚያ 20 በሸራተን አዲስ ይካሄዳል።

በገቢ ማሰባበሰቢያ ፕሮግራሙ ለ2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት ማስፈፀሚያ የሚውል 1.7ቢሊየን ብር ይሰበሰባል ተብሎ የሚጠበው ሲሆን 2ኛውን ዙር የኮሪደር ልማት መስከረም ወር 2018 ዓ/ም ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ በመደረግ ላይ ነው።

በጎንደር ከተማ የሚካሄደው የኮሪደር ልማት የስራ ባህል የቀየረ ሲሆን ክህበረተሰቡ ጋር በመሆን 24 በትኩረት እየተተገበረ ይገኛል።

በኮሪደር ልማቱ የሚሰሩ ስራዎች ህዝብን ያከበሩና ለህዝብ ቅድሚያ የሚሰጡ ሲሆን ሰዎኛ ባህሪበተላብሰው የሚተገበሩ ናቸው።

የጎንደር ከተማ ከንቲባ የተከበሩ አቶ ቻላቸው ዳኘው በተገኙበት ሰኞ ሚያዚያ 20 ከቀኑ 11:00 ጀምሮ የገቢ ማሰባሰቢያው የሚጀምር ሲሆን እናት ጎንደር በልጆቿ ልትሞሸር ተጣርታለች።

“የጎንደር ወርቃማ ዘመንን ለመመለስ ኑ አብረን እንስራ”

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የውብ ተፈጥሯዊ መስህቦች መገኛው – የጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16509/

#Ethiopia | የጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ብሄራዊ ፓርኮች አንዱ ሲሆን መገኛው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ውስጥ ነው፡፡

የፓርኩ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 360 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ሲሆን በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ ከአበሽጌ፣ ከቸሃ እና ከእኖር ወረዳ የተወጣጡ በአጠቃላይ 24 ቀበሌዎች ያጎራብቱታል፡፡

ፓርኩ ከአዲስ አበባ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ 178 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በዚህም በኢትዮጵያ ከሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች መካከል ለአዲስ አበባ በጣም በቅርበት የሚገኝ ብሔራዊ ፓርክ ያደርገዋል፡፡

ብሔራዊ ፓርኩ ስያሜውን ያገኘው ከጊቤ ወንዝና ሸለቆ መነሻ አድርጎ ነው፡፡ በብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ ሙሉ ቀን በርካታ ወንዞች ያለማቋረጥ ቁልቁል ይወረወራሉ፡፡

የሉቄ ፍል ውሃ ፓርኩን ለየት ካደረጉት ገፅታዎች አንዱ ሲሆን ከ30 እስከ 50 የሚደርሱ የፍል ውሃ ምንጮች ቦታቸውን ጠብቀው ያለማቋረጥ ቀኑን ሙሉ ይፍለቀለቃሉ፡፡

ዳጎሳ ፏፏቴ፣ አቾ ፏፏቴ፣ ቃሽቃሽየ ፏፏቴ፣ ደርኪ ፏፏቴ ቁልቁል ሲወረወሩ ከሚያስተጋቡት ድምፅ ጋር ተዳምሮ ተፈጥሮውን ይበልጥ ያደምቁታል፡፡

ፓርኩ የተለየዩ የሀገር በቀል እፅዋት እና አዕዋፋት መገኛ ሲሆን የተለያዩ ብርቅዬ አዕዋፋት ለመመልከት ሁነኛ ስፍራ ነው፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ መረጃ እንደሚያመለክተው ፓርኩ ከዚህ በተጨማሪም የበርካታ ጉማሬዎች እና ሌሎች የዱር እንስሳቶች መኖሪያ ነው።

#etv #Ethiopia #tourism #tour #attraction #destiny #share #ShareThisPost

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የዘማሪት ሲስተር ሊድያ ታደሰ መልዕክት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16511/

የዘማሪት ሲስተር ሊድያ ታደሰ መልዕክት👇

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
Hon’ble PM’s #MaanKiBaat of 27 April focused on India’s #HADR response left deep impressions on Ethiopians and Indian’s

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16513/

Hon’ble PM’s #MaanKiBaat of 27 April focused on India’s #HADR response left deep impressions on Ethiopians and Indian’s in Ethiopia. The event saw overwhelming response and wide participation from people from all walks of life.

Special mention of the role of Indian Community in Ethiopia in addressing Congenial Heart Disease among Ethiopian children who could not access & afford advanced medical treatment has boosted the morale of Indians in Ethiopia and inspired them to take forward their Mission.
#indiaethiopia
Ministry of External Affairs, Government of India
#MannKiBaat
#HADR
#diasporaengagement
#PMOIndia
#DDIndia
#PIB_India

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ኢራን : ወደብ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር 25 ደረሰ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16515/

🇮🇷

#Ethiopia | በኢራን ወደብ ላይ በደረሰ ከፍተኛ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር 25 ሲደርስ 800 ሰዎች ደግሞ መጎዳታቸው ተገልጿል፡፡

ፍንዳታው የደረሰው ቅዳሜ ጧት በደቡባዊ ባንዳር አባስ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ሻሂድ ራጃኢ የንግድ ወደብ ላይ ነው።

በአደጋው በአቅራቢያ ያሉ ሕንፃዎች እና መኪናዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት እና ከተጎዱት በተጨማሪ ስድስት ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።

የአየር ላይ ምስሎች ቢያንስ ሶስት አካባቢዎች በእሳት መያዛቸውን እና የኢራን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ከጊዜ በኋላ እሳቱ ከአንድ ኮንቴነር ወደ ሌላ እየተዛመተ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አደጋውን ተከትሎ በአካባቢው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዛሬ ዝግ ሆነው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ፍንዳታው ከተከሰተ በኋላ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ተቀጣጣይ ቁሶች ወደሚከማቹበት ኮንቴይነሮች ተዛምቷል።

የኢራን ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው፤ ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16517/

#Ethiopia | መነሻና መድረሻውን መስቀል ዐደባባይ ያደረገው የ2017 ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ፡፡

የሩጫ ውድድሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን፤ ውድድሩም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ 4ኛ ዓመት ዝግጅትን አስመልክቶ የተሰናዳ መሆኑ ተገልጿል።

በዝግጅቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

አቶ መላኩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር ስፖርት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡

የሩጫው ዋና ዓላማ የሀገርን ምርት ለውጭው ማኅበረሰብ ማስተዋወቅ መሆኑን አስረድተው፤ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን ምርት ለብሰው ሲሮጡ በአትሌቲክሱ ያገኘነውን ድል በኢንዱስትሪውም መድገም እንደምንችል ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ወ/ሮ ሸዊት በበኩላቸው፤ የውጭ ምንዛሪን ለማዳን ዜጎች በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የስፖርት አልባሳትንና ሌሎች መስሪያ ቁሳቁሶችን ሊጠቀሙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በሁለቱም ጾታ በቅደም ተከተል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ ተወዳዳሪዎች፤ የ300 ሺህ፣ የ200 ሺህ እና የ100 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በውድድሩ የአምራች ኢንዱስትሪ ተዋናዮች፣ አጋር ድርጅቶች፣ ከ34 በላይ የአትሌቲክስ ክለቦችና መላው የአትሌቲክሱ ቤተሰቦች በአጠቃላይ ከ14 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ አሸነፈች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16519/

🇪🇹

#Ethiopia | ትዕግስት አሰፋ የ2025 የለንደን ማራቶንን የቦታውን ሰዓት በማማሻሻል አሸናፊ ሆናለች አትሌቷ 2:16.16 የነበረውን 2:15.50 ገብታለች

ኬንያዊቷ አትሌት ጄፕኮስፔ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ በውድድሩ ስትጠበቅ የነበረችው ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሳለች።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet