Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
6.07K subscribers
2 photos
4.6K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16063/

#Ethiopia | በኦሮሚያ ክልል ከሚያዝያ 6 እስከ ሚያዝያ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ11 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ12ሰዎች ላይ ከባድ በ7 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ አደጋ ከ6 እስከ 45 ዓመት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ የሆኑት ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራትሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

አብዛኞዎቹ አደጋዎቹ የተከሰቱት በቀኑ እና በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ሲሆን አደጋውን ያደረሱት ወንድ አሽከርካሪዎች ናቸው። አደጋዎቹ በተለያዩ ዞኖች እና ከተሞች የተከሰቱ ናቸው።

የሞት አደጋዎች የደረሱት በጭነት፣ በህዝብ ማመላለሻ ፣በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ) እና በሞተር ሳይክል የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የአደጋዎቹ መንስኤዎቹ ያለመንጃ ፍቃድ ማሽከርከር፣ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር እና ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት መሆኑን ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል::

#ዳጉ_ጆርናል
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የ60 ዓመት ጓረቤቱን በጨለማ በር ሰብሮ በመግባት አስገድዶ የደፈረው ግለሠብ በእስራት ተቀጣ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16065/

#Ethiopia | በምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ ውስጥ የስልሣ ዓመት ጓረቤቱን ጨለማ ተገን በማድረግ በራቸውን ሠብሮ በመግባት የመድፈር ጥቃት የፈፀመው ግለሠብ በእስራት መቀጣቱ የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ አስታውቋል።

የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሉጌታ ጭምዲ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት ተከሣሽ ተስፋዬ ፍቃዱ የተባለው የሀያ አምስት ዓመት ወጣት ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ የቤታቸው በር ዘግተው የተኙትን የስልሣ አመት ጎረቤቱን በር ሠብሮ በመግባት የመድፈር ጥቃት መፈጸሙ ተገልጿል ። ግለሰቡ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ለመሰወር ሲሞክር ጥቃት የደረሠባቸው አዛውንት ባሰሙት ጩኸት በቁጥጥር ሊውል ችሏል።

ፖሊስም በቁጥጥር ስር በዋለው ግለሠብ ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማጠናከር ለዓቃቢ ሕግ ያቀረበ ሲሆን አቃቢ ሕግም በወንጀል ሕግ ቁጥር 620 ንዑስ አንቀፅ ሶስት መሠረት ክስ መስርቷል ። የተመሰረተውን ክስ ሲከታተል የቆየው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሚያዝያ 8 ቀን 2017ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሣሽ ተስፋዬ ፍቃዱ በእድሜ የገፉ እና እናቱ በሚሆኑ ላይ መከላከል በማይችሉበት ምሽት ላይ የመድፈር ጥቃት መፈፀሙ ነውረኛነቱን የሚገልፅ በመሆኑና ይሕም በበቂ ማስረጃ በመረጋገጡ በአምስት ዓመት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ሙጌታ ጭምዲ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

#ዳጉ_ጆርናል

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካዛንቺስን የኮሪደር ልማት በይፋ መረቁ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16067/

#Ethiopia | ከተሞቻችንን የማዘመን ሰፊ ጥረት አይነተኛ ማሳያ የሆነውን በካዛንቺስ ያለዉን የኮሪደር ልማት ክፍል በይፋ መርቀናል።

የተጎሳቆሉ እና በእጅጉ የተጎዱ ቤቶች እና ከባቢ መገኛ የነበረው ካዛንቺስ ዛሬ የጋራ ጥረት እና ለውጥ ሽልማታችን ሆኖ ተገኝቷል።

ከዚሁ አካባቢ ተነስተው ለማኅበረሰባችን የከበረ የኑሮ ሁኔታን ለመፍጠር ያለንን ፅኑ እምነት እና ተግባር በሚያሳይ አኳኋን ለኑሮ ወደ ተሻለ ከባቢ የተዛወሩትን ነዋሪዎች ከጥቂት ቀናት በፊት ጎብኝተን ነበር። የተዛወሩበት ከባቢ እጅግ ምቹ መሆኑን አይተናል። ዛሬ ደግሞ የተነሱበትን ሰፈር ድንቅ የኮሪደር ልማት ሥራ መርቀናል።

በአስደናቂ አጭር ጊዜ የተጠናቀቀው የካዛንቺስ ለውጥ ለዘመነ ከተማ ልማት ሥራችን ለአረንጓዴ፣ ንፁህ እና ዘመናዊ የከተማ ማዕከላት ያለንን ርዕይ ግዘፍ ነስቶ በማሳየት መሠረት የሚጥል ነው። በዚህ ግዝፈት የሚከወኑ ሥራዎች ሰፋ ያለ ጥረት ይሻሉ። ጊዜያዊ ምቾት የሚነሱ ፈተናዎችንም ሊያስከትሉ ይችላሉ። ነገር ግን ለታላቁ የሀገር ጥቅም የሚከፈሉ አስፈላጊ መስዋዕትነቶች ናቸው። ይኽ የእድገት መንገድ መቀጠል ያለበት ነው። የታደሰ ተስፋ ይሰጣልና። በተለይ ለልጆቻችን ነገ።
#etv
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የዓይን ማቃጠል እና መፍትሄዎቹ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16069/

#Ethiopia | በዓይንዎ ውስጥ ያለው የማቃጠል ስሜት ህይወትዎ ከባድና አስደሳች እንዳይሆን እያደረግዎት ይሆን? መንስኤው ምን ሊሆን እንደሚችል እና ከዚህ ችግር እንዴት እፎይታ ማግኘት እንደሚቻል እንመልከት! 🕵️‍♂️

✳️ የዓይን ማቃጠል ምንድን ነው? 🔥
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

የዓይን ማቃጠል ልክ እንደ ቃሉ ነው – በአንዱ ወይም በሁለቱም ዓይኖቻችን ውስጥ የማቃጠል ወይም የመንደድ ስሜት ሲሰማን ነው።

ይህም በጣም ቀላል የሆኑ የዕለት ከዕለት ተግባሮችን እንኳን ለማከናወን ፈታኝ ያደርገብናል፤ እንዲሁም እንቅስቃሴዎቻችንን ሊያስተጓጉል ይችላል።

✳️ መንስኤዎቹ ምን ምን ናቸው?
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

👉👉 የዓይን ማቃጠል በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። ከእነዚህ መንስኤዎች መካከል:-

🏀 አለርጂ:- እንደ የአበባ ዱቄት ወይም የቤት እንስሳ ፀጉር ያሉ አለርጂዎች የአይን ማቃጠል ሊያስከትሉ ይችላሉ።

🏀 የዓይን መድረቅ፡- በቂ ያልሆነ እንባ ማምረት ወይም ፈጣን ትነት ዓይኖችዎን እንዲደርቁ እና እንዲያበሳጩ ሊያደርግ ይችላል።

🏀 የሚያቃጥሉ ኬሚካሎች:- እንደ የጽዳት መጠበቂያ ምርቶች፣ ሽቶ ወይም ክሎሪን (በረኪና) ያሉ በየዕለቱ የምንጠቀምባቸው የማጽጃ ምርቶች ውስጥ ያሉ ኬሚካሎች አነሳሽ ወይም ቀስቃሽ ሊሆኑ ይችላሉ።

🏀 ዝቅተኛ የእርጥበት መጠን፡- ደረቅ የቤት ውስጥ አየር በተለይም በሞቃት ቦታዎች ከአይንዎ እርጥበትን ሊወስድ ወይም ዓይንዎ እንዲደርቅ ሊያደርግ ይችላል።

🏀 ኢንፍላሜሽን፡- እንደ ብለፈራይተስ ወይም ኦኩላር ሮዜሺያ (blepharitis or ocular rosacea) ያሉ ሁኔታዎች የአይን ማቃጠል ሊያስከትሉ ይችላሉ።

🏀 ለአልትራቫዮሌት ጨረር መጋለጥ፡- ለፀሀይ ብርሀን ወይም አርቲፊሻል ዩቪ ጨረሮች ከመጠን በላይ መጋለጥ ፎቶኬራቲትስ ወይም ሰንበርንድ አይስ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

🏀 ኢንፌክሽኖች፡- የአይን መቅላት (ፒንክ መሆን) (conjunctivitis) ወይም አይንን የሚያጠቁ ሽንግልስ በተጨማሪ መንስኤ ሊሆን ይችላል።

🏀 ተጓዳኝ የጤና ችግሮች:- እንደ ሲዎግረን ሲንድረም ወይም ተርጂየም (Sjögren’s syndrome or pterygium) ያሉ ሁኔታዎች ለዓይን ማቃጠል አስተዋፅዖ ያደርጋሉ።

✳️ ሕክምና (እፎይታ ማግኘት)
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

ሕክምናው እንደ መንስኤው ይለያያል። የጤና ባለሙያዎችን ማማከር የመጀመሪያው እርምጃ ሲሆን፤ ባለሙያው ወይም ሐኪምዎ የሚከተሉትን ሊመክርዎት ይችላሉ፡-

🍋 አንቲ-ሂስታሚን:- መንስኤው ወይም ቀስቃሽ ነገሮቹ አለርጂዎች ከሆኑ።

🍋 ቤቢ ሻምፑ፡- ለ ብለፈራይተስ (blepharitis) የዐይን ሽፋሽፍቶችን በውሃ እና በቤቢ ሻምፑ በዝግታ ማጽዳት።

🍋 የዓይን ጠብታዎች:- ለዓይን ድርቀት የማለስለሻ ጠብታዎች ወይም ሰው ሰራሽ እንባ መጠቀም።

🍋 ዓይንን መታጠብ፡- የሚያቃጥሉ ወይም ኢሪታንት ነገሮችን ለማስወገድ ዓይንዎን በደንብ ይታጠቡ።

🍋 ሙቅ ወይም ቀዝቃዛ ኮምፕረሺን:- ለተለያዩ የዓይን ችግሮች ወይም ሁኔታዎች የምቾት ማጣትን ያስወግዳል።

✳️ መከላከል ቁልፍ እርምጃ ነው!
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

👉👉 ሁልጊዜ ከመንስኤዎቹ መራቅ ባይቻልም፤ የሚከተሉትን ማድረግ የዓይን ማቃጠልን ይከላከላል:-

🍑 ለአለርጂዎች መጋለጥዎን ይቀንሱ።
🍑 ዓይኖችዎን ከማሸት ይቆጠቡ።
🍑 ለሽታ ተብሎ ኬሚካል ከሚጨመርባቸው (ከሽታ) ነጻ የሆኑ ምርቶችን ይጠቀሙ።
🍑 የእጅ ንጽህናዎን ይጠብቁ።
🍑 አይኖችዎን ከፀሃይ ብርሃን ጨረር እና ብናኝ ቆሻሻዎች ይጠብቁ።
🍑 እንደ:- የዓይን ጠብታዎች ወይም ፎጣዎች ያሉ የግል መጠቀሚያ ዕቃዎችዎን በፍጽም ለሌሎች ሰዎች አያጋሩ።

✳️ እርዳታ የሚያስፈልግዎት መቼ ነው?👁️
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

ማንኛውንም የዓይን ሕመም ችላ አይበሉ! የዓይን ማቃጠሉ ከቀጠለ ወይም እንደ:- ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የእይታ ለውጦች ወይም ሽፍታ ካሉ፣ እንዲሁም ሌሎች ምልክቶችን ካስተዋሉ የጤና ባለሙያ ወይም ሐኪም ያማክሩ።

🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋 🚋🚋🚋

ጤና ይስጥልን 👋

#ethioTena

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የመጻሕፍት ድጋፍ አደረገ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16071/

#Ethiopia | ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል 200 የሚደርሱ ልዩ ልዩ የህክምና መጻሕፍት ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የተረከቡት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቤተ መጻሕፍትና ኢንፎርሜሽን ዳይሬክተር አስናቀ ሙልዬ(ዶ/ር)፣ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት፤ ከዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ለዩኒቨርሲቲው የተበረከቱት መጻሕፍት በቁጥር 200 የሚደርሱ የህክምናና ልዩ ልዩ መጻሕፍት እንደሆኑ ገልጸው፤ እነዚህ መጻሕፍት በተለይ በዚህ ወቅት ተማሪውን ወደ ንባብ ለመመለስም ይሁን ላይብረሪውን በተሟላ ሁኔታ ለማደራጀት አስተዋጽኦቸው የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል።

ዶ/ር አስናቀ አያይዘውም፤ ይህ በመጻሕፍት ባንኩ የተደረገው ድጋፍ ለአሁኑ እንደ ጅምር ይታይ እንጂ በቀጣይ ከዛጎልም ይሁን ከሌሎች ተቋማት ጋር ግንኙነቶችን በማጠናከር ሌሎች ላይብረሪዎችንም የማደራጀቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው ፤ ለአሁኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ላደረገው ድጋፍ በዩኒቨርሲቲው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አቶ ትዝአለኝ ተስፋዬ ፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚ በበኩላቸው ፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጤናው ዘርፍ የህክምና ትምህርትን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ተማሪዎችን አስተምሮ ለሀገሪቱ የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት ብዙ አመታትን ያስቆጠረ ትልቅ ተቋም እንደመሆኑ ይህ ለኮሌጁ የተበረከቱት መጻሕፍትም ለጤናው የትምህርት ዘርፍ በተለይም ለህክምና ተማሪዎች እጅግ አስፈላጊ በመሆናቸው ለድርጅቱ ምስጋናዬን በሆስፒታሉና በራሴ ስም ላቀርብ እወዳለሁ ብለዋል ።

እነዚህ መጻሕፍት አሁን ላይ በኮሌጁም ላሉም ሆነ ወደፊትም ለሚከፈቱ ትምህርት ክፍሎች አይነተኛ እገዛ የሚያደርጉ በመሆናቸው መጻሕፍቱ ተማሪዎች በተሻለ መልኩ ተቃኝተው ብቁ ሆነው እንዲወጡ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርጉ አቶ ትዝአለኝ አያይዘው ተናግረዋል።

አለማየሁ አካሉ (ዶ/ር) ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ልዩ ረዳት በርክክብ ወቅት እንደገለጹት ፤የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሀገራችን ደካማ የሆነውን የንባብ ባህል ለማሳደግ ዘርፉ ላይ ከሚሰሩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመው ፤ በተለይ ዛጎል የመጻሕት ባንክ አሁን ላይ በሀገሪቱ ንባብን እና አንባቢን ለማወዳጀት እያበረከተ ላለው አስተዋጽኦ ትልቅ አድናቆት እንዳላቸው በመግለጽ ድርጅቱ ዛሬም ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ለደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዛጎል የመጻሕፍት ባንክን ወክለው መጻሕፍቱን ያስረከቡት ወ/ሪት ፍፁም ማሩ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ፤ ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ከ2013 ጀምሮ መጻሕፍትና አንባቢ ለማገናኘት የተቋቋመ የበጎ አድራጎት ድርጅት እንደሆነ አውስተው ፤ ድርጅቱ ይህን አላማውን ለማሳካት ከየግለሰቦችና ተቋማት መጻሕፍትን እያሰባሰበ እስካሁን ወደ 40 ሺህ የሚደርሱ መጻሕፍትን እንዳሰራጨ በመግለጽ በዛሬው ዕለትም ለዲላ ዩኒቨርሲቲ 200 የሚደርሱ የህክምናና ልዩ ልዩ መጻሕፍትን እንዳስረከበ ተናግረዋል።

ወ/ሪት ፍፁም አክለውም፥ በቀጣይም ይህንኑ ድጋፍ በሌሎች መስኮች ላይም አጠናክሮ ለማስቀጥል ከዩኒቨርሲቲው ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ ገልጸው ፤ በዩኒቨርሲቲው ለተደረገላቸው መልካም አቀባባል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የማንችስተር ሲቲ እና አስቶንቪላ በሊጉ ተጠባቂ የዛሬ መርሃ ግብር

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16073/

#Ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከአስቶንቪላ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኢትሃድ ስታዲየም ይደረጋል።

ማንችስተር ሲቲ በ58 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲሆን አስቶንቪላ በ57 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሁለቱ ክለቦች በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ብርቱ ፉክክር እያደረጉ ይገኛሉ።

ለቡድኖቹ ማሸነፍ ለሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ህልማቸው ወሳኝ የሚባል ነው።

በሌላኛው የ34ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ነገ አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ ጋር ይገናኛሉ።

ሁለቱ ጨዋታዎች በሳምንቱ አጋማሽ እንዲደረጉ የተወሰነው ክሪስታል ፓላስ ከአስቶንቪላ እና ማንችስተር ሲቲ ከኖቲንግሃም ፎረስት በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በሚያደርጉት የኤፍኤ ካፕ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ምክንያት ነው።

ኖቲንግሃም ፎረስት ከብሬንትፎርድ ጋር ሊያደርገው የነበረው የ34ኛ ሳምንት ጨዋታም ወደ ቀጣዩ ሳምንት መዘዋወሩን የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር አስታውቋል።

ሌሎቹ መርሃ ግብሮች በተያዘላቸው ጊዜ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ይደረጋሉ።

#ena

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
” የትግራይ ህዝብ ከሰጠኝ እውቅናና ክብር በላይ የምመኘው የክብርና የምስጋና መድረክ የለም ” – አቶ ጌታቸው ረዳ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16075/

#Ethiopia | የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በአዲሱ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) የቀረበላቸው የክብርና የምስጋና የሽኝት መድረክ ውድቅ አደረጉ።

አቶ ጌታቸው ረዳ ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚድያ ቃለ-መጠይቅ ሰጥተዋል።

ሚንስትሩ UMD ለተባለ ሚድያ በትግርኛ ቋንቋ በሰጡት ቃለመጠይቅ ” በትግራይ የተደረገው የስልጣን ሽግግር የትግራይ ህዝብን ደህንነትና ህልውና የሚያስጠብቅ አይደለም ” ብለውታል።

የኢፌዱሪ ጠቅላይ ሚንስትር ለድህንነታቸው ያደረጉትን ጥንቃቄ እውቅና በመስጠት ያመሰገኑት አቶ ጌታቸው ፤ በማንኛውም መመዘኛ የትግራይ ህዝብ መልሶ ወደ ጦርነት እንዳይገባ የቻሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከጫፍ እንዲደርስ አበክረው እንደሚሰሩ ገልጸው ‘” በትግራይ የተጀመረው የለውጥ ፍላጎት ወደ ኋላ የሚጎትት ማንኛውም እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም ” አይሳካም ብለዋል።

ትግራይ ላይ እሳቸውን ለመግደል የተሸረበ ሴራ እንደነበር ፤ ይህንን ሽሽተው ከትግራይ ፓለቲካ የመውጣት አንዳች ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

” የተደረገው የስልጣን ሽግግር ጠቅላይ ሚንስትሩ በተገኙበት በትግራይ መቐለ ቢሆን ትልቅ ትርጉም ይኖረው ነበር ” ያሉት አቶ ጌታቸው ” ትናንትን እየመዘዙ ቁርሾና ቂም በቀል ማቀጣጠል ፋይዳ የለውም ” በማለት ተናግረዋል።

” እኔን በክብር መሸኘት ቅድሚያ የሚሰጠው አይደለም ፤ ቅድሚያ የሚሰጠው በትግራይ የሰፈነው ህግ አልባ አካሄድ እንዲስተካከል መስራት ነው ” ሲሉ አክለዋል።

” የትግራይ ህዝብ የሰጠኝ ክብርና እውቅና ከፍተኛ ነው ፤ ከዚህ ክብርና እውቅና በላይ የምመኘው የምስጋና መድረክ የለም ” ሲሉ የገለፁ ሲሆን በአዲሱ ፕሬዜዳንት የቀረበላቸው የምስጋናና የክብር የሸኝት መድረክ እንደማይቀበሉት አሳውቀዋል።

በክልሉ ያሉ ሌቦችና ህገ-ወጦች አደብ ለማስገዛት ለሚደረገው ጥረት እንደሚያግዙ ህዝቡ ለማገለገል እንደ ትናንት ዛሬም ዝግጁ እንደሆኑም ገልጸዋል።

#Tikvah

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ ሮቦቶች የግማሽ ማራቶን ሩጫ ላይ ተሳተፉ።

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16077/

#Ethiopia | በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በሚሳተፉበት Yizhuang በተሰኘ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ላይ ከ20 በላይ ሮቦቶች መሳተፋቸው ተገለፀ።

ውድድሩ ላይ የተሳተፉት ሮቦቶች እንደ DroidUP እና Noetix Robotics ባሉ ዝነኛ የቻይና ድርጅቶች የተሰሩ ሲሆኑ ውድድሩ ላይም ትላልቅ እና መለስተኛ ሮቦቶች ሲሮጡ ተስተውሏል።

የ21 ኪ.ሜ አልያም 13 ማይል ገደማ ሩጫ ከተወዳደሩት ሮቦቶች መካከል ጫማ ለብሰው መወዳራቸው እና አንዳንዶቹ ገና ከመጀመራቸው መውደቃቸው ትኩረት ከሳቡ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ።

አሸናፊውም ከBeijing Innovation Center of Human Robotics የመጣው Tiangong Ultra የተሰኘው ሮቦት ነው። ውድድሩን ለማጠናቀቅም 2 ሰዓት ከ40 ደቂቃ የፈጀበት ሲሆን በአንፃሩ ከሰዎች ተዎዳዳሪዎች አንደኛ የወጣው 1 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ብቻ ነው የፈጀበት።
#bh

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የአሜሪካ ድምፅ ነገር …

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16079/

BREAKING: A federal judge has ordered the Trump administration to restore Voice of America and several affiliated news services.

የግራ ቀኙን ክርክር ሲያደምጡ የቆየቱ የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ፣ የአሜሪካ ድምፅ እና ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ ሚዲያ ኤጀንሲ (ዩ.ኤስ.ኤ.ጂ.ኤም.) ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ አዘዙ።

አስተዳደራዊ ዕረፍት የተሰጣቸው ቋሚና የኮንትራት ሠራተኞች ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ወሰኑ።

Via Tsion Girma

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
” ዣቪ አሎንሶ ከተጫወተባቸው ክለቦች ጋር መደራደር የሚያስችለው ቅድመ ስምምነት አለን” የባየር ሊቨርኩሰን ዋና ስራ አስፈጻሚ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16081/

#Ethiopia | ሪያል ማድሪድ ከአሰልጣኙ ካርሎ አንቸሎቲ ጋር በውድድር አመቱ መጨረሻ መለያየቱ አይቀሬ ይመስላል። ማሪንጌዎቹ አንጋፋውን አሰልጣኝ ለመተካት ቀዳሚ ምርጫቸው የቀድሞ ኮከብ ተጫዎቻቸው ዣቪ አሎንሶ እንደሆነ ተደጋግሞ ተነግሯል። አሁን በቡንደስሊጋው ባየር ሊቨርኩሰንን እያሰለጠነ የሚገኘው የቀድሞው አማካኝ ባለፈው አመት ያሳየውን ብቃት ባይደግምም ወደ ሀገሩ ሊመለስ በዝግጅት ላይ ነው።

ጉዳዩን አስመልክቶ የተጠየቁት የሊቨርኩሰኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፈርናንዶ ካሮ አሎንሶ ተጫውቶ ካለፈባቸው ክለቦች ጋር መደራደር ከፈለገ የማይከለከልበት የጋራ ስምምነት መኖሩን አስታውሰዋል። አሎንሶ በሪያል ሶሲየዳድ ፣ ሊቨርፑል ፣ ሪያል ማድሪድና ባየር ሙኒክ ተጫውቶ አሳልፏል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ክለባችን በቀጣይ አመት አሎንሶን ይፈልገዋል ግን ማድሪድ አሰልጣኙን ሊሸኝ ስለተዘጋጀ ከአሎንሶ ላይ አይኑን እንዳሳረፈ እናውቃለን በስምምነታችን መሰረትም መነጋገር ይችላሉ ብለዋል። እነዚህ ክለቦች ከፈለጉት ቁጭ ብለን መነጋገር እንጂ በጉዞው ላይ እንቅፋት አንሆንም ብለው ስምምነታቸውን እንደሚያከብሩ አስረግጠዋል።

ከ4ቱ የቀድም ክለቦቹ አሎንሶን ፈልጎ የሊቨርኩሰንን በር የሚያንኳኳ ከመጣ የጀርመኑ ክለብ ለመልቀቅ ዝግጁ ነው። ሊቨርፑል በአርነ ስሎት ስር የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ጫፍ የደረሰ ፣ ባየር ሙኒክም በቪንሶን ኮምፓኒ የድሉ ጫፍ በመቆማቸው አሎንሶን ይፈልጋሉ ተብሎ አይጠበቅም። ሪያል ማድሪድ ብቸኛ ፈላጊው መሆኑ እርግጥ ነው።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ፈርናንዶ ካኖ ከስፔኑ ሀያል ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላቸውም ተናግረዋል።

በሁሴን ግዛው

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በኢትዮጵያ በበይነ መረብ አማካኝነት መረጃን ከሚያስተላለፉት መካከል 65 ያህሉ ህጋዊ ፈቃድ እንዳገኙ ተነገረ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16083/

#Ethiopia | በዚህም በኢትዮጵያ ፈቃድ ያላቸው የመገናኛ ብዙኃን አጠቃላይ ብዛት 292 እንደደረሱ ሰምተናል፡፡

የመገናኛ ብዙኃኑ የሚመዘገቡበት ዘርፍም ወደ አስር አድጓል ተብሏል፡፡

ከእነዚህ ዘርፎችም፣ የህዝብ፣ የማህበረሰብ፣ የሀይማኖት፣ የንግድ፣ የበይነ መረብ፣ የክፍያ(እንደ ዲኤስ ቲቪ ያሉ) እና የትምህርት የመገናኛ ብዙሃን እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተከትለው እየመጡ ያሉ የመገናኛ ብዙሀን ዘርፎችን ወደ አሰራሬ አስገብቼ ለመመዝገብ እየበረታሁ ነው ብሏል፡፡

በአሁን ሰዓት በሀገሪቱ 236 በስርጭት ላይ እንዲሁም 56 ፍቃድ ወስደው በዝግጅት ላይ ያሉትን ጨምሮ በድምሩ 292 በባለስልጣኑ የተመዘገቡ የመገናኛ ብዙሃን እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ 65ቱ በበይነ መረብ በመደበኛነት የሚድያን ስራ ለመስራት የተመዘገቡ ናቸው ተብሏል፡፡

ይህንን ለሸገር ራዲዮ የተናገሩት በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለልጣን የመገናኛ ብዙሀን ፈቃድ ምዝገባና እውቅና ዴስክ ሀላፊ ደሴ ከፋለ ናቸው፡፡

በተለይም ዘመኑ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እያመጣ ስለሆነም እነዚህን ታክከው የሚመጡ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፎችንም በፈቃድ ስርዓት ለማካተት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል፤ ኦቨር ዘ ቶፕ #OTT ወይም በኢንተርኔት አማካኝነት የተጫኑ ይዘቶችን ማንኛውም ሰው በፈለገው ሰዓት ማግኘት የሚችልባቸው፤ እንዲሁም ኢንተራክቲቭ ቮይስ ሪስፖንስ #IVR የሞባይል ኔትዎርክን በመጠቀም በሬድዮ እንደሚሰራጩትንና መሰል ይዘቶችን በአጭር ቁጥር ደውሎ ማድመጥ የሚያስችሉ ዘመንኛ መላዎችን እንደምሳሌነት ተጠቅሰዋል፡፡
#shegerFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የፋሲካ በዓልን ምክንያት አድርገው ለጤና ጠንቅ የሆኑ የምግብ ምርቶችን ይዘው የተገኙ 14 ተቋማት መታሸጋቸው ተሰማ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16085/

#Ethiopia | ለገበያ ቀርበው ነበር ከተባሉት ምርቶች መካከል የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ይገኙበታል፡፡

የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ከወንኩት ባለው የቁጥጥር ስራ ለበዓሉ ሊኖር የሚችለውን የማህበረሰቡን የመሸመት ፍላጎት ባልተገባ መንገድ ሲጠቀሙ ያገኋቸውን 14 ተቋማት አሽጊያቸዋለሁ ብሎናል፡፡

ተቋማቱም የምግብ ዘይት ማምረቻዎች፣ የ #ባልትና ውጤት መሸጫዎችና ወፍጮ ቤቶች መሆናቸውን የነገሩን በአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወ/ሮ ወርቅነሽ ብርቄ ናቸው፡፡

በክትትሉ የተገኙት የምግብ ምርቶች ምን አይነት የጤና እክል ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ ምርመራ እየተደረገበት ነው፤የላብራቶሪ ውጤቱ ታይቶ ተጨማሪ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

በዓሉን ተከትሎ ሊኖር የሚችልን የምርትና ሽያጭ ወቅት ችግር ለመቆጣጠር በተደረገው ክትትል የተፈተሹት 2500 ተቋማት ናቸው ያሉን ሃላፊዋ ከእነዚህ ውስጥ 14 ታሽገዋል፤ 82ቱ በፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ታልፈዋል፤ ቀሪዎቹ እንከል እንዳልተገኘባቸው ጠቅሰዋል፡፡

የታሸጉት የምግብ ዘይት ፋብሪካዎች፣ ባልትና መሸጫዎችና ወፍጮ ቤቶች ወደ ቀደመ ስራቸው ለመመለስ የተገኘባቸውን ችግር ማስተካከላቸውን ለባለስልጣኑ ያሳውቃሉ፤ተቆጣጣሪው ባለስልጣንም ችግሩ መስተካከሉን ሲያረጋግጥ እንዲከፍቱ ይፈቅድላቸዋል ብለውናል ወ/ሮ ወርቅነሽ፡፡

በተጨማሪም በቁጥጥር ስራው ከ2መቶ ሺህ ብር በላይ ዋጋቸው የተገመተ ምግብና መጠጦችን ባለስልጣኑ የማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ ናቸው ሲል ከገበያ ሰብስቦ ማስወገዱንም ከሃላፊዋ ሰምተናል፡፡
#Tikvah

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ማስተዋል በማስተዋል አልበም ሲሰራ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16087/

(በተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ)

#Ethiopia | በማስተዋል የሚደመጥ አልበም በየዘመኑ እንዲህ አይነት ክስተት ዘፋኞች ብቅ ይላሉ በሙዚቃ መንገድ ታሽቶ የመጣ እንዲህ ያለ የሚስብ አቅም ያደርሰናል፡፡ ማስተዋል እያዩ ያበት ደረጃ ሌላ የሱ ሙዚቃ ዓለም አለው፡ በትዝታ በሀሳብ ላቅ ያለ የማስተዋል የድምፅ እርከን ስፋት ፣ ቀለም ፣ ሬንጅ ፣ የቅኝት ባለቤት ጉሮሮው እንደ ፈለገ የሚተታጠፍ የመሳሰሉት ያየንበት ነው፡፡

አንድ ወዳጄ የፋና ላምሮት ፈርጥ ድምፃዊ ናሆም ነጋሽ ስለዚህ አልበም ስናወራ እንዲህ አለኝ ” ወይን እያደር አይደል የሚጣፍጠው ይህ አልበም እንዲያ ነው ደሞ ከ ጣፈጠ በኃላ ደረጃውም ቦታውም ይልቃል”አለኝ፡፡ ልክ ነው ከልብ ማድመጥ ጆሮ የሚሻ ሙዚቃ እና በአዕምሮዬ ሲዘዋወር የነበረውን ሐሳብ በሙሉ ቋንቋ ገልፆልኛል፡፡

ጠቅላላ ሙዚቃዎች ሲሰሩ በስሜታቸው እና በስልተ ምቱ በአግባቡ መግለፅ ያስፈልጋል ምክንያቱም የሙዚቃ ነፍሱ እሱ ስለ ሆነ ፡፡በነጠላ ሙዚቃዎቹ እና Ep ሙዚቃዎቹ አቅም እና ችሎታውን በሚገባ አሳይቶን ወደ አልበሙ ተከስቶ ታዕምራዊ አልበም ሰቶናል፡፡

‘እዚራ’ አልበም እዚራ አንድ ኢትዮጲያዊ የሆነ የሙዚቃ መሳርያ ነው፡፡ በዚህ ስያሜ መምጣቱ አልበሙን በብዙ መንገድ እንዳስበው አርጎኛል፡፡ በሙዚቃዎቹ ውስጥ ተወዳጁን ማዲንጎ አፈወርቅን እንድናስታውስ የሚደርገን ብሎም አብዛኛው በዜማ የሰራው እራሱ ማስተዋል ሲሆን ይህ ሌላኛው የማዳመጥ ክህሎት የመጣበት የሙዚቃ ደረጃ ምን ያህል እንደሆነ ይነገርናል፡፡የሙዚቃ ቫራይቲ(የተለያየ አይነት ስልት እና ሐሳብ ) ሬጌ ፣ ሱዳኒክ ፣ ትዝታ፣ ፎክ (ባህላዊ የሙዚቃ አዛዝያም)፣የቅኝትሙዚቃዎች ተሰርተዋል፡፡14 የሙዚቃ ክሮች ሲኖሩት ደጉ ትዝታ ፣ መጥቼ ነበር ፣ በምን ቃል፣ ደግሰን ፣ ከፋኝ ፣ እንዚራ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

ከአልበሙ የገረመኝ እና የወደድኳቸው የሙዚቃ ስራዎች ከአብዛኛው ጥቂቱን ልገልፅላችሁ፡፡

“ከፋኝ” (ትዝታ) የተሰኘ ሙዚቃ ሐሳብ የግጥም ውህደቱ ለዚህ ዓለም ጉዞ በሰውኛ አገላለፅ ሌላው መንገድ ሰውኛ እውነትን ሆኖ እዉነትነትን ሳይስት ይናገናል፡፡ በመከፍት በህመም መደራረብ ውስጥ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮች አሉ አብረን የኖርነው መልክ እያየነው ሲጠወልግ ዛሬ ላይ ያሉ ትናንትናዋን ያላወቁ ሰዎች በመልኳ ሲሳለቁ እሱ ግን ቆም ብሎ ትናንት አውቃታለሁ ለዚህ እንኳን ገላጋይ ዳኛ አያስፈልግም እኔ ምስክር ነኝ በምንም በሁሉም የትማርክ ነበረች ጊዜ ጥሏት እንጂ፡፡ግጥም ጥላሁን ሰማው ዜማ አበበ ብርሀኔ ቅንብር ታምሩ አማረ(ቶሚ)

“የማለዳው ለምለም- ውበቷ ቄጤማው
ጠውልጎ አየሁ ዛሬ – ሲፈርድ እድሜ ዳኛው
አወይ ዘመን – ባዳ አቤት ጊዜ ክፉ
ለምልክት እንኳን – አንድ አለ ማትረፉ”…

“(እቴ)” (ሞደርን ፎክ) ባህል ዘመናዊ የተሰኘው ሙዚቃ ቅንብሩ የዘጠዎቹ /ሰባዎቹ ሙዚቃ ቅርፅ እንድናስታውስ ያደርገናል የሙዚቃ ቅንብሮቹ በምክንያት የተሰሩ የማስተዋል የድምፅ እርከን ስፋት በሚገባው የድምፅ ጉልበት የተጠቀመበት ድንቅ ሙዚቃ ፅዱ ማንነት ገለጣ፡፡ ዜማ ምረት አብ ደስታ ግጥም ናትናኤል ግርማቸው ቅንብር ሚካኤል ሀይሉ(ሚኪ ጃኖ)::

“የቆንጆ ፍቅር – እና- ትንታ ያለበት
ሞት ቅርቡ ነው- እና- ውሀ አታርቁበት
ችዬው ልኑር እንጂ – ስራበው ወይ ስጠማሽ
መቼም ሰው አይድንም – ከሐመልማሎ ገላሽ”

“ጉብልዬ(ቅኝት)” የነፀብራቅ ድምፅ የሙዚቃ ጉልበቱ የታየበት የመጀመርያ ቅኝትን መቆጣጠር ፣ ሁለተኛው የእተቀባበሉ መዝፈን ፈተናው እና የውበት ፍሰቱን በመግለፅ ብዙ ነገሩ ስኬታማ አጫዋች ሆኖ ያየንበት ነው፡፡ሐሳቡ ትዝታን ወደ ኃላ እየቃኘ ስለ አንድ ሰው እሱ በሌለበት ወዳጆቹ ሲነጋገሩ ሲጨዋወቱ፡፡ ግጥም ናትናኤል ግርማቸው ዜማ የህዝብ እና መስተዋል እ ቅንብር ሚካኤል ሀይሉ፡፡

”አጋርሽ መሆኑን ሰምቼ ፣ ያ የጥንት ወዳጅሽ ወዳጄ
እቴ ሙች ግራ ነው የገባኝ ፣ ሕይወት እንቆቅልሽ ሆኖ ባይ
እስኪ ግለጪልኝ ይሄን ነገር ፣ ያ ሰው የዛን ጊዜ ምንሽ ነበር”::

“እመጣለሁ” የፍቅር ትርጉም አንዱ አገላለፅ ይህንን አሳብ የተሸከመ ነው፡፡የግጥሙ ሐሳብ የምትወደው ሰው ህመምን መዋዋስ ሳይሆን እመምን ብቻህን መጋፈጥ ለምትጋፈጥበለት ሰው ደስታውን ሁሉ መመልከት ምክንያቱም ፍቅር በስቃይ ይጣፋል እና…ግጥም እና ዜማ አቡዲ ቅንብር ሚካኤል ሀይሉ፡፡

ከጀርባሽም ብሆንም – እንደ ዓይንሽ ልይልሽ
እንቅፋት ሲያይብኝ – እኔ እንድመታልሽ
————
እኔ አንቺን – ስለምወድ ስለምወድ
እመጣለሁ ሂጂ እና – በአንቺ መንገድ

እነዚህ እና የመሳሰሉት ጣዕም ያላቸው ሙዚቃዎች ሰቶናል፡፡ነፍስ እንዲዘራ ደግሞ የሙዚቃ ከያኒያን በዚህ ልክ አጥብቀው ሙዚቃ የሚፈልገውን ስሜት ሰተውታል በቅንብር ብሩክ አፈርቅ ፣ ሚካኤል ሀይሉ(ሚኪ ጃኖ) ፣ ታምሩ አማረ(ቶሚ) በጥግም ዜማ ናትናኤል ግርማቸው ፣ ፍሬዘር አበበ ወርቅ ፣ ማስተዋል እያዩ ፣ አብዲ ፣ጥላሁን ሰማሁ ፣ ታመነ መኮንን ፣ ብሬ ብራይት ፣ እሱባለሁ ይታየሁ( የሺ )፣ አበበ ብርሀኔ ፣ ቢኒያምር አህመድ ፣ አንባቸው እሸቱ፣ ምረት አብ ደስታ ማስተሪንግ ሰለሞን ሀይለማርያም የመሳሰሉ ሰርተውታል፡፡

በዚህ አልበም ላይ እጃችሁ ያሳረፋችሁ ሁሉ በግሌ አመሰግናለሁ
የሙዚቃ ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪዩሪቲስ የመጀመሪያውን የባለአክሲዮኖች ጉባኤ አካሄደ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16089/

#Ethiopia |ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪዩሪቲስ አ.ማ የመጀመሪያውን የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄዱን ዛሬ ይፋ አደረገ። ኩባንያው በዚህ ጉባኤ ላይ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሴኪዩሪቲስ ዲለር (የመዋለ ንዋዮች ገበያ ሰነድ አከናዋኝ) ፈቃድ ማግኘቱንና በቀጣይ አገልግሎት በመስጠት ወደ ትርፋማነት ለመሸጋገር ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

የኩባንያው የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበባው ዘውዴ እንደገለጹት፣ ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪዩሪቲስ በ50 ሚሊዮን ብር የተፈረመ ካፒታልና ከ14.2 ሚሊዮን ብር በላይ በተከፈለ ካፒታል የተመሠረተ ነው። መስራቾቹም በፋይናንስው ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸውና በተለያዩ የባንክ፣ የኢንሹራንስና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የሰሩ እንዲሁም በርካታ ተቋማትን የመሰረቱና በቦርድ አመራርነትም ልምድ ያላቸው 40 ባለአክሲዮኖች ናቸው።

አቶ አበባው አክለውም የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለሴኪዩሪቲስ ዲለርነት የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የካፒታል መጠን 10 ሚሊዮን ብር ቢሆንም፣ ኢትዮ ፊደሊቲ ከዚህ መጠን በላይ በማስመዝገብ ገበያውን መቀላቀሉ የኩባንያውን የፋይናንስ አቅምና ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

ኩባንያው በአዲሱ የካፒታል ገበያ ውስጥ ግንባር ቀደም ተዋናይ ለመሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁንና የባለሥልጣኑን ሕግና መመሪያዎች በመከተል ሙያዊ ሥነ ምግባርን በጠበቀ መልኩ የግብይት ሥርዓቱን ለማሳለጥ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።

በተጨማሪም ኩባንያው የአገልግሎት ተደራሽነቱን በመላ አገሪቱ ለማስፋፋትና ይበልጥ የተቀላጠፈ ለማድረግ ከተለያዩ የግል ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር የቅድመ መግባቢያ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቋል። የደንበኞችን ምዝገባና የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥርዓት ለመዘርጋትም እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል።

በቀጣይነት በካፒታል ገበያው ውስጥ ሊሰጡ የሚችሉ አዋጭ የሆኑ የአገልግሎት ዓይነቶች በዝርዝር ተለይተው ለባለአክሲዮኖች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። የኩባንያው ቦርድ የአይቲና የስትራቴጂ ንዑስ ኮሚቴዎችን በማቋቋም የአመራር ቡድኑን ለመምራትና ለመደገፍ የሶስት ዓመታት ስትራቴጂክ ዕቅድ በመንደፍ ላይ ይገኛል።

ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪዩሪቲስ ቀደም ሲል የነበረውን የአክሲዮን ግብይት ሂደት ጠንቅቆ እንደሚያውቅ በመግለጽ፣ አዲሱ የካፒታል ገበያ ለሁሉም ተሳታፊዎችና ተጠቃሚዎች እኩል ዕድል የሚፈጥር እንደሚሆን ገልጸዋል ። ኩባንያው ከመረጃ አቅርቦት ጀምሮ ገበያው እንዲዳብር ከባለሥልጣኑና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል።

አዲሱ የካፒታል ገበያ ለነባርና ለሚቋቋሙ ኩባንያዎች ምቹ የገበያ አማራጭ በመሆኑ ግንዛቤን መፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት መሆኑን ኩባንያው አፅንኦት ሰጥቷል። በተጨማሪም ወደፊት ቦንድና ሌሎች የፋይናንስ ሰነዶች በገበያው ላይ ሲቀርቡ ለዘርፉ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክቷል።

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
መጪውን የ ፋሲካ በዓል አስሞልክቶ ከ 2,000,000 ብር በላይ ቅናሽ ይጠቀሙ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16091/

ይህ የምስራች ለውድ ደንበኞቻችን ስናቀርብ በታላቅ ደስታ ነው::

📌📌 በ ቁጥር 3ሳይት በሳርስ ዓደይ አበባ B+G+7
የሆነው ህንፃችን ላይ ከረጅም አከፋፈል ጋር እንጠብቆታለን!
ያስተውሉ ብልሆች የ እድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ለውስን ቤቶች ብቻ የቀረበ ዕድል ሞሆኑ ይገንዘቡ!

‘አልቲማ ሪል እስቴት’

“ህልምዎን ይኑሩ!”

“Live Your Dreams!”

ለበለጠ መረጃ :-. ☎️0996000000 / 0995222222

➡️Website: http://www.ultimaet.com

➡️Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61568957484689

➡️Whatsapp: https://whatsapp.com/channel/0029VawOxno545uoGPoLfH3X

➡️Telegram: https://t.me/ultimarealestate1

➡️YouTube: https://www.youtube.com/@UltimaRealestate

➡️ TikTok: tiktok.com/@ultimareal.estate

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የፖፕ ፍራንሲስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በመጪው ቅዳሜ ይፈፀማል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16093/

#Ethiopia | የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በመጪው ቅዳሜ እንደሚከናወን ተገለፀ፡፡

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በትናንትናው ዕለት በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ቫቲካን ማስታወቋ ይታወሳል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት የሚፈጸምበትን ቀን ለመወሰን ካርዲናሎች በዛሬው ዕለት በቫቲካን መምከራቸውም ተገልጿል።

በካርዲናሎች ውሳኔ መሰረት ቫቲካን የፖፕ ፍራንሲስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በመጪው ቅዳሜ እንደሚፈፀም ማስታወቋን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ህልፈት ተከትሎ ቤተ ክርስቲያኗ በቀጣዮቹ ሶስት ሳምንታት ውስጥ አዲስ መሪ እንደምትመርጥ ተገልጿል።

የፖፕ ፍራንሲስ ህልፈት ከተሰማ በኋላ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሃይማኖት መሪዎች፣ የአገር መሪዎች እና ታዋቂ ሰዎች ሐዘናቸውን እና አክብሮታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ጊፍት ሪል ስቴት ከደንበኞች በቀረበልን ጥያቄ ከሚያዚያ 23-26/2017 ዓ.ም. የሚቆይ ታላቅ የሽያጭ መርሃ ግብር ዳግም አዘጋጅተናል።

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16095/

በዚህ መርሃ ግብር ላይ በለገሃር፣ በተክለ ሀይማኖት፣ በ22 ማዞሪያ፣ በሲኤምሲ እና ሌሎች አፓርትመንቶችና የንግድ ሱቆች ቅናሽ ተደርጎባቸው ለሽያጭ ይቀርባሉ፡፡

እርስዎም በዚህ የሽያጭ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ፤ የቤት ባለቤት እንዲሆን በክብር ተጋብዘዋል።

መኖር በጊፍት መንደር።

ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ዛሬ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን ነው!!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16097/

የእናንት ምርጡ መጽሐፍ የትኛው ነው?

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ላይ ያነጣጠር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከሸፈ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16099/

#Ethiopia | የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው በርካታ ወታደራዊ አባላትን ያሳተፈ እንደነበር የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና አስታውቀዋል።

የሀገሪቱ የደህንነት አገልግሎት ተቋማት የሴራው አካል በሆኑ የቡርኪናቢ ወታደሮች እና የታጣቂ ቡድን መሪዎች መካከል የነበረውን ግንኙነት በመጥለፍ የሚገኙበትን ቦታ እና የወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ዝርዝር ሁኔታ እንዳገኙ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ላይ የተሴረው መፈንቅለ መንግሥት በመጀመሪያ ሚያዝያ 8 ቀን ለማካሄድ ታቅዶ እንደነበር ሚኒስትሩ ተናግረዋል ።
#ethioFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የብልት ፈንገስ ኢንፌክሽን በግብረስጋ ግንኙነት ብቻ የሚመጣ አለመሆኑ ተገለፀ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16101/

#Ethiopia | የብልት ፈንገስ ኢንፌክሽን በበርካታ ሴቶች ላይ የሚታይ ችግር ሲሆን በዋናነት ይህ ኢንፌክሽን የሚከሰተው በብልት አካባቢ በአነስተኛ መጠን የሚገኙ ፈንገሶች በብዛት ሲራቡ ነው። በመሆኑም የብልት ማሳከክ በተለይ በሴቶች ላይ በብዛት የሚከሰት ችግር ሲሆን ካልታከሙ ምቾት ከመንሳቱ ባሻገር ለጤና አሳሳቢ ሊሆን ይችላል ሲሉ በማሪስቶፕ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ሀኪም የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ዶ/ር ዘነበ ሹምዬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ይህ የኢንፌክሽን አይነት የሴት ልጅ የውጪኛው መራቢያ አካል ላይ የሚከሰት መታከም የሚችል በሽታ ሲሆን ብዙ ሴቶች በግንዛቤ እጥረት ምክንያት ህክምና ሳያገኙ ይቀራሉ። ኢንፌክሽኑ እንዲከሰት ምክንያት የሚሆነው ፈንገስ ሳንዲዱ አልቤኒካ ተብሎ ይጠራል። በመሆኑም በሴት ልጅ ብልት ውስጥ የተለያዩ ባክቴሪያዎች እና ፈንገሶች የሚኖሩ ሲሆን እነዚህን ባክቴሪያና ፈንገሶች በሚፈለጉት መጠን እስከተገኙ ድረስ የሚጠቅሙ እንጂ ለጉዳት የሚያጋልጡ አይደሉም ሲሉ ገልፀዋል::

የብልት ፈንገስ ኢንፌክሽን በበርካታ ሴቶች ላይ የሚስተዋል በመሆኑ ምልክቶቹም ከፍተኛ የብልት አካባቢ ማሳከክ ፣ ነጭና ወፍራም ፈሳሽ መኖር ፣ ውሃ ሽንት ሲሸኑ ማቃጠል፣ የብልት አካባቢ መቅላት እና መላጥ ናቸው። እንደዚህ አይነት ምልክቶች ሲታዩ በግብረ ስጋ ግንኙነት ብቻ ነው የሚፈጠሩት እና የሚተላለፋት ተብሎ በስህተት በማህበረሰብ ውስጥ የመረዳት ችግር እንዳለም ገልፀዋል።

አንቲባዮቲክ በብዛት መጠቀም በብልት ውስጥ ያሉ ጤናማ ባክቴሪያዎች እንዲሞቱ ምክንያት ሊሆን ይችላል።ይህም በብልት ውስጥ ያሉ ፈንገሶች ከተገቢው መጠን በላይ ተራብተው ለኢንፌክሽን መከሰት ምክንያት እንዲሆኑ መንገድ ይከፍታል። የኢስትሮጂን ሆርሞን መጠናቸው ከፍ ያለ ሴቶች ለብልት ኢንፌክሽን ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ ነው። በዚህም ምክንያት ነፍሰ ጡር ሴቶች እና የኢስትሮጂን መጠኑ ከፍ ያለ የወሊድ መከላከያ የሚወስዱ ሴቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይመከራል ብለዋል።

በተጨማሪም ብልትን ለመታጠብ የሚውሉ የተለያዩ ኬሚካሎችን አለመጠቀም ፣አላስፈላጊ አንቲባዮቲኮችን ከመውሰድ መቆጠብ አስፈላጊ መሆኑን አክለው ተገቢውን ህክምና ካደረጉ ቢታከም ሊድን የሚችል መሆኑን ዶ/ር ዘነበ ሹምዬ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet