Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
6.15K subscribers
2 photos
4.68K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
ግማሽ ሚሊዮን አዲስ ተፈናቃዮች በጋዛ መኖራቸው ተገለፀ።

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16406/

#Ethiopia | የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በእስራኤል ጦር የተሰጡ በርካታ የማፈናቀል ትእዛዞች ፍልስጤማውያን በጋዛ ከአንድ ሶስተኛ ባነሰ አካባቢ እንዲኖሩ አድርጓቸዋል ብሏል።

ባለፉት ወራት በጋዛ 5መቶ ሺህ የሚጠጉ ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጦር ጥቃት ሳቢያ በግዳጅ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ አስታውቋል።

ድርጅቱ በሰጠው መግለጫ ባለፈው ወር በጋዛ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ አዲስ ዜጎች ተፈናቅለዋል።

በእስራኤል ጦር በተሰጡ በርካታ የማፈናቀል ትእዛዛት ፍልስጤማውያን በጋዛ ከአንድ ሦስተኛ ያነሰ ቦታ ላይ እንዲኖሩ አድርጓቸዋል፤ የቀረው ቦታም የተበታተነ ፣ደህንነቱ ያልተጠበቀ እና ለኑሮ ምቹ ያልሆነ ነው ብሏል።

መጠለያዎች በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ናቸው። አገልግሎት ሰጪዎችም ለመሥራት እየታገሉ ቢሆንም ያለው ግብዓትም እየተሟጠጠ ነው ብሏል።

ከጥቅምት 2023 ጀምሮ አብዛኞቹ ሴቶች እና ህፃናት የሆኑ 51 ሺህ 4መቶ የሚጠጉ ፍልስጤማውያን በጋዛ ተገድለዋል።
#ethioFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በየቦታዉ የጣልነዉ የኘላስቲክ ቆሻሻ ወዴት ይሄዳል ? መዘዙስ ?

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16408/

(ካህኑ ሞገስ)

#Ethiopia | የፕላስቲክ ቆሻሻ፡ የአካባቢ፣ የሰው ጤና እና የከተማ መሠረተ ልማት ቀውስ ያመጣል።

የፕላስቲክ ቆሻሻ ተከታታይ እና ሁሉን አቀፍ የአካባቢ ችግር ሲሆን የስነ-ምህዳርን፣ የሰው ጤናን እና የከተማ መሠረተ ልማትን ይጎዳል። ፕላስቲክ ለመበስበስ በመቶዎች እስከ ሺዎች ዓመታት ሊፈጅ ይችላል። ፕላስቲክ ከመበስበስ ይልቅ ወደ ትናንሽ ቅንጣቶች፣ ማይክሮፕላስቲክ ተብለው ወደሚጠሩ፣ ይከፋፈላል፣ እነዚህም ወደ አፈር፣ ውሃ እና የምግብ ሰንሰለት ውስጥ ዘልቀው ይገባሉ።

1. የፕላስቲክ ቆሻሻ ጉዞ
ፕላስቲክ ከሰው አጠቃቀም ጀምሮ እስከ አካባቢያዊ ጉዳት የሚያደርስ ዑደት ውስጥ ይጓዛል፡

ከእጅዎ ወደ መሬት፡ እንደ ፕላስቲክ ከረጢቶች፣ ጠርሙሶች እና ማሸጊያዎች ያሉ ለአንድ ጊዜ ጥቅም የሚውሉ ፕላስቲኮች ብዙውን ጊዜ ከትንሽ አገልግሎት በኋላ ይጣላሉ። በቂ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት በሌለባቸው አካባቢዎች እነዚህ ነገሮች በቆሻሻ ማጠራቀሚያ፣ በመንገዶች ወይም በተፈጥሮ አካባቢዎች ያርፋሉ። ለምሳሌ፣ የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ፕሮግራም (UNEP) መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በየዓመቱ 8 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ፕላስቲክ ወደ ውቅያኖስ ይገባል፣ ይህም በየደቂቃው አንድ የቆሻሻ መኪና ጭነት ጋር እኩል ነው።

ከመንገድ ወደ ሆድዎ፡ የፕላስቲክ ቆሻሻ የማይንቀሳቀስ አይደለም። በነፋስ፣ በውሃ ወይም በሰው እንቅስቃሴ ተጓጉዞ ወደ ማይክሮፕላስቲክ (5 ሚሜ ያነሱ ቅንጣቶች) ይከፋፈላል። እነዚህ ማይክሮፕላስቲኮች በባህር ህይወት፣ በግብርና አፈር እና በሰው ደምና አካላት ውስጥ ተገኝተዋል፣ እንደ Environmental Science & Technology (2022) ጥናቶች ያሳያሉ። በምግብ ሰንሰለት በኩል ማይክሮፕላስቲኮች በባህር ምግቦች፣ ሰብሎች እና የመጠጥ ውሃ ውስጥ ይገኛሉ፣ ይህም እንደ ሆርሞን መዛባት ያሉ የጤና አደጋዎችን ያስከትላል፣ ምንም እንኳን የረጅም ጊዜ ተፅዕኖዎች አሁንም እየተጠኑ ቢሆንም።

2. የአካባቢ እና ማህበራዊ ተፅዕኖዎች
የፕላስቲክ ቆሻሻ ሥነ-ምህዳርን እና የሰው ኑሮን የሚያውኩ ተከታታይ ችግሮችን ይፈጥራል፡

የፍሳሽ መዘጋት እና የጎርፍ መባባስ፡ “70% የከተማ ጎርፍ በፕላስቲክ ቆሻሻ ይባባሳል” የሚለው መግለጫ በተለይ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ውስጥ ካሉ ከተሞች ምልከታዎች ጋር ይጣጣማል። የፕላስቲክ ከረጢቶች እና ፍርስራሾች የዝናብ ፍሳሾችን እና የውሃ መስመሮችን ይዘጋሉ፣ በከባድ ዝናብ ወቅት ጎርፍን ያባብሳሉ።

ለምሳሌ፣ በሙምባይ ወይም ላጎስ ከተሞች ውስጥ በፕላስቲክ የተዘጉ የፍሳሽ ሥርዓቶች ከባድ የጎርፍ ክስተቶችን አስከትለዋል፣ ይህም የንብረት ውድመትና የህይወት መጥፋትን ያስከትላል። የአለም ባንክ የ2018 ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ደካማ የቆሻሻ አያያዝ፣ የፕላስቲክ ቆሻሻን ጨምሮ፣ የከተማ ጎርፍ አደጋን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።

ወንዞችን እና ውቅያኖሶችን መመረዝ፡ በወንዞች ውስጥ ያለ የፕላስቲክ ቆሻሻ የውሃ ሥነ-ምህዳርን ያውካል፣ ዓሳዎችን፣ ኤሊዎችን እና ሌሎች የዱር እንስሳትን ያንቃል። ታላቁ የፓስፊክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ፣ ተንሳፋፊ የፕላስቲክ ፍርስራሽ ስብስብ፣ የቴክሳስ መጠን ሁለት እጥፍ የሆነ ቦታ ይሸፍናል። እንደ BPA እና ፋታሌትስ ያሉ ከፕላስቲክ የሚወጡ ኬሚካሎች የውሃ ምንጮችን የበለጠ ይበክላሉ፣ የተለያዩ ተህዋስያን እና በእነዚህ ሥነ-ምህዳሮች ላይ ጥገኛ የሆኑ የሰው ማህበረሰቦችን ይጎዳሉ።

በግጦሽ መስኮች መከማቸት፡ እንደ ላሞች እና ፍየሎች ያሉ እንስሳት ብዙውን ጊዜ የፕላስቲክ ከረጢቶችን እንደ ምግብ ተሳስተው ይመገባሉ። ይህ የአንጀት መዘጋት፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና ሞትን ያስከትላል። በህንድ፣ ለምሳሌ፣ የእንስሳት ሐኪሞች ከላሞች ሆድ ውስጥ ኪሎግራም ፕላስቲክን ለማስወገድ ቀዶ ጥገና መፈጸማቸውን ይናገራሉ፣ ይህም “የፕላስቲክ ላም ሲንድሮም” ተብሎ ይጠራል። ይህ የእንስሳትን ደህንነት ብቻ ሳይሆን በእንስሳት ላይ ጥገኛ የሆኑ የግብርና ኢኮኖሚዎችን ያውካል።

ማይክሮፕላስቲኮች በምግብ ውስጥ፡ ማይክሮፕላስቲኮች ወደ ሰው ምግብ ሰንሰለት ውስጥ ገብተዋል፣ በባህር ምግቦች፣ ጨው፣ ማር እና በጠርሙስ ውሃ ውስጥ ተገኝተዋል። የ2019 የኒውካስል ዩኒቨርሲቲ ጥናት እንደሚገምተው ሰዎች በሳምንት 5 ግራም ፕላስቲክ ይመገባሉ።

3. የፕላስቲክ ችግር መጠን አስቸኳይ እርምጃ ይጠይቃል፡

ዓለም አቀፍ ምርት እና ቆሻሻ፡
በየዓመቱ ከ400 ሚሊዮን ቶን በላይ ፕላስቲክ ይመረታል፣ ከ10% ያነሰ ይገልበጣል፣ በUNEP መረጃ። አብዛኛው በቆሻሻ ማጠራቀሚያ፣ በተቃጠለ ወይም በአካባቢ ውስጥ ያርፋል።

የጤና አደጋዎች፡ ከማይክሮፕላስቲኮች ባሻገር፣ የፕላስቲክ ምርትና አወጋገድ እንደ ዳይኦክሲን ያሉ ብክለቶችን ይለቃል፣ እነዚህም ከካንሰር እና የመራባት ችግሮች ጋር የተያያዙ ናቸው። በአንዳንድ አካባቢዎች የተለመደ የፕላስቲክ ቆሻሻ ማቃጠል የአየር ብክለትን እና የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ያባብሳል።

የኢኮኖሚ ወጪዎች፡ የፕላስቲክ ብክለት በቱሪዝም፣ በዓሣ ማጥመድ እና በመሠረተ ልማት ላይ በየዓመቱ ቢሊዮኖች ዶላር ጉዳት ያደርሳል። የአለም ባንክ ግምት እንደሚያመለክተው የባህር ፕላስቲክ ብክለት ብቻ በዓመት 13 ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ኪሳራ ያስከትላል።

4. ተግባራዊ መፍትሄዎች
የተጠቆሙት እርምጃዎች—እንደገና ጥቅም ላይ የሚውሉ ከረጢቶችን መጠቀም፣ ለአንድ ጊዜ ጥቅም የሚውሉ ጠርሙሶችን መተካት፣ ቆሻሻ መልሶ መጠቀም እና ዘላቂ ንግዶችን መደገፍ—ግለሰቦች እና ማህበረሰቦች ሊወስዷቸው የሚችሉ ተግባራዊ እርምጃዎች ናቸው፡

እንደገና ጥቅም ላይ የሚውል ከረጢት ይዘው ይምጡ፡ ለአንድ ጊዜ ጥቅም የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች ዋነኛ የቆሻሻ መንስኤ ናቸው። በጨርቅ ወይም ዘላቂ ከረጢቶች መጠቀም የፕላስቲክ ምርትን ፍላጎት ይቀንሳል። ለምሳሌ፣ በኬንያ እና በሩዋንዳ ያሉ የፕላስቲክ ከረጢት እገዳዎች የሚታዩ ቆሻሾችን በእጅጉ ቀንሰዋል እና እንደገና ጥቅም ላይ የሚውሉ አማራጮችን አበረታተዋል።

ለአንድ ጊዜ ጥቅም የሚውሉ ጠርሙሶችን በመተካት፡ እንደገና ጥቅም ላይ የሚውሉ የውሃ ጠርሙሶች ወይም የብረት ኮንቴይነሮች በPET ጠርሙሶች ላይ ጥገኝነትን ይቀንሳሉ፣ እነዚህም የአለም ፕላስቲክ ቆሻሻ 12% ይይዛሉ።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
#ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) እና የአክሲዮን ማህበር ተመሳሳይነትና ልዩነት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16410/

#Ethiopia | በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC ) እና የአክሲዮን ማህበር ይገኙበታል ።

ሁለቱም ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ።

#ተመሳሳይነታቸዉ

• ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣
• የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣
• የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣
• የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣
• ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑን (የንግድ ህግ 256 እና 501 )
• በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣
• በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ ፣

#ልዩነታቸዉ

አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ አንቀጽ 495(4) ላይ ተገልጿል። የአክሲዮን ማህበርን ( share company ) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ አንቀጽ 248(3) ላይ ይገኛል።

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር አንድ በመቶ ማነስ አይችልም (የንግድ ህግ ቁጥር (496)

• አክሲዮን ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች መሆን አይችልም (የንግድ ህግ ቁጥር 247)

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4 (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል (የንግድ ህግ ቁጥር (495(1)

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ ክፍት የሚደርግ አይደለም አንቀጽ 495(2) ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ (የንግድ ህግ ቁጥር248)

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transfrable አይደለም። ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ።

• አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( plc) ዉስጥ ቦርድ የለም።

Via Lawyer tsegaye demeke

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
እንድታውቁት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16412/

⚠️⚠️

#Ethiopia | ነገ ቅዳሜ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 እስክ ለሊቱ 8፡00 ድረስ የሲስተም ማሻሻያ ስራ ስለምናከናውን፤ ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባችሁን በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የምትፈጽሙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ ከላይ ከተገለፀው ቀንና ሰዓት አስቀድማችሁ ክፍያችሁን እንድትፈፅሙ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አለኝታ ነፃ የስልክ መስመር በኢትዮ ቴሌኮም ተዘጋ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16414/

#Ethiopia | ሴታዊት በተሰኘችው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት የተመሠረተው ‘አለኝታ’ ነፃ የስልክ መስመር ለፆታዊ ጥቃት ተጎጂዎች ይሰጥ የነበረውን የሥነ ልቦና ምክር እና ድጋፍ አገልግሎት ማቋረጡን አስታወቀ።

ላለፉት ስድስት ዓመታት በ’6388′ ነፃ የስልክ መስመር ለተጎጂዎች የሥነ ልቦና ድጋፍን ጨምሮ የሕክምና እና የሕግ ጥቆማ ሲሰጥ የቆየው አለኝታ፤ ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ በኢትዮ ቴሌኮም ውሳኔ መቋረጡን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ስኅን ተፈራ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በፆታዊ ጥቃት ተጎጂዎች ጥያቄ እና በኢትዮጵያ በቀላሉ ምክር እና ድጋፍ የሚሰጥ ነፃ የስልክ መስመር አለመኖር አለኝታን ለመመሥረት ገፊ ምክንያት እንደነበር የሚያስረዱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በስምምነት አገልግሎቱ በ2011 ዓ.ም መጀመሩን ተናግረዋል።

የፆታዊ ጥቃት ተጎጂዎች ድጋፍ መስጫ የሆነው አለኝታ፤ በኢትዮ ቴሌኮም ውሳኔ መሠረት እንደተቋረጠ የሴታዊት ዳይሬክተር ተናግረዋል።

ቢቢሲ “የኢትዮ ቴሌኮምን የሥራ ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለማግኘት ያደረግኩት ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም” ብሏል።

ነፃ የስልክ መስመሩን ያለ ክፍያ ከሚያቀርበው ኢትዮ ቴሌኮም ጋር በየዓመቱ ውል እንደሚያድሱ የጠቆሙት ኃላፊዋ፤ የኩባንያው ኃላፊዎች ‘በደንብ አላስተዋወቃችሁንም’ የሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ እንደሚያነሱም ጠቁመዋል።
#Addisinsider

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተቋሙን አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የተዛባ መረጃ እየተሰራጨበት መሆኑን ገለፀ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16416/

#Ethiopia | ፌደራል ፖሊስ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለዜጎቹ ባስተላለፈው የፌስቡክ መልዕክት ስር በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፄ የሰጠሁት አስተያየት የለም ብሏል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የአሜሪካ ኤምባሲ ያስተላለፈውን የጥንቃቄ መልዕክትም ሆነ በማህበራዊ ሚዲያ ስለተቋሙ እየተሰራጨ ነው ያለውን የተዛባ መረጃ መመልከቱን አስታውቋል።

በመሆኑ ኤምባሲው ለዜጎቹ የደህንነት ጥንቃቄ መልዕክት በማስተላለፍ በከተማዋ የፀጥታ ችግር እንዳለ ለማመላከት ሞክሯል ያለ ሲሆን፥ ለዚሁ የኤምባሲው መልዕክት በፌደራል ፖሊስ ኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፅ እንደተሰራጨ በምስል የሚታየው መረጃ ተቋሙን የሚወክል አይደለም ብሏል።

ፖሊስ ጉዳዩን በይበልጥ እንዲያጣራ እየተደረገ እንደሚገኝም አመላክቷል።

ኤምባሲው ያስተላለፈው የጥንቃቄ መልዕክትም ከአዲስ አበባ ከተማ ነባራዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር የማይገናኝ ነው ብሏል።
#aradaFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
መልአኩ በችግራችሁ ይድረስላችሁ የምስራቹን ያምጣላችሁ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16418/

መልአኩ በችግራችሁ ይድረስላችሁ የምስራቹን ያምጣላችሁ 🤲 🤲 🤲 🤲

ቅዱስ ገብርኤል 200 ብር ይጠይቃችኋል
⛪️
ቅዱስ ገብርኤል በችግራችሁ የደረሰላችሁ÷ስሙን ጠርታችሁ ከመከራ የወጣችሁ ÷በጸበሉ የተፈወሳችሁ የቅዱስገብርኤል ወዳጆች የመልአኩ ቤተ መቅደስ ሊፈስብን ድረሱልን ።፨

⛪️ይህ በለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ የሚገኘው አራብሳ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያሉበት ቢሆንም በዋናነት የቤተክርስቲያኑ ቆርቆሮ አፍስሶብን ንዋየተ ቅዱሳቶቹ ከጥቅም ውጭ እየሆነብን ለማገልገል ተቸገርን ቦታው ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ ምዕመናን ቆመው የሚያስቀድሱበት አጥተው ተቸግረናል።ክረምቱ ሳይገባ ጊዜያዊ መፍትሔ ለመፈለግ እና ለማስተካከል የተቻላችሁን በቅዱስ ገብርኤል ስም አግዙን

⛪️ከሰኳር ÷ከካንስር ÷ከደም ግፊት ÷ ከመተት ከተለያዩ የአጋንት እስራት የሚፈታው የቅዱስ ገብርኤል ጸበል ቦታ የከብቶች መዋያ ሆነብን ኦርቶዶክሳውያን የምንቆርብበትን ÷የምንጽናናበትን ቤተ መቅደስ ከመፍረስ ትታደጉልን ዘንድ በቅዱስ ገብርኤል ስም እንማጸናችኃላን።
ለቅዱስ ገብርኤል ከ200 ጀምራችሁ የተቻላችሁን አግዙን

የገዳሙ አካውንት 1000660699671
ለበለጠ መረጃ 0912376444/0910871679 ይደውሉ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ማሜሎዲ ሰንዳውስ እና ፒራሚድስ ለፍጻሜ ደረሱ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16420/

#Ethiopia | በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ማሜሎዲ ሰንዳውስ አል አህሊን በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሷል።

በካይሮ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም በተደረገው ጨዋታ የደቡብ አፍሪካው ክለብ ሰንዳውስ ከአል አህሊ አንድ አቻ ተለያይቷል።

ሁለቱ ቡድኖች ፕሪቶሪያ ላይ የተገናኙበት ጨዋታ 0 ለ 0 መጠናቀቁን ተከትሎ ማሜሎዲ ሰንዳውስ ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ህግ ለፍጻሜ የደረሰበትን ውጤት አስመዝግቧል።

የ12 ጊዜ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው አል አህሊ ከ2021 በኋላ ሰንዳውስን ማሸነፍ አልቻለም።

በዚያው በግብፅ በተደረገ ሌላ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ፒራሚድስ ኦርላንዶ ፓይሬትስን 3 ለ 2 አሸንፎ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።

የግብጹ ክለብ ፒራሚድስ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ ሲደርስ ኦርላንዶ ፓይሬትስ 2ኛ ዋንጫውን ለማሳካት ቢቃረብም ለፈጻሜ ሳይደረስ ቀርቷል።

በፍጻሜው ፒራሚድስ ከማሜሎዲ ሰንዳውስ የሚገናኙ ይሆናል።

በአንተነህ ሲሳይ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
መጪውን የ ፋሲካ በዓል አስሞልክቶ ከ 2,000,000 ብር በላይ ቅናሽ ይጠቀሙ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16422/

ይህ የምስራች ለውድ ደንበኞቻችን ስናቀርብ በታላቅ ደስታ ነው::

📌📌 በ ቁጥር 3ሳይት በሳርስ ዓደይ አበባ B+G+7
የሆነው ህንፃችን ላይ ከረጅም አከፋፈል ጋር እንጠብቆታለን!
ያስተውሉ ብልሆች የ እድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ለውስን ቤቶች ብቻ የቀረበ ዕድል ሞሆኑ ይገንዘቡ!

‘አልቲማ ሪል እስቴት’

“ህልምዎን ይኑሩ!”

“Live Your Dreams!”

ለበለጠ መረጃ :-. ☎️0996000000 / 0995222222

➡️Website: http://www.ultimaet.com

➡️Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61568957484689

➡️Whatsapp: https://whatsapp.com/channel/0029VawOxno545uoGPoLfH3X

➡️Telegram: https://t.me/ultimarealestate1

➡️YouTube: https://www.youtube.com/@UltimaRealestate

➡️ TikTok: tiktok.com/@ultimareal.estate

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
“ ከመቼውም በተሻለ ቁመና ላይ ነኝ “ ትግስት አሰፋ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16424/

#Ethiopia | በአለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ የተቀመጠው ተጠባቂው የለንደን ማራቶን ውድድር ነገ እሁድ ይካሄዳል።

በሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ የምትጠበቅ ሲሆን ከኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሰን ጋር ጠንካራ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ከአለም ምርጥ ሶስት የማራቶን ሰዓቶቹ የሁለቱ ባለቤት የሆኑት አትሌቶቹ ለማሸነፍ እንደሚፎካከሩ ከውድድሩ በፊት ለአዘጋጆቹ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

“ ለውድድሩ ጥሩ ዝግጅት አድርጌያለሁ “ ያለችው ትግስት አሰፋ በርሊን ላይ የአለም የማራቶን ሪከርድ ስሰብር ከነበረኝ የተሻለ ቁመና ላይ እገኛለሁ ብላለች።

“ውድድር የምጀምረው አሸንፋለሁ ብዬ ነው የሚፈጠረው አይታወቅም ነገርግን ለማሸነፍ ነው ተዘጋጅቼ የመጣሁት ” ስትል ትግስ አሰፋ ተናግራለች።

” ለንደን ማራቶን ትልቅ ውድድር ነው እዚህ መሮጥ እንድወድ ያደረገኝ ብዙ ምክንያቶች አሉኝ እዚህ ማሸነፍ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው።” ትግስት አሰፋ

አትሌት ሲፋን ሀሰን በበኩሏ “ በለንደን ማራቶን ስትሮጥ የኦሎምፒክ ፉክክር ይመስላል ለውድድሩ ጓጉቻለሁ ምክንያቱም እርስበርስ እንተዋወቃለን “ ስትል ተደምጣለች።

በወንዶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ ፣ የባለፈው አመት የቦታው አሸናፊ አሌክሳንደር ሙቲሶ ፣ አሊዩድ ኪፕቾግ እና ሰባስትያን ሳዌ ቅድም ግምት ያገኙ አትሌቶች ናቸው፡፡
#tikvah
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ስርዓተ ቀብር

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16426/

#Ethiopia | የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በሁሉም የኢቢሲ ዶትስትሪም ዲጂታል ሚዲያ አማራጮች በቀጥታ ይከታተሉ፦

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ለመጨረሻው ዕረፍታቸው የመረጡት ልዩ ስፍራ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16428/

#Ethiopia | የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ እ.አ.አ በ2022 ባደረጉት ኑዛዜ ድካሙ በዝቶባቸው ካረፉ እንደ ቀደምት ጳጳሳት ሁሉ ቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አልቀበርም ብለው ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ በዚሁ ወቅት በሮም ኢስኪሊኖ ሰፈር ውስጥ በቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ማጊዮር ባዚሊካ ውስጥ መቃብራቸውን አስቀድመው እንዳዘጋጁም ተናግረው ነበር።

በፈረንጆቹ 1269 ዓ.ም ከነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆኖሪየስ 3ኛ ጀምሮ እስከ 1669 ዓ.ም ከነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ኬልመንት 9ኛ ድረስ ሰባት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቀብራቸው የተፈፀመው በቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ነው።

ቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ግንባታው ከተጠናቀቀበት እ.አ.አ 1626 ዓ.ም ወዲህ ከ31 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ 24ቱ በቤተ ክርስቲያኑ ዋሻ ውስጥ ነው የተቀበሩት።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ልምዱን ለመቀየር ለምን ፈለጉ?

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ከቫቲካን ውጭ ቀብራቸውን ለማድረግ የፈለጉት ለኢየሱስ እናት ለቅድስት ማርያም ባላቸው የተለየ ፍቅር መሆኑንም በወቅቱ ገልጸዋል።

እንደ ቢቢሲ መረጃ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ከዚህች በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከተገነባች የቅድስ ማርያም ቤተክርስቲያን ጋር የተለየ ቁርኝት ያላቸው ሲሆን፣ ከመቶ ጊዜ በላይም ጎብኝተዋታል።

ባለፈው ዓመት በወጣ አዲስ የአምልኮ ሥርዓት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በአንድ ዚንክ በተሸፈነ የእንጨት ሳጥን ውስጥ እንደሚያርፋ ተናግረው ነበር።

ከእርሳቸው በፊት የነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ቤኔዲክት 16ኛ በሬሳ ሳጥን ውስጥ ነው የተቀበሩት።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የሳንባ ምች ሕመማቸው ብሶባቸው ወደ ሆስፒታል ያመሩት የካቲት አጋማሽ ሲሆን፣ በማገገሚያ ውስጥ በርካታ ጊዜያት ቆይተው ወደ መኖሪያቸው ከተመለሱ በኋላ ሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ይታወሳል።

ሥርዓተ ቀብራቸውም በዛሬው ዕለት በዚሁ በመረጡት ስፍራ የሚፈፀም ሲሆን አሁን ላይ የአስከሬን ሽኝት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የሀገራት መሪዎች በሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ስርአተ ቀብር ላይ ለመታደም ሮም ገብተዋል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16430/

#Ethiopia | የዓለም ሀገራት መሪዎች በሮማውጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ስርአተ ቀብር ላይ ለመታደም ሮም ገብተዋል።

ባለፈው ሰኞ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ፖፕ ፍራንሲስ ስርአተቀብር በዛሬው ዕለት ይፈጸማል።

ስርአተ ቀብሩ ከምሳ ሠአት ጀምሮ በሚካሄድ ፕሮግራም የሚካሄድ ሲሆን፥ የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎችም በስነስርአቱ ላይ ለመገኘት ሮም ገብተዋል።

እንደ ቫቲካን መረጃ ከሆነ ሊቀ ጳጳሱ ካረፉበት እለት ጀምሮ ከ250 ሺህ በላይ ምዕመን በስፍራው በመገኘት ተሰናብተዋል።
#aradafm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታውች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16432/

#Ethiopia | በስፔን ኮፓ ዴላሬይ የፍጻሜ ጨዋታ

ምሽት 04:00 ባርሴሎና ከ ሪያል ማድሪድ

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የዛሬ ተጠባባቂ ጨዋታዎች

8:30 ኤቨርተን ከ ቼልሲ
11:00 ብራይተን ከ ዌስትሃም
11:00 ኒውካስትል ከ ኢፕስዊች
11:00 ሳውዝሃፕተን ከ ፉልሃም
01:30 ወልቭስ ከ ሌስተር ሲቲ

በጀርመን ቡንደስሊጋ የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች

10:30 ባየር ሌቨርኩሰን ከ ኦግስበርግ
10:30 ባየር ሙኒክ ከ ሜንዝ
10:30 ሆፈናየም ከ ዶርትሙንድ
10:30 ሆልስታይን ኪል ከ ዶርትሙንድ
10:30 ውለቭስበርግ ከ ፍራይበርግ
ምሽት 1:30 ፍራንክፈርት ከ RB ሌፕዝሽ

#ዳጉ_ስፖርት
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የተራራ ላይ ሩጫ በኢትዮጵያ (Hiking)

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16434/

ክብር፣ፍቅርና ህብር በሚል መሪ ቃል የተራራ ላይ ሩጫ ተዘጋጅቷል።

#Ethiopia | በኢትዮጵያ ታላቅ የተራራ ጉዞ ውድድር በእንጦጦ ፓርክ ይደረጋል።

በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ በሚዘጋጀው የተራራ ላይ ውድድር በሴትም በወንድም ለአሸናፊዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ሽልማት ተዘጋጅቷል ተብሏል።

ይህንን ውድድር ያዘጋጀው 90 ቀናት ሁለተናዊ ለውጥ ስፖርት በማሰልጠን የሚታወቀው ማስተር ሔኖክ ነው።

ማስተር ሔኖክ እንደተናገረው በኢትዮጵያ ያሉ ተራራዎች ለቱሪዝምና ለስፖርቱ ዘርፍ መጠቀም እንዲያስችል ተደረጎ የተዘጋጀ ነው ብሏል።

የስፖርት ባህላችን እያጠናከርን እርስ በእስሳችን ግኑኝነታችን የሚጠናከርበት መንገድ ለመፍጠር ነው ተብሏል።

በዝግጅቱ ሁሉም አገልግሎት እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን መኪና ማቆምያ ቦታ ከሙሉ ጥበቃ ጋር መዘጋጀቱን ነው ማስተር ሔኖክ የተናገረው።

በውድድሩ ከ10ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉበት የተነገረ ሲሆን በውድድሩ ለሚሳተፉ ሰዎች ቲሸርቱን በ500 ብር ቀርቦላቸዋል ተብሏል።

ውድድሩ 5ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ለአሸናፊዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ሽልማት ተዘጋጅቷል።

በውድድሩ እድሜያቸው ከ10 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት በነጻ ይሳተፋሉ ተብሏል።

ውድድሩ የሚደረገው ብዙዎች እንዲሳተፉ በማሰብ ሚያዝያ የሜዴይ ቀን በሚከበርበት ቀን ሲሆን ሚያዝያ 23/2017 አመተ ምህረት መሆኑ ነው የተገለጸው።

በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች ከ30ሺህ ብር እስከ10 ሺህ ብር እንደቅደም ተከተላቸው ሽልማት መዘጋጀቱን ነው ማስተር ሔኖክ የተናገረው።
==
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክ ቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ኮምቦልቻ : የኢንዱስትሪ እና ፋይናንስ ኤክስፖ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16436/

#Ethiopia | ከሚዚያ 20 እስከ ሚያዚያ 30 2017 ዓ.ም ለሚካሄደው የኢንዱስትሪ እና ፋይናንስ ኤክስፖ ዝግጅት መጠናቀቁን ከተማ አሥተዳደሩ አስታውቋል።

የቀጣናውን እምቅ የመልማት አቅም ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክተውን የኢንዱስትሪ እና የፋይናንስ ኤክስፖ ለማካሄድ ጥቂት ቀናት ቀርተዋል።

ኤክስፖው “ሰላም የኢንቨስትመንት ፓስፖርት ነው” በሚል መልእክት እንደሚካሄድ ነው የተገለጸው።

በኮምቦልቻው ኤክስፖ ላይ:-

📌ከ300 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኢንቨስተሮች፣

📌 50 የሚኾኑ የፋይናንስ ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት፣

📌 ከ30 በላይ የመንግሥት ተቋማት

📌ከ20 ያላነሱ ሥራ ፈጣሪዎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ዘመን ጠቀስ ዘመነኛ ዕድል!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16438/

http://xn--ethiolotterey-ok6c.et/ ይመዝገቡ፤

የ50 ሚሊየን ብር ሎተሪ ይቁረጡ!

ሲመዘገቡ በሚሊኒየም፣ በማሪዮት እና ግዮን ኮንሰርቶች ዘና ፈታ እያሉ በእያንዳንዱ ኮንሰርቶች 50 ሺህ ብር ያሸንፉ!

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አስደሳች ዜና ከስልጤ ዞን ከወራቤ!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16440/

#Ethiopia | “ሽልማት ጣመኝ ፔፕሲ ድገመኝ” በሚል መሪ ቃል ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንደስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማ ለደንበኞቹ ካዘጋጃቸው ሽልማቶች ውስጥ አንዱ ID4 የኤሌክትሪክ መኪና በሥልጤ ዞን – ወራቤ ከተማ ለዕድለኛ ወጥቷል።

ዕድለኛው አሸናፊ ፋሪስ ሱለይማን የሚያሸልመውን እጣ ያገኘው ሚሪንዳ ጠጥቶ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

አሸናፊው ፋሪስ ሽልማቱን በወራቤ ከተማ ሚያዝያ 18 ቀን 2017ዓ.ም. በተከናወነ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም የተረከበ ሲሆን ከዚህ በፊት በተለያዩ ከተሞች ነዋሪ የሆኑ ሌሎች ዕድለኞች ሚሪንዳ፥ ፔፕሲ እና ሰቨን አፕ ጠጥተው የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማቶች ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ከብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16442/

#Ethiopia | የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሚያዝያ 17 እስከ 18/ 2017 ዓም መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡ በዚህ ስብሰባም የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ ኢትዮጵያ በ2018 ከተስፋ ወደሚጨበጥ ብርሃን ለመሻገር፤ በ2023 የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለመሆን፤ በ2040 ደግሞ ዓለም አቀፍ የብልጽግና አርአያ ለመሆን ያስቀመጠችው ርእይ እንደሚሳካ የሚያረጋግጡ የስኬት ፍንጮች መታየታቸውን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡ እነዚህ የስኬት ፍንጮች የያዝነው ፍኖተ ብልጽግና ትክክል መሆኑን አመላክተውናል፡፡

ከብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በኋላ አያሌ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡ ከተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በየደረጃው የሚደረገው ምክክርና ትብብር በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ወደ አዲስ ምእራፍ ገብቷል፡፡ ከአንድ ክልል በስተቀር፣ ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ምእራፍ በሁሉም ክልሎች ተጠናቅቋል፡፡ በሀገሪቱ የጸጥታ ችግር በነበረባቸው አንዳንድ አካባቢዎችም ሰላም እየሰፈነ ነው፡፡ መንግስት በተደጋጋሚ ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ እጅ የሚሰጡና ወደ ሰላም ድርድር የሚመጡ ታጣቂዎች ከዕለት ወደ ዕለት ቁጥራቸው እየጨመረ ይገኛል፡፡ የመንግሥት ሕግ የማስከበርና የማድረግ ዐቅም እየጎለበተ መጥቷል፡፡ ከሶማሊያ ጋር ተፈጥሮ የነበረው ውዝግብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ተፈትቷል፡፡ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዲኖራት የተያዘው አቋም ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነቱ እየጨመረ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ያላት ግንኙነት ከመሻሻሉም በላይ የሚደረግላት ድጋፍ እያደገ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት ጨምሯል፡፡ የዲፕሎማሲ ግንኙነቷም በሁሉም አቅጣጫ ከፍ ብሏል፡፡

እስከአሁን ያለው አፈፃፀም የሚያሳየው በያዝነው አመት አጠቃላይ ኢኮኖሚው በታቀደው መሠረት በ8.4 በመቶ የሚያድግ መሆኑን የሥራ አስፈጻሚው ገምግሟል፡፡ በዘርፍ ደረጃ ደግሞ ግብርና በ6.1 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ በ12.8 በመቶ፣ ማኑፋክቸሪንግ በ12.0 በመቶ፣ ኮንስትራክሽን በ12.3 በመቶ፣ አገልግሎት ደግሞ በ7.1 በመቶ የሚያድጉ መሆናቸው ተገምግሟል፡፡ ያለፉት 9 ወራት ጠቅላላ የመንግሥት ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ134 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡ የውጭ ብድር ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ወደ 13.7 በመቶ ወርዷል፡፡ ወደ ውጭ ገበያ የሚቀርቡት ስድስት ዋና ዋና ምርቶች፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸሩ ከ82 በመቶ እስከ 386 በመቶ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡ በስንዴ፣ በሩዝ፣ በቡና፣ በሻሂ ቅጠል እና በፍራፍሬ ምርቶች በአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ለመውጣት እየተደረገ ያለው ትግል ፍሬ እያፈራ መሆኑን አይተናል፡፡

ውድ የብልፅግና አመራሮች፣ የብልፅግና አባላትና መላው ሕዝባችን፣
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ዝቅተኛ ኑሮ በሚኖሩ ወገኖች ላይ ጫና እንዳያሳድር አስፈላጊ የሆኑና የታቀዱ የድጋፍ መርሐ ግብሮች መከናወናቸውንም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መርምሯል፡፡ ለማዳበሪያ 62 ቢልዮን ብር፣ ለሴፍቲኔት 41.2 ቢልዮን ብር፣ ለነዳጅ 60 ቢልዮን ብር፣ ለመድኃኒት 3.5 ቢልዮን ብር፣ ለምግብ ዘይት 6.1 ቢልዮን ብር፣ እንዲሁም ለደመወዝ 38.4 ቢልዮን ብር ድጎማ ተደርጓል፡፡ ባለፉት 9 ወራት ብቻ 344790 የውጭ ሀገር ሕጋዊ የሥራ ዕድሎች እና ከ3 ሚልዮን በላይ የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድሎች ተፈጥረዋል፡፡ የርቀት የሥራ ዕድሎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱ ታይቷል፡፡

የመንግሥት የልማት ተቋማትን በአዲስ አስተሳሰብና በአዲስ መንገድ መልሶ ለማደራጀትና ለመምራት መቻሉ፣ እያስገኘው ያለው ውጤት ለሌሎች አርአያ የሚሆን እንደሆነ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አሁን ያለው ጠቅላላ ገቢ 1.5 ትሪልዮን መድረሱ ታይቷል፡፡ ከባለፈው ዓመት የ9 ወራት አፈጻጸም አንጻር የዘንድሮ ገቢው የ86 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱም ተረጋግጧል፡፡ ይሄም መንግሥት የሀገርን ሀብት ለማወቅ፣ ዐውቆም በሚገባ ለማስተዳደር፣ አስተዳድሮም ወረት ለማከማቸት የተከተለው መርሕ ትክክል መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የውጭ ምንዛሬ ክምችት ዕድገት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ 9 ወራት ጋር ሲነጻጸር የ203.99 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ የባንኮች ተቀማጭ ገንዘብ ከ3 ትሪልየን በላይ ተሻግሯል፡፡ የ9 ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከ5 ቢልዮን ዶላር በላይ ሲሆን፣ ይሄም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ150.39 በመቶ ዕድገት አምጥቷል፡፡ ባለፉት ስምንት ወራት 473.9 ቢልዮን ብር ብድር ከንግድ ባንኮች ተለቅቋል፡፡ ይሄም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አንጻር በ61.9 በመቶ ከፍ ይላል፡፡ ከዚህ ብድር ውስጥም 76.6 በመቶ ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ ነው፡፡ ለግሉ ዘርፍ የበለጠ ብድር መሰጠቱ፣ የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ተገቢውን ሚና እንዲጫወት ያስቀመጥነው ፖሊሲ በተግባር እየተገለጠ መሆኑን አመላካች ነው፡፡

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት የጀመርናቸው ሁሉን አቀፍ ጥረቶች ፍሬያቸው እየጎመራ ነው፡፡ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 50.2 ሚልዮን፣ የሞባይል ተጠቃሚዎችም 86.6 ሚልዮን ደርሰዋል፡፡ የቴሌ ብር ደንበኞችም ከ52.56 ሚሊዮን በላይ ናቸው፡፡ ዲጂታል ፋይናንስ፣ የኅብረተሰቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢኮኖሚው መሣለጥ ጉልህ ድርሻ እያበረከተ ነው፡፡ ባለፉት 9 ወራት በዲጂታል መንገዶች 7.73 ቢልዮን ብር ተቆጥቧል፡፡ 26.77 ቢልዮን ብር በዲጂታል በኩል ብድር ተሰጠ ሲሆን፣ የ12.51 ትሪሊዮን ብር ግብይት ደግሞ በዚሁ መንገድ ተከናውኗል፡፡

ዋና ዋና ፕሮጀክቶችን በጊዜና በተገቢ ደረጃ ለማጠናቀቅ የተሰጠው አቅጣጫ ብዙዎችን ለፍጻሜ እያበቃቸው ነው፡፡ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 98.66 በመቶ ደርሷል፡፡ የኮይሻ፣ አይሻና አሰላ የኃይል ማመንጫዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሠረት እየተጓዙ መሆናቸው ተገምግሟል፡፡ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታም የኢትዮጵያን ነገ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የቅድመ ዝግጅት ምእራፉ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የኮሪደር ልማት በአዲስ አበባ በ8 ኮሪደሮች እና በመላው ኢትዮጵያ በ65 ከተሞች እየተከናወነ መሆኑ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡ ብዙዎቹ የመስኖ ግድቦች ወደ ፍጻሜያቸው እየደረሱ ናቸው፡፡ ከዘጠኙ የመስኖ ግድቦች ውስጥ ስድስቱ አፈጻጸማቸው ከ75 በመቶ በላይ ደርሷል፡፡
“ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪ ቃል ከ82 ቢልዮን ብር በላይ ድጋፍ የተሰበሰበ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 6815 ትምህርት ቤቶች በመላ ሀገሪቱ ተገንብተዋል፡፡ የነባር ትምህርት ቤቶችን ዐቅም ለማሻሻል እና በግጭት የተጎዱትን ለመጠገን የተደረገው ጥረት በትውልድ ላይ ለሚሠራው ሥራ መሠረት የሚጥል መሆኑ ታይቷል፡፡ የወላድ እናቶችን እና የጨቅላ ሕጻናትን ሞት በመቀነስ ረገድ የተሻለ ውጤት መመዝገቡም ታይቷል፡፡

በኢትዮጵያ የቱሪዝም መዳረሻዎችና የስፖርት ሥፍራዎች በቁጥርም፣ በዓይነትም እያደጉ መጥተዋል፡፡ በተለያዩ ከተሞች በመገንባት ላይ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ስታዲየሞች በመጠናቀቂያ ምእራፍ ላይ ናቸው፡፡ ይሄም ኢትዮጵያ ታላላቅ አፍሪካዊ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ ለያዘችው ዕቅድ መሳካት ወሳኝ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ…
የባህር ማዶ ወሬዎች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16444/

#ርዕሰ_ሊቃነ_ጳጳሳት_አባ_ፍራንችስኮስ

#Ethiopia | በሳምንቱ መጀመሪያ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንስስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይፈፀማል፡፡

አባ ፍራንሲስ በአንጎል ውስጥ የደም መፍሰስ እና በልብ ድካም በ88 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ባለፈው ሰኞ ነው፡፡

እጅግ በርካታ ካቶሊካውያን በቫቲካን በአባ ፍራንሲስ ሕልፍት ሐዘናቸው ሲገልጹ ሰንብተዋል፡፡

የአባ ፍራንሲስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ በሮም ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ይፈፅማል፡፡

የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ የ50 አገራት መሪዎች በርዕሰ ሊቀ ጳጳሱ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

ከአለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች መካከል የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም የሥነ ሥርዓቱ ተካፋይ ናቸው ተብሏል፡፡

ቀጣዩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቤተ ክርስቲያኒቱ ካርዲናሎች በዝግ በሚከናወን ሥነ ሥርዓት እንደሚመረጡ መረጃው አስታውሷል፡፡

#አሜሪካ

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ እና ዩክሬይን የሚያሂዱትን ጦርነት ለማስቆም ወደ ስምምነት እየተቃረቡ ነው አሉ፡፡

ቀደም ሲል ትራምፕ ሁለቱ አገሮች በብዙ የጦርነት ማስቆሚያ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ማስፈራቸውን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡

የዩክሬይኑ ፕሬዘዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ትናንት በቪዲዮ ተቀርፆ በተላለፈ መልእክታቸው ለተሟላ የተኩስ አቁም በሩሲያ ላይ ጫና እንዲበረታባት መጠየቃቸው ተጠቅሷል፡፡

እንደሚባለው ድርድሩ የግዛት ሽግሽግንም ይጨምራል፡፡

አሜሪካ የክራሚያ ልሳነ ምድር ለሩሲያ እንዲፀናላት የሚጠይቅ ሀሳብ ማቅረቧ ሲነገር ሰንብቷል፡፡

ቀደም ሲል የዩክሬይን መሪዎች ለሩሲያ ስንዝር መሬት አንተውላትም ሲሉ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡

#ጋቦን

በጋቦኑ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ብሪስ አሊጉ ንጉየማ ማሸነፋቸው በህገ መንግስታዊው ፍርድ ቤት ፀደቀላቸው፡፡

ንጉየማ ለፕሬዘዳንታዊ ምርጫው ከተሰጠው ድምፅ 95 በመቶ ያህሉን በማግኘት ማሸነፋቸው ሲነገር መሰንበቱን አናዶሉ ፅፏል፡፡

ሕገ መንግስታዊው ፍርድ ቤት ደግሞ ውጤቱን ተቀብሎ ማፅደቁ ተሰምቷል፡፡
#shegerFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet