Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
6.09K subscribers
2 photos
4.63K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
በአዲስ አበባ ለጨረታ ከወጡ ቦታዎች በአራዳ ክፍለ ከተማ የቀረበው መሰረዙ ተሰማ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16345/

– ከጨረታው ስድስት ቢሊዮን ብር ገቢ ይጠበቃል ተብሏል፣

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለጨረታ ካቀረበው 18 ሔክታር መሬት ውስጥ፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ የተዘጋጀው 1.2 ሔክታር መሬት፣ መንግሥት ለልማት ስለፈለገው ሙሉ ለሙሉ ከጨረታ መሰረዙን አስታወቀ፡፡

የመሬት ልማት አስተደደር ቢሮ የመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ለጨረታ ከቀረቡ ዘጠኝ ክፍላተ ከተሞች ሥር ከሚገኙ ቦታዎች መካከል፣ የአራዳ ክፍለ ከተማ መሬት መንግሥት ለልማት በመፈለጉ ምክንያት ከጨረታ ተሰርዟል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር የመሬትና ልማት አስተዳደር ቢሮ በሊዝ አዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ በከተማዋ ለጨረታ ከቀረቡ ቦታዎች ውስጥ ከዚህ በፊት ሙሉ ለሙሉና በከፊል ቦታዎችን መሰረዙን አስታውሰዋል፡፡

ለጨረታ ከቀረቡ ቦታዎች ውስጥ ካዛንቺስ የሚገኝ አንድ ቦታ በካሬ ሜትር 265 ሺሕ ብር ለመግዛት ከተጫራቾች ዋጋ መቅረቡን፣ በአጠቃላይ በስምንት ክፍላተ ከተሞች 380 ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው መታወቁን ገልጸዋል፡፡

በስምንት ክፍላተ ከተሞች የተደረገውን ጨረታ ያሸነፉት 38ዐ ተጫራቾች ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸውን ሲያጠናቅቁ 6.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

ቢሮው በአጠቃላይ ካቀረባቸው 427 ቦታዎች ውስጥ የተጠቀሱት አሸናፊዎች ተለይተው ቅድመ ክፍያ እንዲፈጽሙ በጋዜጣ እንዲታተም መላኩን ጠቅሰው፣ በጨረታው የቀረበው አነስተኛ ዋጋ በካሬ ሜትር ስምንት ሺሕ ብር እንደሆነና ይህም አቃቂ ክፍለ ከተማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎች በስምንት ክፍላተ ከተሞች ውስጥ እንደሚገኙ የተናገሩት ዳይሬክተሩ፣ በአጠቃላይ የጨረታ ሰነዱን ገዝተው የተጫረቱት ብዛታቸው 6,885 እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡

ለአምስተኛ ዙር የመሬት ጨረታ በአዲስ ከተማ፣ በኮልፌ ቀራኒዮና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍላተ ከተሞች 96 ቦታዎች ሲቀርቡ፣ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎቻቸው በተገኙበት በመመርያው መሠረት ተገቢውን መሥፈርት ባለማሟላታቸው ከጨረታ ውጪ ሲደረጉ፣ 14 ቦታዎች በቂ ተጫራቾች ባለማቅረባቸው ጨረታው መሰረዙን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡
(ሪፖርተር)

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በ ኤሌጋንስ ኮንሰርት እየተዝናኑ ዕድለኛ ይሁኑ!በዕለቱ 50ሺ ብር ለማሸነፍ፤

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16347/

Ethiolottery.et ላይ አሁኑኑ ይመዝገቡ፤
የ50 ሚሊየን ብር ሎተሪ ይቁረጡ!

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በ ልዑል ኮንሰርት እየተዝናኑ ዕድለኛ ይሁኑ!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16349/

በዕለቱ 50,000 ብር ለማሸነፍ፤ Ethiolottery.et ላይ አሁኑኑ ይመዝገቡ ፤ የ5ዐ ሚሊየን ብር ሎተሪ ይቁረጡ!

SCAN and REGISTER

POLAR Plus2

Ethiolottery

TAMCON

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ከታሪፍ በላይ በማስከፈልና ትርፍ በመጫን ህዝብን ያማረሩ 247 ግለሰቦች ርምጃ ተወሰደባቸው

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16351/

#Ethiopia | በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከአስሩም የክላስተር ከተሞች ተነስተው ወደ አዲስ አበባ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ሕግ እና ሥርዓት ያላከበሩ 247 ግለሰቦች ላይ ርምጃ መወሰዱን የክልሉ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ገለፀ፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመሰረተ ልማት አስተባባሪና የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ መሀመድ ኑሪዬ (ዶ/ር) ከኢቢሲ ዶትስትሪም ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በተወሰደው ርምጃ 14 የአሽከርካሪዎች ማህበራት ተቀጣሪዎች መባረራቸውን ተናግረዋል፡፡

10 የስምሪት ባለሙያዎችና ሌሎች የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች የእርምት ርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ትርፍ በመጫን ተሳፋሪውን ማመናጨቅ፣ ከመንገድ ላይ ማውረድ ከመነሐሪያ ውጭ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የሚታይ ሥርዓት አልበኝነት እና የሥነ ምግባር ጉድለት መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ ይህን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ በመሆኑ ተጠቃሚው በ8934 ነጸ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ቅሬታውን እንዲያቀርብ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ርምጃ የተወሰደባቸው ሌሎች ግለሰቦች ከታሪፍ በላይ በማስከፈልና ትርፍ መጫን ላይ ተሰማርተው እንደነበርም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

ሕግ እና ሥርዓት አክብረው የሚሠሩ እንዳሉ ሁሉ ተሳፋሪውን የሚያጉላሉ በርካቶች መሆናቸውን ያወሱት ኃላፊው፣ የቁጥጥር ሥርዓቱን ዘመናዊ ለማድረግም የኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት በክልሉ በሚገኙ 10 የክላስተር ከተሞች መተግበሩን አንስተዋል፡፡

በሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ቡታጂራ – አዲስ አበባ መስመር የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች የሚያነሷቸው ከታሪፍ በላይ ማስከፈል፣ ትርፍ መጫን እና ተገልጋዩን ማንገላታት ቅሬታ መኖሩን ጠቅሰው፤ የክልሉ ትራፊኮች ቁጥጥር የላላ መሆኑ ለችግሩ መባባስ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ትራፊክ ፖሊሶች ገንዘብ እና እጅ መንሻ እየተቀበሉ ለተሳፋሪው ምንም ሳይጨነቁ መኪናውን እና አሽከርካሪውን ሳይቆጣጠሩ የሚያሳልፉበት መንገድ መኖሩን መታዘባቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

ይህን የአገልግሎት ችግር በዛላቂነት ለመፍታት በቅንጅት መሠራት እንዳለበት የገለጹት ኃላፊው፣ ማህበረሰቡን በማንቃት እና የቁጥጥር ሥርዓቱን ይበልጥ በማጠናከር ሕግ የማያከብሩትን ሥርዓት የማስያዙ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
#etv

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተጭበርበሩ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16353/

#Ethiopia | 28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርትን ጠቅሶ የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሞሽን ይፋ አደረገ፡፡

የባንኩ ሪፖርት እስከ ሰኔ 2024 ድረስ ያሉ የገንዘብ እንቅስቀሴዎች ዙሪያ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

ባንኩ በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው 28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በአጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን አጥተዋል ብሏል።

የማጭበርበር ድርጊቶቹ የተፈጸሙት በሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች፣ በተሰረቁ የኤትኤም ማሽኖች፣ በሐሰተኛ ቼኮች፣ በሐሰተኛ የስልክ መልዕክት እና ተያያዥ መንገዶች አማካኝነት ነው፡፡

በዚህ ዓመት ባንኮች ያጡት ገንዘብ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ300 ሚሊዮን ብር ጭማሪ እንዳሳየም በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ካሉ 31 ባንኮች ውስጥ 28ቱ ሲጭበረበሩ የቀሪዎቹ ሶስት ባንኮች ማንነት ግን በሪፖርቱ ላይ አልተጠቀሰም፡፡

ባንኮች ከአነስተኛ የብድር እና ቁጠባ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ብድሮችን እየሰጡ ነው የተባለ ሲሆን ይህ አገልግሎት እየጨመረ መሄድ እና የበይነ መረብ ማጭበርበሮች መበራከት ባንኮች የሚያጡት ገንዘብ ሊጨምር እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ በሪፖርቱ ላይ ጠቅሷል፡፡
(ፌ/ሥ/ፀ/ሙ/ኮ)

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚቀርበው የቡና ምርት ማሻቀቡ ለሀገር ውስጥ የሚቀርበው ቡና ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ተባለ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16355/

#Ethiopia | ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ለሀገር ውስጥ ገበያ እየቀረበ የሚገኘው የጥሬ ቡና ዋጋ እስከ አንድ ሺሕ ብር እየተሸጠ ይገኛል።

“የጥሬ ቡና የሀገር ውስጥ የመሸጫ ዋጋ በዚህ መጠን ያሻቀበበት ምክንያት ምንድን ነው?” ሲል አሐዱ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣንን ጠይቋል።

የባለስልጣኑ የገበያ እና መረጃ ደህንነት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ቸሩ ይሁን በሰጡት ምላሽ፤ የቡና ነጋዴዎች ከሀገር ውስጥ ይልቅ ለውጭ ገበያው ትኩረት መስጠታቸው ለሀገር ውስጡ ዋጋ መናር ዋነኛ ምክንያት ስለመሆኑ አንስተዋል።

“ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በኋላ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት በማደጉ እና የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት መጨመሩ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ሲውል የነበረ ቡና በዝቅተኛ ደረጃ ወደ ውጭ እየተላከ ነው” ያሉት መሪ ሥራ አስፈጻሚው፤ ይህ መሆኑ የሀገር ውስጥ ገበያው ላይ ጭማሪ እንዲፈጠር ምክንያት ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡

ቡና ላኪዎች እና የሀገር ውስጥ አምራቾች እሴት ተጨምሮበት ለውጭ ገበያ የሚቀርበው ቡና ላይ ትኩረት ማድረጋቸው፤ ሌላኛው ‘የሀገር ውስጥን ገበያ ዋጋ ጨምሮታል’ የተባለ ሰበብ ነው፡፡

ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚቀርበው የጥሬ ቡና ዋጋ በከፍተኛ መጠን መጨመሩ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እንዲያደርግ በመካከል ላይ ያሉ ደላሎችን ከግብይት ስርዓቱ የማስወጣት ሥራው ተጠናክሮ ስለመቀጡሉም አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል የቡና መዳረሻ ሀገራት በመጨመር ወደ ውጭ ሀገራት የሚላከው ኤክስፖርት ስታንዳርድ ቡና መጠን መጨመር ተጨማሪ ምክንያት ስለመሆኑ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

አክለውም በሕገ-ወጥ የቡና ርክክብ እና ንግድ ላይ ተሳትፈው በሚገኙ ነጋዴዎች ላይ ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እርምጃ እየተወሰደ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
#ahaduRadio

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ናይጄሪያ በአፍሪካ ፍጹም ድሆችን በመያዝ ቀዳሚዋ ሆናለች አለ የአለም ባንክ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16357/

#Ethiopia | ናይጄሪያ በ ቦላ ቲኑቡ ስር ከፍተኛውን የድሆች ቁጥር ማስመዝገቧን የአለም ባንክ አስታወቀ

የአለም ባንክ በሪፖርቱ እንዳስታወቀው ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት ከፍተኛውን የድሆች ቁጥር በመያዝ ከአናት የተቀመጡ ሲሆን ጥቂት ሃገራት ደግሞ ሰፊውን ድርሻ ወስደዋል ብሉዋል፡፡

ከአፍሪካ ሃገራት አንዱዋ የሆነችው ናይጄሪያ በቦላ ቲኑቡ እየተመራች 19 በመቶ ፍጹም ድሆችን በመያዝ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡

ከናይጄሪያ በመቀጠል ፍጹም ድሆችን በመያዝ ዲሞክራቲክ ኮንጎ በ14 በመቶ ስትከተል እንደ የ አለም ባንክ ሪፖርት ሃገራችን ኢትዮጵያ በ 9 በመቶ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡አራተኛውን ደረጃው ሱዳን በ 6 በመቶ ይዛለች፡፡

እንደአለም ባንክ ዘገባ በ2024 ሰራሁት ባለው ጥናት 80 በመቶ ወይንም 695 ሚሊየን ፍጹም ድሆች የሚገኙት ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት እንደሆነ የገለጸ ሲሆን የደቡብ እሲያ ሃራት 8 በመቶውን ይይዛሉ፡፡

የተቀሩት ደግሞ 2 በመቶ ሰሜን ኤዢያ እና የፓስፊክ ሃገራት 5 በመቶ ደግሞ የመካከለኛው ምስራቅና የሰሜን አፍሪካ ሃገራት እንዲሁም 3 በመቶ ላቲን አሜሪካና የካረቢያን ሃገራት ይይዛሉ ዘገባው የ ወርልድ ባንክ ነው፡፡
#ethioFm

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ሃምሳ ቴብሎች ብቻ ተዘጋጅተዋል!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16359/

አንዱ ቴብል ላይ አምስት የክብር ሰዎች ብቻ ይገኛሉ።

ቡክ የሚደረገው
በዚህ ስልክ ብቻ ነው።
0911225998

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
“ሁሉም ሰዉ እሁድን በጉጉት ይጠብቃል” አርነ ስሎት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16361/

#Ethiopia | የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ኔዘርላንዳዊዉ አርነ ስሎት ከቶተተንሀም ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል።

ስሎት ይናገራሉ “ሊቨርፑል ለመጨረሻ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ያሸነፈበት ሰአት ኮቪድ ነበር ያንን ስለምናዉቅ ሁሉም ሰዉ እሁድን በጉጉት ይጠብቃል አሁንም መስራት ያለብን ነገር አለ ቢያንስ አንድ ነጥብ ማሳካት አለብን ደጋፊዎቻችን ሁሌም ከእኛ ጋር ናቸዉ በሚችሉት ነገር ሁሉ ይደግፉናል እኛም እናዉቃለን በጉጉት የምንጠብቀዉ ጨዋታ ነዉ”

“ወደ እዚህ ሊግ የመጣሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ በዚህ የወድድር ዘመን ያጋጠመኝን ለመናገር ያህል በእኔ አስተያየት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በጣም ከባድ ሊግ ነዉ ስሎት ይቀጥላሉ በዚህ ሊግ አንድን ጨዋታ በሶስትና በአራት ጎሎች ልዮነት ማሸነፍ የሚከብደን እኛን ብቻ አይደለም ቀላል ጨዋታ አላጋጠመንም ከሁለት ሶስት አራትና አምስት አመታት በፊት ግን ቀላል ነበር”

“አርሰናል ማንችስተር ሲቲ እና እኛ አሁንም ጥሩ ቡድኖች ነን ሌሎች ቡድኖች ከእኛ የበለጠ ገንዘብ አዉጥተዋል”

በመጀመሪያ የዉድድር አመትህ ዋንጫ አሳካለሁ ብለህ አስበህ ነበር” ስሎት ሲመልሱ ብዙ ጊዜ ተናግሪያለሁ በዚህ ክለብ በር ስትሔድ የሚጠበቅብህ ዋንጫ ብቻ ነዉ ከተጫዋቾችህ ጋር በመሆን የአጨዋወት መንገድህን ለመፍጠር ትሰራለህ ግን ብዙ ለዉጦችን እንደማናደርግ እናዉቅ ነበር እሁድ እስከ ሚደርስ ጓጉተናል በማለት ስሎት ሀሳባቸዉን አጋርተዋል”

በአሁኑ ሰአት የሊቨርፑል ጎዳናዎች አሸብርቀዋል ደጋፊዎቹ የተለያዮ ባነሮችን እያዘጋጁ ነዉ አሰልጣኝ አርነ ስሎት የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳካ አሰልጣኝ ተብለዉ ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅተዋል።
#bisratRadio

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የአስረስ በቀለ 60ኛ ዓመት በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 በቀጥታ ስርጭት ሊከበር ነው

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16363/

#Ethiopia | በሀገራችን የኪነ-ጥበብ መስክ የራሱን አስተዋጾ ያበረከተው የአንጋፋው አርቲስት አስረስ በቀለ 60ኛ ዓመት የልደት በዓል ልዩ ፕሮግራም ነገ በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ከቀኑ 8 እስከ 10 ሰዓት በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል፡፡

አስቂኝ ጭብጥ ባላቸው የኮሜዲ ስራዎች እና በድርሰት ሙያ ትልቅ አሻራ ያኖረው አንጋፋው አስረስ በቀለ 60ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ከአደናቂዎቹ ከሙያ አጋሮቹ እና ከአድማጮች ጋር ልዩ ቆይታን ያደረጋል፡፡

አርቲስት አስረስ በቀለ ባለፉት 35 ዓመታት በኪነ ጥበብ እና በልጆች መፅሐፍ ደራሲነቱ የራሱን ቀለም የፈጠረው የፈጠረ በርካታ አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን አሁንም በሚወደው ሙያ እያገለገለ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የመዝናኛ ጭውውቶችን በመድረስና በመተወን ትልቅ ከበሬታን አትርፏል፡፡
በልጆች ክፍለ ጊዜ አዘጋጅነቱም ስመ ጥር ከመሆኑም በላይ ኪነ-ጥበብ ለትውልድ ግንባታ እንዲውል ከፍተኛ ሚናውን አበረክቷል፡፡

በዚህም ልዩ ልዩ ይዘት ያላቸው 16 የልጆች የተረት መፅሐፎችን በማሳተም ለትውልድ እንዲደርስም አስችሏል፡፡

በትውና፣ በድርሰት እና በመሳሰሉት ዘርፎች ከ70 በላይ ልዩ ልዩ የጥበብ ሥራዎች ላይ በመሳተፍም አድናቆትን አትርፏል፡፡
ጣቢያችን አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ሀገራቸውን በትጋት ያገለገሉ ለትውልድ አርአያ የሆኑ አንጋፋ የኪነ-ጥበብና የስነ-ጥበብ ሰዎችን ተሞክሮ እያከበሩ ለትውልድ ማስተላለፉን የቀጠለ ሲሆን የአንጋፋው አርቲስት አስረስ በቀለም ይህን ታሳቢ በማድረግ የሚከወን መርሃ -ግብር ነው፡፡

ቀደም ብሎም ፀሐፌ ተውኔት ኃይሉ ፀጋዬ የሬድዮ ድራማ ማቅረብ የጀመረበትን 40ኛ አመት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በቀጥታ ስርጭት ማክበሩ ይታወቃል፡፡

ነገ ቅዳሜ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ከቀኑ 8 እስከ 10 ሰዓት በሚኖረው መሰናዶ በአገር ውስጥና በባህር ማዶ የሚገኙ የአስረስ በቀለ ወዳጆች ምስክርነታቸውን እና መልካም ምኞታቸውን ይገልፃሉ፡፡

በተጨማሪም፣ የአስረስ አድናቂ አድማጮች በቀጥታ ስርጭት ገብተው ሐሳብ የሚሰጡ ሲሆን የአስረስ የጥበብ ሥራዎችም ላይ ቅኝት ይደረጋል፡፡

ይህ ፕሮግራም እንዲሳካ ከአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ጋር በትብብር ያዘጋጀው ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ሲሆን የሕይወት ታሪክን እና ታላላቆችን በማክበር የሚታወቅ ድርጅት ነው፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ኢትዮ ቴሌኮም ያወጣውን አክስዮን ሽያጭ 47 ሺ 377 ኢትዮጵያውያን መግዛታቸውን ይፋ አደረገ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16365/

#Ethiopia | የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የኩባንያቸውን የ10% አክሲዮን ድርሻ ሽያጭን አስመልክቶ ይፋ እንዳደረጉት:-

– 47,377 ኢትዮጵያውያን ሼር ገዝተዋል (የኢትዮቴሌኮም ባለቤት ኾነዋል)

– የሼር ብዛት 10.7 ሚልየን ነው፣

– የተሸጠው ሼር 3.2 ቢልየን ብር ነው፣
– ትንሹ አክስዮን 33 ወይንም 9ሺ 900 ብር፣
– ትልቁ አክስዮን 3ሺ 333 ወይንም 999 ሺ 900 ብር ነበር።

ዋና ሥራአስፈፃሚዋ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
***

ኢትዮ ቴሌኮም ከ47 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ባለድርሻ የሚሆኑበት ወሳኝ ታሪካዊ
ምዕራፍ ላይ በመድረሱ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል!!

መንግስት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው በርካታ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን በማድረግ ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ የጋራ እድገትን ለማረጋገጥ ከወሰዳቸው ስትራቴጂያዊ እርምጃዎች መካከል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ በማቋቋም ዜጎች በመንግስት ልማት ድርጅቶች ውስጥ የባለቤትነት መብት እንዲኖራቸው ማድረግ ሲሆን ለዚህም ያወጣቸውን የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎች ተከትሎ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ለ130 ዓመታት በትጋት ሲያገለግል የቆየው የኢትዮ ቴሌኮምን በኢትዮጵያ
የንግድ ሕግ መሠረት ከልማት ድርጅትነት ወደ አክሲዮን ማኀበርነት ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራት በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መመሪያ መሰረት ሲከናወን ቆይቷል፡፡

በዚህም መሰረት የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ሽያጭ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ በማስጀመር የአክሲዮን ሽያጩን እስከ ታኅሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ማከናወኑ ይታወሳል፡፡

በመቀጠልም ውጤቱን ለሚመለከተው የመንግስት አካል እና ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በማቅረብ እና በመገምገም በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የሽያጭ ቀነ-ገደቡን በማራዘም እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ማለትም ለ121 ቀናት (የዕረፍትና የበዓል ቀናትን ጨምሮ) በዲጂታል መንገድ ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት የተከናወነው የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ሽያጭ ውጤት በየደረጃው በሚገኙ የመንግስት አካላት ተገምግሞ እንዲሁም በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (Ethiopian Capital Market Authority) ታይቶ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

በመሆኑም በዛሬው ዕለት ኩባንያችን በመላ ሀገሪቱ የሚኖሩ ዜጎችን በማሳተፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ47 ሺህ በላይ ዜጎችን በኢትዮ ቴሌኮም ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ እንዲኖራቸው የሚያስችል ወሳኝ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ መድረሳችንን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም የባለቤትነት ድርሻ ሽያጭ በዋናነት መንግስት አካታች እና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ልማትና ዕድገትን ለማፋጠን በተለይም በርካታ ዜጎች በሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት በስፋት በማሳተፍ ጠንካራ የካፒታል ገበያ ስርዓት እንዲኖር በማቀድ የአክሲዮን ሽያጩ በዲጂታል መንገድ ፍትሃዊ፣ ግልጽ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በስፋት እና በመላ ሀገሪቱ ተግባራዊ ለማድረግ በመቻሉ የዲጂታል ማህበረሰብ በመገንባት ረገድ የበኩሉን ሚና ለመጫወት ተችሏል፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በ900 ሚሊዮን ብር የዱቤ ሽያጭ የስራ ዕድል በኢትዮጵያ ተጀመረ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16367/

#Ethiopia| ጤግሮስ ትሬዲንግ ከሊንክ አስ ትሬዲንግ እና ከቻይናው ‘ኢዩ ሸገር ካምፓኒጋር በመተባበር በኦሮሚያ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከ60 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር የዱቤ ሽያጭ ስርዓት በ900 ሚሊዮን ብር በጀት መጀመሩን አሳወቁ።

የጤግሮስ ትሬዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሐኔ ጌታቸው ኘሮጀክቱን መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት” ይህ የዱቤ ሽያጭ ስርዓት ወጣቶችን ከስራ ፍለጋ ጫና ነፃ የሚያወጣ ሲሆን ለዚህም ስራ ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደብን” ገልጸዋል።

ከቻይና ሀገር የተገኘው ይህ ዘመናዊ የስራ ልምድ በዲጂታል ኔትወርክ የተሳሰረ በመሆኑ ለአነስተኛ ንግድ ስራዎች ዕድገት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል ያሉት አቶ ብርሐኔ ጌታቸው እስካሁን በኦሮሚያ ክልል ከ3 ሺህ በላይ ወጣቶች የተመዘገቡ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር የስልጠና መርሃ ግብር ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 10 ድረስ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የሊንካስ ትሬዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፊሊሞን ካሳሁን በበኩላቸው ተቋማቸው እንደተናገሩት “በኦሮሚያ እና በሌሎች ክልሎች ለበርካታ ወጣቶች የስልጠና እድል በመስጠት የስራ ዕድል እየፈጠረ መሆኑን ገልጸው በተጨማሪም ተቋሙ ስልጠና በመስጠት ወጣቶችን ያለ ምንም የጅማሬ ካፒታል ወደ ስራው የሚያስገባ ሲሆን ድርጅቱ ራሱ ቅድሚያ ካፒታል በመስጠት ከቻይና የሚመጡ እና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶችን በመሸጥ ወጣቶች ራሳቸውን እንዲችሉ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ይህንን ፕሮጀክት ስኬታማ ለማድረግ ብርሃን ገበያ ከዳሽን ባንክ፣ ከስንቄ ባንክ፣ ከኢንሳ እና ከመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ተገልጿል።

ብርሃን ገበያ ከ ጤግሮስ ትሬዲንግ’ ጋር በመተባበር በመጀመሪያው ዙር 10 ሺህ ለሚሆኑ ስራ ፈላጊዎች የአነስተኛ ሱፐር ማርኬት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል እቅድ ይዘው እየሰሩ ሲሆን በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ ወደ ትላልቅ የገበያ ማዕከላት ባለቤትነት ለማሳደግም ራዕይ አላቸው።
.
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የቻይና አየር መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ የበረራ አገልግሎት ሊሰጡ ነው

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16369/

#Ethiopia | ሁለት የቻይና አየር መንገዶች በተያዘው የፈረንጆች 2025 መጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ የበረራ አገልግሎት ለመጀመር ማቀዳቸውን አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግሥቴ በቻይና ባለሀብቶች ባለቤትነት ከተያዙ አፍሪካን ወርልድ እና ሀይናን አየር መንገዶች የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በዚሁ ወቅት፥ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ከኢትዮ-ቻይና የትብብር መስኮቹ አንዱ መሆኑን ጠቁመው፥ በሁለቱ አገራት የአየር አገልግሎት ስምምነት መሠረት ባለሥልጣኑ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል ሲሉ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል ፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ታላቅ የክብር ቀን ሚያዚያ 17/18/19

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16371/

🚩

ማን ይቀራል በወንጌል ያልዳኑትን አዳዲስ ነፍሳት -ህሙማን -በአጋንት እስራት የተያዙትን -በተለያዩ ስቃይ ውስጥ ያሉትን ጌታ ቢፈቅድ በህይወት ብንኖር …ይዘን እንገናኝ

ከማለዳው 12:00 እስከ ከሰአት 9:30 ድረስ

መጽሐፈ ምሳሌ 15:3፤ የእግዚአብሔር ዓይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው፤
ክፉዎችንና ደጎችን ይመለከታሉ።
🕊️ 🕊️ ታላቅ የክብር ቀን 🕊️ 🕊️
ምሳሌ 15:3 “የእግዚአብሔር ዓይኖች በየስፍራው ናቸው ክፉዎችንና ደጉን ያዩ” ይላል።

እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ እንዳለ እና ሁሉንም ነገር እንደሚመለከት የኃጥአን እና የጻድቃንን ድርጊት እንደሚያይ ይህ ቃል ያጎላል

ከእግዚአብሔር እይታ የተሰወረ የሚያቅተው የማያየው ምንም ነገር እንደሌለ ይናገራል

ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እግዚአብሔር ጣልቃ ሊገባ ልናመሰግነው ከፊታችን ይህንን አዘጋጀልን

ከእግዚአብሔር እይታ የተሰወረ የሚያቅተው የማያየው ምንም ነገር እንደሌለ እነሆ
እንዲህ አለን
ኑ እፈርዳለው ኑ እዳኛለው አሜን!!

እግዚአብሔር ይህንን ቀን አዘጋጀልን
ወንጌል ይሰበካል ብዙዎች ይፈወሳሉ ነፃ ይወጣሉ
እስራቶችን ይበጠሳል የልጁ የኢየሱስ ስም ይከብራል
ብዙዎች ወደ መንግስቱ ይጨመራሉ

🚩ማንም ሰው እንዳይቀር ከማለዳው 12:00 ጀምሮ
የሚያበቃበት ሰአት ከሰአት 9:30 ይሆናል

የመንግስቱ ወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አድራሻ፡-ታክሲ ወይም አውቶቡስ ለምትይዙ

ከአራት ኪሎ ታክሲ ተራ ቤላ ታክሲ በመሳፈር ቤላ አስራ አስራ ስምንት ማዞሪያ ወደ አቦ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ዳገቱን እንደወጡ በስተግራ በኩል ያገኙናል !
Our church Address Gps
Taxi 🚖 ride|| taxi 🚕

https://maps.app.goo.gl/26Gu8Y9VFS8eCi96A?g_st=it

ለበለጠ -መረጃ
+251944723090
+251944723091
+251944723092
+251944723093

www.thegospelofkingdom.org

🚩ኑ በ4 ኪሎ ቤላ 18 ማዞሪያ ሲደርሱ ይውረዱ የመንግሥቱ ወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን

Gps location just click
https://maps.app.goo.gl/ks7RCA2krKzB9kjZ8?g_st=ic

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የሩሲያ ከፍተኛ ጄኔራል በሞስኮ አቅራቢያ በመኪና በተጠመደ ቦምብ ተገደሉ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16373/

#Ethiopia | ከሞስኮ ምስራቃዊ ክፍል በምትገኘው ባላሺካ ከተማ ውስጥ በቤት ውስጥ በተሰራ ፈንጂ በቆመ መኪና ላይ በመውደቁ አንድ የሩሲያ ከፍተኛ ጄኔራል ተገድለዋል ሲል በሀገሪቱ የሚፈጸሙ ዋና ዋና ወንጀሎችን የሚመረምረው የምርመራ ኮሚቴ አስታወቀ።

ከባድ ወንጀሎችን የሚያጣራው የሩሲያ የምርመራ ኮሚቴ የሞተውን መኮንን የ59 ዓመቱ ያሮስላቭ ሞስካሊክ የሩሲያ ጦር ሃይሎች አጠቃላይ ሰራተኛ ዋና ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ሃላፊ መሆናቸውን አሳውቋል

በተገኘው መረጃ መሰረት ፍንዳታው የተከሰተው በቤት ውስጥ በተሰራ ፈንጂ በአውዳሚ አካላት የተሞላ ፈንጂ በመፈንዳቱ ነው ሲል መርማሪ ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

መርማሪዎች አክለውም በባላሺካ ከሚገኙት አፓርታማዎች ውጭ በቆመ የቮልስዋገን ፍንዳታ ከተፈፀመ በኋላ በደረሰው አሰቃቂ ጥቃት ላይ ምርመራ እንደከፈቱ ተናግረዋል ። መግለጫው ከበስተጀርባው ማን ሊሆን እንደሚችል አልገለጸም።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
12 የኤቲኤም ካርድ ከግለሰቦች አታሎ በመውሰድ ገንዘብ የዘረፈ ተጠርጣሪ ግለሰብም መያዙ ተጠቀመ።

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16375/

#Ethiopia | በመዲናዋ በተካሄደው ኦፕሬሽን የወንጀል ድርጊት በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ መምጣቱ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን የወንጀል ድርጊት በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ መምጣቱ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ የአዲስ አበባ ከተማ አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታን ገምግመዋል።

በመድረኩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዦችና የወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በሁሉም ክፍለ-ከተሞች በተካሄደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በተሽከርካሪ ስርቆት፣ በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር፣ በሀሰተኛ የብር ኖቶች ዝውውር፣ በሞባይልና ላፕቶፕ ኮምፒዩተሮች እና ሌሎች ንብረቶች ስርቆት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ቴክኖሎጂን ተጠቅመው የተሰረቁ ሞባይሎች እንዳይገኙ የሚያደርጉ፣ በሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ተጠቅመው ዝርፊያ የሚፈፀሙ እና በርካታ የሺሻ ማስጨሻ ዕቃዎችን ይዘው የተገኙ ከነ-ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።

በተለይም በቂርቆስና በቦሌ ክ/ከተሞች በቅንጅት በተካሄደ ልዩ ኦፕሬሽን ተደራጅተው በመንግስት መሠረተ ልማቶች ላይ ዝርፊያ የፈፀሙና በሞተር ሳይክል ሞባይል የሚነጥቁ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነግሯል።

12 የኤቲኤም ካርድ ከግለሰቦች አታሎ በመውሰድ ገንዘብ የዘረፈ ተጠርጣሪ ግለሰብም መያዙ ተጠቁሟል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸዉ በምርመራ እየተጣራ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ፤ በተካሄደው ኦፕሬሽን የከተማዋ ሰላምና ደኅንነት አስተማማኝ መሆኑንና ወንጀልም በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ መምጣቱ መገምገሙን አመልክቷል።

የከተማዋን ፀጥታ እና ደኅንነት የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተደረገ ባለው የተቀናጀ ኦፕሬሽን የፀጥታ አካላት ቅንጅታዊ አሠራር እና የማድረግ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ማደጉ ተነግሯል።

የጋራ ኦፕሬሽኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በኦፕሬሽኑ የተገኘው ውጤትም እየተገመገሙ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረጉ በግምግማው ላይ ተነስቷል።

==
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክ ቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet