Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
6.15K subscribers
2 photos
4.68K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
“ ከመቼውም በተሻለ ቁመና ላይ ነኝ “ ትግስት አሰፋ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16424/

#Ethiopia | በአለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ የተቀመጠው ተጠባቂው የለንደን ማራቶን ውድድር ነገ እሁድ ይካሄዳል።

በሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ የምትጠበቅ ሲሆን ከኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሰን ጋር ጠንካራ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ከአለም ምርጥ ሶስት የማራቶን ሰዓቶቹ የሁለቱ ባለቤት የሆኑት አትሌቶቹ ለማሸነፍ እንደሚፎካከሩ ከውድድሩ በፊት ለአዘጋጆቹ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

“ ለውድድሩ ጥሩ ዝግጅት አድርጌያለሁ “ ያለችው ትግስት አሰፋ በርሊን ላይ የአለም የማራቶን ሪከርድ ስሰብር ከነበረኝ የተሻለ ቁመና ላይ እገኛለሁ ብላለች።

“ውድድር የምጀምረው አሸንፋለሁ ብዬ ነው የሚፈጠረው አይታወቅም ነገርግን ለማሸነፍ ነው ተዘጋጅቼ የመጣሁት ” ስትል ትግስ አሰፋ ተናግራለች።

” ለንደን ማራቶን ትልቅ ውድድር ነው እዚህ መሮጥ እንድወድ ያደረገኝ ብዙ ምክንያቶች አሉኝ እዚህ ማሸነፍ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው።” ትግስት አሰፋ

አትሌት ሲፋን ሀሰን በበኩሏ “ በለንደን ማራቶን ስትሮጥ የኦሎምፒክ ፉክክር ይመስላል ለውድድሩ ጓጉቻለሁ ምክንያቱም እርስበርስ እንተዋወቃለን “ ስትል ተደምጣለች።

በወንዶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ ፣ የባለፈው አመት የቦታው አሸናፊ አሌክሳንደር ሙቲሶ ፣ አሊዩድ ኪፕቾግ እና ሰባስትያን ሳዌ ቅድም ግምት ያገኙ አትሌቶች ናቸው፡፡
#tikvah
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ስርዓተ ቀብር

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16426/

#Ethiopia | የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በሁሉም የኢቢሲ ዶትስትሪም ዲጂታል ሚዲያ አማራጮች በቀጥታ ይከታተሉ፦

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ለመጨረሻው ዕረፍታቸው የመረጡት ልዩ ስፍራ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16428/

#Ethiopia | የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ እ.አ.አ በ2022 ባደረጉት ኑዛዜ ድካሙ በዝቶባቸው ካረፉ እንደ ቀደምት ጳጳሳት ሁሉ ቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አልቀበርም ብለው ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ በዚሁ ወቅት በሮም ኢስኪሊኖ ሰፈር ውስጥ በቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ማጊዮር ባዚሊካ ውስጥ መቃብራቸውን አስቀድመው እንዳዘጋጁም ተናግረው ነበር።

በፈረንጆቹ 1269 ዓ.ም ከነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆኖሪየስ 3ኛ ጀምሮ እስከ 1669 ዓ.ም ከነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ኬልመንት 9ኛ ድረስ ሰባት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቀብራቸው የተፈፀመው በቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ነው።

ቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ግንባታው ከተጠናቀቀበት እ.አ.አ 1626 ዓ.ም ወዲህ ከ31 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ 24ቱ በቤተ ክርስቲያኑ ዋሻ ውስጥ ነው የተቀበሩት።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ልምዱን ለመቀየር ለምን ፈለጉ?

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ከቫቲካን ውጭ ቀብራቸውን ለማድረግ የፈለጉት ለኢየሱስ እናት ለቅድስት ማርያም ባላቸው የተለየ ፍቅር መሆኑንም በወቅቱ ገልጸዋል።

እንደ ቢቢሲ መረጃ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ከዚህች በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከተገነባች የቅድስ ማርያም ቤተክርስቲያን ጋር የተለየ ቁርኝት ያላቸው ሲሆን፣ ከመቶ ጊዜ በላይም ጎብኝተዋታል።

ባለፈው ዓመት በወጣ አዲስ የአምልኮ ሥርዓት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በአንድ ዚንክ በተሸፈነ የእንጨት ሳጥን ውስጥ እንደሚያርፋ ተናግረው ነበር።

ከእርሳቸው በፊት የነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ቤኔዲክት 16ኛ በሬሳ ሳጥን ውስጥ ነው የተቀበሩት።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የሳንባ ምች ሕመማቸው ብሶባቸው ወደ ሆስፒታል ያመሩት የካቲት አጋማሽ ሲሆን፣ በማገገሚያ ውስጥ በርካታ ጊዜያት ቆይተው ወደ መኖሪያቸው ከተመለሱ በኋላ ሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ይታወሳል።

ሥርዓተ ቀብራቸውም በዛሬው ዕለት በዚሁ በመረጡት ስፍራ የሚፈፀም ሲሆን አሁን ላይ የአስከሬን ሽኝት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የሀገራት መሪዎች በሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ስርአተ ቀብር ላይ ለመታደም ሮም ገብተዋል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16430/

#Ethiopia | የዓለም ሀገራት መሪዎች በሮማውጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ስርአተ ቀብር ላይ ለመታደም ሮም ገብተዋል።

ባለፈው ሰኞ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ፖፕ ፍራንሲስ ስርአተቀብር በዛሬው ዕለት ይፈጸማል።

ስርአተ ቀብሩ ከምሳ ሠአት ጀምሮ በሚካሄድ ፕሮግራም የሚካሄድ ሲሆን፥ የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎችም በስነስርአቱ ላይ ለመገኘት ሮም ገብተዋል።

እንደ ቫቲካን መረጃ ከሆነ ሊቀ ጳጳሱ ካረፉበት እለት ጀምሮ ከ250 ሺህ በላይ ምዕመን በስፍራው በመገኘት ተሰናብተዋል።
#aradafm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታውች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16432/

#Ethiopia | በስፔን ኮፓ ዴላሬይ የፍጻሜ ጨዋታ

ምሽት 04:00 ባርሴሎና ከ ሪያል ማድሪድ

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የዛሬ ተጠባባቂ ጨዋታዎች

8:30 ኤቨርተን ከ ቼልሲ
11:00 ብራይተን ከ ዌስትሃም
11:00 ኒውካስትል ከ ኢፕስዊች
11:00 ሳውዝሃፕተን ከ ፉልሃም
01:30 ወልቭስ ከ ሌስተር ሲቲ

በጀርመን ቡንደስሊጋ የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች

10:30 ባየር ሌቨርኩሰን ከ ኦግስበርግ
10:30 ባየር ሙኒክ ከ ሜንዝ
10:30 ሆፈናየም ከ ዶርትሙንድ
10:30 ሆልስታይን ኪል ከ ዶርትሙንድ
10:30 ውለቭስበርግ ከ ፍራይበርግ
ምሽት 1:30 ፍራንክፈርት ከ RB ሌፕዝሽ

#ዳጉ_ስፖርት
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የተራራ ላይ ሩጫ በኢትዮጵያ (Hiking)

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16434/

ክብር፣ፍቅርና ህብር በሚል መሪ ቃል የተራራ ላይ ሩጫ ተዘጋጅቷል።

#Ethiopia | በኢትዮጵያ ታላቅ የተራራ ጉዞ ውድድር በእንጦጦ ፓርክ ይደረጋል።

በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ በሚዘጋጀው የተራራ ላይ ውድድር በሴትም በወንድም ለአሸናፊዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ሽልማት ተዘጋጅቷል ተብሏል።

ይህንን ውድድር ያዘጋጀው 90 ቀናት ሁለተናዊ ለውጥ ስፖርት በማሰልጠን የሚታወቀው ማስተር ሔኖክ ነው።

ማስተር ሔኖክ እንደተናገረው በኢትዮጵያ ያሉ ተራራዎች ለቱሪዝምና ለስፖርቱ ዘርፍ መጠቀም እንዲያስችል ተደረጎ የተዘጋጀ ነው ብሏል።

የስፖርት ባህላችን እያጠናከርን እርስ በእስሳችን ግኑኝነታችን የሚጠናከርበት መንገድ ለመፍጠር ነው ተብሏል።

በዝግጅቱ ሁሉም አገልግሎት እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን መኪና ማቆምያ ቦታ ከሙሉ ጥበቃ ጋር መዘጋጀቱን ነው ማስተር ሔኖክ የተናገረው።

በውድድሩ ከ10ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉበት የተነገረ ሲሆን በውድድሩ ለሚሳተፉ ሰዎች ቲሸርቱን በ500 ብር ቀርቦላቸዋል ተብሏል።

ውድድሩ 5ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ለአሸናፊዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ሽልማት ተዘጋጅቷል።

በውድድሩ እድሜያቸው ከ10 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት በነጻ ይሳተፋሉ ተብሏል።

ውድድሩ የሚደረገው ብዙዎች እንዲሳተፉ በማሰብ ሚያዝያ የሜዴይ ቀን በሚከበርበት ቀን ሲሆን ሚያዝያ 23/2017 አመተ ምህረት መሆኑ ነው የተገለጸው።

በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች ከ30ሺህ ብር እስከ10 ሺህ ብር እንደቅደም ተከተላቸው ሽልማት መዘጋጀቱን ነው ማስተር ሔኖክ የተናገረው።
==
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክ ቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ኮምቦልቻ : የኢንዱስትሪ እና ፋይናንስ ኤክስፖ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16436/

#Ethiopia | ከሚዚያ 20 እስከ ሚያዚያ 30 2017 ዓ.ም ለሚካሄደው የኢንዱስትሪ እና ፋይናንስ ኤክስፖ ዝግጅት መጠናቀቁን ከተማ አሥተዳደሩ አስታውቋል።

የቀጣናውን እምቅ የመልማት አቅም ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክተውን የኢንዱስትሪ እና የፋይናንስ ኤክስፖ ለማካሄድ ጥቂት ቀናት ቀርተዋል።

ኤክስፖው “ሰላም የኢንቨስትመንት ፓስፖርት ነው” በሚል መልእክት እንደሚካሄድ ነው የተገለጸው።

በኮምቦልቻው ኤክስፖ ላይ:-

📌ከ300 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኢንቨስተሮች፣

📌 50 የሚኾኑ የፋይናንስ ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት፣

📌 ከ30 በላይ የመንግሥት ተቋማት

📌ከ20 ያላነሱ ሥራ ፈጣሪዎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ዘመን ጠቀስ ዘመነኛ ዕድል!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16438/

http://xn--ethiolotterey-ok6c.et/ ይመዝገቡ፤

የ50 ሚሊየን ብር ሎተሪ ይቁረጡ!

ሲመዘገቡ በሚሊኒየም፣ በማሪዮት እና ግዮን ኮንሰርቶች ዘና ፈታ እያሉ በእያንዳንዱ ኮንሰርቶች 50 ሺህ ብር ያሸንፉ!

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አስደሳች ዜና ከስልጤ ዞን ከወራቤ!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16440/

#Ethiopia | “ሽልማት ጣመኝ ፔፕሲ ድገመኝ” በሚል መሪ ቃል ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንደስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማ ለደንበኞቹ ካዘጋጃቸው ሽልማቶች ውስጥ አንዱ ID4 የኤሌክትሪክ መኪና በሥልጤ ዞን – ወራቤ ከተማ ለዕድለኛ ወጥቷል።

ዕድለኛው አሸናፊ ፋሪስ ሱለይማን የሚያሸልመውን እጣ ያገኘው ሚሪንዳ ጠጥቶ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

አሸናፊው ፋሪስ ሽልማቱን በወራቤ ከተማ ሚያዝያ 18 ቀን 2017ዓ.ም. በተከናወነ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም የተረከበ ሲሆን ከዚህ በፊት በተለያዩ ከተሞች ነዋሪ የሆኑ ሌሎች ዕድለኞች ሚሪንዳ፥ ፔፕሲ እና ሰቨን አፕ ጠጥተው የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማቶች ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ከብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16442/

#Ethiopia | የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሚያዝያ 17 እስከ 18/ 2017 ዓም መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡ በዚህ ስብሰባም የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ ኢትዮጵያ በ2018 ከተስፋ ወደሚጨበጥ ብርሃን ለመሻገር፤ በ2023 የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለመሆን፤ በ2040 ደግሞ ዓለም አቀፍ የብልጽግና አርአያ ለመሆን ያስቀመጠችው ርእይ እንደሚሳካ የሚያረጋግጡ የስኬት ፍንጮች መታየታቸውን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡ እነዚህ የስኬት ፍንጮች የያዝነው ፍኖተ ብልጽግና ትክክል መሆኑን አመላክተውናል፡፡

ከብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በኋላ አያሌ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡ ከተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በየደረጃው የሚደረገው ምክክርና ትብብር በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ወደ አዲስ ምእራፍ ገብቷል፡፡ ከአንድ ክልል በስተቀር፣ ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ምእራፍ በሁሉም ክልሎች ተጠናቅቋል፡፡ በሀገሪቱ የጸጥታ ችግር በነበረባቸው አንዳንድ አካባቢዎችም ሰላም እየሰፈነ ነው፡፡ መንግስት በተደጋጋሚ ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ እጅ የሚሰጡና ወደ ሰላም ድርድር የሚመጡ ታጣቂዎች ከዕለት ወደ ዕለት ቁጥራቸው እየጨመረ ይገኛል፡፡ የመንግሥት ሕግ የማስከበርና የማድረግ ዐቅም እየጎለበተ መጥቷል፡፡ ከሶማሊያ ጋር ተፈጥሮ የነበረው ውዝግብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ተፈትቷል፡፡ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዲኖራት የተያዘው አቋም ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነቱ እየጨመረ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ያላት ግንኙነት ከመሻሻሉም በላይ የሚደረግላት ድጋፍ እያደገ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት ጨምሯል፡፡ የዲፕሎማሲ ግንኙነቷም በሁሉም አቅጣጫ ከፍ ብሏል፡፡

እስከአሁን ያለው አፈፃፀም የሚያሳየው በያዝነው አመት አጠቃላይ ኢኮኖሚው በታቀደው መሠረት በ8.4 በመቶ የሚያድግ መሆኑን የሥራ አስፈጻሚው ገምግሟል፡፡ በዘርፍ ደረጃ ደግሞ ግብርና በ6.1 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ በ12.8 በመቶ፣ ማኑፋክቸሪንግ በ12.0 በመቶ፣ ኮንስትራክሽን በ12.3 በመቶ፣ አገልግሎት ደግሞ በ7.1 በመቶ የሚያድጉ መሆናቸው ተገምግሟል፡፡ ያለፉት 9 ወራት ጠቅላላ የመንግሥት ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ134 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡ የውጭ ብድር ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ወደ 13.7 በመቶ ወርዷል፡፡ ወደ ውጭ ገበያ የሚቀርቡት ስድስት ዋና ዋና ምርቶች፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸሩ ከ82 በመቶ እስከ 386 በመቶ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡ በስንዴ፣ በሩዝ፣ በቡና፣ በሻሂ ቅጠል እና በፍራፍሬ ምርቶች በአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ለመውጣት እየተደረገ ያለው ትግል ፍሬ እያፈራ መሆኑን አይተናል፡፡

ውድ የብልፅግና አመራሮች፣ የብልፅግና አባላትና መላው ሕዝባችን፣
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ዝቅተኛ ኑሮ በሚኖሩ ወገኖች ላይ ጫና እንዳያሳድር አስፈላጊ የሆኑና የታቀዱ የድጋፍ መርሐ ግብሮች መከናወናቸውንም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መርምሯል፡፡ ለማዳበሪያ 62 ቢልዮን ብር፣ ለሴፍቲኔት 41.2 ቢልዮን ብር፣ ለነዳጅ 60 ቢልዮን ብር፣ ለመድኃኒት 3.5 ቢልዮን ብር፣ ለምግብ ዘይት 6.1 ቢልዮን ብር፣ እንዲሁም ለደመወዝ 38.4 ቢልዮን ብር ድጎማ ተደርጓል፡፡ ባለፉት 9 ወራት ብቻ 344790 የውጭ ሀገር ሕጋዊ የሥራ ዕድሎች እና ከ3 ሚልዮን በላይ የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድሎች ተፈጥረዋል፡፡ የርቀት የሥራ ዕድሎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱ ታይቷል፡፡

የመንግሥት የልማት ተቋማትን በአዲስ አስተሳሰብና በአዲስ መንገድ መልሶ ለማደራጀትና ለመምራት መቻሉ፣ እያስገኘው ያለው ውጤት ለሌሎች አርአያ የሚሆን እንደሆነ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አሁን ያለው ጠቅላላ ገቢ 1.5 ትሪልዮን መድረሱ ታይቷል፡፡ ከባለፈው ዓመት የ9 ወራት አፈጻጸም አንጻር የዘንድሮ ገቢው የ86 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱም ተረጋግጧል፡፡ ይሄም መንግሥት የሀገርን ሀብት ለማወቅ፣ ዐውቆም በሚገባ ለማስተዳደር፣ አስተዳድሮም ወረት ለማከማቸት የተከተለው መርሕ ትክክል መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የውጭ ምንዛሬ ክምችት ዕድገት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ 9 ወራት ጋር ሲነጻጸር የ203.99 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ የባንኮች ተቀማጭ ገንዘብ ከ3 ትሪልየን በላይ ተሻግሯል፡፡ የ9 ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከ5 ቢልዮን ዶላር በላይ ሲሆን፣ ይሄም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ150.39 በመቶ ዕድገት አምጥቷል፡፡ ባለፉት ስምንት ወራት 473.9 ቢልዮን ብር ብድር ከንግድ ባንኮች ተለቅቋል፡፡ ይሄም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አንጻር በ61.9 በመቶ ከፍ ይላል፡፡ ከዚህ ብድር ውስጥም 76.6 በመቶ ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ ነው፡፡ ለግሉ ዘርፍ የበለጠ ብድር መሰጠቱ፣ የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ተገቢውን ሚና እንዲጫወት ያስቀመጥነው ፖሊሲ በተግባር እየተገለጠ መሆኑን አመላካች ነው፡፡

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት የጀመርናቸው ሁሉን አቀፍ ጥረቶች ፍሬያቸው እየጎመራ ነው፡፡ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 50.2 ሚልዮን፣ የሞባይል ተጠቃሚዎችም 86.6 ሚልዮን ደርሰዋል፡፡ የቴሌ ብር ደንበኞችም ከ52.56 ሚሊዮን በላይ ናቸው፡፡ ዲጂታል ፋይናንስ፣ የኅብረተሰቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢኮኖሚው መሣለጥ ጉልህ ድርሻ እያበረከተ ነው፡፡ ባለፉት 9 ወራት በዲጂታል መንገዶች 7.73 ቢልዮን ብር ተቆጥቧል፡፡ 26.77 ቢልዮን ብር በዲጂታል በኩል ብድር ተሰጠ ሲሆን፣ የ12.51 ትሪሊዮን ብር ግብይት ደግሞ በዚሁ መንገድ ተከናውኗል፡፡

ዋና ዋና ፕሮጀክቶችን በጊዜና በተገቢ ደረጃ ለማጠናቀቅ የተሰጠው አቅጣጫ ብዙዎችን ለፍጻሜ እያበቃቸው ነው፡፡ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 98.66 በመቶ ደርሷል፡፡ የኮይሻ፣ አይሻና አሰላ የኃይል ማመንጫዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሠረት እየተጓዙ መሆናቸው ተገምግሟል፡፡ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታም የኢትዮጵያን ነገ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የቅድመ ዝግጅት ምእራፉ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የኮሪደር ልማት በአዲስ አበባ በ8 ኮሪደሮች እና በመላው ኢትዮጵያ በ65 ከተሞች እየተከናወነ መሆኑ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡ ብዙዎቹ የመስኖ ግድቦች ወደ ፍጻሜያቸው እየደረሱ ናቸው፡፡ ከዘጠኙ የመስኖ ግድቦች ውስጥ ስድስቱ አፈጻጸማቸው ከ75 በመቶ በላይ ደርሷል፡፡
“ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪ ቃል ከ82 ቢልዮን ብር በላይ ድጋፍ የተሰበሰበ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 6815 ትምህርት ቤቶች በመላ ሀገሪቱ ተገንብተዋል፡፡ የነባር ትምህርት ቤቶችን ዐቅም ለማሻሻል እና በግጭት የተጎዱትን ለመጠገን የተደረገው ጥረት በትውልድ ላይ ለሚሠራው ሥራ መሠረት የሚጥል መሆኑ ታይቷል፡፡ የወላድ እናቶችን እና የጨቅላ ሕጻናትን ሞት በመቀነስ ረገድ የተሻለ ውጤት መመዝገቡም ታይቷል፡፡

በኢትዮጵያ የቱሪዝም መዳረሻዎችና የስፖርት ሥፍራዎች በቁጥርም፣ በዓይነትም እያደጉ መጥተዋል፡፡ በተለያዩ ከተሞች በመገንባት ላይ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ስታዲየሞች በመጠናቀቂያ ምእራፍ ላይ ናቸው፡፡ ይሄም ኢትዮጵያ ታላላቅ አፍሪካዊ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ ለያዘችው ዕቅድ መሳካት ወሳኝ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ…
የባህር ማዶ ወሬዎች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16444/

#ርዕሰ_ሊቃነ_ጳጳሳት_አባ_ፍራንችስኮስ

#Ethiopia | በሳምንቱ መጀመሪያ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንስስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይፈፀማል፡፡

አባ ፍራንሲስ በአንጎል ውስጥ የደም መፍሰስ እና በልብ ድካም በ88 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ባለፈው ሰኞ ነው፡፡

እጅግ በርካታ ካቶሊካውያን በቫቲካን በአባ ፍራንሲስ ሕልፍት ሐዘናቸው ሲገልጹ ሰንብተዋል፡፡

የአባ ፍራንሲስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ በሮም ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ይፈፅማል፡፡

የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ የ50 አገራት መሪዎች በርዕሰ ሊቀ ጳጳሱ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

ከአለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች መካከል የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም የሥነ ሥርዓቱ ተካፋይ ናቸው ተብሏል፡፡

ቀጣዩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቤተ ክርስቲያኒቱ ካርዲናሎች በዝግ በሚከናወን ሥነ ሥርዓት እንደሚመረጡ መረጃው አስታውሷል፡፡

#አሜሪካ

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ እና ዩክሬይን የሚያሂዱትን ጦርነት ለማስቆም ወደ ስምምነት እየተቃረቡ ነው አሉ፡፡

ቀደም ሲል ትራምፕ ሁለቱ አገሮች በብዙ የጦርነት ማስቆሚያ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ማስፈራቸውን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡

የዩክሬይኑ ፕሬዘዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ትናንት በቪዲዮ ተቀርፆ በተላለፈ መልእክታቸው ለተሟላ የተኩስ አቁም በሩሲያ ላይ ጫና እንዲበረታባት መጠየቃቸው ተጠቅሷል፡፡

እንደሚባለው ድርድሩ የግዛት ሽግሽግንም ይጨምራል፡፡

አሜሪካ የክራሚያ ልሳነ ምድር ለሩሲያ እንዲፀናላት የሚጠይቅ ሀሳብ ማቅረቧ ሲነገር ሰንብቷል፡፡

ቀደም ሲል የዩክሬይን መሪዎች ለሩሲያ ስንዝር መሬት አንተውላትም ሲሉ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡

#ጋቦን

በጋቦኑ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ብሪስ አሊጉ ንጉየማ ማሸነፋቸው በህገ መንግስታዊው ፍርድ ቤት ፀደቀላቸው፡፡

ንጉየማ ለፕሬዘዳንታዊ ምርጫው ከተሰጠው ድምፅ 95 በመቶ ያህሉን በማግኘት ማሸነፋቸው ሲነገር መሰንበቱን አናዶሉ ፅፏል፡፡

ሕገ መንግስታዊው ፍርድ ቤት ደግሞ ውጤቱን ተቀብሎ ማፅደቁ ተሰምቷል፡፡
#shegerFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አዋሽ ባንክ በአዲስ መልክ ያደሰዉን ትሬድ ሰርቪስ ቢሮዉን አስመረቀ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16446/

#Ethiopia |አዋሽ ባንክ በአዲስ መልክ ያደሰዉን የወጭና ገቢ ንግድ (Import- Export) ሥራዉን እንዲያሳልጥና ለደንበኞቹ አገልግሎት እንዲሰጥ ሪብራንድ ተደርጎ የታደሰውን የባንኩን የትሬድ ሰርቭስ ቢሮ የምረቃ ስነ ሥርዓት አካሄደ፡፡

በአምስት ቅርንጫፎች አንድ ብሎ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ባንኩ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በአሁኑ ወቅት ከ980 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ከ14.5 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉ ተገልጿል።
ቁጥራቸዉ እየጨመረ ለሚሄደው ደንበኞቹ ምቹ የአገልግሎት ማግኛ ካባቢን በመፍጠር ብቃት ባላቸው በስነ-ምግባር በታነጹ ሠራተኞችና በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ቀልጣፋ እና ሁሉን ያማከለ አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ ግዴታዉም ጭምር መሆኑን ባንኩ ገልጿል፡፡

የባንኩ መሥራች አባቶች ያወጡለትን የታዋቂውን የአዋሽ ወንዝ ስም ሳይለቅ በባንኩ ሎጎ ዲዛይንና በኮርፖሬት ቀለሞቹ ላይ መጠነኛ ማሻሻያ ተደርጎ በአዲስ መልክ ሪብራንድ ከተደረገ ወዲህ የባንኩ ዝናና ገጽታ በህብረተሰቡ ዘንድ ይበልጥ እንዲሰርጽ እና እንዲታወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉም ታዉቋል፡፡

የባንኩን አዲሱ ብራንድ መሠረት በማድረግም በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የተከፈቱት ቅርንጫፎች በሙሉ በአዲሱ የባንኩን ብራንዲንግ መመሪያና መስፈርት መሠረት ተከፍተው ወደ ሥራ እንዲገቡ ብዙ ሥራዎች የተሠሩ ሲሆን ነባር ቅርንጫፎችም አብኛዎቹ ሪብራንድ ተደርገዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩም አሁን እንደዋና መሥሪያ ቤት እየተገለገለበት ያለው ሕንጻ በባንኩን የብራንዲንግ መመሪያና መስፈርት ጠብቆ የዉስጥ ዕድሳት በማደረግ ለባንኩ ሠራተኞች ምቹ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር ተችሏል፡፡

ዛሬ ሪብራንድ ተደርጎ የውስጥ ዕድሳት የተደረገለት የባንኩ የትሬድ ሰርቪስ ቢሮ(Trade Service Office) ለሀገራችን የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ሚና ያለዉን የዉጭ ምንዛሪ ግኝት የሚሳለጥበት እና የወጪና ገቢ ንግድ ደንበኞች የሚስተናገዱበት ወሳኝ ቢሮ መሆኑም ተገልጿል።
.
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የሥዕል ጋለሪዎችና ተመልካች እየበዛ ቢመጣም ባህልና ወግን በማድመቅ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎለብቱ የስዕል ውጤቶች አነስተኛ መሆናቸው ተገለጸ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16448/

#Ethiopia | የስዕል ጋለሪዎችና ተመልካች እየበዛ ቢመጣም ባህልና ወግን በማድመቅ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎለብቱ የስዕል ውጤቶች ዝቅተኛ መሆናቸውን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ሃሳባቸውን ያሳፈሩ ሰአሊያን ተናግረዋል።

ከቀድሞው ዘመን አንጻር በዚህ ዘመን ሰአሊያንም ተመልካችም እያደገ የመጣበት ነው በማለት ነገር ግን በዚኛው ዘመን ባህልና ታሪክን በጥልቀት የተመለከቱ ስራዎች በቁጥር አነስተኛ መሆናቸውን ሰአሊ ይልቃል ቦጋለ ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በተለይ እንዲህ ባሉ የበአል ሳምንታት ከሃይማኖታዊ መሰረትም ይሁን ከባህላዊ ትውፊት የተቀዱ ማንነቶችን ተረድቶ ማህበራዊ ትስስርን ለማስፋፋት የሚሰሩ የስእል ጥበባት አነስተኛ መሆናቸውን ባለሙያው ይናገራሉ። ፈረንጆቹ እንደ ጸሎተ ሃሙስ ያሉትን በአላት ታላቁ እራት በማለት በስፋትና በጥልቀት ለየትውልዳቸው እሳቤውንና ሰዋዊ ትርጓሚውንም በስእል ጥበባቸው አኑረው አልፈዋል የሚሉት ባለሙያው በኛ ሀገር መሰል ጠቃሚ ሁነቶችን ለመስራት የሙያም የፍላጎትም ችግር መኖሩን በመግለጽ ፖለቲካዊ እሳቤን ምክንያት በማድረግም የማይሰሩ መኖራቸውንም ገልጸዋል።

ችግሩ የራሱ የባለሙያው ነው ሲሉ ለጣቢያችን ሃሳባቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላኛው ሰአሊ ማህደር ታሪኩ ናቸው። የታሪክ መረጣም፣ ፍላጎትም፣ ጥረትም እንብዛም አይስተዋልም የሚሉት ባለሙያው ነገር ግን እንደ ሀገር የሃይማኖታዊ ሆነ ባህላዊ ታሪክና ትውፊት ሃብታም ነን ሲሉ ተናግረዋል። ተመልካቹም ከፍ ባለ ስራቸው ከፍ ያለ እይታና ምልከታ ኖሮት እንዳይሞግታቸው የባለሙያዎቹ ጥረትና ውጤት ወሳኝነት አለው በማለት በራሱ የስእል ጋለሪና ተመልካች መስፋፋቱ ግን መበረታታት አለበት ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያዊ ሰአሊያን እንዲህ ያሉ የበአል ሳምንታትንም ሆነ መጪውን ሰፋፊ የሰርግ ሁነቶች በጥበባቸው ሰርተው የሀገሩን መልክ በማጉላት ሂደት ውስጥ ማለፋቸውን በመግለጽ የአሁኖቹ የዘርፉ ባለሙያዎችን የሀገር ሁለንተናዊ አስተሳሳሪ ማንነት ግድ ሊላቸው እንደሚገባ ባለሙያዎቹ አመላክተዋል።
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ሁሌ ቡና – ምርቃት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16450/

COFFEE HOUSE

#Ethiopia | ቁጥር 2 ሁሌ ቡና ሬስቶራንታችንን እየተመረቀ ነው

ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም
እና
እሁድ ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

ሬስቶራንታችንን እዲመርቁልን በአክብሮት ጠርተንዎታል።

ጠሪ አክባሪዎ
መላከ አየነው
ምግባሯ ደስላኝ

አድራሻ
ስታዲየም ወጋገን ባንክ ህንጻ ጎን
+251911-406388

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ታሪክ ፃፉ!..

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16452/

#Ethiopia | በዳይመንድ ሊግ 5000 ሜትር ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሁለተኛ እስከ ሰባተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

በቻይናው ዢያመን ዛሬ በተጀመረው ውድድር በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቺቤት በ14:27.12 የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል አሸንፋለች ።

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ፣የርቀቱ የአለም ክብረ ወሰን ባለቤት 14 :28.18 በመግባት የዓመቱን የግል ምርጥ ስዓቷን በማስመዝገብ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች ።

አትሌት ብርቄ ሀየሎም በ14:28.80 ሶስተኛ ፣አትሌት ሂሩት መሸሻ በ14:29.29 አራተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።(ኢአፌ)

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet