Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
6.17K subscribers
2 photos
4.71K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
የሥዕል ጋለሪዎችና ተመልካች እየበዛ ቢመጣም ባህልና ወግን በማድመቅ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎለብቱ የስዕል ውጤቶች አነስተኛ መሆናቸው ተገለጸ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16448/

#Ethiopia | የስዕል ጋለሪዎችና ተመልካች እየበዛ ቢመጣም ባህልና ወግን በማድመቅ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎለብቱ የስዕል ውጤቶች ዝቅተኛ መሆናቸውን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ሃሳባቸውን ያሳፈሩ ሰአሊያን ተናግረዋል።

ከቀድሞው ዘመን አንጻር በዚህ ዘመን ሰአሊያንም ተመልካችም እያደገ የመጣበት ነው በማለት ነገር ግን በዚኛው ዘመን ባህልና ታሪክን በጥልቀት የተመለከቱ ስራዎች በቁጥር አነስተኛ መሆናቸውን ሰአሊ ይልቃል ቦጋለ ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በተለይ እንዲህ ባሉ የበአል ሳምንታት ከሃይማኖታዊ መሰረትም ይሁን ከባህላዊ ትውፊት የተቀዱ ማንነቶችን ተረድቶ ማህበራዊ ትስስርን ለማስፋፋት የሚሰሩ የስእል ጥበባት አነስተኛ መሆናቸውን ባለሙያው ይናገራሉ። ፈረንጆቹ እንደ ጸሎተ ሃሙስ ያሉትን በአላት ታላቁ እራት በማለት በስፋትና በጥልቀት ለየትውልዳቸው እሳቤውንና ሰዋዊ ትርጓሚውንም በስእል ጥበባቸው አኑረው አልፈዋል የሚሉት ባለሙያው በኛ ሀገር መሰል ጠቃሚ ሁነቶችን ለመስራት የሙያም የፍላጎትም ችግር መኖሩን በመግለጽ ፖለቲካዊ እሳቤን ምክንያት በማድረግም የማይሰሩ መኖራቸውንም ገልጸዋል።

ችግሩ የራሱ የባለሙያው ነው ሲሉ ለጣቢያችን ሃሳባቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላኛው ሰአሊ ማህደር ታሪኩ ናቸው። የታሪክ መረጣም፣ ፍላጎትም፣ ጥረትም እንብዛም አይስተዋልም የሚሉት ባለሙያው ነገር ግን እንደ ሀገር የሃይማኖታዊ ሆነ ባህላዊ ታሪክና ትውፊት ሃብታም ነን ሲሉ ተናግረዋል። ተመልካቹም ከፍ ባለ ስራቸው ከፍ ያለ እይታና ምልከታ ኖሮት እንዳይሞግታቸው የባለሙያዎቹ ጥረትና ውጤት ወሳኝነት አለው በማለት በራሱ የስእል ጋለሪና ተመልካች መስፋፋቱ ግን መበረታታት አለበት ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያዊ ሰአሊያን እንዲህ ያሉ የበአል ሳምንታትንም ሆነ መጪውን ሰፋፊ የሰርግ ሁነቶች በጥበባቸው ሰርተው የሀገሩን መልክ በማጉላት ሂደት ውስጥ ማለፋቸውን በመግለጽ የአሁኖቹ የዘርፉ ባለሙያዎችን የሀገር ሁለንተናዊ አስተሳሳሪ ማንነት ግድ ሊላቸው እንደሚገባ ባለሙያዎቹ አመላክተዋል።
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ሁሌ ቡና – ምርቃት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16450/

COFFEE HOUSE

#Ethiopia | ቁጥር 2 ሁሌ ቡና ሬስቶራንታችንን እየተመረቀ ነው

ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም
እና
እሁድ ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

ሬስቶራንታችንን እዲመርቁልን በአክብሮት ጠርተንዎታል።

ጠሪ አክባሪዎ
መላከ አየነው
ምግባሯ ደስላኝ

አድራሻ
ስታዲየም ወጋገን ባንክ ህንጻ ጎን
+251911-406388

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ታሪክ ፃፉ!..

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16452/

#Ethiopia | በዳይመንድ ሊግ 5000 ሜትር ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሁለተኛ እስከ ሰባተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

በቻይናው ዢያመን ዛሬ በተጀመረው ውድድር በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቺቤት በ14:27.12 የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል አሸንፋለች ።

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ፣የርቀቱ የአለም ክብረ ወሰን ባለቤት 14 :28.18 በመግባት የዓመቱን የግል ምርጥ ስዓቷን በማስመዝገብ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች ።

አትሌት ብርቄ ሀየሎም በ14:28.80 ሶስተኛ ፣አትሌት ሂሩት መሸሻ በ14:29.29 አራተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።(ኢአፌ)

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ስለጣይቱ ማዕከል!…

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16454/

#Ethiopia | ዛሬ የጣይቱ የባህል እና የትምህርት ማዕከልን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

120 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ የቅርስ ቤት የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የንግድና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የአዲስ አበባ 2ኛ ከንቲባ የነበሩት ቢትወደድ ኃይለጊዮርጊስ ኃይለሚካኤል መኖሪያ ቤት እንዲሁም የመጀመሪያ የማዘጋጃ ቤት እና የፍትህ ማዕከል ሆኖ ያገለገለ ታሪካዊ ቤት ነው።

በመሆኑም፤ በተወዳጇ አርቲስት ዓለምፀሃይ ወዳጆ አስተባባሪነት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 39 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም በርካታ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዉበት ውብ ሆኖ ታድሷል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ ከሰራናቸው ስራዎች ጎን ለጎን፣ ከተማችንን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ቅርሶችን አድሰን የከተማችን ተጨማሪ ውበት እና የቱሪስት መስህብ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን የሰራን ሲሆን፣ ለአብነትም በፒያሳ አካባቢ ያሉ የቅርስ ስፍራዎች ይዘታቸውን ሳይለቁ አቧራቸው ተራግፎ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ታድሰው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ አድርገናል።

ይህ የባህልና የትምህርት ማዕከል ለከተማችን ከሚሰጠው የቱሪስት መዳረሻነት በተጨማሪ ለሃገራችን ተተኪ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ለማፍራት የሚያግዝ ሲሆን ማዕከሉ እውን እንዲሆን ትልቁን ድርሻ የተወጣችውን አርቲስት አለምጸሃይ ወዳጆን ላመሰግናት እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የፖፕ ፍራንሲስ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16456/

#Ethiopia | የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ተፈጽሟል።

በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የበርካታ ሀገራት መሪዎች እና የተለያዩ ሀገራት ንጉሶች ተገኝተዋል።

በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች እና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የመጡ ሰዎችም በስነ ስርዓቱ ላይ ታድመዋል።

የፖፕ ፍራንሲስ አስጅሬን ሮም በሚገኘው ሳንታ ማሪያ ማጆሬ ቤተ ክርስቲያን (ባዚሊካ) በክብር አርፏል።

ሊቀ ጳጳሱ ባደረባቸው ከፍተኛ የሳንባ ሕመም የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው በያዝነው ሳምንት ሰኞ በ88 ዓመታቸው በመኖሪያ ቤታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ይታወቃል።

==
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክ ቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ እና ዶናልድ ትራምፕ ከኦቫል ቢሮ ውይይታቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተው ተወያዩ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16458/

#Ethiopia | 👉መሪዎቹ ንግግሮችን ለመቀጠል መስማማታቸው ተገልጿል

#Ethiopia | የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው ዕለት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ በፊት ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ሁለቱ መሪዎች በዋይት ሃውስ ኦቫል ኦፊስ ካደረጉትን በሃይለቃል የተሞላ ውይይት በኋላ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ፊት ለፊት የተገናኙት።

የዋይት ሀውስ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ስቲቨን ቼንግ፤ “ሁለቱ መሪዎች ዛሬ በአካል ተገናኝተው በጣም ውጤታማ ውይይት አድርገዋል” ብለዋል።

አሜሪካ በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ሰላምን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት እንደምታቋርጥ ስትዝት የቆየች ሲሆን፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑን አቻቸውን ቮሎዲሚር ዘለንስኪን “ሩሲያ ክሬሚያን እንድትቆጣጠር ዩክሬን እውቅና አትሰጥም” በማለት የሰላም ድርድሩ ላይ ጉዳት አድርሰዋል ሲሉ ወቅሰዋል።

ነገር ግን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የትራምፕ የዩክሬን ተወካይ የሆኑት ስቲቭ ዊትኮፍ አዲስ ውይይት ካደረጉ በኋላ፤ ትራምፕ ዩክሬን እና ሩሲያ “ለስምምነት በጣም ቅርብ ናቸው” ሲሉ አስታውቀዋል።

ይህንንም ተከትሎ ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ እና ትራምፕ በዛሬው ዕለት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ተገናኝተው መወያየታቸውን የሚያመለክቱ ፎቶግራፎች ተለቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም መሪዎቹ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በጋራ መወያየታቸውን የሚያሳዩ ምስሎች ተለቀዋል።

በዚህም ሁለቱ መሪዎች በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማቆም ስምምነት ላይ ለመድረስ አመርቂ ውይይት ማካሄዳቸውን የዋይት ሀውስ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ስቲቨን ቼንግ ተናግረዋል።

የዜለንስኪ ቃል አቀባይ በበኩላቸው ውይይቱ 15 ደቂቃ ያህል የፈጀ እንደነበር የገለጹ ሲሆን፤ መሪዎቹ ንግግሮችን ለመቀጠል መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ውይይት ተደራዳሪ ቡድኖቹ በማደራጀት ላይ እየሰሩ መሆኑን ቃል አቀባዩ መናገራቸውን ሲኤን ኤን ዘግቧል።

በሌላ በኩል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተካሄደው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተካሄደው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የሽኝት መርሃ ግብር በአሁን ሰዓት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሱ አስክሬን አሁን በቲበር ወንዝ በኩል ሮም በሚገኘው ሳንታ ማሪያ ማጆሬ ቤተ ክርስቲያን (ባዚሊካ) በመጓዝ ላይ ይገኛል።

በዚህ የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይም ከ250 ሺሕ በላይ ሰዎች መገኘታቸውን የቫቲካን ባለስልጣናት ያስታወቁ ሲሆን፤ ሕዝቡ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ አስክሬን ወደቀብር ስፍራው በመሸኘት ላይ ይገኛል፡፡
#ahaduRadio
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ወላይታ ድቻ በኢትዮጵያ ዋንጫ ለፍጻሜ አለፈ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16460/

#Ethiopia | በኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ሸገር ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ወደ ፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል፡፡

ወላይታ ድቻ ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገውን ሸገር ከተማን ባሸነፈበት ጨዋታ ዘላለም አባተ እና ብዙዓየሁ ሰይፈ የማሸነፊያ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡

ወላይታ ድቻ ድሉን ተከትሎ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታቸውን ከሚያደርጉት መቻልና ሲዳማ ቡና አሸናፊ ጋር በፍጻሜው ይፋለማል፡፡

በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚ የነበረው ወላይታ ድቻ በፍጻሜው በኢትዮጵያ ቡና ተሸንፎ ዋንጫውን ማጣቱ ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን የሚሆነው ክለብ በቀጣዩ ዓመት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ ተሳታፊ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ዘሪቱ እንደምን ተጽናናች?

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16462/

#Ethiopia | መጽሐፍ እንደሚል “የሰው ልጅ ህይወቱ ብርቱ ሰልፍ ነው” ግን ደግሞ ከደረሰብን ይልቅ የደረሰልን እግዚአብሔር ትልቅ መሆኑን ለማሰብ አንድ እንዲገባን የሚያስፈልግ ነገር አለ::
ትንሳዔ ባለብዙ ትርጉም በዓል ቢሆንም “ትውልድ የተጽናናበት” የትንሳዔው ባለቤት ዕቅድ ነው::

በሕይወት አጋጣሚ ብዙ ሃዘን ብዙ ህመም ይፈራረቁብናል::መድሃኒቱ መጽናናት ብቻ ነው::

የደራው መጽሔት በተወደደችው ቅዳሜ በዳግም ትንሳዔ ዋዜማ ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ይዞ በደጆ ነው!!

📌ካሜራ ባይኖርም
📌የሰሞኑን ውዝግብ
📌የከተማችን ታላቁ ፍልሚያ
📌ተስፍ አስቆራጭ ሰዎች
📌የደራው ሰሌዳ
📌አዲስ ቅኔ : ሌላ ምስጋና

እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮችን በነፃ ይኮምኩሙ

መጽሔቱን ለማንበብ
👇👇👇
www.yederaw.com/magazine/

መጽሔቱን የግሎ ለማድረግ
👇👇👇
https://t.me/yederaw

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የበልሻ ፋውንዴሽን በካንሰር በሽታ ላይ ለመስራት ተመሠረተ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16464/

#Ethiopia | በሀገረ አሜሪካ ኖረው በበጎ አድራጎት ተግባራቸው በሰፊው የሚታወሱትና በካንሰር ህመም ህይወታቸው ያለፈው የወ/ሮ በለጠች ሞላ (በልሻ) ትሩፋትን ለማስታወስና ለመዘከር፣ በባለቤታቸው፣ በቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው በስምቸው
“የበልሻ ፋውንዴሽን” በሚል ስያሜ በዛሬው እለት ተመሠረተ።

የፋውንዴሽኑን መመስረት አስመልክቶ መስራቹና ዋና ስራ አስፈፃሚ እንዲሁም የወ/ሮ በለጠች ሞላ”በልሻ” ባለቤት የሆኑት አቶ አበበ መብራቴ በፋውንዴሽኑ ምስረታ ላይ እንደገለፁት ፣ ይህን ፋውንዴሽን ለማቋቋም የወሰኑት ባለቤታቸውን በካንሰር በሽታ በሞት በመነጠቃቸው ያደረባቸውን ጥልቅ ሀዘንና ቁጭት በመገንዘብ እንደሆነ ተናግረዋል።

የበልሻ የነበራትን በጎ አድራጎት መንፈስና ተግባር ዘላቂ ለማድረግ እንዲሁም እርሷን የነጠቀውን ካንሰርን ለመዋጋት ይህ ድርጅት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ፣ ፋውንዴሽኑ በካንሰርና በሌሎች አሳዛኝ ምክንያቶች ወላጅ አልባ ለሆኑና ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ ህጻናት ሁሉ የዕለት ተዕለት ድጋፍና እንክብካቤ በመስጠት የህይወት ተስፋቸው እንዲያንሰራራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የበልሻ ፋውንዴሽን የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶክተር ሙላቱ መብራቴ እንደተናገሩት፣ ድርጅቱ በሀገር ውስጥ ህግ መሰረት የተቋቋመ በመሆኑ በካንሰር ላይ ያተኮሩ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራትን በስፋት ለመተግበር የሚያስችለው ስራዎቻቸውን
ለመስራት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የፋውንዴሽኑ የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጆኒ ግርማ በበኩላቸው ፋውንዴሽኑ በርካታና ወሳኝ የሆኑ ዓላማዎችን አንግቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስረድተዋል። ከእነዚህም መካከል የካንሰር በሽታን ከመከላከል ጀምሮ፣ ህሙማን ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎትና አስፈላጊው ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፣ ለካንሰር ህሙማን የረጅም ጊዜ እንክብካቤ መስጠትና ለዘላቂ እረፍት መዘጋጀት እንደሚገኝበት ተናግረዋል።

በተጨማሪም፣ ፋውንዴሽኑ በካንሰርና በሌሎች ምክንያቶች ወላጅ ያጡና ለችግር የተጋለጡ ህጻናትን በመደገፍና በመንከባከብ፣ ህጻናት በኑሮ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ የትምህርት ቁሳቁስና የምግብ ድጋፍ በማድረግ፣ እንዲሁም አቅመ ደካማና አረጋውያንን በመርዳትና በመንከባከብ ሰፊ የሆነ የማህበራዊ ድጋፍ ሥራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አቶ ጆኒግርማ አክለው ገልጸዋል።

የበልሻ ፋውንዴሽን ዓላማውን በተሳካ ሁኔታ ለማሳካትና ተደራሽነቱን ለማስፋት ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ስምምነቶችን ከኢትዮጵያ ህክምና ማኀበር ፣ ተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ካንሰር እና ኢቴክ ሼር ካንፖኒ ከተሰኙ ተቋማት ጋር በቀጣይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት በመርሐግብሩ ላይ ተፈራርመዋል።

“የበልሻ ፋውንዴሽን” ተብሎ የተሰየመው ይህ ድርጅት ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሠረት በቁጥር 7416 ተመዝግቦ ሕጋዊ እውቅና ያገኘ ሲሆን፣ በቀጣይ ትኩረቱን በዋነኝነት በካንሰር መከላከልና በበሽታው ለሚሰቃዩት ሁሉ የሕክምና አገልግሎትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ ያደርጋል።
.
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
#ልጅ_ለመውለድ_የሰራተኛቸውን_ማህጸን_የተከራዩት_ባለትዳሮች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16466/

ፊልሙ አሁን በምሳሌ ሚዲያ ላይ ተለቀቀ!!

ልጅ እንቢ ያላቸው ባለትዳሮች ትዳራቸው ወደ ፍቺ ሊያመራ ከባድ አደጋ ተደቅኖባቸው ሳለ አንድ ሀሳብ ይመጣላቸዋል። የመጣላቸው ሀሳብ የት ድረስ ይወስዳቸው ይሆን? ሙሉ ቪዲዮው Misale Media ላይ አሁን ስለተለቀቀ እንድታዩት ጋብዘናል።

ያለ ጥርጥር ትወዱታላችሁ!!!

👇👇👇
https://youtu.be/9vCzalQHXB8?si=vMGgzo5_X1rG-lmW

አዳዲስ የምንለቃቸው ፊልሞች እንዲደርሷችሁ ቻናሉን #ሰብስክራይብ#ሼርና #ላይክ በማድረግ ቤተሰብ እንድትሆኑ እንጋብዛለን።

👇👇👇
https://youtu.be/9vCzalQHXB8?si=vMGgzo5_X1rG-lmW

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
” እንደ ሀገር የትምህርት ስብራት ያጋጠመን የንድፈ ሀሳብ ትምህርቶች በተግባር ስለማይደገፉ ነው!» መምህር ባንታየሁ አለሙ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16469/

#Ethiopia | መምህር ባንታየሁ አለሙ የጂንካ ሚሊየን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኬሚስትሪ የተግባር መምህር ናቸው።

በአርባምንጭ መምህራን ኮሌጅ በሊነር ኬሚስትሪ ዲፕሎማቸውን የተቀበሉት መምህር ባንታየሁ፥ከአምቦ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በኬሚካል ላቭራቶሪ ሳይንስ በመጀመሪያ ድግሪ ተመርቀዋል ።

በመምህርነት የ11 ዓመታት ልምድ ያላቸው መምህሩ ፥ትምህርት የሁሉም መሰረት በመሆኑ አሁንም ትኩረት ያሻዋል ይላሉ።

” እንደ ሀገር የትምህርት ስብራት ያጋጠመን የንድፈ ሀሳብ ትምህርቶች በተግባር ስለማይደገፉ ነው!» የሚሉት መምህር ባንታየሁ፥የትምህርት ስርአቱን አንድ እርምጃ ወደፊት ለማስቀጠል ከተፈለገ የንድፈ ሀሳብ ትምህርቶች በተግባር መለወጥ አለባቸው ብለዋል።

በመንግሥትም ሆነ በግል ትምህርት ቤቶች የቤተ ሙከራ ቁሳቁሶች በሚገባ የተሟሉላቸው አይደለም ያሉት መምህሩ፥ እነዚህን ግብአቶች ማሟላት ለነገ የሚባል አይደለም ብለዋል።

መምህር ባንታየሁ አለሙ በአሁኑ ሰአት በትምህርት ቤታቸው ተማሪዎች የንድፈ ሀሳብ ትምህርቶችን በተግባር እንዲማሩ ጥረት እያደረጉ ሲሆን ፥በቤተ ሙከራቸውም የገላ ሳሙና፣የልብስ ሳሙና፣ሽቶ፣ፀረ-ተባይ እና ሌሎች የፈጠራ ስራዎችን በመስራት ዕውቅና አግኝተዋል።

እነዚህ የፈጠራ ስራዎች ከማስተማሪያነት አልፎ ለአከባቢው ማህበረሰብ ለሽያጭ በማቅረብ የገቢ ምንጭም መሆን ችለዋል።

መምህር ባንታየሁ በቃጣይ ይህን የጎጆ እንዱስትሪ ወደ ፋብሪካ ደረጃ የማሳደግ ህልም አንግበው እየተጉ ነው።

ዕውቀታቸውንም ከተማሪዎቻቸው አልፈው ለአከባቢው ማህበረሰብ በማሸጋገር ለበርካቶች የስራ ዕድል እየፈጠሩ ይገኛሉ።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ፖሊስ ነገ የሚዘጉ መንገዶችን እቁልኝ ብሏል ⵑⵑ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16471/

#Ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ ነገ ለሚደረገው የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ለተሽከርካሪዎችና ለእግረኞች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ እወቁልኝ ብሏል ፡፡

የውድድሩ መነሻ ቦታ መስቀል አደባባይ ሲሆን ለገሃር መብራት፣ ቡናና ሻይ ሜክሲኮ አደባባይ፣ አፍሪካ ህብረት ሳር ቤት (ፑሽኪን አደባባይ)፣ ቄራ አዲሱ መሿለኪያ ድልድይ፣ ጎተራ ማሳለጫ፣ አጎና ሲኒማ፣ ግሎባል ሆቴል፣ መስከረም ማዞሪያ፣ ጥላሁን አደባባይ፣ ሳንጆሴፍ መብራት አድርጎ መስቀል አደባባይ ያበቃል።

በዚህም መሠረት :-

* ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መስቀለኛ ላይ )

* ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)

* ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ)

* ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት

* ከብሔራዊ ቲያትር ወደ ለገሀር መብራት

* ከሠንጋ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

* ከአረቄ ፋብሪካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

* ከልደታ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

* ከልደታ ፀበል ወደ አፍሪካ ህብረት መብራት

* ከካርል አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ

* ከቫቲካን ወደ ሳርቤት አደባባይ

* ከቄራ አልማዝዬ ሜዳ ወደ ቄራ መብራት

* ከጎፋ ገብርኤል አቅጣጫ ወደ ጎፋ መስቀለኛ በስር

* ከዮሴፍ ወደ ጎተራ ማሳለጫ

* ከመስቀል ፍላዎር ወደ አጎና መስቀለኛ

* ከጋዜቦ አደባባይ ወደ በቅሎ ቤት ድልድይ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ይዘጋሉ።

በተጠቀሱት መስመሮችም ከዛሬ ምሽት 12 ሠዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አዋጆች ከፀደቁ በኋላ ደንብ እስከሚወጣ ረጅም ጊዜ በመውሰዱ ይጣሳሉ ተባለ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16473/

#Ethiopia | አዋጆች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቁ በኋላ ደንብ እስከሚወጣ ድረስ ረዥም ጊዜ እየወሰደ በመሆኑ አዋጆቹ እየተጣሱ እንደሚገኙ ተገለጸ።

በተለይም በቅርቡ የፀደቀው የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ደንብ ሳይወጣለት በመዘግየቱ ምክንያት በአዋጁ የተከለከሉ ተግባራት እየተፈጸሙ መሆኑን ምክር ቤቱ የከተማና መሰረተ ልማት የ9 ወራት ሪፖርት ባደመጠበት ወቅት አንስቷል።

ምክር ቤቱ እንደ ምሳሌ የጠቀሰው ይኸው አዋጅ 80 በመቶ የሪል እስቴት ግንባታ ሳይጠናቀቅ መሸጥን የሚከለክል ቢሆንም፣ ደንብ ባለመውጣቱ በአሁኑ ወቅት ግንባታ ያልተጀመረባቸው መሬቶች ሳይቀሩ እየተሸጡ እንዲሁም የተለያዩ ድርድሮች እየተካሄዱ መሆኑን አመልክቷል።

አዋጆች በቶሎ ደንብ ሳይወጣላቸው በመዘግየታቸው ክፍተቶች በመፈጠር አዋጁን የሚጥሱ አካላት እየተበራከቱ መምጣታቸው ስጋት እንደፈጠረም ካፒታል ሰምቷል።

በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት ደንቦችን በማፋጠን የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ጥሪ ቀርቧል።

ይሁን እንጂ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር በበኩላቸው የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅ ተዘጋጅቶ እንዲጸድቅ መደረጉንና አዋጁን ተከትሎ የማስፈጸሚያ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ረቂቅ ደንቡን የማዳበር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ በሪፖርታቸው አስታውቀዋል።

አዋጁ በመጽደቁ በሪል እስቴት አልሚዎች እና በቤት ገዥዎች መካከል ለዘመናት ሳይፈቱ የቆዩ ችግሮችን እየተፈቱ መምጣታቸው እና በቀጣይም አዋጁ ሲተገበር ችግሮችን መሰረታዊ በሆነ መልኩ አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል።

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ የጥርስ ህክምና ማስታወቂያዎች አብዛኛዎቹ ግነት ይታይባቸዋል ተባለ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16475/

#Ethiopia | በዛሬዉ ዕለት የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የጥርስ ህክምና ማህበር ጋር በመሆን የጥርስ ህክምና አገልግሎት መስጫ ጤና ተቋማት ባለቤቶችና በጤና ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በጤና ተቋማት የሚሰሩ ማስታወቂያዎች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ግምገማ አካሄዷል።

በዉይይቱም በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፋ የጥርስ ህክምና ማስታወቂያዎችን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ማስታወቂያዎች ግነት የበዛባቸው መሆኑንና አንዳንዶቹም ከባህላችን የወጡ መልዕክቶችን ያዘሉ መሆናቸዉን በጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ዮርዳኖስ አለባቸዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ሜሮን ያዕቆብ በበኩላቸው ከጥርስ ህክምና ጋር የተያያዙ ወጣ ያሉ የማስታወቂያ ስራዎችን በተመለከተ የሚስተዋሉ ግነቶች መዘዝ ሳያመጡና ወደ ሌሎችም ሙያዎች ሳያዛመቱ እንዴት ወደ መስመር ማስገባትና መቆጣጠር ይቻላል የሚለዉ ላይ ለመወያየት የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል ።

በተለያዩ ማሕበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ግነት የበዛባቸዉ ከመሆናቸዉ ባሻገር ከማህበረሰባችን ባህልና ወግ የወጡ አንዳንዶቹም ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚይዙ በመሆናቸዉ ትኩረት በመስጠት የማስታወቂያ ኢንዱስትሪው ላይ እንዴት እንስራ የሚለዉ ላይ ሰፊ ዉይይት ተካሄዷል።
#ዳጉ_ጆርናል
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
░▒▓█► ዳ ግ ም ት ን ሣ ኤ ◄█▓▒░

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16477/

░▒▓█► ዳ ግ ም ት ን ሣ ኤ ◄█▓▒░
𝗔𝗻𝘁𝗶𝗽𝗮𝘀𝗰𝗵𝗮, 𝙏𝙝𝙤𝙢𝙖𝙨 𝙎𝙪𝙣𝙙𝙖𝙮, 𝙏𝙝𝙚 𝙉𝙚𝙬 𝙎𝙪𝙣𝙙𝙖𝙮
▬▬▬▬▬▬▬▬

ከትንሣኤ በኋላ እስከ ጰራቅሊጦስ ያሉት ኅምሳ ቀናት በዓለ ኅምሳ (በጽርዕ ቋንቋ ፔንዲኮንዳ) ይባላሉ፡፡ የሰሙነ ትንሣኤ መጨረሻው (ስምንተኛው ቀን) ዳግም ትንሣኤ ነው፡፡ የዳግም ትንሣኤ ሰንበተ ክርስቲያን እሑድ በተጨማሪም ፈጸምነ፣ አግብዖተ ግብር ፣ የቶማስ ምስክርነት ሰንበት ( Thomas Sunday) ወዘተ እተባለች ትጠራለች።

የትንሣኤን በዓል በሳምንቱ በድጋሜ ለምን እናከብራለን? ቢባል
ሰሙነ ሕማማትና ሰሙነ ትንሣኤን እንድናከብር አስቀድሞ በዲዲስቅልያ ኋላም በፍትሐ ነገሥት ታዝዟልና ነው፡፡
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፱ “እስመ ሰሙነ ዐቢይ ሰሙነ ሕማማት እንተ ትተልዋሄ ሰሙነ ትንሣኤ ወዘይትፈቀድ ከመ ናእምር እስመ ዘሐመ ናሁ ትንሣኤ” ሲል ይገኛል፡፡
የሰሙነ ትንሣኤ መጨረሻው ስምንተኛው ቀን ዳግም ትንሣኤ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣው አንድ ጊዜ ነው፡፡
ዳግም ትንሣኤ ለምን ተባለ ? ቢባል፥ ዳግም ትንሣኤ የተባለበት ምክንያት፡- በአከባበር፥ በሥርዓት የመጀመሪያውን ትንሣኤ ስለሚመስል ነው፡፡ የትንሣኤ ዕለት የሚባለው የሚነገረው ቃለ እግዚአብሔር ሳይለወጥ በሙሉ በዚህ ቀንም ይደገማል፡፡ በዕለተ ትንሣኤው የነበረው ሥርዓተ ማኅሌትና ቅዳሴ፣ የነበሩት መዝሙራትና ምስባኮች በድጋሜ ስለሚዘመሩ [ ድኅረ ቁርባን (ከ‹‹ነአኩቶ›› እስከ “እትዉ በሰላም”) ካሉ አንዳንድ የጸሎት ክፍሎች በስተቀር ] አከባበሩ እንደ ቀደመው ( ከ8 ቀናት በፊት እንደነበረው) ትንሣኤ ስለሆነ ዳግም (ሁለተኛ) ትንሣኤ አልነው እንጂ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግማዊ (ሁለተኛ ትንሣኤ) አለው ለማለት አይደለም።

ዳግም ትንሣኤ ከዚህም ሌላ ሁለት ተጨማሪ መጠሪያ ስሞች አሉት፡፡
እነዚህም “ፈጸምነ ወአግብዖተ ግብር” ይባላሉ፡፡
“ፈጸምነ” የተባለበትም፤ ሰሙነ ትንሣኤ በዓል አክብረን ፈጸምን ማለት ነው፡፡
“አግብዖተ ግብር” የተባለበትም፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “አንሰ ሰባሕኩከ በዲበ ምድር ፈጺምየ ግብረ ዘወሀብከኒ ከመ እግበር” ዮሐ 17:3 “አባ ወአቡየ ግብር ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ… እኔ ልሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርሁህ” ያለውን ከቅዳሴ በኋላ ሊቃውንት በዚህ ቀን ስለሚዘምሩት ነው፡፡ ዮሐንስ ፯፥፬

በተጨማሪም የሐዋርያው ቶማስ ምስክርነት የሚታሰብበት ነው፡፡

ወመስዮ ውእቱ ዕለት ዘውእቱ እሑድ ሰንበት እንዘ ዕፅው ኆኅት ኀበ ሀለዉ አርዳኢሁ ጉቡአን በእንተ ፍርሃቶሙ ለአይሁድ መጽአ እግዚእ ኢየሱስ ወቆመ ማእከሎሙ ወይቤሎሙ ሰላም ለክሙ።

ዳግመኛ ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በዝግ ቤት ሳሉ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ሳለ ደጁም ተዘግቶ ሳለ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ በመካከላቸው ቁሞ እንዴት ሰነበታችሁ አስታረቅኋችሁ” አላቸው፡፡

ወእምድኅረ ሰሙን መዋዕል እንዘ ሀለዉ ካዕበ አርዳኢሁ ውስጠ ወቶማስኒ ሀሎ ምስሌሆሙ እንዘ ዕፅው ኆኅት መጽአ እግዚእ ኢየሱስ ወቆመ ማእከሎሙ ወይቤሎሙ ሰላም ለክሙ።

ሁለት ሰዓት አሳልፎ ስለመጣ “እምድኅረ ሰሙነ” አለ እንጅ፥ በስምንተኛው ቀን ሲል ነው፡፡ በመጀመሪያው መገለጡ ያልተገኘው ሐዋርያው ቶማስ ትንሣኤውን አላመነም ነበርና፤ “ጣትህን ወደዚህ አምጣ እጆቼንም እይ፤ እመን እንጅ ተጠራጣሪ አትሁን” አለው፡፡ ዲዲሞስ የተባለው ቶማስም መለሰ “ጌታዬ አምላኬ ሆይ” አለ፡፡ መዳሰሱን ሲያይ “ጌታዬ”፤ መቃጠሉን ሲያይ “አምላኬ ሆይ “አለ፡፡ ገቦ መለኮቱን የዳሰሰች እጁ ሕያዊት ሁና፤ (በሕይወት ትኖራለች) በሕንድ አገር ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ያስቀምጧታል፡፡ በዓመት በዓመት በእምቤታችን በዓል በአስተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ፥ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች፤ ዓመት አገልግሎ ያርፋል፤ እንዲሁ በዓመቱ የሚሾመውን ተራምዳ ትይዘዋለች፤ እንዲህ እያለች ትኖራለች፡፡ ይህም የሚያስተምረን የጌታን ተአምራት፤ የሐዋርውን ሥልጣንና ብቃት ነው፡፡ ጌታም ቶማስ ሆይ! ብታየኝ አመንክን? ሳያዩኝ የሚያምንብኝ ብፁዓን ናቸው አለው፡፡ ዮሐ ፳፩፥፳፬–፳፱

ከሌሎቹ ኃዋርያት በተለየ ቶማስ ለምን ተጠራጠረ እንዴትስ አላምንም አለ? አንድም ቶማስ ትንሣኤ ሙታን የለም ከሚሉት ከሰዱቃውያን ዘር ነውና ለመቀበል ከበደው። አንድም ሌሎቹ ኃዋርያት እነርሱ ሞተ ተቀበረ ተነሣ እንደ ተነሣ አይተነዋል ለኛም ተገልጾልናል ብለው ሲሰብኩ እኔ ሳላይ አየሁ ብዬ ልሰብክ እንዴት ይቻለኛል? በሚል ጥርጣሬ ( ምንፍ*ቅና) ነው።
ቶማስ ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል።
(ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡

ከትንሣኤ በኋላ እስከ ጰራቅሊጦስ ያሉት ኅምሳ ቀናት በዓለ ኅምሳ (በጽርዕ ቋንቋ ፔንዲኮንዳ) ይባላሉ፡፡ በነዚህ ኅምሳ ቀናት ረቡዕና ዓርብ ጨምሮ በጾም አይዋሉም፡፡ የጾሙ ( የሱባኤው) ወቅት የዚህ ዓለም፤ ከትንሣኤ እስከ በዓለ ሃምሣ የሚመጣው ዓለም (የመንግሥተ ሰማያት) ምሳሌ ናቸው፡፡ (ማቴ ፲፪፥፴፪) በጾም ወራት ስግደት፣ ጸሎት.. ድካም እንዳለ ሁሉ፤ በዚህ ዓለም ብዙ ፈተና አለና በሚመጣው ዓለም ግን እንደዚህ ዓለም ይህ ሁሉ የለበትም፡፡ ከትንሣኤ በኋላ ፶ ቀን ሙሉ ረቡዕና ዓርብ ሳይቀሩ ጥሉላት ሁሉ እንደሚበሉና ደስታ እንደሚደረግ በመንግሥተ ሰማያትም ምእመናን በተድላ ነፍስ የሚኖሩበት፤ የአዝማነ መንግሥተ ሰማያት መታሰቢያ ነው፡፡ (ማቴ ፳፪፥፴)

ሥርዓተ ማኅሌት ዘዳግም ትንሣኤ

ይኽም እንደ ትንሣኤ ዋዜማ ሁሉ ደወል እንደተደወለ ነቢያት ተደግሞ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል። “ተፈሥሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ” ይባላል።
ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል። ወተንሥአ ይሰበክና አራቱም ወንጌላት ተነበው “አርያም” በተባለው ምስጋና ማኅሌቱ ይጀመራል።

ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፸፯ : ፷፭

ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፤
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፤
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።

አርያም

ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤
ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ ትፍሥሕት
እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ፤
ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ።

ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ይገብሩ በዓለ ሰማያት፤
ይገብሩ በዓለ ደመናት፤
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።

አንገርጋሪ

ዮም ፍሥሃ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፤
እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤
ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ፤
አማን ተንሥአ እምነ ሙታን።

አመላለስ

‘አማን በአማን’/፪/ ተንሥአ ‘አማን በአማን’/፪//፩/
ተንሥአ እምነ ሙታን/፬/

ወረብ

ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን/፪/
ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል/፪/

እስመ ለዓለም

ትንሣኤከ ለእለ አመነ፤
ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ።

አመላለስ

ትንሣኤከ ለእለ አመነ/፪/
ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ/፪/

ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ…
በ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች አትሌት ሳሙኤል ፍሬው አሸንፈዋል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16479/

#Ethiopia | በቻይና ዢያሚንግ የ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሳሙኤል ፍሬው አሸንፈዋል ።

አትሌት ሳሙኤል በ8:05.61 በመግባት የቦታው ክብረወሰንና የዓመቱ የርቀቱ ፈጣን ስዓት በማስመዝገብ በድንቅ ብቃት በበላይነት ማሸነፍ ችሏል።

ሞሮኳዊው የኦሎምፒክ ሻምፒዮን አትሌት ኤልባካሊን ሁለተኛ እንዲሁም ኬንያዊ ሲሞን ኮኤች ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል ።
(ኢአፌ)

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በ ኤሌጋንስ ኮንሰርት እየተዝናኑ ዕድለኛ ይሁኑ!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16481/

በዕለቱ 50ሺ ብር ለማሸነፍ፤
Ethiolottery.et ላይ አሁኑኑ ይመዝገቡ፤
የ50 ሚሊየን ብር ሎተሪ ይቁረጡ!

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet