Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
5.93K subscribers
2 photos
4.51K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
“…ወለራትዓን ይደልዎሙ ክብር፣ለቅኖች ምስጋና ይገባል።”(መዝ.፴፫፥፩)

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16029/

የምስጋና ሕይወት የሚኖር ሰው የተደረገለትን ሥራ እና የተፈጸመለትን መልካም ነገር ሁሉ የማይረሳ ለዚህም ምስጋናውን በደስታ የሚገልጽ አዋቂ ሰው ነው ይባላል። ለእግዚአብሔር እና ለሰዎች የሚያቀርበው ምስጋና በልቡ ጽላት ላይ ተጽፎ የተቀመጠ በመሆኑ ምስጋና ከአንደበቱ ፈጽሞ ጠፍቶ አያውቅም።

ለተደረገልን ነገር ሁሉ ምስጋን ስናቀርብ እግዚአብሔርን እየባረክን፣ የሰጠንን ፍቅሩንና ትህትናውን እየገለጽን መሆኑም ልንረዳ ይገባል። እግዚአብሔር በምንም በኩል የተለያዩ መልካም ነገሮችን ካደረገልን ከእግዚአብሔር በተጨማሪ እነዚያን መልካም ነገሮች እንድንቀበል ምክንያት ለሆኑ ሰዎች ምስጋና መስጠት ተገቢ ነው።

እንደ እግዚአብሔር ቸርነት በየዓመቱ ላለፉት 29 ዓመታት በትንሣኤ ሌሊት ሰው በየቤቱ ፆሙን ሲፈስክ እኛ በአቃቂ ቃሊቲ በመንበረ ሕይወት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ያደግን ወንድሞች ነዳያንንና (የኔ ቢጤዎችን)፣ አስቀዳሾችን እናስፈስካለን። አቅመ ደካሞችን በየቤታቸው የዶሮና የእንቁላል እንዲገዙ ገንዘብ በመስጠት እና የሕግ ታራሚዎችን በፖሊስ ጣቢያ እየተገኘን ፆም የምናስፈስክበት መርሐ ግብር ዘንድሮም በዚህ መልካም ተግባር ሁሌ በሚተባበሩን ወንድሞችና እህቶች ድጋፍ ደስ በሚል ሁኔታ ተከናውኗል።

በእውነት የሚሰጡ ቅን እጆች ሊመሰገኑ ይገባል፤ የሚሰጡ እጆች የተባረኩ ናቸውና በዚህም መልካም ተግባራቸው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተናገረው በደካማ እጃቸው የሰማይ ቤታቸውን ሠርተዋልና ሊመሠገኑ ይገባል እናንተም የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ቅኖች እንዲበዙ አመስግኑልን ። በዚህ መልካም ተግባር ላይ በገንዘብና በጉልበት ለተሳተፉት ሁሉ ምስጋና እናቀርባለን።

በዚህ በጎ ሥራ የተሳተፉትም:-
⏺️ኮሜርሻል ኖሚኒስን፤ የማነ ብርሃንን፤ገብረ ፃድቅን፤ ኪዳነ ማርያምን አስካለ ሥላሴን ወለተ ሕይወትን ፤ ህንፀተ ድንግልን፤ተከስተ ብርሃንን፤ ወልደ እስጢፋኖስን፤ ወልደ ዮሐንስን፤ መዓዛ ቅዱሳን፤ ገብረ ሕይወትን።

እንዲሁም እነ ምትኩ ልዑልን፣ ኮማንደር ጥላሁን፣ጥላሁን ገረሱና ቤተሰቡ፤ወንደሰን ወርቁን፤ ዶክተር ጌታቸው ድንቁን፣ ቁምላቸው ዘኤልያስ፤ ዮሴፍ ወርቅነህን (ናቲ) ወይንሸት አበበ፤መኮንንወርቅነህ (ሞኬ ፎቶ) የሺእመቤት ደመቀ፤ትእግስት ባዮን፤ ጴጥሮስ ፀጋዬ፣ ዘካሪያስ በሱዬ፣ በድሉ ተሰማ፣ እሙሽ ሳህለ፣ ሀብታሙ አሰፋ፣ ደሳለኝ እና ባለቤቱ፤ ብሩክ ገዛህኝ፣አስኒ፤ አልዓዛር ሻምበል፤ ብሌን ሻምበል ውዷ ባለቤቴ አዜብ ተስፋዬ፤አልማዝ፣ሃና እና ናሆምን፤ እስጢፋኖስ፣ ሱራፌል ፀጋዬ፣ ሐይለ አብ ቶታል፣ የአብ ቃል ጌታሁን፣ ገነት (ፔጊ ) ቴውድሮ ጌታቸው፤ ኮማንደር ሽመልስ፤ ስአሁን ማስታወስ ያልቻልኳችሁ ሁሉ።

ዋጋን የማያስቀረው የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በረድኤት ይጠብቅልን፣ እድሜና ጤና ይስጥልን፣ ከማያልቀው በረከቱ ይስጥልን፤ መልካሙን ዋጋ ይክፈልልን። መርሐ ግብሩን 29 ዓመታት እንድናከናውን እንደቸርነቱ ያበረታን እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን።

በዚህመርሐ ግብር 200 በላይ ነዳያን፣ 120 ታራሚዎች፣ 700 በላይ የሚሆኑ አክፋዮች/ትንሣኤን ያስቀደሱ ምእመናን/ ፆማቸውን የፈሰኩ ሲሆን፤ ለ29 ረጂ ለሌላቸው አቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ ለየአንዳንዳቸው2000 ብር መስጠት ተችሏል። መርሐ ግብሩን በፎቶ ጥቂቱን እናጋራችሁ።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
#እጁን በተወጋው ጎኑ ውስጥ ከተተው

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16031/

ከትንሣኤ በኋላ ያለው ማክሰኞ ቶማስ ተብሎ ይጠራል፡፡ ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ሲሆን በተጣራራሪነቱ ይታወቃል፡፡ በቀዳሚ ስሙ ‘ዲዲሞስ’ ወይም ጨለማ የሚባል ስም ቢኖረውም በኋላ ግን ቶማስ ወይም ፀሐይ ተብሏል፡፡ ቅዱስ ቶማስ ሲጠራ ከሰዱቃውያን ወገን ስለነበር በትንሣኤ ሙታን ከማያምኑት ወገኖቹ የወሰደውን ትምህርት ይዞ ጌታችን ከሙታን በተነሳ ጊዜ እጆቹን ካልዳሰስኩ በጦር የተወጋ ጎኑን ካልነካሁ አላምንም ብሎ ዳሶ ካረጋገጠ በኋላ ግን ጌታዬ አምላኬ ብሎ ሰግዷል፡፡ ቶማስ አንድን ነገር ለመቀበል በቂ እውቀት የሚፈልግ ሲሆን ላመነበት ነገርም ቆራጥ የሆነ ሐዋርያ ነው ። ቶማስ ክርስቶስን መከተል ሞትን እንደሚያስከትል አውቆ ዋጋ ተምኖ የሚጓዝ ከክርስቶስ ጋር ለመሞትም ዝግጁነቱን የገለጠ ፣ ደፍሮ ሌሎችንም በማደፋፈር የታወቀ ሐዋርያ ነው።

ሕይወቱንም አስቀምጦ የተከተለ ነው። በዮሐንስ 11፡16 ጌታ ወደ አልዓዛር መቃብር እንደሚሄድ በተናገረ ጊዜ “ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ”። እመቤታችን ስታርግም ከሁሉም ቀድሞ ያየው ነው፡፡ ወደ ሀገረ ስብከቱ ሕንድ የገባው እንደ ባሪያ በ30 ብር ተሽጦ ነበር፡፡ የገባበት አካባቢ አስተዳዳሪ ሉክዮስ አሳዳሪው ሆኖ በቤቱ ሲያገለግል ምን መሥራት እንደሚችል ሲጠይቀው ሕንፃ ማነጽ ሐውልት መቅረጽ እንደሚችል ስለነገረው ብዙ ወርቅና ብር ሰጥቶ ሰርቶ እንዲጠብቀው ነግሮት የተለየ ጥበብኛ ሰው አገኘሁ ለማለት ወደ ንጉሥ ሄደ፡፡ ቅዱስ ቶማስ ግን ገንዘቡን ለነዳያን መጸወተው በርካቶችንም አስተምሮ አሳምኗቸዋል፡፡ የሉክዮስ ሚስትና ልጆቿ ቤቱ ካሉ አገልጋዮች ጋር ሁሉ አምነው ተጠምቀዋል፡፡

ሉክዮስ ከሄደበት ተመልሶ ሕንጻውንና ሐውልቶቹን ለማየት ቢፈልግም ሐዋርያው በወርቅና በብርህ ያነጽኳቸው ሕንጻዎች እኒህ ናቸው ብሎ ያመኑትን አገልጋዮች አሳየው፡፡ ይህ ክፉ ባሪያ ተጫወተብኝ ብሎ እጅ እግሩን አሥሮ ቆዳውን አስገፍፎ ስልቻ አስፍቶ በአሸዋ መልቶ አሸክሞ በገበያው ሲያዞረው ሚስቱ አርሶንዋ አይታ በድንጋጤ ወድቃ ሞተች፡፡ መስፍኑም ደንግጦ ሚስቴን ካዳንካት እኔም በአምላክህ አምናለሁ አለው፡፡ ጌታ ቁስሉን እንደ ውኃ አቀዝቅዞለት ካለችበት ሄዶ ስልቻውን ቢያስነካት ተነሥታለች በዚህም ሉክዮስ አምኖ ተጠምቋል፡፡ ከዚህም በኋላ ስልቻውን ተሸክሞ ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ ሙት እያነሣ ድውይ እየፈወሰ አሕዛብን አሳምኖ አጠመቀ፡፡ በቀንጦፍያ የተገደሉ የአንድ ሽማግሌ ሰባት ልጆች ስልቻውን እያስነካ አስነሥቶለታል፡፡

በኢናስም የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይተው ከንጉሱ ሚስት ጀምሮ እስከ ተራ ገባር ድረስ ያሉት ሁሉ አምነው ተጠመቁ፡፡ በኋላም የጣኦት ካህናተ በተንኮል ከንጉሥና መኳንንቱ ጋር አጣልተው በሰይፍ አስመትተውታል፡፡ ዛሬም ድረስ ሕንድ ውስጥ በመንበሩ ላይ የጌታችንን የተወጋ ጎኑን የዳሰሰች የቅዱስ ቶማስ ቀኝ ቅድስት እጅ በሕይወት እንዳለች ሆና ትታያለች፡፡ በሕንድ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ፓትርያርክ ሲሾሙም የቅዱስ ቶማስን ቀኝ እጅ በሚሾመው ፓትርያርክ ላይ ጭነው ነው፡፡ ገዳማውያን እናቶችና አባቶች በብዙ ስጋዊ መከራ ውስጥ እንኳን አልፈው በእምነታቸው ጸንተው የክርስቶስን ወንጌል በሕይወታቸው ሰብከው፣ ወንጌልን ኖረው ነው የሚያልፉት፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታችውን እናጽና፡፡

በዓሉን በደስታ ስናሳልፍ በችግር ውስጥ የሚገኙ ገዳማዊያንን በመደገፍ ለነፍሳችንም ስንቅን እንያዝ።

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የሦስት ዘመን ሙዚቃ በሚሌኒየም አዳራሽ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16033/

#Ethiopia | ሽርጉድ ኮንሰርት” የፊታችን ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል

የትኬት ዋጋ 700 ብር፣ 3 ሺህ ብር እና 15 ሺህ ብር ነው ተብሏል።

አለማየሁ ሒርጶ፣ ስለ ኢትዮጵያ እናቶች ያቀነቀነው
አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ ማታ ይለቀቃል

ሦስት ትውልድ በአንድ መድረክ የሚገናኝበትና አለማየሁ ሒርጶና ጎሳዬ ተስፋዬ ከ20 ዓመት በኋላ በአንድ መድረክ የሚያቀነቅኑበት ” ሽርጉድ ኮንሰርት”፣ የፊታችን ቅዳሜ ሚያዚያ 18 ቀን 2017 ዓም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

የኮንሰርቱ አዘጋጅ ሽርጉድ ኢንተርቴይመንት ዛሬ ረፋድ በራማዳ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በኮንሰርቱ ላይ ከ10-13 ሺህ ሰው እንደሚታደም ይጠበቃል፡፡

አንጋፋው ድምጻዊ ኤፍሬም ታምሩ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ፣ አለማየሁ ሒርጶና ሜላት ቀለመወርቅ ነግሰው በሚያመሹበት በዚህ መድረክ፣ ያልተጠበቀ ሰርፕራይዝ አርቲስትን ጨምሮ በርካታ ትዕይንቶች ይታዩበታል ተብሏል፡፡

በኮንሰርቱ ለመታደም መደበኛውና ቀድሞ የሚሸጠው የትኬት ዋጋ 700 ብር፣ በዕለቱ በር ላይ 1 ሺህ ብር፣ ቪአይፒ 3 ሺህ ብር እንዲሁም ቪቪአይፒ ትኬት በ15 ሺህ ብር ለሽያጭ መቅረቡንና ትኬቱንም በቴሌ ብር መግዛት እንደሚቻል ሽርጉድ ኢንተርቴይመንት በጋዜጣዊ መግለጫው አብራርቷል።

ሽርጉድ ኢንተርቴይመንት በውጪው ዓለም የተለመደ ቢሆንም ለአገራችን ግን አዲስ የሆነ ነገር አምጥቻለሁ ያለው “ስፔሻል ቴብል” ሲሆን፤ ይህ አሰራር 5 ሰዎች ሆነው አንድ ጠረጴዛ በ250 ሺህ ብር የሚይዙበትና በጣም የተለየ “ንጉሳዊ መስተንግዶ” የሚያገኙበት አሰራር ነው ብሏል፡፡

በኮንሰርቱ የፀጥታና የደህንነት ችግር የለም ያሉት አዘጋጆቹ፤ ከ250 በላይ ሴኩሪቲ ጋርዶች መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።

ኮንሰርቱን የፊታችን ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ከአመሻሽ 12:00 ጀምሮ ክፍት የሚደረግ ሲሆን፤ ልክ 3:00 ላይ የሙዚቃ ድግሱ እንደሚጀመር ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል፤ ከ19 ዓመታት የስደት ህይወት በኋላ በቅርቡ ወደ እናት አገሩ የተመለሰው አለማየሁ ሒርጶ፣ ስለ ኢትዮጵያ እናቶች ያቀነቀነው አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ ማታ እንደሚለቀቅም ታውቋል።

==
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክ ቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ጊፍት ሪል ስቴት ከደንበኞች በቀረበልን ጥያቄ ከሚያዚያ 23-26/2017 ዓ.ም. የሚቆይ ታላቅ የሽያጭ መርሃ ግብር ዳግም አዘጋጅተናል።

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16035/

በዚህ መርሃ ግብር ላይ በለገሃር፣ በተክለ ሀይማኖት፣ በ22 ማዞሪያ፣ በሲኤምሲ እና ሌሎች አፓርትመንቶችና የንግድ ሱቆች ቅናሽ ተደርጎባቸው ለሽያጭ ይቀርባሉ፡፡

እርስዎም በዚህ የሽያጭ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ፤ የቤት ባለቤት እንዲሆን በክብር ተጋብዘዋል።

መኖር በጊፍት መንደር።

ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የሚገርም አጋጣሚ ሳር ቤት 40% ከፍተኛ ቅናሽ እስከ ዳግማዊ ፋሲካ ብቻ የሚቆይ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16037/

❗️

ይፍጠኑ አዲስ ሳይት ነው ቅናሹ ለ 1 ሳምንት ብቻ የሚቆይ

ባለ 2 መኝታ 91 ካሬ በ 5.8 ሚሊየን ብር ብቻ ሙሉ ለሚከፍል

ባለ 3 መኝታ 130 ካሬ በ 8.3 ሚሊየን ብር ብቻ ሙሉ ለሚከፍል

ሳር ቤት አፍሪካ ህብረት ፊትለፊት

አፍሪካ ህብረት አጠገብ ስለሚገኙ ለዲፕሎማት በዶላር ብቻ የሚከራዩ

ሙሉውን ከከፈሉ በካሬ ከ 64,200 ብር ጀምሮ

ከፍለው እስኪጨርሱ በዶላርም ሆነ በግንባታ እቃዎች ግሽበት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አናደርግም

ቴምር ሪልስቴት

ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ ባላችሁበት ሆናችሁ መግዛት የምትችሉበትን አማራጭ ይዘን ቀርበናል

ለበለጠ መረጃ በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ዋናው ቢሮ ይደውሉ

+251908770077
+251961770077

በዋትሳፕ ለማውራት
https://wa.me/251908770077?text

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
‘አገባሻለሁ’ በማለት ወጣቷን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ6 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16039/

#Ethiopia | በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን በምስራቅ ስልጢ ወረዳ በሰዳጎራ ቀበሌ አካባቢ ታሕሳስ 05 ቀን 2017 ዓ.ም የግል ተበዳይን ‘አገባሻለሁ’ በማለት አታሎ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት መቀጣቱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

አዋል ከይሬ ራመቶ የተባለው ግለሰብ የግል ተበዳይ የሆነችዋን ወጣት ራህመት ጠይብን ‘አገባሻለው’ ብሎ እያታለለ ሰዓቱ እንዲመሽባት ካደረገ በኋላ አስገድዶ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈጸመባት የፖሊስ መምሪያው ለአሐዱ በላከው መረጃ ገልጿል።

ግለሰቡ ተበዳይዋ ላይ ወንጀሉን ፈጽሞባት ጥሏት በመሄዱ ይህን ወንጀል መፈጸሙን የሰሙ ግለሰቦች ለምስራቅ ስልጢ ወረዳ ፖሊስ ጥቆማ ማድረሳቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ፖሊስም በቦታው በመድረስ ተጎጂዋን ለሕክምና በመላክ ስለድርጊቱ አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን በማሰባሰብና ተጠርጣሪውን ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን አፈላልጎ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ማድረጉ ተነግሯል።

ፖሊስም ምርመራ አጣርቶ መዝገብ በማደራጀት ለምስራቅ ስልጤ ወረዳ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበ ሲሆን፤ ዐቃቤ ሕግ ከፖሊስ የቀረበለትን መዝገብ አይቶና ፈትሾ ተከሳሹ በፈጸመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ በመመስረት ለምስራቅ ስልጢ ወረዳ ፍ/ቤት አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱም የቀረበለትን ሴትን ልጅ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ ከተገቢ ማስረጃዎች ጋር አገናዝቦ ከመዘነ በኋላ ተከሳሹ ጥፋተኛ መሆኑን ብይን ሰጥቷል።

በዚህም መሠረት ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን ያርማል ሌሎችን ያስተምራል በማለት፤ ተከሳሽ አወል ከይሬ ራመቶ በ6 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲል የምስራቅ ስልጢ ወረዳ ፖሊስ መምሪያ ሕዝብ ግንኙነት አስታውቋል።
#ahaduRadio
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዓለም አቀፉን የአእምሯዊ ንብረት ቀን በልዩ ትኩረት ሊያከብር ነው

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16041/

(ከዕዝራ እጅጉ)

#Ethiopia | ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፣ ከፈጠራ ባለመብቶች፣ ባለድርሻ አካላትና አጋር ተቋማት ጋር በመሆን ግንዛቤንና የፈጠራ ባህልን ለማጎልበት ብሎም ዘርፉን ለማሳደግ በትብብር በሚከናወኑ ዝግጅቶች የአእምሯዊ ንብረት ቀንን በየአመቱ ያከብራል፡፡

ሚያዝያ 20 እና 21/2017 በሳይንስ ሙዚየም በሚደረገው መርሀ ግብር ለጉዳዩ ቀረቤታ ያላቸው ባለሙያዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡

“IP and music: Feel the beat of IP” በሚል መሪ ቃል በዓሉ ይከበራል።

ይህ ዝግጅት፣ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ባለቤቶችና ማህበራት፣ መገናኛ ብዙኃን፣ የመንግሥት ባለድርሻ አካላትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በሚገኙበት ደመቅ ተደርጎ ይታሰባል፡፡

በዕለቱ የፓናል ውይይት፣ የኪነ-ጥበብ ሥራ፣ አውደ-ርዕይና ሌሎች ዝግጅቶችም ይቀርባሉ፡፡ በሀገራችን የሮያሊቲ ሥርዓት የሚጀመርበት ምዕራፍ ላይ እየተቃረብን ሲሆን በዓሉ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ለሀገር እድገት፤ ሰላምና አብሮነት መጎልበት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚበረታቱበትን አጋጣሚ የሚፈጥር ነው።

የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ለሙዚቃ ኢንዱስትሪ እያበረከተ ያለውን ሚና በዕለቱ እንደሚዘከር ለማወቅ ተችሏል፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ላይ ያነጣጠር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከሸፈ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16043/

#Ethiopia | የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው በርካታ ወታደራዊ አባላትን ያሳተፈ እንደነበር የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና አስታውቀዋል።

የሀገሪቱ የደህንነት አገልግሎት ተቋማት የሴራው አካል በሆኑ የቡርኪናቢ ወታደሮች እና የታጣቂ ቡድን መሪዎች መካከል የነበረውን ግንኙነት በመጥለፍ የሚገኙበትን ቦታ እና የወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ዝርዝር ሁኔታ እንዳገኙ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ላይ የተሴረው መፈንቅለ መንግሥት በመጀመሪያ ሚያዝያ 8 ቀን ለማካሄድ ታቅዶ እንደነበር ሚኒስትሩ ተናግረዋል ።
#ethioFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
#አርብምሽት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16045/

#ደጉያገሬሰው

ተወዳጇ ድምፃዊት #ሰኢዳ_ተስፋዬ(አፋር) ከዚህ ቀደም ለአድማጭ ተመልካች ባደረሰቻቸው #ዞሮዞሮ#ያመራል በተሰኙ ስራዎቿ ተወዳጅነትን አትርፋለች አሁን ደግሞ
#ደጉ ያገሬሰው የተሰኘ ስራዋንአርብ ምሽት ወደናንተ ለማድረስ ዝግጅቷን አጠናቃለች
👇👇👇👇
#Nahomrecordsinc

ይሆንን ጨምሮ በድርጅታችን የሚለቀቁ አዳዲስ የሙዚቃ ስራዎች ሲወጡ ቅድሚያ እንዲደርስዎት የናሆም ሬከርድስን የዩቱብ ቻናል ሠብስክራይ ያድርጉ !
👇👇ሊንኩ እዚህ አለ 👇👇)
ዩቲዩብ 👇 https://YouTube.com/c/NahomRecordsIncMusic
ቴሌግራም 👉 https://t.me/nahomrecords
ቲክቶክ 👇https://www.tiktok.com/@nahom_records_music

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ክልሎች የአእምሮ ሕመም መድኃኒትን በራሳቸውም በጀት እንዲገዙ ለማድረግ አቅጣጫ መቀመጡ ተገለጸ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16047/

#Ethiopia | በኢትዮጵያ ሁሉም ክልሎች በራሳቸው በጀት የአእምሮ ሕመም መድኃኒት እንዲገዙ አቅጣጫ መቀመጡን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሀገሪቱ የተለያዩ መድኃኒቶች እጥረት መኖሩ የሚገለጽ ሲሆን፤ ለአእምሮ ሕመም መድኃኒቶች በይበልጥ የሚሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑ በተደጋጋሚ ይነገራል።

ይህንን ክፍተት በተወሰነ ደረጃ ለመፍታትም ክልሎች በራሳቸው በጀት የአእምሮ ሕመም መድኃኒት እንዲገዙ አቅጣጫ መቀመጡን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

በጤና ሚኒስቴር የተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና የአእምሮ ጤና ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ሶፊያ ሰዒድ እንደገለጹት፤ በሌሎች ሕመሞች የመድኃኒት አቅርቦት ላይ እንዳለው ችግር ሁሉ በአዕምሮ ሕመም ላይ እጥረት አለ፡፡

ይህም የመድሃኒት እጥረት ሌላው የሚኒስቴሩ ተግዳሮት መሆኑን አንስተዋል።

ለዚህም በተለይም ክልሎች ለአዕምሮ ሕመመም የሚውሉ መድኃኒቶችን ትኩረት በመስጠት በራሳቸው በጀት እንዲገዙ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።

በተጨማሪም ከጤና ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ከሚሰሩ አካላት ጋር በጋራ በመሆን፤ የመድኃኒት ፍላጎቱን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአንጻሩ የተያዘው የብሔራዊ አዕምሮ ስትራቴጂ እቅድ የአዕምሮ ሕመም መድኃኒቶች በነጻ የሚሰጡበት ሁኔታ እንዳለ የሚያመላክት ቢሆንም፤ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ያንን ማድረግ አለመቻሉን ገልጸዋል።
#ahaduRadio
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ጳጳስ ፍራንሲስን ሰኔ 22ቀን 2014 ዓ.ም.የተናገሩት መንፈሳዊ ኑዛዜ ታትሟል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16049/

እንዲህም ይላል;

#Ethiopia | የምድራዊ ህይወቴ ድንግዝግዝታ እየቀረበ እንደሆነ እየተሰማኝ እና ለዘላለማዊ ህይወት ጽኑ ተስፋ እያደረግሁ፣ ስለቀብሬ ቦታ ብቻ የሚመለከቱ የመጨረሻ ምኞቶቼን ላስቀምጥ እወዳለሁ።

በህይወቴ በሙሉ እና እንደ ቄስ እና ጳጳስ ባገለገልኩባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ ሁልጊዜም ጌታችን እናቱን፣ የተባረከችውን ድንግል ማርያምን ታምኜያለሁ። በዚህ ምክንያት፣ አስከሬኔ – የትንሳኤን ቀን በመጠባበቅ – በሳንታ ማሪያ ማጆሬ የጳጳሳት ባሲሊካ ውስጥ እንዲያርፍ እጠይቃለሁ።

የመጨረሻው የምድራዊ ጉዞዬ በዚህ ጥንታዊ የማርያም ቤተመቅደስ ውስጥ እንዲጠናቀቅ እፈልጋለሁ፣

ሐዋርያዊ ጉዞዬ መጀመሪያ እና መጨረሻ ላይ ለማምለክ ሁልጊዜም እቆምበት የነበረው፣ ዓላማዬን ለንጽሕተ ንጽሕት እናት በአስተማማኝ ሁኔታ አደራ እየሰጠሁ እና ለእናትነት እንክብካቤዋ እያመሰገንኳት ነው።

መቃብሬ በጳውሎስ ጸሎት ቤት (የሳሉስ ፖፑሊ ሮማኒ ጸሎት ቤት) እና በባሲሊካው የስፎርዛ ጸሎት ቤት መካከል ባለው የጎን መተላለፊያ ውስጥ ባለው የመቃብር ጎጆ ውስጥ እንዲዘጋጅ እጠይቃለሁ።
#fidelPost
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የጤና ባለሙያዎች የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ተቋም በኢትዮጵያ ስራ ጀመረ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16051/

#Ethiopia | በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ላለፉት አስር ዓመታት የጎላ አስተዋጽኦ ሲያበረክት የቆየው ድሮጋ ፋርማ አስረኛ አመት የምስረታ በዓሉን በአከበረበት መርሐግብር ላይ እንደገለጸው በአይነቱ ልዩ የሆነ “የጤና ባለሙያዎች ሀገር ዓቀፍ የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ተቋም” መመስረቱን አበሰረ።

የድሮጋ ፋርማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ተካ እንደተናገሩት “የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ተቋም የጤና ባለሙያዎች የቤትና የመኪና ግዢን እንዲያመቻች እንዲሁም የሕክምና ተቋም ወይም ፋርማሲ ለመክፈት ሲያስቡ የገንዘብ እጥረት እንዳይገጥማቸው በማድረግ ህልማቸውን እንዲያሳኩ ይረዳል” ብለዋል።

ድሮጋ ፋርማ ባለፉት አስር ዓመታት በመድኃኒትና የህክምና ግብዓቶች አቅርቦት፣ በፊዚዮቴራፒ አገልግሎት መስጠት፣ በውጭ ንግድ፣ ጥራት ያለው የመድኃኒት ምርመራና ምዝገባ እንዲሁም በመንግስት ጨረታዎች ላይ በመሳተፍ ጉልህ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል። በተለይም በአራት የአዲስ አበባ አቅጣጫዎች የፊዚዮቴራፒ አገልግሎት መስጠታቸውንና ቀበና አካባቢ የሚገኘው የህጻናት ልዩ የፊዚዮቴራፒ ማዕከል በአይነቱ በግል ዘርፍ የመጀመሪያው መሆኑን አንስተዋል።

በተጨማሪም ድርጅቱ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በደብረ ብርሃን ለቆዳ ህክምና የሚውሉ መድኃኒቶችን የሚያመርት ፋብሪካ በመገንባት ላይ መሆኑንና ይህም ፋብሪካ ሲጠናቀቅ ሀገርን ከመድኃኒት እራስን ለመቻል ከማገዙም በላይ ለውጭ ገበያ ምርቶችን በመላክ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል። በቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፓርክ እየተገነባ ያለው የድሮጋ ጥናትና ምርምር ማዕከል በኢትዮጵያ የመድኃኒት ምርምር ዘርፍ የመጀመሪያው መሆኑም ጠቅሰዋል።

የድሮጋ ፋርማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አቢዲ ኤርሞሎ በበኩላቸው ድርጅቱ በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍም በርካታ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸው በኢትዮጵያ የጤና መድን ሽፋን ውስንነትን በመገንዘብ ዋስ ኢንሹራንስ አ.ማ. (በምስረታ ላይ) የተባለ የኢንሹራንስ ኩባንያ በመመስረት የመጨረሻውን የብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ለሚቀጥሉት ዓመታት ድሮጋ ፋርማ በርካታ ዕቅዶች እንዳሉት የገለጹ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የጤና መድን ሽፋን ማስፋፋት፣ የድሮጋ ፋርማሲ ቅርንጫፎችን ወደ 1000 ማሳደግ፣ ተጨማሪ የፊዚዮቴራፒ ማዕከላትን መክፈትና በምስራቅ አፍሪካ ቅርንጫፎችን ማስፋፋት እንደሚገኙበት አመልክተዋል።

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ለትንሳኤ በዓል 5 ሺ 756 እንስሳት እርድ መከናወኑ ተገለጸ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16053/

#Ethiopia | ባለፈው እሁድ ሚያዝያ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በተከበረው የትንሳኤ በዓል ላይ ወደ 6 ሺሕ 500 እንስሳት ይታረዳሉ ተብሎ ታቅዶ የነበረ ሲሆን፤ 5 ሺ 756 እንስሳት እርድ መፈጸሙን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታውቋል፡፡

በዚህም ድርጅቱ የእቅዱን 86 ነጥብ 6 በመቶ ማከናወን መቻሉን የድርጅቱ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል ለአሐዱ ተናግረዋል።

ከእነዚህም ውስጥ 3 ሺ 200 የሚሆኑት የከብት ዘሮች ትላልቅ እንስሳት ሲሆኑ፤ እንደ በግና ፍየል አይነቶች ትናንሽ እንስሳት ደግሞ 2 ሺ 547 መሆናቸውን ገልጸዋል።

5 ሺ 756ቱም እንስሳት በዋናው የእንስሳት ማረጃ ቦታ “ቄራ” እና አቃቂ ቅርንጫፍ በሚገኘው ቦታ እንዲታረዱ መደረጉንም አስታውቀዋል።

በድርጅቱ ሱቆች በኩል የሚደረጉ ግብይቶችን በተመለከተም ተመጣጣኝና የአገልግሎት ክፍያ ብቻ እንደሚያስከፍሉ አንስተዋል።

“በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የታረዱ እንስሳትን ተረፈ ሥጋ ወደ ተረፈ ምርት የመቀየር ሥራ በጥሩ ሁኔታ ተከናውኗል” ሲሉም ገልጸዋል።
#Addisinsider
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የ10 ዓመቱን ጃፓናዊውን ተማሪ በስለት የገደለው ቻይናዊ በሞት ተቀጣ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16055/

#Ethiopia | ቻይና ባለፈው መስከረም ወር የ10 ዓመቱን ጃፓናዊ ታዳጊ በስለት ወግቶ የገደለውን ግለሰብ በሞት መቅጣቷን በቻይና የሚገኘው የጃፓን ኤምባሲ አስታውቋል።

በደቡብ ምሥራቃዊ ቻይና ሼንዘን ከተማ ወደሚገኝ የጃፓን ትምህርት ቤት ሲሄድ የነበረውን ታዳጊ በማጥቃት ዦንግ ቻንግቹን በጥር ወር የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል።

ጉዳዩ የጥላቻ ጥቃት መሆኑን በቀረበበት ክስ የተገለጨ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ዘንድ አስደንጋጭ ውዝግብ እና ዲፕሎማሲያዊ ውጥረቶችን እንዲጨምር አድርጓል። የጃፓን መንግስት የንፁህ ህጻን ግድያ ይቅር የማይባል ወንጀል እንደሆነ መናገሩ ይታወሳል።

ከዚህ ክስተት አንፃር የጃፓን መንግስት ሁሉንም የደህንነት እርምጃዎች መውሰዱን ይቀጥላል እንዲሁም የቻይና መንግስይ በቻይና ውስጥ የሚገኙ የጃፓን ዜጎችን ደህንነት እንዲያረጋግጥ አጥብቆ ያሳስባል ብሏል።

ክስተቱ በቻይና በሚኖሩ ጃፓናውያን ዘንድ ፍራቻ እንዲጨምር ያደረገ ሲሆን ቶዮታን ጨምሮ የጃፓን ኩባንያዎች ሰራተኞቻቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ሌሎች፣ ልክ እንደ ፓናሶኒክ ያሉ ኩባንያዎች ደግሞ በቻይና ለሚኖሩ ሰራተኞቻቸው ወደ ጃፓን መመለስ ከፈለሁ ነፃ በረራ አቅርበዋል።ክስተቱ በቻይና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚታየው ያልተገታ ብሔርተኝነት ነው በሚል ተተችቷል ፣ይህም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ፀረ-የውጪ ዜጎች አቋም እንዲጨምር አድርጓል።

የትምህርት ቤቱ ልጅ ግድያ የተፈፀመው በፖለቲካዊ ስሜት በተሞላበት ቀን ሴፕቴምበር 18 ሲሆን ይህም በ 1930 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ጃፓን ቻይናን በመውጋት ማንቹሪያን የተቆጣጠረችበት እለት ነው። የታሪክ ቅሬታዎች በቻይና እና በጃፓን መካከል ያለውን የፖለቲካ ውጥረት ለረጅም ጊዜ እንዲሻክር አድርጓል።

ቻይና በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ እና አጋማሽ ላይ በጃፓን ለደረሰባት የቅኝ ግዛት እና የጦርነት ጥቃት ጃፓን ይቅርታ እንድትጠይቅ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ስትወተውት ቆይታለች። ጃፓን በቻይና የፈፀመችውን ጭካኔ የተሞላበት ወታደራዊ ርምጃ በታሪክ መፅሃፍቷ ላይ ጎልቶ ይታያል ስትል ወንጅላለች።
#BisratFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በመዲናዋ ሰርግን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ የሚፈጽሙ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል – ፖሊስ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16057/

#Ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ በዓላትና ሰርግን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ የሚፈጽሙ መንገድ የሚዘጉ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ።

ሕብረተሰቡ የጸጥታ አካላት የሚያስተላልፉትን የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶች በአግባቡ እየተገበረ መሆኑን ተከትሎ በከተማዋ የወንጀል ድርጊቶች እየቀነሱ መምጣታቸውንም ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንዳሉት፣ በከተማዋ የትንሳኤ በዓል በሰላማዊ ሁኔታ ተከብሯል።

ቀላል ከሚባሉ የስርቆትና የማጭበርበር ድርጊቶች ውጪ በዓሉን ተከትሎ ውስብስብና ከባድ የወንጀል ድርጊቶች አለመፈጸማቸውንም አመልክተዋል።

ለዚህ ደግሞ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በአግባቡ በመተግበሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መጪውን የሰርግ ወራት ተከትሎ በከተማዋ የትራፊክ ፍሰት ላይ ያልተገባ የመንገድ መጨናነቅ የሚፈጽሙ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

ከተማዋን በማይመጥን መልኩ መንገድ በሚዘጉና የትራፊክ ፍሰቱን በሚያስተጓጉሉ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ እና ኬንያ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ሰረዙ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16059/

#Ethiopia | የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ በናይሮቢ እና በአዲስ አበባ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት መሰረዛቸው ተሰምቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት የሰረዙት፤ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለአምስት ቀናት በቻይና ጉብኝት ለማድረግ ወደ ቤጂንግ ካቀኑ ከሰዓታት በኋላ መሆኑ ነው የተገለጸው።

እንደ አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዘገባ ከሆነ የሩቢዮ የመጀመሪያው የአፍሪካ ጉብኝት ‘በደህንነት እና የንግድ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደርጋል’ ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም፤ ጉብኝቱ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ሩቶ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ዋሽንግተንን ሊጎበኙ ይችላሉ ተብሏል፡፡

በቻይና ጉብኝታቸው ዛሬ የጀመረው የኬንያው ፕሬዚደንት ዊልያም ሩቶ፤ የአሜሪካ ታሪፍ የዓለም ንግድን ካቋረጠ ወዲህ ቤጂንግን የጎበኙ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ሆነዋል።

የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በጣለው የንግድ ታሪፍ ከተጎዱ 185 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ እና ኬንያ ይገኙበታል።

ከመጋቢት ወር መጨረሻ ጀምሮ የ10 በመቶ የመነሻ ታሪፍ ከእነዚህ አገሮች ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሁሉም ምርቶች ላይ ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል።

የትራምፕ የ10 በመቶ ቀረጥ “የመጀመሪያ ታሪፍ” ተብሎ የተገለጸም ሲሆን፣ ይህ ማለት አሜሪካ ባለፉት ዓመታት ‘ኢኮኖሚዋን ተጠቅመዋል’ ብላ ለምታምንባቸው አገሮች ተጨማሪ ታሪፍ ይኖራል የሚል ግምትን አስሰጥቷል።

ይህንንም ተከትሎ አሜሪካ የጣለችውን አዲስ ታሪፍ ከቻይና በስተቀር ባሉ አገሮች ላይ የተፈጻሚነት ጊዜውን ለ90 ቀናት ማራዘሟን አስታውቃለች፡፡

አዲሱ ዝቅተኛ ታሪፍ ከኬንያ ወደ አሜሪካ የሚላኩ ምርቶች በሙሉ የኮታና የቀረጥ ነፃ ዕድል (አጎዋ)ሥር ያሉ ምርቶችን ጨምሮ፤ ኬንያ ከ50 በመቶ በላይ እቃዎቿን ከቀረጥ ነጻ ወደ አሜሪካ እንድትልክ አስችሏታል።

ይህም 25 ዓመታትን ያስቆጠረው የአፍሪካ አገራትን ከቀረጥ ነፃ የሚያደርጋቸው አጎዋ፤ በአዲሱ የታሪፍ ተመን መሰረት የአፍሪካ አገራት ከዕድሉ ውጭ እንደሚያደርጋቸው ተዘግቧል፡፡

በዚህ የንግድ ጉዳይ እና በደህንነት ጉዳዮች ላይ ለመወያየት በመጀመሪያ ወደ ናይሮቢ በማምራት ከዛም ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ የተገለጸው ማርክ ሩቢዮ፤ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በቻይና ጉብኝት ለማድረግ ወደ ቤጂንግ ማቅናታቸውን ተከትሎ ጉብኝታቸውን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘማቸው ተነግሯል።
#ahaduRadio
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የብዙ ሰዎች “ጀምሮ የመጨረስ” ጥያቄ!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16061/

#Ethiopia | የማከናውናቸው ተግባሮችና ስራዎች በርካታ በመሆናቸው፣ እነዚህን ተግባሮች ለመጀመር እንዴት መነሳሳቱን (motivation) እንደማገኝ፣ እንዲሁም በምን አይነት ዲሲፕሊን እንደምቀጥልና እንደምጨርስ ከልምምዴ በመነሳት እንዳጋራቸው የሚጠይቁኝ ተከታታዮች በርካታ ናቸው፡፡

እነዚህ ጥያቄዎች ሲጨመቁ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡-

1. አንድን ያሰቡትን ነገር መጀመር እንዴት ይቻላል? (ይህ የmotivation ጥያቄ ነው)

2. አንድን የጀመሩትን ነገር እንዴት ካለማቋረጥ መቀጠል ይቻላል? (ይህ የdiscipline ጥያቄ ነው)

3. አንድን የቀጠሉትን ነገር ታስቦ በተጀመረበት ጥራትና ብቃት እንዴት መጨረስ ይቻላል? (ይህ የfocus ጥያቄ ነው)

ከእነዚህ ተያያዥ ጥያቄዎች በመነሳት . . .

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”) የተሰኝ ለአራት ቀናት ብቻ የሚቆይ አጭር ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16063/

#Ethiopia | በኦሮሚያ ክልል ከሚያዝያ 6 እስከ ሚያዝያ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ11 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ12ሰዎች ላይ ከባድ በ7 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ አደጋ ከ6 እስከ 45 ዓመት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ የሆኑት ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራትሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

አብዛኞዎቹ አደጋዎቹ የተከሰቱት በቀኑ እና በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ሲሆን አደጋውን ያደረሱት ወንድ አሽከርካሪዎች ናቸው። አደጋዎቹ በተለያዩ ዞኖች እና ከተሞች የተከሰቱ ናቸው።

የሞት አደጋዎች የደረሱት በጭነት፣ በህዝብ ማመላለሻ ፣በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ) እና በሞተር ሳይክል የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የአደጋዎቹ መንስኤዎቹ ያለመንጃ ፍቃድ ማሽከርከር፣ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር እና ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት መሆኑን ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል::

#ዳጉ_ጆርናል
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የ60 ዓመት ጓረቤቱን በጨለማ በር ሰብሮ በመግባት አስገድዶ የደፈረው ግለሠብ በእስራት ተቀጣ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16065/

#Ethiopia | በምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ ውስጥ የስልሣ ዓመት ጓረቤቱን ጨለማ ተገን በማድረግ በራቸውን ሠብሮ በመግባት የመድፈር ጥቃት የፈፀመው ግለሠብ በእስራት መቀጣቱ የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ አስታውቋል።

የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሉጌታ ጭምዲ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት ተከሣሽ ተስፋዬ ፍቃዱ የተባለው የሀያ አምስት ዓመት ወጣት ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ የቤታቸው በር ዘግተው የተኙትን የስልሣ አመት ጎረቤቱን በር ሠብሮ በመግባት የመድፈር ጥቃት መፈጸሙ ተገልጿል ። ግለሰቡ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ለመሰወር ሲሞክር ጥቃት የደረሠባቸው አዛውንት ባሰሙት ጩኸት በቁጥጥር ሊውል ችሏል።

ፖሊስም በቁጥጥር ስር በዋለው ግለሠብ ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማጠናከር ለዓቃቢ ሕግ ያቀረበ ሲሆን አቃቢ ሕግም በወንጀል ሕግ ቁጥር 620 ንዑስ አንቀፅ ሶስት መሠረት ክስ መስርቷል ። የተመሰረተውን ክስ ሲከታተል የቆየው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሚያዝያ 8 ቀን 2017ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሣሽ ተስፋዬ ፍቃዱ በእድሜ የገፉ እና እናቱ በሚሆኑ ላይ መከላከል በማይችሉበት ምሽት ላይ የመድፈር ጥቃት መፈፀሙ ነውረኛነቱን የሚገልፅ በመሆኑና ይሕም በበቂ ማስረጃ በመረጋገጡ በአምስት ዓመት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ሙጌታ ጭምዲ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

#ዳጉ_ጆርናል

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካዛንቺስን የኮሪደር ልማት በይፋ መረቁ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16067/

#Ethiopia | ከተሞቻችንን የማዘመን ሰፊ ጥረት አይነተኛ ማሳያ የሆነውን በካዛንቺስ ያለዉን የኮሪደር ልማት ክፍል በይፋ መርቀናል።

የተጎሳቆሉ እና በእጅጉ የተጎዱ ቤቶች እና ከባቢ መገኛ የነበረው ካዛንቺስ ዛሬ የጋራ ጥረት እና ለውጥ ሽልማታችን ሆኖ ተገኝቷል።

ከዚሁ አካባቢ ተነስተው ለማኅበረሰባችን የከበረ የኑሮ ሁኔታን ለመፍጠር ያለንን ፅኑ እምነት እና ተግባር በሚያሳይ አኳኋን ለኑሮ ወደ ተሻለ ከባቢ የተዛወሩትን ነዋሪዎች ከጥቂት ቀናት በፊት ጎብኝተን ነበር። የተዛወሩበት ከባቢ እጅግ ምቹ መሆኑን አይተናል። ዛሬ ደግሞ የተነሱበትን ሰፈር ድንቅ የኮሪደር ልማት ሥራ መርቀናል።

በአስደናቂ አጭር ጊዜ የተጠናቀቀው የካዛንቺስ ለውጥ ለዘመነ ከተማ ልማት ሥራችን ለአረንጓዴ፣ ንፁህ እና ዘመናዊ የከተማ ማዕከላት ያለንን ርዕይ ግዘፍ ነስቶ በማሳየት መሠረት የሚጥል ነው። በዚህ ግዝፈት የሚከወኑ ሥራዎች ሰፋ ያለ ጥረት ይሻሉ። ጊዜያዊ ምቾት የሚነሱ ፈተናዎችንም ሊያስከትሉ ይችላሉ። ነገር ግን ለታላቁ የሀገር ጥቅም የሚከፈሉ አስፈላጊ መስዋዕትነቶች ናቸው። ይኽ የእድገት መንገድ መቀጠል ያለበት ነው። የታደሰ ተስፋ ይሰጣልና። በተለይ ለልጆቻችን ነገ።
#etv
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet