Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
6.07K subscribers
2 photos
4.6K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
” ዣቪ አሎንሶ ከተጫወተባቸው ክለቦች ጋር መደራደር የሚያስችለው ቅድመ ስምምነት አለን” የባየር ሊቨርኩሰን ዋና ስራ አስፈጻሚ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16081/

#Ethiopia | ሪያል ማድሪድ ከአሰልጣኙ ካርሎ አንቸሎቲ ጋር በውድድር አመቱ መጨረሻ መለያየቱ አይቀሬ ይመስላል። ማሪንጌዎቹ አንጋፋውን አሰልጣኝ ለመተካት ቀዳሚ ምርጫቸው የቀድሞ ኮከብ ተጫዎቻቸው ዣቪ አሎንሶ እንደሆነ ተደጋግሞ ተነግሯል። አሁን በቡንደስሊጋው ባየር ሊቨርኩሰንን እያሰለጠነ የሚገኘው የቀድሞው አማካኝ ባለፈው አመት ያሳየውን ብቃት ባይደግምም ወደ ሀገሩ ሊመለስ በዝግጅት ላይ ነው።

ጉዳዩን አስመልክቶ የተጠየቁት የሊቨርኩሰኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፈርናንዶ ካሮ አሎንሶ ተጫውቶ ካለፈባቸው ክለቦች ጋር መደራደር ከፈለገ የማይከለከልበት የጋራ ስምምነት መኖሩን አስታውሰዋል። አሎንሶ በሪያል ሶሲየዳድ ፣ ሊቨርፑል ፣ ሪያል ማድሪድና ባየር ሙኒክ ተጫውቶ አሳልፏል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ክለባችን በቀጣይ አመት አሎንሶን ይፈልገዋል ግን ማድሪድ አሰልጣኙን ሊሸኝ ስለተዘጋጀ ከአሎንሶ ላይ አይኑን እንዳሳረፈ እናውቃለን በስምምነታችን መሰረትም መነጋገር ይችላሉ ብለዋል። እነዚህ ክለቦች ከፈለጉት ቁጭ ብለን መነጋገር እንጂ በጉዞው ላይ እንቅፋት አንሆንም ብለው ስምምነታቸውን እንደሚያከብሩ አስረግጠዋል።

ከ4ቱ የቀድም ክለቦቹ አሎንሶን ፈልጎ የሊቨርኩሰንን በር የሚያንኳኳ ከመጣ የጀርመኑ ክለብ ለመልቀቅ ዝግጁ ነው። ሊቨርፑል በአርነ ስሎት ስር የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ጫፍ የደረሰ ፣ ባየር ሙኒክም በቪንሶን ኮምፓኒ የድሉ ጫፍ በመቆማቸው አሎንሶን ይፈልጋሉ ተብሎ አይጠበቅም። ሪያል ማድሪድ ብቸኛ ፈላጊው መሆኑ እርግጥ ነው።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ፈርናንዶ ካኖ ከስፔኑ ሀያል ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላቸውም ተናግረዋል።

በሁሴን ግዛው

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በኢትዮጵያ በበይነ መረብ አማካኝነት መረጃን ከሚያስተላለፉት መካከል 65 ያህሉ ህጋዊ ፈቃድ እንዳገኙ ተነገረ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16083/

#Ethiopia | በዚህም በኢትዮጵያ ፈቃድ ያላቸው የመገናኛ ብዙኃን አጠቃላይ ብዛት 292 እንደደረሱ ሰምተናል፡፡

የመገናኛ ብዙኃኑ የሚመዘገቡበት ዘርፍም ወደ አስር አድጓል ተብሏል፡፡

ከእነዚህ ዘርፎችም፣ የህዝብ፣ የማህበረሰብ፣ የሀይማኖት፣ የንግድ፣ የበይነ መረብ፣ የክፍያ(እንደ ዲኤስ ቲቪ ያሉ) እና የትምህርት የመገናኛ ብዙሃን እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተከትለው እየመጡ ያሉ የመገናኛ ብዙሀን ዘርፎችን ወደ አሰራሬ አስገብቼ ለመመዝገብ እየበረታሁ ነው ብሏል፡፡

በአሁን ሰዓት በሀገሪቱ 236 በስርጭት ላይ እንዲሁም 56 ፍቃድ ወስደው በዝግጅት ላይ ያሉትን ጨምሮ በድምሩ 292 በባለስልጣኑ የተመዘገቡ የመገናኛ ብዙሃን እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ 65ቱ በበይነ መረብ በመደበኛነት የሚድያን ስራ ለመስራት የተመዘገቡ ናቸው ተብሏል፡፡

ይህንን ለሸገር ራዲዮ የተናገሩት በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለልጣን የመገናኛ ብዙሀን ፈቃድ ምዝገባና እውቅና ዴስክ ሀላፊ ደሴ ከፋለ ናቸው፡፡

በተለይም ዘመኑ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እያመጣ ስለሆነም እነዚህን ታክከው የሚመጡ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፎችንም በፈቃድ ስርዓት ለማካተት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል፤ ኦቨር ዘ ቶፕ #OTT ወይም በኢንተርኔት አማካኝነት የተጫኑ ይዘቶችን ማንኛውም ሰው በፈለገው ሰዓት ማግኘት የሚችልባቸው፤ እንዲሁም ኢንተራክቲቭ ቮይስ ሪስፖንስ #IVR የሞባይል ኔትዎርክን በመጠቀም በሬድዮ እንደሚሰራጩትንና መሰል ይዘቶችን በአጭር ቁጥር ደውሎ ማድመጥ የሚያስችሉ ዘመንኛ መላዎችን እንደምሳሌነት ተጠቅሰዋል፡፡
#shegerFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የፋሲካ በዓልን ምክንያት አድርገው ለጤና ጠንቅ የሆኑ የምግብ ምርቶችን ይዘው የተገኙ 14 ተቋማት መታሸጋቸው ተሰማ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16085/

#Ethiopia | ለገበያ ቀርበው ነበር ከተባሉት ምርቶች መካከል የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ይገኙበታል፡፡

የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ከወንኩት ባለው የቁጥጥር ስራ ለበዓሉ ሊኖር የሚችለውን የማህበረሰቡን የመሸመት ፍላጎት ባልተገባ መንገድ ሲጠቀሙ ያገኋቸውን 14 ተቋማት አሽጊያቸዋለሁ ብሎናል፡፡

ተቋማቱም የምግብ ዘይት ማምረቻዎች፣ የ #ባልትና ውጤት መሸጫዎችና ወፍጮ ቤቶች መሆናቸውን የነገሩን በአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወ/ሮ ወርቅነሽ ብርቄ ናቸው፡፡

በክትትሉ የተገኙት የምግብ ምርቶች ምን አይነት የጤና እክል ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ ምርመራ እየተደረገበት ነው፤የላብራቶሪ ውጤቱ ታይቶ ተጨማሪ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

በዓሉን ተከትሎ ሊኖር የሚችልን የምርትና ሽያጭ ወቅት ችግር ለመቆጣጠር በተደረገው ክትትል የተፈተሹት 2500 ተቋማት ናቸው ያሉን ሃላፊዋ ከእነዚህ ውስጥ 14 ታሽገዋል፤ 82ቱ በፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ታልፈዋል፤ ቀሪዎቹ እንከል እንዳልተገኘባቸው ጠቅሰዋል፡፡

የታሸጉት የምግብ ዘይት ፋብሪካዎች፣ ባልትና መሸጫዎችና ወፍጮ ቤቶች ወደ ቀደመ ስራቸው ለመመለስ የተገኘባቸውን ችግር ማስተካከላቸውን ለባለስልጣኑ ያሳውቃሉ፤ተቆጣጣሪው ባለስልጣንም ችግሩ መስተካከሉን ሲያረጋግጥ እንዲከፍቱ ይፈቅድላቸዋል ብለውናል ወ/ሮ ወርቅነሽ፡፡

በተጨማሪም በቁጥጥር ስራው ከ2መቶ ሺህ ብር በላይ ዋጋቸው የተገመተ ምግብና መጠጦችን ባለስልጣኑ የማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ ናቸው ሲል ከገበያ ሰብስቦ ማስወገዱንም ከሃላፊዋ ሰምተናል፡፡
#Tikvah

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ማስተዋል በማስተዋል አልበም ሲሰራ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16087/

(በተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ)

#Ethiopia | በማስተዋል የሚደመጥ አልበም በየዘመኑ እንዲህ አይነት ክስተት ዘፋኞች ብቅ ይላሉ በሙዚቃ መንገድ ታሽቶ የመጣ እንዲህ ያለ የሚስብ አቅም ያደርሰናል፡፡ ማስተዋል እያዩ ያበት ደረጃ ሌላ የሱ ሙዚቃ ዓለም አለው፡ በትዝታ በሀሳብ ላቅ ያለ የማስተዋል የድምፅ እርከን ስፋት ፣ ቀለም ፣ ሬንጅ ፣ የቅኝት ባለቤት ጉሮሮው እንደ ፈለገ የሚተታጠፍ የመሳሰሉት ያየንበት ነው፡፡

አንድ ወዳጄ የፋና ላምሮት ፈርጥ ድምፃዊ ናሆም ነጋሽ ስለዚህ አልበም ስናወራ እንዲህ አለኝ ” ወይን እያደር አይደል የሚጣፍጠው ይህ አልበም እንዲያ ነው ደሞ ከ ጣፈጠ በኃላ ደረጃውም ቦታውም ይልቃል”አለኝ፡፡ ልክ ነው ከልብ ማድመጥ ጆሮ የሚሻ ሙዚቃ እና በአዕምሮዬ ሲዘዋወር የነበረውን ሐሳብ በሙሉ ቋንቋ ገልፆልኛል፡፡

ጠቅላላ ሙዚቃዎች ሲሰሩ በስሜታቸው እና በስልተ ምቱ በአግባቡ መግለፅ ያስፈልጋል ምክንያቱም የሙዚቃ ነፍሱ እሱ ስለ ሆነ ፡፡በነጠላ ሙዚቃዎቹ እና Ep ሙዚቃዎቹ አቅም እና ችሎታውን በሚገባ አሳይቶን ወደ አልበሙ ተከስቶ ታዕምራዊ አልበም ሰቶናል፡፡

‘እዚራ’ አልበም እዚራ አንድ ኢትዮጲያዊ የሆነ የሙዚቃ መሳርያ ነው፡፡ በዚህ ስያሜ መምጣቱ አልበሙን በብዙ መንገድ እንዳስበው አርጎኛል፡፡ በሙዚቃዎቹ ውስጥ ተወዳጁን ማዲንጎ አፈወርቅን እንድናስታውስ የሚደርገን ብሎም አብዛኛው በዜማ የሰራው እራሱ ማስተዋል ሲሆን ይህ ሌላኛው የማዳመጥ ክህሎት የመጣበት የሙዚቃ ደረጃ ምን ያህል እንደሆነ ይነገርናል፡፡የሙዚቃ ቫራይቲ(የተለያየ አይነት ስልት እና ሐሳብ ) ሬጌ ፣ ሱዳኒክ ፣ ትዝታ፣ ፎክ (ባህላዊ የሙዚቃ አዛዝያም)፣የቅኝትሙዚቃዎች ተሰርተዋል፡፡14 የሙዚቃ ክሮች ሲኖሩት ደጉ ትዝታ ፣ መጥቼ ነበር ፣ በምን ቃል፣ ደግሰን ፣ ከፋኝ ፣ እንዚራ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

ከአልበሙ የገረመኝ እና የወደድኳቸው የሙዚቃ ስራዎች ከአብዛኛው ጥቂቱን ልገልፅላችሁ፡፡

“ከፋኝ” (ትዝታ) የተሰኘ ሙዚቃ ሐሳብ የግጥም ውህደቱ ለዚህ ዓለም ጉዞ በሰውኛ አገላለፅ ሌላው መንገድ ሰውኛ እውነትን ሆኖ እዉነትነትን ሳይስት ይናገናል፡፡ በመከፍት በህመም መደራረብ ውስጥ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮች አሉ አብረን የኖርነው መልክ እያየነው ሲጠወልግ ዛሬ ላይ ያሉ ትናንትናዋን ያላወቁ ሰዎች በመልኳ ሲሳለቁ እሱ ግን ቆም ብሎ ትናንት አውቃታለሁ ለዚህ እንኳን ገላጋይ ዳኛ አያስፈልግም እኔ ምስክር ነኝ በምንም በሁሉም የትማርክ ነበረች ጊዜ ጥሏት እንጂ፡፡ግጥም ጥላሁን ሰማው ዜማ አበበ ብርሀኔ ቅንብር ታምሩ አማረ(ቶሚ)

“የማለዳው ለምለም- ውበቷ ቄጤማው
ጠውልጎ አየሁ ዛሬ – ሲፈርድ እድሜ ዳኛው
አወይ ዘመን – ባዳ አቤት ጊዜ ክፉ
ለምልክት እንኳን – አንድ አለ ማትረፉ”…

“(እቴ)” (ሞደርን ፎክ) ባህል ዘመናዊ የተሰኘው ሙዚቃ ቅንብሩ የዘጠዎቹ /ሰባዎቹ ሙዚቃ ቅርፅ እንድናስታውስ ያደርገናል የሙዚቃ ቅንብሮቹ በምክንያት የተሰሩ የማስተዋል የድምፅ እርከን ስፋት በሚገባው የድምፅ ጉልበት የተጠቀመበት ድንቅ ሙዚቃ ፅዱ ማንነት ገለጣ፡፡ ዜማ ምረት አብ ደስታ ግጥም ናትናኤል ግርማቸው ቅንብር ሚካኤል ሀይሉ(ሚኪ ጃኖ)::

“የቆንጆ ፍቅር – እና- ትንታ ያለበት
ሞት ቅርቡ ነው- እና- ውሀ አታርቁበት
ችዬው ልኑር እንጂ – ስራበው ወይ ስጠማሽ
መቼም ሰው አይድንም – ከሐመልማሎ ገላሽ”

“ጉብልዬ(ቅኝት)” የነፀብራቅ ድምፅ የሙዚቃ ጉልበቱ የታየበት የመጀመርያ ቅኝትን መቆጣጠር ፣ ሁለተኛው የእተቀባበሉ መዝፈን ፈተናው እና የውበት ፍሰቱን በመግለፅ ብዙ ነገሩ ስኬታማ አጫዋች ሆኖ ያየንበት ነው፡፡ሐሳቡ ትዝታን ወደ ኃላ እየቃኘ ስለ አንድ ሰው እሱ በሌለበት ወዳጆቹ ሲነጋገሩ ሲጨዋወቱ፡፡ ግጥም ናትናኤል ግርማቸው ዜማ የህዝብ እና መስተዋል እ ቅንብር ሚካኤል ሀይሉ፡፡

”አጋርሽ መሆኑን ሰምቼ ፣ ያ የጥንት ወዳጅሽ ወዳጄ
እቴ ሙች ግራ ነው የገባኝ ፣ ሕይወት እንቆቅልሽ ሆኖ ባይ
እስኪ ግለጪልኝ ይሄን ነገር ፣ ያ ሰው የዛን ጊዜ ምንሽ ነበር”::

“እመጣለሁ” የፍቅር ትርጉም አንዱ አገላለፅ ይህንን አሳብ የተሸከመ ነው፡፡የግጥሙ ሐሳብ የምትወደው ሰው ህመምን መዋዋስ ሳይሆን እመምን ብቻህን መጋፈጥ ለምትጋፈጥበለት ሰው ደስታውን ሁሉ መመልከት ምክንያቱም ፍቅር በስቃይ ይጣፋል እና…ግጥም እና ዜማ አቡዲ ቅንብር ሚካኤል ሀይሉ፡፡

ከጀርባሽም ብሆንም – እንደ ዓይንሽ ልይልሽ
እንቅፋት ሲያይብኝ – እኔ እንድመታልሽ
————
እኔ አንቺን – ስለምወድ ስለምወድ
እመጣለሁ ሂጂ እና – በአንቺ መንገድ

እነዚህ እና የመሳሰሉት ጣዕም ያላቸው ሙዚቃዎች ሰቶናል፡፡ነፍስ እንዲዘራ ደግሞ የሙዚቃ ከያኒያን በዚህ ልክ አጥብቀው ሙዚቃ የሚፈልገውን ስሜት ሰተውታል በቅንብር ብሩክ አፈርቅ ፣ ሚካኤል ሀይሉ(ሚኪ ጃኖ) ፣ ታምሩ አማረ(ቶሚ) በጥግም ዜማ ናትናኤል ግርማቸው ፣ ፍሬዘር አበበ ወርቅ ፣ ማስተዋል እያዩ ፣ አብዲ ፣ጥላሁን ሰማሁ ፣ ታመነ መኮንን ፣ ብሬ ብራይት ፣ እሱባለሁ ይታየሁ( የሺ )፣ አበበ ብርሀኔ ፣ ቢኒያምር አህመድ ፣ አንባቸው እሸቱ፣ ምረት አብ ደስታ ማስተሪንግ ሰለሞን ሀይለማርያም የመሳሰሉ ሰርተውታል፡፡

በዚህ አልበም ላይ እጃችሁ ያሳረፋችሁ ሁሉ በግሌ አመሰግናለሁ
የሙዚቃ ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪዩሪቲስ የመጀመሪያውን የባለአክሲዮኖች ጉባኤ አካሄደ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16089/

#Ethiopia |ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪዩሪቲስ አ.ማ የመጀመሪያውን የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄዱን ዛሬ ይፋ አደረገ። ኩባንያው በዚህ ጉባኤ ላይ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሴኪዩሪቲስ ዲለር (የመዋለ ንዋዮች ገበያ ሰነድ አከናዋኝ) ፈቃድ ማግኘቱንና በቀጣይ አገልግሎት በመስጠት ወደ ትርፋማነት ለመሸጋገር ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

የኩባንያው የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበባው ዘውዴ እንደገለጹት፣ ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪዩሪቲስ በ50 ሚሊዮን ብር የተፈረመ ካፒታልና ከ14.2 ሚሊዮን ብር በላይ በተከፈለ ካፒታል የተመሠረተ ነው። መስራቾቹም በፋይናንስው ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸውና በተለያዩ የባንክ፣ የኢንሹራንስና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የሰሩ እንዲሁም በርካታ ተቋማትን የመሰረቱና በቦርድ አመራርነትም ልምድ ያላቸው 40 ባለአክሲዮኖች ናቸው።

አቶ አበባው አክለውም የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለሴኪዩሪቲስ ዲለርነት የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የካፒታል መጠን 10 ሚሊዮን ብር ቢሆንም፣ ኢትዮ ፊደሊቲ ከዚህ መጠን በላይ በማስመዝገብ ገበያውን መቀላቀሉ የኩባንያውን የፋይናንስ አቅምና ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

ኩባንያው በአዲሱ የካፒታል ገበያ ውስጥ ግንባር ቀደም ተዋናይ ለመሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁንና የባለሥልጣኑን ሕግና መመሪያዎች በመከተል ሙያዊ ሥነ ምግባርን በጠበቀ መልኩ የግብይት ሥርዓቱን ለማሳለጥ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።

በተጨማሪም ኩባንያው የአገልግሎት ተደራሽነቱን በመላ አገሪቱ ለማስፋፋትና ይበልጥ የተቀላጠፈ ለማድረግ ከተለያዩ የግል ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር የቅድመ መግባቢያ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቋል። የደንበኞችን ምዝገባና የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥርዓት ለመዘርጋትም እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል።

በቀጣይነት በካፒታል ገበያው ውስጥ ሊሰጡ የሚችሉ አዋጭ የሆኑ የአገልግሎት ዓይነቶች በዝርዝር ተለይተው ለባለአክሲዮኖች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። የኩባንያው ቦርድ የአይቲና የስትራቴጂ ንዑስ ኮሚቴዎችን በማቋቋም የአመራር ቡድኑን ለመምራትና ለመደገፍ የሶስት ዓመታት ስትራቴጂክ ዕቅድ በመንደፍ ላይ ይገኛል።

ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪዩሪቲስ ቀደም ሲል የነበረውን የአክሲዮን ግብይት ሂደት ጠንቅቆ እንደሚያውቅ በመግለጽ፣ አዲሱ የካፒታል ገበያ ለሁሉም ተሳታፊዎችና ተጠቃሚዎች እኩል ዕድል የሚፈጥር እንደሚሆን ገልጸዋል ። ኩባንያው ከመረጃ አቅርቦት ጀምሮ ገበያው እንዲዳብር ከባለሥልጣኑና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል።

አዲሱ የካፒታል ገበያ ለነባርና ለሚቋቋሙ ኩባንያዎች ምቹ የገበያ አማራጭ በመሆኑ ግንዛቤን መፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት መሆኑን ኩባንያው አፅንኦት ሰጥቷል። በተጨማሪም ወደፊት ቦንድና ሌሎች የፋይናንስ ሰነዶች በገበያው ላይ ሲቀርቡ ለዘርፉ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክቷል።

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
መጪውን የ ፋሲካ በዓል አስሞልክቶ ከ 2,000,000 ብር በላይ ቅናሽ ይጠቀሙ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16091/

ይህ የምስራች ለውድ ደንበኞቻችን ስናቀርብ በታላቅ ደስታ ነው::

📌📌 በ ቁጥር 3ሳይት በሳርስ ዓደይ አበባ B+G+7
የሆነው ህንፃችን ላይ ከረጅም አከፋፈል ጋር እንጠብቆታለን!
ያስተውሉ ብልሆች የ እድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ለውስን ቤቶች ብቻ የቀረበ ዕድል ሞሆኑ ይገንዘቡ!

‘አልቲማ ሪል እስቴት’

“ህልምዎን ይኑሩ!”

“Live Your Dreams!”

ለበለጠ መረጃ :-. ☎️0996000000 / 0995222222

➡️Website: http://www.ultimaet.com

➡️Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61568957484689

➡️Whatsapp: https://whatsapp.com/channel/0029VawOxno545uoGPoLfH3X

➡️Telegram: https://t.me/ultimarealestate1

➡️YouTube: https://www.youtube.com/@UltimaRealestate

➡️ TikTok: tiktok.com/@ultimareal.estate

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የፖፕ ፍራንሲስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በመጪው ቅዳሜ ይፈፀማል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16093/

#Ethiopia | የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በመጪው ቅዳሜ እንደሚከናወን ተገለፀ፡፡

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በትናንትናው ዕለት በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ቫቲካን ማስታወቋ ይታወሳል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት የሚፈጸምበትን ቀን ለመወሰን ካርዲናሎች በዛሬው ዕለት በቫቲካን መምከራቸውም ተገልጿል።

በካርዲናሎች ውሳኔ መሰረት ቫቲካን የፖፕ ፍራንሲስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በመጪው ቅዳሜ እንደሚፈፀም ማስታወቋን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ህልፈት ተከትሎ ቤተ ክርስቲያኗ በቀጣዮቹ ሶስት ሳምንታት ውስጥ አዲስ መሪ እንደምትመርጥ ተገልጿል።

የፖፕ ፍራንሲስ ህልፈት ከተሰማ በኋላ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሃይማኖት መሪዎች፣ የአገር መሪዎች እና ታዋቂ ሰዎች ሐዘናቸውን እና አክብሮታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ጊፍት ሪል ስቴት ከደንበኞች በቀረበልን ጥያቄ ከሚያዚያ 23-26/2017 ዓ.ም. የሚቆይ ታላቅ የሽያጭ መርሃ ግብር ዳግም አዘጋጅተናል።

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16095/

በዚህ መርሃ ግብር ላይ በለገሃር፣ በተክለ ሀይማኖት፣ በ22 ማዞሪያ፣ በሲኤምሲ እና ሌሎች አፓርትመንቶችና የንግድ ሱቆች ቅናሽ ተደርጎባቸው ለሽያጭ ይቀርባሉ፡፡

እርስዎም በዚህ የሽያጭ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ፤ የቤት ባለቤት እንዲሆን በክብር ተጋብዘዋል።

መኖር በጊፍት መንደር።

ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ዛሬ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን ነው!!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16097/

የእናንት ምርጡ መጽሐፍ የትኛው ነው?

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ላይ ያነጣጠር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከሸፈ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16099/

#Ethiopia | የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው በርካታ ወታደራዊ አባላትን ያሳተፈ እንደነበር የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና አስታውቀዋል።

የሀገሪቱ የደህንነት አገልግሎት ተቋማት የሴራው አካል በሆኑ የቡርኪናቢ ወታደሮች እና የታጣቂ ቡድን መሪዎች መካከል የነበረውን ግንኙነት በመጥለፍ የሚገኙበትን ቦታ እና የወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ዝርዝር ሁኔታ እንዳገኙ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ላይ የተሴረው መፈንቅለ መንግሥት በመጀመሪያ ሚያዝያ 8 ቀን ለማካሄድ ታቅዶ እንደነበር ሚኒስትሩ ተናግረዋል ።
#ethioFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የብልት ፈንገስ ኢንፌክሽን በግብረስጋ ግንኙነት ብቻ የሚመጣ አለመሆኑ ተገለፀ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16101/

#Ethiopia | የብልት ፈንገስ ኢንፌክሽን በበርካታ ሴቶች ላይ የሚታይ ችግር ሲሆን በዋናነት ይህ ኢንፌክሽን የሚከሰተው በብልት አካባቢ በአነስተኛ መጠን የሚገኙ ፈንገሶች በብዛት ሲራቡ ነው። በመሆኑም የብልት ማሳከክ በተለይ በሴቶች ላይ በብዛት የሚከሰት ችግር ሲሆን ካልታከሙ ምቾት ከመንሳቱ ባሻገር ለጤና አሳሳቢ ሊሆን ይችላል ሲሉ በማሪስቶፕ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ሀኪም የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ዶ/ር ዘነበ ሹምዬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ይህ የኢንፌክሽን አይነት የሴት ልጅ የውጪኛው መራቢያ አካል ላይ የሚከሰት መታከም የሚችል በሽታ ሲሆን ብዙ ሴቶች በግንዛቤ እጥረት ምክንያት ህክምና ሳያገኙ ይቀራሉ። ኢንፌክሽኑ እንዲከሰት ምክንያት የሚሆነው ፈንገስ ሳንዲዱ አልቤኒካ ተብሎ ይጠራል። በመሆኑም በሴት ልጅ ብልት ውስጥ የተለያዩ ባክቴሪያዎች እና ፈንገሶች የሚኖሩ ሲሆን እነዚህን ባክቴሪያና ፈንገሶች በሚፈለጉት መጠን እስከተገኙ ድረስ የሚጠቅሙ እንጂ ለጉዳት የሚያጋልጡ አይደሉም ሲሉ ገልፀዋል::

የብልት ፈንገስ ኢንፌክሽን በበርካታ ሴቶች ላይ የሚስተዋል በመሆኑ ምልክቶቹም ከፍተኛ የብልት አካባቢ ማሳከክ ፣ ነጭና ወፍራም ፈሳሽ መኖር ፣ ውሃ ሽንት ሲሸኑ ማቃጠል፣ የብልት አካባቢ መቅላት እና መላጥ ናቸው። እንደዚህ አይነት ምልክቶች ሲታዩ በግብረ ስጋ ግንኙነት ብቻ ነው የሚፈጠሩት እና የሚተላለፋት ተብሎ በስህተት በማህበረሰብ ውስጥ የመረዳት ችግር እንዳለም ገልፀዋል።

አንቲባዮቲክ በብዛት መጠቀም በብልት ውስጥ ያሉ ጤናማ ባክቴሪያዎች እንዲሞቱ ምክንያት ሊሆን ይችላል።ይህም በብልት ውስጥ ያሉ ፈንገሶች ከተገቢው መጠን በላይ ተራብተው ለኢንፌክሽን መከሰት ምክንያት እንዲሆኑ መንገድ ይከፍታል። የኢስትሮጂን ሆርሞን መጠናቸው ከፍ ያለ ሴቶች ለብልት ኢንፌክሽን ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ ነው። በዚህም ምክንያት ነፍሰ ጡር ሴቶች እና የኢስትሮጂን መጠኑ ከፍ ያለ የወሊድ መከላከያ የሚወስዱ ሴቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይመከራል ብለዋል።

በተጨማሪም ብልትን ለመታጠብ የሚውሉ የተለያዩ ኬሚካሎችን አለመጠቀም ፣አላስፈላጊ አንቲባዮቲኮችን ከመውሰድ መቆጠብ አስፈላጊ መሆኑን አክለው ተገቢውን ህክምና ካደረጉ ቢታከም ሊድን የሚችል መሆኑን ዶ/ር ዘነበ ሹምዬ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
“በኢትዮያ ከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተከስቷል” – የዓለም ምግብ ፕሮግራም

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16103/

#Ethiopia | በኢትዮጵያ በድምሩ 10 ሚሊዮን ህዝብ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድጋፎች በመቀነሳቸው 650,000 ለሚሆኑ እናቶች እና ህጻናት ሲያቀርበው የነበረውን ድጋፍ ማቋጡን ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት 4.4 ሚሊዮን ነፍሰ ጡር እናቶች የተመጣጠነ ምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው በኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዝላታን ሚሊሲች ተናግረዋል፡፡

ሚሊሲች በጄኔቫ በነበረው ውይይት ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ ችግሩ በሶማሊያ፣ አፋር፣ ትግራይና ኦሮሚያ ክልሎች በተለየ መልኩ መንሰራፋቱን ገልጸዋል፡፡ #anadoluagency
#Thiqah
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ትራምፕ ወደ መካከለኛው ምስራቅ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16105/

#Ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ወር ወደ መካከለኛው ምስርቅ ብቅ ሊሉ ነው ተባለ፡፡

ሪፐብሊካኑ ትራምፕ ሳውዲ አረቢያን፣ ኳታርን እና አረብ ኤሚሬቶችን ግንቢት ላይ ይጎበኛሉ፡፡

ወደ ቀጠናው ከፈረንጆቹ ግንቦት 13 እስከ 16 ሲመጡ በርካታ ጉዳዮችን ግምት ውስጥ አስገብተው ነው ተብሏል፡፡

በመጀመሪያው ዙር የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ትተውት የሄዱትን የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ በአሁኑ ጉብኝታቸው እንደማያገኙትም ተነግሯል፡፡

ኢራን እና ሳውዲ አረቢያ በቻይና አማካኝነት መታረቃቸው እንዲሁም እስራኤል እና ሃማስ የገቡበት ጦርነት እንግዳ ጉዳይ ይሆንባቸዋል ተብሏል፡፡

የሚጓዙት ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማምጣት ነው የተባለ ሲሆን እስከዛው ግን ከኢራን ጋር ያለው ውጥረት ወይ ይረግባል አሊያም ይለይለታል የሚል መረጃ ወቷል፡፡
በየመን ከሁቲዎች ጋር ያለው ውጥረትም አብሮ ፖለቲካዊ ግምት ውስጥ የሚገባ ጉዳይ ነው ብሏል የፕሬዚዳንቱ ቢሮ ዖቫል ኦፊስ፡፡

ፕሬዚዳንቱ እስከዛው የጋዛውን ጦርነት መቋጨት ካልቻሉም በመካከለኛው ምስራቅ መልካም አቀባበል አይጠብቃቸውም እየተባለ ነው።

የዶናልድ ትራምፕ ጉዞ ከፍተኛ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ትርጓሜ እንደሚኖረው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
#Nbc Ethiopia
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ኢትዮጵያ በአፋጣኝ የራሰዋን የንግድ ሰርአት ፖሊሲ በማሻሻል አሜሪካ ካወጣችዉ አለም አቀፍ ፖሊሲ ጋር እንዲጣጣም ማድረግ እንደሚገባት ተጠቆመ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16107/

#Ethiopia | በቅርቡ አሜሪካ ባስተላለፈችው የታሪፍ ማሻሻያ መሰረት ኢትዮጵያ ምን አይነት ስራዎች ይጠበቁባታል የሚለዉን መናኸሪያ ሬዲዮ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችን አነጋግሯል፡፡

ኢትዮጵያ ላይ የንግድ ታሪፉ ተፅዕኖ ከመፍጠሩ በፊት ሌሎች አማራጭ የገበያ መዳረሻዎችን ማስፋት እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የንግድ ስርዓትን ማሳደግ ላይ ልትሰራ ይገባል ሲሉ የገለፁት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር ሞላ አለማየሁ ናቸው፡፡

እንዲሁም መሰል አሁን ላይ የተጣለውን የታሪፍ ጭማሪም ሆነ ከዚህ በኋላ የሚጣሉ ታሪፎችን ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ፖሊሲ በማውጣት እንዲሁም የመፍትሄ ሃሳቦችን በማምጣት በኩል ቀድሞ መስራት አስፈላጊ ነው ሲሉ ሃሳባቸውን ገልፀዋል፡፡

ሌላኛው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በረኸተስፋ እንዳነሱት ሀገሪትዋ ያላትን ምርቶች ለውጪ ገበያ የሚያቀርቡ ላኪዎችን በማበረታት ብሎም እሴት እየጨመሩ እንዲልኩ በማድረግ በውጭ ገበያ ላይ ተፈላጊነታቸዉ እንዲጨመር ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ከውጪ የምናስገባቸው ምርቶችን ለመቀነስ ለአምራች ኢንደስተሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

ባለሙያዎቹ የንግድ ማህበረስቡ ከመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ወቅቱ የሚጠይቀዉን አይነት ማሻሺያ ማድረግ እንደሚገባቸዉ ጠቁመዋል፡፡
#MenahriaFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የቤት ካርታ ከሌለህ ሲም ካርድ አይኖርህም

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16109/

(ይህ ህግ ነው!)

#Ethiopia | ሞባይል ስልክ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ አገልግሎቱን ለማግኘት ያስፈልጉ የነበሩት አስገራሚ መስፈርቶች

ግንቦት 9 1991 ዓ.ም ፡ ቴሌ. ለወራት ሲያስተዋውቅ የከረመውን የሞባይል ስልክ አገልግሎት መስጠት የሚጀምርበት ቀን ነበር

እና በዚያን እለት ግንዛቤው የነበራቸው ባለሃብቶች ለ ኢትዮጵያ አዲስ የሆነውን ሞባይል ስልክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ወደ ቴሌ ቢሮዎች በጠዋት መምጣት ጀምረዋል ።

በቢሮው መግቢያ ላይ አንድ ማስታወቂያ ተለጥፎአል .. .. ሲም ካርድ ለመውሰድ ሲመጡ ኦሪጅናል እና ኮፒ የመኖሪያ ቤት ካርታ .. ይዘው መምጣት እንዳለባቸውና የ አገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን የቤት ካርታቸውን ማስያዝ እንዳለባቸው የሚገልጽ ማስታወቂያ ።

በነገሩ የተስማሙና ቀድመው መረጃውን ያገኙ ሰዎች ፡ የቤት ካርታቸውን እያስያዙ ለሲም ካርዱና ፡ ቴሌ በብቸኝነት ያስመጣው የነበረውን ይህን በፎቶው የሚታየውን ትልቅ የ ኢሪክሰን ቀፎ 5,000 ሺህ ብር አካባቢ እየከፈሉ መውሰድ ጀመሩ .. የዚያኑ እለትም የመጀመሪያዎቹ ባለሞባይሎች በአዲስ አበባ ከተማ ይታዩ ጀመር ።

እነዚህ ጥቂት የከተማችን ባለሞባይሎች በሱሪያቸው ቀበቶ ላይ በታሰረ የቆዳ ቦርሳ ያንጠለጠሉትን ትልቅ ሞባይል እያየ ማን ያልተገረመ ነበር … በነገራችን ላይ ከነዚህ ቴሌ ከሚያስመጣቸው ስልኮች ውጭ በሌላ ቀፎ መጠቀም ፈፅሞ የተከለከለ ሲሆን በኢትዮጵያ ብቸኛው የሞባይል ቀፎ ሻጭ ቴሌ ብቻ ነበር ።

ቆየት ብሎ ታድያ የሞባይል ስልክ መጠቀም ፈልገው ነገር ግን የቤት ካርታ የሌላቸው ባለሃብቶች ቅር መሰኘታቸውን የተረዳው ቴሌ ፡ የቤት ካርታ ላላቸው የተመዘገቡ ባለሃብቶች ስልክ ሰጥቶ እንደጨረሰ ፡ ካርታ ለሌላቸው መስመር ፈላጊዎች 50 ሺህ ብር በማስያዝ ሲም ካርድ መውሰድ እንደሚችሉ አስታወቀ ።

በጥቂት ወራት እድሚው የሞባይል ስልክን አስፈላጊነቱን የተረዱ ሰዎች በርከት በማለታቸው 50 ሺ ብር አስይዞ ሞባይል የሚወስደው የ አዲስ አበባ ባለሃብት ተበራከተ ።

በዚያን ጊዜ የሞባይል አገልግሎት የሚሰራው በ 100 ኪሚ ራዲየስ ብቻ ነበረና የሞባይል ስልክ ብቸኛ መናሃሪያ አዲስ አበባ ከተማ ብቻ ነበረች ። ( ከአዲስ አበባ ከመቶ ኪሎ ሜትር በላይ ከራቀ ሞባይሉ አይሰራም ) 🤔
………..
ከዚህ በሁዋላ ቴሌ ለብዙ ወራት ሲም ካርድ መሸጥ አቁሞ ላሉት ጥቂት ባለሞባይሎች አገልገሎቱን ለማዳረስ ኔት ወርክ በማስፋፋት ሰራ ላይ ተጠምዶ ከቆየ በሁዋላ ከአዲስ ማስታወቂያ ጋር ብቅ አለ ።

. ቴሌ በአዲሱ ማስታወቂያው ብዛት ያላቸውን ሲም ካርዶች ያለምንም ማስያዣ በቀበሌ መታወቂያ ብቻ መስጠት ሊጀምር እንደሆነና በተጨማሪም ፡ የሞባይል ተጠቃሚው ቴሌ በብቸኝነት ከሚሸጠው ኤሪክሰን ስልክ ውጭ በፈለገው ስልክ መጠቀም እንደሚችል ገልጾ ምዝገባ ጀመረ ። በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች አገልግሎቱን ለማገኘት በመመዝገባቸውም ሲም ካርድ ለማገኘት ከ 6 ወር እስከ አንድ አመት መጠበቅ ግድ ነበር ።

በዚህ ወቅት የሲምካርድ ዋጋ ከአምስት ሺህ ብር ወርዶ 550 ብር ፡ ከዚያም 440 ብር 365 ብር ፡ 169 ብር ይሸጥ ነበር ። ይህን ተከትሎም የሞባይል ቀፎዎች በግለሰብ ሱቆች ውስጥ መሸጥ ጀመሩ ።

ዛሬ ላይ ሁሉ ነገር ቀላል ሆኖ. . ከየትኛውም ሱቅ ልንገዛው የምንችል እቃ ከመሆኑ በፊት .. … ሲም ካርድ ተመዝገበው ደርሷቸው የቀፎ መግዣ ካጡ ሰዎች ሲሙን በወር ከ 70 እስከ 100 ብር መከራየት ይቻልም ነበር ።

እናንተስ መጀመሪያ የያዛችሁት ስልክ ምን አይነት ነበር ? ለመጀመሪያ ቀን ስልክ ስታወጡ የነበራችሁ ስሜት ?
በመጀመሪያ ቀን የት ደወላችሁ ? ከሞባይል ጋር በተያያዘ ያጋጠማችሁ ?

Credit : #wasyhun_tesfaye

ለስራ ከተነሳን ፀሐይ አትጠልቅም!

የደራው መጽሔት “ፀሐይ አትጠልቅም!”

https://t.me/yederaw

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
“በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ359 ሺህ በላይ ዜጎች የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ተጠቃሚ ሆነዋል” ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16111/

#Ethiopia | በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ከ359 ሺህ በላይ ዜጎች የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆናቸውን የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዕቅድ አፈፃፀማ ግምገማ ተካሂዷል።

በግምገማው ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ከሰለጠነ የሰው ኃይል አቅርቦት፣ ከሥራ ገበያው ፍላጎት እና ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ የተከናውኑ ሥራዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፥ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 359 ሺህ 291 ዜጎችን በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ካለው የሥራ ገበያ ፍላጎት አኳያ አቅርቦት እና ጥራት ላይ ያሉ ችግሮችን በመፍታት ውጤቱን ለማላቅ እና የዜጎችን ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን አመልክተዋል።

በዘርፉ በመንግስትና በግል ተቋማት የሚሰጠው ሥልጠና የሥራ ገበያውን ፍላጎት የሚመልስ እና ፍላጎትና አቅርቦቱን ማጣጣም የሚያስችል መሆኑን የማረጋገጥ እንዲሁም ማነቆዎችን መፍታትና ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በዘርፉ የተጀመረው የዜጎችን መብት ደህንነትና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሥራ እንዲሁም ህገ-ወጥነትን መከላከልና ህግና ስርዓትን ማስከበር በልዩ ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ሚኒስትሯ።

ለዚህም በየደረጃው የሚመለከታቸው ባለድርሻ እና አስፈፃሚ አካላት ሁሉን አቀፍ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
#ena
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን አይሮጥም

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16113/

#Ethiopia | ኢትዮጵያዊ የረጅም ርቀት ንጉስ የሆነው ቀነኒሳ በቀለ የፊታችን እሁድ በሚደረገው የለንደን ማራቶን እንደማይሳተፍ ይፋ አድርጓል ።

ውድድሩን ለማድረግ ቀናት እየቆጠርኩኝ የነበር ቢሆንም በልምድ ወቅት መጠነኛ የሚባል ጉዳት በማስተናገዴ በዚህኛው ውድድር አልሳተፍም በዚህም መሰረት በአለም ላይ ለምተገኙ አድናቂዎቹ ድጋፋችሁን ስለሰጣችሁኝ አመሰግናለሁ ሲል በማህበራዊ ትስስር ግፁ አስቀምጧል ።
#aradaFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ከሱዳን የተፈናቀሉ ከ7 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ሰሜን ወሎ መግባታቸው ተገለጸ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16115/

#Ethiopia | ከ7 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሱዳን ተፈናቅለው አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን መግባታቸውን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ዓለሙ ይመር፤ ከቅርብ ዜያት ወዲህ ከሱዳን ድንበር ተፈናቅለው ሀርቡ ወረዳ በሚገኝ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙት ፍልሰተኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዳሻቀበ የገለጹ ሲሆን፤ 945 አባወራዎች ወይም ከ7 ሺሕ በላይ ሰዎች መሆናቸውን አሐዱ ተናግረዋል።

አክለውም፤ “ከሀገር ውስጥም ሆነ ከጎረቤት ሀገራት ተፈናቅለው ወደ ዞኑ የሚገቡ ተፈናቃዮች ሀርቡ ወረዳ በሚገኝ መጠለያ ጣቢያ ይገኛሉ” ብለዋል፡፡

“የተፈናቃዮች ቁጥር ከአቅማችን በላይ ሆኗል” ያሉት ኃላፊው፤ የመጠለያ ጣቢያ ካምፖቹ ሲመሰረቱ ለ6 ወር ብቻ እንዲያገለግሉ ቢሆንም አሁን 7 ዓመት እየሆናቸው እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ከታሰበው በላይ ረዥም ዓመት ያገለገሉት ካምፖችም በእርጅና ምክንያት ከጥቅም ውጪ እየሆኑ እንደሚገኙም አንስተዋል፡፡

“መጪው ክረምት እንደመሆኑ የችግሩን አሳሳቢነት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለሚመለከታቸው አካላት ከክልል እስከ ፌደራል ባለው የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ እያገኘን አይደለም” ብለዋል።

በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍል እና ከሱዳን የተፈናቀሉ ከ32 ሺሕ 800 በላይ ተፈናቃዮች በ7 መጠለያ ጣቢያ ጣቢያዎች ውስጥ እና ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው እየኖሩ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።
#ahaduRadio
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በኦፔክ ላይ የተጣለዉ የአሜሪካ ቀረጥ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሃገራት የነዳጅ ምርት ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ ነዉ ተባለ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16117/

#Ethiopia | የአሜሪካ ቀረጥ በተለይም ዶናልድ ትራምፕ ከተመረጡ በኋላ ያሉት ዓለም አቀፍ የንግድ ግንኙነቶች እንዲሁም ዓለም አቀፋዊው የንግድ ጦርነት ለተለያዩ ሃገራት ስጋት እና እድል ይዞ እንደሚመጣ ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ እንደገለጹት፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የአንድ አገር አጠቃላይ እድገት ላይ ትልቅ ሚና ያለዉ እንደመሆኑ ለዘርፉ የነዳጅ ፍላጎት እና አቅርቦት ወሳኝነት ጥያቄ ዉስጥ የሚገባ አለመሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡

በዚህም በአሜሪካ የሚጣሉ ቀረጦች እንደ ኦፔክ(The Organization of the Petroleum Exporting Countries (OPEC)) ያሉ የነዳጅ ምርት አምራች አገራት ላይ የሚፈጥረዉ ጫና ከፍተኛ በመሆኑ ወደ አሜሪካ ገበያ የሚያሰገቡትን ምርት ቀንሰዉ ወደ ሌሎች ሃገራት ለመላክ እንደሚያስገድዳቸዉ እና ኢትዮጵያ በዚህ ተጠቃሚ ልትሆን እንደምትችል አስረድተዋል፡፡

ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋዎች የሚወሰኑት በአለም አቀፍ ገበያ መሆኑ ቢታወቅም ሚኒስቴሩ የዋጋ ቅናሽ ለማድረግ ድርድር ሊያደርግ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪሙ አቶ ወንድሙ መንግስት የነዳጅ ዋጋ መጨመር የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ በአሁኑ ወቅት አረንጓዴ ኢኮኖሚን በማሳደግ ላይ ያተኮረ ፖሊሲን እየተገበረ በመሆኑ ብሎም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሃብት በመጠቀም የሚንቀሳቀሱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ እንዲዉሉ እየተደረገ በመሆኑ ፤በነዳጅ ላይ የተመሰረተ ትራንስፖርትን ቀስ በቀስ በመቀነስ ለነዳጅ የሚወጣዉን ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ የንግድ ፖሊሲ ለኢትዮጵያ ፈተና ሊሆን ቢችልም መንግስት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን በማስፋፋት እና በአለም አቀፍ ገበያ ላይ ተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት በመደራደር እነዚህን ተግዳሮቶች ወደ ዕድል መቀየር እንደሚችል የሚኒስቴር መስራ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ አመላክተዋል ።
#menahriaFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ስብሰባና ቢዝነስ ፎረም ተካሄደ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16119/

#Ethiopia | የኢትዮ-ሳዑዲ የጋራ ንግድ ም/ቤት የመጀመሪያ ስብሰባ እና የቢዝነስ ፎረም ሚያዚያ 14 ቀን 2017 በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ ተካሄዷል።

ስብሰባው በኢትዮጵያ ወገን በኢፌዴሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ በክቡር ዶር አብዱልሃኪም ሙሉ የተመራ ሲሆን የሳዑዲ አረቢያን ልኡካን የሳኡዲ አረቢያ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሃሰን ቢን ሙጂብ አልሁዋዚ መርተዋል።

በፎረሙ ላይ ከ100 በላይ የሁለቱ አገሮች የንግድ ማህበረሰብ አባላትን የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፥ በሁሉቱም አገሮች ለንግዱ ማህበረሰብ ያሉ መልካም እድሎችን በተመለከተ ገለጻዎች ተደርገዋል፥ በንግዱ ማህበረሰብ አባላት መካከልም የቢ2ቢ ውይይቶች ተካሂደዋል።

በቢዝነስ ፎረሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብዱልሃኪም ሙሉ እኤአ በጁን 2024 በአዲስ አበባ የተቋቋመው የጋራ ንግድ ም/ቤት የሁለቱን አገራት ታሪካዊ እና ጂኦግራፊያዊ ቅርበትን እንደ እድል በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ጠቅሰው በኢትዮጵያ ሰፊ የንግድና የኢንቨስትመንት አማራጮችn እንዳሉ በመግለፅ የሳዑዲ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በተመሳሳይ በሳኡዲ አረቢያ የኢፌዴሪ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ዶ/ር ሙክታር ከድር የጋራ ንግድ ምክር ቤቱ ስራ መጀመርና የቢዝነስ ፎረሙ መካሄድ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትስስር እንደሚያጠብቅ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር አያይዘውም በቀጣይ በግንቦት ወር 2017 በአዲስ አበባ በሚካሄደው ኢትዮጵያ ታምርትና ኢንቨስት እን ኢትዮጵያ መድረኮች የሳኡዲ አረቢያ ባለሀብቶች በስፋት እንዲሳተፉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በሌላ በኩል በስብሰባው ተካፋይ የሆኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ እስያ እና ፓሲፊክ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ንጉስ ከበደ ባቀረቡርት ገለጻ በኢትዮጵያ ስላሉ መልካምና ተመራጭ የኢንቨስትመንትና ንግድ እድሎች በተለይም የመንግስት ፖሊሲ ትኩረት አቅጣጫ በሆኑት በግብርና፣ በቴክኖሎጂ፣ በማዕዲን ዘርፍ፣ በማኑፋክቸሪንግ ፥ ቱሪዝምና በመሳሳሉ ዘርፎች መንግስት ለውጭ ባለሀብቶች ያመቻቸው እድሎችን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፥ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ እንቨስትመንት ሆልድንግስት ምክትል ዋና አስፈጻሚ በዘርፉ መንግስት በሚሰራቸው ስራዎች ላይ ጠቃሚ መረጃዎቸን ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ሰብሳቢ የሆኑት ክቡር አቶ ሰብስቤ አባፊራ መድረኩ በሁለቱም አገራት ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት እድልን ያጎለብታል ሲሉ ተናግረዋል።

በሳኡዲ ወገን በኩል በ2030 የሳዑዲ አረቢያ ሁለንተናዊ እድገት ራዕይ የአፍሪካን አህጉር በኢኮኖሚው ዘርፍ ዋና መዳረሻ ያደረገ እንደሆነና ኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ የንግድና ኢንቨስትመንት አጋር በማድረግ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጡ አብራርተዋል።

የምክር ቤቱ ስብሰባ በሁለቱ አገሮች መካካል ያሉ የንግድ፥ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም እድሎችን እየለየና የሚያጋጥሙ0
ችግሮችን እየፈታ በመስኮቹ የሚኖሩ ትብብሮችን እንደሚያጎለብት የተገለፀ ሲሆን፥ የቢዝነስ ፎረሙ የቀረቡ ሃሳቦችና የንግድ ማህበረሰብ መካከል የተደረጉ ውይይቶች እጅግ ጠቃሚ መሆናቸውን መገንዘብ ተችሏል።

ፎረሙ በግንቦት 2016 ዓ.ም በሁለቱ አገሮች ንግድ ምክር ቤቶች መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት የተካሄደ ሲሆን፥ በቀጣይ አመት አዲስ አበባ ላይ የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet