Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
5.81K subscribers
2 photos
4.46K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
በተጠባቂው የቦስተን ማራቶን ኬንያዊያን በሁለቱም ፆታ አሸናፊ ሆኑ(በወንዶች)

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/15979/

📌

📌ጆን ኮርዬር የቦስተንን ማራቶን በማሸነፍ የወንድሙን ታሪክ ደግሟል

📌በቦስተን ማራቶን(በወንዶች)

👉ኬንያዊው ጆን ኮሪዬር(2:04:45)በመግባት አሸናፊ ሆኗል

👉ከ13 ዓመት በኃላ ወንድሙ በቦስተን ማራቶን የሠራውን ገድል ደግሞታል

👉 ወንድሙ ዌስሊይ ኮሪዬር በ2012 የቦስተን ማራቶንን(2:12:40)በመግባት ማሸነፉ ይታወሳል።

👉የ28 ዓመቱ ጆን ኮርዬር ማሸነፉን ተከትሎ የቦስተን ማራቶንን በማሸነፍ ታሪክ የሠሩ ወንድማማቾች ሆነው በታሪክ ተመዝግበዋል።

👉ኬንያዊው ጆን ኮሪዬር ውድድሩን በአሸናፊነት በማጠናቀቁ 150ሺ ዶላር ወደ ካዝናው ይከታል።

👉ኢትዮጵያዊው ሙክታር እድሪስ አምስተኛ በመውጣት ትልቅ ውጤት አስመዝግቧል

👉የአምናው የውድድሩ አሸናፊ የሆነው ሲሳይ ለማ ውድድሩን አቋርጦ ወጥቷል።

📌በቦስተን ማራቶን(በሴቶች)

👉129ኛው የቦስተን ማራቶን በሴቶችም ድሉ ወደ ኬንያ ሄዷል፤ኬንያዊቷ አትሌት ሻሮን ሎከዲ 2:17:22 በመግባት አሸናፊ ሆናለች።

👉ኬንያዊቷ አትሌት ሻሮን ሎከዲ በውድድሩ ከማሸነፍ በዘለለ የቦታውን ሠዓት በ2 ደቂቃ በማሻሻል አዲስ ክብረወሠን አስመዝግባለች፤2:19:59 የነበረውን የቀድሞ የአሸናፊነት ሪከርድ 2:17:20 በመግባት በ2 ደቂቃ አሻሽላለች።

👉ለሶስተኛ ጊዜ በተከታታይ በማሸነፍ ከኢትዮጵያዊቷ ፋጡማ ሮባ ጋር የታሪክ ተጋሪ ትሆናለች ተብላ የተጠበቀችው ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ 2:17:41 በመግባት ሁለተኛ ወጥታለች።

👉ኢትዮጵያዊቷ የአለምዘርፍ የኋላ 2:18:06 በመግባት ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች።

👉የ129 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ የሆነው ተጠባቂው የቦስተን ማራቶን በወንዶችም በሴቶችም በኬንያዊያን ኮሪዬር አሸናፊነት ተጠናቋል።

📌የቦስተን ማራቶን ወንዶች ከ1-3
1.ጆን ኮሪዬር(ኬንያ) 2:04:45
2.አልፎንሴ ፊሊክስ(ታንዛኒያ) 2:05:04
3.ሳይብሪያን ኮቱት(ኬንያ) 2:05:04

📌የቦስተን ማራቶን ሴቶች ከ1-3

1.ሻሮን ሎኮዲ(ኬንያ) 2:17:22
2.ሄለን ኦቢሪ(ኬንያ) 2:17:41
3.የአለምዘርፍ የኃላው(ኢትዮጵያ)2:18:06

✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ልጄን የማሳድግበት ሥራዬን ታደጉልኝ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/15981/

🙏🙏

በሀገር ውስጥም በውጭም ያላይሁ እንኳን ለጌታችን መድኅኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ አደረሳችሁ።

በማርያም ሥራ አሰሩኝ🙏

#Ethiopia | Abraham Tsegaye አባላለሁ። ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ነበርኩ። You gar have to run here and there to fight and overcome life’s struggles. በመንግስት ሠራተኛነት፣ በክሊኒክ ውስጥ (Psychologist) ፣ በመምህርነት፣ ብሎም በተለያዩ የግል ሥራዎች፥ ሥዕል፣ ቅርፃቅርፅ፣ ሀውልት እና አብዛኛው የኪነጥበብ ሥራዎች እሰራ ነበር። (As most of ya recognise me here on fb with my previous deeds.)

እናም አሁን አምላክ ፈቅዶ ለብዙ ጊዜ የምመኘውን የምወደውን የ furniture ሥራ እየሰራሁ እገኛለሁ። ምክንያቱም የሕይወት ትንቅንቋ አሁን ላይ እጅግ እየከረረ ነው። ሥራዬን የጀመርኩ ሰሞን ደህና ነበር። አነሰም በዛ እንቀሳቀሳለሁ። ኋላ ቆይቶ ኼድ መለስ ይላል። እየተከፋን እየተደሰትን እየደነገጥንም አለን። የሥራው ባህሪ ነው።

But now a days its a bit Scarry , ያስደነግጣል። አንደኛ almost ለ 3ወራት ያህል ያለ ትዕዛዝ ነው ያለሁት። የምሰራው ኮንዶሚኒዬም ላይ ነው እና መብራት አይሰጡም። የምጠቀመው ጀኔነተር በተደጋጋሚ ይበላሻል ይባስ ሶስት ማሽኖች ተቃጠሉብኝ። እነዚህን እንደምንም ገዝቼ ተካሁ። አሁን ላይ ግን አቅም አሳጡኝ። ከጥቃቅን ሥራዎች ውጪ ትዕዛዝ ጠፋ። ሥራው ደግሞ ፉክክር እና capital ይጠይቃል። ለጊዜው የcapital ጉዳይ ሥራዬን እያጎሳቆለብኝ ነው። የምወደውን ሥራዬን እያየሁት እየመነመነብኝ ነው። የልጄን ነገ ሳስብ ብርክ ይይዘኛል። በጣም ይጨንቃል። Somehow I precisely know that መተማመኛዬ የድንግል ልጅ አ-ይ-ጥ-ለ-ኝ-ም።

እናም ዛሬ እርዳታችሁን እሻለሁ። ታድያ ይህ እርዳታ የገንዘብ አ-ይ-ደ-ለ-ም!! ከማንም የእኔ ያልሆነ ገንዘብ እየጠየክሁ አይደለም። ሥራ ልሥራላችሁ እና ክፈሉኝ🙏 ምናልባት ከሆነም አቅም ካላቸው ፈቃደኛ ከሆኑ ግለሰቦች እና ተቋማት ብድር ካገኘሁ🙏

እና በሌላ መልኩ ልታግዙኝ ትችላላችሁ፦

#1 ሼር

#2 ይህንን ሀሳቤን copy paste በማድረግ ዳግም በግል ገፃችሁ በመፖሰት

#3 ለማስተዋወቅ(ማስታወቅያ ለመስራት) አቅም ያላቸው ሰዎችን ሜንሺን በማድረግ

#4 በሀሳብ አልያም በሌላ መልኩ ልያግዙ የሚችሉ ተፅእኖ ፈጣሪዎችን #mention በማድረግ

👉#5 More specifically — በCapital ደረጃ አቅም ያላቸው ድርጅቶች አልያም ልበ ቀናዎች ሕጋዊ በሆነ መልኩ ተበድሬ ሰርቼ የምመልስበትን ሁኔታ ብትመሩኝ።

እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን በማድረግ ልትተባበሩኝ አብሮነታችሁን ልታሳዩኝ ትችላላችሁ። ይህን ሥራዬን አብዝቼ እወደዋለሁ። ስለልጄ ስለሥራዬም እጅግ ብዙ ዋጋ ከፍያለሁ። እ-ጅ-ግ በ-ጣ-ም ብዙ ውጣ ውረጆችን አሳልፍያለሁ። አሁንም ይህን አልፈዋለሁ። በተለያዩ ምክንያቶች ሥራዬ እየተመናመነ ነው። ልጄን የማሳድግበትን ሥራዬን ዳግም ተንሰራርቶ በደስታ እንደምንገናኝ ዋስትናዬ መተማመኛዬ የድንግል ልጅ ክርስቶስ ነው።

ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ አልያም ለራሳችሁም ቢሆን ማንኛውንም የፈርኒቸር እና የብረት ሥራዎችን ትዕዛዝ ብቀበል ዳግም ሥራዬን አነሳዋለሁ። (አብረን)

ሶፋ
አልጋ (የልጅ /የአዋቂ)
ቁምሳጥን
ወንበር
Doors/Window
ጠረጴዛ
Tv Stand
Kitchen Cabinet
Metal works
Home Decore
+
የሥዕል ሥራ
የሐውልት ሥራ

እነዚህን ለማዘዝ አልያም ቀብድ ለመክፈል

100028 45 09 998 –(CBE)
Abraham Tsegaye Abera

ዳግም በሥራ እንገናኛለን አብረን እናድጋለን።
ቸር ያቆየን።

ማንኛውም ሀሳብ አልያም የመፍትሔ ጥቆማ ካለ በ inbox አልያም

I am available via

09 25 50 71 56
09 01 85 35 84
abrahamtsegaye25@gmail.com

Gethsemane መና (Mena) Furniture
ጌቴሴማኒ (መና ) ፈርኒቸር!

ቸር ያቆየን
ክፉ አያግኘን
ዳግም በሥራ ያገናኘን

🙏

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በወልቂጤ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ግንባታ እየተፋጠነ ነው – አስተዳደሩ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/15983/

#Ethiopia | በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

በከተማዋ የኮሪደር ልማት ሥራው እንዲጠናከር ልማቱ በሚከናወንበት አካባቢ ንብረታቸውን በማንሳትና ይዞታቸውን በመልቀቅ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ሙራድ ከድር ለኢዜአ እንደገለጹት በከተማዋ 25 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ሥራ በመፋጠን ላይ ይገኛል።

የኮሪደር ልማቱም በወልቂጤ ከተማ የሚካሄደውን ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ በሚያሳልጥና የነዋሪውን የልማት ፍላጎት በሚያሳካ መልኩ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኮሪደር ልማቱ 25 ኪሎ ሜትር እንደሚያካትት ገልጸው፣ ልማቱን ውጤታማ ለማድረግም ህዝብን በማወያየት በማሳተፍና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ልምድ መወሰዱን ገልጸዋል።

እንደ ከንቲባው ገለጻ የኮሪደር ልማት ሥራው በከተማው በአራት ሳይቶች ተለይቶ እየተከናወነ ይገኛል።

እነዚህም በተለምዶ አደባባይ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ አንስቶ እስከ ኮሌጅ፣ ከአፓርታማ እስከ ጉብሬ አደባባይ፣ ከጉብሬ አደባባይ ታች ገበያ ወይም መስጊድ እና ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እስከ ጉብሬ አደባባይ ድረስ ያካተተ ነው።

የኮሪደር ልማት ሥራው የአረንጓዴና የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የእግረኛ መንገዶች፣ የሳይክል መጋለቢያ እንዲሁም መናፈሻዎችን ባካተተ መልኩ ነው እየተከናወነ መሆኑን ከንቲባው ጠቁመዋል።

በልማቱ ከተማዋን ከማስዋብና ተወዳዳሪነቷን ከማሳደግ ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ጠቅሰው፣ የህብረተሰቡም የሥራ ባህል እየተቀየረ መምጣቱን ነው የተናገሩት።

በግንባታ ሂደት ላይ ለሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ከአስተዳደሩ እና ከማህበረሰቡ ተሳትፎ መመደቡንም አክለዋል።

በኮሪደር ልማት ሥራው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የጉልበት ሥራ በማገዝ ልማቱ እንዲፋጠን የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ወጣት ቶፊቅ ኢንድሪያስ ተናግሯል።

በተለያዩ ከተሞች የተተገበረው የኮሪደር ልማት ሥራ ያስገኘውን ጥቅም በማየቱ ለድጋፍ መናሳቱን ጠቁሞ፣ የከተማው ወጣቶችም ልማትን ከመጠየቅ ባለፈ ለልማቱ ውጤታማነት የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለባቸው መክሯል።

ለከተማዋ ልማት የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን የተናገሩት ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ አብዱልሰመድ አስፋው፣ በአሁኑ ወቅት የተጀመሩ የኮርደር ልማት ሥራዎች ከተማዋ ለረጅም ዓመታት ሳታድግ የቆየችበትን ሁኔታ የሚቀይር መሆኑን አስረድተዋል።

በተለይም ከከተማዋ መንገድ መጥበብ ጋር ተያይዞ በዋና መንገድ የሚስተዋለውን የትራፊክ እንቅስቀሴ መጨናነቅ በኮሪደር ልማቱ መፍትሄ ይሰጣል የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል።

#ኢዜአ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የሱዳን ነፃነት ንቅናቄ የአርኤስኤፍ ምክትል አዛዥ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት መጠየቅ አለበት አለ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/15985/

#Ethiopia | በሚኒ ሚናዊ የሚመራው የሱዳን ነፃ አውጪ ንቅናቄ (ኤስ.ኤም.ኤም) ቅዳሜ እለት በሰሜን ዳርፉር በዛምዛም የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ የጅምላ ጭፍጨፋ ፈጽሟል በሚል የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (RSF) ምክትል አዛዥ አብደል ራሂም ዳግሎ በአለምአቀፍ ህግ እንዲጠየቅ አሳስቧል።

ከኤል ፋሸር በስተደቡብ ምዕራብ 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የዛምዛም ካምፕ ከሚያዝያ 14 ቀን ጀምሮ ለሶስት ቀናት በዘለቀው ግጭት ሴቶች፣ ህፃናት እና የእርዳታ ሰራተኞችን ጨምሮ 400 ተፈናቃዮችን በመግደል ስፍራውን አርኤስኤፍ ተቆጣጥሮታል።

በኤስኤልኤም ቃል አቀባይ ሳዲቅ አሊ አልኑር የወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሆነም ዳግሎ “በዛምዛም ካምፕ ውስጥ እልቂት መከሰቱ ምክትል አዛዡ ሂደቱን መምራቱን እና ጭፍጨፋውን ማስፈጸሙን ያረጋግጣል ብሏል። በመሆኑም በአሰቃቂው ወንጀል ከተሳተፉት ጋር በመሆን ለአለም አቀፍ ፍርድ ቤች መቅረብ አለበት” ብለዋል።

አል ኑር የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት በኤል ፋሸር ከተማ፣ በአቡ ሹክ እና ዛምዛም ካምፖች ላይ የተፈጸመውን የRSF ጥቃት በማውገዝ የሰጡትን መግለጫ በደስታ ተቀብለውታል፣ይህም “በአርኤስኤፍ እና በደጋፊዎቹ ላይ አዲስ ጉዳት ነው” ብሏል። አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) በዛምዛም ካምፕ ላይ በተፈፀመው ጥቃቶች እስከ 80ሺ የሚደርሱ ቤተሰቦች ማለትም ከ400 ሺ በላይ ሰዎች እንዲሰደዱ አስገድዷቸዋል ብሏል።

በግምት 30 ሺ ቤተሰቦች ወደ ኤል ፋሸር ፣ 36,000 ወደ ታዊላ የሄዱ ሲሆን የተቀሩት ወደ ሰሜን እና መካከለኛው ዳርፉር አካባቢዎች ተበታትነዋል ሲልም አይኦኤም ተናግሯል።

ድንበር የለሽ የዶክተሮች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) 25,000 ከዛምዛም የተፈናቀሉ ዜጎችን በታዊላ ማግኘታቸውን አስታውቋል። ከነሱ መካከል 170 ሰዎች የተኩስ ወይም የፍንዳታ ቁስለኛ ሲሆኑ 40 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ብሏል።

ኤምኤስኤፍ ተጨማሪ 1,600 ድንገተኛ እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንዳገኘ የገለፀ ሲሆን በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉም ብሏል። አል ኑር አክለውም የፀጥታው ምክር ቤት የኤል ፋሸር ከበባ እና ጦርነቱ እንዲቆም፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ተጠያቂነት እና የሲቪል ጥበቃ እርምጃዎችን በመጠየቅ የአር ኤስ ኤፍ ተጠያቂነት እንዲሰፍን አሳስቧል።
#bisratRadio
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ለሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ቀድሞ የነበረው ከቀረጥ ነጻ አገልግሎት አለመኖሩ ተገለጸ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/15987/

#Ethiopia | የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ለሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ከውጭ ሀገራት የሚያመጧቸውን ግብዓቶች ከቀረጥ ነጻ አገልግሎት የሚያስገባ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ላይ ግን ይህ አገልግሎት መቋረጡን አስታውቋል።

የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አህመድ ሁሴን “ቀድሞ የነበረ አሰራር ቢሆንም በመሃል ግን ከቀረጥ ነጻ አገልግሎት ተቋርጧል” ያሉ ሲሆን፤ ምክንያቱ ግን አለመታወቁን ተናግረዋል።

“ከመንግሥት በኩል ያለው አቋም ከዚህ በኃላ አያስፈልግም በሚል ይሁን ወይ ሌላ አማራጭ በመኖሩ ግልጽ አይደለም” ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ “የሲቪል ማህበራቱ ተደጋጋሚ ጥያቄ በመሆኑ ይሕን ለመጠየቅ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መፈረሙ አጋዥ ነው” ብለዋል።

“ይህ ግልጽ ባልሆነበት ሁኔታ ሁሉም ሰው የየራሱን ምክንያት እንዲያስቀምጥ ያደርጋል” ያሉም ሲሆን፤ ‘ምህዳሩን ለማጥበብ ነው’ የሚሉ አመለካከቶችን እንደሚፈጥር አንስተዋል።

ይህ ደግሞ በትብብር የሚሰሩ ሥራዎችን በማስቀረት ጥርጣሬ እንዲሰፋ ያደርጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ያለውን ትብብር ለማጎልበት ያለመ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል።

የዚህ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ዓላማ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና በኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት መካከል የተቀናጀ እና ስትራቴጂካዊ የትብብር ማዕቀፍ በመመስረት፤ ሕዝባዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መደበኛ ተሳትፎ፣ ትብብር እና የጋራ ጅምር ሥራዎችን ለማመቻቸት መሆኑ ተገልጿል።
#ahaduRadio
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የአልቃይዳ አጋር ቡድን በቤኒን 70 ወታደሮችን ገድያለሁ ሲል አስታወቀ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/15989/

#Ethiopia | የአልቃይዳ ተባባሪ ጃማህ ኑስራት የተሰኘው ታጣቂ ቡድን በሰሜን ቤኒን በሚገኙ ሁለት ወታደራዊ ማዕከሎች ላይ ባደረገው ወረራ 70 ወታደሮችን መግደሉን ተናግሯል፣ይህም ከፍተኛ እልቂት በሀገሪቱ ውስጥ በታጣቂዎች የተፈፀመ መሆኑን ከስፍራው የሚወጡ ዘገባዎች አመላክተዋል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከአይ ኤስ እና ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች ከሳህል ክልል አልፎ ወደ ሰሜን ግዛቶች በማስፋፋታቸው የምዕራብ አፍሪካ ግዛት እና የባህር ዳርቻዋ ቶጎ ተከታታይ ጥቃቶች ደርሶባቸዋል።

የቤኒን ጦር ቃል አቀባይ ኢቤኔዘር ሆንፎጋ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።የጃማአ ኑስራት ታጣቂ ቡድን የሰጠውን መግለጫ እንደሚያሳየው ከሆነ ግን በቤኒን ሰሜናዊ ምስራቅ ካንዲ ግዛት ከዋና ከተማዋ ኮቶኑ 500 ኪሜ ርቃ በምትገኘው አሊቦሪ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ወታደራዊ ማዕከሎች ላይ በፈፀመው ጥቃት 70 ወታደሮች ተገድለዋል።

የሳህል የታጣቂ ቡድኖች እንቅስቃሴ ስር ከመስደዱ በፊት በ2012 በሰሜን ማሊ የቱዋሬግ አመጽ የተጀመረ ነበር። በመቀጠል ወደ ጎረቤት ቡርኪናፋሶ እና ኒጀር ተዛምቶ በቅርቡ እንደ ቤኒን ባሉ የባህር ዳርቻ ምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ሰሜናዊ ክፍል ደርሷል።

በ 2020 እስከ 2023 ባሉት ዓመታት በማሊ ፣ቡርኪናፋሶ እና ኒጀር አምስት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እንዲቀሰቀስ ምክንያት የሆነው ይህው ግጭቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲገደሉ ምክንያት ሲሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል ።

#ዳጉ_ጆርናል
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ጥሬ ስጋና የዳውሮ ማህበረሰብ ያልተነገሩ ታሪኮች..!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/15991/

በዕድገቱ በዛብህ ከዳውሮ

#Ethiopia | ጥሬ ስጋ በዳውሮ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የምግብ አይነት ነው። ወንዶች ስጋን በቅርጫ አርደው ሆነ አድነው ወደ ቤት ስያመጡ ሴቷ (ምስት) እንያንዳንዱን የስጋ ዓይነትና ክፍል ቆጥራ ትረከባለች፤ አይነት በአይነቱ ትለያለች።

በዚህ መሀል የጎደለ የስጋ አይነት ካለ ወንዱ ይወቀሳል መወቀስ ብቻ ሳይሆን የወንድነት ልኩም ጭምር ጥያቄ ውስጥ ይገባል። ስለዚህ የጥሬ ስጋ በዳውሮ ማህበረሰብ ዘንድ የትዳር መለኪያም ተደርጎ ይወሰዳል።

በዳውሮ ማህበረሰብ ጥሬ ስጋን ከተከበረ እንግዳ ጋር አብሮ መብላት የተለመደ ባህል ሲሆን ወንዶች በአደን ጊዜ ስጋን ይዘው ለመምጣት፣ ጀግና ለመባል እንዲሁም ከለሎች አዳኞች በልጠው ለመገኘት ገና ወደ አደን ቦታ ከመሄዳቸው በምስቶቻቸው እና በፈጣሪያቸው ተመርቀው መሄድ ግድ ይላል!!

በአደን ጊዜ ድል ስቀናቸው ስለራሳቸው ፣ ስለ ሚስቶቻቸው እና ስለ አምላካቸው ሽለላ ፋከራና ቀረርቶ ማቅረቡ የተለመደ ነው በዚህም መሀል ለገዳዩ የተለዬ ክብርና ሙገሳ ከጓደኞቹ እንዲሁም የጀግንነት ምልክት ይሆነው ዘንድ በዳውሮኛ “ጋሳ” የጀግንነት ምልክት ይሰጠዋል።

በዚህ ሁሉ መሀል የሴቶች (ምስቶች) ሚና የጎላ ነው። የመጣውን ስጋ አይነት በአይነት በመለየት የተለያዩ የምግብ አይነቶች ያዘጋጃሉ። “ሱልሶ” የሚባለው የባህል ምግብ ቀይ ስጋ ተመርጦ በቅቤና በቅመም ቀመም ተለውሶ በተለበለበ ቅጠል ምስት ባሏን እያጎረሰች ታበላዋለች።

በዳውሮ ማህበረሰብ ጥሬ ስጋ በተለየ ሁኔታ ጥሬ ስጋ የወንድ ልጅ ፈተናው ነው ብንል ማጋነን አይሆንም፣ ጥሬ ስጋ ስነሳ አንድ አብሮ የሚነሳ ነገር “ማንጤ” ይባላል። ማንጤ ማለት በእንስሳት ትንሹ አንጀት ተፈጭቶ ለእስሳት ሰውነት ያለቀለት እና ሰውንት መቀበል ወደ ሚችልበት ደረጃ የደረሰ የምግብ አይተን ማለት ነው። አይነቱም ‘ስታርች’፣ ‘ጉሉኮስ’፣ ‘ፋይቨር’ እና ለሰውነት ጠቃሚ የሆነ የተለያዩ ቪታሚን የያዘ ነው።

እናም ማንጤ ከጥሬ ስጋ ጋር አብሮ እንደ ማበያ በዶቆ ጋር ተቀላቅሎ እንዲሁም ብቻውን ከጥሬ ስጋ ጋር በቅቤ ተለውሶ የሚቀርበው ተወዳጅ የጥንት ዳውሮዎች ግኚት ነው።

ማንጤ የተለያዩ የጤና ጥቅሞች ያሉት ሲሆን በዋናነት ለመተንፈሻ ህመሞች (ጉንፋን፣ የጎሮሮ ህመም) እንዲሁም ለአጠቃላይ የሰውነት ህመም እንደ ፍቱን መፍተሔ ተደርጎ ይወሰዳል።

ዛሬ ዛሬ በዳውሮ አከባቢ በየሆቴሉ እየተለመደ የመጣው ማንጤ ዘርፍ ብዙ የጤና በረከት አለው።

ወደ ዳውሮ ዞን፣ ታርጫ ከተማ እግር ጥሏችሁ የመጣችሁ እንዲሆነ ማንጤን ይሞክሩ🙏
መልካም በዓል!!

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
“የድሆች ጳጳስ” | Pope of the Slums

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/15993/

#Ethiopia | ለምስኪኖችና ስደተኞች ባላቸው ጥብቅና ” Pope of the Slums … “የድሆች ጳጳስ” የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቷቸዋል

ዛሬ ህልፈታቸው የተሰማው የካቶሊኩ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በወር 32 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ደሞዝ የነበራቸው ቢሆንም አንድም ቀን ተቀብለው አያውቁም ።

ፖፑ ይህንን ደሞዛቸውን ጠቅላላ ለበጎ አድራጎት ያውሉት ነበር ።
ሌላው ፖፕ ፍራንሲስ የሚታወቁት እጅግ በበዛ ትሁትና ሰብአዊነታቸው ነው ።

ከአመታት በፊት እስካሁን ድረስ የሰላም አየር በራቃት ጎረቤታችን ሱዳን ተገኝተው ፡ በሀገሪቱ ላይ ሰላም እንዲሰፍን ፡ ሁለቱ የጦር አበጋዞች ሰልቫኬርና ሪክ ማቻር እንዲስማሙ የበኩላቸውን የጣሩ ሲሆን ፡ በሳቸው ጥረት በተደረሰው ስምምነት በተፈረመብት ቀን ፡ ሳይታሰብ ጎንበስ ብለው የሰልቫኬርና ሪክ ማቻር እግር ስር ወድቀው ስምምነቱ እንዲፀና ተማፅነው ነበር ።

በአንድ ወቅት ደግሞ በፀሎተ ሀሙስ ቀን ፡ ከጣልያን ወጣ ብሎ በሚገኝ አንድ የስደተኞች ጣቢያ በመታዊውን የእግር ማጠብ ስነስርአት የስደተኞችን እግር በማጠብ ቀኑን ያሰቡ ሲሆን ከነዚህ እግራቸውን ካጠቧቸው ፡ የኢትዮጵያ ኤርትራና የሌሎች ሀገራት ሰወች መሀከል ሰወች ሶስቱ ከሌሎች ሀገራት የመጡ ሙስሊም ስደተኞች ነበሩ ።

ፖፕ ፍራንሲስ ሁላችንም የአምላክ ፍጡራን ናቸው በማለት ከዘርና ሀይማኖት ባሻገር ስለ ሰው ልጅ አንድነት ይሰብኩ ነበር ።

እኚህ ጳጳስ በመካከለኛው ምስራቅ ፡ በተለይ በእስራኤልና ፍልስጤም እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነትን በተመለከተ ፡ በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን የተኩስ አቁም እንዲታወጅ ከማሳሰብ ጀምሮ ፡ የሰብአዊ እርዳታ የሚቀርብበትን መንገድ እንዲፈለግ ሲወተውቱ የኖሩ ሰው ናቸው ።

ለዚህም ነው የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥ የሆኑት ባሲም ናኢም ዛሬ የፍልስጤማውያን የልብ ወዳጅ እና የመብት ተከራካሪ የነበሩትን ታላቅ ሰው አጥተናል በማለት በፖፕ ፍራንሲስ ህልፈት የገለፁ ሲሆን የአረብ ሊግ ዋና ፀሀፊ አህመድ አቡል ጌይት በበኩላቸው ፡

ፖፕ ፍራንሲስ እስከ ህይወቱ የመጨረሻ ቀናት ስለፍልስጤም ጉዳይ ግድ የሚለው ሰው ነበር ካሉ በኋላ ጳጳሱ ፡ እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ የምትወስደውን የጭካኔ እርምጃ ረገድ ያላቸው አቋም ግልፅ የነበረ ሲሆን ፡ በጋዛ ብሎም በመላው ፍልስጤም ላይ የሚደረገውን ግፍ በየቀኑ በአትኩሮት ይከታተሉ ነበር ብለዋል ።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፍልስጤምን እንደሀገር እውቅና ሰጥታ ፡ ባንዲራዋ በቫቲካን እንዲውለበለብ ያደረጉትም እኚህ ጳጳስ ናቸው።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በተመሳሳይ ጾታ ላይ ያላትን አመለካከት ጳጳሱ በማያሻማና ግልፅ በሆነ መልኩ በሚገባ እየደገፉ አይደለም በሚል ወቀሳ ሲቀርብባቸው የነበረ ከመሆኑም በላይ ፡ በአንድ ወቅት ይህን አላማ በሚደግፉ ተቋማት የተቃውሞ ሰልፍ ተወጥቶባቸው ነበር ።

እጅግ በበዛ ትህትናቸው እና ሰብአዊነታቸው የሚታወቁት ፖፕ ፍራንሲስ አንዳንዴ የራሳቸውን ሻንጣ ለረዳቶቻቸው ከማስያዝ ይልቅ ፡ ራሳቸው ተሸክመው እስከመሄድ ድረስ የበዛ ትህትና ያሳዩ ነበር ።

Apostolic Palace በቫቲካን ከተማ የሚገኝ
የካቶሊክ ጳጳሳት ሲሾሙ የሚኖሩበትን እጅግ ውብና ግዙፍ የጳጳሳት መኖሪያ ቤተመንግስት ነው ።

ፖፕ ፍራንሲስ ግን በዚህ ግዙፍ ቤተመንግስት ከመኖር ይልቅ በአንድ ዘመናዊ ገስት ሀውስ ለመኖር መርጠው እድሜ ዘመናቸውን በዚያ ነበሩ ።
Wasihune Tesfaye

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ቶተንሀም ከ ኖቲንግሀም ይጋጠማሉ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/15995/

#Ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 33ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሀ ግብር ቶተንሀም ከ ኖቲንግሀም ፎረስት ማታ 4 ሰዓት በቶተንሀም ሆትስፐር ስታዲየም ይጋጠማሉ።

በምሽቱ ጨዋታ በደረጃ ሰንጠረዡ 6ኛ ደረጃን የያዘው ኖቲንግሀም ወደ 3ኛ ደረጃ ከፍ ለማለት ማሸነፍ የሚጠበቅበት ይህን ጨዋታ ብቻ ነው።

ታዲያ ለቡድኑ ሰፊ የደረጃ ልዩነት ሊያቀዳጀው የሚችለው የምሽቱ ጨዋታ ኖቲንግሃም ፎረስትን ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር አንድ እርምጃ የሚያቀርበውም ጭምር ነው።

በተጨማሪም ባለፈው የውድድር ዘመን ከመውረድ የተረፈውን ቡድን ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ ተፎካካሪነት የቀየረው የኖቲንግሀሙ አሰልጣኝ ኑኖ ኢስፔሪቶ ሳንቶ ህልሙን እውን ለማድረግ 6 ጨዋታዎች ብቻ ይቀሩታል።

በመሆኑም የምሽቱ ጨዋታ ለኖቲንግሀም የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ቡድኑ ወደ 3ኛ ደረጃ ከፍ ለማለት የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

#etv
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ማንችስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ዣቪ ሲሞንስን በክረምት ለማስፈርም ፉክክር ውስጥ ገቡ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/15997/

#Ethiopia | በአርቢ ላይብዚሽ ለሁለት አመታት ድንቅ አቋም ያሳየውን የመስመር አጥቂ ለመስፈረም በርካታ ክለቦች ፍላጎት ቢኖራቸውም ዩናይትድ እና ሊቨርፑል በተሻለ መንገድ ላይ ስለመሆናቸው የጀርመኑ ስካይ ስፖርት ዘግቧል።

በክረምት የልዊዝ ዲያዝ እና ዲዮጎ ጆታን ቆይታ ያላረጋገጠው ሊቨርፑል፣ሲሞንስ ሁነኛ ተተኪ እንደሚሆን ተማምኗል።

ማንችስተር ዩናይትድም በአሌሃንድሮ ጋርናቾ ወቅታዊ አቋም ምክንያት በክረምቱ ወደ ገበያ መውጣቱ አይቀሬ ነው ተብሏል።

ፕሪምየር ሊጉን ለማሸነፍ ጥቂት ነጥብ የቀረው ሊቨርፑል የ21 አመቱን ፈረንሳዊ ለማስፈረም የተሻለ እድል እንደሚኖረው ተገምቷል።

በደረጃ ሰንጠረዥ ከአውሮፓ ስፍራ ርቆ 14ተኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው ዩናይትድ፣ ይሮፓ ሊግን አሸንፎ የቻምፒዮንስ ሊግ ታሳትፎን ማረጋገጥ ካልቻለ ተጫዋቹን ለመግኘት ይቸግረዋል።

አርቢ ላይብዚሽ እስከ 2027 ቀሪ ኮንትራት ያለውን ተጫዋች ለመውሰድ የሚፈልግ ክለብ 70 ሚሊዮን ዩሮ የውል ማፍረሻ መክፈል እንደሚኖርበት ገልጿል።
#nbc
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በኮንትሮባንድ ንግድ የተሳተፋ ከ50 በላይ የቡና ላኪዎች እገዳ ተጣለባቸው

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/15999/

#Ethiopia | የቡና ምርት ለኮንትሮባንድና ለተለያዩ ህገወጥ ድርጊቶች እየተጋለጠ በመሆኑ የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት እየጎዳው ይገኛል ሲል የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ቡናን ለአልባሌ ነገር እንዳይውል ለማድረግ በሶፍት ዌር አማካኝነት እያንዳንዱ ምርት ከመነሻ እስከ መድረሻ መድረሱን ለማረጋገጥ የሚያስችል የቁጥጥር ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

ይህም በተለይም ቡናን በአግባቡ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀው ምርቱን ለኮንትሮባንድ ንግድ የሚያውሉ አካላት ላይ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

በዚህም መሰረት ቡናን ወደ ትክክለኛው መዳረሻ እንዲደርስ ባላደረጉት አካላት ላይ ከአስተዳደራዊ እርምጃ አንስቶ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል።

በህገወጥ መልኩ ቡናን እየደበቁ ያሉትን በተመለከተ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከብሄራዊ መረጃ ደህንነት እና ከህግ አካላት ጋር በመሆን የቁጥጥር ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ያነሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዚህም ምርቱን በቁጥጥር ስር ማዋልና መያዝ እንደተቻለ አብራርተዋል።

ከጉዳዮ ጋር በተያያዘ 14 የቡና ላኪዎች ለህግ እንዲቀርቡ መደረጋቸውን ጠቅሰው ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ታግደው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል በማለት አቶ ሻፊ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ቡናን በህገወጥ ተግባር ለማሸሽ መሞከር የሀገርንና የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት በእጅጉ የሚጎዳ እንደመሆኑ ለጉዳዮ መፍትሄ ለማምጣት አሁን ላይ እየተከናወኑ ያሉ የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

#ዳጉ_ጆርናል

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ጳጳስ ፍራንሲስ በሮም በሚገኘው በቅድስት ማርያም ማጆር ባዚሊካ መቀበር እንደሚፈልጉ ተናዘዋል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16001/

#Ethiopia | የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ሲሞቱ አቀባበራቸው እንዴት ይከናወናል? ተተኪው ጳጳስ እንዴት ይመረጣሉ?

👉በመጀመሪያ አይሪሽ-አሜሪካዊው ካርዲናል ኬቨን ፋረል የጳጳሱን ሞት በይፋ ያረጋግጣሉ።

👉እኚህ ካርዲናል የብር መዶሻ በመያዝ ሦስት ጊዜ የሞቱትን ጳጳስ ጭንቅላታቸውን ስማቸውን እየጠሩ በቀስታ ይመታሉ።

👉ከዚያም አይሪሻዊው የጳጳሱን የግል ክፍሎች ያሽጋሉ። የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ያዘጋጃሉ።

👉አይሪሻዊው ጳጳስ እና እና በዕጣ የተመረጡ ሦስት የካርዲናል መራጮችን ያካተተ ቡድን አስከሬኑ ለሕዝብ ለማሳየት ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የሚዘዋወርበትን ጊዜ ይወስናል።

👉የጳጳሱ የአሣ አጥማጅ ቀለበት እና ህጋዊው የእርሳስ ማኅተም አላግባብ መጠቀምን ለመከላከል በሥርዓት ይወገዳል።

አስከሬን ምርመራ አይደረግም

የዘጠኝ ቀናት የሐዘን ጊዜ ይታወጃል፣ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ጳጳሱ ከሞቱ ከ4 እስከ 6 ቀናት በኋላ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ይካሄዳል።

አብዛኞቹ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ሥር በሚገኘው መቃብር ውስጥ ቢቀበሩም፣ ጳጳስ ፍራንሲስ ቀደም ሲል በሮም በሚገኘው በቅድስት ማርያም ማጆር ባዚሊካ መቀበር እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር።

ተተኪ

ተተኪውን ለመምረጥ ከጳጳሱ ሞት በኋላ ከ15 እስከ 20 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ በሲስቲን ቻፕል ጉባኤ ይሰበሰባል።

ከ80 ዓመት በታች የሆኑ ካርዲናሎች በድብቅ ድምጽ ይሰጣሉ፣ ይህም አዲስ ጳጳስ ለመምረጥ ከሁለት ሦስተኛ በላይ ድምጽ ያስፈልገዋል።

ልዩ ኬሚካሎች በመጨመር የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን በማቃጠል ከሲስቲን ቻፕል ጭስ ማውጫ ነጭ ጭስ ሲወጣ የተሳካ ድምጽ መገኘቱ ዓለምን ያሳውቃል።

ጥቁር ጭስ እስካሁን ምንም ውሳኔ ላይ እንዳልተደረሰ ያመለክታል።

አዲሱ የተመረጠው ጳጳስ በአደባባዩ ላይ ለተሰበሰበው ሕዝብ የመጀመሪያውን በረከት ለመስጠት ይሄዳል።

#FidelPost
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ከወርቅ የወጪ ንግድ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16003/

#Ethiopia | ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወርቅ የወጪ ንግድ ከሁለት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኝቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ለጋዜጣ ፕላስ እንደተናገሩት፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው ለአምራቾችና ለአቅራቢዎች ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ ከወርቅ የወጪ ንግድ ሁለት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል፡፡

በ2016 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት 286 ሚሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን፤ በ2017 ዓ.ም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከፍተኛ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።

በ2017 ዓ.ም ዘጠኝ ወራት አዳዲስና በተለያዩ ምክንያቶች የወርቅ ምርት ማምረት አቁመው የነበሩ አነስተኛ የወርቅ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ስራ ጀምረዋል ሲሉ ገለጸዋል፡፡

ኢትኖ ማይኒግ፣ ዋይኤምጂ ጎልድ፣ የኢዛናና ቱሉካፒ አነስተኛ የወርቅ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ወርቅ ማምረት መጀመራቸውን አብራርተዋል።

#GazettePlus
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ጅቡቲ የመኖሪያ ፈቃድ ለሌላቸው ኢትዮጵያዊያን ከሀገር መውጫ ጊዜ ገደቡን እንደማታራዝም ገለጸች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16005/

#Ethiopia | በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢንባሲ የጅቡቲ መንግስት በሀገሪቱ የሚኖሩና ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማስታወቁን ተከትሎ ማሻሻያ እንዲደረግ ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀላፊዎች ጋር የተደረገው ውይይት አለመሳካቱን አስታወቀ።

የጅቡቲ መንግስት ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ ሳይኖራቸው በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ከመጋቢት 25፣ 2017 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 24፣ 2017 ዓ.ም ባለው በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ፤ ይህንን የማይተገብሩ ደግሞ በፖሊስ ሀይል ወደመጡበት ሀገር እንዲመለሱ የሚደረግ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

በነበረው ውይይት የተለያዩ ጉዳዮችን በማንሳት ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው የመመለሻው ቀን ቢያንስ በሶስት ወር እንዲራዘም ጥያቄ መቅረቡን ኢንባሲው ገልጿል።

የጁቡቲ መንግስት ግን የተያዘው ዕቅድ የሚሻሻልበትና በልዩ ሁኔታ የሚታይ ሀገር እንደሌለ በግልጽ አስቀምጧል።

በኢትዮጵያውያን ባለቤትነት የተያዙ የንግድ ድርጅቶችን በተመለከተም ባለቤቶቹ በጅቡቲ መኖር የሚያስችላቸው ህጋዊነታቸውን እስኪያረጋግጡ ድረስ ንብረታቸውን በአደራ ሰጥተው ሊሄዱ እንደሚችሉ ገልጿል።
#Tikvah
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የአሜሪካ ታሪፍ በኢትዮጵያ የአበባ ላኪዎች ላይ ስጋት ፈጠረ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16007/

#Ethiopia | የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር የጣለው አዲስ ታሪፍ በአፍሪካ አበባ ላኪዎች ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑ ተገለጸ። በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአሜሪካ ገበያ ውስጥ ለመግባት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ የኢትዮጵያ የአበባ ላኪዎች አሁን ላይ ይህ ታሪፍ እንቅፋት እየሆነባቸው ነው።

ሪፖርተር እንደዘገበው በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የሚጣለው 10 በመቶ ታሪፍ ለአዲስ የተቆረጡ አበባ ላኪዎች ከባድ ፈተና ፈጥሯል።

ይህ አዲስ ታሪፍ በአሜሪካ ላይ ከዚህ ቀደም በነበረው ሶስት በመቶ የአበባ ቀረጥ ላይ የሚጨመር ሲሆን ይህም ከፍተኛ ጭማሪ ላኪዎች ባለፉት አራት ዓመታት በአሜሪካ ገበያ ያገኙትን እድገት ሊያዘገየው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንም እንኳን ከኢትዮጵያ ከሚላከው የአበባ ምርት ውስጥ ሁለት ሶስተኛው ወደ ኔዘርላንድስ የሚሄድ ቢሆንም፣ አሜሪካ ባለፈው ዓመት 45 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኘት ተስፋ ሰጪ ገበያ ሆና ቆይታለች።

ይሁን እንጂ አዲሱ ታሪፍ የኢትዮጵያን አበባዎች ዋጋ እንዲጨምር በማድረግ በክልሉ ከሚገኙ ሌሎች እንደ ኢኳዶር እና ኮሎምቢያ ካሉ የአበባ ላኪዎች ጋር ተወዳዳሪነታቸው እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል። እነዚህ ሀገራት በአሜሪካ የአበባ ገበያ ውስጥ የኢትዮጵያ ዋነኛ ተፎካካሪዎች ሲሆኑ የትራንስፖርት ወጪን በተመለከተም የተሻለ ጥቅም አላቸው።

በአጠቃላይ የአሜሪካ ገበያ ለአፍሪካ የአበባ ላኪዎች በተለይም ለኢትዮጵያ እያደገ ቢመጣም የትራምፕ አስተዳደር የጣለው አዲሱ ታሪፍ ይህን እድገት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
መጪውን የ ፋሲካ በዓል አስሞልክቶ ከ 2,000,000 ብር በላይ ቅናሽ ይጠቀሙ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16009/

ይህ የምስራች ለውድ ደንበኞቻችን ስናቀርብ በታላቅ ደስታ ነው::

📌📌 በ ቁጥር 3ሳይት በሳርስ ዓደይ አበባ B+G+7
የሆነው ህንፃችን ላይ ከረጅም አከፋፈል ጋር እንጠብቆታለን!
ያስተውሉ ብልሆች የ እድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ለውስን ቤቶች ብቻ የቀረበ ዕድል ሞሆኑ ይገንዘቡ!

‘አልቲማ ሪል እስቴት’

“ህልምዎን ይኑሩ!”

“Live Your Dreams!”

ለበለጠ መረጃ :-. ☎️0996000000 / 0995222222

➡️Website: http://www.ultimaet.com

➡️Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61568957484689

➡️Whatsapp: https://whatsapp.com/channel/0029VawOxno545uoGPoLfH3X

➡️Telegram: https://t.me/ultimarealestate1

➡️YouTube: https://www.youtube.com/@UltimaRealestate

➡️ TikTok: tiktok.com/@ultimareal.estate

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አፍሪካ በአጋሮች የዕርዳታ ቅነሳና አዲስ ታሪፍ ተግዳሮት ገጠማት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16011/

#Ethiopia | የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ቁልፍ አለም አቀፍ አጋሮች የእርዳታን መጠን በመቀነስና በአፍሪካ ምርቶች ላይ አዲስ ታሪፍ በመጣል አህጉሪቱን እየፈተኑ መሆናቸውን አስታወቀ።

የህብረቱ ሊቀመንበር ሙሀመድ አሊ ዩሱፍ በ24ኛው ልዩ የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ከአሜሪካ የሚገኘው የዕርዳታ ቅነሳ፣ የአጎዋ ድጋፍ መዳከምና የታቀደው የታሪፍ ጭማሪ በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው።

ካፒታል እንደዘገበዉ አህጉሪቱ እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቋቋም የሀገር ውስጥ ሀብቷን በማሳደግና AfCFTAን በማጠናከር ላይ ትኩረት ማድረግ አለባት ሲሉ ሊቀመንበሩ አሳስበዋል።

#KgEthiopia
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ለጠቅላይ ቤተክህነት የገባ ምንም አይነት ደብዳቤ የለም።

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16013/

#Ethiopia | በአንዳንድ ማኅበራዊ ሚዲያዎች”እፎይ” የተባለ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂን ለብፁዕ አቡነ አብርሃም የገባ ደብዳቤ አመራር እንዳይሰጥበትና ቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዳይሰጥበት ተደርጓል። ይህ የሆነው ደግሞ በብፁዕ አቡነ አብርሃም ቀጥተኛ ትዕዛዝ እንደሆነ ተደርጎ በስፋት የሚሰራጭ ዜና መኖሩና ብዙዎችን እያደናገረ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁንና ወደ ቋሚ ሲኖዶስም ሆነ ወደ ብፁዕ አቡነ አብርሃም “እፎይ”የተባለ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂን በተመለከተ በአካል ቀርቦ ምንም አይነት ማመልከቻ ያስገባ አካል አለመኖሩንና በማኅበራዊ ሚዲያ በዚህ ዙሪያ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን መሰረት በማድረግ የሚተላለፈው ዘገባ ፍፁም ሐሰተኛና መሰረተ ቢስ መሆኑን እየጠቆምን እውነትነት የሌለው መረጃን በማሰራጨት የብፁዓን አባቶችን ስም ለማጥፋትና መልካም ስማቸውን ለማጠልሸት የሚደረገው ሙከራ ሁሉ ተቀባይነት የሌለውና
ሐሰት ለሆነ ምዕመናንና ምዕመናት ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ሊያደናግሩ ከሚፈልጉ አካላት ራሳችሁን እንድትጠብቁ ለማሳሰብ እንወዳለን።

ሚያዚያ ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
እንዳያመልጥዎ!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16015/

በ2% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት የመሆን ዕድል

አዎ በትክክል ሰምተዋል?

በ2% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት ይሁኑ!

ጊፍት ሪል ስቴት ከደንበኞች በቀረበልን ጥያቄ ከሚያዚያ 23-26/2017 ዓ.ም. የሚቆይ ታላቅ የሽያጭ መርሃ ግብር ዳግም አዘጋጅተናል።

በዚህ መርሃ ግብር ላይ በለገሃር፣ በተክለ ሀይማኖት፣ በ22 ማዞሪያ፣ በሲኤምሲ እና ሌሎች አፓርትመንቶችና የንግድ ሱቆች ቅናሽ ተደርጎባቸው ለሽያጭ ይቀርባሉ፡፡

እርስዎም በዚህ የሽያጭ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ፤ የቤት ባለቤት እንዲሆን በክብር ተጋብዘዋል።

መኖር በጊፍት መንደር።

ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን።

ለበለጠ መረጃ:-
Website: https://www.giftrealestate.com.et
+251984 65 65 65/+251979 65 65 65 / 8055

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አሜሪካ ሰንደቅ ዓላማዋ ዝቅ ብለው እንዲውብለበለቡ አደረገች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16017/

#Ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፖፕ ፍራንሲስ ሞት ተከትሎ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ እንዲል ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ክብር የፌደራል እና የግዛቶች ሰንደቅ ዓላማዎች ዝቅ ብለው እንዲውለበለቡ መመሪያ ሰጥተዋል።

እስካሁን የተያዘ ዕቅድ ባይኖርም፤ ትራምፕ በቀድሞው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ሥርዓተ ቀብር ላይ ለመታደም ወደ ሮም ሊያቀኑ እንደሚችሉም ነው ዋይት ሀውስ ያመላከተው።

==
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክ ቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet